en
Feedback
Volunteer Vet Care

Volunteer Vet Care

Open in Telegram

​"Volenter Vet.Care | የእንስሳትዎን ጤና እና ደህንነት ከፍ የሚያደርግ ትምህርት! 🐾 ስለ ጤና፣ እርባታ እና እንክብካቤ አስተማማኝ መረጃ ያግኙ። ​💡 ይከታተሉን እና ለቤት እንስሳትዎ ምርጥ ባለቤት ይሁኑ።"

Show more
763
Subscribers
No data24 hours
+177 days
+3930 days

Data loading in progress...

Similar Channels
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
September '26
September '26
+18
in 0 channels
August '26
+50
in 0 channels
Get PRO
July '26
+94
in 0 channels
Get PRO
June '26
+5
in 0 channels
Get PRO
May '26
+14
in 1 channels
Get PRO
April '26
+39
in 0 channels
Get PRO
March '26
+21
in 0 channels
Get PRO
February '26
+25
in 0 channels
Get PRO
January '26
+54
in 0 channels
Get PRO
December '25
+150
in 1 channels
Get PRO
November '25
+422
in 2 channels
Date
Subscriber Growth
Mentions
Channels
09 September0
08 September0
07 September+4
06 September+2
05 September+3
04 September+1
03 September+1
02 September+6
01 September+1
Channel Posts
🚨 በዌራ ወረዳ በደረሰ የእሳት አደጋ በእንስሳት ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰ፤ ተጠርጣሪው ተያዘ ​ በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ቁፌ ቀበሌ ትላንት ምሽት 9፡00 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ 2 በሬዎ
+4
🚨 በዌራ ወረዳ በደረሰ የእሳት አደጋ በእንስሳት ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰ፤ ተጠርጣሪው ተያዘ ​ በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ቁፌ ቀበሌ ትላንት ምሽት 9፡00 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ 2 በሬዎችና 1 ጊደር ሲሞቱ 2 ላሞችና 1 አህያ ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የወረዳው እንስሳት ጤና ሥራ ሂደት አቶ ኤሊያስ ሀቢብ ገለጹ። የወረዳው እንስሳት ጤና ስራ ሂደት አቶ ኤሊያስ ሀቢብ ከቀበሌው የጤና ባለሙያና ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በስፍራው በመገኘት በሕይወት ለተረፉት አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ሰጥተዋል። ​አደጋው በደረሰበት ወቅት እንስሳቱ በቤት ውስጥ ታስረው በሩ በመዘጋቱ ራሳቸውን ማዳን አልቻሉም። የወረዳው ፖሊስም ከአደጋው ጋር በተያያዘ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ጀምሯል። ጉዳዩ​ ተጣርቶ ጥርጣሬው እውን ከሆነ ፦«የግል ቂም በእንስሳት ላይ መወጣት የሞራል ውድቀት ነው» ​ክስተቱን አስመልክቶ እኛ እንደ Volunteer Vet Care የአቋም መግለጫችን፦ በሰዎች ፀብ ምክንያት እራሳቸውን መከላከል የማይችሉ እንስሳትን ሰለባ ማድረግ አረመኔያዊ ድርጊት መሆኑን እንገልፃለን። ​ድርጊቱ ሆን ተብሎ የተፈፀመ ከሆነ በጥብቅ እናወግዛለን። ​የተያዘው ተጠርጣሪ ጉዳይ ተመርምሮ ሕጉ በፍጥነት ውሳኔ እንዲሰጥና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ እንጠይቃለን። ​

2
‎🐣ጉምቦሮ፦ ጫጩቶችን በማዳከም የዶሮ እርባታን ሊጎዳ የሚችል በሽታ ‎ ‎በዶሮ እርባታ ውስጥ በተለይም በጫጩቶች ላይ ከሚታዩ አደገኛ በቫይረስ አማካኝነት ከሚመጣ በሽታዎች መካከል የጉምቦሮ በሽታ አንዱ ነው። ‎ ‎ይህ በሽታ የዶሮዎችን የበሽታ መከላከል አቅም በማዳከም ለሌሎች በሽታዎች ቀላል ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋል። ስለዚህ ችግሩ ከመባባሱ በፊት መከላከል ወሳኝ ነው። ‎ ‎የጉምቦሮ በሽታ ምልክቶች፦ ‎ ‎ • የጫጩቶች ድካምና ተለይተው መቀመጥ ‎ • የመኖ ፍላጎት መቀነ ‎ • ተቅማጥ ‎ • የክብደት መጨመር መዘግየት ‎ • የሞት መጠን መጨመር ‎ ‎በሽታው እንዴት ይሰራጫል? ‎ ‎ቫይረሱ በተበከሉ ቁሳቁሶች፣ የዕግር ኮቴዎች፣ ልብሶች እና በእርባታው አካባቢ ባለ ብክለት ሊተላለፍ ይችላል። ለዚህም ጥሩ የባዮሴኩሪቲ አሰራር አስፈላጊ ነው። ‎ ‎✅ የመከላከያ መንገዶች፦ ‎ ‎✔ የክትባት መርሃ ግብርን በትክክል መከተል ‎✔ የዶሮ ቤትን ንፁህና ደረቅ ማድረግ ‎✔ የፋርም መግቢያ ቁጥጥርን ማሻሻል ‎✔ የታመሙ ዶሮዎችን መለየት ‎ ✔ ጥርጣሬ ሲኖር የእንስሳት ሐኪምን ማማከር ‎ ‎የዶሮ እርባታ ስኬት የሚጀምረው ከጤናማ ጫጩት ነው። በሽታን ከመታገል ይልቅ ቀድሞ መከላከል የአርቢውን ጊዜ፣ ገንዘብ እና ምርት ይጠብቃል። ‎ ‎#GumboroDisease #PoultryHealth #AnimalHealth #VeterinaryMedicine #OneHealth #VolunteerVetCare
390
3
🐄📊 ባለሙያውን ያላካተተው ጥናት የእንስሳት ሀብታችንን ለማዘመን፣ ምርታማነትን ለማሳደግና ሀገሪቱ ከዘርፉ የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ የተለያዩ ጥናቶች ተካሂደዋል፣ እየተካሄዱም ነው ተብሎ ይነገራል። ግን አንድ ጥያቄ አለኝ፦ እነዚህ ጥናቶች የመስክ ባለሙያውን ምን ያህል ያውቁታል? በቀበሌ ደረጃ የሚሰራው የእንስሳት ጤና ባለሙያ ብዙ ጊዜ ከቢሮ ይልቅ በመስክ ላይ ነው። በጭቃና በአቧራ ውስጥ ይጓዛል፣ በዝናብና በፀሐይ ይሰራል፣ አንዳንዴም ሌሊት ሳይቀር ለታመመ እንስሳ ለመድረስ ይጥራል። የአርቢውን ችግር ከማንም በፊት ያያል። በሽታ ሲከሰት ወደ መንደር የሚደርሰው እሱ ነው። የእንስሳት ጤናን ብቻ ሳይሆን የአርቢውን ኑሮና የሀገሪቱን ምርት በቀጥታ ይነካል። ነገር ግን ይህ ሁሉ መስዋዕትነት በምን ይመለስለታል? የሚገባው የሥራ ሁኔታ፣ ተመጣጣኝ ደመወዝ፣ የመጓጓዣ አቅም፣ የሥራ መሳሪያዎች፣ የሙያ ማሻሻያ ዕድል፣ የአደጋና የመስክ ሥራ አበል እና ሌሎች የሚገቡት ጥቅማጥቅሞች ሳይሟሉ፣ ከእሱ ብቻ ብዙ ውጤት መጠበቅ ይቻላል? ባለሙያውን ማሳተፍ ብቻ አይበቃም፤ ማክበርና ማበረታታትም ያስፈልጋል። የእንስሳት ሀብታችንን ለማዘመን ጥናት እንስራ፤ ነገር ግን ጥናቱን ወደ መስክ የሚያደርሰውን፣ ከአርቢው ጋር በየቀኑ የሚሰራውን ባለሙያም እናስብ። በቀበሌ ደረጃ የሚሰራውን ባለሙያ ካልጠበቅን፣ የእንስሳት ሀብታችንን ለመጠበቅና ለማሳደግ የምናደርገው ጥረት ሙሉ ውጤት አያመጣም። 🐄🇪🇹 ባለሙያውን ማክበር ለባለሙያው ብቻ የሚደረግ ድጋፍ አይደለም፤ ለእንስሳት ሀብታችንና ለሀገራችን ኢኮኖሚ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ነው። 💬 እርስዎ ምን ይላሉ? በቀበሌ ደረጃ የሚሰራው የእንስሳት ጤና ባለሙያ ለሚያደርገው መስዋዕትነት ተገቢውን ክብርና ጥቅማጥቅም እያገኘ ነው ብለው ያስባሉ? 👇 የመስክ ልምድዎንና አስተያየትዎን በኮሜንት ያካፍሉን። — Volunteer Vet Care 🩺 #VolunteerVetCare #AnimalHealth #VeterinaryProfessionals #LivestockDevelopment #Ethiopia #EthiopianVeterinarians #የእንስሳትጤና #የእንስሳትሀብት #የእንስሳትሐኪሞች #የገጠርልማት #የሙያክብር #የባለሙያመብት
939
4
ውሃ መድኃኒት አይደለም እንላለን... ግን ብዙ በሽታዎችን ይከላከላል! 💧🐄 ​ብዙዎቻችን እንስሳትን ስንከባከብ ትኩረታችን ሙሉ በሙሉ የሚሆነው መኖ ላይ ብቻ ነው። ነገር ግን ከንጹህ ውሃ ውጪ የሚደረግ የእንስሳት እርባታ ሁሌም ጎדם አለው። ​ከቆሸሸ (ከተበከለ) ውሃ ጋር ስንገናኝ ምን ይፈጠራል? ❌ ተቅማጥ እና ከባድ የአንጀት በሽታዎች ❌ እንስሳው ምግብ የመብላት ፍላጎቱ ይቀንሳል ❌ የወተትና የስጋ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ ይወርዳል ❌ የሰውነት ክብደት ማጣት ይከሰታል ​ታዲያ ምን ማድረግ ይኖርብናል? ✅ ዕለታዊ የንጹህ ውሃ አቅርቦት ማረጋገጥ ✅ የውሃ ማጠጫ ገንዳዎችን አዘውትሮ ማጽዳት ✅ እንስሳት ቆሻሻ የቆመ ውሃ እንዳይጠጡ መጠበቅ ​የእንስሳት ጤናማ እድገት የሚጀምረው በንጹህ ውሃ፣ በተመጣጠነ መኖ እና በመደበኛ ክትባት ጥምረት ነው። ​👇 አንተ/እርስዎ በቆሎ/በቀን ከብቶችዎን ምን ያህል ጊዜ ንጹህ ውሃ ያጠጣሉ? (በአካባቢዎ) የውሃ አቅርቦት ሁኔታውስ ምን ይመስላል? ሃሳብዎን በአስተያየት መስጫው ያጋሩን! ​#VolunteerVetCare #AnimalHealth #Livestock #CleanWater #OneHealth #Ethiopia
537
5
የምንጠጣው ወተት ጤነኛ ነው? የወተት ከብቶችን ማርባት ትልቅ በረከት ነው። ነገር ግን በማህበረሰባችን ውስጥ ጥሬ ወተት ሳይፈላ የመጠጣት ልምድ ትልቅ አደጋ አለው። ሳናፈላ የምንጠጣው ወተት እንደ ሳንባ ነቀርሳ ቲቢ እና ብሩሴሎሲስ የመሳሰሉ ከእንስሳት ወደ ሰው በቀላሉ የሚሻገሩ አደገኛ በሽታዎችን ያስተላልፋል። #ብሩሴሎሲስ ፦በከብቶች ላይ ውርጃ የሚያስከትለው በሽታታ ሲሆን ሰው ላይ ከፍተኛ ማይለቅ ትኩሳት የመገጣጠሚያ ህመም እና ማህፀን/ብልት ላይ ከባድ ችግር ያመጣል። #ቲቢ፦ በበሽታው የተያዘች ላም ወተት ሳይፈላ ከተጠጣ ሳንባንና ሌሎችንም የሰውነት ክፍሎች ያጠቃል። ምን እናድርግ? ወተትን ከመጠጣታችን በፊት በሚገባ ማፍላት። ላም ውርጃንገ ሲያጋጥማት ፋንየንግዴ ልጁን በባዶ እጅ በፍጹም አለመንካት! የግድ ጓንት ወይም ንጹህ ላስቲክ መጠቀም አለብን። የወተት ከብቶችን ንጽህና መጠበቅ እና በየጊዜው በባለሙያ ማስመርመር። ጤናችን በእጃችን ነው ወተትን አፍልተን እንጠጣ!
550
6
🐄 እንስሳትዎ ከመታመማቸው በፊት የሚሰጧቸው ጥንቃቄ እና እንክብካቤ ከታመሙ በኋላ ከሚያወጡት ወጪ የተሻለ ዋጋ አለው። በእንስሳት ጤና ዘርፍ በሰራሁባቸው ዓመታት አንድ ነገር በግልጽ ተረድቻለሁ እሱም ምንድነው ካላችሁኝ፦ ትርፋማ እርባታ የሚጀምረው በሚያስወጓቸው መድኃኒቶች ሳይሆን፣ በሚሰጧቸው አያያዝና እንክብካቤ ነው። ብዙ አርብቶአደሮች የሚያጋጥማቸው ኪሳራ በሽታው ስለበረታ ሳይሆን የበሽታውን የመጀመሪያ ምልክቶች በጊዜ ስላለዩ ነው። ስለዚህ ሁልጊዜ የምመክረው እነዚህን ሦስት መሠረታዊ ነገሮችን ነው፦ #ንጹህና_በቂ_ውሃ – ጤናማ እንስሳ የሚጀምረው ከንጹህ ውሃ ነው። #ንጽህናው_የተጠበቀ_መኖሪያ – በሽታን ከመድኃኒት ይልቅ ንጽህና በተሻለ ሁኔታ ይከላከላል። #በየቀኑ_ክትትል – የምግብ ፍላጎት፣ የእንቅስቃሴ ለውጥ ወይም የባህሪ ለውጥ ቀደም ብሎ የሚታይ የጤና መልዕክት ነው። እንስሳት መናገር አይችሉም ጤናቸውን የሚገልጹት በባህሪያቸው ነው። ይህን ማንበብ የሚችል አርቢ ሁልጊዜ ከኪሳራ አንድ እርምጃ ቀድሞ ይሄዳል። በእርባታ ውስጥ ትርፍ በአጋጣሚ አይመጣም፤ በየቀኑ በሚደረግ ትክክለኛ አስተዳደር ይገነባል። እርስዎስ በእርባታዎ ውስጥ ትልቁ ፈተና ምንድን ነው? ልምድዎን በኮመንት ያካፍሉን እንማማርበታለን። — Volunteer Vet Care #የእንስሳትጤና #የከብትእርባታ #ዘመናዊእርባታ #አርብቶአደር #አርሶአደር #የወተትከብት #የስጋከብት #የእርሻእናእርባታ #የእንስሳትሕክምና #የእንስሳትእንክብካቤ #የእርባታሥራ #የእርባታአስተዳደር #የእርሻልማት #ኢትዮጵያ
561
7
‎🛑 ስኬታማ የከብት እርባታ የሚጀመረው በምንድ ነው? ‎ ‎​ከብት ማርባት የቤተሰብ ገቢ ምንጭ ብቻ ሳይሆን የሀብት እና የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ዋስትና ነው። ውጤታማ አርብቶ አደር ለመሆን ግን ጥረት ብቻውን በቂ አይደለም! ጥቂት መሠረታዊ ህጎችን መተግበር ያስፈልጋል። ‎ ‎በመጀመሪያ፣ ለአካባቢያችን የአየር ንብረት ተስማሚ እና ምርታማ የሆኑ የከብት ዝርያዎችን መምረጥ ለስኬት መሰረት ነው። በመቀጠልም እንስሳቱ በቂና የተመጣጠነ መኖ እንዲሁም ንጹህ የመጠጥ ውሃ እንዲያገኙ ማድረግ እድገታቸውንና ምርታማነታቸውን ይወስናል። ‎ ‎ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ወቅታዊ ክትባቶችን ማድረግ እና የጤና ባለሙያ ምክርን መተግበር ከብቶቻችንን ከአላስፈላጊ በሽታዎች እና ከሞት ለመከላከል የግድ ይላል። ‎ ‎​የስኬት ሚስጥር በትዕግስት፣ በጥንቃቄ እና በዘመናዊ የእርባታ ዘዴዎች ላይ የተመሰረተ ነው። እንስሳትን በፍቅር እንከባከባቸው፤ እነሱም የቤተሰባችንን ምርታማነት ከፍ ያደርጉልናል! ‎ ‎#የእርባታስራ #ዘመናዊእርባታ #አርሶአደር ‎#የእንስሳት_እርባታ #የከብት_እርባታ #የእንስሳት_ጤና #ግብርና #ኢትዮ_ቬት #የሜዳ_ላይ_ተሞክሮ #የእንስሳት_ሕክምና #ኢትዮጵያ
433
8
https://t.me/volentervetcare
431
9
የእግርና አፍ በሽታ (FMD) አርቢዎቻችን ምን ሊያውቁ ይገባል? ​የዝናቡ መጀመር ለከብቶቻችን እፎይታ ቢሆንም የእግርና አፍ በሽታ (FMD) በብዛት የሚሰራጭበት ወቅት ነው። በምስሉ ላይ እንደምታዩት
የእግርና አፍ በሽታ (FMD) አርቢዎቻችን ምን ሊያውቁ ይገባል? ​የዝናቡ መጀመር ለከብቶቻችን እፎይታ ቢሆንም የእግርና አፍ በሽታ (FMD) በብዛት የሚሰራጭበት ወቅት ነው። በምስሉ ላይ እንደምታዩት፣ በሽታው በከብቶች አፍ ምላስ እና እግር ሰንጣቂ ላይ ቁስል ያወጣል። ​በሽታው የሚታወቅባቸው ዋና ዋና ምልክቶች፦ ​ከባድ ምራቅ መዝረክረክ። ​የመብላት ፍላጎት መቀነስ እና ትኩሳት። ​በእግር ቁስሉ ምክንያት መንከስ ወይም ለመራመድ መቸገር። ​እንደ ባለሙያ ምክራችን፦ ​ለይቶ ያቆዩ፦የታመመ እንስሳ ካለ ወዲያውኑ ከጤነኞቹ ይለዩ። ​ንጽህና፡ የእንስሳት መኖሪያን ደረቅ እና ንጹህ ያድርጉ። ​ያማክሩ፡ ምልክቶች እንደታዩ የባህል ህክምና ከመጀመር ይልቅ፣ በአካባቢዎ የሚገኘውን የእንስሳት ጤና ባለሙያ ያነጋግሩ። ​ጥያቄ አለዎት? በአስተያየት መስጫው ላይ በመጻፍ ያሳውቁን አብረን እንስሳቶቻችንን እንጠብቅ።
468
10
የእንስሳት ጤና የጥያቄና መልስ መድረክ - ከባለሙያ ​ጤና ይስጥልኝ የተከበራችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች እና የእንስሳት አርቢዎች። ​ከረጅም ድርቅ በኋላ የዘነበው ካፊያ ለከብቶቻችን እፎይታ ቢሆንም ድንገተኛ የአየር ንብረት ለውጥ ተከትሎ የሚመጡ የጤና እክሎች እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። በዚህ የቴሌግራም ገጽ ምን ታገኛላችሁ? ​ወቅታዊ የሆኑ የከብቶች በሽታ መከላከያ ምክሮች። ​የአርሶ አደሩን ችግሮች የያዘ የውይይት መድረክ። ​የእንስሳት አመጋገብ እና ዘመናዊ የመራቢያ ዘዴዎች። ​አሁን ምን ማድረግ ይጠበቅብዎታል? በአካባቢያችሁ ያሉ ከብቶች ላይ የታዩ እንግዳ ምልክቶች ወይም የጤና ችግሮች ካሉ፣ አስተያየት መስጫው ላይ በመጻፍ ያሳውቁን። እንደ ባለሙያ መፍትሄውን አብረን እንፈልጋለን። ​አብረን እንስሳቶቻችንን እንጠብቅ!
349
11
ዶሮዎ እንቁላሉን እየሰበረ ነው? ይህን ችግር በአስቸኳይ ይግቱት! እንደ አንድ የሙያ አጋርዎ፣ በየቀኑ በሥራ ቦታዬ ከሚገጥሙኝ ተግዳሮቶች አንዱ የዶሮ እንቁላል መብላት ነው። ብዙ አርሶ አደሮች ይህን
ዶሮዎ እንቁላሉን እየሰበረ ነው? ይህን ችግር በአስቸኳይ ይግቱት! እንደ አንድ የሙያ አጋርዎ፣ በየቀኑ በሥራ ቦታዬ ከሚገጥሙኝ ተግዳሮቶች አንዱ የዶሮ እንቁላል መብላት ነው። ብዙ አርሶ አደሮች ይህንን ችግር ሲያዩ "ዶሮው ተበላሸ" ብለው ተስፋ ይቆርጣሉ። ነገር ግን ልምድ እንደሚነግረን፣ ይህ ችግር በባህሪ የመጣ እንጂ ዶሮው ላይ የተፈጠረ የጤና እክል አይደለም። አንዴ ዶሮ ይህን ልማድ ከያዘ ግን እንደ ቫይረስ ወደ ሌሎቹ ዶሮዎች የመዛመት ባሕርይ አለው። ለምን ይህን ያደርጋሉ? ብዙ ጊዜ የምታዘበው፣ ዶሮዎች እንቁላል የሚበሉት በዋናነት ሁለት ምክንያቶች ነው፦ #​የካልሲየም_እጥረት፡ ሰውነታቸው የሚፈልገውን ማዕድን ባለማግኘታቸው፣ በደመ-ነፍስ ወደ እንቁላሉ ቅርፊት ይዞራሉ። #​ሰልችቷቸው፡ በቂ እንቅስቃሴ የሌላቸው፣ የተጨናነቁ ዶሮዎች ለጉዳይ እንቁላሉን እንደ መጫወቻ መስበር ይጀምራሉ። አንዴ ከተሰበረ ደግሞ ጣዕሙን ስለሚወዱት ልማድ ይሆናል። እንደ ባለሙያ የምሰጠው መፍትሔ፦ ​የካልሲየም ምንጭ ጨምሩ፦ የተፈጨ የእንቁላል ቅርፊት ወይም የኦይስተር ሼል (Oyster shell) በመኖው ላይ መደባለቅ የዘወትር ተግባርዎ ያድርጉ። ​ጎጆውን ቶሎ ይፈትሹ፡ እንቁላሉ ረጅም ሰዓት በጎጆው ውስጥ መቆየቱ ዶሮውን ይፈታተነዋል። በዕለቱ ቶሎ ቶሎ መሰብሰብ በጣም አስፈላጊ ነው። ​የውሸት እንቁላል ይጠቀሙ፦ይህ በዘርፉ የምንጠቀምበት ውጤታማ ዘዴ ነው። የፕላስቲክ ወይም የድንጋይ እንቁላል በጎጆው ውስጥ ያስቀምጡ። ዶሮው መስበር ሲሞክር ስለማይሰበርበት፣ "እንቁላል አይሰበርም" የሚል ትምህርት ይወስዳል። ​ይህ ችግር በእርሻዎ ላይ አጋጥሞ ያውቃል? ምን ዓይነት መፍትሄ ነው የሞከሩት? ልምድዎን ኮሜንት ላይ ያጋሩ፤ እንወያይ! 👇 ​#የዶሮእርባታ #የእንስሳትጤና #የዶሮእንክብካቤ #ዘመናዊእርባታ #ኢትዮጵያ
423
12
የፍየል ማድለብ፡ ከባህላዊ ወደ ዘመናዊ አሰራር የሚደረግ ሽግግር የኢትዮጵያ የእንስሳት ሀብት ልማት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ትልቅ ድርሻ አለው። በተለይም የፍየል ማድለብ ስራ እንደ ዘመናዊ የእርባታ ስልት እየተወሰደ ሲሆን፣ አርሶ አደሮችና ሁሉም አርቢዎች ከባህላዊ አሰራር በመውጣት ሳይንሳዊ መርሆዎችን በመተግበር ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ይገኛል። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደመሆኔ ውጤታማ የፍየል ማድለብ ከምግብ አቅርቦት ባሻገር ጥንቃቄ የተሞላበት የጤና አያያዝን የሚጠይቅ መሆኑን ልጠቁማችሁ እወዳለሁ። ለስኬታማ ማድለብ የሚከተሉት ነጥቦች ወሳኝ ናቸው፦ የእንስሳት ምርጫ፡ ለማድለብ የሚመረጡ ፍየሎች ከ1 እስከ 2 ዓመት ባለው የእድሜ ክልል የሚገኙ፣ ጤናማ እና አካላዊ ቁመናቸው የተሟላ መሆን ይገባቸዋል። ​ሚዛናዊ የመኖ አጠቃቀም፡ ፍየሎች በፍጥነት እንዲያደልቡ በተፈጥሮ ሳር ብቻ መወሰን በቂ አይደለም። የሰብል ተረፈ ምርቶችን ጥራጥሬዎችን እና ብሬን በማቀላቀል ሚዛናዊ የሆነ መኖ ማቅረብ የምርታማነት መሰረት ነው። ​የጤና ክትትልና በሽታ መከላከል፦እንደ እብድ ውሻ፣ የቆዳ እባጭ ወይም ጉርብርብ (Lumpy Skin Disease) እና የፍየልና በግ ተላላፊ ሳንባ በሽታ (CPPP) ያሉ ተላላፊ በሽታዎችን መከላከል ዋነኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው። ከማከም ይልቅ መደበኛ የክትባት መርሃ ግብሮችን መከተል ለኪሳራ የሚዳርግ የጤና ችግርን ያስቀራል። ​የመረጃ አያያዝ፦የዘመናዊ እርባታ ቁልፉ የመረጃ አያያዝ ነው። የእንስሳትን የጤና ታሪክ እና የምርታማነት መረጃዎችን መዝግቦ መያዝ ለወደፊት ትክክለኛ ውሳኔ ለመወሰን ወሳኝ ነው። ​በአሁኑ ወቅት እንደ "Volunteer-Vet Care" ባሉ የዲጂታል መተግበሪያዎች በመታገዝ የጤና መረጃዎችን መመዝገብ መጀመሩ ዘመናዊ የእርባታ ዘዴን ለማስፋፋት ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አርሶ አደሮች እና ባለሙያዎች ልምዳቸውን በመለዋወጥ እና ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመከተል ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንደሚችሉ ባለሙያዎቹ ይመክራሉ። ​ተጨማሪ መረጃ እና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የቴሌግራም ቻናላችንን እና የፌስቡክ ፔጃችንን በመጎብኘት ከባለሙያዎች ጋር መገናኘት ይቻላል። ጠለቅ ያለ መረጃ እና የልምድ ልውውጥ ከፈለጉ፡ ​👉 ለበለጠ መረጃ እና ትምህርታዊ ቪዲዮዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ https://t.me/volentervetcare 👉 በዕለታዊ ጠቃሚ መረጃዎች ዙሪያ ለመወያየት የፌስቡክ ፔጃችንን ይከተሉ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=61590485563532 ​አብረን እንደግ፣ ምርታማነትን እናሳድግ! ​ከ"ዘመናዊ የእርባታ ዘዴ" አስተዳደር #ዘመናዊየእርባታዘዴ #ፍየልማድለብ #የእንስሳትጤና #የኢትዮጵያግብርና #VetCare #Kulito
387
13
‎የዶሮ እርባታ ስኬት እና ዋና ዋና የዶሮ በሽታዎች መከላከያ ‎ ‎ብዙ ጊዜ አርቢዎች ከሚጠይቁኝ ጥያቄዎች አንዱ "ዶሮዎቼ በድንገት እየታመሙ ነው ምን ላድርግ?" የሚለው ነው። የዶሮ እርባታን እንደ ንግድ ወይም እንደ የቤት ውስጥ አማራጭ ገቢ የምንጠቀም ከሆነ በሽታዎችን አስቀድሞ መከላከል ወሳኝ ነው። ‎ ‎አርቢዎች ማወቅ ያለባችሁ 3 ዋና ዋና ነጥቦች፦ ‎ ‎1ኛ #የበሽታ_ምልክቶችን_ማወቅ፦ ዶሮዎች ሲታመሙ የምግብ ፍላጎታቸው ይቀንሳል ‎ላባዎቻቸው ይራገፋል ወይም ለመተንፈስም ይቸገራሉ። እነዚህን ምልክቶች በአንድ ዶሮ ላይ ካዩ ወዲያውኑ ከሌሎች መንጋዎች ለይተው ማስቀመጥ የብዙ ዶሮዎችን ህይወት ያድናል። ‎ ‎2ኛ ​#ክትባት፦ በሽታ መጣ ብሎ ከማከም፣ በክትባት አስቀድሞ መከላከል በብዙ እጥፍ ይሻላል። የእያንዳንዱን ክትባት ጊዜ (Schedule) በአግባቡ መከተል ለስኬታማ እርባታ መሰረት ነው። ‎ ‎3ኛ #ንጽህና_እና_አየር_ዝውውር፦ አብዛኛው የዶሮ በሽታ የሚመነጨው ከእርጥበት እና ከቆሻሻ ነው። የዶሮ ቤትን በየጊዜው ማጽዳት፣ አየር እንዲዘዋወር ማድረግ እና ውሃ መጠጫቸውን ንፁህ ማድረግ የባክቴሪያዎችን መራባት ይቆጣጠራል። ‎ ‎እንደ ባለሙያ የእኔ ምክር የሚሆነው፦ "በሽታ ከመጣ በኋላ መፍትሄ ከመፈለግ ንጽህናን መጠበቅ እና ክትባትን መተግበር ትርፋማነታችሁን ይጨምራል" ነው። ‎ ‎በአካባቢያችሁ በብዛት የሚያጋጥሟችሁ የዶሮ በሽታዎች አሉ? ወይም በዚህ ዙሪያ የምትጠይቁት ጥያቄ ካለ ኮሜንት ላይ አሳውቁኝ። ‎ ‎​#VetCare #የዶሮእርባታ #የእንስሳትጤና #የዶሮበሽታዎች #ግብርና #Ethiopia
348
14
ዛሬ በስራዬ ሂደት ብዙ አርቢዎች "የዶሮ እርባታ ከቀድሞው የበለጠ ከባድ እየሆነ ነው" ሲሉ ሰማሁ። የኑሮ ውድነቱ እና የመኖ ዋጋ መናሩ እውነት ቢሆንም ከልምዴ እንደምታዘበው ግን ስኬታማ ለመሆን ዋና
ዛሬ በስራዬ ሂደት ብዙ አርቢዎች "የዶሮ እርባታ ከቀድሞው የበለጠ ከባድ እየሆነ ነው" ሲሉ ሰማሁ። የኑሮ ውድነቱ እና የመኖ ዋጋ መናሩ እውነት ቢሆንም ከልምዴ እንደምታዘበው ግን ስኬታማ ለመሆን ዋናው ሚስጥር የምናደርገው ጥንቃቄ ነው። በተለይ በእነዚህ ሶስት ነገሮች ላይ ስህተት ከሰራን መክሰራችን አይቀርም፦ 1ኛ፦ መኖ ላይ መደራደር፦ መኖ ውድ ነው ብለን ጥራቱን ዝቅ ማድረግ፣ ምርትን ከመቀነስ በላይ ዶሮዎችን ለበሽታ ይዳርጋል። አቅም በፈቀደ መጠን የተመጣጠነ መኖ መስጠት ግዴታ ነው። 2ኛ፦ አየር ዝውውር፦ ብዙዎች የዶሮ ቤትን በደንብ ይዘጋሉ፤ ይህ ግን ለዶሮዎች የሳንባ ችግር መነሻ ነው። ቤቱ ሁሌም ደረቅና በደንብ አየር የሚያገኝ መሆን አለበት። 3ኛ፦ የመከላከል አቅም፦ በሽታ እስኪመጣ መጠበቅ ትልቅ ስህተት ነው። ክትባት መስጠት ወጪ ሳይሆን ኢንቨስትመንት ነው። ​እኔ በበኩሌ በሀላባ ቁሊቶ አካባቢ ስዞር የምታዘበው በትንሽ ጥንቃቄ ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ነው። እናንተስ በዶሮ እርባታ ላይ ምን ያጋጠማችሁ ፈተና አለ? ምን ብንጨምርበት ይሻላል? እንወያይበት። #የዶሮእርባታ #የአካባቢልምድ #ኩሊቶ #የእርሻኑሮ #VetCare
376
15
የከብት እርባታ፦ የትርፍ ሚስጥሩ በትናንሽ ጥንቃቄዎች ውስጥ! የከብት እርባታችንን ለማሳደግ ሁልጊዜ ውስብስብ ቴክኖሎጂዎችን አንፈልግም። ከረጅም ዓመታት የመስክ ልምዴ እንደታዘብኩት የስኬት ቁልፍ ያለው እኛ እንደ ቀላል በምናያቸው የዕለት ተዕለት ጥንቃቄዎች ውስጥ ነው። ​ትርፋማ እርባታ በሦስት መሠረቶች ላይ ይቆማል፦ #​የውሃ_ጥራት፦ንፁህና በቂ ውሃ ለጤና እና ለምርታማነት የመጀመሪያው ቅድመ ሁኔታ ነው። #​የንፅህና_አጠባበቅ፦እርጥበት የለለበት እና አየር የተዘዋወረበት መኝታ ለበሽታዎች ትልቁ መከላከያ ነው። #የቅርብ_ክትትል፦እንስሳትን መመገብ ብቻ በቂ አይደለም ባህሪያቸውን መታዘብ የችግሮችን መነሻ በፍጥነት ለመለየት ይረዳል። እነዚህ ትንንሽ የሚመስሉ ልምዶች በኪሳራ እና በትርፍ መካከል ትልቅ ልዩነት ይፈጥራሉ። በቮለንተር ቬት ኬር ገፃችን በኩል ዓላማችን ሳይንሳዊ እውቀትን ከአርሶ አደሩ ተሞክሮ ጋር በማዋሃድ ዘመናዊ እርባታን መገንባት ነው። ​ውድ አንባቢያን በእርሶ እርባታ ላይ ያጋጠመዎት ልዩ ተሞክሮ ወይም ጥያቄ አለ? ልምድ መለዋወጥ ለዘርፉ እድገት ትልቅ ብርሃን ነው። ኮሜንት ላይ ያጋሩኝ! ለበለጠ ሙያዊ መረጃ 👉 Volunteer Vet Care ይከታተሉ። ​#የእንስሳትጤና #ዘመናዊእርባታ #የከብትእርባታ #ቮልቬትኬር #ኢትዮጵያ #VolvetCare #Ethiopia #AnimalHealth #FarmersLife #LivestockManagement
379
16
ግብርናን ማዘመን፡ ከባህላዊ አሰራር ወደ ሳይንሳዊ ምርታማነት የግብርና ዘርፍ የኢኮኖሚ እድገታችን ዋነኛ ሞተር ነው። ሆኖም ዘርፉን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ለማሸጋገር "ማዘመን" የሚለው ጽንሰ-ሀሳብ ከቃላ
ግብርናን ማዘመን፡ ከባህላዊ አሰራር ወደ ሳይንሳዊ ምርታማነት የግብርና ዘርፍ የኢኮኖሚ እድገታችን ዋነኛ ሞተር ነው። ሆኖም ዘርፉን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ለማሸጋገር "ማዘመን" የሚለው ጽንሰ-ሀሳብ ከቃላት ባለፈ በተግባር ሊፈታ ይገባል። ግብርናን ማዘመን ስንል በአብዛኛው የሚያተኩረው በሁለት ዋና ዋና ነገሮች ላይ ነው፦ ​1. ግብዓቶች (The "What"): ዘመናዊ ግብርና የሚጀምረው በትክክለኛ ምርጫ ነው። በሽታን የሚቋቋሙ ዝርያዎች፣ ምርታማ የእንስሳት ዝርያዎች፣ እንዲሁም በአፈር ምርመራ እና በሳይንሳዊ ግኝቶች ላይ የተመሰረተ ግብዓት አጠቃቀም (እንደ ክትባቶችና ህክምናዎች) የዘርፉን ምርታማነት በአጭር ጊዜ ለመቀየር ወሳኝ ናቸው። በተጨማሪም፣ ከሰው ጉልበት ወደ ሜካናይዜሽን መሸጋገር ጊዜንና ጉልበትን ለመቆጠብ አይነተኛ መንገድ ነው። ​2. አሰራር (The "How"): ቴክኖሎጂ ብቻውን በቂ አይደለም። አሰራራችንም ከባህላዊ ወደ ሳይንሳዊ ሊሸጋገር ይገባል። ግብርናን እንደ አንድ የንግድ ስራ (Agribusiness) ማየት፣ በውሂብ (Data) ላይ የተመሰረተ ውሳኔ መስጠት፣ እና የዲጂታል መረጃ ልውውጥን ለገበያ ትስስር መጠቀም ዘርፉን ትርፋማ ያደርገዋል። ይህ ሁሉ የሚሳካው ደግሞ የባለሙያዎችን እውቀት ወደ መሬት በማውረድ ቀጣይነት ያለው ክህሎት ሲገነባ ነው። ​ግብርናን ማዘመን ማለት የድካምን መጠን ቀንሶ ጥራትን ጠብቆ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ነው። ​በዘርፉ ላይ ለምትሰሩ ባለሙያዎች፡ እናንተ በሙያችሁ ግብርናን ለማዘመን ምን አይነት ስልቶችን ትጠቀማላችሁ? ​#Agriculture #Innovation #Agribusiness #SustainableDevelopment #Ethiopia #AgriculturalTransformation
392
17
🚨 ከብቶችን ከመመረዝ ይታደጉ! የሕይወት አድን መረጃ እና ወዲያውኑ የሚደረጉ እርምጃዎች 🚨 ከብትዎ፣ በጎችዎ እና ፍየሎችዎ ለአደጋ ተጋልጠዋል! ⚠️ ጤናማ የእንስሳት እርባታ ለሀገራዊ ብልጽግና እና ለቤተሰብ ዋስትና ወሳኝ ነው። ነገር ግን በእርባታዎ ላይ የሚፈጠሩ ጥቂት ጥንቃቄ የጎደላቸው ስህተቶች የእንስሳትዎን ሕይወት በደቂቃዎች ውስጥ አደጋ ላይ ሊጥሉ ይችላሉ። 🔍 ለመሆኑ የመመረዝ ዋና ዋና መንስኤዎች ምንድናቸው? ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የሚሰጥ መድኃኒት 💊: አንዳንድ ጊዜ ከሚፈቀደው መጠን በላይ የሚሰጥ መድኃኒት ወይም በአግባቡ ያልተሰጡ የፀረ-ትል መድኃኒቶች (Dewormers) እንስሳቱን በቀጥታ ይመርዛሉ። የተበከለ ግጦሽ እና ውሃ 💧🌱: በኬሚካል (እንደ አረም ማጥፊያ፣ ፀረ-ተባይ መድኃኒት ወይም በናይትሬት የበለጸገ ፍግ) የተበከለ ሳር መጋጥ ወይም ውሃ ማጠጣት። የተጣለ ቆሻሻ 🗑️🔋: በአካባቢው የተጣሉ የፕላስቲክ ዕቃዎችን፣ የባትሪ ፍርፋሪዎችን ወይም መርዛማ ንጥረ ነገሮችን እንስሳቱ ሲልሱ ወይም ሲበሉ ፈጣን መመረዝ ይከሰታል። ⚠️ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች! (ጊዜ አይስጡ!) ከሚከተሉት ምልክቶች አንዱን ወይም ከዚያ በላይ ካዩ አስቸኳይ እርምጃ ያስፈልጋል፦ ድንገተኛ የባህሪ ለውጥ፦ ድንገተኛ መንቀጥቀጥ፣ መውደቅ፣ መፈራገጥ ወይም ያለአግባብ መጮህ። የምግብ መፈጨት መታወክ፦ ከፍተኛ ተቅማጥ፣ ደም የቀላቀለ ሰገራ ወይም አጠቃላይ የምግብ ፍላጎት ማጣት። የአተነፋፈስ ችግር፦ ለመተንፈስ መቸገር፣ አየር ማጠር ወይም ከአፍንጫ ፈሳሽ መውጣት። የዓይን ለውጥ፦ የዓይን ብሌን በጣም ማጥበብ (Pinpoint Pupils) ወይም በጣም የሰፋ ዓይን። ✅ ወዲያውኑ ምን ማድረግ አለብን? (የመጀመሪያ እርዳታ) 📌 ባለሙያ እስኪደርስ እነዚህን ያድርጉ፦ ከምንጩ ማራቅ፦ እንስሳውን መርዛማ ሊሆን ከሚችልበት ቦታ (ከግጦሹ፣ ከቆሻሻው ወይም ከተበከለው ውሃ) በፍጥነት ያርቁት። መድኃኒት በራስዎ አይሞክሩ፦ ያለባለሙያ ፈቃድ እንስሳውን እንዲያስመልስ/እንዲያስታውክ ለማድረግ አይሞክሩ፤ መርዙ ወደ ሳንባ ገብቶ ጉዳቱን ሊያባብሰው ይችላል። ለእንስሳት ጤና ባለሙያ በፍጥነት ይደውሉ፦ የመመረዝ አደጋ የሰዓታት ሳይሆን የደቂቃዎች ጉዳይ ስለሆነ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ባለሙያ ወዲያውኑ ስልክ ይምቱ። 💡 ምክር ለሁሉም አርቢዎች ሁልጊዜም የእርሻ ኬሚካሎችን፣ ፀረ-ተባዮችን እና መድኃኒቶችን ደህንነቱ በተጠበቀና እንስሳት በማይደርሱበት ቦታ ያስቀምጡ። ጤናማ እርባታ ለጤናማ ኢትዮጵያ! 🔄 መልዕክቱ ለሁሉም አርቢዎች እንዲዳረስ ሼር (Share) በማድረግ ግዴታዎን ይወጡ! 🙏 💬 ለመወያያ፦ በእንስሳትዎ ላይ የመመረዝ አደጋ ደርሶባቸው ያውቃል? ምን እርምጃስ ወሰዱ? ተሞክሮዎን በኮሜንት ስፍራ ያካፍሉን! #የኢትዮጵያ_እርባታ #የእንስሳት_ጤና #የእንስሳት_መመረዝ #አርሶ_አደር #የእንስሳት_ሐኪም #VolunteerVetCare
364
18
አዲሱ የእንስሳት ጤና እና ደህንነት አዋጅ፦ ለዘርፋችን ዕድገትና ለአመራሮቻችን ስኬት ትልቅ አቅም!" 📜🤝 ሰላም የ Volunteer Vet Care ቤተሰቦች፤ ዛሬ በግብርና ሚኒስቴር በኩል የተሰማው የምስራች ሁላችንንም ባለሙያዎች ያስደሰተ ነው። የእንስሳት ጤና እና ደህንነት አዋጅ ቁጥር 1376/2017 በኢፌድሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ፣ ለዘርፉ መዘመን እና ለሀገራችን የሌማት ትሩፋት ስኬት ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው። ይህ አዋጅ ውጤታማ እንዲሆንና በየደረጃው ላሉ አመራሮቻችን የሥራ ስኬት እንዲያመጣ፣ እኛ ባለሙያዎች ከአመራሮቻችን ጎን በመሆን የሚከተሉትን ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች በቁርጠኝነት ልናከናውን ይገባል፦ የአመራሩን ስኬት ማገዝ፦ አዋጁ የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጥራትና ደህንነት ቁጥጥሮችን "አስገዳጅ" ያደርጋል። እኛ ባለሙያዎች ይህንን ሕግ መሠረት አድርገን በመሥራት፣ አመራሮቻችን በዘርፉ የያዙት የልማት ዕቅድ እንዲሳካ የላቀ ሙያዊ ድጋፍ እንሰጣለን። ሕጋዊ አሠራርን በማስፈን ጫናን መቀነስ፦ በዘርፉ የሚታዩ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችና ያልተገባ የመድኃኒት ዝውውር ለአመራሩም ትልቅ ራስ ምታት ናቸው። አዲሱ አዋጅ እነዚህን ችግሮች በሕግ ለመፍታት ሥልጣን ስለሚሰጥ፣ እኛ ባለሙያዎች ከጸጥታና ከንግድ አካላት ጋር በመቀናጀት ለአመራሩ ምቹ የሥራ አካባቢ እንፈጥራለን። ለሌማት ትሩፋት ስኬት ዋስትና መሆን፦ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘው የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም ውጤታማ የሚሆነው የእንስሳት ጤና ሲጠበቅ ነው። ይህ አዋጅ ደግሞ ለዚህ ትልቅ ዋስትና ስለሆነ፣ እኛ ባለሙያዎች የአዋጁን ዝርዝር መመሪያዎች በመተግበር የአመራሩን ራዕይ እናሳካለን። ግንዛቤ በመፍጠር የሕግ ተገዥነትን ማሳደግ፦ አርሶ አደሩ ስለ አዲሱ አዋጅ ፋይዳ እንዲረዳ በማድረግ፣ በአመራሩና በሕዝቡ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከርና የእንስሳት ሀብቱ በትክክለኛ መንገድ እንዲጠበቅ ማገዝ የባለሙያው የቤት ሥራ ነው። ማጠቃለያ፦ ይህ አዋጅ መውጣቱ መንግሥት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ያሳያል። እኛም ባለሙያዎች ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ ከአመራሮቻችን ጋር በቅንጅት በመሥራት ለዘርፉ ዕድገት፣ ለሀገራችን ብልጽግናና ለሕዝባችን ጤና በትጋት እንሠራለን! #VolunteerVetCare #OneHealthEthiopia #Proclamation1376 #LivestockDevelopment #MoA #Ethiopia #ከማምረትበላይ
401
19
ለዕርባታችን ምርጥ ዝርያ እንዴት እንመርጣለን????
ለዕርባታችን ምርጥ ዝርያ እንዴት እንመርጣለን????
347
20
ውድ የ 'Volunteer Vet Care' የቴሌግራም ቤተሰቦች፣ እንደምን አላችሁ! 🐾 ‎ ‎ዛሬ ከእለት ተዕለት የሙያ ምክሮቻችን በተለየ ከልባችን የምንነጋገረው አሳዛኝ ነገር አለ። የፌስቡክ ፔጃችን
ውድ የ 'Volunteer Vet Care' የቴሌግራም ቤተሰቦች፣ እንደምን አላችሁ! 🐾 ‎ ‎ዛሬ ከእለት ተዕለት የሙያ ምክሮቻችን በተለየ ከልባችን የምንነጋገረው አሳዛኝ ነገር አለ። የፌስቡክ ፔጃችንን በተመለከተ እስካሁን ያልነገርናችሁ ነገር አለ። እንደምታውቁት Volunteer Vet Care በፌስቡክ ላይ ትልቅ ማህበረሰብ ገንብተን ነበር ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የፔጃችንን መዳረሻ (Admin Access) በተደራጁ ሪፖርት አድራጊወች በግፍ ተነጥቀናል። ‎ ‎ይህ ድርጊት የተፈፀመው የዘርፉን እድገት፣ የጤናውን፣የእርባታውን፣የአዳቃዩንና አጠቃላይ ለባለሙያው መብትና ክብር መታገል ከልብ የማይፈልጉ በስራችን የሚቀኑና በምቀኝነት የታወሩ ግለሰቦች የፈጠሩት መሰናክል ነው። ለዘርፉ መሻሻል የምንታገልለትን ትግል በዚህ አይነት የክፋት ተግባር ማፈን እንደሚቻል ማሰባቸው በእጅጉ ያሳዝናል። ‎ ‎ይሁን እንጂ እናንተ ያሳያችሁን ፍቅር እና ድጋፍ ለዚህ ዘርፍ ስንል የምንቀጥልበት ብርታት ነው። ከክፋትና ከምቀኝነት በላይ ከጎናችን ለቆማችሁ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን። ‎ ‎ይህ መሰናክል አላማችንን ሊያደናቅፈው አይችልም። አዲሱን ፔጃችንን በራሱ በቀድሞው ስም የከፈትነው የእንስሳትን ህይወት ለመታደግ ብቻ ሳይሆን ለዘርፉ፣ ለባለሙያው እና ለአርቢው የምናደርገውን ትግል እንደውም ከወትሮው ይበልጥ በሙሉ ሀይላችን አጠናክረን ለመቀጠል ነው። ‎ ‎​እባክዎን አዲሱን ፔጃችንን በመቀላቀልና ጓደኞችዎን ወደ ፔጁ ኢንቫይት በማድረግ ለዘርፉ መሻሻል በጋራ እንቁም ።👇 ‎https://www.facebook.com/share/1EjQLhiy1E/ ‎ ‎ለእንስሳት ጤንነት፣ ለእርባታው ጥራት፣ ለዘርፉ ክብር! ‎​Volunteer Vet Care 🩺🐾
493