Dbu students voice
Open in Telegram
ለደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተቋቋመ!
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
819
Subscribers
+1024 hours
+777 days
+10430 days
Posts Archive
Repost from DBU INSIDER
Department cutt point updated.pdf
For 1st year students ‼️
@DBUINSIDER
@DBUINSIDER
For 1st year students ‼️
1 ምደባ ያላገኛችሁ ተማሪዎች ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 06 ሄዳችሁ በጸሑፍ ማመልከት አለባችሁ፡፡
2. በሕጉ መሰረት ምርጫ መርጣችሁ ቅሬታ ያለባችሁ ተማሪዎች በየኮሌጃችሁ በጸሑፍ ማመልከት አለባችሁ፡፡
ለምሳሌ .፡- የማሕበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ማሕበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ማመልከት አለባችሁ፡፡
የተማሪዎች ህብረት
@dbudbu11
ደብረዘይት‼️
አዩዘሀበሻ እንደዘገበው ደብረዘይት አየር ሀይል ግቢ ውስጥ 'ቴክኒሽያን ክበብ' አካባቢ መስከረም 17/2019 ዓ.ም ጠዋት አጥፍቶ ጠፊ የሚባለው አይነት ከምስራቅ አቅጣጫ የመጣ 2 ድሮን ጥቃት 4 ሰዎች መሞታቸውን፣3 መቁሰላቸውን አዩዘሀበሻ መዘገቡ ይታወሳል።
አሁን ላይ የደረሰን መረጃ እንደሚያመላክተው በዕለቱ 4 ድሮኖች በአየር መቃወሚያ ተመትተው ወድቀዋል።
Horn review የሱዳን ድሮን ኢትዮጵያ ውስጥ ተመትቶ መውደቁን ዘግቧል። መንግሥት በዚህ ጉዳት መረጃ አልሰጠም።
@dbudbu11
የምስጋና እና የአክብሮት መግለጫ
ከ፡ ተማሪ ነገሠ ይቻለዋል
በነበረብኝ ከባድ የኩላሊት ህመም ምክንያት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ቀዶ ህክምና አድርጌ ሙሉ ጤንነቴን መልሼ ለዚህ ላበቃኝ ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋናዬ ይድረስ። በመቀጠልም ህይወቴን ለማትረፍ በፀሎት፣ በሀሳብና በገንዘብ ከጎኔ ለቆማችሁ ውድ ጓደኞቼ፣ ወዳጆቼ እና ዘመዶቼ በሙሉ የከበረ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
በተለይም ህክምናዬ እንዲሳካ ላደረጉልኝ ከፍተኛ ድጋፍ ለሚከተሉት አካላት የላቀ ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ፡-
🙏 ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አስማረ እና ለፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ባዩ — ላሳዩት አባታዊ ድጋፍና ትኩረት፤
🙏ለተማሪዎች ክሊኒክ ሰራተኞች (ለዶክተር ነጋ) እና ለሀኪም ግዛው ሆስፒታል ሰራተኞች (ለዶክተር ዘመድ እና ዶክተር ዮሐንስ)፣ለኢትዮጵያ ጤና ተማሪዎች ማህበር EHPSA — ላደረጉልኝ የህክምና እንክብካቤ እና ትብብር፤
🙏ለተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት (በተለይም ለአቶ ጊዜው ፈጠነ) — ህክምናውን በጥሩ ሁኔታ እንድከታተል ላደረጉት ብርቱ ጥረት፤
🙏ለዩኒቨርሲቲው ሰላምና ደህንነት (ለሳጅን አበበ) — ላደረጉት ጥበቃና አጋርነት፤
🙏ለሴቶችና ህፃናት ዳይሬክቶሬት (ለአድስ አስፍው ወሰን) — ስፖንሰር በማፈላለግ ላደረገችው ያልተጠበቀ effort፤
🙏ለ DBU Daily News፣ Ambashaw TV ፣ DBU Insider፣ DBU Students Voice፣ — መረጃ በማሰራጨትና ገንዘብ በማሰባሰብ ላደረጉት የጎላ አስተዋጽኦ።
🙏ለህግ ተማሪዎች ማኅበር፣ ተማሪ ፖሊስ፣ ተማሪዎች ህብረት እና በጎ አድራጎት ክበብ — ገንዘብ በማሰባሰብ ላደረጉት አስተዋጽኦ፤
🙏ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ ለማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ፣ ለአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል እና ለደብረ ብርሃን ህዝብ — ላሳዩኝ ደግነትና አጋርነት፤
በእናንተና ስማችሁ ባልተጠቀሱ ቅን አሳቢዎች ብርቱ ጥረት ህክምናዬ በስኬት ተጠናቆ በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጤንነት ላይ እገኛለሁ። ላደረጋችሁልኝ መልካም ምግባር በሙሉ ፈጣሪ ዋጋችሁን ይክፈላችሁ።
ከታላቅ አክብሮትና ምስጋና ጋር!
@dbudbu11
What a music is it?
ከዘፈኑስ አይቀር እንደዚህ ነው😍
ሀገር ያለ ሸዋ ድምድም የሌለው ቤት
ሀገር ያለ ወሎ ጣሪያ እንደሌለው ቤት
ሀገር ያለ ጎንደር መዝጊያ እንደሌለው ቤት
ሀገር ያለ ጎጃም ምሰሶ የለው ቤት
ሀገር ያለ አምሓራ🔥
ምን አይነት ስራ ነው?🫢🫢🫢ትችላለች
@dbudbu11
የተማሪ ህብረት ምርጫ ሊደረግ እንደሆነ መረጃ እጃችን ላይ ገብቷል።
Students Voice የታገለችለት እና እየታገለችለት የሚገኘው የተማሪዎች የውክልና ጥያቄ መፍትሄ የሚያገኝበት እድል ከፊታችን እየመጣ ይመስላል።
የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጉዳዩን በትኩረት እየሰራበት እንደሆነም ደርሰንበታል።
ምርጫው ግልፅ እና ፍትሀዊ እንዲሆን ቻናላችን የበኩሏን እየተወጣች ትቀጥላለች።
በዚህ አጋጣሚ DBU insider በተማሪ ህብረት ዙሪያ ላደረጋቸው አስተዎፅኦ ምስጋና ሰጥተን ማለፍ እንፈልጋለን!
@dbudbu11
ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓልን በደብረ ብርሀን ባከብር የደብረ ብርሃን ከተማ ህዝብ ፍቅር እና ደግነት እስከ የት ድረስ እንደሆነ በደንብ ተመለከትሁት😍
ደብርሾች የእውነት ትለያላችሁ የደግነትን ጥግ የተላበሰ ህዝብ😍ፈጣሪ ሰላምን ያድልልኝ🥰
@dbudbu11
ግጥም ተጋበዙልኝ የድሮ ፍቅረኛችሁን መርሳት እና ከአዲስ ሰው መግባባት ላልቻላችሁ👀
በልክሽ ተሰርቶ፤ ቀልዴ ቁምነገሬ
ከተውሽኝ በኋላ…..❤️🔥
አንቺን ለመርሳት ስል ፤
ከብዙ ሴቶች ጋር፤ ልላመድ ሞክሬ
ለማንም አልሆንኩም!
ላንዷ እጠባታለሁ፤😕
ላንዷ እሰፋታለሁ፤
ላንዷ እረዝማታለሁ፤ ላንደኛዋ አጥሬ፡፡🙄
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ይኸው በቀደም ለት…..
ሳቅሽን የሚመስል ፤
ሳቋን የምትስቅ ፤ አንዲት ሴት ወድጄ😊
ሳቋን ለማፅናት ስል..
አንቺን ባሳቅሁሽ ቀልድ፤ እንድትስቅ ቀልጄ
ቀልዴ አላስቅ ብሏት ...😐
ያንቺን የሚመስለው ፤ ያ ሳቋ ቢጠፋ
በቅፅበት ጠላኋት…😖
አንቺን ባሳቀሽ ቀልድ፤ ሳያት እሷ አኩርፋ፡፡😠
።።።።።።።፣፣፣፣፣፣፣።።።።።።።።።።።፣።።
ባለፈው ለት ደሞ…
ያንቺን የሚመስል፤
ኩርፊያ ካኮረፈች፤ ከአንዲት ሴት ጋራ☺️
ላንች የነገርሁሽን...
አስኮራፊ ታሪክ ፣
ኩርፊያዋን ለማፅናት፤ አኩርፌ ሳወራ😕
ያንቺን የሚመስል ፣
ኩርፊያዋ እስኪጠፋ ፣ ሳቋን ብትለቀው😧
ድንገት አስጠላችኝ….🤦♂️
እሷ ማን ሆና ነው?
አንቺን ባስኮረፈሽ ፤ ታሪክ የምትስቀው!?😡
።፣፣፣፣፣።።።።፣።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣።፣።።።፣፣፣፣
ሰሞኑን ደግሞ አንዷን…
የዋናውን መንገድ፤ ትንሽ ገባ ብላ
አራቴ ወደ ቀኝ...
ሶስቴ ወደ ግራ፤ ከታጠፈች ኋላ
ወደ ሌላ ሚወስድ
ሌላ ዋና መንገድ
ከማግኘቷ በፊት...
ያለው ድልድይ ጋር ፣ እንገናኝ ስላት😕
አንቺ ከምትወጂው...
አንቺ ከምትቀጥሪኝ፤ ቦታ ላይ ስቀጥራት😤
‹‹እንዲህ ያለ ቦታ...
በጭራሽ አላውቅም›› ፣ የሚል ነበር መልሷ፤
ዘልዓለም ጠላኀት!
አንቺ ምትወጂውን
ቦታ የማታውቀው ፤ ማን ሆና ነው እሷ?😡!
፣፣፣፣፣፣።።።።።፣፣፣፣፣፣።።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ብቻ ምን ልበልሽ….💔
በልክሽ ተሰርቶ፤ ቀልዴ ቁምነገሬ
ከተውሽኝ በኋላ…..
አንቺን ለመርሳት ስል ፤😥
ከብዙ ሴቶች ጋር፤ ልላመድ ሞክሬ
ለማንም አልሆንኩም!
ላንዷ እጠባታለሁ፤
ላንዷ እሰፋታለሁ፤
ላንዷ እረዝማታለሁ፤ ላንደኛዋ አጥሬ፡፡🤥
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ይኸው ደሞ ዛሬ…
የሌላ እንዳልሆን ፤በልክሽ ሰርተሸኝ
ከተውሽኝ በኋላ…….
ምትወርጂውን መንገድ ፣
እኔ እወጣሁት፤ ድንገት አግኝተሸኝ
‹‹እንዴት ነህ? ››ስስትዪኝ ...
እንዴትም እስክሆን ፣ ግራ አጋባሽኝ
አንቺ ነሽ? እኔን ነው? እንዴት አናገርሽኝ?
እንዴት ነኝ ልበልሽ?
እንደዚያው ነኝ በቃ!🙄
እንደዚህ አድርገሽ ፣ያኔው እንደተውሽኝ፡፡💔
አንቺ ግን እንዴት ነሽ?😊🥰
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
(በላይ በቀለ ወያ)
የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መልካም የደመራ በዓል ይሁንላችሁ!
ደመራ የማታከብሩ የሌላ እምነት ተከታዮች መልካም የዕረፍት ቀን ተመኘንላችሁ!
ሰናይ ቀዳሚት😍
@dbudbu11
በሩ አካባቢ ያለው ጭቃ😢😳ዝናብ ሲጥል ጭቃው ፀሀይ ሲሆን አቧራው😢
ለነገሩ እኛ ነን በእግራችን ለምንሄደው እንጅ በመኪና ለሚሄዱት አይታይም😯
@dbudbu11
