en
Feedback
4-3-3 Tech

4-3-3 Tech

Open in Telegram

Welcome to 4-3-3 Tech On this channel, you will find everything from the latest tech updates to helpful app reviews and powerful web tools.

Show more
4 033
Subscribers
+1724 hours
+5987 days
+53630 days
Posts Archive
በ19 የአፍሪካ ሀገራት በተካሄደ የሳይበር ወንጀል መከላከል ዘመቻ 574 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ... በ19 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ላለፉት 30 ቀናት ሲካሄድ የቆየው መጠነ-ሰፊ የሳይበር ወን
በ19 የአፍሪካ ሀገራት በተካሄደ የሳይበር ወንጀል መከላከል ዘመቻ 574 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ... በ19 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ላለፉት 30 ቀናት ሲካሄድ የቆየው መጠነ-ሰፊ የሳይበር ወንጀል መከላከያ ዘመቻ 574 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል መጠናቀቁን ኢንተርፖል አስታውቋል። "ኦፕሬሽን ሴንቲነል" በሚል ስያሜ በተካሄደው በዚህ ዘመቻ፣ 3 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የተዘረፈ ገንዘብ ማስመለስ የተቻለ ሲሆን፤ ከ6 ሺህ በላይ ጎጂ የሆኑ የኢንተርኔት ድረ-ገጾችም እንዲዘጉ ተደርጓል። ዘመቻው በተለይ በንግድ ድርጅቶች ኢሜል ዝርፊያ፣ በዲጂታል የማስፈራራት ወንጀል እና በፋይል መቆለፊያ ጥቃቶች ላይ ያተኮረ ነበር። በዘመቻው ሂደት በሴኔጋል 7.9 ሚሊዮን ዶላር ሊዘርፉ የነበሩ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ በጋና ደግሞ ታዋቂ የንግድ ተቋማትን በመምሰል ከ200 በላይ ሰዎችን ያታለለ የወንጀል ቡድን ማፍረስ ተችሏል ነው የተባለው። የኢንተርፖል የሳይበር ወንጀል ዳይሬክተር ኒል ጄተን እንደገለጹት፤ በአፍሪካ የፋይናንስ እና ኢነርጂ ዘርፎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እየጨመሩ ነው ብለዋል። በመሆኑም ሀገራት በቅንጅት መስራታቸው የዜጎችን መረጃና የሀገራትን መሠረተ ልማት ለመጠበቅ አስችሏል ነው ያሉት። በዚህ ዘመቻ ወቅት እንደ ትሬንድ ማይክሮ ያሉ የቴክኖሎጂ ተቋማት የወንጀለኞችን የኢንተርኔት አድራሻ በመከታተል ረገድ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል። እንዲህ አይነት የተደራጁ የሳይበር ወንጀሎችን ለመገታት ሀገራት የዲጂታል ሥራቸውን ዘመናዊ ከማድረግ ጎን ለጎን የሳይበር ደህንነት ሥራ ላይ በትጋት መስራት እንዳለባቸው ተመላክቷል። በሰለሞን ገዳ @Tech_433et @Tech_433et

ሩሲያ በአስር ዓመታት ውስጥ በጨረቃ ላይ የኒውክሌር ሀይል ማመንጫ ለመትከል ማቀዷን አስታወቀች ሩሲያ በሚቀጥሉት አስርት አመታት ውስጥ የጨረቃን የጠፈር መርሃ ግብሯን በማስቀጠል የኒውክሌር ሃይል ማመ
ሩሲያ በአስር ዓመታት ውስጥ በጨረቃ ላይ የኒውክሌር ሀይል ማመንጫ ለመትከል ማቀዷን አስታወቀች ሩሲያ በሚቀጥሉት አስርት አመታት ውስጥ የጨረቃን የጠፈር መርሃ ግብሯን በማስቀጠል የኒውክሌር ሃይል ማመንጫ ጣቢያን በጨረቃ ላይ ለመትከል አቅዳለች። ዋናዎቹ የዓለም ኃያል ሀገራት የምድርን ብቸኛ የተፈጥሮ ሳተላይት ለመቃኘት እየተጣደፉ ይገኛል። እ.ኤ.አ. በ 1961 የሶቪየት ኮስሞናዊት ዩሪ ጋጋሪን ወደ ህዋ በመላክ የመጀመሪያው ሰው ከሆነ ወዲህ ሩሲያ በህዋ ምርምር ላይ ቀዳሚ ሃይል ነበረች። ከቅርብ አስርት አመታት ወዲህ ግን ከአሜሪካ እና ቻይና ስር ለመከተል ተገዳለች።እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2023 የራሺያ ፍላጎት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ የሚታወስ ሲሆን ሰው አልባው ሉና-25 ተልእኮ ወደ ጨረቃ ላይ ለማረፍ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። በአንፃሩ ኤሎን ማስክ የጠፈር ተሽከርካሪዎችን በማምጠቅ ላይ ለውጥ አሳይቷል። የሩሲያ ግዛት የጠፈር ኮርፖሬሽን ሮስኮስሞስ በ2036 የጨረቃ ሃይል ማመንጫ ለመገንባት አቅዶ ከላቮችኪን ማህበር ኤሮስፔስ ኩባንያ ጋር ውል መፈራረሙን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሮስስኮስሞስ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫው አላማ የሩስያን የጨረቃ መርሃ ግብር ማለትም ሮቨርስ፣ ኦብዘርቫቶሪ እና የጋራ የሩሲያ-ቻይና አለም አቀፍ የጨረቃ ምርምር ጣቢያ መሠረተ ልማትን ማጎልበት ነው ብሏል። "ፕሮጀክቱ በቋሚነት የሚሰራ ሳይንሳዊ የጨረቃ ጣቢያን ለመፍጠር እና ከአንድ ጊዜ ተልዕኮዎች ወደ የረጅም ጊዜ የጨረቃ ፍለጋ መርሃ ግብር ለመሸጋገር ጠቃሚ እርምጃ ነው" ሲል በመግለጫው አክሏል።(በስምዖን ደረጄ) @Tech_433et @Tech_433et

ናይጄሪያ የማይክሮሶፍት ተጠቃሚዎችን ኢላማ ያደረገ የማጭበርበር ተግባር ሲፈፅም የነበረ ግለሰብ ማሰሯን ገለፀች። ናይጄሪያ ኦኪቲፒ ሳሙኤል የተባለና "Raccoon0365" በመባል የሚታወቀው ግለሰብ በ
ናይጄሪያ የማይክሮሶፍት ተጠቃሚዎችን ኢላማ ያደረገ የማጭበርበር ተግባር ሲፈፅም የነበረ ግለሰብ ማሰሯን ገለፀች። ናይጄሪያ ኦኪቲፒ ሳሙኤል የተባለና "Raccoon0365" በመባል የሚታወቀው ግለሰብ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ የማይክሮሶፍት ተጠቃሚዎችን ኢላማ ያደረገ የማጭበርበር ስራዎችን ሲሰራ ነበር ብላለች። ሳሙኤል የቴሌግራም ቻናል በመጠቀም ሃሰተኛ የመግቢያ ማስፈንጠሪያዎችን ይሸጥ እንደነበርና ክሪፕቶከረንሲ ለመዝረፍ የሚያገለግሉ ገፆችን ያዘጋጅ እንደነበር ተገልጿል። የሳሙኤል እስር የመጣው ኤፍቢአይ እና ማይክሮሶፍት "Raccoon0365" የተባለው አገልግሎት ከአጭበርባሪ ድህረገፆች ጋር መተሳሰሩን እና የበርካቶች መረጃ መሰረቁን ካስታወቁ በኋላ ነው። የዲጂታል ፎረንሲክ ምርመራዎች ከማጭበርበሩ ብቸኛው ተጠቃሚ እራሱ ሳሙኤል ብቻ መሆኑን ሲያመላክቱ ተጨማሪ ምርመራዎች ይቀጥላሉ ተብሏል። ማይክሮሶፍት ባለፈው መስከረም ወር በዚሁ "Raccoon0365" በተባለ አገልግሎት ስር ከ94 ሃገራት የ5000 የማይክሮሶፍት ተጠቃሚዎች መረጃ መሰረቁን እና ለዚሁ አገልግሎት የሚውሉ 338 ድህረገፆችን መዝጋቱን መግለፁ ይታወሳል። ዘገባው የDW ነው። @Tech_433et @Tech_433et

የስማርት ስልክዎ በቫይረስ ወይም በተንኮል አዘል ሶፍትዌር Malware መጠቃቱን ካወቁ፤ ስልኩን ለማጽዳት እና መረጃዎን ለመጠበቅ የሚከተሉትን እርምጃዎች በፍጥነት ይውሰዱ 1. ስልኩን ማጥፋት ወይም
የስማርት ስልክዎ በቫይረስ ወይም በተንኮል አዘል ሶፍትዌር Malware መጠቃቱን ካወቁ፤ ስልኩን ለማጽዳት እና መረጃዎን ለመጠበቅ የሚከተሉትን እርምጃዎች በፍጥነት ይውሰዱ 1. ስልኩን ማጥፋት ወይም ወደ "Safe Mode" መቀየር 👉Safe_Mode: አብዛኛዎቹ አንድሮይድ ስልኮች የኃይል ማጥፊያ ቁልፉን ተጭነው ሲይዙ ወደ Safe Mode የመግቢያ አማራጭ ይሰጡዎታል። በዚህ ሁኔታ ስልኩ ሲከፈት ከስልኩ ጋር ከመጡት መተግበሪያዎች ውጪ ሌሎች አይሰሩም። ይህም ቫይረሱ እንዳይሰራጭ ያግዳል፤ ለማጥፋትም ይመቻል። 2. የማያውቁትንና አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን ማጥፋት Uninstall • 👉ወደ Settings > Apps (ወይም Applications) ይግቡ። • 👉በቅርቡ የጫኑትን ወይም እርስዎ ያልጫኑትን ማንኛውንም መተግበሪያ ይፈልጉ። • 👉መተግበሪያውን ይጫኑና Uninstall የሚለውን በመምረጥ ያጥፉት። ❗ማሳሰቢያ: አንዳንድ ቫይረሶች የ "Administrator" ፈቃድ ስለሚወስዱ በቀላሉ ሊጠፉ አይችሉም። በዚህ ጊዜ Settings > Security > Device Administrators ውስጥ ገብተው ፈቃዱን ቀድመው ማንሳት ይኖርብዎታል። 3. የብሮውዘር Browser መረጃዎችን ማጽዳት 👉ብዙ ጊዜ ቫይረሶች የሚመጡት በድረ-ገጾች በኩል ስለሆነ፣ የሚጠቀሙበትን ብሮውዘር (ለምሳሌ Chrome) ታሪክና ዳታ ያጽዱ። 👉 Settings > Apps > Chrome > Storage > Clear Cache / Clear Data የሚለውን ይጫኑ። 4. የፀረ-ቫይረስ Antivirus መተግበሪያ መጠቀም 👉ከታመነ ቦታ (ለምሳሌ Google Play Store) ታዋቂ የፀረ-ቫይረስ መተግበሪያዎችን በመጫን ስልኩን "Scan" ያድርጉ። 5. የመጨረሻው አማራጭ፦ ወደ ፋብሪካ ሁኔታ መመለስ Factory_Reset 👉ከላይ ያሉት እርምጃዎች ካልሰሩ፣ ስልኩን ሙሉ በሙሉ ማጽዳት ሊኖርብዎ ይችላል። 👉ይህ እርምጃ በስልኩ ላይ ያለውን ማንኛውንም መረጃ (ፎቶ፣ ስልክ ቁጥር፣ ፋይሎች) ስለሚያጠፋ፣ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች አስቀድመው Back up ማድረጋቸውን ያረጋግጡ። 👉ወደ Settings > System > Reset options > Erase all data (factory reset) በመግባት ያጽዱት። @Tech_433et @Tech_433et

የስማርት ስልክዎ በቫይረስ ወይም በተንኮል አዘል ሶፍትዌር Malware መጠቃቱን ካወቁ፤ ስልኩን ለማጽዳት እና መረጃዎን ለመጠበቅ የሚከተሉትን እርምጃዎች በፍጥነት ይውሰዱ 1. ስልኩን ማጥፋት ወይም
የስማርት ስልክዎ በቫይረስ ወይም በተንኮል አዘል ሶፍትዌር Malware መጠቃቱን ካወቁ፤ ስልኩን ለማጽዳት እና መረጃዎን ለመጠበቅ የሚከተሉትን እርምጃዎች በፍጥነት ይውሰዱ 1. ስልኩን ማጥፋት ወይም ወደ "Safe Mode" መቀየር 👉Safe_Mode: አብዛኛዎቹ አንድሮይድ ስልኮች የኃይል ማጥፊያ ቁልፉን ተጭነው ሲይዙ ወደ Safe Mode የመግቢያ አማራጭ ይሰጡዎታል። በዚህ ሁኔታ ስልኩ ሲከፈት ከስልኩ ጋር ከመጡት መተግበሪያዎች ውጪ ሌሎች አይሰሩም። ይህም ቫይረሱ እንዳይሰራጭ ያግዳል፤ ለማጥፋትም ይመቻል። 2. የማያውቁትንና አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን ማጥፋት Uninstall • 👉ወደ Settings > Apps (ወይም Applications) ይግቡ። • 👉በቅርቡ የጫኑትን ወይም እርስዎ ያልጫኑትን ማንኛውንም መተግበሪያ ይፈልጉ። • 👉መተግበሪያውን ይጫኑና Uninstall የሚለውን በመምረጥ ያጥፉት። ❗ማሳሰቢያ: አንዳንድ ቫይረሶች የ "Administrator" ፈቃድ ስለሚወስዱ በቀላሉ ሊጠፉ አይችሉም። በዚህ ጊዜ Settings > Security > Device Administrators ውስጥ ገብተው ፈቃዱን ቀድመው ማንሳት ይኖርብዎታል። 3. የብሮውዘር Browser መረጃዎችን ማጽዳት 👉ብዙ ጊዜ ቫይረሶች የሚመጡት በድረ-ገጾች በኩል ስለሆነ፣ የሚጠቀሙበትን ብሮውዘር (ለምሳሌ Chrome) ታሪክና ዳታ ያጽዱ። 👉 Settings > Apps > Chrome > Storage > Clear Cache / Clear Data የሚለውን ይጫኑ። 4. የፀረ-ቫይረስ Antivirus መተግበሪያ መጠቀም 👉ከታመነ ቦታ (ለምሳሌ Google Play Store) ታዋቂ የፀረ-ቫይረስ መተግበሪያዎችን በመጫን ስልኩን "Scan" ያድርጉ። 5. የመጨረሻው አማራጭ፦ ወደ ፋብሪካ ሁኔታ መመለስ Factory_Reset 👉ከላይ ያሉት እርምጃዎች ካልሰሩ፣ ስልኩን ሙሉ በሙሉ ማጽዳት ሊኖርብዎ ይችላል። 👉ይህ እርምጃ በስልኩ ላይ ያለውን ማንኛውንም መረጃ (ፎቶ፣ ስልክ ቁጥር፣ ፋይሎች) ስለሚያጠፋ፣ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች አስቀድመው Back up ማድረጋቸውን ያረጋግጡ። 👉ወደ Settings > System > Reset options > Erase all data (factory reset) በመግባት ያጽዱት። @Tech_433et @Tech_433et

ለሳይበር ጥቃት የሚያጋልጡ የስማርት ስልክ አጠቃቀም ልምዶች ስማርት ስልኮች በዘመናዊው የሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ የማይተኩ የዕለት ተዕለት መገልገያዎች ሆነዋል። ሆኖም፣ ጥቅማቸው በጨመረ ቁጥር ከደህን
ለሳይበር ጥቃት የሚያጋልጡ የስማርት ስልክ አጠቃቀም ልምዶች ስማርት ስልኮች በዘመናዊው የሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ የማይተኩ የዕለት ተዕለት መገልገያዎች ሆነዋል። ሆኖም፣ ጥቅማቸው በጨመረ ቁጥር ከደህንነት ጋር የተያያዙ ስጋቶችም አብረው ያድጋሉ። ለዚህም ምክንያቱ ስማርት ስልኮቻችን የተለያዩ የግልና ሚስጥራዊ መረጃዎቻችንን ስለምንይዝባቸዉ ለመረጃ መንታፊዎች ኢላማ የመሆንና ለጥቃት የመጋለጥ እድላችን ከፍተኛ ነው። ስማርት ስልኮቻችንን ለጥቃት የሚያጋልጡ ጎጂ የአጠቃቀም ልምዶቻችን ዉስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፥- 👉ያልተረጋገጡ አፕሊኬሽኖችን በስልካችን መጫን ብዙዎቻችን ከዋናው የሶፍትዌር መደብር (Play Store ወይም App Store) ውጭ ያሉ አፕሊኬሽኖችን (APK) በቴሌግራም ወይም በተለያዩ ድረ-ገጾች አማካኝነት እንጭናለን። እነዚህ አፕሊኬሽኖች ስልካችንን ለመሰለል ወይም መረጃ ለመሰረቅ የተዘጋጁ ቫይረሶችን ሊይዙ ይችላሉ። 👉የሶፍትዌር ማሻሻያዎችን (Updates) አለማድረግ የስልክ አምራቾች በየጊዜው የደህንነት ማሻሻያዎችን ይለቃሉ። እነዚህን ማሻሻያዎች ችላ ማለት ጠላፊዎች (Hackers) በድሮው የሶፍትዌር ስሪት ላይ ያሉ ክፍተቶችን ተጠቅመው ስልካችን ውስጥ ሰርገዉ እንዲገቡ መንገድ ይከፍትላቸዋል። 👉 ለሁሉም አፕሊኬሽኖች "ፈቃድ" (Permission) መስጠት አንድ አፕሊኬሽን ስንጭን "Allow" የሚል ምርጫ ይጠይቀናል። ለአንድ ፎቶ ማቀናበሪያ አፕሊኬሽን ስልክ ቁጥሮችን(Contacts) ወይም ያሉበትን ቦታ (Location) እንዲያይ ፈቃድ መስጠት አላስፈላጊ እና ለመረጃ ስርቆት የሚያጋልጥ ነው። 👉 ደህንነታቸው ያልተጠበቁ የዋይፋይ (Public Wi-Fi) አጠቃቀም በካፌዎች፣ በአውሮፕላን ማረፊያዎች ወይም ሕዝብ በስፋት በሚንቀሳቀስባቸዉ ቦታዎች የሚገኙ ነፃ የዋይፋይ ኔትዎርኮች በቀላሉ ለመጠለፍ የተመቹ ናቸው። በእነዚህ ኔትዎርኮችን ተጠቅመን የባንክ አካውንታችንን መክፈት ወይም ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችን መላላክ ከፍተኛ አደጋ አለው። 👉አጠራጣሪ ሊንኮችን መክፈት "ሎተሪ ደርሶዎታል"፣ ወይም "ነፃ የኢንተርኔት ጥቅል" የሚሉ አሳሳች መልዕክቶች ውስጥ ያሉ ሊንኮችን መጫን ስልካችንን ለጠላፊዎች አሳልፎ ይሰጣል። 👉ቀላል የይለፍ ቃላትን (Passwords) መጠቀም እንደ "1234"፣ "0000" ወይም የልደት ቀንን የመሳሰሉ በቀላሉ የሚገመቱ የይለፍ ቃላትን መጠቀም ስልካችን በእጃችን ቢሆን እንኳ በሩቅ ሆኖ ለመገመት ለሚሞክር የመረጃ መንታፊ ስራውን ያቀልለታል። በመሆኑም ለመረጃ መንታፊዎች እንዳይጋለጡ ከላይ የተቀመጡ ጎጂ አጠቃቀሞችን ያስወግዱ። @Tech_433et @Tech_433et

ጎግል በጆሮ ማዳመጫ አማካኝነት ቋንቋዎችን የሚተረጉም መተግበሪያ ይፋ አደረገ ***** በጆሮ ማዳመጫ አማካኝነት የተለያዩ ሀገራት ቋንቋዎችን የሚተረጉመው የጎግል መተግበሪያ ለሙከራ ይፋ ሆኗል፡፡ ኩባ
ጎግል በጆሮ ማዳመጫ አማካኝነት ቋንቋዎችን የሚተረጉም መተግበሪያ ይፋ አደረገ ***** በጆሮ ማዳመጫ አማካኝነት የተለያዩ ሀገራት ቋንቋዎችን የሚተረጉመው የጎግል መተግበሪያ ለሙከራ ይፋ ሆኗል፡፡ ኩባንያው ከትርጉም እና ቋንቋ ነክ አገልግሎቶቹ ጋር ተያይዞ መተግበሪያው ላይ ማሻሻያ አድርጓል፡፡ በመተግበሪያው ላይ የተካተተው ማሻሻያ የተናጋሪውን የንግግር ቅድመ ተከተል እና የድምፅ ቃና በጠበቀ መልኩ ለአድማጭ እንዲተረጉም ተደርጎ የበለፀገ ነው፡፡ ይህም በየትኛውም ቦታ ሆኖ በተለያዩ ቋንቋዎች እየተደረጉ ያሉ ንግግሮች፣ ትዕይንቶች፣ ፊልሞች እና ሌሎችም ይዘቶችን ለመረዳት መተግበሪያውን ማስጀመር እና የጆሮ ማዳመጫ መጠቀም በቂ ነው ተብሏል፡፡ ለሙከራ ይፋ በተደረገው መተግበሪያ የ70 ሀገራት ቋንቋን የሚተረጉም ሲሆን በዋናነት እንደ አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ህንድ ባሉ ሀገራት ላይ እየተሞከረ መሆኑ ተነግሯል፡፡ የጎግል ኩባንያ እ.ኤ.አ በ2010 የቋንቋ መተግበሪያውን ይፋ ካደረገ ጀምሮ በርካታ የማበልፀግ ስራዎችን መስራቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በአፎምያ ክበበው @Tech_433et @Tech_433et

የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን የግል መረጃ አደጋ ላይ የጣለ አዲስ የክሮም Chrome ክፍተት መገኘቱ ተገለጸ ይህን ተከትሎም ጎግል ለክሮም መረጃ ማፈላለጊያዉ Browser በአስቸኳይ ሊተገበሩ የሚገባቸው
የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን የግል መረጃ አደጋ ላይ የጣለ አዲስ የክሮም Chrome ክፍተት መገኘቱ ተገለጸ ይህን ተከትሎም ጎግል ለክሮም መረጃ ማፈላለጊያዉ Browser በአስቸኳይ ሊተገበሩ የሚገባቸው ለሶስት አደገኛ ክፍተቶች መድፈኛ አዲስ ማሻሻያ Patch መልቀቁን አስታውቋል። ከእነዚህ ክፍተቶች መካከል አንዱ በተለይ እጅግ አደገኛ ሲሆን፣ የግል መረጃዎችን ለመጥለፍ በመረጃ ጠላፊዎች በንቃት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ Zero_day ጥቃት መሆኑ ታዉቋል። የደህንነት ባለሙያዎች እንዳስጠነቀቁት ከሆነም ይህ አደገኛ ክፍተት የመረጃ ጠላፊዎች ኮምፒውተራችንን ወይም ስልካችንን ዘልቀው በመግባት የይለፍ-ቃሎችንና ሌሎች ሚስጥራዊ መረጃዎችን እንዲሰርቁ የሚያስችል መሆኑ ታዉቋል። እስካሁን መለያ ቁጥር (CVE) ያልተሰጠውና በጎግል የውስጥ መለያ 466192044 ብቻ የሚታወቀው ይኸው ክፍተት፣ በክሮም ተጠቃሚዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ተገልጿል። ይህ ጥቃት በፈረንጆቹ 2025 ዓ.ም. የመረጃ ጠላፊዎች በስፋት ሲጠቀሙበት የተገኘ ስምንተኛው የክሮም "ዜሮ-ዴይ" ጥቃት መሆኑም ተረጋግጧል። ይህ የሚያሳየው የክሮም ተጠቃሚዎች በተደጋጋሚ የጥቃት ኢላማ መሆናቸዉን ነው። ታኅሣሥ 1, 2018 ዓ.ም. የተለቀቀው ይህ ማሻሻያ ከላይ ከተጠቀሰው ከፍተኛ አደጋ በተጨማሪ፣ ሁለት መካከለኛ ደረጃ የተሰጣቸውን የደህንነት ክፍተቶችም ይደፍናል ተብሎለታል። ሁሉም የክሮም ተጠቃሚዎች የግል መረጃቸዉ ሳይጠለፍ እና የባንክ አካውንታቸዉ አደጋ ላይ ሳይወድቅ ለመከላከል፣ እንዲችሉ ሁሉንም የክሮም የመረጃ ማፈላለጊያቸዉን በአስቸኳይ እንዲያዘምኑ Update በጥብቅ ይመከራል።(INSA) @Tech_433et @Tech_433et

ጉግል 'ዐይን ላይ የሚደረግ ኮምፒውተር' የተባለ በኤአይ የሚሠራ ስማርት መነጽር ለገበያ ሊያቀርብ ነው ጉግል በመጪው የአውሮፓውያን ዓመት በሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የሚሠራ ስማርት መነጽር ለገ
ጉግል 'ዐይን ላይ የሚደረግ ኮምፒውተር' የተባለ በኤአይ የሚሠራ ስማርት መነጽር ለገበያ ሊያቀርብ ነው ጉግል በመጪው የአውሮፓውያን ዓመት በሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የሚሠራ ስማርት መነጽር ለገበያ እንደሚያቀርብ አስታወቀ።ከዚህ ቀደም ስማርት መነጽር ለማቅረብ ያደረገው ጥረት ባይሳካም በቅርቡ እንደ አዲስ መነጽሩን የሚያስተዋውቅ ይሆናል።ጉግል በአውሮፓውያኑ 2013 መነጽሩን ሲያስተዋውቅ የወደፊቱ ቴክኖሎጂ ማሳያ ተደርጎ ተወስዶ ነበር። መነጽሩ ከዐይን በላይ ጎልቶ የሚታይ ስክሪን የተገጠመለትም ነበር።መነጽሩ በ2015 (እአአ) ከገበያ ውጪ ቢደረግም አሁን ግን በድጋሚ ለማቅረብ ጉግል ወስኗል።ሜታ ባለፈው ዓመት የካቲት ላይ ስማርት መነጽር ያስተዋወቀ ሲሆን፤ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ገዝተውታል።የጉግል ስማርት መነጽር ከሌሎች የጉግል ምርቶች ጋር የተሳሰሩ ናቸው። መነጽሩን የሚያደርጉ ሰዎች እንደ ጄምኒ ያሉ የጉግል መተግበሪያዎችን መጠቀም ይችላሉ። ጄምኒ በጽሑፍ እና በድምጽ ለጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥ የጉግል ቻትቦት ነው።ጉግል ለገበያ ከሚያቀርባቸው መነጽሮች አንደኛው ስክሪን የሌለው ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ በመነጽሩ ሌንስ ላይ ስክሪን የተገጠመለት ነው።የቴክኖሎጂ ተንታኝ ፓውሎ ፔስካቶሬ "ጉግል ከቀደመው ስህተት መማር አለበት። ከዚህ ቀደም መነጽሩን ያስተዋወቀው መውጣት ከነበረበት ጊዜ ቀድሞ ነው" ብለዋል።ጄምኒ ቻትቦት ስኬታማ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የጉግል ስማርት መነጽር ውጤታማ ሊሆን እንደሚችልም ተናግረዋል። በስምዖን ደረጄ @Tech_433et @Tech_433et

"React2Shell" የተሰኘ አደገኛ የዌብ መተግበሪያ የደህንነት ተጋላጭነት መከሰቱ ተገለጸ "React2Shell" (CVE-2025-55182) የተሰኘው አደገኛ የዌብ መተግበሪያ የደህንነት ተጋላጭነት
"React2Shell" የተሰኘ አደገኛ የዌብ መተግበሪያ የደህንነት ተጋላጭነት መከሰቱ ተገለጸ "React2Shell" (CVE-2025-55182) የተሰኘው አደገኛ የዌብ መተግበሪያ የደህንነት ተጋላጭነት በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ጥቅም ላይ በሚውሉት React እና Next.js በተሰኙ የዌብ አፕሊኬሽን ወሳኝ መዋቅሮች ላይ እጅግ አደገኛ የሆነ የጥቃት ተጋላጭነት መከሰቱ ተገልጿል፡፡ ይህ ተጋላጭነት የመረጃ ጠላፊዎች የተቋማትን ሰርቨር ከርቀት ሆነው ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠሩ የሚያስችል (Remote Code Execution - RCE) ክፍተትን የፈጠረ ነው። በዚህም የድርጅቶች ጥብቅ መረጃዎች ላልተገባው አካል ወይም የመረጃ መዝባሪዎች እጅ እንዲወድቅ ያደርገዋል፡፡ አሁን ላይ ይህ የጥቃት ተጋላጭነት ክፍተት እንደ አማዞን የዌብ አገልግሎት ደህንነት እና ሌሎችም የስጋት መከታተያ ተቋማት ይፋ እንዳደረጉት መረጃ፤ ተጋላጭነቱ ከተገኘበት እለት አንስቶ ከፍተኛ ፍተሻ እየተደረገ ይገኛል ተብሏል፡፡ በዚህ ክፍተት የሚከተሉት የሶፍትዌር ስሪቶች (Versions) ለጥቃት ተጋላጭ መሆናቸው ተገልጿል፡- ● React: Versions 19.0.0 እስከ 19.0.1 (Experimental releases ጨምሮ) ● Next.js: Versions 13, 14, እና 15 (App Router የሚጠቀሙ ከሆነ) ● React Server Components (RSC) የሚጠቀም ማንኛውም ዌብ አፕሊኬሽን ተጋላጭነቱን ለመከላከል መወሰድ ያለባቸው የመፍትሄ እርምጃዎች (Mitigation Strategies) 1. ክፍተት አስተዳደር Patch Management (Immediate Action): • React Framework ወደ version 19.0.2 ወይም ከዚያ በላይ ማዘመን፤ • Next.js Framework ወደ version 15.1.0 ወይም ከዚያ በላይ ማዘመን፤ 2. ክትትተል እና ምርመራ ማድረግ (Monitoring and Detection) ማድረግ • በተቋማት ዌብ አፕሊኬሽን (Web Application Firewall - WAF) ላይ ያልተለመዱ HTTP ጥያቄዎች እና አጠራጣሪ እንቅስቀሴዎችን መከታተል፤ • በሰርቨር ላይ አዳዲስ እና ያልታወቁ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን በ Endpoint Detection and Response (EDR) በኩል ማረጋገጥ። 3. አውታረ መረቡን መለየት (Network Segmentation): • የዌብ ሰርቨር (Web Servers) ከውስጣዊ ወሳኝ የዳታቤዝ መረጃዎች (Critical Databases) እና ከውስጣዊ ኔትዎርክ (Internal Networks) ጋር ያላቸውን ግንኙነት መገደብ (Isolate)፤

ሳምሰንግ የመጀመሪያውን ሶስት ቦታ የሚተጣጠፍ ስልክ ይፋ አደረገ **. ሳምሰንግ ኩባንያ "ጋላክሲ ዚ ትሪፎልድ" የተሰኘ የመጀመሪያውን 3 ቦታ የሚተጣጠፈ ስማርት ስልክ ይፋ አደረገ። አዲሱ ስልክ 3
ሳምሰንግ የመጀመሪያውን ሶስት ቦታ የሚተጣጠፍ ስልክ ይፋ አደረገ **. ሳምሰንግ ኩባንያ "ጋላክሲ ዚ ትሪፎልድ" የተሰኘ የመጀመሪያውን 3 ቦታ የሚተጣጠፈ ስማርት ስልክ ይፋ አደረገ። አዲሱ ስልክ 3 ክፍሎች ሲኖሩት፤ ሙሉ ለሙሉ ሲዘረጋ 10 ኢንች ወይም 25.4 ሳ.ሜ ያህል ስፋት አለው። ስልኩ ከሌሎች የሳምሰንግ ስልኮች የተለቀ ባትሪ ያለው ሲሆን፤ በ30 ደቂቃ ውስጥ እስከ 50 ፐርሰንት ቻርጅ ማድረግ ይችላል ተብሏል። የአዲሱ ስልክ ስክሪን ከዚህ ቀደም ከነበረው የሳምሰንግ ባለ 2 ታጣፊ ስልክ (ጋላክሲ ዚ ፎልድ) በ25 በመቶ እንደሚበልጥ ታውቋል። 3 ቦታ የሚተጣጠፈው "ጋላክሲ ዚ ትሪፎልድ" ዋጋው ወደ 2 ሺህ 440 ዶላር ገደማ እንደሆነ ተገልጿል። በደቡብ ኮሪያ የተሰራው ትሪፎልድ በዲሴምበር 12 ለሽያጭ እንደሚቀርብም ነው የተገለጸው። በተጨማሪም በዚህ ዓመት መጨረሻ በቻይና፣ በሲንጋፖር፣ በታይዋን እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለሽያጭ የሚቀርብ ሲሆን፤ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ደግሞ በአሜሪካ ለገበያ እንደሚቀርብ ተዘግቧል። "ጋላክሲ ዚ ትሪፎልድ" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ገበያው በመጡት ስክሪናቸው የሚታጠፍ ስልኮች መካከል ያለውን ውድድር ከፍ እንደሚያደርገው ይጠበቃል። በሴራን ታደሰ @Tech_433et @Tech_433et

ለተራራማዎቹ የቻይና ግዛቶች የትራንስፖርት ችግር መፍትሔ እየሆኑ ያሉት የጭነት ድሮኖች በደቡብ ምዕራብ ቻይና የምትገኘው የጉዊዡ ግዛት ባላት የተፈጥሮ አቀማመጥ ምክንያት ለዘመናዊ ትራንስፖርት አመቺ
+3
ለተራራማዎቹ የቻይና ግዛቶች የትራንስፖርት ችግር መፍትሔ እየሆኑ ያሉት የጭነት ድሮኖች በደቡብ ምዕራብ ቻይና የምትገኘው የጉዊዡ ግዛት ባላት የተፈጥሮ አቀማመጥ ምክንያት ለዘመናዊ ትራንስፖርት አመቺ የምትባል አይደለችም። በግዛቷ አደጋ ሲከሰት እና በፍጥነት መድኃኒቶችን እና አስፈላጊ ግብዓቶችን ለማከፋፈል በሚያስፈልግበት ወቅት የሚወስደውን ጊዜ ለመቀነስ መፍትሔ በማፈላለግ ላይ የነበሩ የግዛቷ ባለሥልጣናት የጭነት ድሮኖችን መጠቀም ተመራጩ መፍትሔ መሆኑን ለይተው ወደ ሥራ ገብተዋል። በኤሌክትሪክ የሚሠሩት የጭነት ድሮኖቹ ከመደበኛው የድሮን ዓይነቶች የሚለዩት በሚይዙት የጭነት ብዛት በዝቅተኛ ከፍታ መብረር መቻላቸው ነው ተብሏል። በዚህም ለተራራማዋ መንደር አስፈላጊ ናቸው የተባሉ መድኃኒቶችን እና የግብርና ምርቶችን የያዘ እስከ 2 ቶን የመሸከም አቅም ያለው ድሮን 118 ኪ.ሜ በተሳካ ሁኔታ በረራ ማድረግ ችሏል። በሀብተሚካኤል ክፍሉ @Tech_433et @Tech_433et

በዓለም ዙሪያ የዋትስአፕ ተጠቃሚዎችን ያነጣጠረ መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት ዘመቻ መከፈቱ ተገለጸ። ይህ የሳይበር ጥቃት አላማም የዋትስአፕ አካውንቶችን በመጥለፍ ተጠቃሚው በዋትስአፕ WhatsApp ፕላ
በዓለም ዙሪያ የዋትስአፕ ተጠቃሚዎችን ያነጣጠረ መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት ዘመቻ መከፈቱ ተገለጸ። ይህ የሳይበር ጥቃት አላማም የዋትስአፕ አካውንቶችን በመጥለፍ ተጠቃሚው በዋትስአፕ WhatsApp ፕላትፎርም ላይ ያለውን እምነት ማሳጣት እንደሆነ CTM360 የተባለዉ የሳይበር ደህንነት ምርት አቅራቢ ኩባንያ ጠቁሟል። ይህ ዋትሳፕን ኢላማ አድርጎ የተከፈተዉ ዘመቻ “HackOnChatˮ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ከዚህ አጥፊ ተልዕኮ ጀርባ ያሉ አጭበርባሪዎች ጥቃታቸዉን ለመሰንዘር የተለያዩ የማጭበርበሪያ አማራጮችን የሚጠቀሙ ሲሆን ከእነዚህ መካከልም ተመሳስሎ የተሰራ ድረ-ገጽ በመፍጠርና የዋትሳፕ ገጽታን በመላበስ የሚፈጸም ማጭበርበር ነዉ። የመረጃ መንታፊዎቹ ተጠቃሚዉ ወደ አካዉንቱ ከፍቶ ሲገባ እንዳይጠራጠር ጉዳዩ አስቸኳይ እንደሆነ በማስመሰል ትኩረት የመበተን ታክቲክን እንደሚጠቀሙ ተገልጿል። “HackOnChatˮ የጥቃት ዘመቻ የተለያዩ የማህበራዊ ምህንድስና ቴክኒኮችን የሚጠቀም ሲሆን አለምአቀፍ የዋትሳፕ ተጠቃሚዎችን ለማጥቃት በተለያዩ ቋንቋዎች ሀሰተኛ ገፆችን በመክፈት ተጽእኖዉን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ማሳደጉ ታዉቋል። “የCTM360” የስጋት ትንተና ቡድን በአሁኑ ሰዓት የዚህን የጥቃት ዘመቻ ዝግመተ ለውጥ የመከታተል፣ ቴክኒካል ስልቶቻቸውን የመተንተን እና ስርጭታቸውን ለመግታት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ ገልጿል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በሃገራችን የዋትሳፕና የቴሌግራም አካዉንቶች ጠለፋ እየተበራከተ ይገኛል። በመሆኑም ዋትሳፕን ጭምሮ ሌሎች አካዉንቶታችንን ከፍተን ስንገባ የምንገባበት ድረ-ገጽ ትክክለኛ ገጽ መሆኑን በማረጋገጥ ሊድርስብን የሚችልን ጥቃት ልንከላከል ይገባል። @Tech_433et @Tech_433et

‘በጣም ቆንጆ ይደንሳል’፡ ፑቲን በቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ላይ ለቀረበው የሮቦትን ዳንስ የሰጡት ግምገማ የሩሲያው መሪ 'ግሪን' ተብሎ የተሰየመው የስቤርባንክ መሐንዲሶች እንደ ሁለንተናዊ ረዳት ባዘጋጁት እና በገጣጠሙት የባንኩ የመጀመሪያው የሰው ቅርጽ ያለው ሮቦት ሰላምታ ቀርቦላቸዋል። ሮቦቱ በቅርቡ የተማረውን ዳንስ ለፕሬዝዳንቱ አሳይቷል። ‘ግሪን’ ሮቦት ደህንነቱ የተጠበቀ ሥራውን የሚያረጋግጥ ውስብስብ የስሜት ሕዋሳት (ሴንሰውሮች) ሥርዓት ተገጥሞለታል። የተገጠሙለት አስር ሴንሰሮች የእይታ መረጃን ሲያብላሉ፣ የማይንቀሳቀሱ እና የኃይል ሴንሰሮች ደግሞ እንቅስቃሴዎቹ ሚዛናዊ እና ትክክለኛ እንዲሆኑ ያረጋግጣሉ። በተጨማሪም፣ የጊጋቻት ድምፅና መገናኛ ሥርዓት በመዋሃዱ ሮቦቱ መናገር እና የድምፅ ትዕዛዞችን መረዳት ይችላል። @Tech_433et @Tech_433et

6ጂ ኔትወርክን ቀድሞ ለማስተዋወቅ የሚደረገው ፉክክር *** በዓለማችን ላይ በአሁኑ ሰዓት ከአምስተኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ (5ጂ) ወደ ስድስተኛው ትውልድ (6ጂ) ለመሸጋገር በርካታ ምርምሮች
6ጂ ኔትወርክን ቀድሞ ለማስተዋወቅ የሚደረገው ፉክክር *** በዓለማችን ላይ በአሁኑ ሰዓት ከአምስተኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ (5ጂ) ወደ ስድስተኛው ትውልድ (6ጂ) ለመሸጋገር በርካታ ምርምሮች በመደረግ ላይ ናቸው። በፈረንጆቹ 2030 ምርምሮች ወደ መሬት ወርደው የ6ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ ጊዜ ቀድሞ የፈጠራው ባለቤት ለመሆን ሀገራት ፉክክር ውስጥ ገብተዋል። ከአምስተኛው ትውልድ ኔትወርክ በ100 እጥፍ ፍጥነት እንደሚበልጥ የተነገረለት የ6ኛው ትውልድ ኔትወርክ አንድ ቴራ ባይት ፋይል ለማውረድ በቀደመው ጊዜ 13 ደቂቃ ይፈጅ የነበረውን ጊዜ ወደ 8 ሰከንድ የሚያሳጥር ነው፡፡ ቻይና አሁን ባለው የምርምር ሁኔታ በ6ጂ ኔትወርክ ፈጠራ ላይ የሚታይ እድገት በማሳየት ላይ ትገኛለች፡፡ እንደቻይና ሳይንስ ዘገባ ሀገሪቱ በሲስተም ዲዛይን እና የኔትወርክ አርክቴክቸርን ጨምሮ ከ300 በላይ ቁልፍ የ6ጂ ኔትወርክ ምርምር እንዳላት አስታውቃለች። በዚህ ብቻ ያላቆመው የቻይና የሙከራ ሂደት የ6ጂ የሙከራ ሳታላይት ማበልጸግ መጀመሯ አንድ እርምጃ መቅደሟን አመላካች ነው ተብሏል። አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ደቡብ ኮርያ፣ ጃፓን እና የአውሮፓ ሀገራትም በዘርፉ ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት መድበው በመስራት ላይ የሚገኙ ሲሆን ማን ቀድሞ የቴክኖሎጂው ባለቤት ይሆናል የሚለው የሚጠበቅ ነው። በቦታዎች ተወስኖ አገልግሎት የሚሰጠውን የአምስተኛው ትውልድ ኔትወርክ አዲሱ የስድስተኛ ትውልድ ኔትወርክ ያለገደብ እንዲሰራም የሚያደርግ ነው፡፡ በሀብተሚካኤል ክፍሉ @Tech_433et @Tech_433et

AI የሚለውን ሁሉ በጭፍን አትመኑ- የአልፋቤት ኩባንያ ሀላፊ ሰንደር ፒቻይ ሰዎች የAI መሳሪያዎች የሚነግራቸውን ሁሉ በጭፍን ማመን የለባቸውም ሲሉ የጎግል እናት ኩባንያ አልፋቤት ኃላፊ ለቢቢሲ ተና
AI የሚለውን ሁሉ በጭፍን አትመኑ- የአልፋቤት ኩባንያ ሀላፊ ሰንደር ፒቻይ ሰዎች የAI መሳሪያዎች የሚነግራቸውን ሁሉ በጭፍን ማመን የለባቸውም ሲሉ የጎግል እናት ኩባንያ አልፋቤት ኃላፊ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ልዩ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ሱንዳር ፒቻይ፤ የAI ሞዴሎች ለስህተት የተጋለጡ መሆናቸውን በመግለፅ ሰዎች እነዚን መተግበሪያዎች ከሌሎች አጋዥ መሳሪያዎች ጋር እንዲጠቀሙ አሳስበዋል፡፡ በAI ቴክኖሎጂ ላይ ብቻ ከመተማመን ይልቅ የበለፀገ እና ሰፊ የሆነ የመረጃ ስነ-ምህዳርን መፍጠር ወይንም መፈለግ ተገቢ ነውም ብለዋል፡፡ ለዚህም ነው ሰዎች ሌሎች የጎግል ፍለጋ አማራጮችን የሚጠቀሙት ያሉት ሀላፊው፤ የበለጠ ትክክለኛ መረጃን ለማቅረብ የተመሰረቱ ሌሎች ምርቶችም አሉን ነዉ ያሉት፡፡ አንዳንድ ባለሙያዎች እንደ ጎግል ላሉ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የመሳሪያዎቻቸውን ውጤት እንዲፈትሹ እና እንዲያጣሩ ከመጋበዝ ይልቅ ስርዓቶቻቸውን ይበልጥ አስተማማኝ ማድረግ ላይ ማተኮር አለባቸው ብለዋል። የAI መሳሪያዎች ጠቃሚዎች ናቸው፤ የፈጠራ ስራዎችን ለመስራት ያግዛሉ ነገር ግን ሰዎች እነዚህን መሳሪያዎች ምን ላይ ጥሩ እንደሆኑ በመለየት መጠቀምን መማር አለባቸው ፤ሁሉንም በጭፍን ማመን ተገቢ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በተቻለ መጠን AI ትክክለኛ መረጃ እንዲሰጥ በምንሰራው ስራ እንኮራለን፤ ነገርግን አሁን ያለው ዘመናዊ የAI ቴክኖሎጂ ለአንዳንድ ስህተቶች የተጋለጠ ነው ብለዋል፡፡ ድርጅታችን ስህተት ሊሰራ እንደሚችል ለተጠቃሚዎች ያሳዉቃል፤ ይህም ግን ከትችት አያድንም ማለታቸዉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ሀና ሰይፉ @Tech_433et @Tech_433et

ኬንያ የሳይበር ጥቃት ተፈጽሞባታል። በኬንያ በተፈጸመ የሳይበር ጥቃት የፕሬዚዳንቱን ፅህፈት ቤት ጨምሮ የበርካታ ሚኒስቴሮች ድረ-ገጽ ተጠልፎ የነበረ ሲሆን ከሰዓታት በኋላ ዳግም ተመልሷል። በዚህ የተ
ኬንያ የሳይበር ጥቃት ተፈጽሞባታል። በኬንያ በተፈጸመ የሳይበር ጥቃት የፕሬዚዳንቱን ፅህፈት ቤት ጨምሮ የበርካታ ሚኒስቴሮች ድረ-ገጽ ተጠልፎ የነበረ ሲሆን ከሰዓታት በኋላ ዳግም ተመልሷል። በዚህ የተቀናጀ የሳይበር ጥቃት የፕሬዚዳንቱን ጽህፈት ቤት ጨምሮ የጤና፣ የትምህርት፣ የስራ፣ የአካባቢ፣ የሃገር ውስጥ፣ የቱሪዝምና የቴክኖሎጂ ሚኒስቴሮች ድህረገጽ መጠለፉ ተነግሯል። ድረ-ገጾቹ መጠለፋቸውን ተከትሎ በድሀረገፆቹ ላይ "Access denied by PCP", "We will rise again", "White power worldwide", and "14:88 Heil Hitler" የሚል ፅሁፍ ታይቷል። ድህረገፆቹ ከተጠለፉ በኋላም መንግስት በኦንላይን የሚሰጣቸው አገልግሎቶች አቋርጦ ቆይቷል። የመከላከያ እና የገንዘብ ሚኒስቴር በጥቃቱ ሰለባ አልሆኑም ሲባል ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን እስካሁን የለም። በ2023 በኬንያ መንግስታዊ ተቋማት ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ደርሶ የነበረ ሲሆን የሱዳን የመረጃ መዝባሪዎች ቡድን ኃላፊነቱን ወስዶ ነበር። ዘገባው የኬንያንስ ነው። @Tech_433et @Tech_433et

በዓለም ለመጀመሪያ ግዜ በሮቦት ማሽን የታገዘ የስትሮክ ቀዶ ሕክምና ተደረገ * በስኮትላንድና በአሜሪካ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች በዓለም ለመጀመሪያ ግዜ በሮቦት የታገዘ የስትሮክ ቀዶ ሕክምና ማድረ
+2
በዓለም ለመጀመሪያ ግዜ በሮቦት ማሽን የታገዘ የስትሮክ ቀዶ ሕክምና ተደረገ * በስኮትላንድና በአሜሪካ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች በዓለም ለመጀመሪያ ግዜ በሮቦት የታገዘ የስትሮክ ቀዶ ሕክምና ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡ ቀዶ ህክምናውን የስኮትላንድ ዱንድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ኢይሪስ ግራንዋልድ እና በአሜርካ ፍሎሪዳ የሚገኙት ዶክተር ሪቻርድ ሀኔል በሮቦት ማሽን በመታገዝ ማከናወናቸው ተጠቅሷል፡፡ በሮቦት የታገዘውን የቀዶ ሕክምና ሂደት ከዩኒቨርሲቲው አንድ ማዕከል ላይ ሆነው ሲከታተሉ የነበሩት ፕሮፌሰር ኢይሪስ፤ የሮቦት ማሽኑ ከዩኒቨርሲቲው አንድ የህክምና ምርምር ማዕከል ላይ ሆኖ ስራውን እንዲያከናውን መደረጉን ገልፀዋል፡፡ ዶክተር ሪቻርድ ሀኔል ደግሞ ከአሜርካ ፊሎሪዳ ከ6 ሺህ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሆነው በሮቦት ማሽኑ እገዛ የተሳካ የስትሮክ ቀዶ ህክምና ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡ በሮቦት ማሽን የታገዘው የስትሮክ ቀዶ ሕክምና በቀጣይም በተማሚዎች ላይ በደንብ ተግባራዊ ሲደረግ ለዘርፉ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር የህክምና ቡድኑ በሰጠው ገለጸ ተመላክቷል፡፡ የሮቦት ማሽኑ ያደረገው የቀዶ ሕክምና የታካሚውን የደም ዝውውር ጤናማ እንዲሆን በማድረግ ተማሚው በፍጥነት የሚያገግምበት፣ የተለየ ህክምና በመስጠት የሰውን ህይወትን መታደግ የሚያስችል የሕክምና ምርምር ውጤት የተገኘበት ነው ተብሏል፡፡ ባለፈው ወር ተግባራዊ ተደርጎ ውጤታማነቱ የተረጋገጠው በሮቦት ማሽን የታገዘው የስትሮክ ህክምና ሙከራ የሁለት ሀገራት የምርምር ቡድኖች የተሳተፉበት ሲሆን፤ ሮቦት ማሽኑን በማምረት ሴንታት የተባለ ኩባንያ እንዲሁ የአጋዥነት ሚናውን መወጣጡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ በመሐመድ ፊጣሞ @Tech_433et @Tech_433et

የቴስላ ባለአክሲዮኖች ለኤሎን ማስክ የ1 ትሪሊዮን ዶላር የክፍያ ስምምነት ፈቅደዋል!! 75%+ ባለአክሲዮኖች የእሺታ ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ይህንንም ለማሳካት በ 10 ዓመት ውስጥ ኢሎን ማስክ ማሳካት
+1
የቴስላ ባለአክሲዮኖች ለኤሎን ማስክ የ1 ትሪሊዮን ዶላር የክፍያ ስምምነት ፈቅደዋል!! 75%+ ባለአክሲዮኖች የእሺታ ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ይህንንም ለማሳካት በ 10 ዓመት ውስጥ ኢሎን ማስክ ማሳካት ያለበት: • $TSLA ወደ $8.5T የገበያ ዋጋ ማሳደግ መቻል (ከዛሬው $1.4T የገበያ ዋጋ የ466% ጭማሪ ) • በጥቅል 20 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎች ሰርቶ ለገበያ ማቅረብ • 1 ሚልዮን Optimus humanoid ሮቦቶች መሸጥ • 1 ሚሊዮን ሮቦ-ታክሲ ( Robotaxis ) በስራ ላይ ማዋል • 10 ሚሊዮን Full Self-Driving subscriptions ማሳካት ይህን ማድረግ ከተሳካለት ኢሎን ማስክ በአለማችን የመጀመሪያው Trillionaire እና የ ቴስላ 25% አክሲዮን ባለቤት ይሆናል:: @Tech_433et @Tech_433et

ትራፊኩ ሮቦት በይፋ ሥራውን ጀምሯል..... በቻይና ዤጂያንግ ግዛት፣ ቶንግሺያንግ ከተማ አንድ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ሮቦት በይፋ ሥራውን ጀምሯል። የ1 ሜትር ከ80 ሳ.ሜ ቁመት ያለው ትራፊኩ ሮቦት ዛሬ
ትራፊኩ ሮቦት በይፋ ሥራውን ጀምሯል..... በቻይና ዤጂያንግ ግዛት፣ ቶንግሺያንግ ከተማ አንድ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ሮቦት በይፋ ሥራውን ጀምሯል። የ1 ሜትር ከ80 ሳ.ሜ ቁመት ያለው ትራፊኩ ሮቦት ዛሬ በይፋ ሥራውን መጀመሩን ተከትሎ የቶንግሺያንግ ከተማን የትራፊክ እንቅስቃሴ በማሳለጥ ላይ ይገኛል። አቅጣጫዎችን እና የተለያዩ የመንገድ ትራፊክ ምልክቶችን እንዲረዳ ተደርጎ የተፈበረከው ሮቦቱ የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት በተገቢው መንገድ በመረዳት ሥራውን በአግባቡ እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል። በሀብተሚካኤል ክፍሉ @Tech_433et @Tech_433et