en
Feedback
4-3-3 Tech

4-3-3 Tech

Open in Telegram

Welcome to 4-3-3 Tech On this channel, you will find everything from the latest tech updates to helpful app reviews and powerful web tools.

Show more
4 033
Subscribers
+1724 hours
+5987 days
+53630 days
Posts Archive
በሐሳብ ኃይል የሚታዘዘው የቻይናውያን ድንቅ ተሽከርካሪ ወንበር የሳይንስ ልብ ወለድ ፊልሞች እውን እየሆኑ ነው! በሐሳብ ብቻ የሚታዘዝ መሣሪያ በምናባችን ስንሥለው የኖርነው ቢሆንም፣ ቻይናውያን ተመራ
በሐሳብ ኃይል የሚታዘዘው የቻይናውያን ድንቅ ተሽከርካሪ ወንበር የሳይንስ ልብ ወለድ ፊልሞች እውን እየሆኑ ነው! በሐሳብ ብቻ የሚታዘዝ መሣሪያ በምናባችን ስንሥለው የኖርነው ቢሆንም፣ ቻይናውያን ተመራማሪዎች ግን ይህንን "የሳይንስ ተአምር" ወደ እውነት ቀይረውታል። በዠጂያንግ ዩኒቨርሲቲ የ"Brain-Machine Intelligence" ላቦራቶሪ ሳይንቲስቶች፣ የአዕምሮ ምልክቶችን (Brain signals) በቀጥታ ወደ ተግባር የሚቀይሩ የኤአይ (AI) አልጎሪዝሞችን በመጠቀም፣ በሐሳብ ብቻ የሚቆጣጠሩትን ኮምፒውተሮችና ተሽከርካሪ ወንበሮችን ይፋ አድርገዋል። "Brain-computer interface (BCI)" በተሰኘው በዚህ ዘርፍ፣ ተጠቃሚው በጭንቅላቱ ላይ የሚታሰር የኤሌክትሮኒክ መሣሪያ (EEG headband) ያደርጋል። ይህ መሣሪያ የአዕምሮን መረጃ የማንበብና ትዕዛዞችን የመቀበል ብቃት አለው። የቻይና ግሎባል ቴሌቪዥን (CGTN) ዘጋቢ በቦታው ተገኝቶ በሰጠው ማሳያ፣ ዘጋቢው ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጦ "ወደ ፊት ሂድ" ወይም "ወደ ጎን ታጠፍ" ብሎ ማሰብ ብቻ ነው የጠበቀበት፤ ወንበሩም ልክ እንደ ታዛዥ አገልጋይ የዘጋቢውን የሐሳብ ትዕዛዝ ተቀብሎ ጉዞውን ጀምሯል። የላቦራቶሪው ተመራማሪ ዋንግ ጂኳን እንደሚሉት፣ የመሣሪያው አስደናቂነት በዚህ ብቻ አያበቃም። መሣሪያው የአንድን ሰው የትኩረት ደረጃ መከታተል ይችላል። ለምሳሌ ዘጋቢው ትኩረቱ ሲጠፋ፣ መሣሪያው ወዲያውኑ የትኩረት መቀነስ መኖሩን የሚያሳይ ምልክት ሰጥቷል። ይህ ቴክኖሎጂ ከላቦራቶሪ ወጥቶ በስፋት ጥቅም ላይ መዋል ሲጀምር፣ በተለይ መንቀሳቀስ ለማይችሉ አካል ጉዳተኞችና የአዕምሮ ጤና ችግር ላለባቸው ሕሙማን ትልቅ የኑሮ ለውጥ ይዞ ይመጣል። ተመራማሪዎቹ በአሁኑ ወቅት ይህ "የሐሳብ ሪሞት" ለዕለት ተዕለት አገልግሎት አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን በትጋት እየሠሩ ይገኛሉ። ወደፊት መኪናችንን ለማሽከርከር ወይም የቤታችንን መብራት ለማብራት "ማሰብ" ብቻ በቂ የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ይህ የቻይናውያን እመርታ ፍንጭ ሰጥቷል። በመሐመድ ፊጣሞ @Tech_433et @Tech_433et

በሐሳብ ኃይል የሚታዘዘው የቻይናውያን ድንቅ ተሽከርካሪ ወንበር የሳይንስ ልብ ወለድ ፊልሞች እውን እየሆኑ ነው! በሐሳብ ብቻ የሚታዘዝ መሣሪያ በምናባችን ስንሥለው የኖርነው ቢሆንም፣ ቻይናውያን ተመራ
በሐሳብ ኃይል የሚታዘዘው የቻይናውያን ድንቅ ተሽከርካሪ ወንበር የሳይንስ ልብ ወለድ ፊልሞች እውን እየሆኑ ነው! በሐሳብ ብቻ የሚታዘዝ መሣሪያ በምናባችን ስንሥለው የኖርነው ቢሆንም፣ ቻይናውያን ተመራማሪዎች ግን ይህንን "የሳይንስ ተአምር" ወደ እውነት ቀይረውታል። በዠጂያንግ ዩኒቨርሲቲ የ"Brain-Machine Intelligence" ላቦራቶሪ ሳይንቲስቶች፣ የአዕምሮ ምልክቶችን (Brain signals) በቀጥታ ወደ ተግባር የሚቀይሩ የኤአይ (AI) አልጎሪዝሞችን በመጠቀም፣ በሐሳብ ብቻ የሚቆጣጠሩትን ኮምፒውተሮችና ተሽከርካሪ ወንበሮችን ይፋ አድርገዋል። "Brain-computer interface (BCI)" በተሰኘው በዚህ ዘርፍ፣ ተጠቃሚው በጭንቅላቱ ላይ የሚታሰር የኤሌክትሮኒክ መሣሪያ (EEG headband) ያደርጋል። ይህ መሣሪያ የአዕምሮን መረጃ የማንበብና ትዕዛዞችን የመቀበል ብቃት አለው። የቻይና ግሎባል ቴሌቪዥን (CGTN) ዘጋቢ በቦታው ተገኝቶ በሰጠው ማሳያ፣ ዘጋቢው ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጦ "ወደ ፊት ሂድ" ወይም "ወደ ጎን ታጠፍ" ብሎ ማሰብ ብቻ ነው የጠበቀበት፤ ወንበሩም ልክ እንደ ታዛዥ አገልጋይ የዘጋቢውን የሐሳብ ትዕዛዝ ተቀብሎ ጉዞውን ጀምሯል። የላቦራቶሪው ተመራማሪ ዋንግ ጂኳን እንደሚሉት፣ የመሣሪያው አስደናቂነት በዚህ ብቻ አያበቃም። መሣሪያው የአንድን ሰው የትኩረት ደረጃ መከታተል ይችላል። ለምሳሌ ዘጋቢው ትኩረቱ ሲጠፋ፣ መሣሪያው ወዲያውኑ የትኩረት መቀነስ መኖሩን የሚያሳይ ምልክት ሰጥቷል። ይህ ቴክኖሎጂ ከላቦራቶሪ ወጥቶ በስፋት ጥቅም ላይ መዋል ሲጀምር፣ በተለይ መንቀሳቀስ ለማይችሉ አካል ጉዳተኞችና የአዕምሮ ጤና ችግር ላለባቸው ሕሙማን ትልቅ የኑሮ ለውጥ ይዞ ይመጣል። ተመራማሪዎቹ በአሁኑ ወቅት ይህ "የሐሳብ ሪሞት" ለዕለት ተዕለት አገልግሎት አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን በትጋት እየሠሩ ይገኛሉ። ወደፊት መኪናችንን ለማሽከርከር ወይም የቤታችንን መብራት ለማብራት "ማሰብ" ብቻ በቂ የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ይህ የቻይናውያን እመርታ ፍንጭ ሰጥቷል። በመሐመድ ፊጣሞ @Tech_433et @Tech_433et

ማይክሮሶፍት ለዊንዶውስ ምርቶቹ ያወጣውን ማዘመኛ በመተግበር ራስዎን ከሳይበር ጥቃት ይጠብቁ ማይክሮሶፍት በመጋቢት ወር የሶፍትዌር ማሻሻያ መርሃ ግብሩ፣ ለዊንዶውስ ተጠቃሚዎች ለሳይበር ጥቃት አጋላጭ
ማይክሮሶፍት ለዊንዶውስ ምርቶቹ ያወጣውን ማዘመኛ በመተግበር ራስዎን ከሳይበር ጥቃት ይጠብቁ ማይክሮሶፍት በመጋቢት ወር የሶፍትዌር ማሻሻያ መርሃ ግብሩ፣ ለዊንዶውስ ተጠቃሚዎች ለሳይበር ጥቃት አጋላጭ ለሆኑ ክፍተቶች መፍትሔ የሚሰጡ 79 መጠገኛዎችን (Patches) ይፋ አድርጓል። ይህ የማሻሻያ እርምጃ በተለይ በስፋት ጥቅም ላይ በሚውሉ የዊንዶውስ ምርቶች ላይ የታዩ የደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ የታለመ ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች መረጃዎቻቸውን ከጥቃት ለመከላከልና የሥርዓታቸውን ደህንነት ለማረጋገጥ እነዚህን ዝመናዎች በአፋጣኝ እንዲጭኑ ተመክሯል። በዚህ ወር ማሻሻያ ከተደረገላቸው ክፍተቶች መካከል በዋናነት የሚጠቀሱት ሁለቱ ቀድመው ያልተለዩ የ"Zero-day" ተጋላጭነቶች ናቸው። የመጀመሪያው መረጃዎችን በሥርዓት ለመያዝ እና ለማስተዳደር በሚያገለግለው SQL Server ላይ የተገኘው ነው። ሁለተኛው ደግሞ የተለያዩ የሶፍትዌር ዓይነቶችን ለመሥራት የሚያገለግል ነጻ እና የጋራ የቴክኖሎጂ መድረክ በሆነው በ .NET ሶፍትዌር ላይ የተገኘ የአገልግሎት መቋረጥ (DoS) ስህተት ነው። ይህም የደህንነት መቆጣጠሪያ ወኪሎችን ለጊዜው በማሰናከል አጥቂዎች ሳይታወቁ ሥርዓቱ ውስጥ ዘልቀው እንዲገቡ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። ምንም እንኳ መጋቢት ወር "በጣም አደገኛ" (Critical) ተብለው የተመደቡት ሦስት ተጋላጭነቶች ብቻ ቢሆኑም፣ አብዛኞቹ ክፍተቶች ግን የመረጃ መንታፊዎች የሲስተሙን ሙሉ ቁጥጥር እንዲያገኙ መንገድ የሚከፍቱ መሆናቸው ታውቋል። የቀረበውን ማዘመኛ በመተግበር መረጃዎችዎ እንዳይሰረቁ እና የኮምፒውተርዎ ፍጥነት እንዳይቀንስ፣ ወደ Settings > Windows Update በመግባት "Check for updates" የሚለውን በመጫን የዚህን ወር አዳዲስ ዝመናዎች እንዲጭኑ ይመከራል። @Tech_433et @Tech_433et

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቻት ቦቶች ለታዳጊ ወጣቶች የደህንነት ስጋት እየሆኑ ነው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቻት ቦቶች (AI Chatbots) ታዳጊ ወጣቶች የጥቃት ድርጊቶችን እንዲያቅዱ እና ራሳቸውን እ
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቻት ቦቶች ለታዳጊ ወጣቶች የደህንነት ስጋት እየሆኑ ነው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቻት ቦቶች (AI Chatbots) ታዳጊ ወጣቶች የጥቃት ድርጊቶችን እንዲያቅዱ እና ራሳቸውን እንዲጎዱ የሚያበረታቱ መረጃዎችን እየሰጡ መሆኑን የሲኤንኤን (CNN) የምርመራ ዘገባ አጋለጠ። ተመራማሪዎች እንደ ታዳጊ ወጣቶች በመምሰል ባደረጉት ሙከራ፣ ታዋቂ የሆኑ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቻትቦቶች የጥቃት ድርጊቶችን ለማቀድ፣ ራስን የመጉዳት ሃሳቦችን ለማበረታታት እና አደገኛ ድርጊቶችን ለመፈጸም የሚያስችሉ ዝርዝር መመሪያዎችን እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል። ምንም እንኳን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኩባንያዎች የደህንነት መጠበቂያዎች አሉን ቢሉም፣ ታዳጊዎቹ ጥያቄዎቻቸውን በሌላ መንገድ ሲያቀርቡ ቻት ቦቶቹ በቀላሉ ጥንቃቄ የጎደለው ምላሽ እንደሚሰጡም ታይቷል። ቻትቦቶቹ ከሰዎች ጋር የሚቀራረብ ስሜት ስለሚፈጥሩ፣ በተለይ ስሜታቸው በቀላሉ የሚነካ ታዳጊዎች ከእነዚህ ሮቦቶች ጋር ጥልቅ የሆነ ግንኙነት እንዲመሰርቱ ያደርጋቸዋል። ይህ ደግሞ ቻትቦቶቹ የሚሰጡትን የተሳሳተ ምክር እንደ እውነት እንዲቀበሉ የሚያደርግ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ በጥናቱ ወቅት ቻትቦቶቹ በትምህርት ቤት ውስጥ ጥቃት ለመፈጸም የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል እና የጥቃት ስልቶችን በተመለከተ መረጃዎችን ሲያጋሩ ተስተውለዋል። የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቹ የደህንነት ስርዓታቸውን ለማሻሻል እየሰሩ መሆኑን ቢገልጹም፣ ተቺዎች ግን ትርፍን ከደህንነት በማስቀደማቸው ለወጣቶች ህይወት አደጋ እየፈጠሩ ነው ይላሉ። በመሆኑም የታዳጊዎች የኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ እንዲኖር፣ ወላጆች ልጆቻቸው ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎች ጋር የሚያደርጉትን ግንኙነት በቅርበት እንዲከታተሉ እና የሚመለከታቸው አካላት በቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ማሳሳቡን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡ በማህሌት ብዙነህ @Tech_433et @Tech_433et

ጎግል አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና ሶማሊኛን ጨምሮ 13 የአፍሪካ ቋንቋዎችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የፍለጋ አገልግሎቱ ውስጥ አካተተ ጎግል (Google) በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial
ጎግል አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና ሶማሊኛን ጨምሮ 13 የአፍሪካ ቋንቋዎችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የፍለጋ አገልግሎቱ ውስጥ አካተተ ጎግል (Google) በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial Intelligence - AI) የተደገፈ የፍለጋ አገልግሎቱን ለማሻሻል 13 የአፍሪካ ቋንቋዎችን እንዲደግፍ ማስፋፋቱን አስታወቀ። ከእነዚህ ቋንቋዎች መካከል አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ፣ ሃውሳ፣ ኪንያርዋንዳ፣ ኪስዋሂሊ እና ሌሎች ቋንቋዎች ተካትተዋል። ይህ እርምጃ በአፍሪካ ውስጥ ለሚገኙ ብዙ ተጠቃሚዎች በራሳቸው ቋንቋ መረጃ ለመፈለግ እና ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር በቀላሉ ለመገናኘት እድል ይፈጥራል። የጎግል አዲሱ ባህሪ የሆነው ኤ አይ ምልከታ (AI Overviews) ተጠቃሚዎች ሲፈልጉ በአጭር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተፈጠረ ማጠቃለያ መረጃ እንዲያገኙ ያስችላል፤ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሞድ (AI Mode) ደግሞ በጽሁፍ፣ በድምፅ ወይም በምስል ተጠቅመው ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዲመርመሩ ያግዛል። ይህ ዕድገት የአፍሪካ ቋንቋዎች በዲጂታል መድረኮች ውስጥ ያላቸውን ተወካይነት ለማሳደግ እና ተጠቃሚዎች በራሳቸው ቋንቋ ቴክኖሎጂን እንዲጠቀሙ የሚያበረታታ እንደሆነ ተገልጿል። @Tech_433et @Tech_433et

የቴሌግራም አካውንታቹ ሀክ እንዳትደረግ ምን አይነት እርምጃ መውሰድ አለባቹ? . የ አንድ ደቂቃ ቪዲዮ ዩትዩብ ገፃችን ላይ ለቀናል ይመልከቱና ሴቲንግ ውስጥ በመግባት ያስተካክሉ 👇 በዛውም የዩትዩብ
የቴሌግራም አካውንታቹ ሀክ እንዳትደረግ ምን አይነት እርምጃ መውሰድ አለባቹ? . የ አንድ ደቂቃ ቪዲዮ ዩትዩብ ገፃችን ላይ ለቀናል ይመልከቱና ሴቲንግ ውስጥ በመግባት ያስተካክሉ 👇 በዛውም የዩትዩብ ገፃችንን Subscribe ማድረግ አይረሳ❤️ https://youtu.be/pxLED2AzMjM?si=7OB8LQS4-uTmD6_i

ቢሮ 121 ፡ ናሳን ለሶስት ወራት ሀክ ያደረገው የሰሜን ኮሪያ የሳይበር ተቋም... በሳምንታዊ የ 4-3-3 Tech የዩትዩብ ፕሮግራማችን ይመልከቱ 👇👇 የዩትዩብ ቻናላችንንም Subscribe በማድ
ቢሮ 121 ፡ ናሳን ለሶስት ወራት ሀክ ያደረገው የሰሜን ኮሪያ የሳይበር ተቋም... በሳምንታዊ የ 4-3-3 Tech የዩትዩብ ፕሮግራማችን ይመልከቱ 👇👇 የዩትዩብ ቻናላችንንም Subscribe በማድረግ አብሮነታቹን አሳዩን ❤️ https://youtu.be/kkgrlakdU-A

የእስራኤሉ የሳይበር ጥቃት እስራኤል ከአምስት ሚሊዮን በላይ ኢራናውያን የሚጠቀሙበትን BadeSaba የተሰኘ የሶላት ጥሪ መተግበሪያ በመጥለፍ፣ ለኢራን ወታደሮች መልዕክቶችን መላኳን ዎል ስትሪት ጆርና
+1
የእስራኤሉ የሳይበር ጥቃት እስራኤል ከአምስት ሚሊዮን በላይ ኢራናውያን የሚጠቀሙበትን BadeSaba የተሰኘ የሶላት ጥሪ መተግበሪያ በመጥለፍ፣ ለኢራን ወታደሮች መልዕክቶችን መላኳን ዎል ስትሪት ጆርናል ዘግቧል። በፋርስ ቋንቋ የተላኩት መልዕክቶች፣ ወታደሮች መሣሪያቸውን እንዲያወርዱ እና አገዛዙን እንዲከዱ የሚቀሰቅሱ ናቸው ተብሏል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢራን ይፋዊ የዜና ወኪል (IRNA) ድረ-ገጽም ተጠልፎ በአገዛዙ ላይ የሚቀሰቅሱ መፈክሮች ሲተላለፉበት ውሏል።Tikvah @Tech_433et @Tech_433et

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ ጋር ተያይዞ በዋትስአፕ መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት እየተፈጸም ነው ሲል አስጠነቀቀ 🎯 የጥቃት ዘመቻው በተለይ ከፍተኛ የመንግሥት
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ ጋር ተያይዞ በዋትስአፕ መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት እየተፈጸም ነው ሲል አስጠነቀቀ 🎯 የጥቃት ዘመቻው በተለይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን፣ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ተማሪዎችን፣ በበይነመረብ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ግለሰቦችን እና ታዋቂ ሰዎችን ኢላማ ያደረገ በመሆኑ ማኅበረሱ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡ ⚠️ የመረጃ መንታፊዎቹ፣ የፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊ በመምሰልና የፓርቲዎችን አርማ በመጠቀም፣ “ይህንን ሊንክ በመጫን ለፓርቲያችን ያለዎትን ድጋፍ ይግለጹ” ወይም “የምርጫ ቅስቀሳ ቡድናችንን ይቀላቀሉ” የሚሉ አሳሳች መልዕክቶችን በመላክ የግለሰቦችን አካውንት እንደሚጠልፉ አስተዳደሩ በማሳያነት ጠቅሷል። 👉 አስተዳደሩ ኅብረተሰቡ ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫን እንዲጠቀም፣ የማረጋገጫ ኮዶችን በማንኛውም ሁኔታ ለማንም አሳልፎ ከመስጠት እንዲቆጠብ፣ አጠራጣሪ ሊንኮችን ከመንካት እንዲታቀብ እና የገንዘብ ጥያቄዎች ሲቀርቡ በቀጥታ ስልክ በመደወል እንዲያረጋግጥ መክሯል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያ @Tech_433et @Tech_433et

የጃፓን ተመራማሪዎች በሰውሰራሽ አስተውሎት የሚደገፍ የሮቦት መነኩሴ ሰርተው ዛሬ ይፋ አደረጉ። የሮቦት መነኩሴው መንፈሳዊ የምክር አገልግሎቶች የሚሰጥ ነው ብለዋል። የክዮቶ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች እ
የጃፓን ተመራማሪዎች በሰውሰራሽ አስተውሎት የሚደገፍ የሮቦት መነኩሴ ሰርተው ዛሬ ይፋ አደረጉ። የሮቦት መነኩሴው መንፈሳዊ የምክር አገልግሎቶች የሚሰጥ ነው ብለዋል። የክዮቶ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች እንዳሉት ሮቦቱ ሰዎች ከሌሎች ጋር ሊጋሩአቸው የሚቆጠቡባቸው ጥንቃቄ የሚፈልጉ ሐይማኖታዊ ጥያቄዎችን መመለስ ይችላል ነው ያሉት። እንዲያም ሲል «ምናልባት አንድ ቀን በመሰኩ የሰው ሐይል እጥረት ሲኖር ሊያቃልል ይችላል» ማለታቸውን የዘገበው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ነው። @Tech_433et @Tech_433et

መሬት በድንገት መሽከርከር ብታቆም ምን ሊፈጠር ይችላል? ****** መሬት ያለ እረፍት በደቂቃ 27.7 ኪሎ ሜትር (በሰዓት ከ1,600 ኪሎ ሜትር በላይ) በራሷ ዛቢያ ላይ ትሽከረከራለች። እስቲ አስቡ
መሬት በድንገት መሽከርከር ብታቆም ምን ሊፈጠር ይችላል? ****** መሬት ያለ እረፍት በደቂቃ 27.7 ኪሎ ሜትር (በሰዓት ከ1,600 ኪሎ ሜትር በላይ) በራሷ ዛቢያ ላይ ትሽከረከራለች። እስቲ አስቡት፤ ይህን ያህል ፍጥነት እያላት በድንገት "ቆም" ብትል ምን ሊፈጠር ይችላል? ውጤቱ አስከፊና ምናባዊ ከሚመስል አደጋ በላይ ነው። ልክ በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዘ ያለ መኪና ድንገት ፍሬን ሲይዝ በውስጡ ያለ ሰው ወደ ፊት እንደሚወረወረው ሁሉ፣ መሬትም በድንገት ብትቆም በላዩዋ ላይ ያለን እኛ ሰዎች፣ ቤቶች፣ ተሽከርካሪዎች እና ተራራዎች ጭምር በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ምስራቅ አቅጣጫ እንወረወራለን። መሬት ወደ ምስራቅ እየተጓዘች በመሆኑ፣ እርሷ ብትቆምም እኛ ግን በነበረን ፍጥነት ጉዟችንን ስለምንቀጥል ከመሬት አካል ላይ ተፈንጥረን እንወጣለን። አደጋው በዚህ ብቻ አያበቃም፤ የውቅያኖስ ውሃዎች ሁሉ ካሉበት ተነቅለው ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ግዙፍ ማዕበልና ሱናሚ ምድርን ያጥለቀልቋታል። መሬት ለአንድ ዓመት መሽከርከር ብታቆም ደግሞ ወቅቶችና የሌሊትና ቀን ዑደት ይናጋል። ለስድስት ወራት ያህል በአንድ በኩል ያለው የምድር ክፍል የፀሐይ ንዳድ ውስጥ ስለሚቆይ ይቃጠላል፤ ቀሪው ስድስት ወር ደግሞ በሌላኛው በኩል ድቅድቅ ጨለማና የማይቻል ቅዝቃዜ (በረዶ) ይነግሳል። መሬት ያለ እረፍትና በጥንቃቄ መሽከርከሯ ለእኛ ለሰው ልጆች ህልውና የተሰጠ ትልቅ ስጦታ መሆኑን የሳይንስ መረጃዎች ይጠቁማሉ። አበባየሁ ከፈኒ @Tech_433et @Tech_433et

ጎግል የክሮም ተጠቃሚዎች ብሮውዘራቸውን በአፋጣኝ እንዲያዘምኑ አሳሰበ ጎግል በክሮም ብሮውዘር ላይ የተገኘን እጅግ አደገኛ የሆነ የጥቃት ተጋላጭነት ለመጠገን አስቸኳይ የደህንነት ማሻሻያ ማውጣቱን አስ
ጎግል የክሮም ተጠቃሚዎች ብሮውዘራቸውን በአፋጣኝ እንዲያዘምኑ አሳሰበ ጎግል በክሮም ብሮውዘር ላይ የተገኘን እጅግ አደገኛ የሆነ የጥቃት ተጋላጭነት ለመጠገን አስቸኳይ የደህንነት ማሻሻያ ማውጣቱን አስታወቀ። ይህ የጥቃት ተጋላጭነት CVE-2026-2441 ተብሎ የተሰየመ ሲሆን፣ በጎርጎሮሳውያኑ 2026 ዓ.ም ክፍተት መሙያ የተደረገለት የመጀመሪያው ከፍተኛ የጥቃት ተጋላጭነት ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ የጥቃት ተጋላጭነት ክፍተት "Use-after-free" በሚባል የስህተት ዓይነት የተፈጠረ ነው። የመረጃ መንታፊዎች (Hackers) ይህንን ክፍተት በመጠቀም የብሮውዘሩን ሲስተም ማሰናከል፣ መረጃዎችን መስረቅ ወይም ሌሎች ያልተፈለጉ ትዕዛዞችን በኮምፒውተራችሁ ላይ ማከናወን እንደሚችሉ ጎግል ገልጿል። ከዚህ ባለፈም፣ ጎግል እንዳረጋገጠው ይህንን ክፍተት በመጠቀም ጥቃት የሚያደርሱ አካላት በአሁኑ ወቅት በስፋት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ብሏል። በመሆኑም ተጠቃሚዎች ጥቃቱን ለመከላከል ጎግል የለቀቃቸውን የሚከተሉትን የክሮም ብሮውዘር ስሪቶች Versions እንዲጠቀሙ ይመከራል፦ 👉ለዊንዶውስ Windows) እና ለማክ macOS ተጠቃሚዎች፦ 145.0.7632.75/76 👉ለሊኑክስ Linux ተጠቃሚዎች፦ 144.0.7559.75 ዝማኔውን Update እንዴት መተግበር ይቻላል? 1. በክሮም ብሮውዘርዎ ላይ በቀኝ በኩል ያሉትን ሦስት ነጥቦች ይጫኑ። 2. Help የሚለውን መርጠው About_Google_Chrome የሚለውን ይጫኑ። 3. ብሮውዘሩ አዲስ ዝማኔ ካለ በራሱ ይፈልጋል፤ ፍለጋውን እንደጨረሰም Relaunch የሚለውን በመጫን ብሮውዘሩን እንደገና ያስጀምሩት። @Tech_433et @Tech_433et

ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት 27,773 የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝሮባታል – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አገሪቱ ከተሰነዘሩባት ጥቃቶች 99 በመቶ (27,505) የሚሆኑን በተሳካ ሁኔታ
ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት 27,773 የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝሮባታል – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አገሪቱ ከተሰነዘሩባት ጥቃቶች 99 በመቶ (27,505) የሚሆኑን በተሳካ ሁኔታ ማምከኗን አስተዳደሩ በግማሽ ዓመት ሪፖርቱ ላይ ገልጿል፡፡ ወደ ቢገቡ የሀገርን ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ 196 የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ማድረግ መቻሉንም ገልጿል፡፡ አስተዳደሩ ከቀረቡለት 253 የፎረንሲክ የምርመራ ጥያቄዎች መካከል ለ245ቱ ለ96.8 በመቶ ምላሽ ሰጥቷል። በተጨማሪም ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ሕሊና ግንባታ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ የዋለ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ለ14 ተቋማት የሳይበር ደህንነት መፍትሔዎችና የቴክኒክ ድጋፍ መስጠቱንም አስተዳደሩ በማኅበራዊ የትስስር ገፁ ላይ አስነብቧል። @Tech_433et @Tech_433et

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተፈጠሩት መንትዮች ብዙዎችን እያነጋገሩ ነው በቅርብ ጊዜ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ቫለሪያ እና ካሚላ በሚል ስም የሚጠሩ መንትዮች ታሪክ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። መን
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተፈጠሩት መንትዮች ብዙዎችን እያነጋገሩ ነው በቅርብ ጊዜ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ቫለሪያ እና ካሚላ በሚል ስም የሚጠሩ መንትዮች ታሪክ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። መንትዮቹ በአካል ተጣብቀው የተወለዱ (Conjoined twins) መሆናቸውንና በሚያሚ አሜሪካ እንደሚኖሩ ቢገልጹም፣ ነገሩ ግን ጉዳዩ ከእውነት የራቀ መሆኑ ታውቋል። ተጣብቀው የተወለዱ መንትዮች በመምሰል በተፈጠረው የማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ ተከታዮችን ማፍራት የቻሉ ሲሆን፣ ምስሎቻቸውም እጅግ እውነተኛ ሰዎች ይመስሉ እንደነበር ተመላክቷል። የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እንደገለፁት እነዚህ መንትያዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተፈጠሩ እንጂ እውነተኛ ሰዎች አይደሉም። በምስሎቻቸው ላይ የሚታዩ አንዳንድ ጥቃቅን ስህተቶች እንደ ጣቶች ቁጥር እና የጀርባ ገጽታዎች ይህንኑ እንደሚያረጋግጡ ተጠቅሷል። መንትያዎቹ "እውነተኛ ሰዎች ነን" በማለት ቢከራከሩም፣ ብዙዎች የሰዎችን የአካል ጉዳት ለንግድ ማስታወቂያነት መጠቀም ተገቢ አይደለም በማለት እየተቹዋቸው ይገኛሉ። የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ምን ያህል እውነትንና የውሸት ይዘትን መለየት እስከሚያቅተን ድረስ እየረቀቀ መምጣቱን የሚያሳይ ትልቅ ምሳሌ ሆኗል ነው የተባለው። በሜሮን ንብረት @Tech_433et @Tech_433et

ቻይና የመጀመሪያውን በረራ ላይ የቀዶ ጥገና ሕክምና የሚሰጥ አውሮፕላን ሥራ አስጀመረች ******** የቴክኖሎጂው ጥግ እና የሕክምናው ዘርፍ ተቀናጅተው አዲስ ታሪክ ተፅፏል፤ ቻይና የመጀመሪያው የሆነ
ቻይና የመጀመሪያውን በረራ ላይ የቀዶ ጥገና ሕክምና የሚሰጥ አውሮፕላን ሥራ አስጀመረች ******** የቴክኖሎጂው ጥግ እና የሕክምናው ዘርፍ ተቀናጅተው አዲስ ታሪክ ተፅፏል፤ ቻይና የመጀመሪያው የሆነውን እና የሕክምና ተቋም የሥራ ፈቃድ ያገኘውን "የአውሮፕላን ሆስፒታል" በይፋ ወደ ሥራ ማስገባቷን አስታውቃለች። ይህ ሆስፒታል በተለይ የፊት ገፅ እና የጭንቅላት አካላት (እንደ አይን፣ ጆሮ እና አፍንጫ) ሕክምና ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፣ የተገነባውም ቻይና በራሷ ቴክኖሎጂ ባመረተችው C909 በተባለ መካከለኛ ርቀት ተጓዥ የመንገደኞች አውሮፕላን ላይ ነው። አውሮፕላኑ እንደ አስፈላጊነቱ በፈጣን ሁኔታ ወደ ሕክምና መስጫነት የሚቀየሩ የመለዋወጫ ክፍሎች (Modular setup) ያሉት ሲሆን፣ በውስጡም የሞባይል ክሊኒክ፣ አጠቃላይ የላቦራቶሪ ምርመራ ክፍል፣ ለቀዶ ጥገና ዝግጅት የሚሆን ስፍራ እና ሙሉ የቀዶ ጥገና ማከናወኛ ክፍልን (Surgical zone) አካትቷል። ይህ በቴክኖሎጂ የተራቀቀ የአየር ላይ ሆስፒታል በውስጡ የያዛቸው የሕክምና መሣሪያዎች በሙሉ በቻይና ሀገር ውስጥ የተመረቱና እጅግ ጥቃቅን የሆኑ የሕክምና ስራዎችን የሚሰሩ መሆናቸው ተገልጿል። በአውሮፓውያኑ መስከረም 2025 የመጀመሪያ በረራውን ወደ ሰሜን ምዕራብ ቻይና በማድረግ ምርመራዎችን ብቻ ሲሰጥ የነበረው ይህ አውሮፕላን፣ አሁን ላይ አቅሙን በማሳደግ በበረራ ላይ እያለ የቀዶ ጥገና ሕክምናዎችን የማከናወን ሙሉ ብቃት አግኝቷል። በያዝነው የ2026 የአውሮፓውያኑ ዓመት ደግሞ አገልግሎቱን ይበልጥ በማስፋት፣ የ"ቤልት ኤንድ ሮድ" (Belt and Road) አጋር ለሆኑና የሕክምና አገልግሎት እጥረት ባለባቸው ሀገራት በበጎ ፈቃድ ተልዕኮ ተደራሽ ለመሆን አቅዷል። ይህ የፈጠራ ስራ የሕክምና አገልግሎትን በመልክዓምድራዊ መሰናክሎች ሳይገደብ በየትኛውም ስፍራ ተደራሽ ለማድረግ የሚቻልበትን አዲስ የቴክኖሎጂ በር ከፍቷል።(EBC) @Tech_433et @Tech_433et

⛔አሁኑኑ የማይክሮሶፍት ኦፊስ ምርትዎን ያዘምኑ በማይክሮሶፍት ኦፊስ ላይ የተከሰተ አደገኛ የደህንነት ክፍተት ጥቃት እያደረሰ መሆኑ ተረጋግጧል። ማይክሮሶፍት ኩባንያ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ፣ በማይክ
⛔አሁኑኑ የማይክሮሶፍት ኦፊስ ምርትዎን ያዘምኑ በማይክሮሶፍት ኦፊስ ላይ የተከሰተ አደገኛ የደህንነት ክፍተት ጥቃት እያደረሰ መሆኑ ተረጋግጧል። ማይክሮሶፍት ኩባንያ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ፣ በማይክሮሶፍት ኦፊስ Microsoft_Office መተግበሪያዎች ላይ አዲስ እና አደገኛ የሳይበር ደህንነት ክፍተት መገኘቱንና ጥቃት ለማድረስ እየዋለ መሆኑን አስታውቋል። CVE-2026-21509 ተብሎ የተሰየመው ይህ ቀድሞ ያልተለየ የደህንነት ክፍተት፣ የደህንነት ስጋት መጠኑ በከፍተኛ ደረጃ (High-severity) የተመደበ ሲሆን፣ ከ10 ነጥብ የ7.8 የአደገኝነት ደረጃ ተሰጥቶታል። ይህ ክፍተት የመረጃ ጠላፊዎች የማይክሮሶፍት ኦፊስ የደህንነት መከላከያዎችን በመጣስ የተጠቃሚዎችን ኮምፒውተር እንዲቆጣጠሩ ወይም ምስጢራዊ መረጃዎችን እንዲሰርቁ መንገድ የሚከፍት መሆኑ ተገልቋል። እንደ ማይክሮሶፍት መግለጫ፣ ጥቃቱ የሚፈጸመው አጥፊዎች "በቫይረስ የተበከለ" የኦፊስ ፋይል (Malicious Office file) ለተጠቃሚዎች በመላክ እና ተጠቃሚው ፋይሉን እንዲከፍተው በማታለል የሚፈጸም መሆኑ ታዉቋል። ይህ በቫይረስ የተበከለዉ ፋይል አንዴ ከተከፈተ በኋላ በኦፊስ መተግበሪያዎች ውስጥ የሚገኘውን የደህንነት መከላከያ (OLE/COM mitigations) በማለፍ ጥቃቱን በስኬት ያከናውናል ተብሏል። ይህ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት የሚከተሉትን የማይክሮሶፍት ኦፊስ አይነቶች እንደሚነካ ታውቋል፦ 👉ማይክሮሶፍት ኦፊስ 2016 እና 2019 (Microsoft Office 2016 & 2019) 👉ኦፊስ LTSC 2021 እና LTSC 2024 👉ማይክሮሶፍት 365 አፕሊኬሽኖች (Microsoft 365 Apps for Enterprise) @Tech_433et @Tech_433et

ሳይንቲስቶች ሙሉ በሙሉ የሚበላ ባትሪ ሰሩ በሕክምናው ዓለም አዲስ ተስፋ የፈነጠቀና ሙሉ በሙሉ ከምግብ ግብዓቶች የተሰራ ባትሪ በጣሊያን የቴክኖሎጂ ተቋም (IIT) ተመራማሪዎች ይፋ ተደርጎል። ይህ ባ
+1
ሳይንቲስቶች ሙሉ በሙሉ የሚበላ ባትሪ ሰሊ በሕክምናው ዓለም አዲስ ተስፋ የፈነጠቀና ሙሉ በሙሉ ከምግብ ግብዓቶች የተሰራ ባትሪ በጣሊያን የቴክኖሎጂ ተቋም (IIT) ተመራማሪዎች ይፋ ተደርጎል። ይህ ባትሪ በሰውነታችን ውስጥ ገብተው ምርመራ ለሚያካሂዱ ጥቃቅን መሣሪያዎች የኃይል ምንጭ እንዲሆን ተደርጎ የተሰራ ነው። ባትሪው የተሰራው በየቀኑ ከምንመገባቸው ምግቦች ውስጥ በሚገኙ ንጥረ ነገሮች ሲሆን  ለምሳሌ የኤሌክትሪክ ፍሰቱን ለመጀመር ቫይታሚን B2፣ ለኤሌክትሪክ መተላለፊያነት ደግሞ የባህር አረም (Nori) እና የምግብ ወርቅ (Gold leaf) ጥቅም ላይ ውለዋል። ባትሪው በሰውነታችን ውስጥ በሚገኙ አሲዶችና ፈሳሾች ቢሟሟም፣ ንጥረ ነገሮቹ ከምግብ የተገኙ በመሆናቸው በጤና ላይ ምንም ዓይነት መርዛማነት ወይም የጎንዮሽ ጉዳት አያስከትልም ሲሉም የፈጠራው ባለቤቶች ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የተሰራው ሞዴል 0.65 ቮልት ኃይል የሚያመነጭ ሲሆን፣ ይህ ኃይል ጥቃቅን ሴንሰሮችንና ካሜራዎችን ለተወሰነ ሰዓት ለማንቀሳቀስ በቂ  ሀይል አለው ተብሏል። ይህ ግኝት በተለይ ሕፃናት በስህተት ባትሪ ውጠው ለሚደርስባቸው አደጋ መፍትሄ ከመሆኑም በላይ፣ ወደፊት በጨጓራና አንጀት ውስጥ የሚደረጉ የሕክምና ምርመራዎችን እጅግ ቀላልና አስተማማኝ እንደሚያደርጋቸው ተገልጿል ሲል CNN Tech ዘግቧል። ሀና ሰይፉ @Tech_433et @Tech_433et

አየገባችሁ ሁላችሁም ( Follow ) አርጉ በ TikTok በቅርቡ በተለያዩ በ Tech መረጃዎች እንገናኛለን ( እስከዛ ሁላችሁም ከታች ባለዉ Link እየገባችሁ የ TikTok አካዉንታችንን Follo
አየገባችሁ ሁላችሁም ( Follow ) አርጉ በ TikTok በቅርቡ በተለያዩ በ Tech መረጃዎች እንገናኛለን ( እስከዛ ሁላችሁም ከታች ባለዉ Link እየገባችሁ የ TikTok አካዉንታችንን Follow አርጉ። ◼️ 𝐅𝐎𝐋𝐋𝐎𝐖 : https://vm.tiktok.com/ZMHofxRcYUXyq-unsbi/ 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄 @Tech_433et 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄 @Tech_433et

𝐀𝐋𝐈𝐆𝐇𝐓𝐌𝐎𝐓𝐈𝐎𝐍 𝐌𝐎𝐃 ( 𝐀𝐏𝐊 ) 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄 @Tech_433et 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄 @Tech_433et

እጅግ ልብ ሰባሪ ዜና 💔 ተወዳጁ የኪነ ጥበብ ባለሙያ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ከዚህ አለም በሞት ተለየ 😭💔 ለረጅም አመታት በፊልሙ አለም እና በቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በሀገራችን ዝናን ያተረፈው
እጅግ ልብ ሰባሪ ዜና 💔 ተወዳጁ የኪነ ጥበብ ባለሙያ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ከዚህ አለም በሞት ተለየ 😭💔 ለረጅም አመታት በፊልሙ አለም እና በቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በሀገራችን ዝናን ያተረፈው ነፃነት ወርቅነህ በዛሬው እለት ባደረበት ህመም ከዚህ አለም ተለይቷል የባለ ብዙ ዘርፍ ባለሙያው ነፃነት ወርቅነህ የባለትዳር እና የ3 ልጆች አባት ነበር💔💔 ለነፃነት ወርቅነህ ቤተሰቦች እና ለመላው ኢትዮጵያውያን ወዳጆቹ 4-3-3 ስፖርት መፅናናቱን ይመኛል 😔😔😔 @Bisrat_sport_433et @Bisrat_sport_433et