en
Feedback
4-3-3 Tech

4-3-3 Tech

Open in Telegram

Welcome to 4-3-3 Tech On this channel, you will find everything from the latest tech updates to helpful app reviews and powerful web tools.

Show more
4 033
Subscribers
+1724 hours
+5987 days
+53630 days
Posts Archive
አይ.ቢ.ኤም የሶፍትዌር ማበልጸጊያ ወጪዎችን ለመቆጣጠር ቦብ (Bob) የተሰኘ የኤ.አይ ፕላትፎርም ይፋ አደረገ፡፡ አይ.ቢ.ኤም (IBM) የሶፍትዌር ልማት ወጪዎችን ለመቆጣጠር እና ደህንነትን ለማረጋገ
አይ.ቢ.ኤም የሶፍትዌር ማበልጸጊያ ወጪዎችን ለመቆጣጠር ቦብ (Bob) የተሰኘ የኤ.አይ ፕላትፎርም ይፋ አደረገ፡፡ አይ.ቢ.ኤም (IBM) የሶፍትዌር ልማት ወጪዎችን ለመቆጣጠር እና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል 'ቦብ' የተባለ አዲስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፕላትፎርም አስተዋውቋል። ይህ የኤ.አይ ፕላትፎርም ኩባንያዎች የኤ.አይ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ሶፍትዌር ሲያበለጽጉ (ኮድ ሲጽፉ) ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የጥራት፣ የደህንነት እና የቁጥጥር ችግሮችን ለመፍታት ታስቦ የተሰራ ነው። 'ቦብ' የሲስተሞቹን ትስስር አስቀድሞ በመለየት ይህንን ውስብስብ ስራ ያቃልላል፤ እንዲሁም ኩባንያዎች የደህንነት ስጋት ሳይገባቸው በፍጥነት እንዲሰሩ ያስችላል። ፕላትፎርሙ ኤ.አይ የሚያመነጫቸው ኮዶች ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት የደህንነት ክፍተቶች እና ስህተቶች እንዳይኖሩት ቀጥታ ቁጥጥር ያደርጋል። እያንዳንዱን የተሰራ ስራ እና ውሳኔም ለኦዲት በሚመች መልኩ ይመዘግባል። በአሁኑ ወቅት ከ80 ሺህ በላይ የአይ.ቢ.ኤም ሰራተኞች ፕላትፎርሙን እየተጠቀሙት ሲሆን፤ በአማካይ የ45 ፐርሰንት የምርታማነት እድገት አስመዝግበዋል። በአንዳንድ ውስብስብ ስራዎች ላይም እስከ 70 ፐርሰንት ጊዜ መቆጠብ አስችሏል። አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኒውስ እንደዘገበው በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱ በሶፍትዌር መልክ የቀረበ ሲሆን የ30 ቀናት ነፃ የሙከራ ጊዜ አለው። ጥብቅ የዳታ ህግ ላለባቸው ተቋማት ደግሞ በቅርቡ በክፍያ ይቀርባል። @Tech_433et @Tech_433et

ኦፕን ኤ.አይ አዲስ የምስል ማመንጫ ሞዴል ይፋ አደረገ ኦፕን ኤ.አይ ኢሜጅስ 2.0 (Images 2.0) የተሰኘ ምስሎችን ከጽሑፍ ጋር አቀናጅቶ መፍጠር የሚችል አዲስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሞዴል
ኦፕን ኤ.አይ አዲስ የምስል ማመንጫ ሞዴል ይፋ አደረገ ኦፕን ኤ.አይ ኢሜጅስ 2.0 (Images 2.0) የተሰኘ ምስሎችን ከጽሑፍ ጋር አቀናጅቶ መፍጠር የሚችል አዲስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሞዴል ይፋ አደረገ። ቀደም ሲል የነበሩ ሞዴሎች በምስል ላይ ጽሑፎችን ሲጽፉ ይሳሳቱ የነበረ ቢሆንም አዲሱ መተግበሪያ ግን ጽሑፎችን ያለስህተት ማመንጨት እንደሚችል ተገልጿል፡፡ ኢሜጅስ 2.0 ድረ-ገጾችን የመፈለግ፣ ከአንድ ትዕዛዝ የተለያዩ ምስሎችን የመፍጠር እና የፈጠራ ውጤቶቹን በድጋሚ የመፈተሽ ችሎታ የሚሰጠው የማሰላሰል አቅም እንዳለው ኩባንያው ገልጿል፡፡ ሞዴሉ እንደ ጃፓንኛ፣ ኮሪያኛ፣ ሂንዲ እና ቤንጋሊ ባሉ የላቲን ባልሆኑ ጽሑፎች አጻጻፍ ላይ ጠንካራ ግንዛቤ እንዳለው ተነግሯል። ኢሜጅስ 2.0 በምስል ፈጠራ ረገድ ዝርዝር ነገሮችን የማገናዘብ እና ጥራት ያላቸውን ምስሎች የማምጣት አቅም መያዙን ኦፕን ኤ.አይ አስታውቋል። ሞዴሉ ውስብስብ የሆኑ ምስሎችን በሀሳብ ደረጃ ከመቅረጽ ባለፈ ውጤታማ በሆነ መንገድ በመተርጎም እና መመሪያዎችን በመከተል እስከ 2K ጥራት ያላቸውን ምስሎች ማመንጨት እንደሚችል የቴክ ክራንች ዘገባ ያመለክታል፡፡ @Tech_433et @Tech_433et

በሳይበር ደህንነት ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ላይ እስከ 10 ዓመት የሚደርስ የጽኑ እስራት ቅጣትን የያዘ አዋጅ ለፓርላማ ሊቀርብ ነው የቁልፍ መሰረተ ልማት አገልግሎት “እንዲቋረጥ”፣ “እንዲስተጓጎል”፣
በሳይበር ደህንነት ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ላይ እስከ 10 ዓመት የሚደርስ የጽኑ እስራት ቅጣትን የያዘ አዋጅ ለፓርላማ ሊቀርብ ነው የቁልፍ መሰረተ ልማት አገልግሎት “እንዲቋረጥ”፣ “እንዲስተጓጎል”፣ “ተዓማኒነቱን እንዲያጣ” ወይም “ሚስጥራዊነቱ እንዲጋለጥ” የሚያደርግ ወንጀል “ሆን ብሎ” እንዲፈጸም ያደረገ የሳይበር ደህንነት ኃላፊ ወይም ሰራተኛ፤ ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የሚያደርግ የአዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ሊቀርብ ነው። ይኸው አዋጅ በቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚያጋጥሙ የሳይበር ደህንነት ክስተቶችን ለብሔራዊ ድንገተኛ የኮምፒውተር አደጋ ምላሽ መስጫ ማዕከል በ48 ሰዓታት ውስጥ ባላሳወቁ ባለቤቶች ላይ እስከ 2 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የአስተዳደራዊ መቀጮ ጥሏል። ይህን የወንጀል ተጠያቂነት እና አስተዳደራዊ እርምጃ የያዘው የህግ ረቂቅ፤ “የቁልፍ መሰረት ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ” የሚል ስያሜ የያዘ ነው። በኢንፎርሜሽን እና መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) የተዘጋጀው ይህ ረቂቅ አዋጅ፤ ነገ ማክሰኞ ሚያዝያ 20፤ 2018 በሚካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ እንዲቀርብ አጀንዳ ተይዞለታል። በ2006 ዓ.ም. የተሻሻለው የ“ኢንሳ” ማቋቋሚያ አዋጅ፤ የኢንፎርሜሽን እና ኮምፒውተርን መሰረት ያደረጉ ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ብሔራዊ የፖሊሲ፣ የህግ፣ የስታንዳርድ እና ስትራቴጂ ረቂቆችን የማዘጋጀት ስልጣን ለመስሪያ ቤቱ ሰጥቶታል። በዚህ መሰረት ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን በመለየት የሳይበር ደህንነት ጥበቃ እና ቁጥጥር ማድረግ የሚያስችል አዋጅ ረቂቅ መስሪያ ቤቱ አዘጋጅቷል። አዲሱ አዋጅ “ቁልፍ መሰረተ ልማት” በሚል የሰየማቸው ለሳይበር ጥቃት ከተጋለጡ “በብሔራዊ ደህንነት እና ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ ጉዳት ያስከትላሉ” የሚላቸውን መሰረተ ልማቶችን እና ተቋሞችን ነው። @Tech_433et @Tech_433et

ከይለፍ-ቃል (Password) ወደ ማለፊያ-ቁልፍ (Passkey)፡ የዲጂታል ደህንነታችንን እናሳድግ! Passkey (የማለፊያ-ቁልፍ) ምንድን ነው? ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ በስልካችን ወይም በኮምፒውተራች
ከይለፍ-ቃል (Password) ወደ ማለፊያ-ቁልፍ (Passkey)፡ የዲጂታል ደህንነታችንን እናሳድግ! Passkey (የማለፊያ-ቁልፍ) ምንድን ነው? ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ በስልካችን ወይም በኮምፒውተራችን ላይ የሚቀመጡ ክሪፕቶግራፊክ (Cryptographic) ቁልፎችን የሚጠቀም ሲሆን፤ የጣት አሻራን (Fingerprint) ወይም የፊት ገጽታን (Facial recognition) በመጠቀም በቀላሉ ወደ አካውንታችን እንድንገባ ያስችለናል። ይህ ማለት ከዚህ በኋላ ረጅም እና ውስብስብ የይለፍ-ቃላትን ማስታወስ ላያስፈልገን ይችላል። በአሁኑ ወቅት እንደ አፕል (Apple)፣ ጉግል (Google)፣ ማይክሮሶፍት (Microsoft) እና ኤክስ (X) የመሳሰሉ ታላላቅ የቴክኖሎጂ ተቋማት ይህንን አሰራር በስፋት እየደገፉት ይገኛሉ። በሀገራችን ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ እና አገልግሎቶች በፍጥነት እያደጉ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ የሳይበር ጥቃቶች እና የመረጃ ስርቆቶችም በተመሳሳይ እየጨመሩ ይገኛሉ። በመሆኑም የማለፊያ-ቁልፎች (Passkeys) አጠቃቀም ከማጭበርበር (Phishing) እና ከመለያ ስርቆት የላቀ ጥበቃን ይሰጡናል። ይሁን እንጂ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች እንደሚያስጠነቅቁት፤ ይህ ቴክኖሎጂ ገና በሁሉም ድረ-ገጾች እና መተግበሪያዎች ላይ ሙሉ ለሙሉ ስላልተተገበረ ብቻውን የመጨረሻ መፍትሄ ሊሆን አይችልም። እንዴት ልንጠቀመው እንችላለን? አብዛኛዎቻችን በስማርት ስልኮቻችን ላይ የምንጠቀማቸው የጉግል እና አፕል አካውንቶች የ Passkey አገልግሎትን ጀምረዋል። በስልካችሁ “Security Settings” ውስጥ በመግባት "Passkeys" የሚለውን በመምረጥ ማስተካከል ትችላላችሁ። @Tech_433et @Tech_433et

Apple.Inc ቲም ኩክ የአፕል ቀጣዩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስራ አስፈፃሚ እንደሚሆን አስታውቋል ይህን ተከትሎ የሃርድዌር ኢንጂነሪንግ ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆነው ጆን ቴሩስ ፤ ቲም ኩክን ተክ
Apple.Inc ቲም ኩክ የአፕል ቀጣዩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስራ አስፈፃሚ እንደሚሆን አስታውቋል ይህን ተከትሎ የሃርድዌር ኢንጂነሪንግ ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆነው ጆን ቴሩስ ፤ ቲም ኩክን ተክቶ የአፕል ቀጣዩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ( CEO ) ተደርጎ ተሹሟል። ይህም ከሴፕቴምበር 1 ቀን 2026 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ። በዳይሬክተሮች ቦርድ ሙሉ ድምፅ የፀደቀው ይሄ ሽግግር የረጅም ጊዜ እቅድ እንደነበር አስታውቀዋል። ኩክ ከቴሩስ ጋር ለተቀላጠፈ ሽግግር ሂደት በቅርበት እየሰራ በቀረው የዋና ስራ አስፈፃሚነት ጊዜው የሚቆይ ይሆናል። @Tech_433et @Tech_433et

ሲስኮ (Cisco) በምርቶቹ ላይ አራት እጅግ አደገኛ የሆኑ የደህንነት ክፍተቶች መገኘታቸውን አስታወቀ ሲስኮ (Cisco) በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በምርቶቹ ላይ አራት እጅግ አደገኛ (Critical)
ሲስኮ (Cisco) በምርቶቹ ላይ አራት እጅግ አደገኛ የሆኑ የደህንነት ክፍተቶች መገኘታቸውን አስታወቀ ሲስኮ (Cisco) በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በምርቶቹ ላይ አራት እጅግ አደገኛ (Critical) የሆኑ የደህንነት ክፍተቶች መገኘታቸውን ያስታወቀ ሲሆን፤ በተለይም የ “Webex” እና “ISE” ስርዓቶችን የሚጠቀሙ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት በአስቸኳይ የደህንነት ማሻሻያዎችን (Security Updates) እንዲያደርጉ አሳስቧል። ከክፍተቶቹ መካከል አንዱ የሲስኮ ዌቤክስ (Cisco Webex Services) ክፍተት (CVE-2026-20184) ሲሆን ይህ ክፍተት የሳይበር ጥቃት አድራሾች የሌላ ህጋዊ ተጠቃሚን ማንነት ወስደው (Impersonate) ያለምንም ፈቃድ ወደ ሲስተም ሰብረው እንዲገቡ የሚያስችል ነው። በዚህም ሲስኮ ክፍተቱን የደፈነው ቢሆንም፤ ተቋማት “Single Sign-On” ሲስተምን የሚጠቀሙ ከሆነ የዕለት ተዕለት የስራ እና የኮሙኒኬሽን አገልግሎት መቋረጥ እንዳያጋጥማቸው አዲስ የ “SAML certificate” ወደ መቆጣጠሪያ ማዕከሉ (Control Hub) መጫን እንዳለባቸው አሳስቧል። ሌሎቹ የሲስኮ ISE ክፍተቶች (CVE-2026-20147, CVE-2026-20180, እና CVE-2026-20186) ሲሆኑ፤ በተጨማሪም በ “Identity Services Engine (ISE)” የፖሊሲ መቆጣጠሪያ ላይ ሶስት አደገኛ ክፍተቶች መገኘታቸውም ተጠቁሟል። እነዚህ ክፍተቶች አጥቂዎች አድሚኒስትሬተር (Admin) መግቢያ ካገኙ ሲስተሙን ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠሩ እና የፈለጉትን ትዕዛዝ እንዲያስተላልፉ እድል የሚሰጡ ናቸው፡፡ ባለፈው ወር ብቻ በሌላ የሲስኮ ምርት (FMC) ላይ በነበረ ክፍተት አጥቂዎች የራንሰምዌር (Ransomware) ጥቃት ማድረሳቸው ይታወሳል። @Tech_433et @Tech_433et

የይለፍ ቃላት (Passwords) ዘመን እያበቃለት ይሆን? አብዛኛዎቹ ዘመናዊ የሳይበር ጥቃቶች የሚጀምሩት በተሰረቁ የተጠቃሚ መለያዎች መሆኑን ተከትሎ፣ የይለፍ ቃላት (Passwords) ለከፍተኛ የሳ
የይለፍ ቃላት (Passwords) ዘመን እያበቃለት ይሆን? አብዛኛዎቹ ዘመናዊ የሳይበር ጥቃቶች የሚጀምሩት በተሰረቁ የተጠቃሚ መለያዎች መሆኑን ተከትሎ፣ የይለፍ ቃላት (Passwords) ለከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸው ተገለጸ። በቅርቡ የወጡ የደህንነት ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፣ ይህ ተጋላጭነት እየሰፋ በመምጣቱ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች "የይለፍ ቃል አስተማማኝነቱ እያበቃ ነው" የሚል ማስጠንቀቂያ እየሰጡ እንደሚገኝ ተገልጿል። የመረጃ መንታፊዎች ሰራተኞችን ለማታለል እውነተኛ የሚመስሉ የሐሰት መግቢያ ገጾችን በመጠቀም መረጃዎችን እየሰረቁ መሆናቸው ተነግሯል። በዚህም የተጠቃሚን መዘናጋት በመጠቀም የብዙ-ደረጃ ማረጋገጫን (MFA) በመጥለፍ ወደ ተቋማት ሚስጥራዊ መረጃ ሰርገዉ መግባት መቻላቸው የችግሩን አሳሳቢነት ጨምሮታል። በተለይ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የሳይበር ወንጀለኞች የሚልኳቸውን መልዕክቶች ይበልጥ አሳማኝ እንዲሆኑና ሰዎችን በቀላሉ እንዲያታልሉ ትልቅ እገዛ እያደረገላቸው እንደሚገኝ ተመልክቷል። የይለፍ ቃላት የተፈጠሩት ሰራተኞች በቢሮ ውስጥ ብቻ በሚሰሩበት ዘመን እንደነበር ያስታወሰው ጥናቱ፣ አሁን ግን ስራ በየትኛውም ቦታና በግል መሣሪያዎች ጭምር የሚከናወን በመሆኑ የቆዩት የደህንነት ፖሊሲዎች በቂ አለመሆናቸውን አመልክቷል። የቲም ቪወር (TeamViewer) የ2025 ጥናት እንደሚያሳየው፣ 80 በመቶ የሚሆኑ ሰራተኞች ከመግቢያ መረጃ ጋር የተያያዘ ችግር የገጠማቸው ሲሆን፣ ውስብስብ የይለፍ ቃል ህጎችም ተጠቃሚዎች መረጃቸውን ደህንነቱ ባልተጠበቀ ቦታ እንዲያስቀምጡ እያገፋፏቸው መሆኑ ተጠቅሷል። የዘርፉ ባለሙያዎችም ተቋማት በባዮሜትሪክስ (የጣት አሻራ እና የፊት ገጽታ) ላይ ወደሚሰሩ "ፓስኪዎች" (Passkeys) እንዲሸጋገሩ የመከሩ ሲሆን፣ ይህም የመረጃ መንታፊዎች መረጃን ቢሰርቁ እንኳን ያለ ተጠቃሚው መሣሪያ መጠቀም ስለማይችሉ ጥቃቱን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንሰዉ ጠቁመዋል። @Tech_433et @Tech_433et

“በኢትዮጵያ የኤ.አይ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ኤ.አይ ራሱ የቦርድ አባል ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትናንትናው ዕለት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ
“በኢትዮጵያ የኤ.አይ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ኤ.አይ ራሱ የቦርድ አባል ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትናንትናው ዕለት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢ.ቢ.ሲ) ጋር ባደረጉት ቆይታ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አንዱ የትኩረት ማዕከላቸው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው እንደገለጹት፤ በአንዳንድ ዓለማቀፍ ተቋማት ውስጥ ከአሥሩ የቦርድ አባላት መካከል አንዱ "ድምፅ አልባው" ኤ.አይ ነው። ይህንኑ ተሞክሮ በማስፋት፤ በኢትዮጵያ እየተገነባ በሚገኘው የኤ.አይ ዩኒቨርሲቲ ውስጥም ኤ.አይ ራሱ የቦርድ አባል እንደሆነ ጠቁመዋል። ኤ.አይ በቦርድ ስብሰባዎች ወቅት ድምፅ ባይሰጥም፤ ክርክር በሚደረግባቸው አጀንዳዎች ላይ ግን ዝርዝር መረጃዎችንና ሐሳቦችን ያቀርባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የቦርድ አባላቱም ከቴክኖሎጂው የሚያገኙትን ግብዓት መነሻ በማድረግ የመጨረሻ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ኤ.አይ ስለ ማንኛውም ጉዳይ ቢጠየቅ መልሱ ከሰው በተሻለ የመረዳት ጥልቀት ያለውና ፈጣን ነው፡፡ ምላሹ ሙሉ በሙሉ የሚወሰድ ባይሆን እንኳን በሰው ልጅ አ ዕምሮ ለሚደረግ ክርክር ትልቅ ግብዓት ይሆናል ብለዋል። ኤ.አይ በኢንዱስትሪው ውስጥ ምርታማነትን በመጨመር፣ ተመራጭ የኤክስፖርት ምርቶችን በመጠቆም፣ የሥራ ፍጥነትን በማሳለጥና ገበያን በማስተሳሰር ረገድ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። @Tech_433et @Tech_433et

ጎግል ክሮም የግል መረጃ መንታፊዎችን ጥቃት የሚመክት አዲስ የደህንነት መከላከያ ስርዓት አስተዋወቀ የጎግል የደህንነት ተመራማሪዎች የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ከሚመነትፉ ሶፍትዌሮች Info
ጎግል ክሮም የግል መረጃ መንታፊዎችን ጥቃት የሚመክት አዲስ የደህንነት መከላከያ ስርዓት አስተዋወቀ የጎግል የደህንነት ተመራማሪዎች የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ከሚመነትፉ ሶፍትዌሮች Infostealers ለመከላከል የሚያስችል አዲስ መከላከያ በጎግል ክሮም ብሮውዘር ላይ መተግበሩን አስታወቁ። ከመሣሪያ ጋር የተቆራኘ የቆይታ ማረጋገጫ (Device Bound Session Credentials) ተብሎ የሚጠራው ይህ አዲስ አሰራር፣ በተለይ የሰዎችን የድረ-ገጽ ቆይታ መረጃዎች #Cookies በመስረቅ የሚፈጸምን የሳይበር ጥቃት ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ኩኪዎች አንድን ድረ-ገጽ ሲጎበኙ ድረ-ገጹ ስለ እርስዎ መረጃ እንዲያስታውስ (ለምሳሌ የይለፍ ቃል ሳይጠይቁዎት እንዲቆዩ ወይም የመረጡትን ቋንቋ እንዲይዝ) በብሮውዘርዎ አማካኝነት በኮምፒውተርዎ ላይ የሚቀመጡ ትናንሽ የመረጃ ፋይሎች ናቸው። ምንም እንኳ እነዚህ ፋይሎች ለድረ-ገጾች ቅልጥፍና አስፈላጊ ቢሆኑም፣ እስካሁን ባለው አሰራር ሌቦች አንዴ የእርስዎን "ኩኪ" (ወደ አካውንትዎ ለመግባት የሚያገለግል ዲጂታል ፈቃድ) ከሰረቁ፣ የእርስዎን የይለፍ ቃል ሳያስፈልጋቸው ወደ ግል ማህበራዊ ገጾችዎ ወይም የባንክ አካውንትዎ መግባት ይችላሉ። አዲሱ ቴክኖሎጂ ይህንን ክፍተት የሚደፍነው የእርስዎን የድረ-ገጽ ቆይታ ከሚጠቀሙበት ኮምፒውተር ሃርድዌር ጋር በጥብቅ በማቆራኘት ሲሆን ሲስተሙ በመሣሪያዎ ውስጥ ብቻ የሚቀመጥና ሊሰረቅ ወይም ሊቀዳ የማይችል ልዩ "ዲጂታል ቁልፍ" ይፈጥራል ተብሏል። በዚህም ምክንያት መረጃ መንታፊዎች የእርስዎን ኩኪዎች ቢሰርቁ እንኳ፣ ያ ልዩ የሃርድዌር ቁልፍ በሌላው ማሽን ላይ ስለማይገኝ የተሰረቀው መረጃ ወዲያውኑ ዋጋ ቢስ ይሆናል። ይህም ሌቦቹ ወደ አካውንትዎ እንዳይገቡ በማድረግ አቅማቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ያዳክማል። ይህ አገልግሎት በአሁኑ ወቅት በChrome 146 እና 147 ስሪቶች ላይ ለዊንዶውስ Windows ተጠቃሚዎች በይፋ ስራ የጀመረ ሲሆን፣ በቅርቡ ደግሞ ለማክ macOS ተጠቃሚዎች እንደሚደርስ ታውቋል። በመሆኑም የክሮም ተጠቃሚዎች የብሮውዘር ስሪታቸውን በማዘመን Update የዚህ አዲስ የደህንነት መከላከያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይመክራሉ። @Tech_433et @Tech_433et

ቻይና አዳዲስ የኢንተርኔት ሳተላይቶችን ወደ ዝቅተኛዉ የምድር ምህዋር አመጠቀች ቻይና ዛሬ ሃሙስ ማለዳ ላይ አዲስ ቡድን ነዉ የተባለ ዝቅተኛ የምድር ምህዋር የኢንተርኔት ሳተላይቶችን በተሳካ ሁኔታ አ
ቻይና አዳዲስ የኢንተርኔት ሳተላይቶችን ወደ ዝቅተኛዉ የምድር ምህዋር አመጠቀች ቻይና ዛሬ ሃሙስ ማለዳ ላይ አዲስ ቡድን ነዉ የተባለ ዝቅተኛ የምድር ምህዋር የኢንተርኔት ሳተላይቶችን በተሳካ ሁኔታ አምጥቃለች ፣ይህም ማስፋፊያ የህዋ ፕሮግራሟ ላይ ሌላ እርምጃ መሆኑን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። ሳተላይቶቹ በሰሜን ሻንዚ ግዛት ከሚገኘው ታይዩዋን የሳተላይት ማስጀመሪያ ማዕከል በጠዋት ወደ ህዋ የተላኩ መሆናቸውን ዢንዋ ዘግቧል። ባለሥልጣናቱ እንዳረጋገጡት የሳተላይት ቡድኑ 21ኛው ባች ሲሆን ዝቅተኛ ምህዋር ሲሆን የኢንተርኔት ሳተላይቶቹ ወደተዘጋጀለት ምህዋር በተሳካ ሁኔታ መግባቱን አረጋግጠዋል። ተልእኮው 637ኛው የሎንግ መጋቢት ሮኬት ተከታታዮች በረራ በመሆን ለቻይና የጠፈር ጥረቶች ምእራፍ አዲስ ምልክት ተደርጓል። በስምዖን ደረጄ @Tech_433et @Tech_433et

የኢራን ሀከሮች በአሜሪካ ላይ ወሳኝ የመሠረተ ልማት አውታሮችን እያነጣጠሩ እንደሆነና ይህም "የሥራ መቆራረጥ እና የፋይናንስ ኪሳራ" አስከትሏል ስትል አሜሪካ አሳውቃለች። @Tech_433et @Tech
የኢራን ሀከሮች በአሜሪካ ላይ ወሳኝ የመሠረተ ልማት አውታሮችን እያነጣጠሩ እንደሆነና ይህም "የሥራ መቆራረጥ እና የፋይናንስ ኪሳራ" አስከትሏል ስትል አሜሪካ አሳውቃለች። @Tech_433et @Tech_433et

Planet Labs በአሜሪካ የሚገኝና በአለም ዙሪያ ታዋቂ የሆነ የሳተላይት ምስል አቅራቢ ድርጅት ነው ይህ ካምፓኒ ወደ ጠፈር ባመጠቃቸው ዶቭስ የሚባሉ ትናንሽ ሳተላይቶች አማካኝነት በየቀኑ ጥራት ያ
Planet Labs በአሜሪካ የሚገኝና በአለም ዙሪያ ታዋቂ የሆነ የሳተላይት ምስል አቅራቢ ድርጅት ነው ይህ ካምፓኒ ወደ ጠፈር ባመጠቃቸው ዶቭስ የሚባሉ ትናንሽ ሳተላይቶች አማካኝነት በየቀኑ ጥራት ያላቸው ምስሎችን እያነሳ ለሽያጭ ያቀርባል ። ....... ፕላኔት ላብስ ወደ ጠፈር ያመጠቃቸው እነዚህ ብዛታቸው 200 የሚደርሱ ትናንሽ ሳተላይቶች ምድርን በተለያየ አቅጣጫ እየዞሩ በየ 24 ሰአታት አዳዲስ ፎቶዎችን ይልካሉ ። .... ይህ ካምፓኒ ፡ የኢራንና የአሜሪካ ጦርነት ከተጀመረ ከባለፈው አንድ ወር ጀምሮ ጦርነቱ በሁለቱም በኩል ያደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ጥራት ያላቸውን ምስሎችም ሲያቀርብ ቆይቷል ። .... በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ በአሜሪካ ጦር ሰፈሮችና እና በእስራኤል ላይ የተደረገው ድብደባ ያደረሰውን ጉዳት የሚያሳዩ ምስሎች ብዙ ሚዲያዎች ከዚህ ካምፓኒ ሲያገኙ ነበር ። ...... ሆኖም በኢራን ያላሰበው ሽንፈት እየደረሰበት የሚገኘው ዶናልድ ትራምፕ በፕላኔት ላብስ የተነሱና ፡ በአሜሪካ ጦር ሰፈሮችና ጥቅሞች ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚያሳዩ ምስሎችን ለሕዝብ ይፋ እንዳይሆኑ ማገዱ ታውቋል ። ...... በዚህም መሰረት በመካከለኛው ምስራቅ በተለይም የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ የሚነሱ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የሳተላይት ምስሎች ለሕዝብ እና ለጋዜጠኞች ማሰራጨት ማቆሙን አስታውቋል። .... አስገራሚው ነገር ይህ አይደለም የትራምፕ እገዳ ፡ ፕላኔት ላብስ ወደ ፊት በሚያነሳቸው ምስሎች ላይ ብቻ ሳይሆን ፡ ወደኋላ ተመልሶ ከማርች 9 ማለትም ጦርነቱ ከተጀመረ እለት አንስቶ የተነሱ ምስሎችን ሀይድ እንዲያደርግ ትእዛዝ ደርሶታል ። ፕላኔት ላብስ ብቻ አይደለም ፡ ተመሳሳይ የምስል ማቅረብ አገልግሎት የሚሰጠው Vantor የተባለው ካምፓኒም ምስሎችን እንዳያሳይ ከታገዱ ድርጅቶች መካከል ይገኝበታል ። .... ይህ ሁሉ ለምን ከተባለ ኢራን በአሜሪካ ጥቅሞች ላይ ያደረሰችውን መጠነ ሰፊ ጉዳት ለመደበቅ በሚል ነው ። እንደው ቢቸግረው እንጂ ሽንፈት ቢደበቅም ድል አይሆንም ። ........ ወደዛሬ መረጃ ስንመጣ ተስፋ መቁረጥና ንዴቱ ጫፍ ደርሶ በአደባባይ በብልግና ቃል መሳደብ በጀመረው ዶናልድ ትራምፕ ፡ መመራት ለአሜሪካውያን ምን አይነት ስሜት እንደሚሰጥ ማሰብ ከባድ ነው ። ግን አሸማቃቂ ስሜት ያለው ይመስላል ። ...... በነገራችን ላይ ትራምፕን እንዲህ እያሳበዱት ያሉት ኢራኖች ምን ያህል ከባድ ናቸው ለማለት ትናንት ምሽት በኢስፋሃን የተደረገውን ፓይለቱን ለመውሰድ ያደረጉትን ትንቅንቅ መጥቀስ ይቻላል ። በዚህ ዘመቻ አሜሪካኖች በርካታ ሄሊኮፕተሮችና የጦር ጀቶችን አጥተዋል ፡ ይሄ ሁሉ ለምንድነው ካልን የራሳቸውን ፓይለት ለመውሰድ ፡ በቬንዙዌላ ዋና ከተማ ፡ ወደ ካራካስ ቤተመንግስት ሰተት ብለው ገብተው ፡ አንዳች ጉዳት ሳይደርስባቸው የሀገሪቱን ፕሬዝደንት ይዘው የሄዱ አሜሪካኖች ፡ በኢራን ለዛውም የተዘጋጀ ብዙ የኢራን ወታደሮች በሌሉበት የወደቀ ፓይለታቸውን ለመውሰድ ያዩት አበሳ ግን አበሳ አልነበረም ። ..... ምክንያቱም ሀገሩ ኢራን ነው ። ... እና አስገራሚው ነገር ፡ ተአምር እንደሚፈጥሩ እናስባቸው የነበሩት አሜሪካኖች ፡ የሰሞኑን ሽንፈትና ውርደት ያካክስላቸው ይመስል ፡ ይህን ፓይለቱን የመውሰድ ወሬ ፡ ዛሬ ቀኑን ሙሉ ሰፊ የዜና ሽፋን ሰጥተውት ውለዋል ። .... ችግሩ ፓይለቱን ከኢራን ምድር ማስወጣታቸውን ከሚገልፀው ዜና ጀርባ ያለው ዋና ፈተና አሁንም አልተፈታም ። ወደ ድንጋይ ዘመን እንመልሳችኋለን ተብለው ወደኋላ ያላሉት እነዚህ ህዝቦች ፡ ዛሬ ደግሞ ወደ ሲኦል እንደሚላኩ ከብልግና ስድብ ጋር ተነግሯቸዋል ። ዶናልድ ትራምፕ እጅግ አድርጎ በንዴት ከመብገኑ የተነሳ እንደ ቺካጎ ጋንግስተር ፀያፍ ስድብ በመሳደብ አሰልቺ ዛቻውን ለአስረኛ ጊዜ አስተላልፏል ። .. ችግሩ ምንድነው ? ኢራናውያን አሁንም ገግመዋል ። ምናል ለሞራሉ ሲሉ እንኳን ትንሽ ቢፈሩ. . ግን አላደረጉትም ፡ ኢራናውያን ትራምፕ ከሰአታት በፊት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ እንኳን በርካታ ሚሳይሎችንና ድሮኖችን ወደተለያዩ የጠላት ይዞታዎች ተኩሰዋል ። በነገራችን ላይ ዛሬ ከነጋ እንኩዋን ትራምፕ ኢራንን ሶስት ጊዜ አስጠንቅቋል ። ከዚም በላይ በቀረችው ጥቂት ሰአታት ኢራናውያን ትራምፕ እንደሚለው ካልተስማሙ ልዩ ወታደሮቹን በመላክ የኢራንን ነዳጅ እንደሚወስድ መናገሩን ተከትሎ የኢራን ባለስልጣናት ትራምፕ ቃሉን እንዲጠብቅና ወታደሮቹን እንዲልክ አደራ ብለውታል ። ... እንኳን ሊፈሩ ጭራሽ. .ወታደሮችህን እየጠበቅናቸው ነው ። እልካለሁ ብለህ አጓጉተኸን እንደማትቀር ተስፋ እናደርጋለን ሲሉ እየተናገሩ ነው ። @Tech_433et @Tech_433et

ከ50 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው የጨረቃ ተልእኮ የሆነው አርጤምስ II ጉዞውን ጀምሯል። ይህ ጉዞ ትናንት ማታ 1:35 Orion የጠፈር መንኮራኩርን የጫነ የናሳ SLS ሮኬት ከLaunch Complex 39B በፍሎሪዳ ኬኔዲ የጠፈር ማእከል ነበር መነሻውን ያደርገው። ሬይድ ዊስማን፣ ጄረሚ ሀንሰን፣ ክርስቲና ኮች እና ቪክቶር ግሎቨር የተባሉት አራት ጠፈርተኞች በጨረቃ ዙሪያ ይበሩና ከ 10 ቀን ተልዕኮ በኋላ ወደ ምድር ይመለሳሉ። ናሳ በ2028 በአርጤምስ IV ጠፈርተኞችን በጨረቃ ላይ ለማሳረፍ ያላቸውን እቅድም አሳውቀዋል። @Tech_433et @Tech_433et

ሚስጥራዊ መረጃዎን ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ከማጋራትዎ በፊት ሊያውቁት የሚገባ ጉዳይ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የዕለት ተዕለት ሥራችንን እጅግ እያቀለለልን ቢሆንም፣ ከእድገቱ ጋር ተያይዘው የሚመ
ሚስጥራዊ መረጃዎን ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ከማጋራትዎ በፊት ሊያውቁት የሚገባ ጉዳይ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የዕለት ተዕለት ሥራችንን እጅግ እያቀለለልን ቢሆንም፣ ከእድገቱ ጋር ተያይዘው የሚመጡ የሳይበር ጥቃቶች ግን አልቆሙም። በቅርቡ በChatGPT የሶፍትዌር ሥርዓት ላይ በተገኘ ከፍተኛ የደህንነት ክፍተት፣ ጥቃት አድራሾች በአንድ "አደገኛና አጥፊ ትእዛዝ" (Malicious Prompt) ብቻ የግልና የተቋማትን መረጃዎች መዝረፍ የሚያስችል አጋጣሚ ተፈጥሮ እንደነበር የቼክ ፖይንት (Check Point) ተመራማሪዎች ይፋ አድርገዋል። ይህ የደህንነት ስጋት፣ አጥፊ የሆኑ የጽሁፍ ትእዛዞችን በመጠቀም የChatGPTን የመከላከያ አጥር በመጣስ፣ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በቀጥታ ወደ ጥቃት ፈጻሚዎች ሰርቨር (Server) ማስተላለፍ ያስችላል። ይህም ተጠቃሚዎች ወደ AIው የሚጭኗቸውን ልዩ ልዩ ፋይሎች፣ የግል መልእክቶች እና ሚስጥራዊ የድርጅት ሰነዶች ለከፍተኛ አደጋ አጋልጦ ቆይቷል። ራስዎን እንዴት ይጠብቁ? 👉 ትእዛዞችን (Prompts) ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ፦ በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በተለያዩ ድረ-ገጾች ላይ "ምርጥ ውጤት ያስገኛሉ" ተብለው የሚሰራጩ የትእዛዝ አይነቶችን ሳያረጋግጡ አይጠቀሙ። እነዚህ ትእዛዞች መረጃዎን በድብቅ ወደ ጥቃት ፈጻሚዎች የሚልኩ ድብቅ መመሪያዎችን ሊይዙ ይችላሉ። 👉ሚስጥራዊ ፋይሎችን ከመጫን ይቆጠቡ፦ የባንክ መረጃዎችን፣ የጤና ሰነዶችን ወይም የተቋማትን ሚስጥራዊ ፋይሎች ወደ AI ሲስተሞች ከመጫንዎ በፊት በደንብ ያስቡ። AIው መረጃውን ለሌላ ወገን እያጋራ መሆኑን ራሱ እንኳ ላያውቀው እንደሚችል ልብ ሊባል ይገባል። 👉ምንጊዜም ንቁ ይሁኑ፦ ምንም እንኳን ለChatGPT የደህንነት ማስተካከያ ቢደረግለትም፣ አጥቂዎች አዳዲስ የጥቃት ዘዴዎችን መፈለጋቸውን አያቆሙም። ስለዚህ ከማይታወቁ ምንጮች የሚመጡ "አቋራጭ መንገዶችን" ሁልጊዜም በጥርጣሬ ይመልከቱ። @Tech_433et @Tech_433et

ኮሄር የተሰኘው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኩባንያ "ትራንስክራይብ" የተሰኘ ንግግርን ወደ ጽሁፍ የሚቀይር አዲስ የድምፅ ሞዴል አስተዋወቀ። ይህ ሞዴል ማንኛውም ሰው በነፃ ሊጠቀምበት የሚችል ሲሆን ዋና
ኮሄር የተሰኘው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኩባንያ "ትራንስክራይብ" የተሰኘ ንግግርን ወደ ጽሁፍ የሚቀይር አዲስ የድምፅ ሞዴል አስተዋወቀ። ይህ ሞዴል ማንኛውም ሰው በነፃ ሊጠቀምበት የሚችል ሲሆን ዋና ተግባሩም የድምፅ መዝገቦችን ወደ ጽሁፍ መቀየር እና ንግግሮችን መተንተን ነው። ሞዴሉ መጠኑ አነስተኛ በመሆኑ መደበኛ ኮምፒውተሮች ላይ ለመጠቀም አመቺ ነው። በአሁኑ ወቅት እንደ እንግሊዝኛ፣ አረብኛ፣ ቻይንኛ እና ፈረንሳይኛ ያሉ 14 ዋና ዋና ቋንቋዎችን ከንግግር ወደ ጽሁፍ መቀየር ይችላል። ኮሄር እንደሚለው ትራንስክራይብ ሌሎች ኩባንያዎች ከሰሯቸው ተመሳሳይ መተግበሪያዎች በተሻለ ትክክለኛ መረጃ የመመዝገብ ብቃት አለው። በሙከራ ወቅትም የቃላት ስህተት የመሥራት ዕድሉ ከሌሎቹ በጣም ዝቅተኛ ሆኖ ተገኝቷል። ሰዎች የትርጉሙን ጥራትና አጠቃቀም በገመገሙበት ወቅት፤ ሞዴሉ ከሌሎች መሰል መተግበሪያዎች በ61 በመቶ ብልጫ አሳይቷል። እንደ ቴክ ክራንች ዘገባ የዚህ ሞዴል አንዱ አስገራሚ ጎን ፍጥነቱ ሲሆን፤ የ525 ደቂቃ (ከ8 ሰዓት) የድምፅ ፋይልን በአንድ ደቂቃ ውስጥ ብቻ ወደ ጽሁፍ መቀየር ይችላል። @Tech_433et @Tech_433et

በቻይና ሸንዘን የሚገኙ ተመራማሪዎች የሰውን የተፈጥሮ እንቅስቃሴ ከሮቦት ጥንካሬ ጋር የሚያቀላቅል ‹‹ሴንታር›› የተሰኘ ልዩ የኃይል ልብስ ይፋ አድርገዋል። ይህ የፈጠራ ውጤት ከተለመዱትና ከአካል ጋ
+1
በቻይና ሸንዘን የሚገኙ ተመራማሪዎች የሰውን የተፈጥሮ እንቅስቃሴ ከሮቦት ጥንካሬ ጋር የሚያቀላቅል ‹‹ሴንታር›› የተሰኘ ልዩ የኃይል ልብስ ይፋ አድርገዋል። ይህ የፈጠራ ውጤት ከተለመዱትና ከአካል ጋር ከሚጣበቁ የኃይል ልብሶች በተለየ መልኩ፤ ከለባሹ ጀርባ እንደ ተጨማሪ ጥንድ እግር በመሆን አብሮ የሚራመድ ሲሆን፤ እስከ 20 ኪሎ ግራም የሚደርስ ሸክምን ሙሉ በሙሉ ተሸክሞ የመጓዝ አቅም አለው። መሣሪያው ለባሹ ወደ ፊት እንዲገፋ የሚያስፈልገውን ሜካኒካዊ ኃይል በራሱ ስለሚያመነጭ በእግር ጉዞ ወቅት የሚባክነውን የሰውነት ጉልበት እስከ 35 በመቶ በመቀነስ ረገድ ከሌሎች መሰል ቴክኖሎጂዎች የላቀ ውጤት አስመዝግቧል። ይህ የቴክኖሎጂ ውጤት የሰውን የመምራት ብቃት እና የሮቦትን የከባድ ስራ አቅም ለማቀናጀት ያለመ ቢሆንም፤በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ግን ከፍተኛ ትችት ገጥሞታል። ብዙዎች ለባሹ ድንገት ቢወድቅ የሮቦቱ ክብደት አከርካሪው ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል። ሐመረ ፍሬዉ @Tech_433et @Tech_433et

ጎግል ካልታወቁ ምንጮች የሚጫኑ መተግበሪያዎችን ለመቆጣጠር የ24 ሰዓት የቆይታ ጊዜን የሚያስገድድ አዲስ አሠራር ይፋ አደረገ ጎግል በአንድሮይድ ስልኮች ላይ ካልታወቁ ምንጮች የሚጫኑ መተግበሪያዎችን
ጎግል ካልታወቁ ምንጮች የሚጫኑ መተግበሪያዎችን ለመቆጣጠር የ24 ሰዓት የቆይታ ጊዜን የሚያስገድድ አዲስ አሠራር ይፋ አደረገ ጎግል በአንድሮይድ ስልኮች ላይ ካልታወቁ ምንጮች የሚጫኑ መተግበሪያዎችን (Sideloading) ለመቆጣጠር እንዲያስችለው የ24 ሰዓት የቆይታ ጊዜን የሚያስገድድ አዲስ አሠራር መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ "Advanced Flow" የተሰኘው አሠራር ተጠቃሚዎች በአጭበርባሪዎች ተገፋፍተውና ተቻኩለው አደገኛ መተግበሪያዎችን በመጫን ለግል መረጃ ስርቆት እንዳይጋለጡ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ጎግል ገልጿል። ይህ ጥብቅ ቁጥጥር ያስፈለገው "Perseus" የተሰኘ አዲስና አደገኛ ቫይረስ እንዲሁም ሌሎች 17 የሚሆኑ የማልዌር ዝርያዎች በዓለም ዙሪያ የሰዎችን የባንክ መረጃና የዲጂታል ማንነት እየዘረፉ ስለሆነ ጎግል በዚህ አሠራር የPlay Protect የደህንነት መጠበቂያን በማጠናከር የተጠቃሚዎችን ስልክ ከአደጋ ለመታደግ በማቀድ ነው። እንደ ጎግል ገለጻ አዲሱ መመሪያ ተፈጻሚ የሚሆነው ማንነታቸው በጎግል ያልተረጋገጠ አልሚዎች (Unverified Developers) ለሚያበለጽጓቸው መተግበሪያች ብቻ ነው። ተጠቃሚዎች እነዚህን መተግበሪያዎች ለመጫን ዴቨሎፐር ሞድን ማብራት፣ ስልካቸውን በድጋሚ ማስጀመር Restart) እና ለ24 ሰዓት በትዕግስት መጠበቅ ይኖርባቸዋል። ይህም በአጥቂዎችና በተጠቃሚች መካከል የጊዜ ልዩነት በመፍጠር ጥቃቱን ለመቀነስ ይረዳል። ይህ የጎግል ውሳኔ ከተለያዩ የመተግበሪያ አልሚዎችና የዲጂታል መብት ተሟጋቾች ትችት እየቀረበበት ይገኛል። ተቺዎቹ አሠራሩ የግል ነፃነትን የሚገድብ፣ የተጠቃሚዎችን መረጃ ለክትትል አሳልፎ የሚሰጥና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ወደ ዘርፉ እንዳይገቡ እንቅፋት የሚፈጥር "የቢሮክራሲ አጥር" ነው በማለት እየተቃወሙት ይገኛሉ። @Tech_433et

30 ቢሊዮን ዶላር እና 30 ሰራተኞች ብቻ! የቴሌግራም አስገራሚው የቢሊዮኖች ግምት በስተጀርባ ያለው ምስጢር ምንድነው? መጋቢት 08 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ በከፍተኛ
30 ቢሊዮን ዶላር እና 30 ሰራተኞች ብቻ! የቴሌግራም አስገራሚው የቢሊዮኖች ግምት በስተጀርባ ያለው ምስጢር ምንድነው? መጋቢት 08 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ በከፍተኛ ፍጥነት እያደጉ ካሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች መካከል ቀዳሚው የሆነው ቴሌግራም በ2026 መጀመሪያ ላይ ባለው መረጃ መሰረት በአስገራሚ የንግድ ስኬት ላይ እንደሚገኝ ተነገረ። ተቋሙ በአሁኑ ወቅት ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ እንዳለው የሚገመት ሲሆን ይህን ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋም የሚመራው ግን እጅግ ጥቂት የሆኑ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች መሆናቸው ብዙዎችን አስገርሟል። ቴሌግራም በአሁኑ ወቅት በአለም ዙሪያ ከ1 ቢሊዮን በላይ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎች ያሉት ቢሆንም ይህን ግዙፍ ፕላትፎርም የሚያንቀሳቅሰው ዋናው የቴክኒክ ቡድን ቁጥር ከ30 እስከ 50 ብቻ እንደሆነ ይገመታል። እንደ ጎግል ወይም ሜታ ያሉ ግዙፍ ቢሮዎች የሌሉት ቴሌግራም ሰራተኞቹ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች ሆነው በሪሞት ስራቸውን እንዲያከናውኑ በማድረግ ወጪን በመቀነስ ረገድ ውጤታማ ሆኗል። የቴሌግራም መስራች ፓቬል ዱሮቭ ለዚህ ስኬት የበቃው አብዛኛዎቹን የቴክኒክ ድጋፎች እና የይዘት ቁጥጥሮች በሰው ሳይሆን በረቀቁ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ወይም አውቶሜሽን አማካኝነት እንዲከናወኑ በማድረጉ ነው። በተጨማሪም በተቋሙ ውስጥ ውስብስብ የሆነ የአስተዳደር እርከን ባለመኖሩ ውሳኔዎች በፍጥነት እንዲተላለፉ ያስችላል። ተቋሙ ሰራተኞችን የሚቀጥረውም በታወቁ የኮዲንግ ውድድሮች ብቃታቸውን ባረጋገጡ ምርጥ ባለሙያዎች ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ ነው። ምንም እንኳን በፋይናንስ በኩል ጠንካራ መሆን ቢችልም ቴሌግራም የይዘት ቁጥጥርን ለማሻሻል አዳዲስ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል። የቴሌግራም ስኬት ለሌሎች የቴክኖሎጂ ጀማሪዎች ጥቂት ግን ብቁ የሆኑ ሰራተኞችን በመያዝ አለምአቀፍ ተጽዕኖ መፍጠር እንደሚቻል ትልቅ ትምህርት የሰጠ ሆኗል። ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን @Tech_433et @Tech_433et

ጂ.ፒ.ዩ ግራፊክስ ፕሮሰሲንግ ዩኒት (GPU) በአንድ ጊዜ ብዙ ተግባራትን ለማከናወን የተነደፈ ከፍተኛ አፈጻጸም ያለው የኮምፒውተር ፕሮሰሰር ነው። ለቪዲዮ ጨዋታዎች እና ምስሎችን ለማጫዎት ታስቦ የተ
ጂ.ፒ.ዩ ግራፊክስ ፕሮሰሲንግ ዩኒት (GPU) በአንድ ጊዜ ብዙ ተግባራትን ለማከናወን የተነደፈ ከፍተኛ አፈጻጸም ያለው የኮምፒውተር ፕሮሰሰር ነው። ለቪዲዮ ጨዋታዎች እና ምስሎችን ለማጫዎት ታስቦ የተሰራ ቢሆንም አሁን የኤ.አይ ሞዴሎችን ለማሰልጠን፣ ግዙፍ ዳታን ለመተንተን እንዲሁም ከፍተኛ አፈጻጸም ያላቸዉ ኮምፒውተሮችን ለማንቀሳቀስ ተመራጭ ነዉ። እነዚህን ተግባራት በሴንትራል ፕሮሰሲንግ ዩኒት (CPU) ማከናወን ቢፈለግ ካለዉ የአቅም ዉስንነት የተነሳ ቀናት አልያም ወራት ሊፈጅበት ይችላል። ሹፌር አልባ ተሽከርካሪዎች፣ ቻት ቦቶች፣ የአየር ሁኔታ ትንበያ እና ሳይንሳዊ ምርምሮች ባሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ውስጥ ጂ.ፒ.ዩ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። እንደ NVIDIA RTX 4090፣ NVIDIA A100 እና AMD Radeon RX 7900 XTX ያሉት ጂ.ፒ.ዩዎች ለቪዲዮ ጌም፣ ለኤ.አይ ቴክኖሎጂ ልማት እዲሁም ምርምር ተመራጭ ናቸዉ። ጂፒዩ ኮምፒዩቲንግ ዘመናዊ የኤ.አይ ቴክኖሎጂን ዉጤታማ የሚያደርግ ኃይል ሆኖ እያገለገለ መሆኑን የአይ.ቢ.ኤም ድረ ገጽ መረጃ ያሳያል። ኤንቪዲያ፣ኤ.ኤም.ዲ እና ኢንቴል ጂ.ፒ.ዩ በማምረት ፈር ቀዳጅ ከሆኑ ኩባንያዎች መካከል ይጠቀሳሉ። @Tech_433et @Tech_433et

ፊፋ የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ለመምራት መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ የዓለማቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ የስራ ክንውኖቹን በኤ.አይ ላይ የተመ
ፊፋ የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ለመምራት መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ የዓለማቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ የስራ ክንውኖቹን በኤ.አይ ላይ የተመሰረተ ለማድረግ ማቀዱን ይፋ አደረገ። ፊፋ ከሌኖቮ ኩባንያ ጋር በመተባበር ያቀረበው ይህ አዲስ አሰራር በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና አሜሪካ የሚካሄደውን ግዙፍ ውድድር ለመምራት ታላቅ ሚና ይኖረዋል። በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ውድድር የቡድኖች ቁጥር ወደ 48 ማደጉና ጨዋታዎቹ በሦስት አገራት መካሄዳቸው ስራውን እጅግ ውስብስብ ያደረገው ሲሆን ለዚህ ደግሞ ኤ.አይን ትልቁ የመፍትሄ መሳሪያ አድርጎ ሊጠቀምበት አቅዷል፡፡ ፊፋ በዚህ ውድድር ሊተገብራቸው ያቀዳቸው የኤ.አይ ቴክኖሎጂዎች የውድድሩን ፍትሃዊነት እና ግልጽነት ለማረጋገጥ ያለሙ ናቸው፡፡ ይህም ለሁሉም 48 ቡድኖች እኩል የትንታኔ ዕድል የሚሰጠውን Football AI Pro፣ የዳኝነት ውሳኔዎችን ለተመልካች ይበልጥ ግልጽ የሚያደርገውን የተሻሻለ የዳኞች ካሜራ (Referee View)፣ እንዲሁም የ"ከጨዋታ ውጭ" ውሳኔዎችን በከፍተኛ ትክክለኛነት ለመለየት የሚያስችሉ የ3D ተጫዋቾች ምስሎችን (Avatars) ያካተተ ነው። አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኒውስ እንደዘገበው እነዚህ ዘመናዊ አሰራሮች በመቶዎች የሚቆጠሩ ጨዋታዎችን እና ስታዲየሞችን በአንድ ማዕከል ሆኖ በብቃት ለመምራት የሚያስችል የመረጃ መቆጣጠሪያ ማዕከል ላይ የተገነቡ በመሆናቸው ውድድሩ በቴክኖሎጂ የታገዘ ስኬታማ አመራር እንዲኖረው ያደርጋሉ። @Tech_433et @Tech_433et