en
Feedback
AAU FM 99.4_Radio Official channel

AAU FM 99.4_Radio Official channel

Open in Telegram

AAU FM 99.4 Brodcast time every day from Morning 6:00Am - Evenning 10፡00PM.ከማለዳ 12:00_ምሽት4፡00አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የተመለከተ ፈጣን የመረጃ ምንጭ! ➮ዩኒቨርሲቲ ተኮር መረጃዎች ➮የሃገር ቤት ትኩስ መረጃዎች ➮የአፍሪካ እና አለምን የተመለከቱ መረጃዎች ➮የዩኒቨርሲቲዉ ምሁራን ቃለ-መጠይቆች... ለበለጠ መረጃ 011-1-26-67-54/41ይደዉሉ

Show more
896
Subscribers
-124 hours
No data7 days
+230 days
Posts Archive
የቴሌግራም ቻናልችንን  በመቀላቀል የAAU FM RADIO 99.4 ወቅታዊ መረጃዎችን ይከታተሉ… https://t.me/AAUFM99point4

በረጅም ጊዜ የተቀናጀ የምርምር ስነ-ዘዴ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ። መስከረም 16 ፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) ​የሰብአዊ መብቶች ማዕከል ከ"ጀንደር ኤንድ አዶለሰንስ፡ ግሎባል
+1
በረጅም ጊዜ የተቀናጀ የምርምር ስነ-ዘዴ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ። መስከረም 16 ፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) ​የሰብአዊ መብቶች ማዕከል ከ"ጀንደር ኤንድ አዶለሰንስ፡ ግሎባል ኤቪደንስ" (GAGE) ፕሮግራም እና ከQUEST የምርምር፣ ስልጠና እና አማካሪ አገልግሎቶች ጋር በመተባበር በመረጃ መሰብሰቢያ እና መተነተኛ ሶፍትዌሮች እንዲሁም መሣሪያዎች ላይ ያተኮረ በረጅም ጊዜ የተቀናጀ የምርምር ዘዴዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና  በሰብአዊ መብቶች ማዕከል ስብሰባ አዳራሽ ሰጥቷል። ​ስልጠናው በረጅም ጊዜ የተቀናጀ የምርምር ዘዴዎች በተለይም በስርዓተ-ፆታ እና በጉርምስና ጥናቶች ዘርፍ ባላቸው ፅንሰ-ሀሳባዊ ግንዛቤ እና ተግባራዊ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ነበር። በክፍለ-ጊዜዎቹ የመረጃ አሰባሰብ ቴክኒኮች፣ የመጠነ-ቁሳዊ (quantitative) መረጃ ትንተና፣ የዓይነታዊ (qualitative) መረጃ ኮዲንግ እና ትንተና፣ የመረጃ ጥራት ማረጋገጫ እና አስተማማኝነት ዘዴዎች ላይ ያተኮረ ነው። ​ከተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የተወጣጡ ተመራማሪዎች፣ መምህራን እና የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች በቲዎሪቲካል ውይይቶች እና በተግባራዊ ልምምዶች ላይ በንቃት ተሳታፊ ሆነዋል። ፕሮግራሙ የተሳታፊዎችን እውቀት እና ተግባራዊ ክህሎት በረጅም ጊዜ የተቀናጀ የምርምር ስራዎችን ለማካሄድ እና ዘመናዊ የመረጃ መሰብሰቢያ እና መተነተኛ መሣሪያዎችን በጥቅም ላይ ለማዋል አቅማቸውን አሳድጓል። ​ስልጠናው ሁሉንም ተሳታፊዎች ፕሮግራሙን በስኬት ማጠናቀቃቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት በመስጠት ተጠናቋል። ይህ ጥረት በስርዓተ-ፆታ እና በጉርምስና መስኮች የምርምር አቅምን ለማጠናከር እና በማስረጃ ላይ የተመሰረቱ ጥናቶችን ለማስፋፋት አስተዋፅኦ ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል። ​

የመርሳት ችግርን በቶሎ ለመለየት የግንዛቤ ማስጨበጫና ነፃ የምርመራ አገልግሎት ተሰጠ። መስከረም 15፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) በዓለም አቀፍ የመርሳት ችግር ወር ምክንያት በማድ
+1
የመርሳት ችግርን በቶሎ ለመለየት የግንዛቤ ማስጨበጫና ነፃ የምርመራ አገልግሎት ተሰጠ። መስከረም 15፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) በዓለም አቀፍ የመርሳት ችግር ወር ምክንያት በማድረግ በመዘንጋት ችግር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫና ነፃ የምርመራ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ ተካሂዷል። መርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና ከልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት ፣ ከኤን አይ ኤች ፣ ከብሪጅ አፍሪካ እና ከዳውን አልዛይመር ሪሰርች ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው ። የመርሃ ግብሩ ዋና አላማ ማህበረሰቡ የመርሳት ችግር ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ እና ተገቢውን የሕክምና ዕርዳታ እንዲያገኝ ለማስቻል መዘጋጀቱን የመርሃ ግብሩ አስተባባሪ ዶክተር ሳሙኤል ዘሪሁን ገልጸዋል ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የነርቭ ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ሰዒድ ዓሊ በበኩላቸው ፣ የግንዛቤ መስጫ  መርሀግብር የጤና ባለሙያዎች ሙያዊ ግዴታ መሆኑን አንስተዋል።
ዶክተር  ሰዒድ አክለው ፣ ለህብረተሰቡ ቅድሚያ የሚሰጣቸው የጤና ጉዳዮች በመለየት፣ ትክክለኛና አስተማማኝ መረጃ ለማቅረብ የተዘጋጀ የጤና ትምህርት እቅድ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በተለይም ህመሙ ከመደበኛ የእርጅና ሂደት ጋር ብቻ ተያይዞ መታየቱ፣ ታካሚዎችና ቤተሰቦቻቸው በህክምና ተቋም በመቅረብ ተገቢውን ምርመራና ሕክምና እንዳያገኙ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆኑን ጠቁመዋል ። ይህንን የግንዛቤ ክፍተት ለመቀነስና የጤና አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ መርሃ ግብሩ መዘጋጀቱን አስረድተዋል ። በመርሃ ግብሩም ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ከመስጠት ባለፈ፣ ነፃ የምርመራ አገልግሎት እየተሰጠ  ይገኛል። በአዲሱ አለማየሁ

«ልዩ መሰናዶ » የመስቀል ዕለት የታላቁ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉሥ ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ የልደት ቀን መስከረም 17 ቀን 1933 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 27 ወይም 29፣ 1940)
«ልዩ መሰናዶ Âť የመስቀል ዕለት የታላቁ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉሥ ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ የልደት ቀን መስከረም 17 ቀን 1933 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 27 ወይም 29፣ 1940) ነው። ድምፃዊው የተወለደው በኢትዮጵያ በታላቅ ድምቀት በሚከበረው በመስቀል በዓል ዕለት በመሆኑ በቅርብ ወዳጆቹ ዘንድ "መስቀል ልደት" እየተባለም ይጠራ ነበር። 👉ከፊታችን እሁድ ከመስከረም 17/2019 ዓ.ም ልዩ የትውስታ መሰናዶ በ አዲስ አባባ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ሬዲዮ fm 99.4 አየር ላይ ይውላል። 👉​ከድምፃዊው የቀድሞ ወዳጅ እና የስራ ባልደረባ ከነበሩት ከሻንበል አፈወርቅ ዮሀንስ ልጅ ጋር አንተነህ ጌታቸው ቆይታ አድርጓል ። 👉ያልተሰሙ የጥላሁን ገሰሰ የስራ  ገጠመኞች እና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተሰሩ ሙዚቃዎች ይዳሰሳሉ ። ❤አዲስ አበባ  ዩኒቨርሲቲ ሬዲዮ ኤፍ ኤም 99.4"የማህበረሰቡ ድምፅ"❤  Tune: AAU FM Radio 99.4 Phone: 011_1-26-67-41/54 Telegram: https://t.me/AAUFM99point4 Email: aaufm.radio@aau.edu.et

የቴሌግራም ቻናልችንን  በመቀላቀል የAAU FM RADIO 99.4 ወቅታዊ መረጃዎችን ይከታተሉ… https://t.me/AAUFM99point4

አዲስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጽሐፍ በሳይንስ ሙዚየም ተመረቀ። መስከረም 13፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) በቴክኖሎጂ አማካሪው ሰለሞን ሙሉጌታ ካሳ ተደርሶ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል
አዲስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጽሐፍ በሳይንስ ሙዚየም ተመረቀ። መስከረም 13፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) በቴክኖሎጂ አማካሪው ሰለሞን ሙሉጌታ ካሳ ተደርሶ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ተባባሪነት የተዘጋጀው "አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ" የተሰኘው አዲስ የአማርኛ መጽሐፍ በሳይንስ ሙዚየም ለንባብ በቃ። መጽሐፉ የኤ.አይ ቴክኖሎጂን ምንነት፣ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የሚኖረውን ከፍተኛ አበርክቶ እንዲሁም ሊያስከትሉ የሚችሉትን ስጋቶች በጥልቀት ይዳስሳል። በምርቃ መርኃግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) እና ዶ/ር ምህረት ደበበ፤ ቴክኖሎጂውን በተጠና መንገድ ለመጠቀምና ከሰው ልጆች አዕምሮና ማህበራዊ ህይወት ጋር ያላቸውን ቁርኝት በተለያዩ መነጽሮች ለመረዳት መጽሐፉ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

በወጣቶች መብትና ማህበራዊ ተሳትፎ ላይ ያተኮረ የምርምር መድረክ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው ። መስከረም 13፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ
+1
በወጣቶች መብትና ማህበራዊ ተሳትፎ ላይ ያተኮረ የምርምር መድረክ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  እየተካሄደ ነው ። መስከረም 13፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብት ማዕከል  በወጣቶች መብት፣ ማህበራዊ ተሳትፎ እና ዲጂታላይዜሽን ዙሪያ የተሰሩ ጥናቶችንና የምርምር ውጤቶችን ከተግባር  ጋር ለማገናኘት ያለመ  መድረክ መካሄድ  ጀምሯል ።
መድረኩ የወጣቶችን መብት እና በህይወታቸው የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በመመርመር ፣ ወጣቶች  ችግሮቻቸውን ተቋቁመው ለሀገራቸው የሚኖራቸውን አስተዋጽኦ ለማጠናከር ያለመ መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብት ማዕከል ሃላፊ ዶክተር አንቺነሽ ሽፈራው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
  በዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ  ተማሪዎች ከ18 እስከ 24 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች በመሆናቸው፣ በእነርሱ ዙሪያ  የሚካሄዱ ጥናቶች በጤና፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፏቸውና ባላቸው ግንኙነት ላይ ማተኮሩ ጠቅሰዋል ። ዶክተር ካሳሁን ጥላሁን በበኩላቸው ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምርምር የሚያመነጩትን ማስረጃ ወደ ተግባር ለማሸጋገር ከፕሮጀክት አስፈጻሚ ተቋማት፣ ከአለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ከለጋሽ አካላትና ከፖሊሲ አውጪዎች ጋር  ትስስር መፍጠር እንዳለባቸው አመልክተዋል ። ዶክተር አንቺነሽ  አክለውም ፣ መድረኩ  ወጣት ተመራማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው አንጋፋ ተመራማሪዎችና ከመምህራን የምርምር ልምድ እንዲቀስሙና በቀጣይ የምርምር ሥራዎች እንዲበረታቱ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል ። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማስተማር፣ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ሦስት ተቀዳሚ ተግባራትን በማጣመር፣ የምርምር ውጤቶች  የማህበረሰቡን ችግር እንዲፈቱ መሠል መድረኮች መዘጋጀታቸው አስፈላጊ ነው ብለዋል። በአዲሱ አለማየሁ

ማስታወቂያ! በዜናና በሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጅት ስትሰሩ ለነበራችሁ በጎ ፍቃደኛ ተማሪዎች በሙሉ! በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬዲዮ ኤፍ ኤም 99.4 ላይ በ2018 ዓ.ም በሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጅት እና በዜ
ማስታወቂያ! በዜናና በሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጅት ስትሰሩ ለነበራችሁ በጎ ፍቃደኛ ተማሪዎች በሙሉ! በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬዲዮ ኤፍ ኤም 99.4 ላይ በ2018 ዓ.ም በሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጅት እና በዜና ንባብ ስትሰሩ የነበራችሁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፊታችን ሰኞ መስከረም 18/2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት በሬዲዮ ጣቢያው ስቱዲዮ ዳሬክተር ቢሮ በመገኘት የተለመደው ስራችሁን ለመጀመር ማሳወቅ እንደምትችሉ እንገልፃለን። በሚዲያው የፕሮግራም ዝግጅት መሳተፍ ለምትፈልጉ አዳዲስ ተማሪዎች ወደፊት ማስታወቂያ እናወጣለን። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬዲዮ "የማህበረሰቡ ድምፅ" የቴሌግራም ቻናልችንን  በመቀላቀል የAAU FM RADIO 99.4 ወቅታዊ መረጃዎችን ይከታተሉ… https://t.me/AAUFM99point4

የቴሌግራም ቻናልችንን  በመቀላቀል የAAU FM RADIO 99.4 ወቅታዊ መረጃዎችን ይከታተሉ… https://t.me/AAUFM99point4

#Internship_Opportunity በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ Peace and Security Studies ኢንስቲትዩት (IPSS) ለጣና ፎረም 2026 ድጋፍ የሚሰጡ ተማሪዎች ወይም በቅርቡ የተመረ
#Internship_Opportunity በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ Peace and Security Studies ኢንስቲትዩት (IPSS) ለጣና ፎረም 2026 ድጋፍ የሚሰጡ ተማሪዎች ወይም በቅርቡ የተመረቁ ተለማማጆችን (Interns) ይፈልጋል፡፡ በዚህ ክፍያ በሌለው ኢንተርንሺፕ ሲሳተፉ፤ በሰላም ግንባታ፣ በደኅንነት ለውጦች፣ እና በውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ላይ በዘርፉ ልምድ ካላቸው ባለሙያዎች የተግባር ልምድ ያገኛሉ፡፡ የማመልከቻ ጊዜው መስከረም 13/2019 ዓ.ም ያበቃል፡፡ CV እና Motivation Letter ወደ application@ipss-addis.org በመላክ በቀሩት ሰዓታት ይመዝገቡ! ለተጨማሪ መረጃ፦ https://ipss-addis.org/call-for-internship-tana-high-level-forum-2026-support/

የቴሌግራም ቻናልችንን  በመቀላቀል የAAU FM RADIO 99.4 ወቅታዊ መረጃዎችን ይከታተሉ… https://t.me/AAUFM99point4

የመጀመሪያው የአፍሪካ የውሃ ዋስትና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተጀመረ፡፡ መስከረም 11፤2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) የመጀመሪያው የአፍሪካ የውሃ ዋስትና
የመጀመሪያው የአፍሪካ የውሃ ዋስትና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተጀመረ፡፡ መስከረም 11፤2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) የመጀመሪያው የአፍሪካ የውሃ ዋስትና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል። የኮንፈረንሱ ዋና ትኩረት አቅጣጫዎች ውሃን እንደ ትልቅ የሪጅናል ኮርፖሬሽን ማዕከል አድርጎ ማስተሳሰር እና የኢትዮጵያን የውሃ አስተዳደር አጠቃላይ ገጽታ ለሌሎች አገሮች ማካፈል መሆኑ ተመላክቷል። የኢትዮጵያ ውሃ አጠቃላይ አስተዳደር ሁኔታ፣ አቋም እና የውሃ ላይ ያላት ግንዛቤ ለቀጣይ አህጉራዊ ትብብሮች መሠረት እንዲሆን በሰፊው ውይይት እንደሚደረግበት ላይ ተመላክቷል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ የውሃ ልቀት ማዕከል ኃላፊ ፕሮፌሰር ፈለቀ ዘውገ እንደገለፁት፣ አገራዊና አህጉራዊ የውሃ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ሰፊ ሥራዎች መሠራት እንዳለባቸው ገልፀዋል።
ፕሮፌሰር ፈለቀ አያይዘውም የውሃ ሀብት አስተዳደርን ውጤታማ ለማድረግ የጥናት ውጤቶችና በፖሊሲ አቅጣጫዎች ዙሪያ  á‹á‹­á‹­á‰śá‰˝ በማድረግ ሀገራት የጋራ መፍትሄዎችን እንዲያበጁ ለማረግ የዚህ አይነት ውይይት አስፈላጊ ነው ብለዋል። በጉባኤው ላይ የተገኙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር  á‹¨á‰°á‰€áŠ›áŒ€ የውሀ ሀብት አስተዳደር ሾል አስፈፃሚ ደበበ ደፈርሶ በበኩላቸው የሳይንስ ማህበረሰቡንና የፖሊሲ አውጪዎችን ግንኙነት በማጠናከር የውሃ ሀብት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የሚቀጥሉት የኮንፈረንሱ ቀናት ውይይቶች እንደሚያደርጉባቸው  á‰°áŠáŒáˆ¨á‹‹áˆá˘
በተጨማሪም መድረኩ የኢትዮጵያን የውሃ አስተዳደር አጠቃላይ ሁኔታ፣ አቋም እና ግንዛቤ ለሌሎች አገሮች ሌምድ ለማጋራት ያለመ ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡
በአንተነህ ጌታቸው

የቴሌግራም ቻናልችንን  በመቀላቀል የAAU FM RADIO 99.4 ወቅታዊ መረጃዎችን ይከታተሉ… https://t.me/AAUFM99point4

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የAAU FM 99.4 ወቅታዊ መረጃዎችን ይከታተሉ…

የ60 ታዋቂ ሰዎች ታሪክ የያዘው «የዘመን አሻራ» መጽሐፍ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ተመረቀ። መስከረም 10፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) በደራሲ እና የታሪክ ተ
+1
የ60 ታዋቂ ሰዎች ታሪክ የያዘው «የዘመን አሻራ» መጽሐፍ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ተመረቀ። መስከረም 10፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) በደራሲ እና የታሪክ ተመራማሪ ፍጹም ወልደማርያም የተጻፈው «የዘመን አሻራ» የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ራስ መኮንን አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል። መጽሐፉ "60 ህይወቶች፣ 60 ታሪኮች እና አንድ የትውልድ አሻራ" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የ57 ኢትዮጵያውያንን እና የ3 የኢትዮጵያ ወዳጅ የውጭ ዜጎችን (ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት፣ ሲልቪያ ፓንክረስት እና ደጃዝማች ዑመር ሰመተር) አጠቃላይ የሕይወት ታሪክ ሰንዶ ይዟል። መጽሐፉ ረጅም ጊዜ የፈጀ ምርምር ተደርጎበት የታሪክ ምሁራን፣ የኪነ-ጥበብ ሰዎችና የአርበኞችን ታሪክ ያካተተ ሲሆን፣ ለጥናትና ምርምር በማጣቀሻነት የሚያገለግልና ቀጣዩ ትውልድ የራሱን ታሪክ እንዲጽፍ የሚያነሳሳ ነው። በምረቃው ወቅት የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዮሃንስ አድገህ እና ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ደራሲው ለትውልድ የሚተርፍ ሥራ በመሥራቱ ምስጋና አቅርበዋል። በተጨማሪም ደራሲ ፍጹም ወልደማርያም ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ሙሉ ገቢ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ቤተ-መጻሕፍትን ለማጠናከር እንደሚውል ያበሰረ ሲሆን፣ ለተቋሙም የሶፍት ኮፒ እና የሀርድ ኮፒ መጻሕፍትን በስጦታ አበርክቷል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ1978 ዓ.ም የመካኒካል ምህንድስና ተመራቂዎች በአልሙናይ መድረክ ተገናኙ ። መስከረም 10፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) የቀደሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ1978 ዓ.ም የመካኒካል ምህንድስና ተመራቂዎች በአልሙናይ መድረክ ተገናኙ ። መስከረም 10፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) የቀደሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂና የቢውልት ኢንቫሮመንት ኮሌጅ  የ1978 ዓ.ም መካኒካል ምህንድስና  ተመራቂዎች ከተቋሙ ከተለዩ በኋላ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያካበቱትን ዕውቀትና ልምድ ለማካፈል ተገናኝተዋል ። ይህንንም ትስስር ለማጠናከር የተዘጋጀው የአልሙናይ መድረክ የተመራቂዎችን ልምድ ከዩኒቨርሲቲው የአሁኑ  ተግባር  ጋር  ለማገናኘት የሚያስችል ውይይት አካሂዷል ። የአልሙናይ መድረኩ ተመራቂዎች ከዩኒቨርሲቲው ጋር ያላቸውን ቀጣይነት ያለው ትስስር ማጠናከር ፣ የሙያ ልምድና ዕውቀትን ማጋራት እና በተቋሙ የልማትና የትምህርት ሥራዎች ላይ የተመራቂዎችን ተሳትፎ ማሳደግን ያለመ ነው ። በውይይቱ ተመራቂዎች በሥራ ዓለም ያጋጠሟቸውን ልምዶች ፣ ያገኙትን ዕውቀትና  በዩኒቨርሲቲው  ለሚማሩ ተማሪዎች ሊያበረክቱ የሚችሉትን አስተዋጽኦ  አካፍለዋል። አልሙናይዎች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሚገኙ በመሆናቸው ፣ ያካበቱት ልምድ ለአሁኑ ተማሪዎች የሙያ መመሪያና የልምድ ማስተላለፊያ እድል ሊፈጥር እንደሚችል ተጠቁሟል።
ተመራቂዎች በምርምር፣ በፈጠራ፣ በኢንዱስትሪ ትስስር፣ በሙያዊ አማካሪነት እና በተማሪዎች የሙያ እድገት ላይ የሚኖራቸውን ሚና ማጠናከር  በመድረኩ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል ናቸው ።
የአልሙናይ መድረኩ በተመራቂዎች እና በዩኒቨርሲቲው መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር ፣ ዕውቀትና ልምድን ለቀጣዩ ትውልድ  ለማስተላለፍ የሚያስችል መድረክ መሆኑ ተገልጿል። በአዲሱ አለማየሁ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎቹ የቅበላ እና የመተዋወቂያ መርሃ-ግብር አካሄደ:: ነሐሴ 8፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ201
+2
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎቹ የቅበላ እና የመተዋወቂያ መርሃ-ግብር አካሄደ:: ነሐሴ 8፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎቹን የተቀበለ ሲሆን፣ ለነዚሁ ተማሪዎች የማስተዋወቂያ ወይም የኦሬንቴሽን መርሃ ግብር አካሂዷል።   በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተማሪዎች ከባድ ውድድርና ፈተናዎችን አልፈው አ.አ.ዩን በመቀላቀላቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡   አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሀገር እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂና ብቁ ምሁራንን በማፍራት ለሀገር ያበረከተ ተቋም መሆኑን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ከነዚህ ተማሪዎችም የተሻለ ስኬትን እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በትምህርታቸው የላቀ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ከጎናቸው እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡   የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የልማት እና ሙያ ማበልጸጊያ ጽህፈት ቤት ዳይሬክትር ዶ/ር ሽብሩ ተመስገን በበኩላቸው መርሃ ግብሩ  á‰°áˆ›áˆŞá‹Žá‰˝ ወደ ዋናው የመማር ማስተማር ሂደት ከመግባታቸው በፊት ሾለ ዩኒቨርሲቲው እና ሾለ አዲሱ አካባቢያቸው አስፈላጊ እና ትክክለኛ መረጃዎችን እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ገልጸዋል። ኦሬንቴሽኑ ቢሺፍቱ በሚገኘው የግብርና እና የእንስሳት ህክምና ኮሌጅ ጨምሮ በአምስት የተለያዩ ካምፓሶች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኝ የስራ አመራሮች በተገኙበት ተሰጥቷል፡፡   ዶ/ር ሽብሩ አክለውም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ  በሚኖራቸው ቆይታ መረጃዎችን ከዩኒቨርሲቲው ትክክለኛ የመረጃ ምንጮን እንዲያገኙ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በነፃነት መረተ  

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር «አፍሪካዊ የውሃ ዋስትና» ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ሊያካሂድ ነው። ነሐሴ 08፤2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) አዲስ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር «አፍሪካዊ የውሃ ዋስትና» ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ሊያካሂድ ነው። ነሐሴ 08፤2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር «African Water Security: Towards a Water-Security and Resilient Africa» በሚል መሪ ሀሳብ አህጉራዊ የውሃ ኮንፈረንስ (AWS-2026) ሊያካሂድ መሆኑን አስታወቀ። ኮንፈረንሱ ከሰንደቅ ዓላማ እስከ ፖሊሲ ማዕቀፎች ያሉ ጉዳዮችን የሚዳስስ ሲሆን፤ ከሰላም፣ ከልማት እና ከጸጥታ ጋር የተያያዙ አህጉራዊ የውሃ ፈተናዎችንና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለመዳሰስ ያለመ ነው። ሶስት ቀን በሚቆየው በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተውጣጡ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እና ምሁራንን ጨምሮ ከ300 በላይ የሚሆኑ ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ክንውኑ የሚካሄደው ከመስከረም 11 እስከ 13 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኘው ታሪካዊው አድዋ ሙዚየም ላይ እንደሆነ በመግለጫው ተገልጿል። በአንተነህ ጌታቸው

የተማሪዎች ቅድመ ዝግጅት በዩኒቨርሲቲ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት እና በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት የሚደረግ ጥሩ ዝግጅት የትምህርት ጊዜን ስኬታማ እና ሰላማዊ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው። ​ሰነዶችን ማደራጀት፡ የ12ኛ ክፍል ውጤት፣ የማትሪክ ሰርተፊኬት፣ የነዋሪነት መታወቂያ፣ የዩኒቨርሲቲ ጥሪ ደብዳቤ እና ጉርድ ፎቶግራፎችን በግልጽ እና በጥንቃቄ መያዝ። ​ምዝገባ ማጠናቀቅ፡ ወደ ካምፓስ እንደገቡ የወረቀትና የዲጂታል ምዝገባዎችን በወቅቱ ማጠናቀቅ እና የተማሪነት መታወቂያ (ID) መቀበል። ​የዶርም እና የካፌ አሰራርን ማወቅ፡ የተመደቡበትን የማደሪያ ክፍል ማወቅ፣ የዶርም ደንቦችን ማንበብ እና የካፌ ኩፖን/መታወቂያ ማስተካከል. ​የመኝታ እና የግል ቁሳቁሶች፡ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ፣ የንፅህና መጠበቂያዎች (ሳሙና፣ የጥርስ ቡሩሽ፣ ፎጣ) እና ተስማሚ አልባሳት። ​የትምህርት መሣሪያዎች፡ ደብተሮች፣ እስክሪብቶዎች፣ ፍላሽ ዲስክ፣ እንዲሁም ከተቻለ ላፕቶፕ ወይም ሳይንቲፊክ ካልኩሌተር። ​የበጀት እቅድ፡ ለመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ለተለያዩ ድገተኛ ወጪዎች (ለፎቶ ኮፒ፣ ለትራንስፖርት፣ ለጽህፈት መሳሪያዎች) የሚሆን መጠነኛ ገንዘብ አስቀድሞ ማዘጋጀት። ​3. የአካዳሚክ ዝግጅት ​የኮርስ ዝርዝር (Syllabus) መረዳት፡ በመጀመሪያው ሳምንት በሚሰጡ ገለጻዎች (Orientations) ላይ በመገኘት የትምህርት ፕሮግራሙን፣ የክሬዲት አወቃቀርን እና የፈተና ግምገማ መንገዶችን ማወቅ። ​የቤተ-መጻሕፍት እና የመማሪያ ክፍሎች ቦታ፡ ቤተ-መጻሕፍት (Library)፣ የኮምፒውተር ላብራቶሪዎች እና የመማሪያ ብሎኮች የሚገኙበትን ቦታ አስቀድሞ ማወቅ። ​የጊዜ ሰሌዳ ማውጣት፡ የመማሪያ ክፍለ-ጊዜዎችን (Timetable) መያዝ እና ለጥናት የሚሆን ቋሚ ጊዜ መመደብ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ትምህርት ቤት አገልግሎት ጀመረ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ1ኛ እስከ 7ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ጥራቱን የጠበቀና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት ለመስጠት ያቋቋመው የሞ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ትምህርት ቤት አገልግሎት ጀመረ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ1ኛ እስከ 7ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ጥራቱን የጠበቀና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት ለመስጠት ያቋቋመው የሞዴል ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት በይፋ አገልግሎት ጀምሯል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ትምህርት ቤቱ በሥነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ ከማፍራት ባለፈ፣ ቴክኖሎጂን የተጠቀመ ሁሉን አካታች የትምህርት ሥርዓት ለመተግበር ታስቦ መቋቋሙን ገልጸዋል። ትምህርት ቤቱ ከዚህ ባለፈ የትምህርት ምርምር ማዕከል በመሆን በትምህርት ዘርፍ ለሚወጡ ሀገራዊ ፖሊሲዎችና የትምህርት አሠራሮች ግብዓት የሚሰጥ ተቋም እንዲሆን መታሰቡን ተገልጿል። በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ ዩኒቨርሲቲው ይህን የሞዴል ትምህርት ቤት ማቋቋሉ ለሌሎች ተቋማት አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። የከተማው ትምህርት ቢሮም ከዩኒቨርሲቲው ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር ለሞዴል ትምህርት ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል። @Adis standard