en
Feedback
MAHIR | صَوْتُ الْحَقّ

MAHIR | صَوْتُ الْحَقّ

Open in Telegram

ISLAM IS THE SOLUTION OF HUMANITY

Show more
3 337
Subscribers
+624 hours
+37 days
+5530 days
Posts Archive
አታነቡም ግን አንብቡ እስኪ

የስነ ልቦና ህክምና ዋና አላማው ግለሰቦችን ማከም እና ወደ ማህበረሰቡ መደበኛ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ መመለስ ነው። ነገር ግን አንድ ግለሰብ ሊላመደው የሚገደደው ማህበረሰብ ራሱ በበሽታ የተበከለ ቢሆንስ? ችግሩ ያለው ስቃይ ላይ ባለው ግለሰብ አእምሮ ውስጥ ሳይሆን እብደቱን እና ስቃዩን በማምረት ላይ ባለው የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መዋቅር ውስጥ ከሆነስ? ​እንደ Michel Foucault እና Erich Fromm ያሉ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች እንደሚከራከሩት ዘመናዊው ማህበራዊ መዋቅር ሰዎችን ከተፈጥሮአዊ ማንነታቸው ከእውነተኛ ፍላጎቶቻቸው እና ከሌሎች ሰዎች ጋር ካላቸው ጥልቅ ግንኙነት ይነጥላቸዋል። ማህበረሰቡ ለውድድር፣ ለቁሳቁስ መሰብሰብ፣ ለውጫዊ ስኬት እና ማለቂያ የሌለው ድካም የሚሰጠው አክብሮት ሰዎችን ማሺን እንዲሆኑ ያስገድዳቸዋል። ​በዚህ አስከፊ የውድድር ሂደት ውስጥ የአእምሮ ጭንቀት ፣ ድብርት እና የባዶነት ስሜት መፈጠሩ ተፈጥሮአዊ ምላሽ እንጂ የግለሰቡ ጉድለት አይደለም። አእምሮው ለሚደርስበት መዋቅራዊ ጫና የሚሰጠው ጤናማ ተቃውሞ ሲሆን የ ስነ ልቦና ህክምናው ግን ይህንን ተቃውሞ እንደ በሽታ በመቁጠር ግለሰቡን መድኃኒት አሸክሞ እንደገና ለዚያው ጎጂ ስርዓት ብቁ ለማድረግ ይጥራል። ህንዳዊ ፈላስፋው ጂዱ ክሪሽናሙርቲ እንዳለው በጣም በታመመ ማህበረሰብ ውስጥ  መላመድ ወይም እንደነሱ መሆን የጤናማነት ምልክት አይደለም። ​ይሁን እንጂ ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ በማህበረሰቡ ላይ ብቻ መጫንም ሌላኛው አደገኛ እይታ ነው። በአንድ በኩል የሰው ልጅ ባዮሎጂያዊና አእምሮአዊ የኬሚካል መዛባቶች  ወይም የዘር ውርስ ተፅዕኖዎች በግል ህክምናና መድኃኒት መታገዝ እንዳለባቸው የማይካድ እውነታ ነው። ​ነገር ግን ዋናው ችግር የሚፈጠረው የህክምናው ዘርፍ ሁሉንም የሰው ልጅ የስነ ልቦና ስቃይ ወደ ባዮሎጂያዊ ምክንያት ብቻ ሲያሳንሰው ነው።  ብቸኝነት የኢኮኖሚ ውጥረት፣ የመደብ ልዩነት እና ትርጉም አልባ ልፋት ሰዎችን አእምሯዊ ስቃይ ውስጥ ሲከቷቸው መፍትሔው ማህበራዊ ሁኔታዎችን መቀየር እንጂ ግለሰቡን ብቻ ማስተካከል ሊሆን አይችልም።  ዘመናዊ የምንለው  ማህበረሰብ አእምሮአዊ ህመምን የሚያመርቱ ሁኔታዎችን እያፋጠነ በሌላ በኩል ደግሞ ከሲስተሙ ጋር ያልተግባቡትን ወይም ሲስተሙን ያልተቀበሉትን ሰዎች እንደ ጨለል መረዳቱ የተለመደ ነገር ሆኗል። መሆን ያለበት  ግለሰቡን እንደ ጨለል ማየቱን አቁመን የሚያበሳጨውንና እና የሚያናድደውን ማህበራዊ መዋቅር ለመፈተሽ ስንደፍር ብቻ ነው። ማህበረሰቡ ራሱ ህመምተኛ በሆነበት አለም ውስጥ ጤናማ መሆን እና አጉል ነገሮችን አልቀበልም ማለት ለሁኔታው የምንሰጠው ምላሽ እንጂ እ ብ ደ ት አይደለም።

አንብቡት ያው እምታነቡ ከሆነ

እኛ የትኛውን ነን? ━━━━━━━━ "Is he willing to prevent evil, but not able? then he is impotent. Is he able, but not willing? then he is malevolent. Is he both able and willing? whence then is evil?" — David Hume, Principal Writings on Religion... (Oxford University Press, 2008), pp. 100 ━━━━━━━ ✥ ━━━━━━━ "ክፋትን ለማስቀረት ፈቃደኝነቱ ኖሮት፣ ነገር ግን አቅሙ የለውም? እንግዲያውስ እርሱ ደካማ ነው። ክፋትን ለማስቀረት አቅሙ አለው፣ ነገር ግን ፈቃደኝነቱ የለውም? እንግዲያውስ እርሱ ክፉ ነው። ክፋትን ለማስቀረት አቅሙም ፈቃደኝነቱም አለው? እንግዲያውስ ክፋት ከየት መጣ?" ― ዴቪድ ሂዩም፣ ስለ ሃይማኖት የተጻፉ ዋና ዋና ጽሑፎች (2008 እ.ኤ.አ.)፣ ገጽ 100 ከላይ ያለውን ጥያቄ ያነሳው የ18ኛ ክፍለ ዘመኑ ዕውቅ የስኮትላንድ ፈላስፋ ዴቪድ ሂዩም ነው። በእርግጥ እሱ ይህንን ሙግት ያቀረበው በስነ-መለኮታዊ ትንታኔዎቹ ውስጥ ስለ አምላክ ባህርይ ሲመራመር ነው። ለጊዜው ግን የፈላስፋውን ሎጂክ ብቻ እንውሰድና በሰውኛ ለውጠን እናስበው። ስለ ፈጣሪ ሳይሆን፣ ስለ ራስህ ወይንም ስለ አንድ ማኅበረሰብ አድርገህ ብትጠይቀው ምላሽህ ምን ይሆን? በግለሰብ ደረጃ ራስህን ጠይቅ፦ • ክፋትን ለማስቀረት ፈቃደኝነቱ ኖሮህ፣ አቅሙ ግን ከሌለህ — አንተ ደካማ ነህ ማለት ነው! • ክፋትን ለማስቀረት አቅሙ ኖሮህ፣ ፈቃደኝነቱ ግን ከሌለህ — አንተ ክፉ ሰው ነህ ማለት ነው! • ክፋትን ለማስቀረት አቅሙም ፈቃደኝነቱም (ሁለቱም) ካለህ — እንዲያ ቢሆን ኖሮ፣ በዙሪያህ ክፋት ቦታ አይኖረውም ነበር! • የከፋው አራተኛው ደረጃ ደግሞ አለ፦ አቅምህን ሁሉ የምትጠቀምበት ክፋትን ለማምጣት ከሆነ — አንተ የለየልህ ዲያብሎስ (Evil) ነህ ማለት ነው! በሕዝብ (በሀገር) ደረጃስ? ይህንን መለኪያ ሰፋ አድርገን በአንድ ማኅበረሰብ ላይ ብንተገብረውስ? በአንድ ሕዝብ መሐል ክፋቶች ሁልጊዜ ከቀጠሉ፣ እውነታው ከእነዚህ አራቱ አንዱ ነው፦ • ደካማ ሕዝብ፦ ክፋትን የማስቀረት ፍላጎት አለው፣ ግን አቅሙ የለውም። • ክፉና ዳተኛ ሕዝብ፦ ክፋትን የማስቀረት አቅም አለው፣ ግን ፍላጎቱ (ቁርጠኝነቱ) የለውም። • ሠይጣናዊ ሕዝብ፦ ጉልበቱንና አቅሙን ሁሉ የሚያውለው ክፋቶችን ለመዝራትና ለማባዛት ነው። • ነፃና የነቃ ሕዝብ፦ ክፋትን የማስቀረት ፍላጎቱም አቅሙም አለው፤ በመሆኑም ክፋት ሊፈፀም የሚችልበት ዕድል ጠባብ ነው። በግልም፣ በሥራም፣ በማኅበራዊ ኑሮም፣ በሀገርም ደረጃ ሲፈፀሙ የምታያቸው ክፋቶች የየትኛው ውጤት ይመስሉሃል? እያንዳንዱን አካል በእነዚህ ጥያቄዎች አንፃር ብትመዝነው የዚያን አካል እውነተኛ ባህርይ በግልፅ ታየዋለህ። ታዲያ እኛ የትኛውን ነን? — ከባድ ጥያቄ ነው። መልሱን ለአንባቢ ህሊና ትቼዋለሁ። !!!!!!!

https://youtu.be/bOUvDZoxEPQ?si=SKg6zff9Q-PN3SnC አስቸክዋይ መልእክት ለ ህዝበ ሙስሊም ይደመጥ ሼር አድርጉት

ምናለ ረጅም ሰአት ባወራት ስልክ ምን አስቸኮለኝ ለመዝጋት 🥹

اللَّهُمْ صَلَّ وَسَلَّمَ عَلَى نَبِيْنَا وَحَبِيبِنَا مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِهِ وَصَحَبِهِ وَسَلَّمَ

تلاوة للقارئ علاء المزجاجي #إذاعة_القرآن_الكريم

وَمَا لَنَآ أَلَّا نَتَوَكَّلَ عَلَى ٱللَّهِ وَقَدۡ هَدَىٰنَا سُبُلَنَاۚ وَلَنَصۡبِرَنَّ عَلَىٰ مَآ ءَاذَيۡتُمُونَاۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُتَوَكِّلُونَ
And why should we not rely upon Allāh while He has guided us to our [good] ways. And we will surely be patient against whatever harm you should cause us. And upon Allāh let those who would rely [indeed] rely."
«መንገዳችንንም በእርግጥ የመራን ሲኾን በአላህ ላይ የማንመካ ለእኛ ምን አለን በማሰቃየታችሁም ላይ በእርግጥ እንታገሳለን፡፡ በአላህም ላይ ተመኪዎች ሁሉ ይመኩ፡፡»
#ተሳተፉ #تلاوةالقرآن #quran[62] #HollyQuran@mahir_Respond

እንዴ በልጅነቴ አግብቼ ነበር ለካ አሁን ፍልግዋት ዳይ 😭😁
እንዴ በልጅነቴ አግብቼ ነበር ለካ አሁን ፍልግዋት ዳይ 😭😁

አንድ ሰው ተሳዳቢ መሆኑ እየታወቀ ካፊር ቤት መግባት ከዛ እስልምና እየተሰደበ ረሱል እየተሰደቡ እዛ ቁጭ ማለት እና መከራከር መጮህ ወይ ገስት ሰትገቡ Private አታደርጉ በዲኑ ጠንካራ ያልሂነን ሙስሊም አስከትላቹህ መሄድ ! ሸሪዓው እንዴት ይመለከተዋል ? መልሱልኝ

https://youtu.be/Zq6Y5tz2f-g?si=0T20kCMdO8pssKqQ መልካም ሰው አዲስ ቪድዮ ሙሉወን ተመልከቱት ለሁሉም እንዲዳረስ ኡስታዝ አህምድ አደም

إِنَّ عِبَادِي لَيۡسَ لَكَ عَلَيۡهِمۡ سُلۡطَٰنٌ إِلَّا مَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلۡغَاوِينَ
«እነሆ ባሮቼ በእነሱ ላይ ላንተ ስልጣን የለህም፡፡ ከጠማሞቹ የተከተለህ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡»
وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمَوۡعِدُهُمۡ أَجۡمَعِينَ
«ገሀነምም (ለርሱና ለተከተሉት) ለመላውም በእርግጥ ቀጠሯቸው ናት፡፡
لَهَا سَبۡعَةُ أَبۡوَٰبٖ لِّكُلِّ بَابٖ مِّنۡهُمۡ جُزۡءٞ مَّقۡسُومٌ
«ለእርሷ ሰባት ደጃፎች አሏት፡፡ ለየደጀፉም ሁሉ ከእነሱ የተከፈለ ፋንታ አለ፡፡
إِنَّ ٱلۡمُتَّقِينَ فِي جَنَّٰتٖ وَعُيُونٍ
«እነዚያ (ከኀጢአት) የተጠነቀቁት በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡
ٱدۡخُلُوهَا بِسَلَٰمٍ ءَامِنِينَ
«ጸጥተኞች ኾናችሁ በሰላም ግቧት (ይባላሉ)፡፡
وَنَزَعۡنَا مَا فِي صُدُورِهِم مِّنۡ غِلٍّ إِخۡوَٰنًا عَلَىٰ سُرُرٖ مُّتَقَٰبِلِينَ
«ባልጋዎችም ላይ ፊት ለፊት የሚቅጣጩ ወንድማማቾች ኾነው በደረቶቻቸው ውስጥ ከቂም ያለውን ሁሉ እናስወግዳለን፡፡
#ተሳተፉ #تلاوةالقرآن #quran[61] #HollyQuran@mahir_Respond

እሄ ልጅ መሀመደረ ይባላል የ አክሱም ልጅ ነው አክሱም ላይ እህትህ ሂጃብ አትለብስም ብለው ክልክለው እሱን ደሞ በ ግድ አፍሰው ምንም ስልጠና ሳይሰጡ ወደ ጦርነት ምሸግ አስገቡት አላህ ሲወደወ ትረፍ
እሄ ልጅ መሀመደረ ይባላል የ አክሱም ልጅ ነው አክሱም ላይ እህትህ ሂጃብ አትለብስም ብለው ክልክለው እሱን ደሞ በ ግድ አፍሰው ምንም ስልጠና ሳይሰጡ ወደ ጦርነት ምሸግ አስገቡት አላህ ሲወደወ ትረፍ ሲለው መተኮስ እማያቅ ልጅ ከስንት ድሮን ጥይት ተርፎ ተገኘ የ አፍር ሰራዊት እና TPF እሚባሉ ማረኩት ቪድዮ ላይ ልጁ ከመደንገጡ የተነሳ እየተንቀጠቀጠ በ አላህ ምንም አላቅም ይላል ልጁ ደሞ የማረከው አይዞህ እኔም የትግራይ ልጅ ወንድምህ ነኝ አይዞህ እያለ እያቀፈ ያፅናናዋል አላህየ ሰላም አድርገው ሀገራችንን

እሄ ሰወየ የሆነ ሰሙን ንፅፅር ቤት ሲገባ ሳየው ነበር ምን አይነት ድነቁርና ነው ሰው ቢሞት ቢጨፈጨፈም እንዳተለቅሱ ብሎ ማለት ?
እሄ ሰወየ የሆነ ሰሙን ንፅፅር ቤት ሲገባ ሳየው ነበር ምን አይነት ድነቁርና ነው ሰው ቢሞት ቢጨፈጨፈም እንዳተለቅሱ ብሎ ማለት ?

ሙሉ አድምጡት እና እስኪ የተሰማችሁን በ አጭሩ አስቀምጡ ሌላም ሰው እንዲማር የኔ ዕንቁ ልጆች 😇

https://youtu.be/_2F9EjYNN4Q?si=H1VoFGPdSKvfBVXy ኡስታዝ አህመድ አደም አመስግን ሁሉም ይስማው ሙሉወን አድምጡት ለሁሉም እንዲዳረስ

ተራ ውግያ እንዳይመስላቹህ ኤርትራ ዱባይ አሜሪካ ጁብቲ ግብፅ ኢ/ያ ሶማልያ ሱዳን እምያደርጉት እልቂት ነው ሁሉም ወገን ድሮን ታንክ መድፍ ይዞ ነው የዘመተው አላህ ከዚህ ይጠብቀን በዙህ ጥዋት ብቻ በ 1 ሰአት ብቻ መቀሌ ውስጥ 30 ግዜ የድሮን ድብደባ ተደርግዋል

ትግራይ ሙሉ በ ሙሉ ድጋሚ ጦርነት ተነስትዋል መንገድም ባንክም ምንም የለም ጨርጨር ሮቃ አፍር ሽረ ፀለምት ሙሉ ዙርያ በድሮን እና ጀት የታገዛ ከፍተኛ እልቂት ውግያ እየተካሄደ ነው ባለፈው ሶስት አ
ትግራይ ሙሉ በ ሙሉ ድጋሚ ጦርነት ተነስትዋል መንገድም ባንክም ምንም የለም ጨርጨር ሮቃ አፍር ሽረ ፀለምት ሙሉ ዙርያ በድሮን እና ጀት የታገዛ ከፍተኛ እልቂት ውግያ እየተካሄደ ነው ባለፈው ሶስት አመት በነበረው ጦርነት 1 ሚልዮን ሰው እንደሞተ የ አለም ሰብ አዊ መብት ድርጅት ገልጦ ነበር አሁን ደሞ የከፍ ይሆናል ። አላህ ሰላም ያድርግልን ሀገራችንን