አሻራ Technology™
Open in Telegram
⚡️Empower Your Tech Journey with @ashara_technology 🎮📲💻❗️ 🔹Technology-based news, 🔹Daily tech tips & tricks, 🔹Tutorials, 🔹Software updates & reviews &..... 👉Join our community of tech dive into the exciting world of technology together.🚀🚀
Show more221
Subscribers
+424 hours
+27 days
+1530 days
Posts Archive
Fully Funded BSc Scholarship in Harar for Ethiopian Grade 12 & TVET Graduates
MfM-ATTC in Harar offers full scholarships for technology degrees to Grade 12 graduates, remedial students, and Level IV COC holders.
Programs:
📌 BSc Automotive Technology
📌 BSc Electrical & Electronics Technology
📌 BSc Manufacturing Technology
Benefits:
🔹 Full tuition, free dormitory, and meals
🔹 Practical education (70% practical, 30% theory)
🔹 Employment/entrepreneurship support
🔹 High national exam success rate
Eligibility:
🔸 Grade 12 completers (2015–2018 EC) with admission results
🔸 Remedial Tutorial passers (2015–2018 EC)
🔸 Level IV COC holders with 2+ years relevant experience
🔸 Female applicants encouraged
Exam: September 16, 2026 (Math, English, Physics)
Location: Harar, Ethiopia
Deadline: September 10, 2026
🔗 Apply: https://mfmattc.edu.et/?p=2830
Share with interested individuals. 🙏
@ashara_technology
Google Assistant ሊዘጋ ነው!
ግዙፉ የቴክኖሎጂ ድርጅት Google በብዙ ሚሊዮን አንድሮይድ ተጠቃሚዎች ለዓመታት ስንጠቀምበት የነበረውን Google Assistant ሙሉ በሙሉ ሊዘጋው መሆኑን ይፋ አድርጓል። በአዲሱ የGenerative AI Gemini እንደሚተካ ተገልጿል።
አሁን ላይ በአንድሮይድ ስልኮች እና ስማርት device ላይ ዋናው የድምፅ ረዳት (Default Voice Assistant) ሆኖ የሚሰራው Gemini ነው።
የGoogle Assistant ሞዴል አሁን ካለው የGenerative AI ቴክኖሎጂ ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ ተጠቃሚዎች ሙሉ በሙሉ ወደ Gemini እንዲሸጋገሩ ጉግል ግፊት እያደረገ ይገኛል።
ኩባንያው አገልግሎቱን September 2026 ከአገልግሎት ውጪ እንደሚያደርገው 9to5Google ዘግቧል።
ትራምፕ ጨረቃን “የእኛ ናት” ማለታቸው አነጋጋሪ ሆኗል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ማህበራዊ ገጻቸው ላይ ጨረቃ የአሜሪካ ንብረት መሆኗን በመግለጽ “ጨረቃ የኛ ናት” የሚል ጽሑፍ እና የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ ያለበትን ምስል አጋርተዋል። ከዚህ ልጥፍ ጥቂት ደቂቃዎች በፊትም፣ ለአሜሪካ የጠፈር ኃይል (Space Force) የተዘጋጁ አዲስ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የዩኒፎርም ምስሎችን ይፋ አድርገዋል። ይህ የጨረቃ የይገባኛል ጥያቄ እና ዩኒፎርሞቹ ከታዋቂው ፊልም ከ«ስታር ዋርስ» (Star Wars) ወታደሮች ጋር በመመሳሰላቸው በማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ መሣለቂያና መነጋገሪያ ሆነዋል። ይሁን እንጂ፣ አሜሪካን ጨምሮ ከ100 በላይ አገሮች የፈረሙት የ1967ቱ የውጪ ጠፈር ስምምነት ማንም አገር ጨረቃን ወይም ሌሎችን የሰማይ አካላት በባለቤትነት መያዝ እንደማይችል በግልጽ ይከለክላል።
አእምሮን ከኮምፒውተር ጋር የሚያገናኘው "NEO" ቴክኖሎጂ ለገበያ ቀረበ ቻይና የሳንቲም ያህል መጠን ያለው እና አእምሮን ከኮምፒውተር ጋር የሚያገናኝ "NEO" የተባለ ቴክኖሎጂ ለገበያ እንዲቀርብ ፈቃድ ሰጥታለች። በጽንግሁዋ ዩኒቨርሲቲ እና በኒውራክል ቴክኖሎጂ የተሰራው ይህ መሳሪያ፣ የሰዎችን የእንቅስቃሴ አቅም ለመመለስ ለገበያ እንዲቀርብ ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው በአእምሮ ውስጥ የሚተከል ቴክኖሎጂ ሆኗል። የኢሎን መስክ ኒውራሊንክ (Neuralink) አሁንም በሙከራ ላይ ባለበት ወቅት፣ ይህ መሳሪያ ደህንነቱ የተጠበቀ በመሆኑ ቀድሞ የንግድ ፈቃድ ማግኘት ችሏል። ይህ ቴክኖሎጂ ሙሉ በሙሉ የእጅና የእግር ሽባነት ላጋጠማቸው ሰዎች የሚጠቅም ሲሆን፣ የአእምሮ ሕብረ ሕዋሳትን ሳይጎዳ በውጫዊው ሽፋን ላይ ብቻ በማረፍ ይሰራል። በሆስፒታሎች በተደረጉ ሙከራዎችም ታካሚዎች በሃሳባቸው ብቻ ዕቃዎችን በመጨበጥ መብላትና መጠጣት እንዲችሉ በማድረግ ሙሉ ስኬት አሳይቷል።
🚀 GCI World September 2026 — Registration is NOW OPEN!
Exciting news! 🎉 Registration for GCI World September 2026 has officially started.
🎓 Want to build valuable skills and join the GCI community? Now is the perfect time to apply!
⚠️ Important: When registering, make sure you use the invitation code provided below:
🎟️ Invitation Code:
X8TGQG
👉 Apply now and secure your spot! 🚀
If you’ve completed the GCI course, don’t keep this opportunity to yourself! 🔥 Share it with your friends, classmates, and university peers who may benefit from the program.
⏰ Registration Deadline: September 10, 2026
✨ Don’t miss out — register today and take the next step with GCI World!ኢሎን መስክ: AI በ2027 ከሰው በላይ አቅም ይኖረዋል! ኢሎን መስክ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እጅን በመጠቀም አካላዊ ንክኪ ከማይጠይቁት የኮምፒዩተር ስራዎች ውጭ ማንኛውንም ዲጂታል ስራ ከሰው በላይ በሆነ ፍጥነትና ጥራት መስራት የሚችልበት ደረጃ ላይ በ2027 ዓ.ም. መጨረሻ እንደሚደርስ ተናግሯል። ይህንን ሃሳብ መጀመሪያ በኤክስ (X) ገጹ ያጋራው ሲሆን፣ በኋላም በጂ20 ጉባኤ ላይ እንደተናገረው፣ AI ሶፍትዌር በመጻፍ ረገድ ከሰው ልጅ ጋር ፈጽሞ የማይወዳደርበት ደረጃ ላይ ይደርሳል። መስክ የዚህን ቴክኖሎጂ አቅም ከኃይለኛው የቼዝ ጨዋታ ማሽን ጋር በማወዳደር፣ በኮምፒዩተር ፕሮግራሚንግ ከ AI ጋር መወዳደር እንደማይቻል ገልጿል። የእሱ ትንበያ ትኩረቱን በዲጂታል ስራዎች ላይ ብቻ ያደረገ ሲሆን፣ አካላዊ ንክኪ የሚጠይቁ የጉልበት ስራዎችን ግን ከዚህ አቅም ውጭ አድርጓቸዋል።
WATCH : Tesla unveiled its two-seater Cybercab at an event in Texas, offering a closer look at the autonomous vehicle that CEO Elon Musk has said is key to transforming the company into a dominant force in driverless vehicles reut.rs/4x3RLp1የትራምፕ ፊት ያለበት $1 ሳንቲም‼️
አሜሪካ የዶናልድ ትራምፕ ፊት ያረፈበት የአንድ ዶላር ሳንቲም ይፋ አደረገች።
ይህ ሳንቲም፣ በአገሪቱ ገንዘብ ላይ በህይወት ያለ ሰው ሲታይ ከ200 ዓመታት ገደማ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ያሳያል።
በአሜሪካ የገንዘብ ኖቶች ላይ የሚሰሙ ግለሰቦች ብዙ ጊዜ ህይወታቸው ያለፈ ግለሰቦች ወይም መሪዎች ሲሆን ትራምፕ በህይወት እያሉ ይህ መደረጉ ትክክል እንዳልሆነ ተቃውሞ እየተሰማ ይገኛል።
"የኤአይ ቴክኖሎጂ እንደ ውሃና
ኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ሊታይ ይገባል"
ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እንደ ውሃ፣ መንገድ እና ኤሌክትሪክ ሁሉ የሀገራት መሠረተ ልማት አካል ሊሆን እንደሚገባ የኤንቪዲያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጄንሰን ሁዋንግ ገለጹ። በሰሜን ካሮላይና በተካሄደው የጂ20 የቴክኖሎጂ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ሁዋንግ፤ የዳታ ማዕከላትን በብዛት መገንባት አማራጭ የሌለው የሞት ሽረት ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
እንደ ሁዋንግ ገለጻ፣ እነዚህ የዳታ ማዕከላት ለተማሪዎች፣ ኢንዱስትሪዎችና ስታርታፖች ወሳኝ የዲጂታል አቅም የሚሰጡ ናቸው። ሀገራት ቴክኖሎጂውን በፍርሃት ከመመልከት ይልቅ እድሎቹን መጠቀም እንዳለባቸው ያሳሰቡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በዘርፉ ወደኋላ መቅረት የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነትን እንደሚያሳጣ አስጠንቅቀዋል።
EAII-
"My Seed" የተሰኘ የሞባይል ስልክ መተግበሪያ ይፋ ተደረገ! በማህበራዊ ሚዲያ «ቲቸር ዳኒ» በሚል ስሙ የሚታወቀው መምህር ዳኛቸው ሻምበል፣ ተማሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በስልካቸው በቀላሉ ትምህርት የሚከታተሉበትን "My Seed" የተሰኘ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ማድረጉን ገለጸ። መተግበሪያው በተለይም ከአምስተኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የተዘጋጀ ሲሆን በገጠርም ሆነ በከተማ የሚገኙ ተማሪዎችን በቴክኖሎጂ ታግዞ እኩል የትምህርት እድል ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልጿል። በላይ የተጫነው ይህ መተግበሪያ ተማሪዎች የሀገሪቱን የትምህርት ካሪኩለም መሰረት ያደረጉ ትምህርቶችን አሰልቺ ባልሆነና ልክ እንደ ፊልም የተቃኙ ማራኪ ቪዲዮዎች አማካኝነት እንጅ በማድረግ እንዲማሩ ተደርጎ የተቃኘ ነው። ከተለመዱት የትምህርት አይነቶች በተጨማሪ የመንፈስ ጥንካሬና አስተሳሰብን የሚያጎለብቱ የማይንደሴት ስልጠናዎችን እንዲሁም ተማሪዎች ወደፊት መሆን የሚፈልጉትን ሙያ እንደ ዶክተር ኢንጂነርና ፓይለት የመሳሰሉትን እንዲረዱ የሚያስችሉ ትምህርቶችን አካቷል። አፕሊኬሽኑ በአሁኑ ወቅት በአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን ወደፊትም እያንዳንዱ ተማሪ በአፍ መፈቻ ቋንቋው እንዲማር ለማስቻል በሌሎች አራት የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል። አፕሊኬሽኑን ተጠቃሚ ለማድረግ በቀረበው እቅድ መሰረት ተማሪዎች በወር 399 ብር ክፍያ በመፈፀም ሁሉንም የትምህርት አይነቶች ማስታወሻዎችንና የልምምድ ጥያቄዎችን ማግኘት ይችላሉ። በተጨማሪም በኔትወርክ ችግር ምክንያት የዳታ እጥረት እንዳይገጥማቸው ቪዲዮዎችን አንድ ጊዜ ዳውንሎድ በማድረግ ያለ ኢንተርኔት ኮኔክሽን መከታተል የሚችሉበት አሰራር የተዘረጋ ሲሆን በቅርቡም ሙሉ በሙሉ ዳታ በማይስፈልግበት መልኩ አገልግሎቱን ለማስፋፋት እየሰራ መሆኑን መምህር ዳኛቸው አስታውቋል። ተማሪዎችን ለማበረታታትም በአመቱ መጨረሻ የተሻለ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተጠቃሚዎችን በልዩ መስፈርት በመምረጥ የመኪና ሽልማት የሚያበረክት "መማር ያሸልማል" የተሰኘ ፕሮግራም ማዘጋጀቱ ተገልጿል። @ashara_technology
ኦርቢክስ ቴክኖሎጂስ የኢትዮጵያን ከተሞች የሚያዘምኑ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ይፋ አደረገ በኢትዮጵያ ከተሞች እየታየ ያለውን ፈጣን እድገትና የመሰረተ ልማት ስፋት ተከትሎ፣ የዜጎችን የእለት ተእለት ህይወት እና የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያቀልሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን ይዞ መውጣቱን ኦርቢክስ ቴክኖሎጂስ አስታወቀ። የኦርቢክስ ቴክኖሎጂስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ስዩም ተስፋዬ እንደገለጹት፣ ድርጅታቸው እንደ ስታርትአፕ ካምፓኒ የዜጎችን እለታዊ እንግልት የሚቀንሱ እና ከተሞችን ዘመናዊ የሚያደርጉ አራት ዋና ዋና የቴክኖሎጂ አሰራሮችን አስተዋውቋል። እንደ አቶ ስዩም ማብራሪያ፣ የመጀመሪያው የቴክኖሎጂ መፍትሄ የመኪና ማቆሚያ ወይም የፓርኪንግ ችግርን የሚያቃልል ነው። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ዋና ዋና ከተሞች የተገነቡ የፓርኪንግ ቦታዎች ቢኖሩም፣ አሽከርካሪዎች በቅጽበት ትክክለኛውን መረጃ ለማግኘት እንደሚቸገሩ ጠቁመዋል። ኦርቢክስ የሰራው ስርዓት ግን የግል እና የመንግስት የፓርኪንግ ቦታዎችን ወደ አንድ ማዕከላዊ የመረጃ ቋት በማምጣት አሽከርካሪዎች ባሉበት ሆነው ክፍት ቦታዎችን በስልካቸው እንዲያዩ፣ እንዲይዙ እና ያለምንም ሰው ንክኪ በራሳቸው አገልግሎት አግኝተው እንዲወጡ ያስችላቸዋል ብለዋል። ሌላው ሁለተኛው ስራ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ ወይም የቻርጂንግ ስርዓትን ማዕከላዊ ማድረግ ሲሆን ኢትዮጵያ እስከ 2030 ድረስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ስራ ለማስገባት እና በርካታ የኃይል መሙያ ጣቢያዎችን ለመገንባት ባስቀመጠችው እቅድ መሰረት፣ አገልግሎቱ በተበታተነ መልኩ እንዳይሰጥ "ኦርቢክስ ኢቪ "የተሰኘ የተቀናጀ መተግበሪያ አልምቷል። አቶ ስዩም አክለውም፣ ይህ ስርዓት ተጠቃሚዎች በአንድ መተግበሪያ ብቻ የትኛውም ቦታ የሚገኝ የኃይል መሙያ ጣቢያን እንዲጠቀሙ ከማድረጉም በላይ፣ የአገሪቱን የኢነርጂ መረጃ ደህንነት በአገር ውስጥ የመረጃ ቋት ውስጥ ጠብቆ ለማቆየት እና የመንግስት አካላት የኃይል ፍጆታውን በአንድ ማዕከል እንዲከታተሉ የሚያስችል እንደሆነ ገልጸዋል። በሶስተኛ ደረጃ የቀረበው «አይ ሀብ» የተሰኘው የዜጎችና የመንግስት ግንኙነት ማጠናከሪያ መድረክ ሲሆን፣ ነዋሪዎች በመንገድ፣ በኤሌክትሪክ፣ በትራፊክ በድንገተኛ አደጋዎች ላይ የሚያዩአቸውን ችግሮች እና መረጃዎች በስልካቸው ለሚመለከተው የመንግስት አካል በቀጥታ እንዲያደርሱ ያደርጋል። ስርዓቱ መረጃዎችን በየአካባቢው ክልል በመለየት እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመተንተን ለአስፈጻሚ አካላት የሚልክ በመሆኑ፣ ለቀረቡት ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እና በህዝብና በመንግስት መካከል ያለውን እምነት ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። «ኢትዮ ፓርክስ» የተሰኘው አራተኛው የቴክኖሎጂ ማዕቀፍ፣ በከተሞችና ከከተሞች ውጭ ያሉ የተፈጥሮ፣ የባህል እና የቪዲዮ መዝናኛ ቦታዎችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች የሚያቀርብ ነው። ተጠቃሚዎች የፓርኮችን መረጃ፣ የሚሰጡትን አገልግሎት እና የመግቢያ ክፍያዎችን አስቀድመው በመተግበሪያው በማጠናቀቅ የሚፈልጉትን መዝናኛ በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። አቶ ስዩም ተስፋዬ ሲደመድሙ፣ ኦርቢክስ ተራ መተግበሪያ ሳይሆን አጠቃላይ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን የሚደግፍ እና ወደፊት ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ለማስፋፋት የታቀደ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ምህዳር መሆኑን አብራርተዋል። 📸 ከበደ መክብብ @ashara_technology
