የሽቶ ገለፃ | አሮማ ሽቶ
Open in Telegram
Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
208
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
+2
Emporio Armani Stronger With You Intensely — የጥልቅ ፍቅርና የስሜት ኃይል ሽቶ
Stronger With You Intensely በ2019 የተለቀቀ ሲሆን፤ የመጀመሪያውን Stronger With You ሽቶ ወደ ከፍ ያለ ደረጃ የሚያደርስ እና የበለጠ ጠንካራ ስሜት የሚያቀርብ ነው። ይህ ሽቶ ቀላል ፍቅርን አይናገርም — ጥልቅ፣ የማይጠፋ እና የሚቀጥል ግንኙነትን ይወክላል።
Armani ይህን ሽቶ ሲፈጥር፣ ፍቅር በጊዜ ሲያድግ እና ሲጠነክር የሚፈጠረውን ስሜት ለማሳየት ነበር። Stronger With You Intensely የሚያሳየው ፍቅር ጊዜን የሚያሸንፍ፣ ሙቀትና መሳሳብ ያለው እና በልብ የሚቀር ነው። ይህ ሽቶ ሁለት ሰዎች መካከል ያለ ጠንካራ ትስስርን ይወክላል።
ይህ ሽቶ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ የሚስብ የመዓዛ ጉዞ ያቀርባል።
Top Notes - Pink Pepper, Juniper, Violet Leaf
ሲጀምር በPink Pepper ነቃ የምታረግ ጣፋጭ ቃና፤ ንፁህ አረንጓዴ ስሜት በሚሰጠው Juniper ቃና እና አሮማቲክ በሚያደርገው Violet Leaf ለስለስ ብሎ ይጀምራል
Heart Notes - Toffee, Cinnamon, Lavender, Sage
ከቆይታ በኋላ ወደ ዋናው ማራኪ ሽታው ሲገባ የToffee እና Cinnamon ቃና ጣፋጭና ሞቅ ያለ ያደርጉታል። Lavender እና Sage ጥፍጥናው መጠኑን የጠበቀ እንዲሆን ያረጋጉታል።
Base Notes - Vanilla, Amber, Tonka Bean, Suede
የመጨረሻው መዓዛ በVanilla እና Tonka Bean ክሬም የመሰለ ምቾት ያለው ጥፍጥና ይሆናል። Amber እና Suede የጠለቀ መዓዛ እንዲሆንና አብሯቹ የሚቆይ ሽታ ያደርገዋል።
በአጠቃላይ፣ ይህ ሽቶ ጣፋጭ (gourmand)፣ ቅመም እና ሞቃት የሆነ ባህሪ አለው።
ይህን ሽቶ ለምሽት ቀጠሮዎች (Date Night) አማላይ እና ሳቢ ሽታ ይሰጥሃል። በቀዝቃዛ አየር ሞቅ ያለ ገፅታ ያላብስሃል። ለልዩ ዝግጅቶች፣ ፌስቲቫል፣ ፓርቲ እና ክለብ ተጫዋችነትህን ያንፀባርቅልሃል።
እድሜያቸው ከ20–35 ዓመት ላሉ፤ ጣፋጭና ሞቃት ሽቶ ለሚወዱ፤ ጮክ የማይል፣ ግን የሚታወስ ሽቶ ለሚፈልጉ ወንዶች የሚመች ሽቶ ነው።
ሽቶው ሙቀትና ምቾት፤ መሳብና መተማመንን፤ ጣፋጭ ሴክሲነትን ይወክላል።
Stronger With You Intensely ሰዎችን ወደ አንተ የሚስብ ሽቶ ነው — አይገፋም፣ ያቀርባል።
+2
PRADA PARADOXE INTENSE
💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕
በ2023 የተለቀቀችው Paradoxe Intense የዋናዋ Paradoxe EDP ሃብታም እና ድራማቲክ ታላቅ እህት ነች። ከተለቀቀች ጀምሮ የብዙዎችን አንገት ስታዞር የምትገኝ ሽቶ ናት። በIntense ስትሰራ የPradaን የParadoxe DNA ከፍ ወዳለ መድረክ አውጥታለች። የለስላሳ አበባዎች እና ሞቅ ያለ ድምቀት ውህድ አይረሴ ገፅታን አላብሷታል።
Prada እንዳብራሩት Paradoxe Intense የተሰራችው በጥንካሬ እና በልስላሴ ላይ ያተኮረ ፓራዶክስ በሆነ መሰረት ነው። ሃሳባቸው ከመጀመሪያዋ Paradoxe የሚጮህ ሽቶ መስራት ሳይሆን፤ በጥንካሬ እና በልስላሴ መሃል ያለውን ስሜታዊ ስበት ለማሳየት ነው። ሃይለኛ ግን ምቹ፤ የተራቀቀ እና የማይረሳ ስሜትን ለመወከል… ። ሽቶዋ የሚቃረኑ ስሜቶችን የምታወድስ ናት።
የሸቶ ቀማሚዎች — Nadege Le Garlantezec፣ Shyamala Maisondieu እና Antoine Maisondieu ከመጀመሪያዋ Paradoxe የአበባ መዓዛ ልቧ ወስደው የበለጠ ስምጥ እንድትሆን እና በሚፈነድቁ አበባዎች መሃል በንጋት እንደመራመድ አይነት ስሜት እንድትፈጥር አድርገዋታል።
Top Notes - Pear, Neroli, Bergamot
አጀማመሯ የPear ጥፍጥና ከNeroli ሲትረስ ቃና ያለው አበባ እና የBergamot የሚያብለጨልጭ ቃና ጋር ፈካ ያለ እና ነቃ የሚያደርግ መዓዛ ትለቃለች።
Heart Notes - Jasmine, Neroli Essence, Moss
የParadoxe Intense ልቧ እዚ ይጀምራል። የአበባ ቃናዋ እና ሚስጥራዊነቷ ይታያል። የJasmine ረቀቅ ያለ ጥፍጥና፤ የNeroli Essence አረንጓዴ ስሜት የሚጭር እና ለሙሉ መዓዛው ምቾት የሚሰጥ ቃና፤ Moss ደሞ ሁሉንም ቃናዎች መረጋጋት ውስጥ የሚከት ቃና የParadoxe Intense ዋና መንፈሷ ነው።
Base Notes - Amber, Vanilla, Ambrofix, Serenolide
እዚጋ ሙሉ መዓዛዋ ስምጥ የሚሆንበት፤ ሞቅታ የሚያይልበት ነው። Amber እና Vanilla ስሜት ያዘለች እንድትሆን ሲያደርጉ፤ Ambrofix እና Serenolide ደሞ ረጅም ቆይታ እና አየር ላይ የመንሳፈፍ አቅሟ ላይ ይጨምራሉ።
Paradoxe Intenseን የምታደረጊው ሁሌ እንድትታወሺ ስትፈልጊ ነው። ሞቅታ እና ስምጠቷ ለምሽት ፕሮግራሞችሽ፣ ለልዩ አጋጣሚዎችሽ፣ ለቀዝቃዛ ወቅቶች እና መጥኖ መቀባት ከቻልሽ ለቀን በቀንም ትሆንሻለች።
Paradoxe Intense ከ20-40 አመት ላሉ ሴቶች እጅጉን ትመቻለች። ትዊስት ያለው ረቀቅ ያለ ስሜት ውስጥ ታስገባሻለች። የገቡበትን ቦታ መቆጣጠር ለሚወዱ የተሰራች ናት። ለአይናፋር ሴት አትሆንም። ቃላቶች ሳይወጣሽ ለመናገር ዝግጁ ከሆንሽ ብቻ ሞክሪያት። በተጨማሪም ልዩ የአበባ ሽቶ ለሚወዱ ሴቶች ትሆናለች።
በራስ መተማመን ሽቶ ብትሆን Paradoxe Intense ናት። ምቾት እና ልስላሴ ያለው ጥንካሬ ታላብስሻለች። ሽቶ ብቻ አይደለችም፤ ራሷን የቻለች ስሜት ናት። በአላማ እና ቆራጥነት ለምትጓዘው እንስት የተከሸነች ናት። ዘመናዊ እና ቅንጦታዊ ደረጃ ላይ የምታስቀምጥሽ ምርጥ ፓራዶክስ የሆነች ሽቶ ናት።
YSL Libre Intense
በሽቶ አለም ላይ ወደ 4 አመት ሳሳልፍ ካስተዋልኩት ነገር አንዱ... ደምበኞቼ የYSL Libre Intense ማብራሪያ አይፈልጉም። ቀጥታ ሽቶ ለመግዛት ወስነው ነው የሚደውሉት።
ይህም የሆነው የሽቶዋ ኳሊቲ በየቦታው ስለሚያስተጋባ ነው። YSL Libre Intense ተጠቅማ ያልወደደቻት ሴት (ከትልቅ ይቅርታ ጋር) የሷን ሃያል መዓዛን የመቋቋም ድክመት እንጂ፤ የሽቶዋ አርኪ አቅሟ ድክመት አይደለም።
YSL Libre Intense በ2020 የተለቀቀች ዘመናዊ እና ክላሲክ መዓዛ ካላቸው ሽቶዎች ምድብ ውስጥ የምትገባ ልዩነቷ የተመሰከረላት ሽቶ ናት። ቅንጦታዊ ይዘት ያለው የአበባ ጥፍጥና የያዘች ሽቶ ስትሆን፤ በስምጥ መዓዛዋ በመላው አለም ተፈላጊ ሆናለች።
የተሰራችበት ቃናዎች 👇👇👇
Top Notes: Bergamot, French Lavender, Mandarin orannge
Heart Notes: Lavender, Moroccan orange blossom absolute, Jasmine sambac absolute, Orchid
Base Notes: Venezuelan tonka bean absolute, Bourbon Vanilla, Ambergris, Vetiver
ልክ እንደተቀባቿት... በበርጋሞት ፈካ ያለ ልኩን ያላለፈ የመንደሪን ጥፍጥና ታገኛላቹ።
ልቧ በአበባ ቃናዎች የተሞላ ሲሆን፤ ላቬንደር ከብርቱካን አበባ፣ ከጃዝሚን እና ከኦርካይድ ጋር ያለውን መዓዛ በህይወታቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ታሸቱታላላቹ። አጨራረሷ ሞቅ ያለ ስሜት የያዘ የቶንካ፣ ቫኒላ እና አምበርግሪስ ውህድ መዓዛ ጀባ ይላቿል።
ይህ ልዩ መዓዛዋ በቆዳ ላይ ከ10 ሰዓታት በላይ ይቆያል ብላቹ ስንቶቻቹ ታምኑኛላቹ?
ልብሳቹ ላይ ከሆነ ደሞ... ልቀቂኝ አልለቅም ሙግት ትጀምራላቹ።
ሽቶ እጠቀማለው ባይ ከሆንሽ እና YSL Libre Intense ከስብስብሸ ውጪ ከሆነች... "ለሙሉ" የጎደለሽ አንድ ነገር አለ።
Libre Intense ስትቀቢ የሰው ልብ ለማሸበር እንጂ፤ አንቺ እንድትርበተበቺ አይደለም እና ብር ከማውጣትሽ በፊት ልብሽን ደንደን አድርጊያት።
Afnan Historic Sahara
ይህ ሽቶ በ2025 የተለቀቀ አዲስ የAfnan ስሪት ሲሆን፤ ገና ከመምጣቱም ጥሩ ተቀባይነት እያገኘ ነው።
የParfums de Marly Althair መዓዛን አመሳስለው የሰሩበት ሙከራቸው ሲሆን፤ እስከዛሬ የFrench Avenue Liquid Brun የያዘውን የመዓዛ መቀራረብ በልጦ ተገኝቷል።
Historic Sahara ጣፋጭ ጎርማንድ መዓዛ ያለው ሽቶ ሲሆን፤ ለወንድም ለሴትም ተስማሚ ሽቶ ነው።
የተሰራበት ቃናዎች 👇👇👇
Top Notes: Bergamot, Cardamom, Cinnamon
Heart Notes: Elemi Resin, Sugar, Vanilla
Base Notes: Almond, Ambroxan, Musk, Chocolate, Tonka, Wood Notes
አጀማመሩ ላይ ፈካ ያለ ፍሬሽ ቅመም ቃና ሲኖረው፤ ከደቂቃዎች በኋላ ወደጣፋጭ እና ቫኒላ ቃና ይለወጣል። ወደ መጨረሻው የቸኮሌት እና ቶንካ ውህድ የሆነ ብሉኝ ብሉኝ ወደሚል ቃና ተቀይሮ ለሰዓታት ይቆያል።
ጠቅላላ መዓዛ እጅግ በጣም ማራኪ፤ ቆይታው ደግሞ አስደማሚ ነው። ልስልስ ያለ መዓዛ ቢይዝም ከ8 ሰዓታት በላይ በቆዳ ላይ፤ ለቀናት ደሞ በልብስ ላይ ይቆያል።
የመዓዛው ልስላሴ ለብዙ አጋጣሚዎች፣ ለቀን እና ለማታ አመቺ ያደርገዋል። እንደ መለያ መዓዛቹ (Signature Scent) መጠቀም ትችላላቹ።
የAfnan ምርት ስለሆነ የሽታው ጥራት አስደሳች ነው።
