Mahtot Eshetie / ማኅቶት እሸቴ
Open in Telegram
መንፈሳዊ የቤተክርስቲያን አስተምህሮና ሙሉ የግእዝ ቋንቋ ሥልጠና ትምህርት ማስተማሪያ የቴሌግራም ገጽ። በመደበኛ መርሐ ግብር የግእዝ ቋንቋ ሥልጠናን መከታተል የምትሹ በኮሜንት መስጫው ጻፉልኝ።
Show more4 635
Subscribers
+5624 hours
+1677 days
+17430 days
Posts Archive
#ጳጕሜን_እንዴት_ተገኘች_? በመጽሐፍ (PDF) ተለቀቀ።
ጳጕሜን 5 : 6 : 7 የመሆኗ ምሥጢር
በዚሁ በቴሌግራም ገጼ ያገኙታል።
ለወዳጆችዎ ሼር በማድረግ ተወዳጁን የጳጕሜን ምስጢር ይጋብዟቸው።
👇👇👇
የቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/MEBspiritualtraining21
👇👇👇
የፌስቡክ አድራሻ
https://www.facebook.com
© መ/ር ማኅቶት እሸቴ
ባሕረ ሐሳብን በቀላሉ በመጽሐፍ መልኩ ይጠቀሙ (pdf)
የ2019/ ፳፻፲፱ ዘመን የበዓላትና የአጽዋማት አወጣጥ ለሁሉም በሚረዳ መልኩ በግልጽና በቀላል መንገድ የቀረበ። እነሆ በመጽሐፍ መልኩ (PDF) በዚሁ በቴሌግራም ገጼ ያገኙታል።
ለወዳጆችዎ ሼር በማድረግ ተወዳጁን የባሕረ ሐሳብ ትምህርት ይጋብዟቸው።
👇👇👇
የቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/MEBspiritualtraining21
👇👇👇
የፌስቡክ አድራሻ
https://www.facebook.com
© መ/ር ማኅቶት እሸቴ
☝ ወደ ኋላ ልመልሳችሁና ትተናት የመጣን 6 ካልዒት አለች ይህችም በየዓመቱ የምትተርፍ ናት። ከዚች ተነስተን ጳጕሜን 7 የምትሆንበትን እናገኛለን።
በየዓመቱ 6 ካልዒት የምትገኘውን ትርፍ በ100 ዓመታት ልዩነቶች ስንት ልትሆን ትችላለች? በዚህም መሠረት ጳጕሜን 7 ስትሆን እናገኛለን።
➤ በ100 ዓመት ውስጥ ስንት ካልዒት ይገኛል?
✦6 × 100 = 600 ካልዒት ይሆናል
👉 600 ካልዒት ስንት ኬክሮስ ይሆናል?
60 ካልዒት = 1 ኬክሮስ
600 ÷60 = 10 ኬክሮስ
✦በ100 ዓመት 10 ኬክሮስ ይገኛል
✦በ200 ዓመት 20 ኬክሮስ
✦በ300 ዓመት 30 ኬክሮስ
✦በ400 ዓመት 40 ኬክሮስ
✦በ500 ዓመት 50 ኬክሮስ
✦በ600 ዓመት 60 ኬክሮስ ይሆናል።
60 ኬክሮስ = 1 ቀን
ስለዚህ በ600 መቶ ዓመት ጳጕሜን 7 ቀን ትሆናለች።
➤የሰአት ፣ የኬክሮስ ፣ የደቂቃ ፣ የካልኢት ፣ የሴኮንድ ፣ የሣልሲት ፣ የራብዒት ፣ የኃምሲት ፣ የሳድሲትን ዝምድና እንደሚከተለው ነው።
✤ 1 ቀን = 24 ሰዓት = 60 ኬክሮስ
✤ 1 ኬክሮስ = 60 ካልኢት
✤ 1 ካልኢት = 60 ሣልሲት
✤ 1 ሣልሲት = 60 ራብዒት
✤ 1 ራብዒት = 60 ኃምሲት
✤ 1 ኃምሲት = 60 ሳድሲት
✤ 1 ሰአት = 2.5 ኬክሮስ or
1 ኬክሮስ = 0.4 ሰአት
✤ 1 ደቂቃ = 2.5 ካልኢት or
1 ካልኢት = 0.4 ደቂቃ
✤ 1 ሴኮንድ = 2.5 ሣልሲት or
1 ሣልሲት = 0.4 ሴኮንድ
✤ 1 ሴኮንድ = 150 ራብዒት
✤ 1 ሴኮንድ = 9000 ኃምሲት
✤ 1 ሴኮንድ = 540000 ሳድሲት
© መ/ር ማኅቶት እሸቴ
ጳጕሜን 1 / 2018 ዓ.ም
👉 የቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/MEBspiritualtraining21
👇👇👇
የፌስቡክ አድራሻ
https://www.facebook.com
#ጳጕሜን_እንዴት_ተገኘች_?
5 : 6 : 7 የመሆኗ ምሥጢር
በሁለት አሰራር ወይም ሒሳባዊ ስሌት እናያለን።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ብቸኛዋ ባለ 13 ወር ናት።
ጳጕሜን ማለት ተረፍ ንዑስ (ትርፍ ፣ ታናሽ) ማለት ነው።
ጳጕሜን የተገኘችው በየቀኑ ከሚተርፉት ሽርፍራፊ ሴኮንዶች ነው።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
የመጀመሪያው የጳጕሜን ማግኛ መንገድ በሴኮንድና በደቂቃ አሠራር ነው።
፩ : በሴኮንድና በደቂቃ
መሠረታዊ የቀናት ስሌቶችን መሠረት በማድረግ በአንድ ቀን ውስጥ የሚተርፉ ደቂቃዎችና ሴኮንዶች ተጠራቅመው ጳጕሜን ያስገኙልናል።
➤1ቀን = 24 ሰዓት = 60 ኬክሮስ
➤ 1ቀን = 24 ሰዓት ከ52 ካልዒት ከ31 ሣልሲት ነው። በ1ቀን ውስጥ 52 ካልዒት 31 ሣልሲት ትርፍ አለ።
✦1ካልዒት = 0.4 ደቂቃ = 24 ሴኮንድ ነው።
✦ 1ሣልሲት = 0.4 ሴኮንድ ነው።
💥 በአንድ ቀን ውስጥ ያለውን 52 ካልዒት ወደ ሴኮንድ ስንቀይረው።
1ካልዒት 24 ሴኮንድ ከሆነ
52 ካልዒት ስንት ሴኮንድ ይሆናል?
52 × 24 ሴኮንድ = 1248 ሴኮንድ 48 ቱን ትተን 1200 ሴኮንድ ወደ ደቂቃ ስንቀይረው
20 ደቂቃ ይሆናል።
1248 ሴኮንድ = 20 ደቂቃ ከ48 ሴኮንድ
💥በአንድ ቀን ውስጥ ያለውን 31 ሣልሲት ወደ ሴኮንድ ስንቀይረው።
1ሣልሲት 0.4 ሴኮንድ ከሆነ
31 ሣልሲት ስንት ሴኮንድ ይሆናል?
31× 0.4 ሴኮንድ = 12.4 ሴኮንድ ይሆናል 12 ቱን ሴኮንድ ከላይ ካገኘነው ከ48 ቱ ሴኮንድ እንደምረዋለን።
💥 ቀሪዋ 0.4 ሴኮንድ ግን ትቆየን። ይህችንን የምንጠቀማት በኋላ ነው።
💎 በአንድ ቀን ውስጥ ያለው 52 ካልዒትና 31 ሣልሲት በጠቅላላው ወደ ደቂቃ ሲቀየሩ ድምር ውጤታቸው ይህ ነው።
▶52 ካልዒት = 20 ደቂቃ ከ48 ሴኮንድ
▶31 ሣልሲት = 12 ሴኮንድ
✍️ 25 ካልዒት + 31 ሣልሲት
= 20 ደቂቃ ከ48 ሴኮንድ + 12 ሴኮንድ
= 20 ደቂቃ ከ60 ሴኮንድ (60 ሴኮንድ = 1ደቂቃ)
= 21ደቂቃ ይሆናል።
💥ስለዚህም በአንድ ቀን ውስጥ የሚገኘው ትርፍ 21 ደቂቃ እና ከላይ የተውናት 0.4 ሴኮንድ ናት።
ይህ ማለት አንድ ቀን 24 ሰዓት ሆኖ 21 ደቂቃ ከ0.4 ሴኮንድ ትርፍ አለው።
በየቀኑ የምናገኛቸው ትርፎቹ ጳጕሜን ያስገኙልናል።
ይህንን መሠረት በማድረግ በአንድ ዓመት ውስጥ የሚተርፈውን ማወቅ እንችላለን።
➤አንድ ወር 30 ቀን ነው
➤12 ወራት ደግሞ 360 ቀናት ናቸው
ጳጕሜን የተገኘች ደግሞ ከ12 ወራት 13ኛ ወር ሁና ከ360 ቀናት 365 እና 366 ቀን ሁና ነው።
💥መጀመሪያ በየቀኑ የተረፈውን ደቂቃ መሠረት አድርገን እንሥራ።
በአንድ ቀን የተረፈው 21 ደቂቃ በዓመት ስንት ይሆናል?
✤ 21 × 360 = 7560 ደቂቃ ይሆናል
✤ 7560÷ 60 = 126 ሰዓት ይሆናል
✤ 126 ÷ 24 = 5ቀን ከ6 ሰዓት ይሆናል ወይም 120ው ሰአት 5 ቀን ነው ትርፍ 6 አለ።
➤ በአንድ ዓመት ውስጥ 5 ቀን ከ6 ሰዓት ትርፍ አለ። ይኼውም የጳጕሜን ቀናት ናቸው። ይህም የዓመቱን ቀን 365 ቀን ያደርገዋል። 6 ሰዓት ግን ትርፍ አለ።
በየዓመቱ የተረፈው 6 ሰዓት ደግሞ ምን እንደሚያስገኝ እንሥራ።
✦ በ1ኛው ዓመት 365ቀን ከ6 ሰዓት
✦ በ2ኛው ዓመት 365ቀን ከ12 ሰዓት
✦ በ3ኛው ዓመት 365ቀን ከ18 ሰዓት
✦ በ4ኛው ዓመት 365ቀን ከ24 ሰዓት ሲሆን ይህም 24ቱ ሰዓት 1ቀን በመሆኑ ዓመቱን 366 ቀን ያደርገዋል። በየአራት ዓመቱ ጳጕሜን 6 የምትሆን ከዚህ የተነሣ ነው።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
☝ ወደ ኋላ ልመልሳችሁና ትተናት የመጣን 0.4 ሴኮንድ አለች ይህችም በየቀኑ የምትተርፍ ናት። ከዚች ተነስተን ጳጕሜን 7 የምትሆንበትን እናገኛለን።
➤ በ12 ወር በ360 ቀናት ስንሠራት
0.4×360 = 144 ሴኮንድ ይህም በአንድ አመት የሚገኘው ትርፍ ሴኮንድ ነው።
➤ በ100 ዓመት ውስጥ ስንት ትሆናለች?
✦144 × 100 = 14400 ሴኮንድ = 240 ደቂቃ = 4 ሰዓት ።
✦በ200 ዓመት 8 ሰዓት
✦በ300 ዓመት 12 ሰዓት
✦በ400 ዓመት 16 ሰዓት
✦በ500 ዓመት 20 ሰዓት
✦በ600 ዓመት 24 ሰዓት (አንድ ቀን) ይሆናል። ጳጕሜን በ600 መቶ ዓመት 7 ቀን ትሆናለች።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ሁለተኛው የጳጕሜን ማግኛ መንገድ በካልዒትና በሣልሲት አሠራር ነው።
፪: በካልዒትና በሣልሲት
መሠረታዊ የቀናት ስሌቶችን መሠረት በማድረግ በአንድ ቀን ውስጥ የሚተርፉ ካልዒትና ሣልሲት ተጠራቅመው ጳጕሜን ያስገኙልናል።
➤1ቀን = 24 ሰዓት = 60 ኬክሮስ
➤ 1ቀን = 60 ኬክሮስ ከ52 ካልዒት ከ31 ሣልሲት ነው። በ1ቀን ውስጥ 52 ካልዒት 31 ሣልሲት ትርፍ አለ።
✔️ በየቀኑ የሚተርፈውን ካልዒት መሠረት በማድረግ በዓመት ምን ያክል ኬክሮስ እናገኛለን
☸️ በ1 ቀን 52 ካልዒት ከተረፈ በ30 ቀን ስንት ይሆናል?
30×52 = 1560 ካልዒት
ወደ ኬክሮስ ስንቀይረው በ60 እንገድፈዋለን ወይም ለ60 እናካፍለዋለን።
👉1 ኬክሮስ = 60 ካልዒት ነው።
1560 ካልዒት ስንት ኬክሮስ ይሆናል ?
1560÷60 = 26 ኬክሮስ።
☸️ በአንድ ወር ውስጥ 26 ኬክሮስ ከተገኘ በዓመት (በ12 ወር) ስንት ኬክሮስ ይገኛል ?
12×26 = 312 ኬክሮስ።
✔️ በየቀኑ የሚተርፈውን ሣልሲት መሠረት በማድረግ በዓመት ምን ያክል ኬክሮስ እናገኛለን
☸️ በ1 ቀን 31 ሣልሲት ከተረፈ በ30 ቀን ስንት ይሆናል?
30×31 = 930 ሣልሲት
☸️ በ1 ወር 930 ሣልሲት ከተረፈ በአንድ ዓመት (12 ወር) ስንት ይሆናል?
12×930 = 11160 ሣልሲት
ወደ ካልዒት ስንቀይረው በ60 እንገድፈዋለን ወይም ለ60 እናካፍለዋለን።
👉1 ካልዒት = 60 ሣልሲት ነው።
11160 ሣልሲት ስንት ካልዒት ይሆናል ?
11160÷60= 186 ካልዒት
ይህንን ወደ ኬክሮስ መቀየር እንችላለን
👉1 ኬክሮስ = 60 ካልዒት
186 ካልዒት ስንት ኬክሮስ ይሆናል ?
186 ካልዒትን በ 60 መግደፍ ወይም ለ 60 ማካፈል።
186 ÷ 60 = 3.1
ይህም ማለት 3 ኬክሮስ ቀሪ 6 ካልዒት ማለት ነው።
✔️ አሁን ሰርተን ያገኘነውን 3 ኬክሮስ ከ 6 ካልዒት መጀመሪያ ካገኘነው 312 ኬክሮስ ጋር እንደምረዋለን።
☸️ በአንድ ዓመት ውስጥ የተገኘ ኬክሮስ
በካልዒት እና በሣልሲት ሰርተን ያገኘነውን ኬክሮስ በመደመር የዓመቱን ኬክሮስ እናገኛለን
312 ኬክሮስ + 3 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት = 315 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት
በዓመት ውስጥ (በ12 ወር)
315 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ትርፍ አለ
6 ካልዒትን በማቆየት
315 ኬክሮስን ወደ ቀን ስንቀይረው
👉1ቀን = 60 ኬክሮስ
315 ኬክሮስ ስንት ቀን ይሆናል?
315 ÷ 60 = 5.25 = 5ቀን ከ15 ኬክሮስ
➤ በአንድ ዓመት ውስጥ 5 ቀን ከ15 ኬክሮስ ትርፍ አለ። ይኼውም የጳጕሜን ቀናት ናቸው። ይህም የዓመቱን ቀን 365 ቀን ያደርገዋል። 15 ኬክሮስ ግን ትርፍ አለ።
✦ በ1ኛው ዓመት 365ቀን ከ15 ኬክሮስ
✦ በ2ኛው ዓመት 365ቀን ከ30 ኬክሮስ
✦ በ3ኛው ዓመት 365ቀን ከ45 ኬክሮስ
✦ በ4ኛው ዓመት 365ቀን ከ60 ኬክሮስ ሲሆን ይህም 60ው ኬክሮስ 1ቀን በመሆኑ ዓመቱን 366 ቀን ያደርገዋል። በየአራት ዓመቱ ጳጕሜን 6 የምትሆን ከዚህ የተነሣ ነው።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
የውዳሴ ማርያም ማብራሪያ በPDF ተለቀቀ።
በጾመ ፍልሰታ በፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጼ በተከታታይ የተማማርነውን የእመቤታችንን ምስጋና (ውዳሴ ማርያም) ትርጓሜና ማብራሪያ
በዚሁ የቴሌግራም ገጼ ያገኙታል።
👇👇👇
የቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/MEBspiritualtraining21
👇👇👇
የፌስቡክ አድራሻ
https://www.facebook.com
ማኅቶት እሸቴ
💠 ጰራቅሊጦስ
ጰራቅሊጦስ = ተውሳክ + መባጃ ሐመር
= 28 + 15 = 43
ሠላሳውን ገድፎ 13 ይቀራል
💥ማወዳደር (ጰራቅሊጦስን ከዕርገት)
13 > 3
ስለዚህ ጰራቅሊጦስ ዕርገት በዋለበት ሰኔ ወር ላይ ይውላል ማለት ነው።
✍️ሰኔ 13 ቀን ምን ዕለት እንደሆነ ለማግኘት የሰኔን መባቻ ይዘን እንቆጥራለን።
ሰኔ ማክሰኞ ይብታል (ሰኔ አንድ ቀን ማክሰኞ ነው)
▶ማክሰኞ ለማክሰኞ (ከመጀመሪያው ሳምንት ወይም መባቻ ማክሰኞ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ ብንቆጥር) 8 ቀን ይሆናል።
▶ከ8ኛ ቀኑ ማክሰኞ ተነስተን እስከ 13ኛ ቀን እንቁጠር ፤
➺ ማክሰኞ 8 ፡
➺ ረቡዕ 9 ፡
➺ ኀሙስ 10 ፡
➺ ዐርብ 11 ፡
➺ ቅዳሜ 12 ፡
➺ እሑድ 13 ፡ ተገኘ።
➤ ጰራቅሊጦስ ሰኔ 13 እሑድ ዕለት ዋለ።
💠 ጾመ ሐዋርያት
ጾመ ሐዋርያት = ተውሳክ + መባጃ ሐመር
= 29 + 15 = 44
ሠላሳውን ገድፎ 14 ይቀራል
💥ማወዳደር (ጾመ ሐዋርያትን ከጰራቅሊጦስ)
14 > 13
ስለዚህ ጾመ ሐዋርያት ጰራቅሊጦስ በዋለበት ሰኔ ወር ላይ ይውላል ማለት ነው።
✍️ሰኔ 14 ቀን ምን ዕለት እንደሆነ ለማግኘት የሰኔን መባቻ ይዘን እንቆጥራለን።
ሰኔ ማክሰኞ ይብታል (ሰኔ አንድ ቀን ማክሰኞ ነው)
▶ማክሰኞ ለማክሰኞ (ከመጀመሪያው ሳምንት ወይም መባቻ ማክሰኞ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ ብንቆጥር) 8 ቀን ይሆናል።
▶ከ8ኛ ቀኑ ማክሰኞ ተነስተን እስከ 14ኛ ቀን እንቁጠር ፤
➺ ማክሰኞ 8 ፡
➺ ረቡዕ 9 ፡
➺ ኀሙስ 10 ፡
➺ ዐርብ 11 ፡
➺ ቅዳሜ 12 ፡
➺ እሑድ 13 ፡
➺ ሰኞ 14 ፡ ተገኘ።
➤ ጾመ ሐዋርያት ሰኔ 14 ሰኞ ዕለት ዋለ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
💠 ጾመ ድኅነት
ጾመ ድኅነት = ተውሳክ + መባጃ ሐመር
= 1 + 15 = 16
💥ማወዳደር (ጾመ ድኅነትን ከጾመ ሐዋርያት)
16 > 14
ስለዚህ ጾመ ድኅነት ጾመ ሐዋርያት በዋለበት ሰኔ ወር ላይ ይውላል ማለት ነው።
✍️ሰኔ 16 ቀን ምን ዕለት እንደሆነ ለማግኘት የሰኔን መባቻ ይዘን እንቆጥራለን።
ሰኔ ማክሰኞ ይብታል (ሰኔ አንድ ቀን ማክሰኞ ነው)
▶ማክሰኞ ለማክሰኞ (ከመጀመሪያው ሳምንት ወይም መባቻ ማክሰኞ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ ብንቆጥር) 8 ቀን ይሆናል።
▶ማክሰኞ ለማክሰኞ (ከ8ኛ ቀኑ ማክሰኞ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ ብንቆጥር) 15 ቀን ይሆናል።
▶ከ15ኛ ቀኑ ማክሰኞ ተነስተን እስከ 16ኛ ቀን እንቁጠር ፤
➺ ማክሰኞ 15 ፡
➺ ረቡዕ 16 ፡ ተገኘ።
➤ ጾመ ድኅነት ሰኔ 16 ረቡዕ ዕለት ሆነ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
በዚህም መሠረት የ2019 ዓ.ም በዓላትና አጽዋማት የሚውሉበት ወርና ቀን ይህ ነው።
✒️ ጾመ ነነዌ የካቲት 15 ቀን።
✒️ ዐቢይ ጾም የካቲት 29 ቀን።
✒️ ደብረ ዘይት መጋቢት 26 ቀን።
✒️ ሆሣዕና ሚያዝያ 17 ቀን።
✒️ ስቅለት ሚያዝያ 22 ቀን።
✒️ ትንሣኤ ሚያዝያ 24 ቀን።
✒️ ርክበ ካህናት ግንቦት 18 ቀን።
✒️ ዕርገት ሰኔ 3 ቀን።
✒️ ጰራቅሊጦስ ሰኔ 13 ቀን።
✒️ ጾመ ሐዋርያት ሰኔ 14 ቀን።
✒️ ጾመ ድኅነት ሰኔ 16 ቀን።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
የበዓላትና የአጽዋማት ኢየዐርግና ኢይወርድ (ከቀናት የማይወጡበትና የማይወርዱበት)
✏️ ነነዌ :- ከጥር 17 በታች አይወርድም ከየካቲት 21 በላይ አይወጣም።
✏️ ዐቢይ ጾም :- ከየካቲት 1 በታች አይወርድም ከመጋቢት 5 በላይ አይወጣም።
✏️ ደብረ ዘይት :- ከየካቲት 28 በታች አይወርድም ከሚያዝያ 2 በላይ አይወጣም።
✏️ ሆሣዕና :- ከመጋቢት 19 በታች አይወርድም ከሚያዝያ 23 በላይ አይወጣም።
✏️ ስቅለት :- ከመጋቢት 24 በታች አይወርድም ከሚያዝያ 28 በላይ አይወጣም።
✏️ ትንሣኤ :- ከመጋቢት 26 በታች አይወርድም ከሚያዝያ 30 በላይ አይወጣም።
✏️ ርክበ ካህናት :- ከሚያዝያ 20 በታች አይወርድም ከግንቦት 24 በላይ አይወጣም።
✏️ ዕርገት :- ከግንቦት 5 በታች አይወርድም ከሰኔ 9 በላይ አይወጣም።
✏️ ጰራቅሊጦስ :- ከግንቦት 15 በታች አይወርድም ከሰኔ 19 በላይ አይወጣም።
✏️ ጾመ ሐዋርያት :- ከግንቦት 16 በታች አይወርድም ከሰኔ 20 በላይ አይወጣም።
✏️ ጾመ ድኅነት :- ከግንቦት 18 በታች አይወርድም ከሰኔ 22 በላይ አይወጣም።
👉 ለብዉ (አስተውሉ)
✦ ነነዌ ፣ ዐቢይ ጾም ፣ ጾመ ሐዋርያት ከሰኞ
✦ ርክበ ካህናት ፣ ጾመ ድኅነት ከረቡዕ
✦ ዕርገት ከኀሙስ
✦ ስቅለት ከዐርብ
✦ ደብረ ዘይት ፣ ሆሣዕና ፣ ትንሣኤ ፣ ጰራቅሊጦስ ከእሑድ አይወጣም።
ተፈጸመ !!!
© መ/ር ማኅቶት እሸቴ
ነሐሴ 28 / 2018 ዓ.ም
👇👇👇
የቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/MEBspiritualtraining21
✍️ የካቲት 29 ቀን ምን ዕለት እንደዋለ ለማግኘት የየካቲትን መባቻ ይዘን እንቆጥራለን።
የካቲት ሰኞ ይብታል (የካቲት አንድ ቀን ሰኞ ነው) ፡
▶ሰኞ ለሰኞ (ከመጀመሪያው ሳምንት ወይም መባቻ ሰኞ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ሰኞ ብንቆጥር) 8 ቀን ይሆናል።
▶ሰኞ ለሰኞ (ከ8ኛ ቀኑ ሰኞ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ሰኞ ብንቆጥር) 15 ቀን ይሆናል።
▶ሰኞ ለሰኞ (ከ15ኛ ቀኑ ሰኞ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ሰኞ ብንቆጥር) 22 ቀን ይሆናል።
▶ሰኞ ለሰኞ (ከ22ኛ ቀኑ ሰኞ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ሰኞ ብንቆጥር) 29 ቀን ይሆናል።
➺ ሰኞ 29 ፡ ተገኘ።
➤ ዐቢይ ጾም የካቲት 29 ሰኞ ዕለት ዋለ።
👉ለብዉ(አስተውሉ) :- በዓላትና አጽዋማትን ስናወጣ መጀመሪያ የወጣው በዓል ወይም ጾም ወር እና ቀን ቀጥሎ ለሚወጣው መሠረት ነው። ይህም ሲባል መጀመሪያ የወጣው ቀን ከሁለተኛው ቢበልጥ ሁለተኛ የወጣው የመጀመሪያው የያዘውን ወር ይለቃል። ዳግመኛ መጀመሪያ የወጣው ቀን ሁለተኛ ከወጣው ቢያን እና ሁለተኛ የወጣው ቢበልጥ ደግሞ ሁለቱም በተመሳሳይ ወር ላይ ይውላሉ።
ይህንንም በጾመ ነነዌና በዐቢይ ጾም መረዳት እንችላለን።
ነነዌ የካቲት 15 ሆነ
ዐቢይ ጾም 29 መጣ
15 < 29
የነነዌ ቀመር ከ ዐቢይ ጾም ቀመር ስላነሰ (ዐቢይ ጾም ከነነዌ ስለበለጠ) ዐቢይ ጾም ነነዌ በዋለበት ወር ላይ ይውላል።
ተከታታይነት ያላቸው ሁሉም በዓላትና አጽዋማት አካሄዳቸው አሁን ካየነው ጋር ተመሳሳይ ነው።
ማለትም በተራ ቅደም ተከተላቸው ይወዳደራሩ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
💠 ደብረ ዘይት
ደብረ ዘይት = ተውሳክ + መባጃ ሐመር
= 11 + 15 = 26
💥 ማወዳደር (ደብረ ዘይትን ከዐቢይ ጾም)
26 > 29
ስለዚህ ደብረ ዘይት ዐቢይ ጾም ከዋለበት ወር ቀጥሎ ባለው በመጋቢት ወር ይውላል ማለት ነው።
✍️መጋቢት 26 ቀን ምን ዕለት እንደሆነ ለማግኘት የመጋቢትን መባቻ ይዘን እንቆጥራለን።
መጋቢት ረቡዕ ይብታል (መጋቢት አንድ ቀን ረቡዕ ነው) ፡
▶ረቡዕ ለረቡዕ (ከመጀመሪያው ሳምንት ወይም መባቻ ረቡዕ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ረቡዕ ብንቆጥር) 8 ቀን ይሆናል።
▶ረቡዕ ለረቡዕ (ከ8ኛ ቀኑ ረቡዕ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ረቡዕ ብንቆጥር) 15 ቀን ይሆናል።
▶ረቡዕ ለረቡዕ (ከ15ኛ ቀኑ ሰኞ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ሰኞ ብንቆጥር) 22 ቀን ይሆናል።
▶ከ22ኛ ቀኑ ረቡዕ ተነስተን እስከ 26ኛ ቀን እንቁጠር ፤
➺ ረቡዕ 22 :
➺ ኀሙስ 23 ፡
➺ ዐርብ 24 :
➺ ቅዳሜ 25 :
➺ እሑድ 26 ፡ ተገኘ።
➤ ደብረ ዘይት መጋቢት 26 እሑድ ዕለት ዋለ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
💠 ሆሣዕና
ሆሳዕና = ተውሳክ + መባጃ ሐመር
= 2 + 15 = 17
💥 ማወዳደር (ሆሣዕናን ከደብረ ዘይት)
17 < 26
ስለዚህ ሆሣዕና ደብረ ዘይት ከዋለበት ወር ቀጥሎ ባለው ሚያዝያ ወር ላይ ይውላል ማለት ነው።
✍️ሚያዝያ 17 ቀን ምን ዕለት እንደሆነ ለማግኘት የሚያዝያን መባቻ ይዘን እንቆጥራለን።
ሚያዝያ ዐርብ ይብታል (ሚያዝያ አንድ ቀን ዐርብ ነው) ፡
▶ዐርብ ለዐርብ (ከመጀመሪያው ሳምንት ወይም መባቻ ዐርብ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ዐርብ ብንቆጥር) 8 ቀን ይሆናል።
▶ዐርብ ለዐርብ (ከ8ኛ ቀኑ ዐርብ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ዐርብ ብንቆጥር) 15 ቀን ይሆናል።
▶ከ15ኛ ቀኑ ዐርብ ተነስተን እስከ 17ኛ ቀን እንቁጠር ፤
➺ ዐርብ 15:
➺ ቅዳሜ 16 ፡
➺ እሑድ 17 : ተገኘ።
➤ ሆሣዕና ሚያዝያ 17 እሑድ ዕለት ዋለ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
💠 ስቅለት
ስቅለት = ተውሳክ + መባጃ ሐመር
= 7 + 15 = 22
💥 ማወዳደር (ስቅለትን ከሆሣዕናን)
22 < 17
ስለዚህ ስቅለት ሆሣዕና በዋለበት ሚያዝያ ወር ላይ ይውላል ማለት ነው።
✍️ሚያዝያ 22 ቀን ምን ዕለት እንደሆነ ለማግኘት የሚያዝያን መባቻ ይዘን እንቆጥራለን።
ሚያዝያ ዐርብ ይብታል (ሚያዝያ አንድ ቀን ዐርብ ነው) ፡
▶ዐርብ ለዐርብ (ከመጀመሪያው ሳምንት ወይም መባቻ ዐርብ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ዐርብ ብንቆጥር) 8 ቀን ይሆናል።
▶ዐርብ ለዐርብ (ከ8ኛ ቀኑ ዐርብ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ዐርብ ብንቆጥር) 15 ቀን ይሆናል።
▶ዐርብ ለዐርብ (ከ15ኛ ቀኑ ዐርብ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ዐርብ ብንቆጥር) 22 ቀን ይሆናል።
➺ ዐርብ 22 : ተገኘ።
➤ ስቅለት ሚያዝያ 22 ዐርብ ዕለት ዋለ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
💠 ትንሣኤ
ትንሣኤ = ተውሳክ + መባጃ ሐመር
= 9 + 15 = 24
💥ማወዳደር (ትንሣኤን ከስቅለት)
24 > 22
ስለዚህ ትንሣኤ ስቅለት በዋለበት ሚያዝያ ወር ላይ ይውላል ማለት ነው።
✍️ሚያዝያ 24 ቀን ምን ዕለት እንደሆነ ለማግኘት የሚያዝያን መባቻ ይዘን እንቆጥራለን።
ሚያዝያ ዐርብ ይብታል (ሚያዝያ አንድ ቀን ዐርብ ነው) ፡
▶ዐርብ ለዐርብ (ከመጀመሪያው ሳምንት ወይም መባቻ ዐርብ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ዐርብ ብንቆጥር) 8 ቀን ይሆናል።
▶ዐርብ ለዐርብ (ከ8ኛ ቀኑ ዐርብ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ዐርብ ብንቆጥር) 15 ቀን ይሆናል።
▶ዐርብ ለዐርብ (ከ15ኛ ቀኑ ዐርብ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ዐርብ ብንቆጥር) 22 ቀን ይሆናል።
▶ከ22ኛ ቀኑ ዐርብ ተነስተን እስከ 24ኛ ቀን እንቁጠር ፤
➺ ዐርብ 22:
➺ ቅዳሜ 23 ፡
➺ እሑድ 24 : ተገኘ።
➤ ትንሣኤ ሚያዝያ 24 እሑድ ዕለት ዋለ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
💠 ርክበ ካህናት
ርክበ ካህናት = ተውሳክ + መባጃ ሐመር
= 3 + 15 = 18
💥ማወዳደር (ርክበ ካህናትን ከትንሣኤ)
18 < 24
ስለዚህ ርክበ ካህናት ትንሣኤ ከዋለበት ወር ቀጥሎ ባለው ግንቦት ወር ላይ ይውላል ማለት ነው።
✍️ግንቦት 18 ቀን ምን ዕለት እንደሆነ ለማግኘት የግንቦትን መባቻ ይዘን እንቆጥራለን።
ግንቦት እሑድ ይብታል (ግንቦት አንድ ቀን እሑድ ነው) ፡
▶እሑድ ለእሑድ (ከመጀመሪያው ሳምንት ወይም መባቻ እሑድ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት እሑድ ብንቆጥር) 8 ቀን ይሆናል።
▶እሑድ ለእሑድ (ከ8ኛ ቀኑ እሑድ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት እሑድ ብንቆጥር) 15 ቀን ይሆናል።
▶ከ15ኛ ቀኑ እሑድ ተነስተን እስከ 18ኛ ቀን እንቁጠር ፤
➺ ሰኞ 16 :
➺ ማክሰኞ 17 :
➺ ረቡዕ 18 ፡ ተገኘ።
➤ ርክበ ካህናት ግንቦት 18 ረቡዕ ዕለት ዋለ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
💠 ዕርገት
ዕርገት = ተውሳክ + መባጃ ሐመር
= 18 + 15 = 33
ሠላሳውን ገድፈን 3 ይቀራል
💥ማወዳደር (ዕርገትን ከርክበ ካህናት)
3 < 18
ስለዚህ ዕርገት ርክበ ካህናት ከዋለበት ወር ቀጥሎ ባለው ሰኔ ወር ላይ ይውላል ማለት ነው።
✍️ሰኔ 3 ቀን ምን ዕለት እንደሆነ ለማግኘት የሰኔን መባቻ ይዘን እንቆጥራለን።
ሰኔ ማክሰኞ ይብታል (ሰኔ አንድ ቀን ማክሰኞ ነው)
▶ከ1ኛ ቀኑ ማክሰኞ ተነስተን እስከ 3ኛ ቀን እንቁጠር ፤
➺ ማክሰኞ 1 :
➺ ረቡዕ 2 :
➺ ኀሙስ 3 : ተገኘ።
➤ ዕርገት ሰኔ 3 ኀሙስ ዕለት ዋለ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌻🌻🌻 ባሕረ ሐሳብን በቀላሉ 🌻🌻🌻
የ2019/ ፳፻፲፱ ዘመን የበዓላትና የአጽዋማት አወጣጥ ለሁሉም ቢሚረዳ መልኩ በግልጽና በቀላል መንገድ የቀረበ።
💠 ዓመተ ዓለም = ዓመተ ፍዳ + ዓመተ ምኅረት
▶ ዓመተ ፍዳ / ዓመተ ኵነኔ አይለወጥም 5500 ዘመን ነው። ይኼውም ዘመነ ብሉይ ነው።
▶ዓመተ ምኅረት ከክርስቶስ ልደት ወዲህ ያለው ነው። ይኼውም 2019 ዘመን ነው።
ዓመተ ዓለም = 5500+2019 = 7519
💠 የዘመኑን ወንጌላዊ
የዘመኑን ወንጌላዊ ለማግኘት ዓመተ ዓለምን በ4 ገድፎ ወይም ለ4 አካፍሎ ቀሪው ወንጌላዊዩን ይነግረናል።
ይኼውም ቀሪው
✦ 1 ቢሆን ወንጌላዊዩ ማቴዎስ
✦ 2 ቢሆን ወንጌላዊዩ ማርቆስ
✦ 3 ቢሆን ወንጌላዊዩ ሉቃስ
✦ 4 ቢሆን ወይም ቢስተካከል ወንጌላዊዩ ዮሐንስ ይሆናል
የ2019 ዓ.ም ወንጌላዊን ለማግኘት
7519÷4 = 1879 ደርሶ ቀሪው 3 ይሆናል
🔆ስለዚህም ወንጌላዊዩ ሉቃስ ነው።
▶1879 መጠነ ራብዒት ይባላል።
💠 የመስከረም መባቻ
የሚውልበትን ዕለት ለማወቅ ዓመተ ዓለምንና መጠነ ራብዒት ደምሮ በሰባት በመግደፍ ወይም ለሰባት በማካፈል ቀሪውን በመያዝ በጥንተ ቀመር አማካኝነት ማግኘት ይቻላል።
▶ ጥንተ ቀመር ማለት ቁጥር የተጀመረበት ዕለት ማለት ሲሆን ይኸውም ማክሰኞ ነው።
✦ ማክሰኞ = 1
✦ ረቡዕ = 2
✦ ኀሙስ = 3
✦ ዐርብ = 4
✦ ቅዳሜ = 5
✦ እሑድ = 6
✦ ሰኞ = 7
ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት = 7519 +1879
= 9398
9398 ÷ 7 = 1342 ደርሶ ቀሪው 4 ይሆናል
ቀሪው 4 ሲሆን ዕለቱ ዐርብ ነው።
🔆 ስለዚህ የ2019 የመስከረም መባቻ ዕለቱ ዐርብ ሆነ።
💠 መጥቅዕ እና አበቅቴ
መጥቅዕ እና አበቅቴን ለማግኘት መጀመሪያ ዓመተ ዓለምን በዐቢይ ቀመር ፣ በማዕከላዊ ቀመር ፣ በንዑስ ቀመር በመግደፍ መደብና ወንበርን ማግጀት መጀመሪያ ስራችን ይሆናል።
✦ ዐቢይ ቀመር = 532
✦ ማዕከላዊ ቀመር = 76
✦ ንዑስ ቀመር = 19
➤ 7519 ÷ 532 = 14 ደርሶ ቀሪው 71
➤ 71 ን በማዕከላዊ ቀመር መግደፍ አይቻም ምክንያቱም ከማዕከላዊ ቀመር በታች ነውና። ስለዚህ መግደፍ የሚቻለው በንዑስ ቀመር ነው።
➤ 71 ÷ 19 = 3 ደርሶ ቀሪ 14 ይሆናል
🔆 መደብ = 14
🔆 ወንበር = መደብ - 1= 14 -1 =13
አንድ የተቀነሰበት ምክንያት አንድ ለቀጣዩ ዘመን ተው በሚለው አካሄድ ነው (አእትት ለዘመን)።
➤ መጥቅዕ = ጥንተ መጥቅዕ × ወንበር
➤ ጥንተ መጥቅዕ = 19 ነው።
🔆 መጥቅዕ = 19 × 13 = 247
247 ን በሠላሳ ስንገድፈው 7 ይቀራል ወይም ለሠላሳ ስናካፍለው ቀሪው 7 ነው።
በ2019 መጥቅዕ = 7 ወጣ ይባላል።
➤ አበቅቴ = ጥንተ አበቅቴ × ወንበር
➤ ጥንተ አበቅቴ = 11
🔆 አበቅቴ = 11 × 13 = 143
143 ን በሠላሳ ስንገድፈው 23 ይቀራል
ወይም ለሠላሳ ስናካፍለው ቀሪው 23 ነው።
በ2019 አበቅቴ = 23 ወጣ ይባላል።
▩Note - መጥቅዕ ወአበቅቴ ኢየዐርጉ ወኢይወርዱ እምሠላሳ ወትረ ይከውኑ ሠላሳ ( መጥቅዕ እና አበቅቴ ከሠላሳ አይወጡም አይወርዱም ሁልጊዜ ሠላሳ ናቸው እንጂ።)
ከላይ ያገኘነውን መጥቅዕ እና አበቅቴ በሠላሳ መግደፋችንም ከሠላሳ በላይ መሆን ስለሌለበት ነው።
የ2019 መጥቅዕና አበቅቴን ቢደምሩ 30 ይሆናሉ።
✤ 7 + 23 =30
👉ለብዉ(አስተውሉ) :- መግደፍ ማለት ማካፈል ማለት ነው። በሠላሳ መግደፍም ሲባል ለሠላሳ ማካፈል ማለት ነው።
ከዚህ በታች ደምረን የምናገኛቸውን ማናቸውም ቁጥሮች ከሠላሳ በላይ ከሆነ በሠላሳ ገድፈን ቀሪውን ይዘን እንሄዳለን። ምክንያቱም በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር አንድ ወር የሚኖረው ከፍተኛ ቀን 30 ብቻ በመሆኑ ነው። ከ30 በላይ ያገኘነውን መግደፋችንም ለዚሁ ነው።
♦️🔹♦️ መባጃ ሐመር
መባጃ ሐመርን ለማግኘት መጥቅዕ እና በዓለ መጥቅዕ የዋለበትን ዕለት ተውሳክ በመደመር እናገኛለን።
🔹🔸🔹 መጥቅዕ ከበዛ ከመስከረም ንዛ መጥቅዕ ቢያንስ ከጥቅምት ዳስ እንዲል ፣ መጥቅዕ ከበለጠ በዓለ መጥቅዕ በመስከረም ወር ላይ ይውላል ፣ መጥቅዕ ካነሰ በዓለ መጥቅዕ በጥቅምት ወር ላይ ይውላል።
ስለዚህ የዚህ ዓመት መጥዕቅ ከአበቅቴ ስለሚያንስ በዓለ መጥቅዕ በጥቅምት ወር ላይ ይውላል ፣ ይኼውም ጥቅምት 7 ቀን ነው።
🔹🔸🔹 በመቀጠል ጥቅምት 7 ቀን መቼ ዕለት እንደሚውል እንፈልጋለን።
➣ ጥቅምት እሑድ ይብታል (ጥቅምት 1 ቀን እሑድ ነው) ከእሑድ ተነስተን ስንቆጥር ጥቅምት 7 ቀን ቅዳሜ ዕለት ይሆናል።
የቅዳሜ ተውሳክ ደግሞ 8 ነው። ይህም በዓለ መጥቅዕ ይባላል። ይኼውም ከዕለታት ተውሳክ የተገኘ ነው።
✤ የዕለታት ተውሳክ
✦ ቅዳሜ = 8
✦ እሑድ = 7
✦ ሰኞ = 6
✦ ማክሰኞ = 5
✦ ረቡዕ = 4
✦ ኀሙስ = 3
✦ ዐርብ = 2
➤ መባጃ ሐመር = መጥቅዕ + በዓለ መጥቅዕ የዋለበት ተውሳክ = 7 + 8 = 15
መባጃ ሐመር = 15 ተገኘ።
♦️🔹♦️ Note - በዓለ መጥቅዕ መስከረም ላይ ከዋለ ነነዌ በጥር ይውላል ፣ በዓለ መጥቅዕ ጥቅምት ላይ ከዋለ ነነዌ በየካቲት ይውላል። ነገር ግን ነነዌ ከጥር 17 አይወርድም ከየካቲት 21 ም አይወጣም ይህም በ ኢየዐርግ እና በ ኢይወርድ ሕግ ነው።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
የበዓላትና የአጽዋማት ተውሳክ
✦ ዐቢይ ጾም = 14
✦ ደብረ ዘይት = 11
✦ ሆሳዕና = 2
✦ ስቅለት = 7
✦ ትንሣኤ = 9
✦ ርክበ ካህናት = 3
✦ ዕርገት = 18
✦ ጰራቅሊጦስ = 28
✦ ጾመ ሐዋርያት = 29
✦ ጾመ ድኅነት = 1
✍️ ከዚህ በላይ የተቀመጡት የበዓላትና የአጽዋማት ተውሳክ ከመባጃ ሐመር ጋር በመደመር በዓሉ እና አጽዋሙ የሚውልበትን ወር ፣ ቀንና ዕለት ለማግኘት ያገለግላሉ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
💠 ነነዌ
ነነዌ የራሱ ተውሳክ የለውም በመባጃ ሐመር ይወጣል።
ነነዌ = መባጃ ሐመር = 15
በዓለ መጥቅዕ በጥቅምት ወር ላይ ስለዋለ ጾመ ነነዌ በየካቲት ወር ላይ ይውላል።
✍️ የካቲት 15 ቀን ምን ዕለት እንደዋለ ለማግኘት የየካቲትን መባቻ ይዘን እንቆጥራለን።
የካቲት ሰኞ ይብታል (የካቲት አንድ ቀን ሰኞ ነው) ፡
▶ሰኞ ለሰኞ (ከመጀመሪያው ሳምንት ወይም መባቻ ሰኞ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ሰኞ ብንቆጥር) 8 ቀን ይሆናል።
▶ሰኞ ለሰኞ (ከስምንተኛ ቀኑ ሰኞ ተነስተን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ሰኞ ብንቆጥር) 15 ቀን ይሆናል።
የምንፈልገው የካቲት 15 ቀንን ስለሆነ ይኸውም ሰኞ ቀን ሆነ
➤ ነነዌ የካቲት 15 ሰኞ ቀን ዋለ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
💠 ዐቢይ ጾም
ዐቢይ ጾም = ተውሳክ + መባጃ ሐመር
= 14+15 = 29
💥 ማወዳደር (ዐቢይ ጾምን ከነነዌ)
29 > 15
ስለዚህ ዐቢይ ጾም ነነዌ በዋለበት ወር ባለው በየካቲት ወር ይውላል ማለት ነው።
ከየካቲት ወር ሳንወጣ የካቲት 29 ቀንን እንፈልጋለን። ምክንያቱም ነነዌ ከዋለበት 15 ቀን ዐቢይ ጾም የሚውልበት 29 ቀን ስለሚበልጥ ከዚሁ ወር አሳንወጣ ዐቢይ ጾም በየካቲት ወር እንደሚውል ከወዲሁ አወቅን።
+1
ቤተክርስቲያን ድንበር የላትም...
ዲያቆን ብንያም በማኅበረ ቅዱሳን አጋዥነት በጎንደር ደብረ ልዑላን ድል አምባ ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ሥር በፋሲል ግቢ ጉባኤ ከ20010 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ዓመታት የአብነት ትምህርትን በመማር ለዲቁና የበቃና በሀገሩ በጉምዝ ክልል ከሌሎች አገልጋይ ወንድሞች ጋር ያላመኑትን በማሳመን ክርስትናን እያስፋፋ ያለ ሲሆን በዛሬው ዕለት በቤተክርስቲያን ሥርዓት ጋብቻውን ፈጽሟል።
👇👇👇
የቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/MEBspiritualtraining21
👇👇👇
የፌስቡክ አድራሻ
https://www.facebook.com
ጎንደር ላይ መጻሕፍትን በብዛት የምታገኙበት የመጀመሪያው ሱቅ ነው ማለት ይቻላል
በጎንደር ደብረ መድኃኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት የአለቃ ወልደ አብ የመጻሕፍት ትርጓሜ ቤት።
ከዚህ ሱቅ ለደብረ ታቦር ጉባኤ ቤት ሲገዙ ቅናሽ (discount) አለው። ሁለቱንም ጉባኤ ቤቶች በአንዴ መደገፍ ነው። "በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ" ማለት ይሄ አይደል።
👇👇👇
የቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/MEBspiritualtraining21
👇👇👇
የፌስቡክ አድራሻ
https://www.facebook.com
ለቤተክርስቲያን አንድ ብሎኬት ከገዛ ይልቅ ለጉባኤ ቤት አንድ መጽሐፍ የለገሰ የበለጠ መልካም አደረገ።
ደንጋይ ለመደርደር ላይቭ የሚሰበሰብ ምእመናን እና አስተባባሪ እንዲሁም የሚዲያ ሰውና ቲክቶከር ቤተክርስቲያንን መልሶ የሚገነባትን ጉባኤ ቤት መጽሐፍ ለመደርደር ሲሆን ዝም ማለቱ ያሳዝናል። ቤተክርስቲያንን ለማስቀጠል ግንባታ ሳይሆን ጉባኤ ቤት ይቅደም።
በእውነቱ ለቤተክርስቲያን አንድ ብሎኬት ከገዛ ይልቅ ለጉባኤ ቤት አንድ መጽሐፍ የለገሰ የበለጠ መልካም አደረገ።
ለደብረ ታቦር የ፬ቱ ጉባኤ ቤት ዓለም አቀፍ ቤተ መጻሕፍት እና የምርምር ማዕከል አንድ መጽሐፍ በመለገስ ቤተክርስቲያንን ይገንቡ።
👇👇👇
የቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/MEBspiritualtraining21
👇👇👇
የፌስቡክ አድራሻ
https://www.facebook.com
ከኢየሱስ ውጭ ሌላ ስግደት ተፈቀደ ...
ጴንጤ ስትሆን ለቅዱሳን ለመላእክት ለእመቤታችን አይሰገድም ትላለህ
ለነቢይህ (ኢዩ ጩፋና መሰሎቹ) ደግሞ እንዲሰገድ ታውጃለህ።
ለነገሩ መላእክት የሚንቀጠቀጡት ለጌቶች ጌታ ብቻ ነበር ለኢዩ ጩፋ ከተንቀጠቀጡማ ስግደት ብቻ ሳይሆን አምልኮም ይገባዋል 😂😂😂
አይ ጴንጤ መሆን ልጓም የሌለው ፈረስነት ነውኮ
👇👇👇
የቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/MEBspiritualtraining21
👇👇👇
የፌስቡክ አድራሻ
https://www.facebook.com
ደብረ ታቦር ጌታ ነቢያትን ሐዋርያትን ሰብስቦ ምስጢረ ሥላሴን በገሀድ አስተምሯል። ዛሬም ምስጢረ ሥላሴ ወደ ሚነገርበት የደብረ ታቦር ፬ቱ ጉባኤ ቤት መጻሕፍትን በመያዝ ለትምህርት እንሰብሰብ።
