cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

🌻የምስጋና ዘመን 🌻

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ቆየት ያሉና አዳዲስ👇👇 👏 የቸብቸቦ መዝሙራት  🎻 የበገና መዝሙራት   👑 የቅዱሳን መዝሙራት    ⛪️ የንግስ መዝሙራት 🤲 የምስጋና  መዝሙራት 🙏 የንስሐ  መዝሙራት 💍 የሠርግ መዝሙራት   🌦 ወቅታዊ መዝሙራት https://t.me/yemisganazemen https://t.me/yemisganazemen

Show more
Advertising posts
287Subscribers
-124 hours
-57 days
-830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ሰንበት ያደረጋቸው ነገሮች የየራሳቸው ትንቢትና ምሳሌ አላቸው፤ አህያዋና ውርንጫዋ የሁለቱ ኪዳናት (የሐዲስ ኪዳንና የብሉይ ኪዳን) ምሳሌ ናቸው፡፡ አህያ የተመረጠችበት ምክንት 1. ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ፡- ‹‹አንቺ የጽዮን ልጅ እጅግ ደስ ይበልሽ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ የሆነው ትሑትም ሆኖ በአህያዋ በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል›› (ዘካ 9፥9)፡፡ 2. ትሕትናን ለማስተማር፡- አህያ በብዙዎች ዘንድ የተናቀች እንስሳ ነበረች፤ በአህያ መቀመጥም ራስን ማዋረድ ነውና ጌታም ትሕትናን ለማስተማር በተናቀችው አህያ ተቀምጧል፡፡ አንድም የዓለም ጥበብና ክብር በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነትና ውርደት መሆኑን ለማስረዳት ዓለም የሚያደንቃቸውን ትቶ ዓለም የናቀውን ተጠቅሞበታል፡፡ 3. እኔ የሰላም አምላክ ነኝ ሲል፡- አህያ የሰላም ምሳሌ ነች፡፡ በጥንት ዘመን ነቢያት በአህያ ተቀምጠው የመጡ እንደሆነ መልካም የምሥራች ትንቢት ሊናገሩ መሆኑ ይታወቃል፤ በፈረስ ተቀምጠው ከመጡ ደግሞ ስለመቅሰፍት ወይም መአት ትንቢት እንደሚናገሩ ይታወቅ ነበርና፡፡ 4. እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል፡- በአህያ ላይ የተቀመጠ ሰው ቢያሳድዱት አያመልጥምና ብትፈልጉኝ እኔ ቅርባችሁ ነኝ ታገኙኛላችሁ ሲለን ነው፤ (ኤር 23፥23) 5. በትሑት ሰው ልቦና አድሬ እኖራለሁ ሲል፡- አህያ ብዙ ጫንክብኝ፣ ጎዳኸኝ ብላ ሳታማርር ራሷን ዝቅ አድርጋ ባለቤቷን ታገለግላለችና እኔም ራሱን ዝቅ አድርጎ በሚገዛልኝ ትሑት ሰው ልብ አድሬ እኖራለሁ ሲል ነው፡፡ አህዮቹን ፈትታችሁ አምጡ ለምን አለ?    አባታችን አዳም ከዲያብሎስ እስራት የሚፈታበት ጊዜ መድረሱን ለማመልከት ነው፤ አንድም ለደቀ መዛሙርቱ የማሰርና የመፍታት ሥልጣን (ሥልጣነ ክህነት) መስጠቱን ለማጠየቅ ነው፤ (ማቴ 16፥18-19 ፣ ዮሐ 20፥22-23)፡፡ ሕፃናቱ ለምን አመሰገኑት?    አስቀድሞ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹ከሕፃናትና ከሚጠቡ ለራስህ ምስጋና አዘጋጀህ›› (መዝ 8፥2) ብሎ የተናገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ይህ የመዝሙር ክፍል የዚህች ሰንበት ምስባክም ነው፡፡ ሕፃናቱ ዘንባባ ይዘው የዘመሩበት ምክንያት ሀ. ዘንባባ በእስራኤል ባሕል የሰላም የደስታ ምልክት ስለሆነ፤ (ነህ 8፥14-15) ለ. የዘንባባ የሚዋጋ እሾህ የእግዚአብሔር ምሳሌ ነው፤ ‹‹እግዚአብሔር ተዋጊ ነው›› ይላልና ዘጸ 14፥14፡፡ ሐ. ዘንባባ የመለኮት ምሳሌ ነው፤ ዘንባባ ቢደርቅ እንኳ በእሳት ይለበለባል እንጂ አይነድምና፡፡ የመለኮትንም ምጥቀቱንና ጥልቀቱን የሰው ኅሊና ሊመረምረው አይችልም፡፡             ወስብሐት ለእግዚአብሔር! ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ጾምና ምጽዋት፣ ሰባቱ አጽዋማት         ═══•꧁🌿🌿🌿꧂•═
Show all...
🥴 1
Boss Beo Reins: 1✞የዘመን ፍፃሜ✞ የዘመን ፍፃሜ እስከዚህ የሌለህ ዘላለም የምትኖር (፫)ፍጹም አምላክነህ 🌿ሆሳዕና (፫) በአርያም🌿 ቡሩክ ሆሳዕና አምላከ እስራኤል ተቀምጦ መጣ (፫) በአህያ ግልገል አዝ= = = = = 🌿 ትንሹም ትልቁም በአንድነት ዘመሩ አመሰገኑት (፫) ሆሳዕና እያሉ 🌿 አዝ= = = = = በጣም ደስ ይበልሽ እልል በይጽዮን ንጉሥሽ መጣልሽ (፫) ሊሆንሽ መድኅን 🌿 🌿 ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮ 🌿ሆሳዕና በአርያም🌿 🌿ለወልደ ዳዊት🌿 ሆሣዕና በአርያም የዳዊት ልጅ ገባ ኢየሩሳሌም(፪) ቤቱን ቢያደርጉበት የዓመጽ መደብር በጌትነት ገባ የሰው ልጅ በክብር(፪) አዝ= = = = = በአህያ ተቀምጦ ሲመጣ ቢያዩት ሕጻናት በአንድነት አመሰገኑት(፪) አዝ= = = = = ሊቃነ ካህናት በጣም ተቆጥተው ይማከሩ ጀመር ብለው እንስቀለው(፪) ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮ 2✞ሆሳዕና✞ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ሆሳዕና ብለን እናቅርብ ምስጋና ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና ለወልደ አምላክ - - - ሆሳዕና ትህትናን አሳየን - - - ሆሳዕና ስሙ ይባረክ - - - ሆሳዕና አዝ= = = = = ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና ለሰማይ ንጉስ - - - ሆሳዕና ግርማ ለብሶ መጣ - - - ሆሳዕና እኛን ሊቀድስ - - - ሆሳዕና አዝ= = = = = ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና ለወልደ ዳዊት - - - ሆሳዕና ነብያት በትንቢት - - - ሆሳዕና ለተናገሩለት - - - ሆሳዕና ሐዋርያት በወንጌል - - - ሆሳዕና ለሰበኩለት - - - ሆሳዕና አዝ= = = = = ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና ለአምላከ ምህረት - - - ሆሳዕና ተወልዶ ከድንግል - - - ሆሳዕና እንደ ህጻናት - - - ሆሳዕና እረኞች በዋሻ - - - ሆሳዕና የሰገዱለት - - - ሆሳዕና የአዳም ልጆች ሁሉ - - - ሆሳዕና ደግሞም መላእክት - - - ሆሳዕና ═•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═ 3✞ ምስጋናዬን ✞ ምስጋናዬን ላምላኬ አቀርባለው በማደሪያው ገብቼ ሠግድለታለው ኤልሻዳይ ነው ጌታ ሁሉን ቻይ ይፈፀማል አምናለሁ የልቤን ጉዳይ(2) ዘንባባዬን ይዤ እደህፃናቱ ሆሣና ልበለው ሠግጄ በፈቱ ምንም ባዶብሆን እውቀት ቢጎድለኝ ለሥሙ ልዘምር ከልካይም የለኝ(2)          አዝ= = = = = አምላኬ በፈትህ ቃል አለብኝ እኔ ቋንቋዬ መዝሙር ነው ያንተ እደመሆኔ ባሚናዳ ደጃፍ በቅድመ ታቦቱ ያየክብርህ ውደር ጠራኝ ማህሌቱ (2)          አዝ= = = = = የህይወት ትርጉሜ አንተነህ ደሥታዬ ስምህን ማገልገል ክብሬነው ሥራዬ ለታመነው ጌታ ምስክር የሆኑ ከብረው ተመለሱ ለበረከት ሆኑ(2)          አዝ= = = = = መነሻዬ አንተነህ ጉልበቴና ክብሬ መድረሻዬም አንተ መደምደሚያ ቅጥሬ በፂሆን ተራራ ስትገለጥ ያኔ ነጩን ልብሥ አልብሠህ አስነሳኸኝ ለቅኔ (2)                     መዝሙር በ    ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮    4#እርሱ_ነው_ቀን_የሚይወጣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ዛሬ ሞልቷል ምስጋናህ ተነሳ ልቤ ዘምር ለጌታ ለእግዚአብሔር 3 አዝ።።።።።።።።።።።።።። በገና ተነስ እንዚራ ማዳኑን እንድናወራ ብትቀርቡ ብትከተሉ ሁላችው ሆሳህና በሉ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።። እግዚአብሔር ዘመን ከሰጠ ይዘምር የተለወጠ እልልታ ይሁን ለስሙ ለዋጀን በወርቅ ደሙ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።።።።።። የክብሬ የቤቴ ጌታ የነፍሴ ባለውለታ ኤፉድ ነው በፍታ ነው ልብሴ ዘማሪ ነኝ ለንጉሴ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።።።።።። ሰገነት ላይ የወጣችው ዝምታን የመረጣችው ከአፋችው ወረት አይውጣ እሱ ነው ቀን የሚያወጣ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።።።። 5✞ሆሣዕና✞ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና ሆሣዕና ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት ህፃናቱ ሁሉ ድንጋዮች ሳይቀሩ ለዘመሩለት ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ እርሱ የተባረከ ነው ቅዱስ ነው መንፈሱ ሰላምን የሚሰብክ የሚናገር ፍቅርን በአህያ ውርንጫ መጥቷል ንጉሣችን አዝ= = = = = ዘንባባውን ይዘው ህፃን አዛውንቱ ልብሳቸውን ሳይቀር አንጥፈው በፊቱ ሆሳሣና ብለው ዘመሩ በእልልታ ግባ ንጉሣችን የሠራዊት ጌታ አዝ= = = = = ዘመንን ለሰጠን እንዘምርለት የምስጋናን መስዋዕት በፊቱ እንሰዋለት እንኳን እኛን ቀርቶ ድንጋይ ያናግራል ከሚጠቡ አንደበት ምስጋናን ይወስዳል አዝ= = = = = መድሃኒት ለሰው ልጅ ስለተገለጠ የመርገም ጨርቃችን ስለተወጠ ሰላም በሰማያት ሆነ በምድር ክብርና ምስጋና ለእርሱ ለእግዚአብሔር አዝ= = = = = እኛ ለክርስቶስ እናስፈልጋለን ቅዱሳኑን ልኮ መፈታትን ይስጠን በትህትና ወድቀን በልባችን ይግባ እንደ ህፃናቱ እንያዝ ዘንባባ መዝሙር ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ የዮሐንስ ወንጌል ፲፪፥፲፫ መዝ ፰፥፪
Show all...
👍 1
✞የዘመን ፍፃሜ✞ የዘመን ፍፃሜ እስከዚህ የሌለህ ዘላለም የምትኖር (፫)ፍጹም አምላክነህ 🌿ሆሳዕና (፫) በአርያም🌿 ቡሩክ ሆሳዕና አምላከ እስራኤል ተቀምጦ መጣ (፫) በአህያ ግልገል አዝ= = = = = 🌿 ትንሹም ትልቁም በአንድነት ዘመሩ አመሰገኑት (፫) ሆሳዕና እያሉ 🌿 አዝ= = = = = በጣም ደስ ይበልሽ እልል በይጽዮን ንጉሥሽ መጣልሽ (፫) ሊሆንሽ መድኅን 🌿 🌿 ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
Show all...
✞ ኒቆዲሞስ ✞ ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ክቡር ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር (፪) በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ በመከራው ፅናት ይህን ዓለም ናቀ መምሕር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ የትዕቢትን ጅረት በትሕትና ተዋርዶ አደረቀ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ ፍርሃትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ የመግነዙን በፍታ በሽቱ ያከበረ ከመቅደሱ አንቀጽ ላይረሳ አምድ ሆኖ ታጠረ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ነገረች ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች ከጨለማው ኃጢአት ነቅታ ብርሃን ካየች እንደ ኒቆዲሞስ ነፍስህም ተምራ ተመለሰች ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ #Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ ❖ @yemisganazemen ❖   ❖ @yemisganazemen ❖         âœžâœžâœžâœžâœžâœžâœžâœžâœžâœžâœžâœžâœžâœž
Show all...
7. ኒቆዲሞስ    ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃና መምህር ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኘው መምህር መሆኑን የሚከተለው ጽሑፍ ያስገነዝበናል፡፡ ‹‹ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ መምህር ሆይ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን›› አለው፡፡ ኢየሱስም መልሶ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም›› አለው፡፡ ኒቆዲሞስም ‹‹ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል?›› አለው፡፡ ኢየሱስም ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካለተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፤ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው፤ ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁ አታድንቅ፤ ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፤ ድምፁንም ትሰማለህ ነገር ግን ከወዴት እንደመጣ ወዴትም እንዲሔድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው›› አለው፤ (ዮሐ 3፥1-8)፡፡ ከውኃና ከመንፈስ ዳግም መወለድ የእግዚአብሔር ልጆች ለሆኑት ልዩ መገለጫ ነው፡፡    ኒቆዲሞስ በሌሊት እየመጣ ከኢየሱስ ክርስቶስ እግር ሼር ቁጭ ብሎ ወንጌልን ይማር ነበር፡፡ ሰንበቱ በእርሱ ስም የተሰየመው ሥራውን ለመዘከር ነው፡፡ በሌሊት መጣ የሚለው በምሥጢር ሲተረጎም አንደኛ ወደፊት በቀን ይመጣልና ከዚያ አስቀድሞ መጣ ለማለት ነው፤ አንድም በኋላ በዕለተ ዓርብ የጌታን ሥጋ ከመስቀሉ አውርዶ ገንዞ ለመቅበር ይመጣልና ከዚያ አስቀድሞ ለመማር መጣ ለማለት ነው፡፡ አንድም ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስን ሳያምን በፊት በኦሪት ጨለማ እያለ መጣ ለማለት በሌሊት መምጣቱን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አመሥጥረው ያስተምራሉ፡፡ ኒቆዲሞስ ከመዓልት ይልቅ በሌሊት መማር የመረጠበት ምክንያቶች ሀ. ውዳሴ ከንቱ ሽቶ፦ እርሱ ልሹ የአይሁድ አለቃና መምህር ስለነበር ከሌላ መምህር (ከኢየሱስ ክርስቶስ) እግር ሼር ተቀምጦ ሲማር አይሁድ ቢያዩት ሳይገባው ነው መምህር ያልነው ብለው ይነቅፉት ነበር፡፡ በሌላ አገላለጽ ኒቆዲሞስ መማርን ይፈልጋል ደቀ መዝሙር መባልን ግን አይፈልግም፡፡ በአንጻሩም ምሁረ ኦሪት ነበረና መምህር መባልን ይፈልጋል፡፡ ለ. የአይሁድን ዛቻና ማስጠንቀቂያ ፈርቶ፦ አይሁድ በክርስቶስ የሚያምንና ትምህርቱንም የሚሰማ ቢገኝ ከማኅበራችን ይለይ ቤቱም የጉድፍ መጣያ ይሁን ብለው ተስማምተው ሕግ አውጥተው ነበርና ቅጣቱን ፈርቶ ላለመታየት ሌሊት መማርን መርጧል፡፡ ሐ. አእምሮ ልቡናውን ሰብስቦ ለመማር ፈልጎ፦ መዓልት ዓይንን፣ ጆሮንና አእምሮን የሚሰርቅ ነገር ብዙ ነውና ከቀን ይልቅ ሌሊትን መረጠ፡፡ አንድም አለቃ እንደመሆኑ ቀን ቀን የራሱ ሼል ይበዛበት ነበረና ሌሊትን መረጠ፡፡    በዚህ ሳምንት ቤተ ክርስቲያን ሾለ ምሥጢረ ጥምቀት ታስተምራለች፡፡ ጥምቀት ሰው ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ዳግመኛ ተወልዶ የክርስቶስ አካል የማኅበረ ምእመናንም አባል የሚሆንበት ምሥጢር ነው፡፡ በጥምቀት ኃጢአት ይሰረያል፤ የእግዚአብሔር ልጅነት ይሰጣል፤ ልጅ ለሆነው ሁሉ ርስት ገነትና መንግሥተ ሰማያትም ይወረሳል፡፡    በዚህ ሰንበት የሚሰበከው ምስባክ ‹‹ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጎበኘኸኝ ፈተንኸኝ ምንም አላገኘኽብኝም፤ የሰውን ሼል አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው››፤ (መዝ 16፥3-4) የሚለው የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ነው፡፡    ዛሬ ብዙዎቻችን ባለሥልጣን ስለሆንን በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውስጥ ባለው መሬት ላይ ቁጭ ብለን መማር ያሳፍረናል፤ ሌሎቻችንም ባለሀብት ስለሆንን ለገንዘባችን እንጂ ለእግዚአብሔር የሚሆን ጊዜ አጥተናል፤ ሌሎች ደግሞ መምህር ነኝ አለቃ ነኝ በቅቻለሁ ነቅቻለሁ ትምህርት አያስፈልገኝም በማለት ከቤቱ ርቀናል፡፡ ቀሪዎቻችን ደግሞ የየራሳችን ምክንያት አበጅተናል፡፡ ኒቆዲሞስ ግን ከጌታ እግር ሼር ቁጭ ብሎ ለመማር እነዚህ ሁሉ ምክንያቶች አልከለከሉትም፡፡ እነዚህን ሁሉ ተጋፍጦ በመማሩ ከዮሴፍ ጋር የክርስቶስን ሥጋ ገንዞ ለመቅበርና በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቦ በታሪክ ለመዘከር በቅቷል፤ (ዮሐ 19፥38-42)፡፡ የእኛንም ሕይወት መቃኘት እንደሚገባን ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሳምንት ከኒቆዲሞስ ሕይወት ጋር በማነጻጸር ታስተምረናለች፡፡ ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣  ሰባቱ አጽዋማት ✍ @yemisganazemen
Show all...