cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የቅዱሳን ታሪክ

ሰማያት የእግዚአብሔር ክብር ይገልፃሉ

Show more
Advertising posts
1 730
Subscribers
+224 hours
+17 days
+11530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"ክርስቲያን ልትሆን ብትወድ አንዳንዴ እንደ ጣዖታት አንዳንዴ እንደ ኪሩቤል ሁን:: ለክፉ ነገር ሲሆን "ዓይን እያላቸው የማያዩ ጆሮ እያላቸው የማይሰሙ" ጣዖታትን ምሰል:: ለመልካም ነገር ግን "ዓይኖቻቸው ብዙ የሆኑ ኪሩቤልን ምሰል" ቅዱስ አባ ሲሶይ
Show all...
12
➥ስለደምህ ፈንታ ደማቸውን አፈሰሱ።         📖🌿📖🌿📖🌿📖 እንደ ስምዖን ጴጥሮስ ፥ እንደ ደቀ መዛሙርትህም ሁሉ። እንደጳውሎስ፥ እንደቅዱሳን ሐዋርያትህም ሁሉ። ➥በመከራቸው ወንጌልህን የተሸከሙ፤ በመሞታቸው የትምህርትህን ስብከት የጠበቁ። እንደ እስጢፋኖስ እንደ ሰማዕታትም ሁሉ ፤ ከጌትነትህ ክብርን ይቀበሉ ዘንድ፣ ስለደምህ ፈንታ ደማቸውን አፈሰሱ። ስማቸውም በሰማያት ባለች ነፃ በምታወጣ በኢየሩሳሌም በሕይወት፤ መጽሐፍ የተፃፈ ነው። ይህችውም በእውነት እናታችን ናት። በቅድስት ቤተ ክርስቲያንህ አምነናል።     🌿🌿🌿⛪️⛪️⛪️🌿🌿🌿 📖ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ📖 ➥ቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ በመድኃኒታችን ስም መስክረው በኔሮን ዘመን በ67 ዓ.ም ምስክር ሆነው ያረፉበት ዕለት ነው። እነረሱ የሰበሰቧት ጉባዔ ፣ የክርስቶስ አካል የሆነች ቤተ ክርስቲያን ግን ዛሬም በሞቱላት በነቢያትና በሐዋርያት የሃይማኖት ትምህርት ጸንታ ቆማለች። ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት ትባላለች።     ⛪️⛪️⛪️🌿🌿⛪️⛪️⛪️        ሐምሌ 05_2016 ዓ.ም
Show all...
11🙏 6👍 1
➥ስለደምህ ፈንታ ደማቸውን አፈሰሱ።         📖🌿📖🌿📖🌿📖 እንደ ስምዖን ጴጥሮስ ፥ እንደ ደቀ መዛሙርትህም ሁሉ። እንደጳውሎስ፥ እንደቅዱሳን ሐዋርያትህም ሁሉ። ➥በመከራቸው ወንጌልህን የተሸከሙ፤ በመሞታቸው የትምህርትህን ስብከት የጠበቁ። እንደ እስጢፋኖስ እንደ ሰማዕታትም ሁሉ ፤ ከጌትነትህ ክብርን ይቀበሉ ዘንድ፣ ስለደምህ ፈንታ ደማቸውን አፈሰሱ። ስማቸውም በሰማያት ባለች ነፃ በምታወጣ በኢየሩሳሌም በሕይወት፤ መጽሐፍ የተፃፈ ነው። ይህችውም በእውነት እናታችን ናት። በቅድስት ቤተ ክርስቲያንህ አምነናል።     🌿🌿🌿⛪️⛪️⛪️🌿🌿🌿 📖ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ📖 ➥ቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ በመድኃኒታችን ስም መስክረው በኔሮን ዘመን በ67 ዓ.ም ምስክር ሆነው ያረፉበት ዕለት ነው። እነረሱ የሰበሰቧት ጉባዔ ፣ የክርስቶስ አካል የሆነች ቤተ ክርስቲያን ግን ዛሬም በሞቱላት በነቢያትና በሐዋርያት የሃይማኖት ትምህርት ጸንታ ቆማለች። ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት ትባላለች።     ⛪️⛪️⛪️🌿🌿⛪️⛪️⛪️        ሐምሌ 05_2016 ዓ.ም
Show all...
ዲያቆን ኢዮአብ ግዛው Deacon Eyoab Gizaw

“የተበተኑትም ቃሉን እየሰበኩ ዞሩ።” ሐዋ. 8፥4 ⛪️እርሶ ደግሞ ካነበቡ በኋላ ፥ መልእክቱ ይዳረስ ዘንድ ለሌሎች በማጋራት ያገልግሉ።⛪️

ከእለታት አንድ ቀን አንድ አባት ወደ አባ መቃርዮስ በኣት ሄደና "አባቴ ሆይ ድኅነትን አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ?" ሲል ጥያቄ አቀረበላቸው። አባታችንም እንዲህ በማለት አሉት። "ወደ መቃብር ሂድና ሙታንን ሰድበሃቸው ና" አሉት። ይህ አባትም የተባለውን አድርጎ ተመለሰ። አባታችንም "ምን አሉህ?" ሲሉ ጠየቁት። ሰውየዉም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባ መቃርዮስም "አሁን ደግሞ ሂድና ሙታንን አመስግናቸው" አሉት። ሄዶም አመሰገናቸው። "አሁንስ ምን አሉህ" ሲል በድጋሚ ጠየቁት። ሰውዬም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባ መቃርዮስም "ስትሰድባቸው፣ ስታመሰግናቸው እና  ስታወድሳቸው ምንም አልመለሱም፤ አንተም ለነፍስህ ድህነትን ከፈለግህ እንደሞተ ሰው ሆነህ ኑር። ሰዎች ክፉ ቢያደርጉብህም፣ ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ" አሉት።
Show all...
17👍 1
Notcoin የመጀመሪያው Phase ላመለጣችሁ አሁን በራሳቸው ቦት Notcoin 2.0 ብለው ባመጡት Update Farm ማድረግ ተጀምሯል - Inviting Friends - Withdraws - Level Up የመጀመሪያው ዙር ላመለጣችሁ አዳዲስ በሚመጡ Task እየሰራችሁ Farm ማድረግ ትችላላችሁ https://t.me/notcoin_bot?start=er_33832662
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
Notcoin የመጀመሪያው Phase ላመለጣችሁ አሁን በራሳቸው ቦት Notcoin 2.0 ብለው ባመጡት Update Farm ማድረግ ተጀምሯል - Inviting Friends - Withdraws - Level Up የመጀመሪያው ዙር ላመለጣችሁ አዳዲስ በሚመጡ Task እየሰራችሁ Farm ማድረግ ትችላላችሁ https://t.me/notcoin_bot?start=er_33832662
Show all...
🤔 1😐 1🤝 1
Photo unavailableShow in Telegram
Notcoin የመጀመሪያው Phase ላመለጣችሁ አሁን በራሳቸው ቦት Notcoin 2.0 ብለው ባመጡት Update Farm ማድረግ ተጀምሯል - Inviting Friends - Withdraws - Level Up የመጀመሪያው ዙር ላመለጣችሁ አዳዲስ በሚመጡ Task እየሰራችሁ Farm ማድረግ ትችላላችሁ Abel: Notcoin የመጀመሪያው Phase ላመለጣችሁ አሁን በራሳቸው ቦት Notcoin 2.0 ብለው ባመጡት Update Farm ማድረግ ተጀምሯል - Inviting Friends - Withdraws - Level Up የመጀመሪያው ዙር ላመለጣችሁ አዳዲስ በሚመጡ Task እየሰራችሁ Farm ማድረግ ትችላላችሁ https://t.me/notcoin_bot?start=er_34463027 https://t.me/notcoin_bot?start=er_33832662
Show all...
ፈርዖን ሕፃናትን አስገድሎ በጣለበት የባሕር ውኃ ሰምጦ ሞተ:: ጎልያድም ብዙዎችን በገደለበት በገዛ ሰይፉ ተቀላ:: ያዕቆብ ኤሳውን ባታለለበት የበግ ደም በልጆቹ ተታለለ:: ሐማም መርዶክዮስን ለማስገደል ባስቆመው እንጨት ራሱ ተሰቀለበት:: በሌላው ላይ የሚደረግ ክፋትና ወጥመድ ተመልሶ እንዲመጣ ሰማይ ቤትን አይጠብቅም:: እግዚአብሔር በምድር ለሚሠራ ግፍ በምድርም ይመልሳል:: ለዚህም ነው "ለሌላው ሰው የምትቆፍረውን ጉድጓድ ብዙ አርቀህ አትቆፍረው አንተም ልትገባበት ትችላለህና" የሚባለው::
Show all...
👏 6💯 6🙏 4🤗 3👍 1
"አንተ ራስህ ለገዛ ወንድምህ ጨካኝና ይቅር የማትል ኾነህ ሳለስ እግዚአብሔር እንዲራራልህና እንዲምርህ እንዴት መለመን ይቻልሃል? "ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል፡፡ አዎ! አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው፡፡ በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበት ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል፡፡ አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ሰድበኸዋል፡፡ እንግዲህ ተመልከት! ነቢዩ፡- “እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፡3)፡፡ እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውንና ሌላ ሰው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያውቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢአታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቈጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድየለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቻቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቈጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው? አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነገር ትጠነቀቃለህ፡፡ ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ፡፡ ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቡናህ ግን እዚህም እዚያም፣ በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል፤ ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው። እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #ትምህርት_በእንተ_ሐውልታት_መጽሐፍ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው
Show all...
❤‍🔥 7👍 4😭 2
#ሰኔ_30 #መጥምቁ_ቅዱስ_ዮሐንስ ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ። ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው። በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጐረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው። በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን አይሆንም ዮሐንስ ይባል አለች። ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም አሏት። አባቱንም ጠቅሰው ማን ሊባል ትወዳለህ አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ። ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው። ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ። የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እነሆ ብሎ ኢሳይያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለሱ እንዲህ አለ። በፊትህ ጐዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልእክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ። ራሱ መድኃኒታችንም ስለርሱ ሲናገር ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም ብሏል። ይህ የእግዚአብሔርን ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና። ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ፡፡ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱም እኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)
Show all...
🙏 2
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.