cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን

በዚህ ቻናል ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ 📚 የየዕለቱ ስንክሳሮች በጠዋት ❄ ትምህርቶች 🎤 ስብከቶች 🎶 መዝሙሮች 📄 ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፎች በpdf 💒የቅዳሴ ምስባክ 🎤 ወቅታዊ የቤ/ክ ዜናዎች ይተላለፉበታል፡፡

Show more
Advertising posts
635
Subscribers
+224 hours
+427 days
+9930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ሚያዝያ_28 ሚያዝያ ሃያ ስምንት በዚች ቀን በኮራሳት ተራራ በገድል ተጠምዶ የሚኖር #ቅዱስ_ሜልዮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ መቅሱር ከሚባል አገር #ቅዱስ_ብስጣውሮስ በሰማዕትነት አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ሜልዮስ_ዘደብረ_ኮራሳን ሚያዝያ ሃያ ስምንት በዚች ቀን በኮራሳት ተራራ በገድል ተጠምዶ የሚኖር ቅዱስ ሜልዮስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም አባት ኮራሳት በሚባል አገር በተራራ ባሉ ዋሻዎች ከሁለት አርድእቱ ጋራ ይኖር ነበር። የኮራሳት ንጉሥ ሁለቱ ልጆቹ ወደዚያ ወጡ ከእርሳቸውም ጋራ አገልጋዮች አሉ አራዊትን አጥምደው በፍላፃዎች ይገሉ ዘንድ መረባቸውን ተክለው አርባ ምዕራፍ ያህል ሔዱ። መረቡን በጠቀለሉት ጊዜ ይህን ቅዱስ አባት ማቅ ለብሶ ጠጉሩም የረዘመ ሁኖ አገኙት። የንጉሥ ልጆችም በአዩት ጊዜ ፈሩ አንተ ሰው ነህን ወይም መንፈስ ብለው ጠየቁት እርሱም በዚህ ተራራ ውስጥ የምኖር ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የምሰግድ ሰው ነኝ ብሎ መለሰላቸው። እነርሱም ከእሳትና ከፀሐይ በቀር አምላክ የለም እንዳንገድልህ ሠዋላቸው አሉት። እርሱም እሳትና ፀሐይ የተፈጠሩ ናቸው እናንተም ተሳስታችኋል ፍጥረቶችን በፈጠረ በዕውነተኛ አምላክ ታምኑ ዘንድ እኔ እለምናችኋለሁ ብሎ መለሰላቸው። በዚያን ጊዜ ይህን አባት ሁለቱን አርድእትም ይዘው ጽኑ ሥቃይ አሠቃዩአቸው በዚህ ወር በዐሥራ ሦስት የሁለቱን አርድእት ራሳቸውን ቆረጡአቸው የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ። አረጋዊ ቅዱስ ሜልዮስን ግን ዐሥራ አምስት ቀን ያህል ሲአሠቃዩት ኖሩ ከዚህ በኋላ በመካከላቸው አቆሙት አንዱ በፊት አንዱ በኋላ ሁነው በፍላፃ ይነድፉት ጀመር። እርሱም በእናንተ ላይ ክፉ ያልሠራውን ለመግደል ሁለታችሁ ስለተስማማችሁ እንዲሁ እንደሥራችሁ በፍላፃችሁ ነገ ትሞታላችሁ አላቸው። ሰምተውም አልፈሩም ነፍሱን እስከሚአሳልፍና ምስክርም ሆኖ የሰማዕትነት አክሊልን እስከሚቀበል ነደፉት እንጂ። በማግሥቱም እንደልማዳቸው ለአደን ወጡ የዱር አህያም አገኙ ተከትለውም ቀስታቸውን አስፈነጠሩ እግዚአብሔርም ፍላፃቸውን ወደልባቸው መለስ ቅዱስ ሜልዮስም እንደተናገረባቸው ሞቱ። በዚህ ቅዱስም እጅ ጌታችን ተአምራትን ገለጠ በአንዲት ዕለትም አልፎ ሲሔድ በመንገድ ላይ የሞተ ሰው አገኘ የአገር ሰዎች ግን አንዱን መነኰስ አንተ ነህ የገደልከው ብለው ያዙት። ቅዱስ ሜልዮስም ጸለየ የሞተውንም በውኑ የገደለህ ይህ መነኵሴ ነውን አለው ያን ጊዜ የሞተው ተነሥቶ እርሱስ አልገደለኝም ነገር ግን ብዙ ገንዘቤን ከአንድ ቄስ ዘንድ አደራ አስጠበቅሁ ስለዚህ ገደለኝ ከዚህም ጣለኝ አለ ደግሞ እንዲህ ብሎ ለመነው ዕገሌ ወደሚባል ወደዚያ ቄስ ሒደህ ገንዘቤን ከርሱ ተቀብለህ ለልጆቼ ስጥ ቅዱስ ሜልዮስም እስከ ትንሣኤ ቀን በሰላም አርፈህ ተኛ እኔ ገንዘብ አከፋፋይ ዳኛ አይደለሁም አለው ያንጊዜም ተኛ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ብስጣውሮስ በዚህችም ቀን መቅሱር ከሚባል አገር ቅዱስ ብስጣውሮስ በሰማዕትነት አረፈ። የዚህም ቅዱስ አባቱ ጻድቅ ሰው ነው እናቱን ግን ሰይጣን አስቷት ወደ እስልምና ገባች እርሱም ፈሪሀ እግዚአብሔርን እየተማረ እስከሚጐለምስ አደገ አካለ መጠንም አድርሶ ሚስት አገባ ከርሷም ልጆችን ወለደ። ብዙ ዘመናትም በአለፉ ጊዜ አንገተ ደንዳና በቀለኛ ሰው በእርሱ ላይ ተነሥቶበት ወደ እስላሞች መኳንንት ሒዶ ሰው ወደ እኛ ሕግ ቢገባ ልጆቹም ሃይማኖቱን ይከተላሉ ይህ ብስጣውሮስ ግን ከሕጋችን የተለየ ነው ብሎ ነገር ሠራበት። የእስላሞች ዳኞችም በሰሙ ጊዜ መልዕክተኞች ልከው ወደርሳቸው ወደ ሸንጎ አቀረቡት ስለ ሃይማኖቱም ጠየቁት ክርስቲያን እንደሆነ ያለ ፍርሀት ክርስቲያን ነኝ ብሎ ታመነ። ዳኛው ግን ይሸነግለው ዘንድ በፍቅር ይናገረው ጀመረ ከከበረችና ከቀናች ሃይማኖቱ ይመልሰው ዘንድ ብዙ ስጦታዎችን እንደሚሰጠው ቃል ገባለት ቅዱሱ ግን ከቶ አልተመለሰም ወደ ስጦታውም ከቶ ልቡ አላዘነበለም። ከዚህ በኋላ ወደ ግዞት ቤት ወስደው በእግረሙቅ እንዲአሥሩት በአንገቱም የተበሳ ታላቅ ግንድ አሥረው በግንባሩ ደፍተው በኲስ ላይ እንዲጥሉት መኰንኑ አዘዘ። እንዲሁም አደረጉበት እስከ ሦስት ቀን በእሥር ቤትም ሳለ ፀዐዳ ርግብ መጥቶ ጋረደው ስለዚህም የእሥር ቤቱ ጠባቂ ምስክር ሆነ። ከዚህም በኋላ ዳኞች ወደ ሸንጎ አስቀርበው ከእንግዲህ አንታገሥህም ወደ ሃይማኖታችን ከምትገባና ወይም በእሳት ከምናቃጥልህ ምረጥ አሉት። እርሱም እኔ ከእናንተ ጋራ ለዘላለሙ ዕድል ፈንታ የለኝምና የወደዳችሁትን አድርጉ ብሎ መለሰላቸው። በዚያን ጊዜም እጅግ ተቆጡ ያለ ርኀራኄ ይደበድቡት ዘንድ አዘዙ ያገር ሰዎችም በጫማቸው መቱት አንዲት ሴትም መጥታ በጫማዋ መታችው ወዲያውኑ እጆቿ ደረቁ። ከዚህም በኋላ ባለ ሰይፍ ከመኰንኑ ታዝዞ ወጣ ሰይፉንም መዝዞ ሳያቋርጥ መላልሶ አንገቱን መታው። ምቱም ወደ ጐን ሒዶ ጆሮውን ቆረጠው አመታቱ ክፉ ስለ ሆነ ከሥሮቿ ብዙ ደም ፈሰሰ። ከዚህም ደግሞ ተዉት ወደ እምነታቸው ሊአስገቡት እምቢ በአላቸውም ጊዜ ሁለተኛ ሰይፉን መዝዞ ሰያፊው የከበረች አንገቱን ቆረጠው በመንግሥተ ሰማያትም የምስክርነት አክሊልን ተቀበለ። ሥጋውንም ከእሳት ጨመሩ ግን አልተቃጠለም። ዘመዶቹም መጥተው በድኑን ወደአገሩ ወሰዱ። በቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ ጐን ቀበሩት። የክብር ባለቤት ጌታችንም ብዙ ድንቆች ተአምራትን ከሥጋው ገለጠ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም ቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።
Show all...
👍 1
ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት ሰኞ ሰኑይ ማእዶት ይባላል እንደ ቤተክርስቲያን ይትባሕል ከትንሣኤ እስከ ዳግማዊ ትንሣኤ ያለውን ሳምንት እንደ አንድ እሁድ እናከብራለን። ለዚህም ነው ዕለታቱን እንደ ሰንበት እናከብራቸው ዘንድ በፍትሐ ነገሥት ላይ አባቶቻችን ትእዛዝ የቀረጹልን። ማእዶት ማለት መሻገር ማለት ነው። አደወ ማለት ተሻገረ ማለት ሲሆን ማእዶት መሸጋገሪያ ማለት ሊሆን ነው። ማእዶት የትንሣኤ እሑድ ማግስት ጌታ ክርስቶስ በትንሣኤው ምዕመናንን ከሞት ወደ ሕይወት ያሻገረበት ቀን የትንሣኤው ማሳሰቢያ ነው። (ከሣቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ገጽ ፻፶) መሻገር በዕብራይስጥ ፓሳሕ ከሚባለው ቃል ይመሳሰላል ትርጉሙም ፋሲካ መሻገር ማለፍ የሚል ትርጉም ይሰጣል። ሁላችን እንደምናውቀው እስራኤላውያን ከሚያክብሯቸው አበይት በዓላት አንዱም ፋሲካ ነው። ምክንያታቸው ደግሞ እግዚአብሔር ከሞተ በኩር ያሳለፋቸውን ዕለት ያስቡበታል። ቤተክርስቲያናችንም ይህንን በዓለ ትንሣኤን የፋሲካ በዓል የማክበሯ ምሥጢር ወይም የትንሣኤው ምሥጢር ነፍሳት በአምላካችን ትንሣኤ ከሞት ወደ ሕይወት ፣ ከአሳር ወደ ክብር ፣ ከሲዖል ወደ ገነት መሻገራቸውን በማሰብ አማናዊው ፋሲካ ወይም አሸጋጋሪው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብላ ታምናለች። እናምናለን። ቅዱስ ጳውሎስ በብሉይ ኪዳን በታረደው የፋሲካ በግ (ዘዳ፲፮:፮) ምትክ አማናዊው ክርስቶስ እንደታረደልን እና ሞት ላያገኘን በሕይወት ለሕይወት እንዳሸጋገረን ሲገልጥ እንዲህ ብሏል:-"" እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤" (፩ ቆሮ ፭:፯) ቅዱስ ጳውሎስ ስለ እርሾም ሆነ ስለ አዲሱ ሊጥ በምሳሌ የሚነግረን እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ፋሲካ ሲያከብሩ ያደርጉት የነበረ ስርዓትን ነው። ይኸውም ፋሲካን ያከበሩት ገና ከነጻነት በፊት ነው። ምክንያቱ ደግሞ ከላይ እንዳየነው ከሞተ በኩር መቅሰፍት ለመዳን እና ከእግዚአብሔር ፍርድ ለመዳን ነበር። በአዲስ ኪዳንም ያለን ክርስቲያኖች በተለይ ይህንን ዕለት ወይም ማእዶትን ስናስብ አምላካችን ከሞት ወደ ሕይወት እንዳሻገረን ፣ ከአሳር ወደ ክብር እንዳሳለፈን ፣ ከድካም ወደ ኃይል እንዳሻገረን ፣ ሁላችን ወደ መንግሥተ ሰማያት ፋሲካችን በሆነው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሸጋገርን በማመን ሊሆን ይገባል። የፋሲካው ጌታ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞት ላይ እንድንዘባበትበት ሞትን ፣ ፍርሃትን ፣ ጭንቀትን ፣ ተስፋ መቁረጥን ፣ ሐዘንን ፣ ለቅሶን ፣ ትካዜን ፣ ድካምን ፣ ሥጋትን እና መቃብርን ሁሉ አጥፍቶ አሻግሮናል። ክብር ማዕዶታችን ለሆነ ለእርሱ ይሁን። አሜን ክብር ይግባውና አምላካችን የሰው ልጅ ሞትን እንዲሻገር ሁለት ነገሮች(እምነት እና ምግባር ) እንደሚያስፈልጉት በመዋለ ስብከቱ እንዲህ ሲል አስተምሮናል:- "እውነት እውነት እላችኋለሁ ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።" (ዮሐ፭:፳፬-፳፭) ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ዕለቷ ፋሲካ እንደሆነችና እንደሰትባት ዘንድ የተገባች እንደሆነች እንዲህ ሲል በመዝሙሩ አዚሞታል:- " ፋሲካ ዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ (ይህቺ የፋሲካ ዕለት ልዩ ናት) ፣ ዛቲ ዕለት ንትፈሳሕ በቲ (በዚህ ዕለት ሐሴት እናድርግባት)..."
Show all...
እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ የወይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኃያልም ሰው፤ ጠላቶቹንም በኋላው ገደለ። መዝ ፸፯፥፷፭ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው  አደረሳችሁ ። https://t.me/orthdoxbot https://t.me/orthdoxbot
Show all...
👍 3