cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

#ማራናታ

"ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።"

Show more
Advertising posts
208
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የማለዳ ትምህርት /02/ ቀን 02/06/16 ዓ/ም አንደኛው ሳምንት (ቅዳሜ) ርዕስ፦ አንተም ለዚህ ዘመን ተመርጠሃልና ዕድልህን ተጠቀም                   ክፍል (2) ውድ የማራናታ ተለግራም ቻናል ቤተሰብ እና የማለዳ ትምህርት ተከታዮች እንዴት አደራችሁ? የኢየሱስ ፈቃድ ሆነና ዛሬም የማለዳ ትምህርት በትላንትናው ርዕስ ይዘንላችሁ ቀርበናል። ትላንት እንደተማሪነው" አንተም ለዚህ ዘመን ተመርጠሃልና ዕድልህን ተጠቀም" በሚል ርዕስ ትንሽ ላካፍላችሁ። በእርግጥ የተሰጠንን ዕድል አለመጠቀም ብዙ ዋጋ ያስከፍላናል። አንድ አምላክ አምነን በስሙ የተጠመቅን ሁላችንም የተመረጠ ትውልድ ነን፣ የተለየ ወገነ ነን፣ የንጉሱ ካህናት ነን፣ ተመርጠናል። ነገር ግን ተመርጠን ዕድላችንን አለመጠቀም የእኛ ድርሻ ነው። ትላንትም እንደተማሪነው በየዘመናቱ እግዚአብሔር የተመረጠ ትውልድ ያዘጋጅ ነበር። በተበላሸና በተረከሰ ትውልድ መካከል እግዚአብሔር ለክብሩ የሚሆን ትውልድ ያዘጋጃል። ምክንያቱም ብዙ የተበላሹ ትውልድ እውነተኛውን መንገድ ቀይረው ወደ ሐሰት እንዳይለወጡ ለመንገዱ የሚጠነቀቅ አምላክ ስለሆነ ከብዙ የተበላሹ ትውልድ መካከል በቁጥር ጥቅት ብሆኑም እውነተኛና ሰርአቱን የሚጠብቁ ትውልድ ያስቀምጣል። ስለዚህ በስሙ የተጠመቃችሁ፣ በመንፈስ ቅዱስ የታተማችሁ ትውልድ ከእናንተ ሌላ የተመረጠ ትውልድ የለምና አትጠራጨሩ፣ እኔም አለው እንደ? አትበሉ፣ ለዚህ ዘመን መፍትሔ የሚያመጣው ከእናንተ ሌላ ትውልድ የለምና እገለ ብኖር አትበሉ። ዛሬ እናንተ የሚትቆጥሩት አባቶቻችን በዘመናቸው ተመርጠው አላማቸውን አውቀው ዕድላቸውን ተጠቅመው ድል ነስተው አልፈዋሉ። ዛሬ ተራው የእኛ ነው እንጅ የእነርሱ አይደለም። ለዘመናቸው የተመረጡትን አንዳንዶቹን ላስታውሳችሁ፦    ☞ ናዖድ መሳፍ 3፥15 በዘመኑ ሠርቶ አለፈ    ☞ ድቦራ መሳ 4፥4  በዘመኑዋ ሠርታ አለፈች    ☞ ኢያኤል መሳፍ 5፥24 በዘመኑዋ ሠርታ አለፈት    ☞ ገድኦን  መሳፍ 6፥12 በዘመኑ ሠርቶ አለፈ    ☞ ኤልያስ፣ ኤልሳዕ...... መቁጠር አልችልም ብዙዎች ዕድላውን ተጠቀሙ፤ በዛውም ልክ ያልተጠቀሙም አሉ ቁጠሩ። እነርሱማ ለዚያች ዘመን የተዘጋጁ ናቸው። እነርሱ ብኖሩ!! ብለን ዛሬ የሚንተኛ እኛ ኖረን ምን ሠርተናል? ያኔ ስሰራ የነበረ እግዚአብሔር ዛሬ ተቀይሯል? ተዓምራቱ አልቆ ነው? እኛና ተዓምራት ሠሪው አልተገናኘንም እንጅ። የእኛ ድክመትና ዕድላችንን አለመጠቀማችን ነው እንጅ። 📌 እድላችንን እንዳንጠቀም ያደረገን ምንድነው? ❀ ትዕቢት፦  የተመረጠ ትውልድ የሚያረክስ ነገር ዋና ትዕብት ነው። ትዕቢት ከተጀመረ ለመፍትሔ እንደተመረጠ ያስረሳል። ምናልባት አንድ ትንሽ ተአምራት ሰርቶ ከሆነ የጥርው ማረጋገጫ ጭላንጭል ነገር መታየት ከጀመረ ሰጭውን ይረሳል። እግዚአብሔር ይህንን አደረገልኝ ከማለት አልፎ እኔ እኔ እኔ ማለት ይጀምራል። በዚህ ምክንያት ነው ለሰጭው ባለቤት የሚከፋው። ዋናው የእግዚአብሔር ባህርይ ምንድነው ስባል ክብሩን ለሌላው አለመስጠት ነው። " እኔ እንዲህ አደረግሁ ከማለት እግዚአብሔር እንዲህ አደረገልኝ" እንድንል ይፈልጋል። አለዚያ ትዕቢተኛ መሆን ይመጣል፤ ትዕብት ስመጣ ደግሞ ውድቀትም ቅርብ ነው። ሙሴ ከንዓንን ሳይገባ እያዬ የቀረው ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ። በአንድ ቃላት ብቻ ወደ ከንዓን ሳይገባ ከቀረ እኛስ ዛሬ የሰጠንን አመስግነን እናውቃለን? " ትዕቢት ጥፋትን፥ ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል። " (መጽሐፈ ምሳሌ 16:18) (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕ. 5) ---------- 5፤ እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል። 6፤ እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤ 7፤ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። ❀ ጥሪውን ለይቶ አለማወቅ፦ ይህም ዕድላችንን እንዳንጠቀም ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱ ነው። ☞ ሳምሶን ጥሪውን ለይቶ አውቆ ዕድሉን በአግባቡ ብጠቀም ኖሮ ከወደቁት ጋር ምሳሌ ሆኖ አልተጻፈም ነበር። ☞ ሳኦልም እንደዛው...... ☞ ብኩርናውን ያቃለለ ኤሳው ቢኩርናውን ጠብቆ ብሄድ ኖሮ የክፉ ምሳሌ ሆኖ አልተጻፈም። ዕድሉን አልተጠቀመም፤ ጥሪውን ስላቃሌለ የወደቁት ምሳሌ ሆነ። በዚህ ዘመንም ስንት ሰው ነው እገለ ተብለበ ስማቸውንም ማንሳት የሚያስፈሩ ሰወች ጥሪያቸውን አቃልለው ዕድላቸውን አበላሸተው፣ ተራ ቦታ የቀሩት? ✅ ወንድሞች እህቶች እኛስ ዛሬ በየትኛው ምሳሌ ውስጥ ልንመደብ ነው? ⚛ ከተመረጡ ትውልድ ምን ይጠበቃል? ☞ እግዚአብሔርን መፍራት ☞ ጥሪውን በማስተዋል መቀበል ☞ የጸጋው ባለቤት ማመስገን ☞ በፍቅር መመላለስ ☞ እርስ በርስ መከባበር፤ ትህትናን መልበስ ጸጋ ማለት በአንድ ጊዜ ብቻ መጥቶ የሚቀመጥ ሳይሆን እለት በእለት እያደገ እየተጨመረ የሚሄድ ነው። አለዚያም እንደገና መሞትም ይቻላል። በአገባቡ ካልያዝነው ይሞታል። ነገር ግን በመሃል እንድቆምና እንድሞት የሚያደርግው የተጠሪው ድርሻ ነው። ስለዚህ ጸጋችን እንድያድግ በእኛ ዘመንም ተአምራት እንድሠራ መጸለይና የሰጠንንን ዕድል መጠቀም ወሳኝ ነገር ነው። እኛ በድካማችን ምክንያት ቁጭ ብለን እያዬን ስንት ተአምራት ቀርቷል እድላችንን ብንጠቀም ኖሮ በየቀኑ አዳዲስ ተአምራቶች ይሠሩ ነበር። ስለዚህ ዕድላችንን መጠቀም ከዛሬውኑ እንጀምር እያልኩኝ የዛሬው ት/ት በዚህ አበቃለሁ       መልካም ቀን!!!! በዚህ ማለዳ ትምህርት ላይ መስተካከል አለበት የምትሉት ሀሳብ ጥቆማ አስተያያት ካለ ከታች ባለ chanal ላይ ማድረስ ትችላላችሁ። 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MARANETHA https://t.me/MARANETHA https://t.me/MARANETHA አይ ኤሄ ይቅርብኝ የሚትሉት ከሆናችሁ እንደአማራጭ ያቀረብንላቸው የማራናታ Group አለ በእሱ ላይ commentachun ማድረስ ትችላላችሁ👇👇👇👇    እግዚአብሔር የልመናችን ድምጽ ይስማልን አሜን!!! 🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂🤷‍♀       🌻የማለዳ ትምህርት በየማለዳ🌻         🌸የውሎአችን ስንቅ ከማራናታ🌸             
Show all...
#ማራናታ

"ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።"

የማለዳ ትምህርት /02/ ቀን 02/06/16 ዓ/ም አንደኛው ሳምንት (ቅዳሜ) ርዕስ፦ አንተም ለዚህ ዘመን ተመርጠሃልና ዕድልህን ተጠቀም                   ክፍል (2) ውድ የማራናታ ተለግራም ቻናል ቤተሰብ እና የማለዳ ትምህርት ተከታዮች እንዴት አደራችሁ? የኢየሱስ ፈቃድ ሆነና ዛሬም የማለዳ ትምህርት በትላንትናው ርዕስ ይዘንላችሁ ቀርበናል። ትላንት እንደተማሪነው" አንተም ለዚህ ዘመን ተመርጠሃልና ዕድልህን ተጠቀም" በሚል ርዕስ ትንሽ ላካፍላችሁ። በእርግጥ የተሰጠንን ዕድል አለመጠቀም ብዙ ዋጋ ያስከፍላናል። አንድ አምላክ አምነን በስሙ የተጠመቅን ሁላችንም የተመረጠ ትውልድ ነን፣ የተለየ ወገነ ነን፣ የንጉሱ ካህናት ነን፣ ተመርጠናል። ነገር ግን ተመርጠን ዕድላችንን አለመጠቀም የእኛ ድርሻ ነው። ትላንትም እንደተማሪነው በየዘመናቱ እግዚአብሔር የተመረጠ ትውልድ ያዘጋጅ ነበር። በተበላሸና በተረከሰ ትውልድ መካከል እግዚአብሔር ለክብሩ የሚሆን ትውልድ ያዘጋጃል። ምክንያቱም ብዙ የተበላሹ ትውልድ እውነተኛውን መንገድ ቀይረው ወደ ሐሰት እንዳይለወጡ ለመንገዱ የሚጠነቀቅ አምላክ ስለሆነ ከብዙ የተበላሹ ትውልድ መካከል በቁጥር ጥቅት ብሆኑም እውነተኛና ሰርአቱን የሚጠብቁ ትውልድ ያስቀምጣል። ስለዚህ በስሙ የተጠመቃችሁ፣ በመንፈስ ቅዱስ የታተማችሁ ትውልድ ከእናንተ ሌላ የተመረጠ ትውልድ የለምና አትጠራጨሩ፣ እኔም አለው እንደ? አትበሉ፣ ለዚህ ዘመን መፍትሔ የሚያመጣው ከእናንተ ሌላ ትውልድ የለምና እገለ ብኖር አትበሉ። ይህን ስላችሁ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፦ አንድ ጊዜ በመክና ውስጥ እየሄድኩ ነበርና እኔን ያላወቁ ልጆች ነበሩ፤ አኔም አላቃቸውምና ስለ ሐዋርያዊት ዶክትርን መነጋገር ጀመርንና ስመስክራቸው፦ አንድ ልጅ "አንተ በዚህ አከባቢ የሚትኖር ብሆን ኖሮ...... ብሎ እኔን ማድነቅ ጀመረ። እኔ ግን ለዚህ አከባቢ እንድመስክሩና እንድያስተምሩ ሌሎች ወንድሞችን አስቀምጧል፤ እኔ ግን ለዚህ አከባቢ አልተፈጠርኩም እንደ እኔ ያሉ ወንድሞች አሉና እነርሱ የሚሉአችሁን ስሙ...." አልኩት። እንደዚሁም በየቦታው እግዚአብሔር ያስቀመጠው ትውልድ ዛሬም አሉ፣ ግን እድላቸውን አልተጠቀመም እንጅ። ዛሬ እናንተ የሚትቆጥሩት አባቶቻችን በዘመናቸው ተመርጠው አላማቸውን አውቀው ዕድላቸውን ተጠቅመው ድል ነስተው አልፈዋሉ። ዛሬ ተራው የእኛ ነው እንጅ የእነርሱ አይደለም። ለዘመናቸው የተመረጡትን አንዳንዶቹን ላስታውሳችሁ፦    ☞ ናዖድ መሳፍ 3፥15 በዘመኑ ሠርቶ አለፈ    ☞ ድቦራ መሳ 4፥4  በዘመኑዋ ሠርታ አለፈች    ☞ ኢያኤል መሳፍ 5፥24 በዘመኑዋ ሠርታ አለፈት    ☞ ገድኦን  መሳፍ 6፥12 በዘመኑ ሠርቶ አለፈ    ☞ ኤልያስ፣ ኤልሳዕ...... መቁጠር አልችልም ብዙዎች ዕድላውን ተጠቀሙ፤ በዛውም ልክ ያልተጠቀሙም አሉ ቁጠሩ። እነርሱማ ለዚያች ዘመን የተዘጋጁ ናቸው። እነርሱ ብኖሩ!! ብለን ዛሬ የሚንተች እኛ ኖረን ምን ሠርተናል? ያኔ ስሰራ የነበረ እግዚአብሔር ዛሬ ተቀይሯል? ተዓምራቱ አልቆ ነው? እኛና ተዓምራት ሠሪው አልተገናኘንም እንጅ። የእኛ ድክመትና ዕድላችንን አለመጠቀማችን ነው እንጅ። 📌 እድላችንን እንዳንጠቀም ያደረገን ምንድነው? ❀ ትዕቢት፦  የተመረጠ ትውልድ የሚያረክስ ነገር ዋና ትዕብት ነው። ትዕቢት ከተጀመረ ለመፍትሔ እንደተመረጠ ያስረሳል። ምናልባት አንድ ትንሽ ተአምራት ሰርቶ ከሆነ የጥርው ማረጋገጫ ጭላንጭል ነገር መታየት ከጀመረ ሰጭውን ይረሳል። እግዚአብሔር ይህንን አደረገልኝ ከማለት አልፎ እኔ እኔ እኔ ማለት ይጀምራል። በዚህ ምክንያት ነው ለሰጭው ባለቤት የሚከፋው። ዋናው የእግዚአብሔር ባህርይ ምንድነው ስባል ክብሩን ለሌላው አለመስጠት ነው። " እኔ እንዲህ አደረግሁ ከማለት እግዚአብሔር እንዲህ አደረገልኝ" እንድንል ይፈልጋል። አለዚያ ትዕቢተኛ መሆን ይመጣል፤ ትዕብት ስመጣ ደግሞ ውድቀትም ቅርብ ነው። ሙሴ ከንዓንን ሳይገባ እያዬ የቀረው ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ። በአንድ ቃላት ብቻ ወደ ከንዓን ሳይገባ ከቀረ እኛስ ዛሬ የሰጠንን አመስግነን እናውቃለን? " ትዕቢት ጥፋትን፥ ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል። " (መጽሐፈ ምሳሌ 16:18) (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕ. 5) ---------- 5፤ እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል። 6፤ እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤ 7፤ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። ❀ ጥሪውን ለይቶ አለማወቅ፦ ይህም ዕድላችንን እንዳንጠቀም ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱ ነው። ☞ ሳምሶን ጥሪውን ለይቶ አውቆ ዕድሉን በአግባቡ ብጠቀም ኖሮ ከወደቁት ጋር ምሳሌ ሆኖ አልተጻፈም ነበር። ☞ ሳኦልም እንደዛው...... ☞ ብኩርናውን ያቃለለ ኤሳው ቢኩርናውን ጠብቆ ብሄድ ኖሮ የክፉ ምሳሌ ሆኖ አልተጻፈም። ዕድሉን አልተጠቀመም፤ ጥሪውን ስላቃሌለ የወደቁት ምሳሌ ሆነ። በዚህ ዘመንም ስንት ሰው ነው እገለ ተብለበ ስማቸውንም ማንሳት የሚያስፈሩ ሰወች ጥሪያቸውን አቃልለው ዕድላቸውን አበላሸተው፣ ተራ ቦታ የቀሩት? ✅ ወንድሞች እህቶች እኛስ ዛሬ በየትኛው ምሳሌ ውስጥ ልንመደብ ነው? ⚛ ከተመረጡ ትውልድ ምን ይጠበቃል? ☞ እግዚአብሔርን መፍራት ☞ ጥሪውን በማስተዋል መቀበል ☞ የጸጋው ባለቤት ማመስገን ☞ በፍቅር መመላለስ ☞ እርስ በርስ መከባበር፤ ትህትናን መልበስ ጸጋ ማለት በአንድ ጊዜ ብቻ መጥቶ የሚቀመጥ ሳይሆን እለት በእለት እያደገ እየተጨመረ የሚሄድ ነው። አለዚያም እንደገና መሞትም ይቻላል። በአገባቡ ካልያዝነው ይሞታል። ነገር ግን በመሃል እንድቆምና እንድሞት የሚያደርግው የተጠሪው ድርሻ ነው። ስለዚህ ጸጋችን እንድያድግ በእኛ ዘመንም ተአምራት እንድሠራ መጸለይና የሰጠንንን ዕድል መጠቀም ወሳኝ ነገር ነው። እኛ በድካማችን ምክንያት ቁጭ ብለን እያዬን ስንት ተአምራት ቀርቷል እድላችንን ብንጠቀም ኖሮ በየቀኑ አዳዲስ ተአምራቶች ይሠሩ ነበር። ስለዚህ ዕድላችንን መጠቀም ከዛሬውኑ እንጀምር እያልኩኝ የዛሬው ት/ት በዚህ አበቃለሁ       መልካም ቀን!!!! በዚህ ማለዳ ትምህርት ላይ መስተካከል አለበት የምትሉት ሀሳብ ጥቆማ አስተያያት ካለ ከታች ባለ chanal ላይ ማድረስ ትችላላችሁ። 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MARANETHA https://t.me/MARANETHA https://t.me/MARANETHA አይ ኤሄ ይቅርብኝ የሚትሉት ከሆናችሁ እንደአማራጭ ያቀረብንላቸው የማራናታ Group አለ በእሱ ላይ commentachun ማድረስ ትችላላችሁ👇👇👇👇    እግዚአብሔር የልመናችን ድምጽ ይስማልን አሜን!!! 🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂🤷‍♀       🌻የማለዳ ትምህርት በየማለዳ🌻         🌸የውሎአችን ስንቅ ከማራናታ🌸             
Show all...
#ማራናታ

"ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።"

3
#አልወጣም #ድንቅ_መልእክት ነው ስሙት በጌታ #ነብይ ዘኔ △△Join Us△△ share💯share💯share 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MARANETHA https://t.me/MARANETHA https://t.me/MARANETHA #ይ🀄️ላ🀄️ሉ☝☝☝☝☝
Show all...
2
የማለዳ ትምህርት ቀን 01/06/16 ዓ/ም 48ኛ ሳምንት (አርብ) ርዕስ፦ አንተም ለዚህ ዘመን ተመርጠሃልና ዕድልህን ተጠቀም                  ክፍል አንድ (1) በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር የተወደዳችሁ ውድ የአንድ አምላክ ልጆች እና የማራናታ ተለግራም ቻናል ቤተሰብ እንድሁም የማለዳ ትምህርት ተከታዮች ደህና አደራችሁ? በምሕረቱ ተሸክሞን ከቀን ወደ ቀን እያሻገረን ለዛሬ ያበቃን አምላካችን ለዘላለም ይባረክ እያልኩኝ ለዛሬ ወደተዘጋጀው የማለዳ ትምህርታችን አልፋለሁ። የዛሬው የማለዳ ትምህርታችን ከላይ በርዕሱ ላይ እንዳያችሁት " አንተም ለዚህ ዘመን ተመርጠሃልና ዕድልህን ተጠቀም" በሚል ርዕስ ነው። እንግድህ ይህ ትምህርት ክፍል በጣም ሰፊ ሀሳብ የሚያካትት ብሆንም እኔ ግን በትንሹ ጸጋየ በተረዳሁት መጠን አጠር ያለ ሀሳብ አካፍላችኋለሁ፣ እኔ ትንሽ ሀሳብ ስሰጣችሁ እናንተ ታሰፋላችሁ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራዕይ ድረስ ስንመለከት በየዘመናቸው የተጠሩና የተመረጡ ሰወች በቁጥሪቸው መግለጽ ባልችልም በጣም ብዙ ሰወች እንደሆኑ ለማንም ግልጽ ነው። አንዳንዶቹ የተመረጡትን ዓላማ አውቀው ዓላማቸውን የፈጸሙ ናቸው፤ አንዳንዶቹ ግን በሩጫቸው ላይ ደክመው በመንገድ ወድቀው የቀሩ ናቸው። በመንገድ ላይ የቀሩት ተመርጠው ዕድላቸውን በአግባቡ ያልተጠቀሙ ናቸው። ብሆንም ግን እግዚአብሔር በየዘመኑ የተመረጠ ትውልድ ያስነሳል። "መርጬ ያነሳው ሰው ጠፍቷልና ከእንግዲህ አላነሳም" አይልም። ምክንያቱም በምህረቱ ባለጠጋ ስለሆነ ለሕዝቡ ይራራልና። ተመርጦ እድሉን አለመጠቀምና በመንገድ ላይ መቅረት የተመረጠ ሰው ድርሻ ስሆን እግዚአብሔር ግን በየዘመኑ የተመረጠ ትውልድ ያነሳል። ለዚህም በምሳሌነት የኤልያስን ዘመን ስንመለከት፥ ኤልያስ ብቻዬ ቀረሁ፣ የእኔ እድል ይጥፋ፣ ግደለኝ እያለ እየለቀሰ ባለበት ሰአት እግዚአብሔር ግን አትፍራ፣ ገና አንተ ያላወከው ትውልድ አለኝ፣ ብቻህ አይደለህም፣ ይልቅ ሂድና ኢዩን ቀባው ብሎ ስያጽናናው እናያለን። (ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕ. 11) ---------- 2፤ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝብ አልጣላቸውም። መጽሐፍ ስለ ኤልያስ በተጻፈው የሚለውን፥ በእግዚአብሔር ፊት እስራኤልን እንዴት እንደሚከስ፥ አታውቁምን? 3፤ ጌታ ሆይ፥ ነቢያትህን ገደሉ መሠዊያዎችህንም አፈረሱ እኔም ብቻዬን ቀረሁ ነፍሴንም ይሹአታል። 4፤ ነገር ግን አምላካዊ መልስ ምን አለው? ለበአል ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀርቼአለሁ። 5፤ እንደዚሁም በአሁን ዘመን ደግሞ በጸጋ የተመረጡ ቅሬታዎች አሉ። እንደዚሁም በአሁኑ ዘመናችንም በጸጋ የተመረጡ ቅሬታወች አሉ። ነገር ግን ከባዱ ነገር የተመረጡ ትውልድ መሆናቸውን መዘንጋትና አልባሌ ቦታዎች ጊዜያቸውን ማሳለፍ ነው እንጅ። ማለትም የተመረጡ መሆናቸውን አለማስተዋል እድላቸውን ያጠፋል እንጅ። አሁን በዚህ ዘመን በየቦታው የሚንሰማው ነገር ስሰለቸንና ሀሰተኞች ነብያት እንደበዙ ስንሰማ፦ ውይ በዚህ ዘመን ኤልያስ ብኖር!!! እንላለን። ነገር ግን ኤልያስ የተዘጋጀውና የተመረጠው ለዚያች ዘመን ነው እንጅ ለዚህ ዘመን አይደለም። ለዚህ ዘመን የተመረጥነው አንተ/ቺ እና እኔ ነኝ። ኤልያስ በዘመኑ ዕድሉን ተጠቅሞ ተዓምራትን ሠርቶ ለኤልሳ አሳለፈ፤ ኤልሳዕም ዕድሉን ተጠቅሞ አለፈ...... አእያለ እያለ ዛሬ ተራው ለእኛ ደረሰ። አንተና እኔ ግን ያኔ እነርሱ የሠሩትን እንተርካለን እንጅ ዛሬ ምን ሠራን? በ2ኛ ጴጥ 2፥7 ስንመለከት በሎጥ ዘመንም ትውልድ ረከሱ፤ ሎጥ ግን ብቻው ቀርቶ ነፍሱን ያስጨነቅ ነበር። ለዚህ ዘመንም በረከሱት ትውልድ መካከል አንድ የተመረጠ ትውልድ ነፍሳቸውን እያስጨነቁ ያሉ አሉ። ከእነዚህ ከተመረጡትና አላማቸውን ካወቁት ጋር እንድንሰለፍ ኢየሱስ ይርዳን። ነገር ግን አንድ የሚያሳዝነው ነገር በየዘመኑም እግዚአብሔርን የማያውቅ ትውልድ ይነሳል። ስለዚህ እኛ እራሳችንን ስንፈትሽ በየትኛው ትውልድ ውስጥ ተመድበናል ብለን መጠየቅ ያስፈልገናል። በመሳፍንት ዘመን እግዚአብሔርንና እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው የሠራውን ተዓምራት ያላወቀ ትውልድ ስነሳ እግዚአብሔር ግን ቸር አምላክ ስለሆነ ሌላ መሳፍንት በመካከላቸው ያስነሳቸዋል። የተነሱ መሳፍንቶችም አንዳንዶቹ ዕድላቸውን ተጠቅመው እንደ ሀሳቡ አገልግለው አሳልፈዋሉ፣ አንዳንዶቹ ግን አልተጠቀሙም። (መጽሐፈ መሳፍንት ምዕ. 2) ---------- 10፤ ትውልድ ሁሉ ደግሞ ወደ አባቶቻቸው ተከማቹ፤ ከእነዚያም በኋላ እግዚአብሔርን ለእስራኤልም ያደረገውን ሥራ ያላወቀ ሌላ ትውልድ ተነሣ። 11፤ የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነ ነገር አደረጉ፥ በኣሊምንም አመለኩ። 12፤ ከግብፅ ምድርም ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፥ በዙሪያቸውም ካሉት ከአሕዛብ አማልክት ሌሎችን አማልክት ተከተሉ፥ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔርንም አስቈጡ። 13፤ እግዚአብሔርንም ትተው በኣልንና አስታሮትን አመለኩ። ዛሬም እኔና አንተ/ቺ የተመረጥን ትውልድ መሆናችንን ብናውቅ ኖሮ ለዚህ ትውልድ መፍትሔ ሊንሆን እንችላለን፣ እድላችንን እንጠቀም። እግዚአብሔር ለዚህ ትውልድ መፍትሔ አድርጎ እንድያስታጥቀን ጸልየን እንውጣ፣ ነገም በዚህ ርዕስ እንቀጥላለን።                       መልካም ቀን!! ነገም በዚህ ርዕስ ይቀጥላል............ በዚህ ማለዳ ትምህርት ላይ መስተካከል አለበት የምትሉት ሀሳብ ጥቆማ አስተያያት ካለ ከታች ባለ ቦት ላይ ማድረስ ትችላላችሁ። 👇👇👇👇👇👇 @DINKU19 አይ ኤሄ ይቅርብኝ የሚትሉት ከሆናችሁ እንደአማራጭ ያቀረብንላቸው የማራናታ Group አለ በእሱ ላይ commentachun ማድረስ ትችላላችሁ👇👇👇👇👇👇                https://t.me/MARANETHA እግዚአብሔር የልመናችን ድምጽ ይስማልን አሜን!!! 🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂🤷‍♀       🌻የማለዳ ትምህርት በየማለዳ🌻         🌸የውሎአችን ስንቅ ከማራናታ🌸                     🌼መልካም ቀን!!!🌼
Show all...
#ማራናታ

"ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።"

2👍 1
ከኢየሱስ ወዴት ሊኬድ!? 1. ጥበብ ቢባል---የሚሻሩትን የዚህችን ዓለም ጥበብ የሚያስንቅ ከየትኛውም ስመ ጥር የትምህርት ተቋማት የማይገኝ ሰማያዊ ጥበብ የሚቀዳብህ የጥበብና የዕውቀት ሁሉ መዝገብ አንተ! “የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና።”   — ቆላስይስ 2፥3 2. ብልጥግና ቢባል----ምንጭህ ዝንተ ዓለም የማይነጥፍ እውነተኛ የሰው ልጅ አንጡራ ሃብት አንተ! አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤”   — ሮሜ 10፥12 3. እርካታ ቢባል........ሲያሻህ ከጭንጫ ድንጋይ ማር አፍልቀህ ሲያሻህ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ምድረ በዳውን አጥግበህ እሱም ሳያንስህ በቀኝህ ባለው የዘላለም ፍስሃ ነፍሳችንን አምነሽንሸህ የምታኖራት እውነተኛ የእርካታ ምንጭ አንተ! “እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም፤ ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ።”   — ኢሳይያስ 55፥1 4. ክብር ቢባል........እስትንፋስህን በአፍንጫው እፍ ብለህበት እንጂ: ደሞ ከአፈር የተሰራ የሰው ልጅ ከአንተ ውጪ ምን ክብር አለውና? የክብር ዘውድ የማዕረግ አክሊል አንተ! “በዚያ ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለቀሩት ሕዝቡ የክብር ዘውድና የጌጥ አክሊል ይሆናል፤”   — ኢሳይያስ 28፥5 “ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ።”   — ሮሜ 8፥18 5. ተስፋ ቢባል----ለህያው ተስፋ: ለማይጠፋ እድፈት ለሌለበት ለማያልፍም ርስት እንደ ምህረትህ ብዛት የጠራኸን አንተ! “አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን?   — መዝሙር 39፥7
Show all...
2
🔥ሰላም ለእናንተ ይብዛላችሁ እያለሁ ዛሬ በአንደ ነገር ተባበሩኝ ሁላችንም ነው እያልኩ ያለሁት በጌታ ፍቅር ታዘዙን አሁን የእናንተ እገዛ የሚያስፈለገን ግዜ ላይ መተናል አይዧችሁ በአካውን ገንዘብ አስገቡ አልላችሁም በዚህ ቻና የተጠቀማችሁ አንዲሁም በቅርቡ የተቀላቀላችሁ ሁላችንም እገዛ ያስፈልገናል እሱም ወደ እዚህ ቴሌግራም ቻና 7 ክርስቲያን ጉዋደኛዎቻችሁን በዚህ ቻናል ሊንክ እንዲቀላቀሉ አደርጉ የአገልገሎታችን ተደራሽነቱ መሰፋት ስላለበት ይሄን ነው እንተ ይህ ስታደርጉ  ለጉአደኞቻችሁ ውለታ ተወሉላችዋላችሁ በእርግጠኝነት እደምታደረጉ እተማመንባችዋለሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ 🙌 💠የእግዚአብሔርየሆነ የእግዚአብሔርንስራ ይሰራሉ                   #ይቀላቀላሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MARANETHA https://t.me/MARANETHA https://t.me/MARANETHA https://t.me/MARANETHA
Show all...
#ማራናታ

"ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።"

🔥ሰላም ለእናንተ ይብዛላችሁ እያለሁ ዛሬ በአንደ ነገር ተባበሩኝ ሁላችንም ነው እያልኩ ያለሁት በጌታ ፍቅር ታዘዙን አሁን የእናንተ እገዛ የሚያስፈለገን ግዜ ላይ መተናል አይዧችሁ በአካውን ገንዘብ አስገቡ አልላችሁም በዚህ ቻና የተጠቀማችሁ አንዲሁም በቅርቡ የተቀላቀላችሁ ሁላችንም እገዛ ያስፈልገናል እሱም ወደ እዚህ ቴሌግራም ቻና 7 ክርስቲያን ጉዋደኛዎቻችሁን በዚህ ቻናል ሊንክ እንዲቀላቀሉ አደርጉ የአገልገሎታችን ተደራሽነቱ መሰፋት ስላለበት ይሄን ነው እንተ ይህ ስታደርጉ  ለጉአደኞቻችሁ ውለታ ተወሉላችዋላችሁ በእርግጠኝነት እደምታደረጉ እተማመንባችዋለሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ 🙌 💠የእግዚአብሔርየሆነ የእግዚአብሔርንስራ ይሰራሉ                   #ይቀላቀላሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MARANETHA https://t.me/MARANETHA https://t.me/MARANETHA https://t.me/MARANETHA
Show all...
#ማራናታ

"ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።"