cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዝዖን ዜና

Show more
Advertising posts
1 256
Subscribers
-1124 hours
-1487 days
-56930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ዲቪ 2025 ዛሬ ምሽት ይፋ ሆኗል። የአሜሪካ ዲቪ (Diversity Visa) ሎተሪ 2025 ዛሬ ምሽት ይፋ መደረጉን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት አሳውቋል። መ/ቤቱ፥ አመልካቾች መመረጥ አለመመረጣቸውን / ደርሷቸው እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማየት የሚችሉት በ dvprogram.state.gov/ESC/ ላይ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት #ብቻ መሆኑን አሳስቧል። ከዚህ ውጭ የዲቪ ውጤት የሚታይበት ምንም አይነት መንገድ የለም። N.B. ዲቪ የሚደርሳቸው ሰዎች የሚስጥር ቁጥሩን እስከ ቀጣይ አመት መስከረም መጨረሻ ቀናት መያዝ አለባቸው። ምናልባትም  " ዲቪ ደርሷችኃል ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው የምንደውለው፣ ኢሜል / ቴክስት መልዕክት የሚንልከው " የሚሉ አጭበርባሪ ስለሚኖሩ ጥንቃቄ አድርጉ ተብሏል። እንደ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ፥ የዲቪ ተመራጭ መሆን ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ ዋስትና አይሆንም። የዲቪ ሎተሪ ተመራጭ መሆን የቪዛ ጥያቄ ለማቅረብ የመጀመሪያው መስፈርት ሲሆን በቀጥታ ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ ዋስትና አይሰጥም። @tikvahethiopia
Show all...
#DV2025 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ (Diversity Visa) 2025 አሸናፊዎች ነገ ይፋ ይደረጋሉ። ለዲቪ (Diversity Visa) 2025 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov/ESC/ ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ። NB. የማረጋገጫ ቁጥር ማመልከቻው ሲሞላ የተሰጠ ነው። ይህ ቁጥር የጠፋበት Forgot Confirmation Number በማለት አስፈለጊ መረጃ በመሙላት በኢሜል አዲስ ቁጥር ማግኘት ይቻላል። ውጤቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽት 1 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ይሆናል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል ፣ ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው ምንደውለው / ይህን ኢሜል / ቴክስት የምንልከው " በማለት #የሚያጭበረብሩ_አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁ አሳስቧል። አንድ አመልካች ዲቪ 2025 ደርሶት እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማወቅ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ከላይ የተጠቀሰው ድረገጽ መሆኑን አስገንዝቧል። አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ (ኢትዮጵያ ጨምሮ) ፣ እስያ ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 55 ሺህ ሰዎችን በዲቪ (DV) ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች። @ZION_NEWS
Show all...
በምሥራቅ ወለጋ ዞን ሁለት ጭንቅላት ያለው ህጻን ተወለደ። በኦሮሚያ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ሲሬ ወረዳ ትላንት ከረፋዱ 10 ሰዓት ላይ አንዲት እናት በተደረገላት የቀዶ ህክምና ከአንገት በላይ ሁለት ጭንቅላት (Dicephalic parapagus) ያለው ወንድ ልጅ፤ ክብደቱ 4.2 ኪ.ግ የሚመዝን በሰላም ተገላግላለች። ልጁ የተወለደው በሲሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ ሲሆን በሆስፒታሉ የህጻናት ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ቶኩማ ባይሳ የልጁን ቀጣይ ህይወት ለመወሰን ወደ ከፍተኛ ሆስፒታል ሪፈር እንዲደረግ መወሰኑን ገልጸዋል። ዶ/ር ቶኩማ አክለውም፥ እናትየው የመጀመሪያ ልጇ እንደሆነ ጠቅሰው አሁን ላይ በጥሩ ጤንነት ላይ እንዳለች ገልጸዋል። ዘገባው የወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው። @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
Show all...
👍 1
#AddisAbaba " የ4 ሰዎች አስክሬን ከተለያየ ቦታ አውጥተናል። ...‘13 ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ’ የሚለው ትክክለኛ መረጃ አይደለም " - አቶ ንጋቱ ማሞ ከቀናት በፊት “ ሰዓሊተ ምህረት ጀርባ ያድሩ የነበሩ 13 የጎዳና ተዳዳሪ ልጆች በጎርፍ ተወስደው ሕይወታቸው እንዳለፈ አካባቢው ላይ ተነግሯል ” ሲሉ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። በስፍራው የእሳት አደጋ ሠራተኞች ፣ ዋናተኞች፣ የፌደራል ፓሊስ አባላት ተገኝተው አስክሬን ለማውጣት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደተመለከቱ የገለጹ ሲሆን ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ስለጉዳዩ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ሥራ አመረራር ኮሚሽንን ጠይቋል። የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በሰጡት ምላሽ፤ “ ባለፈው እንደገለጽነው የ4 ሰዎች አስከሬን አውጥተናል። ‘13 ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ’ የሚለው ትክክለኛ መረጃ አይደለም። ጥቆማ ከሆነ ሊሆን ይችላል ” ብለዋል። “ ምክንያቱም በየትኛውም ጉዳይ ሕይወቱ ያለፈ ሰው ቢኖር ወይ እሳት አደጋ ወይ ፓሊስ ነው የሚያነሳው፤ በግለሰብ ደረጃ አስከሬን አንስቶ ቀብር ያለ አይመስለኝም ” ነው ያሉት። “ በቦታው ነበርን ግን ይሄ አሁን የተጠቀሰው ቁጥር (13) አስከሬን አልተገኘም። ያገኘነው 4 አስከሬን ነው ” ያሉት አቶ ንጋቱ ፣ 4ቱን አስክሬን ለፓሊስ አስረክበናል ሲሉ አስረድተዋል። 4 አስክሬን የት አካባቢ ነው የተገኘው ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ ሰዓሊተ ምህረትም፤ ከተለያዩ ቦታም ነው የገኘነው። ጎዳና ተዳዳሪ ይሁኑ፣ እዛው አካባቢ ነዋሪ ይሁኑ እኛ መረጃ የለንም። ፓሊስ ነው የሚያረጋግጠው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። “ አሁን የሚሉት ጥቆማ ትክክለኛነቱ የሚረጋገጥ ከሆነ ከፓሊስ ጋር ሆነን ፍለጋ እናካሂዳለን። አንዳንድ ጊዜ ጥቆማ ትክክል አይደለም የሚል መደምደሚያ ላይኖር ይችላል” ሲሉ ተናግረዋል። ጎርፉ ተቋማትን ጨምሮ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን፣ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለው ኑሯቸውንና እንቅስቃሴያቸውን ወንዝ አካባቢ ባደረጉ ሰዎች እንደሆነ፣ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ፣ አደጋ ከደረሰም በ #939  የኮሚሽኑ ስልክ በፍጥነት ደውለው እንዲያሳውቁ አስገንዝበዋል።  @ZION_NEWS
Show all...
#AddisAbaba " የ4 ሰዎች አስክሬን ከተለያየ ቦታ አውጥተናል። ...‘13 ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ’ የሚለው ትክክለኛ መረጃ አይደለም " - አቶ ንጋቱ ማሞ ከቀናት በፊት “ ሰዓሊተ ምህረት ጀርባ ያድሩ የነበሩ 13 የጎዳና ተዳዳሪ ልጆች በጎርፍ ተወስደው ሕይወታቸው እንዳለፈ አካባቢው ላይ ተነግሯል ” ሲሉ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። በስፍራው የእሳት አደጋ ሠራተኞች ፣ ዋናተኞች፣ የፌደራል ፓሊስ አባላት ተገኝተው አስክሬን ለማውጣት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደተመለከቱ የገለጹ ሲሆን ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ስለጉዳዩ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ሥራ አመረራር ኮሚሽንን ጠይቋል። የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በሰጡት ምላሽ፤ “ ባለፈው እንደገለጽነው የ4 ሰዎች አስከሬን አውጥተናል። ‘13 ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ’ የሚለው ትክክለኛ መረጃ አይደለም። ጥቆማ ከሆነ ሊሆን ይችላል ” ብለዋል። “ ምክንያቱም በየትኛውም ጉዳይ ሕይወቱ ያለፈ ሰው ቢኖር ወይ እሳት አደጋ ወይ ፓሊስ ነው የሚያነሳው፤ በግለሰብ ደረጃ አስከሬን አንስቶ ቀብር ያለ አይመስለኝም ” ነው ያሉት። “ በቦታው ነበርን ግን ይሄ አሁን የተጠቀሰው ቁጥር (13) አስከሬን አልተገኘም። ያገኘነው 4 አስከሬን ነው ” ያሉት አቶ ንጋቱ ፣ 4ቱን አስክሬን ለፓሊስ አስረክበናል ሲሉ አስረድተዋል። 4 አስክሬን የት አካባቢ ነው የተገኘው ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ ሰዓሊተ ምህረትም፤ ከተለያዩ ቦታም ነው የገኘነው። ጎዳና ተዳዳሪ ይሁኑ፣ እዛው አካባቢ ነዋሪ ይሁኑ እኛ መረጃ የለንም። ፓሊስ ነው የሚያረጋግጠው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። “ አሁን የሚሉት ጥቆማ ትክክለኛነቱ የሚረጋገጥ ከሆነ ከፓሊስ ጋር ሆነን ፍለጋ እናካሂዳለን። አንዳንድ ጊዜ ጥቆማ ትክክል አይደለም የሚል መደምደሚያ ላይኖር ይችላል” ሲሉ ተናግረዋል። ጎርፉ ተቋማትን ጨምሮ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን፣ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለው ኑሯቸውንና እንቅስቃሴያቸውን ወንዝ አካባቢ ባደረጉ ሰዎች እንደሆነ፣ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ፣ አደጋ ከደረሰም በ #939  የኮሚሽኑ ስልክ በፍጥነት ደውለው እንዲያሳውቁ አስገንዝበዋል።  #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Show all...
#CAR የ77 ዓመቱ የቀድሞው የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፍራንሷ ቦዚዜ ላይ የእስር ማዘዣ ትዕዛዝ ወጣ። ማዘዣው የወጣው ሠራዊታቸው ከእአአ 2009 እስከ 2013 ባለው ጊዜ ውስጥ በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል ፈጽሟል በሚል ነው። ማዘዣውን ያወጣው በባንጊ ላይ የተሰየመውና ከሃገር ውጪ ካሉ ፍርድ ቤቶች ጋራ የሚሠራው ልዩ የወንጀል ችሎት ነው። ይህ ችሎት በእ.አ.አ 2015 በተመድ እገዛ የተቋቋመ እንደሆነ ተገልጿል። የቀድሞ የሀገሪቱ መሪ ቦዚዜ ፦ - ግድያ፣ - አስገድዶ መሰወር፣ - ሰቆቃ፣ - መድፈር እና ሌሎች ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን ፈፅመዋል በሚል ተከሰዋል። ቦዚዜ በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡት በእ.አ.አ 2003 ሲሆን ከአስር (10) ዓመታት በኋላ ከወንበራቸው ተወግደዋል። ቦዚዜ ካለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ #በስደት ጊኒ ቢሳዉ የሚገኙ ሲሆን፣ ከዛ ሆነው ዋናኛ የሚባል አማጺ ቡድን በመምራት ላይ ይገኛሉ። ጊኒ ቢሳዉ ተጠርጣሪውን ቦዚዜ #ይዛ እንድታስረክብ ተጠይቋል። #VOA @ZION_NEWS
Show all...
👍 1
“ ማን እንደገደላቸው መረጃ የለኝም ፤  በተተኮሰባቸው ጠይት ተገድለዋል ዞሮ ዞሮ ” - ስሜ አይገለጽ ያሉ ባለስልጣን በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ የላስታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው ጤና ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ትላንት በጥይት  መገደላቸውን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋገጧል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ አንድ የሰሜን ወሎ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ባለስልጣን በሰጡት ቃል፤ “ ትላንት ከዞን ግምገማ ቆይተው ሲመለሱ ነው ግድያው የተፈጸመው። የሞቱት የወረዳው አስተዳዳሪ የወረዳው ጤና ኃላፊ ናቸው ” ብለዋል። “ ኩል መስክ የሚባል ቦታ ነው ግድያው የተፈጸመው ” ሲሉ ተናግረዋል። ሌላ የተጎዳ ሰው አለ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፣ “ ሌላ እዛው ኩል መስክ የቀበሌ ሊቀመንበር የተጎዳ አለ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። “ አርብና ቅዳሜ ግምገማ ነበረ፤ እዚያ ተመልሰው ኩል መስክ ቆይተዋል ለሁለት ቀናት ” ሲሉም አክለዋል። ግድያውን የፈጸመው ማነው ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ “ እስካሁን መረጃው የለኝም፤ በተተኮሰባቸው ጠይት ተገድለዋል ዞሮ ዞሮ ” ብለው፣ የገዳዮቹን ማንነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል። “ ዞሮ ዞሮ በግድያ የሚመለስ አንድም ጥያቄ የለም። እነዚህ (ሟቾቹ) የሕዝብ አስተዳዳሪዎች ናቸው። ሕዝብም ጥበቃ ሊያደርግላቸው ይገባል እንጂ መሞት አለባቸው ብዬ አላስብም ” ብለዋል። @ZION_NEWS
Show all...
“ ማን እንደገደላቸው መረጃ የለኝም ፤  በተተኮሰባቸው ጠይት ተገድለዋል ዞሮ ዞሮ ” - ስሜ አይገለጽ ያሉ ባለስልጣን በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ የላስታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው ጤና ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ትላንት በጥይት  መገደላቸውን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋገጧል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ አንድ የሰሜን ወሎ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ባለስልጣን በሰጡት ቃል፤ “ ትላንት ከዞን ግምገማ ቆይተው ሲመለሱ ነው ግድያው የተፈጸመው። የሞቱት የወረዳው አስተዳዳሪ የወረዳው ጤና ኃላፊ ናቸው ” ብለዋል። “ ኩል መስክ የሚባል ቦታ ነው ግድያው የተፈጸመው ” ሲሉ ተናግረዋል። ሌላ የተጎዳ ሰው አለ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፣ “ ሌላ እዛው ኩል መስክ የቀበሌ ሊቀመንበር የተጎዳ አለ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። “ አርብና ቅዳሜ ግምገማ ነበረ፤ እዚያ ተመልሰው ኩል መስክ ቆይተዋል ለሁለት ቀናት ” ሲሉም አክለዋል። ግድያውን የፈጸመው ማነው ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ “ እስካሁን መረጃው የለኝም፤ በተተኮሰባቸው ጠይት ተገድለዋል ዞሮ ዞሮ ” ብለው፣ የገዳዮቹን ማንነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል። “ ዞሮ ዞሮ በግድያ የሚመለስ አንድም ጥያቄ የለም። እነዚህ (ሟቾቹ) የሕዝብ አስተዳዳሪዎች ናቸው። ሕዝብም ጥበቃ ሊያደርግላቸው ይገባል እንጂ መሞት አለባቸው ብዬ አላስብም ” ብለዋል። @ZION_NEWS
Show all...
" ወደቡ ዝግጁ ነው፤ መንገዱም ከሞላ ጎደል ዝግጁ ነው " - ሰዓድ አሊ ሽሬ ሶማሌላንድ የበርበራ ወደብ #የኢትዮጵያን 30% ጭነት እንዲያስተናግድ ትፈልጋለች። ለዚህ ደግሞ አስፈላጊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልጸለች። አሁን ላይ ስምምነት እንዲፈረም እየተሰራ ነው ተብሏል። የሶማሌላንድ የፋይናንስ ሚኒስትር ሰዓድ አሊ ሽሬ ምን አሉ ? " አካላዊ መሰረተ ልማትን በተመለከተ ወደቡን ገንበተናል። ☑ አንድ ኪሎሜትር የሚሰፋ የመርከብ ማቆሚያ፤ ☑ ኮንቴነሮችን መጫንና ማውረድ የሚችሉ ክሬኖች ያሉት ዓለም አቀፍ ወደብ አለ፤ ☑ ከበርበራ ወደብ ድንበር ላይ እስከምትገኘው #ውጫሌ ያለውን መንገድ ገንብተናል፤ ስለዚህ ወደቡ ዝግጁ ነው። መንገዱም ከሞላ ጎደል ዝግጁ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በበርበራ ነጻ የኢኮኖሚ ዞኖች አሉን። የነዳጅ ማጠራቀሚያ ጋኖች ከነዳጅ ጫኝ መርከቦች ማራገፊያ አዘጋጅተናል። አካላዊ ክፍል ከሞላ ጎደል አልቋል። ለምሳሌ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል የወደብ አጠቃቀም ስምምነት (Transit Agreement) ሊኖረን ይገባል። የጉምሩክ ስርዓቶቻችን ማገናኘት ወይም ማስተሳሰር ይኖርብናል ይህ አሁንም በስራ ላይ ነው። የመጓጓዣ ስምምነትም ማባጀት አለብን ይሄም ሂደት ላይ ነው። ከስርዓት አኳያ በሂደት ላይ የሚገኙ የተወሰኑ ጉዳዮች አሉ " ብለዋል። እንደ ሶማሌላንድ የወደቦች አስተዳደር ዳይሬክተር ሰኢድ ሀሰን አብዱላሂ ማብራሪያ ደግሞ ፥ ➡ ህጋዊው ጉዳይ በመንግስታት መካከል የሚፈርም እንደሆነ ➡ ስምምነቱ እየተጠናቀቀ ስለመሆኑ ➡ በአንድ እና ሁለት ቀሪ ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ➡ በመጪው 60 ቀናት ስምምነቱ ሊጠናቀቅ እንደሚችልን ከ60 ቀናት በኃላ እንደሚፈረምና ኮሪደሩ ጥቅም መስጠት ይጀምራል። በተጨማሪ ፦ ° የUAE ዲፒ ወርልድ እና ሶማሌላንድ ከበርበራ ወደብ 15 ኪ/ሜ ርቀት ነጻ የኢኮኖሚ ቀጣራ ማበጀታቸውን ° ነጻው የኢኮኖሚ ቀጠና ከወደቡ ወደ ኢትዮጵያ በሚያመራው መንገድ ላይ እንደሚገኝ ° ነጻው የኢኮኖሚ ዞን 300 ሺህ ካሬ ጫማ የሚሰፋ ከማብሰያ ዘይት ማሸጊያ ፋብሪካ ጭምር አለው። ከ6 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ከሶማሌላድ እና ዲፒ ወርልድ ጋር በተፈራረመችው ስምምነት በበርበራ ወደብ ልማት 19% ድርሻ ነበራት ግን አልዘለቀችበትም። ግን አሁን ኢትዮጵያ ወደቡ ላይ ድርሻ እንዲኖራት ትፈልጋለች። የበርበራ ወደብ ያለበት ቀጠና ለዓለም አቀፍ የመርከብ እንቅስቃሴ ወሳኝ በመሆኑ ሶማሌላንድ እና ዲፒ ወርልድ አሁንም ማስፋታ ይፈልጋሉ። ግዙፍ የኮንቴነር ተርሚናል ለመገንባት ሙከራ እየተደረገ መሆኑ፣ ተጨማሪ 600 ሜትር የሚሰፋ የመርከብ ማቆሚያ ፣ 7 ግዙፍ የእቃ መጫኛና ማውረጃ ለመጨመር እቅድ እንዳለ ታውቋል። ይህን ተከትሎ የበርበራ ወደብ መርከብ መቆሚያ 1650 ሜርት እንደሚሆን 2 ሚሊዮን ኮንቴነርም ማስተናገድ እንደሚችል ለኢትዮጵያም ትልቅ አማራጭ መሆኑ በሶማሌላንድ ባለስልጣናት ተገልጿል። Credit - DW (Eshete Bekele) @tikvahethiopia
Show all...
👍 1
" ... ኢትዮጵያ ጎረቤታችን ናት፤ ከእነሱ ጋር ቢዝነስ መስራት እንፈልጋለን " - ሰኢድ ሀሰን አቡዱለሂ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች / #UAE / ንብረት የሆነው ዱባይ ወርልድ ኩባንያ የሚያስተዳድረው የበርበራ ወደብ የኢትዮጵያን 30 በመቶ ጭነት እንዲያስተናግድ የሶማሌላንድ ባለስልጣናት ማቀዳቸው ተሰምቷል። ለዚህ የወደብ አጠቃቀምና የጉምሩክ ሥርዓቶችን የተመለከተ ስምምነት በኢትዮጵያና ሶማሌላንድ መካከል መፈረም አለበት። ስምምነቱ በሚቀጥሉት 60 ቀናት ሊፈረም እንደሚችል የሶማሌላንድ የወደቦች አስተዳደር አሳውቋል። የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ሰኢድ ሀሰን አቡዱለሂ ፥ " ኢትዮጵያ ጎረቤታችን ናት፤ ከእነሱ ጋር ቢዝነስ መስራት እንፈልጋለን በአሁን ወቅት የወደብ አጠቃቀም ስምምነት ወይም Transit Agreement እያዘጋጀን ነው። አንዴ ስምምነቱን ከተፈራረምን በመጀመሪያው ዓመት ከኢትዮጵያ ጭነት 30% እናስተናግዳለን። " ብለዋል። ከወራት በፊት እ.አ.አ ጥር 1 ላይ ኢትዮጵያ እና ሶማሌላድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት (MoU) በተመሳሳይ ወደ ተግባር የሚገባበት የመጨረሻው ስምምነት በ2 ወራት ገደማ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሌላንድ ባለስልጣናት ገልጸዋል። መግባቢያ ምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ውይይቶች ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን የቴክኒክ ኮሚቴዎችም መታጨታቸውን ተናግረዋል። ይህ የመግባቢያ ስምምነት ወደ #መጨረሻው ደርሶ ወደ ተግባር ከገባ ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ የባህር ዳርቻ የጦር ሰፈር በሊዝ ኪራይ የምታገኝ ሲሆን ሶማሌላንድ በበኩሏ ለረጅም አመታት ስትፈልገው የነበረውን እውቃና የማግኘት እድል እንደሚፈጥርላት ባለስልጣናቱ አመልክተዋል። ለንግድ ስራ ሌላ ወደብ መገንባት ሳያስፈልግ የበርበራ ወደብን ኢትዮጵያ እንደምትጠቀምበት ገልጸዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው ያገኘው። @tikvahethiopia
Show all...
👍 1