Orthodox My Religion Mary my Mother 21
Open in Telegram
በዚህ ቻናል ላይ ኦርቶዶክሳዊ ❖ ❖ መዝሙሮችን ❖ ትምህርቶችን ❖ መንፈሳዊ ምስሎችን ❖ መንፈሳዊ ፅሁፎችን ያገኛሉ orthodox_photo
Show more268
Subscribers
+224 hours
+157 days
+4430 days
Posts Archive
#ሰአሊ_ለነ_ቅድስት
"እንደ እንሰሳት ለሆንን ፤ ከእንሰሳትም ስለከፋነው ስለ እኛ ለምኚ !አማልጂም!!!"
_የዘማሪ_ዲያቆን_ሄኖክ_ሞገስ_የንስሓ_መዝሙራት_ስብስብ_mahtot_o_TNf9pJDI_251.ogg31.81 MB
መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር
መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር (፪)
ይቀሰቅሰኛል ለስሙ እንድዘምር (፪)
ፊቱን እያጣፉት እየተንገላታ
በጦር እየወጉት ይሰጣል ይቅርታ
እነርሱ እየጠሉት እርሱ ይወዳቸዋል
አስረው ሲጎትቱት ይከተላቸዋል
አዝ= = = = =
ፃድቁን ኃጥዕ ነው እውነቱን ሐሰት
እያሉ ሲጮሁ ይሰቀል ይሙት
እየመረመረው ፍጡር ፈጣሪን
ክርስቶስን አስሮ ፈታው በርባንን
አዝ= = = = =
ጀርባውን ሲገርፉት በሚያቃጥል ጅራፍ
በምህረት ያዛቸው በይቅርታው እቅፍ
ጨክነው ሲያጠጡት መራራ ሐሞት
ደም ውሃ ፈሰሰ ጎኑን ሲወጉት
አዝ= = = = =
ግምጃን አለበሱት ቀሚሱን ገፈው
በራሱም አኖሩ እሾህ ጎንጉነው
የአይሁድ ንጉስ ሆይ እያሉ ዘበቱ
ለህይወት ሆናቸው የኢየሱስ ሞቱ
መዝሙር
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
"በፍቅር ላዚምህ"
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
በፍቅር ላዚምህ ፍቅር ነህ ጌታዬ
በደም የገዛኸኝ ባለውለታዬ
በቃየን ጎዳና እንዳልጓዝ እርዳኝ
በቀናው መንፈስህ ወደ ጽድቅ ምራኝ
በልቤ ትከሻ በቀል ተሸክሜ
ወንድሜን ጠልቼ ካንተ ፊት መቆሜ
ፃድቅ ቢያስመስለኝ በሰዎች እይታ
ጉዴን ስለምታውቅ እስራቴን ፍታ(፪)
አዝ = = = = =
ዙሪያውን ተከቦ በእሾህ ጥላቻ
ስብከቴ መዝሙሬ ሆኗል የቃል ብቻ
ማረኝ እና ይብቃኝ ለኃጢአት መዝመቱ
ፍቅር የሌለው ሰው ነው የከንቱ ከንቱ(፪)
አዝ = = = = =
አሸንፈህልኝ እኔ ግን ተሸነፍኩ
በእጄ ማልነካውን ለሰው እያሸከምኩ
በቃሌ ጠርቼ በግብሬ ረገምኩህ
በአስመሳይ ማንነትእየሸነገልኩህ(፪,)
"አብሠራ ገብርኤል"
አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
ወይቤላ /2/ ትወልዲ ወልድ
ሚካኤል መላዕክ በክነፍ ፆራ
መንጦላዕት ደመና ሰወራ
ንፅህት በድንግልና አልባቲ ሙስና
ተወልደ ወልድ እምኔሐ
ገብርኤል ማርያምን አበሰራት አበሰራት
ወንድ ልጅም ትወልጃለሺ አላት
ሚካኤል መላዕክ በክንፋ ከለላት
የሰማይ መጋረጃውን ሸፈናት
ንፅህት ናትና በድንግልና /2/
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
አዳም በጥፋቱ ከገነት ሲባረር
በሚካኤል ክንፎች ቀድሞ አይቶሽ ነበር
ሔዋንን ሲጠራት ሕይወቴ ነሽ አላት
እንደሚድን አውቆ ድንግል በአንች ምክንያት
ንፅህት ናትና በድንግልና /2/
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
እግዚአብሔር የላከው የከበረው መላዕክ
ድንግል ሆይ ለክብርሽ ዐየን ሲንበረከክ
በፍቅር በትህትና በፍፁም ሰላምታ
የጌታ ሰው መሆን የነገረሽ በደስታ
ንፅህት ናትና በድንግልና /2/
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
ደስተኛዬቷ ሆይ ደስ ይበልሽ ድንግል
የአብ ቃል ክርስቶስ ሥጋሽን ይለብሳል
አንቺም ትይዋለሽ ስሙን ኢየሱስ
መድኋኒት ነውና ለሥጋ ወነፍስ
ንፅህት ናትና በድንግልና /2/
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
አንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ
አንደ ዘኬርያስ ሳትጠራጠሪ
ይሁነኒ ብለሽ ቃልን ተቀበልሽ
ከፍጥረት ማነው አንቺ የሚመስልሽ
ንፅህት ናትና በድንግልና /2/
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @ctwobek
🔸🔹🔸 @ctwobek
🔸 @ctwobek
"እንደበደሌ አልከፈልከኝም"
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
እንደ በደሌ
ሊቀ.መዘ ቴዎድሮስ ዮሴፍ
===========
እንደበደሌ አልከፈልከኝ
ፍቅር ነህና እያለፍከኝ
ምን እከፍላለሁ ላንተ የሚሆን
ታቀው የለም ወይ ችሎታዬን/2/
አዝ---------------//
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል
ታርቀዋለህ የኔን በደል
እንደምትወደኝ አቃለሁ እኔ
ባስመርርህም በእድሜ ዘመኔ
አዝ-------------//
ከሰው ሁሉ ጋር ብትፈራረድ
የትኛው ይሆን ፀድቆ የሚሄድ
የአለምን ሐጥያት ደምህ ሸፈነው
የተፈወስኩት እኔም በእርሱ ነው
አዝ------------------//
ዘመኔ እንደ ሳር መሆኑን አስብ
እድሜዬ ታጥሯል በግዜ ገደብ
መልካም ሰርቼ እንዲያልፍ ወራቴ
በጎውን አብዛ በሰውነቴ
አዝ-------------------//
🔸 @ctwobek
🔸🔹🔸 @ctwobek
🔸 @ctwobek
