cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Radio Addis ✍️

ይህ Channel አስተማሪ እና ቁምነገር ያላቸው፦ 👉 አጫጭር ታሪኮችን፣ 👉የህይወት ልምዶች፣ 👉 ልቦለዶች፣ የምናቀርብበት Channel ነው! @minilk7

Show more
Advertising posts
234
Subscribers
+424 hours
+127 days
+2530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ባወጣ ባወርድ አንድ ነገር፣ አንዳንዴ ምክንያቱን ለራሳችን እንኳ በማይገባን ምክንያት ለቅርቦቻችን፣ ብዙ ለዋሉልን- ባይውሉልንም፣ ምንም ላልበደሉን ሰዎች ይሁዳ ሆነን አሳልፈን ለሐዘን ስንሰጣቸው፤ ሕይወታችንን ላመሰቃቀሉ ክፉዎች ግን፣ እንደ ክርስቶስ ካልተሰቀልንላችሁ ስንል የመገኘታችን ነገር ምን ይሆን ሚስጥሩ? 👉( ማህደረ ሰላም ከ አልተዘዋወረችም መፅሐፍ የተወሰደ ) ✍️ አሌክስ አብርሃም 👉@Radioaddis ⚠️Share!
Show all...
👍
🤔
❤️
🥀....አይዞኝ!....🥀 አሁን እናት ነኝ፤ ስለ ልጆቼ ዕጣ ፋንታ ማሰብ አለብኝ፡፡ ለሞተ ትላንቴ ሳለቃቅስ መኖር ገና የተጀመረ የልጆቼን ነገ ማበላሸት ነው፡፡ እኔ ምርጫዬን ኖሪያለሁ፤ ለዚህ ውሳኔ ያበቃኝ አስተዳደግም ይሁን ስሜታዊነት ሁሉም ነገር የራሴ ውሳኔ ነበር፡፡ በሕይወት ውስጥ ማንኛውንም የውሳኔ ጠጠር ከመወርወራችን በፊት፣ ፊት ለፊታችን የቆመ የነገ መስተዋታችን ላይ ምን ሊፈጥር እንደሚችል ማሰብ የእኛው ኃላፊነት ነው፡፡ ግን ደግሞ ሰውነን እና ብዙ ከማስተዋል ጎዳና የሚያስወጣን ስሜት ይኖራል፡፡ የእኔው ጠጠር መስተዋቴን ሰንጥቆት ይሆናል እንጂ ጨርሶ አልተንኮታኮተም። በሕይወት እስካሉ ጨርሶ መንኮታኮት የሚባል ነገር የለም፡፡ ጥሩ ባል ያላት ባለትዳር፣ የአንዲት ቆንጆ ልጅ እናት እና ሁለተኛ ልጅ ያረገዝኩ ሴት ነኝ፡፡ልጆቼ ያልተረበሸ ነገ ያላቸው፣ ማንንም የማይፈሩ፣ ማንንም የማይለማመጡ፤ ሰውን ከመውደድና ከማክበር ያለፈ ዕዳ የሌለባቸው ልጆች እንዲሆኑ የትኛውንም ዋጋ የመክፈል አለብኝ፡፡ አይዞኝ! ጥሩ ወላጅ ማለት ከጊዜ ጎርፍ ፊት ቆሞ ስቃይን ወደ ትውልድ እንዳያልፍ አግዶ የሚይዝ ጽኑ ግንብ ነው፡፡ አምላኬ ብርታቱን ይስጠኝ፡፡ 👉( ማህደረ ሰላም ከ አልተዘዋወረችም መፅሐፍ የተወሰደ ) ✍️ አሌክስ አብርሃም 👉@Radioaddis ⚠️Share!
Show all...
❤️
👍
👎
• ምንም ነገር ለዘላም አይቆይም፡፡ ችግሮችህ፣ የከበቡህ ሰዎች፣ ስራህ፣ ትዳርህና ግንኙነቶችህ ሁሉ ለጊዜዉ ነዉ፡፡ የሁሉም ነገር ፍፃሜ የሆነ ቀን ላይ ሲሆን ታየዋለህ፡፡ በህይወቴ ሁሉ አብረዉኝ ይኖራሉ ያልካቸዉ ነገሮች እንኳን ሳይቀሩ ሲፈረካከሹ ታያቸዋለህ   • ለሁሉም ነገር ተራ አለዉ፡፡ ሰዉን ብትጠቅም ጊዜዉን ጠብቆ አምላክህ ይከፍልሃል፡፡ ብትጎዳም እንዲሁ...በሰፈርከዉ ማንነት ጊዜዉ ሲደርስ ትሰፈራለህ   • ማንም ሰዉ ስላንተ አይጨነቅም፡፡ 20 ፐርሰንቱ ብቻ ስላንተ ሲጨነቁ (እነሱም የቅርብ ጓደኞችህና ቤተሰቦችህ መሆናቸዉን አትዘንጋ) 80 ፐርሰንቱ ግን ኑር አትኑር አንዳች ቅንጣት ስላንተ አያስቡም፡፡ ችግሮችህን ለነዚህ ለ 80 ፐርሰንት መናገር እራስህን ማባከን ነዉ ምክንያቱም ችግርህ ለነሱ ምናቸዉም አይደለምና! የራሳቸዉ ጉዳይ ብቻ ያሳስባቸዋልና ቆጠብ በል   • ሰዎች በህይወትህ ይመጣሉ ደግሞም ይሄዳሉ፡፡ አንድ ቀን ለብቻህ ሰዉ በሌለበት ልትሞት ትችላለህና ሰዎችን አትደገፍ   • ከ5-6 የልብ የምትላቸዉ ሰዎች በቀር ፌስቡክ ላይ ያሉት የጓደኛ ጋጋታ ምንም አይጠቅሙህም፡፡ ብትሞት እንኳ ቀብርህ ላይ የማይመጡ ብዙዎች መሆናቸዉን እወቅ   • የስራ አለቃህ እንድታድግና የተሻለ ቦታ እንድትይዝ ሊመኝ ይችላል ግን መቼም እንድትበልጠዉ አይፈልግም፡፡ ምንም ሽልማትና ጭብጨባ ቢበዛልህ ከሱ እንደምትበልጥ ካሰበ አንተን ለመገፍተር ወደኋላ አይልም   • 98 ፐርሰንቱ ሰዉ መቼ እንደተወለድክ እንኳን አያዉቅም(2 ፐርሰንቱ መቼም እነማን እንደሆኑ መገመት አያቅትህም)፡፡ ካላመንከኝ ሞክረህ እየዉ!   • የዉሸት ጓደኞችህ የተሻለ ህይወት እንድትመራ በፍጹም አይፈልጉም፡፡ ነገሮች መልካም ሲሆኑ የሚሰበሰቡ ሰዎች ሊያስገርምህ አይገባም! አንድ ቀን ህልምህ 'ወለም' ብሎ ካዩ እጃቸዉን ቀስረዉ ይስቁብሃል፡፡ የዛኔ ያልሳቁብህን የልብ ጓደኞችህ አድርጋቸዉ   • ገንዘብ ያለዉና ፀዳ ብሎ የሚመላስን ሰዉ ብዙዎች ሲያከብሩት ትመለከታለህ ፡፡ የማያዉቅህ እንኳን ቢሆን ፀዳ ካልክበት ሊያከብርህ ሲዳዳዉ ታየዋለህ   • ለሰዎች ምክር መስጠት በጣም ቀላል ነዉ ነገር ግን ምክርን ወደተግባር መቀየር ከባዱና አስቸጋሪዉ ነገር ነዉ፡፡ አንዳንዴ ሰዉን ካለበት ማጥ ለማዉጣት ካሰብክ ከምክር በላይ የሆነ ስብዕና ሊኖርህ ይገባል፡፡   • አንድ ዉሸታም ጓደኛህ ከ 100 ጠላትህ ጋር እኩል ጥፋት ያደርሳል፡፡ ጠላቶችህን ተከታተላቸዉ ጓደኞችህን ደግሞ በጣም ተከታተላቸዉ   • ነገሮች መልካም እንዲሆኑና እንዲሳኩ ያለ የሌለ ጥረትህን አድርገህ ሳይሳካልህ ቀርቶ ይሆናል፡፡ ይሄ ያንተ ደካማነት ሳይሆን ህይወት እንዲህ አይነት ገፅታም ስላላት ነገሩን ተቀበለዉ፡፡   • ለመወደድ ልዩ ሰዉና ሁሉንም ሞካሪ መሆን አይጠበቅህም፡፡ እንዳንዴ ሰዉ ሁሉ ባይወድህ እንኳን ይሄ ምንም ማለት እንዳልሆነ ተረዳ፡፡ በሰዎች መጠላትንም ቀለል አድርገህ ዉሰደዉ ምክንያቱም እንዴት እራስህን ማሳደግ እንዳለብህ ማጤን ወሳኙ ነገር ሲሆን የሰዎችን ስሜት እያዳመጥክ ከፍና ዝቅ እያልክ መኖር አይጠበቅብህም፡፡   • የራስህ አስተሳስብ ይኖርሃል፡፡ ሌሎችም እንዲሁ...ሰዎች በሀሳብህ አለመስማማታቸዉ አንተነትህ ላይ የሚያመጣዉ ነገር የለም፡፡ ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን አስተሳሰብ ረጋግጠህ አትዉጣ፡፡ የሰዎችን ሃሳብ አክብር ሰዎችም ሃሳብህን እንዲያከብሩ አድርግ   • ይቺ አለም የምትፈልግህ ጠቃሚ ነገር አንተ ጋር እንዳለ ስታምን ብቻ ነዉ፡፡ ባጠቃላይ አለም እራስ ወዳድ ናት   • ሰዎች ስለ ደስታ አጋነዉ ሲያወሩ ትሰማ ይሆናል፡፡ በኣጭሩ ደስታ ማለት ስሜትህ ሳይሆን አእምሮህ ያለበት ሁኔታ ነዉ፡፡ ደስተኛ ሆነህ በሰዎች ልትጎዳ ትችላለህ፡፡   • ህይወት እኩል አይደለችም፡፡በሆነ ነገር ጎበዝ ብትሆን ካንተ የበለጠ በጣም ጎበዝ ሰዉ አለ...እኩልነት ዉሸት ነዉ፡ ስለዚህ በመኖርህ ብቻ ተደሰት፡፡ ❤️መልካም ቀን! 👉@Radioaddis ⚠️Share!
Show all...
🔥 1
❤️
👍
👌
ትረካውን ለወደዳችሁት Part 3
Show all...
❤️
👍
👎
Audio book 😃 🎧
👉 Don't Waste Your Time! Don't give your time away any longer. Don't waste your time living in the darkness anymore. ⚠️ If you feel that you are wasting your time, then you just need to tell yourself one thing:- ⚠️ "I WANT TO DO SOMETHING USEFUL NOW!" 👉This may sound simple, but it is very powerful when you say it to yourself. ⚠️Share! 👉@Radioaddis
Show all...
❤️
👍
👌
👉"ሰዎች መጠየቅ የሚፈሩት ለምንድነው?" ሰዎች መጠየቅ ለምን ይፈራሉ? ብዙ ነገሮች ያስፈሯቸዋል፣ ለምሳሌ የተቸገረ ሞኝ ወይም የማይረባ መስሎ መታየት ስለማይፈልጉ ነው፡፡ በአብዛኛው ደግሞ አለመፈለግ እንዲያጋጥማቸው ስለማይፈልጉ ነው፡፡ አይሆንም የሚለውን ቃል መስማት ስለሚያስፈራቸውም ነው፡፡ የሚያሳዝነው ነገር እነርሱ ራሳቸውን አስቀድመው አይሆንም ማለታቸው ነው፡፡ ሌላኛው ስው አይሆንም የማለት እድል ከማግኘቱ በፊት ራሳቸውን አይሆንም ይሉታል፡፡ ⚠️‹አይሆንም› የሚል መልስ አገኛለሁ ብለህ አትገምት:: የምትፈልገውንና የሚያስፈልግህን የመጠየቅ አደጋ ተጋፈጥ፡፡ መልሱ አይሆንም, የሚል ቢሆን እንኳን መጀመሪያ ከነበርክበት ሁኔታ መጥፎ የሆነ ነገር አይፈጠርም፡፡ እሺ ከሆነ ደግሞ በጣም የተሻለ ይሆንልሃል:: ለመጠየቅ በመድፈርህ ብቻ የደሞዝ ጭማሪ፣ ስጦታ፣ የዋጋ ቅናሽና የመሳሰሉትን ጥቅሞች ማግኘት ትችላለሀ። 🤗ወዳጄ ዝም ብለህ ጠይቅ! 👍 ❤️መልካም ቀን!❤️ 👉@Radioaddis ⚠️Share! Share! Share!
Show all...
❤️
👍
👌
👉ለውጥን ተቀበል! "ለውጥ የሕይወት ህግ ነው። ያለፈውንና ያሁኑን ብቻ የሚመለከቱ ሰዎች በእርግጠኝነት የወደፊቱን አጥተውታል!" (ጆን ኤፍ ኬኔዲ) ለውጥ የማይቀር ነው፡፡ በዚህ ቅጽበት ለምሳሌ አካልህና ሴሎችህ እየተለወጡ ነው፡፡ ምድር እየተለወጠች ነው:: ኢኮኖሚው፣ ቴክኖሎጂው፣ ቢዝነስ የምንስራበት መንገድ፣ የእርስ በርስ ግንኙነታችን ሳይቀር እየተለወጠ ነው:: ለውጥን መቋቋም እንደምንችለውና በለውጥ መመለስ እንዳለ ሁሉ፤ ከለውጥ ጋር መተባበር፣ መስማማትና ከለውጥ ተጠቃሚ መሆንን መምረጥ ትችላለህ/ሽ። 👉@Radioaddis ⚠️please Share!
Show all...
👍 3
❤️
👍
👎
ክፍል ሁለት
Show all...
❤️
👍
👌
ትረካ 🎧
😁‹‹ይሄም ያልፋል ››😁 ✍️ (አሌክስ አብርሃም) ነገሩ እንኳን ቁም ነገር ሁኖ አይደለም እንደው ትዝ ብላኝ እንጅ አንዲት ወጣት የስራ ባልደረባ ነበረችኝ …ሳሮን የምትባል ሳሪ  ቢሮ ውስጥ የማይወዳት የለም …ለሁሉም ሰው የምትጨነቅ …በቃ ማንም ካዘነ እርሷ አሳዳ ነው የምታፅናናው ለቅሶ አሳዳ ትደርሳለች የታመመ ትጠይቃለች የምታውቀው ሰው እንኳን ባይኖር አንዳንድ ቀን ብርቱካን ገዝታ ሆስፒታል ትሄድና አንዱን ህመምተኛ ጠይቃ ተዋውቃም ትመለሳለች ! ታሪከኛ ልጅ ናት ! አንድ ቀን ታዲያ የዛሬ አመት አካባቢ ነው … ቡና ልጋብዝህ ብላኝ አንድ ካፌ ውስጥ ተቀምጠናል ....ድንገት ከእኔ በስተግራ ወዳለው ጠረንቤዛ ዙራ የሆነ ነገር አየችና ፊቷ በሃዘን ቅጭም አለ …በዛ ላይ አስር ጊዜ በሃዘን ከንሯን ትመጣለች ….እንደውም ጭራሽ አይኗ እንባ ኳተረ ! ምንድነው ጉዱ ብየ ቀስ አልኩና ወደምታይበት አቅጣጫ ዞርኩ …. አንድ ጎረምሳ ፈረንጅ ተቀምጧል ….‹‹ምን እያደረገ ›› አትሉኝም ?…… ቡና እየጠጣ አይደለም …ምግብ እየበላም አይደለም ……እያለቀሰ ! ከምር ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ! ስቅ ስቅ እያለው ቀይ ፊቱ ቲማቲም መስሎ ያለቅሳል ….(ለካ ፈረንጅም ሲያለቅስ አበሻ ነው የሚመስለው ! ) እናም ወዳጀ እንዲህ አለችኝ ‹‹አብርሽ በናትህ ይሄን ፈረንጅ ላፅናናው አገራችን ላይ መጥቶማ እንዲህ ሲሆን ዝም ማለት ከምር ጭካኔ ነው እግዜርስ ይወደዋል ? >> ‹‹ይሻላል ? ማፅናናት ኤክስፖርት ማድረግ ልትጀምሪ ነው? >> አልኳት ለቀልድ ‹‹እንተ ደግሞ በማይቀለደው ትቀልዳለህ >> አለችና ተነስታ ወደፈረንጁ መንገድ ጀመረች ድንገት ከመሃል ተመልሳ በሹክሹክታ እንዲህ ስትል ጠየቀችኝ << ስማ አብርሽ < ይሄም ያልፋል> ማለት በእንግሊዝኛ ምንድነው ?>> አይ ሳሪ ዛሬ በሆነች ጉዳይ ትዝ ብላኝ ብቻየን እንደጅል ላኩ ! ሳሪ ዛሬ አሜሪካ ነች... 😂😂😂 ‹‹ኧረ ይሄም ያልፋል በእንግሊዝኛ ምንድነው ሳሪ ያበደርኩሽን መልሽ >>🧐 👉@Radioaddis
Show all...
👍 2
👍
😁
😂
🤔
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ⚠️ ግን መተው ከባድ ነው.....⚠️ "ይቅር ማለትና መተው እንዴት ከባድ እንደ ሆነ አውቃለሁ። በማላውቀው ሰው ተጠልፌ ጥቃት ደርሶብኛል፤ የአልኮል ሱሰኛ በሆነ አባት አካላዊ ጥቃት ደርሶብኛል፣ በተለወጠ የዘር መድሎ ተጠቂ ነበርኩ፤ ሰራተኞቼ በጣም ብዙ መጠን ያለው ገንዘብ አጭበርብረውኛል፤ በግልጽ በተደረገ መጥፎ ነገር በከንቱ ተከስሼያለሁ፤ እንዲሁም የቢዝነስ ስምምነቶች ላይ ተጠቅመውብኛል። 👉ነገር ግን ከእያንዳንዱ አጋጣሚ ጋር እያንዳንዳቸውን አስቤ ይትር አልኩ። ምክንያቱም ይቅርታ ካላደረክ፣ እነዚያ ያለፉት ጉዳዮቼ ውስጥ ውስጤን  እየበሉኝ አሁን ባለኝ ከመደሰትና የምፈልገውን የወደፊት ሕይወት መፍጠር ላይ ሙሉ ትኩረቴን ከማድረግ እንደሚከለክሉኝ አውቄ ነበር። በእያንዳንዱ ልምምድ እንዴት ሁለተኛ እንደዚያ አይነት ነገር ከመፍጠር ማቆም እንደሚቻል ተምሬያለሁ። የተፈጥሮ እውቀቴን እንዴት በተሻለ መጠቀም እንደምችል ተምሬያለሁ፤ ራሴን፣ ቤተሰቤንና ሰርቼ ያገኘሁትን ንብረቴን እንዴት በተሻለ መከላከል እንደምችል ተምሬያለሁ:: በእያንዳንዱ ጊዜ በመጨረሻ ልምምዴን በመልቀቄ ቀለል እንዳለኝ በጣም ነፃና ጠንካራ እንደ ሆንኩኝ እንዲሰማኝና እኔ ላይ ያለውን አስፈላጊ ስራ ለማከናወን ትኩረት እንዳደረግ አቅም ሰጥቶኛል፡፡ ምንም አይነት አሉታዊ ንግግር ከራሴ ጋር አላደርግም፤ የመረረ ክስ የለም፡፡" 👉"የመረረ ጥላቻ ልክ መርዝ እንደመጠጣት እና ከዚያ ያ መርዝ ጠላቶችህን እንዲገድልልህ ተስፋ ማድረግ ነው። "⚠️                           (ኔልሰን ማንዴላ) መልካም ቀን! 👉@Radioaddis ⚠️Share!
Show all...
❤️
👍
👎
👉ትረካ እወዳለሁ🎧