cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Horizon of Books~የመጻሕፍት አድማስ📚

📚 Books that you need are available here‼ Languages, Literature, Art, Religion, Psychology, Philosophy, Politics, History, Biography, Astronomy, Economics, Health, Environment, Educational Books &More. 🔗 Share the channel with your friends and family.

Show more
Advertising posts
988Subscribers
+324 hours
+247 days
+6530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"ነጩ ዶክተር ካላከመኝ" . ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ከአንድ ነጭ ተማሪያቸው ጋር በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ሆነው ህመምተኞችን እየጎበኙ ነው። አንድ በአንድ ህመምተኞቹን እያዳረሱ ፣ አንድ በእድሜያቸው ገፋ ያሉ አዛውንት ጋር ደረሱ። . አዛውንቱ ነጭ–አምላኩ ነበሩና " ነጩ ዶክተር ካላከመኝ" ብለው ድርቅ አሉ። እንግዲህ ወጣቱ ነጭ ፕሮፌሰር አስራትን ፣ በትምህርት ደረጃ ፣ በስራ ልምድ ፣ በግል ተሰጥኦ ይወዳደራል ተብሎ አይታሰብም ። ከእርሳቸው ሰፊ ልምድ ፣ ስር ሆኖ ሊማር በፈቃደኝነት የመጣ ነው። . አዛውንቱ ግን በሀሳባቸው ፀኑ። ስለዚህ ፕሮፌሰር አሥራት መላ ዘየዱ። እርሳቸው ለነጩ ተማሪ እንደ ረዳት ሆነው አዛውንቱን ሊመረምሩ። በዚህ መሰረት ነጩ ተማሪ የፕሮፌሰር አሥራትን መመሪያ እየተከተለ አዛውንቱን መረመረ። በሽታቸውም ታወቀ። . ፕሮፌሰር አሥራት የፈውስ መድሃኒቱን ማዘዣው ላይ ፅፈው ለነጩ ተማሪ አስረከቡ። ተማሪው ደግሞ ለአዛውንቱ። . አዛውንቱ ፣ መልአክ የመሰለ ነጭ ሰው ስላከማቸው በጣም እየተደሰቱ፣ ገና መድሃኒቱን ሳይወስዱ የመሻል ስሜት እየተሰማቸው ፣ ሆስፒታሉን ለቀው ወጡ። . ከጥቂት ሳምንታት በኋላ፣ ፕሮፌሰር አሥራት ያንን አዛውንት ከመንገድ ያገኟቸዋል። የተለመደ ጥያቄያቸውንም ይሰነዝራሉ ፦ "እንዴት ኖት አሁን? ጨርሶ ተሻሎት?" . አዛውንቱ ሲመልሱ ፦ "አሁን ፍፁም ጤነኛ ነኝ። ጭራሽ አሞኝ አያውቅም። ያ የተባረከ ፈረንጅ በሙሉ ነው የፈወሰኝ" . ፕሮፌሰር አሥራት በአዛውንቱ የጤንነት ሁኔታ ተደስተው፣ አሁን እውነቱን ብነግራቸው ችግር የለውም ብለው አሰቡና፦ "ይኸውሎት አባቴ፣ ፈረንጁ የኔ ተማሪ ነበር ፣ ከኔ ሊማር ነው የመጣው። ያከምዎት ፣ ህመምዎን ያገኘሎት ፣ መድሐኒት ያዘዘሎት እሱ አይደለም፣ እኔ ነኝ" ቢሉ፣ . አዛውንቱ መልሰው፦ "ለዚያ ነዋ ህመሙ እየደጋገመ የሚነሳብኝ!" . ምንጭ: Tewodros Shewangizaw, Book For All
Show all...