cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

South Ethiopia Regional Health Bureau

ይህ የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ነው!

Show more
Advertising posts
370
Subscribers
+124 hours
+137 days
+9130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ውሃ ወለድ በሽታዎች እንዳይከሰቱ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራውን በቅንጅት መሥራት ይገባል በ297 ወረዳዎች የኮሌራ በሽታን መቆጣጠር ተችሏል የክረምት ወራትን ተከትሎ ውሃ ወለድ በሽታዎች እንዳይከሰቱ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራው በቅንጅት ሊሠራ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ በ297 ወረዳዎች የኮሌራ በሽታን መቆጣጠር መቻሉም ተመላክቷል፡፡ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሃይሉ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የክረምት ወራትን ተከትሎ ውሃ ወለድ በሽታዎች እንዳይከሰቱ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ ኮሌራ፣ ወባና ኩፍኝ በሽታዎች በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ የመቆጣጠርና የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የኮሌራና ሌሎች ውሃ ወለድ በሽታዎችን ከመቆጣጠር አንጻር የህክምናና ሌሎች ቁሳቁሶች ቶሎ እንዲደርሱ ክትትል የማድረግ፣ ህብረተሰቡን የማስገንዘብ እና የመጸዳጃ ቤት ሽፋንና አጠቃቀም ዝቅተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ላይ የማሻሻል ስራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡ በድርቅ ምክንያት የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ዝቅተኛ በሆነባቸው አካባቢዎችም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የንጹህ መጠጥ ወሃ አቅርቦትን የማሻሻል ስራ በመሰራቱ ኮሌራ በተከሰተባቸታ በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን፤ በምስራቅ ኦሮሚያ በሶማሌና አፋር ክልሎች የተወሰኑ ወረዳዎች ላይ ያለ በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ኮሌራ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ በተሰራው የመከላከል ስራ በ297 ወረዳዎች ላይ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን ገልጸው፤ በሽታው በባህሪው ተላላፊ በመሆኑ የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋንን በማስፋፋት እና ውሃን አክሞ በመጣጣት ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ይገባል ብለዋል፡፡ የወባ በሽታን ለመከላከል ለማህበረሰቡ ተደራሽ የተደረገውን አጎበር በአግባቡ እንዲጠቀም ግንዛቤ የማስጨበጥ እና የወባ ምልክት የታየባቸውን ሰዎች በመለየት ህክምና እንዲያገኙ የማድረግ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡ ለወባ መራቢያ ምቹ የሆኑና ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን በህበረተሰብ ተሳትፎ የማጽዳት፣ የኬሚካል ርጭት፣ ለወባ ምርመራ የሚያገለግሉ የህክምና ቁሳቁሶችን የማሰራጨት ስራ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል፡፡ እንደ ዶክተር መሳይ ገለጻ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በቤኔሻንጉል እና በምእራብ አማራ፣ ክልሎች ላይ የወባ በሽታ የጨመረበት ሁኔታ በመኖሩ የመከላከል ስራው በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኩፍኝ በሽታን የመደበኛ ክትባትን ማጠናከር እና ተጨማሪ የክትባት ዘመቻ በመደረጉ ከ320 በላይ ወረዳዎች ላይ መቆጣጠር መቻሉን አስረድተዋል፡፡ መደበኛ ክትባትን የማጠናከርና የተማሙ ህጻናት ህክምና እንዲያገኙ በስፋት ይሰራል ብለዋል፡፡ ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ህብረተሰቡን ማንቃት ወሳኝ ነው ያሉት ዶክተር መሳይ፤ የግልና የአካባቢ ንጽህናን፣ የምግብና መጠጥ ውሃ ንጽህናን መጠበቅ እንደ ኮሌራ ያሉ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ጠቀሜታዉ የጎላ ነው ብለዋል። የክረምት ወራትን ተከትሎ ውሃ ወለድ በሽታዎች እንዳይከሰቱ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡
Show all...
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩ ለትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሐነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ! የትንሳኤ በአል ትልቅ ክብርን ተጎናፅፎ ባህላዊና ሀይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ ወዳጅ ከዘመድ አስተሳስሮ ፤ በማህበራዊ መስተጋብር ውስጥ ይከበራል በዓሉ ሰላምን፣ጤናን ፣አብሮነትን፣ አንድነትን ያጎናጽፋል ። እንደ ሀገር ብሎም እንደ ሀገር ጉልህ ስራዎች የማህበራዊ ዘርፍ አካል የሆነው አንዱ የጤናው ዘርፍ ሲሆን ከዚህ አኳያም የዜጎቿን ኑሮና የጤና ሁኔታ ለማሻሻልና ስራዎች በአፅንዖት እንደተችሯቸው ገልጸዋል ። እንደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በ100 ቀን ዕቅድ መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግር በአመራር መደገፍ ፣አፈፃፀምን ማሻሻል ፣ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ማረጋገጥ ግብ ተጥሎ እየተሰራበት ይገኛል ነው ያሉት። በ 100 ቀን ዕቅዱ ህብረተሰብ ጤንነት እንዲጠበቅ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ለመጨመርና የዜጎችን አካለዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ችግሮች ለመግታት እንደ ጤናዉ ሴክተር ወርቃማ ዕድል ተደርጎ ይወሰዳል መልዕክት አስደምጠዋል በንግግራቸው ። ይህንኑ ውጥን በድል ለማጀብ የእናቶችንና የህፃናትን ህመምና ሞት መቀነስ፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከለከልና መቆጣጠር፣ በወባ፣ በቲቢና በኤች.አይ.ቪ መከላከል ላይ የአገልግሎት አሰጣጥን ሊያሻሽሉ የሚችሉ አዳዲስ አሠራሮች ይበልጥ እንደመሚተገበሩ አስረድተዋል ። ከዚህ ሐሳብ ጋር በተያያዘ በአላትና ግብይት እጅግ ይቆራኛሉ ፣ በመሆኑም በበዓላት ግብይት ወቅት እና በዓሉን ስናከብር ለጤናችን መስተጓጎል አስተዋጽዖ ካላቸው የአመጋገብ ዘይቤዎች ከባዕድ ነገር ጋር የተከለሱ የምግብ ምርቶች ግብይትና አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ እንዲደረግ ለማስገንዘብ እወዳለሁ ብለዋል ። በመጨረሻም በዓሉ ስናከብር የተለመደው የመረዳዳት ባህላችንን አጠናክረን በማስቀጠል በየካባቢያችን የሚገኙ አቅመ ደካሞችና ለተቸገሩ ወገኖች በዓሉን በደስታ ማክበር እንዲችሉ አቅማችን የሚችለውን ሁሉ በማድረግ ልንረዳቸው ይገባል። በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳቹ በራሴና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ስም መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡ አብረን እንስራ! የጤናችንን ስኬት እናረጋግጥ መልካም የትንሳኤ በዓል!! አቶ እንደሻው ሽብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጤና ቢሮ ኃላፊ
Show all...
የጥንቃቄ መልዕክት በየአመቱ በህዝበ ክርስቲያኑ  ዘንድ በድምቀት በሚከበረው በተናፋቂው በብርሃነ ትንሳኤው በርካታ ግብይቶች ይካሄዳሉ !! በመሆኑም በበዓላት ግብይት ወቅት እና በዓሉን ሲያከብሩ  ለጤናዎ መስተጓጎል አስተዋጽዖ ካላቸው ከአመጋገብ  ዘይቤዎች ይጠንቀቁ ። ከባዕድ ነገር ጋር የተከለሱ የምግብ ምርቶች ግብይትና አጠቃቀም ላይ ብርቱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ቢሮው ያሳስባል ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ
Show all...
👍 1 1
"እንኳን ለስቅለትና ለብርሃነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሳችሁ! " የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩ ለስቅለትና ትንሣኤ በዓል እንኳን በሰላም፣ በጤና አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ ። የስቅለትና የትንሳኤ በሃል በየአመቱ በህዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ በድምቀት የሚከበር ተናፋቂ በዓል መሆኑን ጠቅሰው በዓሉ የሠላም ፣የፍቅር ፣የመደጋገፍ ፍላጎት የሚንፀባረቅበት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል። አቶ እንደሻው ባስተላለፉት መልዕክት በዓሉን ስናከብር ለጤናችን መስተጓጎል አስተዋጽዖ ካላቸው የአመጋገብ ዘይቤዎች ከባዕድ ነገር ጋር የተከለሱ የምግብ ምርቶች አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ እንዲደረግ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የ100 ቀናት ዕቅድ ትግበራ ከጤና ልማት አንፃር ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችሉ የተለያዩ አሰራሮችን ዘርግቶ ሁለንተናዊ ለውጥን ለማስመዝገብ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል። በዚህም በእናቶችና ህፃናት ጤና፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ፣ በድንገተኛ በሽታዎችና ቅኝትና ምላሽ፣ በህክምና አገልግሎት ዘርፍ፣ በጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ግብዓት አቅርቦትና ቁጥጥር፣ በጤና ልማት ዕቅድ ስራዎች እየተሰራባቸው እንደሚገኝ ጠቁመዋል ለውጤታማነቱ በጋራ እንስራ ጥሪ አቅርበዋል ። የስቅለትና የትንሳሄ በዓላት በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸውና በድምቀት የሚከበሩ በዓላት ናቸው ያሉት አቶ እንደሻው ህዝበ ክርስቲያኑም በዓሉን ሲያከብር የተለመደውን የመረዳዳት እና የመደጋገፍ ባህል በማጠናከር አቅም የሌላቸው ወጎኖችን በማሰብ እንዲያከብሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለስቅለትና ትንሳኤ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ /አደረሰን ። አቶ እንደሻው ሽብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ
Show all...
የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ PHEOC / የሕብረተሠብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ መዕከል/ የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ስራዎችን መገምገማቸው ተገልጿል የሕብረተሠብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል ሪፖርት በመምሪያው የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ታረቀኝ መርዕድ በኩል ሪፖርት ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ ከቀረበው ሪፖርት መረዳት እንደተቻለው በሣምንቱ ውስጥ የሪፖርት ሙሉነት 91 % ላይ ያለ ሲሆን የሣምንታዊ የበሽታ ቅኝት ሪፖርት ከካምባ ዙሪያ ወረዳ ይህ ሪፖርት እስከተዘጋጀ ድረስ ለዞኑ ያለመድረሱን ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡ የሕብረተሠብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል ሣምንታዊ ውይይትን በተመለከተ በሣምንት ውሰጥ በ 13 መዋቅሮች መዋቅሮች የተከሄደ ሲሆን ውይይቱን በሣምንት ውስጥ ያለካሄዱ መዋቅሮች መኖራቸውም ታውቋል፡፡ ከወባ በሽታ ጋር በተያያዘ ከዚህ ሣምንት በፊት ካለው ሣምንት ጋር ሲነጻጸር መጠነኛ መጨመር የታዬበት ሲሆን በሣምንቱ ውስጥ ከፍተኛ የወባ በሽታ ጫና ያስመዘገቡ ወረዳዎች ዳራማሎ 444፣ ቁጫ አልፋ በልተለመደ መልኩ 296፣ ሠላምበር ከተማ 270፣ መዕራብ አባያ 200 እንዲሁም አርባ ምንጭ ከተማ 190 ከማስመዝገባቸውም በላይ የዞኑን የወባ በሽታ ጫና 70 በመቶ ያህሉ እንዲመዘገብ አስተዋዕፆ አበርክተዋል፡፡ በመሆኑም በሽታውን ለመቆጣጠር አሁንም የአካባቢ ቁጥጥር ስራዎች እና የአጎበር አጠቃቀም ክትትል ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ተብሏል፡፡ በሌላ በኩል የተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ልዬታ ስራ በየደረጃው በሚገኙ የጤና ተቋማት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገልፃል፡፡ በሣምንቱ የቲቢ በሽታ ዘመቻ በዞኑ በተመረጡ 14 ወረዳዎች የተካሄደ ሲሆን ሪፖርቱን የመምሪያው የቲቢ በሽታ ኦፊሰር በሆኑት በአቶ ክንፉ ጩቃሎ በኩል የቀረበ ሲሆን በአጠቃላይ በዘመቻው 10 ቀናት ውስጥ 130 ሺህ 225 ሰዎችን ልየታ በማድረግ 4 ሺህ 514 ሰዎች በበሽታው ተጠርጥረዋል፡፡ በበሽታው ከተጠረጠሩት መካከል ከ 2 ሺህ 984 ሰዎች የአክታ ናሙና ተወስዶ የተመረመረ ሲሆን ምርመራ ካደረጉት መካከል 2 መቶ ሰዎች ላይ የቲቢ በሽታ መገኘቱን የቀረበው ሪፖርት ያመለክታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በልማት ዕቅድና ኢኮኖሚ አስተዳደር ባለሙያ በሆኑት በአቶ ተገነ ተድላ በኩል የመቶ ቀን ዕቅድ ሣምንታዊ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በሳምንቱ ውስጥ ከ አርባምንጭ ዙሪያ፣ ከካምባ ዙሪያ ወረዳ፣ ከጨንቻ ዙሪያ፣ ከቦንኬ ወረዳ እንዲሁም ከጋጮ ባባ ወረዳዎች ሪፖርት ያላቀረቡ መዋቅሮች መሆናቸው ታውቋል፡፡ በየደረጃው የሚመለከታቸው አካላት ሪፖርቱን ገምግመው ያለመላክ፣ ሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ ላይ የሠፈሩትን የአፈጻጸም ጠቋሚዎችን በሙሉ የሪፖርት አካል አድርጎ ያለማቅረብ፣ የሣምንት ዕቅድ በግልጽ ያለማሣዬት እና የመረጃ ጥራት መጓደል በጉድለት ከተገመገሙ ዋና ዋና ጉዳዮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በዞን ደረጃ የማህበረሠብ መሪነት ለላቀ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከል በሚል መሪ ቃል የተደረገውን ንቅናቄ ተከትሎ በየደረጃው የንቅናቄ ስራ በአጠረ ጊዜ ተሰርቶ ሪፖርት እንዲደረግ በተቀመጠው አቅጣጫ ይህ ሪፖርት እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ በዲታ ወረዳ፣ በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ በብርብር ከተማ አስተዳደር እና በቦረዳ ወረዳ የተካሄደ ሲሆን በሌሎች የንቅናቄውን መድረክ ያላካሄዱ መዋቅሮች ፈጥነው በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ሊያካሂዱ እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ
Show all...