cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ጣፋጭ የፍቅር ታርኮች 😘💖💑💑

♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር 💟 ማለት፤ ➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤ ➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤ ➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟 ҒϴᏞᏞϴᏔ ϴΝ ҒᎪᏟᎬᏴϴϴᏦ = https://www.facebook.com/fikrenbegtm ᶠᵒʳ ᵃⁿʸ ᵖʳᵒᵐᵒᵗⁱᵒⁿ = +251947534345 = t.me/@yefkr_world2

Show more
Advertising posts
230
Subscribers
No data24 hours
+47 days
+1330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Repost from N/a
ናፍቆት (በላይ በቀለ ወያ) . . እንዲህ እንደዛሬ... በመሀከላችን ንፋስ ሳይግባብን ፣ ፍጥረት ሳይፈጠር በኔና አንቺ መሀል... የነበረው ክፍተት ፣ አንድ ስንዝር ነበር። አንቺ ሰማይ ሆነሽ እኔ ደግሞ ምድር!!! ............................................ በዚህ ስንዝር መሀል.... እስትንፋስ ያላቸው ሰዎች ተፈጠሩ እነዚህ ሰዎችም.... ቅርብ ላለች ሰማይ የምድርን ሀጥያት ይነግሯት ጀመሩ። "ምድር ዘማዊ ነው ምድር ሀጣዊ ነው ብትሸሺው ይሻላል ይህ ዓለም ጠፊ ነው" እያሉ ሲነግሯት የሰው ወሬ ሰምታ ሰማይ ፊኛ ሆና... ትለጠጥ ጀመረ ከኔ ተለይታ በሰዎች እስትንፋስ... ወደ ላይ ተነፍታ ወደጎንም ሰፍታ። ....................................... እንጂማ አውቃለሁ እንጂማ ታውቂያለሽ የሰው ወሬ ሰምቶ ልብሽ ባይረበሽ እንዲህ እንደዛሬ ሳትርቂኝ በፊት ሰማይ ቅርብ ነበርሽ። ................................................ እንደውም እንደውም... በዛ ስንዝር መሀል ያኔ የተፈጠሩ እዛሬ ላይ ሆነው.. "ሰማይ ቅርብ ነበር" እያሉ ሚያወሩ እድሜ የሰጣቸው ጥቂት ሰዎች አሉ የኔና ያንቺ ፍቅር የሚመሰክሩ። ............................................. እንደውም እንደውም.... ሌላ አይነት ማስረጃ ሌላ አይነት ምስክር ሰማይ ቅርብ ሳለሽ ምጣድ ሆኜ ምድር እንዲህ እንደዛሬው... ነፋስ አቀጣጥሎት ነፋስ የሚያጠፋው እሳት ሳይፈጠር የሰው ልጆች ሁሉ በፀሐይ በርሀን ምግብ ያበስሉ ነበር። ............................................. ፀሐይ ውበትሽ ነው ጠዋት የምሞቀው ቀን ተቃጥዬበት ሌት የምናፍቀው። ለሊት ላይ ያመኛል ህመሜም አንቺው ነሽ ቀኑ ጨለማ ነው... ነግቶ እስካይሽ ድረስ ትናፍቂኛለሽ። ........................................... መቼ ነው ሚነጋው? ፀሐዩ ውበትሽ ምድርን የሚከድነው መርዙ መድሀኒትሽ... በሽታዬን ገድሎ ህመሜን ሚያድነው ካፈቀሩት ጋራ.... እንኳን ላንድ ለሊት ላፍታ ያህል እንኳን መለያየት ሞት ነው። ............................................. መቼ ነው ሚነጋው ልቤን ይበርደኛል ንጋት ላይ የሚሸሽ.. ወረተኛ ፍቅር ጤዛው በዝቶብኛል አንቺ የሌለሽበት... ራሴን ሳስበው ራሴን ያዞረኛል። ለራስ ምታት ህመም.. መድሀኒት እንዲሆን በሽታን የሚገድል መርዝ ነው ሚቀመም። ................................... እንጂማ አውቃለሁ እንጂማ ታውቂያለሽ የሰው ወሬ ሰምቶ ልብሽ ባይረበሽ እንዲህ እንደዛሬ. ሳትርቂኝ በፊት ሰማይ ቅርብ ነበርሽ። ........................ እየሔዱ መጠበቅ ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏 Join us 👇👇👇 https://t.me/yefkr_tube_1
Show all...
🥰 1🏆 1
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ 🎖#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ...... ✍ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር #Part ☞ ዘጠኝ ➒ እኔ እናትሽ በመምጣቴ ደስተኛ አይደለሽም አለችኝ? አወ ደስተኛ አይደለሁም... እናትሽ... ይገርማል! ግን ለምን ዋሻቹሁኝ  አክስቴ ! ለምን!!! ለምን . አያቴ ??? ምን በደልኳቹህ ምናለበት የቲም ነሽ ብትሉኝ ???ምን አልሽ ፊርዶሴ  አወ ሁሉንም አዉቂያለሁ እኔን የገረመኝ ዉሸታቹህ... እሽ መልሱልኝ ለምን ዋሻቹህኝ አያቴ??? ቆይ አሁን ይሻልሽና እኔ ሁሉንም ነገር አስረዳሻለሁ አለችኝ። አክስቴ እኔኮ በሽታየ  የናንተዉ ዉሸት ነዉ ሀኪም አይደለም የሚያድነዉ እዉነቱን ስታስረዱኝ ያኔ እድናለሁ። እሽ የኛዉሸት ከሆነ በሽታሽ....... እንግዲያዉስ እዉነቱን ስሚዉ እኔ የአባትሽ እህት ነኝ እማ ደግሞ የአባትሽ እናት ናት እእእ... ምን ላዉራ አፌ ተያያዘብኝ እዉነት ለመናገር እስከ አሁኖ ሰአት ድረስ ተስፋ ነበረኝ አሁን ግን ተስፋየ ተሟጠጠ፣እንባየ እንደ ጎርፍ መዉረድ ጀመረ። እንደምንም ብየ እዉነቱ ቢመረኝም ለመስማት  ተዘጋጀሁ። ግንኳ አክስቴ አልኩ እሷም ምንም አትተንፍሽ ዝም ብለሽ አዳምጭኝ አለችኝ እኔም አማራጭ የለኝምና ዝም ብየ ማዳመጥ ጀመርኩ ማዉራቷን ቀጠለች....   እናትሽ በጣም ትሁት ደግ ሰዉ...  ብቻ ምን ልበልሽ በጣም ጥሩ ልጂ ነበረች።ከባህር ዳር  እኛ ቤት የመጠዉ እንግዳ  ሁሉ ስለሷ ጥሩነት ሳያወራ አይሄድም። ታድያ ይህን የሰማዉ ወንድሜ ምን አይነት ሴት ብትሆን ነዉ ብሎ ጉዞዉን ወደ እናትሽ ሀገር ባህርዳር አረገ።  ይች እንደዚህ የሚያወሩላትን ሴትማ ማየት አለብኝ  ብሎ አድራሻዋን ማፈላለግ ጀመረ ግን አድራሻዋን ለማወቅ ብዙም አልተቸገረም ምክንያቱም አንድ የአክስቴ ልጂ (ሙሀመድ) ባህር ዳር ስለሚኖር ሁሉንም መረጃ እንዲህ ብሎ ነገረዉ ልጂቷ  መርየም ትባላለች እናቷ ሀሊማ አባትዋ ደግሞ ዳዉድ ይባላል። እንደ ሰማሁት ከሆነ ልጂቷን አያቷ ናት ያሳደጓት አባቷ ሞቷል እናቷ ደግሞ መርየምን ለአያቷ እንዲያሳድጋት ጥላት አዲስ አበባ ሀብታም ባል  አግብታ  ሂዳለች። አያቷም በጣም ሀብታም ኢማነኛ ነቸዉ አሁን ከእሱ ጋር የሚኖሩ ብዙ ወንድ ልጆች አሉት። ከቤተሰቡ ሴት መርየም ብቻ  ስለሆነች ሁሉንም ስራ የምትሰራ እሷ ናት ብቻ በጣም ታሳዝናለች የወንዶችን ሁሉ ልብስ የምታጥብ ምግብ ፣ቤት፣ እቃ ሁሉን የምትሰራ እሷ ብቻ ናት። እሽ ሙሀሜ  እሷን እንዴት ነዉ ማየት የምችል??? ዩሱፍ እኔ አላቅም ከቤት ለራሱ አትወጣም እንደዉ በአጋጣሚ ብትወጣ እንኳን መሬቱን እንጂ ሰዉ ቀና ብላ አታይም አያቷ ማሻ አላህ በዲኗ ጠንኳራ እንድትሆን በደንብ ኳትኩተዉ ነዉ ያሳደጓት ምናልባት እድሉን ካገኘከዉ አንድ አጓቷ አለ እና ልጆችም አሉት አንዳንዴ ልጃቹን እሷ ናት ትምህርት ቤት የምታደርሳቸዉ። የዛኔ ማየት ትችል ይሆናል። እሷ ትማራለች እንዴ  ሙሀሜ??? አይ ወንድሜ ስአቱ እንኳን ለትምህርትቷ ስራዋን ለመጨረስ እንኳን የሚበቃት አይመስለኝም። የዚህን ያህል ሙሀሜ!!!   አወ ወንድሜ ብዙ እንግዶች(ደረሳዎች) እነሱ  ቤት ነዉ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያርፉ እና እነሱም መካደም የመርየም ስራ ነዉ።ምን ይሄ ብቻ..... አጓቷም እዘዉ ግቢ ነዉ የሚኖር ሚስቱ በጣም ክፉ ናት። መርየም ያያቷን ስራ ከጨረሰች ቡኋላ  ልጇን እንድታዝልላት አንዳንድ ስራዎችንም እንድትሰራላት ታዝዛታለች።  መርየምም በጣም እየደከማትም ቢሆን ትሰራላታለች። ሚስቱ ብዙ ጊዜ ታስቀይማታለች መርየም ግን ምንም ብታስቀይማት ከዝምታ ዉጭ የምትናገረዉ አንድም ቃል የለም የምር ሙሀሜ ጥሩ ሴት ናት። አይ ወንድሜ ጥሩነቷንማ ሁሉም መስክሮላታል በተለይ ጎረቢቶቻቸዉ በጣም ስለ እሷ ጥሩነት ያወራሉ በተለይ ሰደቃ አድርገዉ ከሆነ አብዛሀኛዉን ስራ የምትሰራላቸዉ እሷ መሆንዋን ያናገራሉ። እሽ ሙሀሜ እንደዚህ አይነት ጥሩ  ሴት ከሆነች እንዴት ሳታገባ ቀረች።  አይ ወንድሜ በጣም ብዙ ሀብታም ባሎች በየ ጊዜዉ ይጎርፋሉ። እሷ ግን አያቴን ለማን ትቸ ነዉ የማገባዉ ትላለች። አያቷ ግን በዲኑ ጠንካራ ጀግና ከመጣ እድራታለሁ ይላል።  በቃ ምን አለፋህ ወንድሜ እነሱ ላይ ገንዘብ፣መልክ፣ ጉራ ምናምን..... አይሰራም። እነሱ ላይ መስፈርቱ የዲኑ ጉዳይ እንዴት ነዉ? ይሄ ነዉ መስፈርታቸዉ ግን ብዙ ወንዶች ይህን መስፈርት አያሟሉም እናሟላለን ቢሉ እንኳን አያቷ ላይ ሲሄዱ ምንም  የተጠየቁትን ሳይመልሱ አፍረዉ ይመለሳሉ... ግን ሙሀሜ ይሄን ሁሉ መረጃ እንዴት አገኘኸዉ? ነዉስ አንተም ከጠያቂዎች ነበርክ?  እኔ እንኳን የመጀመሪያ ጊዜ ባህርዳር ስመጣ የነሱን አንድ ክፍል ቤት ተከራይቸ ነበር የምኖረዉ። እና በደንብ ነዉ የማቃት  እሽ እስኪ አግዘኝ? ምኑን ነዉ የማግዝህ ወንድሜ እሷን እንዳገባት ምን!!!ይህን ካገዝከኝ የምን ጊዜም ባለዉለታየ ነህ በአላህ እሽ በለኝ በዛ ለይ አንተ ትግባባታለህ። አይ ወንድሜ ትቀልዳለህ እንዴ?  ስንትና ስንት ምን የመሳሰሉ ባሎችን አንድርም ብለዉ ላንተ ምንም ለሌለህ ደሀ ይድሩልህ ይመስልሀል? ባክህ አጓጉል ቀልድ ይቅርብህ።  ሆሆ!... ግዴለም ወንድሜ አንተ ብቻ እንዴት እዛ ቤት እንደምገባ ንገረኝ እንጂ ሌላዉ ሁሉ ቀላል ነዉ። እሽ እኔ እንቢ ብለዉህ ከምታፍር ብየ እንጂ  እዛ ቤትማ መግባት ቀላል ነዉ በተለይ በአሁኑ ሰአት.. እሽ እንዴት?  አሁን ረመዳን አይደል  ሁሌም በረመዳን ድሀዎችን(ሀቅም የሌላቸዉን) ያስፈጥራሉ  አንተም ሀቅም የሌለህ ድሀ መስለህ ትገባለህ መርየምንም ማየት ትችላለህ ማለት ነዉ። ይሄማ ከባድ ነዉ የዉም በረመዳን የምበላዉ ሳላጣ እንዴት አጭበርብሬ ገብቸ እበላለሁ። ሙሀሜ እኔ የምበላዉኮ ለአንድ ሚስኪን ማፍጠሪያ ይሆናል። እስኪ ሌላ ሀሳብ ካለህ.... ሌላ እንኳን.. እሽ አያቷ የተለያዪ ደረሳዎችን እቤታቸዉ ያስቀራሉ አንተም ደረሳ ሁነህ መግባት ትችላለህ ግን ትንሽ ከበድ ይላል። ትስማማለህ??? #ይቀጥላል.... #ክፍል_10 https://t.me/yefkr_world2 https://t.me/yefkr_world2 https://t.me/yefkr_world2
Show all...
1
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ 🎖#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ...... ✍ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር #Part ☞ስምንት ➑ እኔም ዞር ብየ ሳይ ያች የናፈኳት ዛሬ ነገ ትመጣለች  ብየ በተስፋ የጠበቋት እናቴ  ናት።  ይገርማል!መልኳን ለመጀመሪያ ጊዜ አየሁት በርግጥ እስከ ሁለት አመቴ ድረስ አብረኝ ብትቆይም አሁን ላይ ምንም የማስታዉሰዉ ነገር የለም።  እንዲህ እያልኩ ሳስብ አያቴና እማ ተቃቅፈዉ ሁለቱም ያለቅሳሉ።  እኔም እነሱን እያየሁ እንባየን መቆጣጠር አልቻልኩም። በጣም ደንግጫለሁ በዛ ላይ ወደ አያቴ መጠጋት እንጂ እማን መጠጋት አልቻልኩም ፈረኋት እሷ ፊርዶሴ መጠሁልሽ፤ ደስ አላለሽም? ሁል ጊዜ ለምን አትመጭም ትይኝ አልነበር። እያለች ስታወራ እኔ መልስም የለ ዝም። እያቴም ፊርዶሴ እናትሽኝ አታወሪያትም እንዴ! እንደዛ በጉጉት ትጠብቂያት አልነበር። በድጋሚ ከዝምታ ዉጭ መልስ የለኝም። እማም አቅፋ ፀጉሬን እየዳበሰች ለምድነዉ ዝም የምትይ ብላ ጥያቄዋን ጀመረች።  አያቴም ፊርዶሴ በጣም ፈሪ ናት። ብዙ ጊዜ መምህሮቿንና መክያን ካልሆነ ሌላ ሰዉ ጋር ለማዉራት ግድ ካልሆነባት በስተቀር ዝምታን ትመርጣለች። በዛ ላይ እኔም ከህፃንነቷ ጀምሬ ዘመዶቻችንን እንድትቀርብ አላረኳትም ሁሌም ዘመድ ሲመጣ ሰላም ትልና ወደነመክያ ቤት እንግዳዎች እስከሚሄዱ ድረስ ተጫወች ብየ እልካታለሁ። መቸም ከነሱ ሌላ ምንም ጎረቢት እንደለለን ታዉቃላቹህ። በሉ እየረፈደነዉ ወሬቹህን እቤት ትጨርሱታላቹህ ብሎ አጎቴ ይዟን ወደ ቤቱ ሄደ።በምንገድ ላይ እያለን ግን ቀይ መብራት በርቶ አጎቴ መንዳቱን አቆመ። ሲገርም አዲስ አበባ እንደዚህ ዉብ ናት?እያልኩ ሳወራ አጎቴ ወደኔ ዞር ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለመጣሽ አዲስ ሁኖብሽ ነዉ አለኝ። እማም ሱኡዲን ብታያት ከዚህ ትበልጣለች እያለች አንዳንድ ወሬዎችን ስናወራ አጎቴ መንዳት ጀመረ።  በፍጥናት ስለነበር የሚያሽከረክር ቶሎ እቤቱ ደረስን። ቤቱንም ስናንኳኳዉ የከፈተችልን እድሜዋ ከኔ አኳያ የነበረች የአጎቴ ልጂ ናት።ሀናን ትባላለች። የአጎቴ ሌላም ልጆች አሉት አንደኛዉአብዱል ሀኪም ሲሆን አንደኛዉ ደግሞ ኻሊድ ይባላሉ። እማም ሰላም ካለቻቸዉ ቡኋላ ወደ ዉስጥ ገባን። የአጎቴ ሚስትም ብዙ ምግቦችን አዘጋጂታ ነበርና የቀረበዉን በልተን ጨዋታ ጀመሩ እኔም በጣም ደስ ስላለኝ ለመኩ ደዉየ እማ መምጣቷን በደስታ ነገርኳት።ከሷ ሌላ እማ መምጣቷን ለማን ልናገር እያልኩ ሳስብ ምንም ሌላ የማዉቀዉ ሰዉ የለኝም ለማትስ መምህሬም ልነግረዉ አሰብኩና ስልኩን አጣሁት። ወይ ፊርዶስ ሰዉ እንዲህ ሲደሰት አይቸ አላዉቅም አለችኝ ሀናን። እኔም እማ ብየ ሳልጨርስ....ወዲያዉ አያቴ መጣች ምን እያወራቹህ ነዉ ኑ ሳሎን ቤት ብላ ይዛን ሄደች። አያቴ ምንም አይነት ወሬ ከሌላ ሰዉ ጋር እንዳወራ አትፈቅድልኝም ለምን እንደሆነ ግን መልስ ያጣሁለት ጥያቄ ነዉ። እኛም ወደ ሳሎን ቤት ስንገባ እማ ሻንጣ እየበረቀሰች ነዉ።  ኑ ያመጠሁላቹህን ልብስ እዩት እያለች ብዙ ልብሷችን አወጣች። ይሄ የፊርዶስ ይሄ ደግሞ ያንች እያለች ሂጃቦችን፤ጫማዎችን፤ቀሚሶችን..... አከፋፈለችን። ሀናን ግን በተሰጠችዉ ነገር ደስተኛ አትመስልም። እኔ ግን ደስ ብሎኛል እዉነት ለመናገር ለኔ የተሰጠሁት ሁሉም ነገሮች በጣም ያምራሉ።  የተሰጠሁትንም ሞክሬም አሳየኋቸዉ ማሻ አላህ ቢረዝምሽም በጣም ያምራል እያሉ.... ደግሞ ሀናን እስኪ ሞክሪዉ ማለት ጀመሩ። ሀናን ግን ለመሞከር ፍቃደኛ አልነበረችም። የተሰጠችዉን ሳቲዝም ወደ ዉስጥ ገባች የተናደደች ትመስላለች ። እኔም የለበስኩትን አዉልቄ በቃ ለሀናን  የተሰጠሁትን ሁሉ እሰጣታለሁ ብየ ሁሉንም የተሰጠሁትን ነገር ሰብስቤ  ወደ ገባችበት ክፍል አመራሁ።ወደ ክፍሉም ጠጋ ስል ሀናንና አባቷ እያወሩ ነዉ። እኔም አዉርተዉ እስከሚጨርሱ በቆምኩበት  ልጠብቃቸዉ ወሰንኩ....  ሲያወሩ ድምፃቸዉ ይሰማል።  አባየ ግን  ለፊርዶስ የተሰጣት ልብስ የሚያማምሩ ለኔ ግን........  እሽ ለምንድን ነዉ አክስቴ የምታዳላ ፊርዶስም የመንድሟ ልጂ እኔም የወንድሟ ልጂ።  ደሞስ እማ ለምን ትላታለች አክስቷ አይደለችም እንዴ? ልጀ ልክ ነሽ አክስቷ ናት ግን እሷ እናቷ እንደሆናች ነዉ የምታዉቅ። እናትና አባቷስ አማየ? እነሱ ሙተዋል ሚሲኪን ፊርዶስ... ቆይ እስኪ ለምን ደበቋት? ከዚህ በላይ ማዳመጥ አልቻልኩም። ብዙ አሰብኩ ግን መክያ ያለችን እዉነት ነዉ?... አላምንም እያልኩ እግሬ ይንዘረዘር ጀመር፣ሰማያና ምድሩ ዞረብኝ፣ ትንፋሽ አጠረኝ ከዛ ቡኋላ የተፈጠረዉን አላስታዉስም..... ብቻ አይኔን ስገልፀዉ አያቴ ታለቅሳለች እማ የምላትም እጀን ይዛ ታለቅሳለች  አጎቴም ፊርዶሴ ፊርዳሴ እያለ ይጮሀል..... እኔም ግራዉ ገብቶኝ እየት ነኝ የተደረገልኝን ግልኮስ  ምንድን ነዉ? ለምን ታለቅሳላቹህ? እያልኩ ጠየኳቸዉ አያቴም አደራየ ደህናነሽ የኔ ዉድ? አወ... አያቴ ደህና ነኝ አታልቅሽ ብየ እንባዋን ልጠርግላት ስል እጀ ላይ የተተከለዉ ግልካስ አስቸገረኝ አጎቴም እጂሽን አታንቀሳቅሽዉ እኔ ዶክተሩን ጠርቸዉ ልምጣ ብሎ ወጣ እናቴም ማለትም ሀያት ፊርዶሴ ምን ሁነሽ ነዉ? ምንም አቶኝብሽም አይዞሽ ትላለች። እዉነት ለመናገር እኔ አሁን ላይ ሁሎችም  አስጠልተዉኛል ምናለበት እናትና አባት የለሽም ብለዉ ቢነግሩኝ  እስከዛሬ በተስፋ ከምጠብቃቸዉ መሞታቸዉን ቢነግሩኝ ጥሩ ነበር  ለካ አያቴ ከሰዉ ጋር ሳወራ የምትከለክለኝ፤ ዘመድ ሲመጣ ተጫወች ብላ የምትልከኝ፤ እንዳይነግሮት ብላ ፈርታ ነዉ።...... እያልኩ አለቅስ ጀመር እዱንያንም በጣም ጠላኋት ምናለ በሞትኩ እያልኩ ተመኘሁ አሁን ላይ ማንንም ማየትም ሆነ ማናገር አልፈልግም ዝም ብየ ፊቴን አዙሬ ማልቀስ ብቻ  ሆነ ስራየ ሀያትም ፊትሽን ለምን ወደ ግድግዳዉ አዞርሽዉ ወደ እኛ አትዟሪም እሽ እኔ እናትሽ በመምጣቴ ደስተኛ አይደለሽም አለችኝ እኔም... #ክፍል_9 #ይቀጥላል.... https://t.me/yefkr_world2 https://t.me/yefkr_world2 https://t.me/yefkr_world2
Show all...

2
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ 🎖#የታሪኩ_ርዕስ ☞ #አደራዬ...... ✍ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር #Part ☞ ሰባት ➐ ማን ይሆን ብየ ስልኩን ሳነሳዉ  አሰላሙ አለይኩም ፊርዶሴ እንዴት ናቹህ??? ማንነቷን ለማወቅ ጊዜ አልፈጀብኝም እማ ናት። እኔም እንባየ እየተናነቀን አልሀምዱሊላህ እኛ ደህና ነን አንች እንዴት ነሽ ስራ ሁሉ ሰላም ነዉ?  አወ ሁሉ ሰላም ነዉ እኔምልሽ ፊርዶሴ እማየ እንዴት ናት? አሁንኮ የመክያ እናት ሚስኮል አድርጋልኝ ምን ሁና ነዉ በሰላም ነዉ ብየ ስደዉልላት እማየን ትንሽ እንዳመማት ነገረችኝ አሁን እንዴት ናት??? አሁን አልሀምዱሊላህ ትኩሳቷም ትንሽ ቀዝቀዝ ብሎላታል እንደዉም እንኪ አናግሪያት ብየ ስልኩን ሰጠኋት። አያቴም...   ሀያቴ እንዴት ነሽ እኔስ አልሀምዱሊላህ አንችን ትንሽ አሞሻል ብለዉኝ እንዴት እንደ ጨነቀኝ። ኧረ ሀያቴ ወላሂ ደህና ነኝ አትጨነቂ.... አሁን እንደዉምተሽሎኝ ምግብ አየበላሁኝ ነበረ የደወልሽ ይልቅ የኔን ተይዉና ጤናሽን አንች  እንዴት ነሽ ሁሉም ነገር ሰላም ነዉ?  አወ አማ ሁሉም ሰላም ነዉ። .... ወላሂ እማ  እንዴት እንደናፈቃቹህኝ አይ ባንናፍቅሽ ነዉ እንጂ ብንናፍቅሽማ  ትመጭ አልነበር እኔም ጤና ሲርቀኝ ምናለ  ብትመጭና ሁላችንም ደስ ባለን ወላሂ እማ አሁንስ ለመምጣት ተዘጋጂቻለሁ። ......  አይ ልጀ ሁሌም እመጣለሁ እያልሽ ተስፋ ትሰጭንና ስንጠብቅሽ አትመጭም። እማ እመኚኝ አሁን መጨረሻየ ነዉ። እሽ ከሆነ ደስ ይለኛል በደስታ እንቀበልሻለን በይ ቆጠረብሽ...... ደህና ሁኚ ብላ  ስልኩን ተዘጋቹዉ።  እኔም ወደ አያቴ ዙሬ አያቴ ምን ብላሽ ነዉ  እንደዚህ ፍንድቅ ያልሽ?   እናትሽ ልትመጣልሽ ነዉ። እእእእእ ምን???እዉነትሽን ነዉ.....   ማመን አቃተኝ የደስታ እንባ አለቀስኩ በቃ ህልሜ እዉን ሊሆን ነዉ ብየ ሱጁድ ወረድኩ አላህየ እስከ ዛሬ ለምን አትመጣም ብየ የተናደድኩትን ይቅር በለኝ ብየ መሳቅ ጀመርኩን ለካ የመክያ እናት ትክክል ነበረች ጊዜ ራሱ ይመልስልሻል ያን ጊዜ ጠብቂ.... ያለችን አሁን ግዜዉ እየደረሰ ነዉ ከጭንቀቴ ልገላገል ነዉ አልሀምዱሊላህ። አያቴ ቤቱንም ቀለም እናስቀባዋለን አሮጌ እቃወችንም በአዲስ እንቀይራቸዋለን ሌላ ደግሞ አሀ.. አስታወስኩ የወለሉ ምንጣፍም በአዲስ መቀየር አለበት ግን ምን አይነት ከለር ይሁን....በቃ ከቤቱ ቀለም ጋር አንዳይነት ይሆናል አይሻልም  አያቴ......  በግርምት ታየኛለች....  እንዴ! አያቴ  ዛሬኮ እንደዚህ የሚያስለፈልፈኝ በጣጣጣም ደስ ስላለኝ ነዉ አንች ግን ቅድም ደስ ብሎሽ ነበር አሁን ግን እንደ ቅድሙ አይደለሽም ነዉስ እናቷ ከመጣች ትረሳኛለች እንደድሮዉ አትወደኝም ብለሽ ፈራሽ....... ሀሀሀ አይዛሽ እንደዉም በጣም ነዉ የምወድሽ  መቸም ቢሆን ደግሞ  እልቤ ዉስጥ እንዳንች ልዩ ቦታ ያለዉ ማንም የለም።    ኢላሂ የአያቴን ነገር አደራ እረዥም አድሜ ከጤና ጋር ስጥልኝ እያልኩ ሁል ግዜም ዱአ አረግልሻለሁ። አደራየ እኔም እኮ ደስታየ ከመጠን በላይ ሲሆንብኝ ነዉ ዝምታን የመረጥኩ እንጂ በጣም ነዉ ደስ ያለኝ። እሽ  አያቴ  ከአሁኑ ጀምረን ቤታችንን ማሳመር አለብን ሆ! በስኡዲ ቤት አይነት የኛን ቤት አይታ ልመለስ እንዳትል....  አይ አደራየ ትቀልጃለሽ የምር እየቀለድኩ አይደለም  እሽ ከቀለሙ እንጀምር ምን አይነት ቀለም ይቀባ እኔ እንደሚመስለኝ ዉሀ ሰማያዊ ወይም ደግሞ ፈዘዝያለ ነጭ አንችስ አያቴ?  እኔ ምኑን አዉቀዋለሁ ብለሽ ነዉ አደራየ  በቃ እሽ ፈዘዝ ያለ ሰማያዊ ይሆናል ትስማሚያለሽ? እሽ ይሁን ከቀለሙ ቡኋላ ሌላዉን እያየን እናስተካክለዋለን........ አሁን የጀመርነዉን ምግብ እንጨርስና የምሄድበት ቦታ አለኝ። አደራየ በዚህ ስአት የት ነዉ የምትሄጂ? ሀሱር እኮ ከተሰገደ ቆየ ጀንበርም ጠልቃለች በቃ እሽ መቅሪብ ሳይደርስ ቶሎ እመለሳለሁ። አንች ብይ.... ቻዉ ቶሎ እመለሳለሁ። እሽ ወዴት ነዉ የምትሄጂ.... እነ መክያ ቤት ቶሎ እመለሳለሁ ባለፈዉ የቀለደችብኝን ዛሬ እማ ልትመጣ መሆኑን ልነግራት ነዉ አይ አደራየ ስትመጣ ታያት የለ አሁን ለምን ትነግሪያታለሽ....  ቢሆንም አያቴ ልንገራት በዛዉም ለእናቷ  እንደ ተሻለሽ ልንገራት በጣም ተጨንቃ ነበር።  እሽ ቶሎ ተመለሽ። እሽ አያቴ....  በፍጥነት ስለሆነ የሄድኩ ለመድረስ ሰአት አልወሰደብኝም ቶሎ ደረስኩ በራፉንም አንኳኳሁት መክያ ከፈተችልኝ ደንገጥ ብላ ምንድን ሁነሽ ነዉ ፊርዶስ ? አያትሽ ደህና አደለችም እንዴ?  ኧረ ደህና ናት ዛሬ እንዴት ደስ እንዳለኝ ልነግርሽ ነዉ እየሮጥኩ የመጠሁ... ምን አይነት ደስታ ተገኝቶ ነዉ እንዲህ አሩጦ ያመጣሽ? እናቴ ልትመጣ ነዉ። እንኳን ደስ ያለሽ ፊርዶሴ ወላሂ በጣም ደስ ይላል ። እሽ ወደ ዉስጥ እንግባና እናዉራ ብርድ ነዉ። አይ! እቸኩላለሁ ይህን ደስታ ልንገርሽ ብየ ነዉ ደሞ እናትሽን ንገሪልኝ አያቴም አልሀምዱ ሊላህ ተሽሏታል ደህና ደሪ ቻዉ እሽ... ቻዉ አያትሽን ሰላም በይልኝ ብላኝ ተለያየን..... እኔም እየሮጥኩ እቤቴ ቶሎ ደረስኩ ። አያቴ ቶሎ መጣሁ አይደል?....  አወ ግን ሳትደርሽ ከምንገድ ተመልሰሽ እንዴ? በጣም ፈጠንሽ...... እቤት አልገባሁም ከዉጭ ነዉ ለመክያ ነግሪያት የተመለስኩ  ለዛ ነዋ የፈጠንሽ። አወ አያቴ ግን መቸ ይሆን የምትመጣ እያልን ቀን መቁጠር ጀመርን ይኸዉ ሳምንት፤ወር፤ከአመትም አልፎ አመታት ተቆጠሩ። አሁን አራት አመታችን ገባ  እኔም አስራ ሁለተኛ ክፍል ደረሰኩ  አያቴም እርጂና እየተጨጫናት መጧል ብዙ ነገሮች ተቀይረዋል እኔ ለራሱ ቁርአኔን ጨርሸ ኪታብ መቅራት ጀምሬለሁ.... በዛ ላይ በትምህርቴም ከበፊቱ በጣም ጎብዛለሁ ሰሞኑን ትምህርት ይጀመራል። በአዲስ አመት አዲስ ተስፋ ሰንቀን ዘንድሮም በተስፋ እየጠበቅናት ነዉ ዘንድሮ ግን ተስፋ ሳይሆን እዉነት ነዉ ምክንያቱም ትኬት እንደቆረጠች ነግራናለች ግን ተስፋችን ስላለቀ  አላመንም። ዛሬ ደዉላ ጥቅምት ሳስት ጁመአ ለሊት በረራዋ እንደሆነ ነገረችን አሁን ተስፋችን ቢያልቅም ትንሽም ቢሆን እዉነት እዉነት መሰለን የማይደርስ የለምና ዛሬ ጥቅምት አንድ ነዉ ሁለት ቀን ቀራት ማለት ነዉ ልትመጣ.... እያልን ልንቀበላት  ወደ አዲስ አበባ  አቀናን እዛም ብዙ ዘመዶች አሉን።ካሉን ዘመዶች መካከል የመጀመሪያዉ አጎቴ ነበርና ደመቅ ባለ አቀባበል ተቀበለን። ወደ ቤቱም ይዟን ሄደ  ማሻ አላህ ቤቱ በጣም ያምራል እኛም እሮብና ሀሙስን ከሱ ጋር አሳልፈን።......... ጁመአ   1 ሰአት ኢትዮጲያ እንደምትገባ ነገረኛለች። ዛሬ ደግሞ ሀሙስ ምሽት ነዉ እኔ እዉነት ለመናገር  ምንም እንቅልፍ አልወሰደኝም በየ ደቂቃዉ ተነስቸ ሰአት ሳይ ነበረ። አሁን አስራአንድ ሰአት ሁኖል ሁሉንም ቀሰቀስኳቸዉ። እነሱም ተነስተዉ ሱቢሂን አንድ ላይ ከሰገድን በኋላ.....   አጎቴም መኪናዉን ይዞ አያቴን፣ እኔን እና የአክስቴን ልጂ በአንድ ላይ ወደ ቦሌ ይዞን  ሄደ። እዛም አስራ አንድ ተኩል ደረስን የኔም አይኔ ወደ ሰማይ ያይ ጀመር እዚህ ፕሌን ላይ ትሆን እማ እያልኩ ስጠባበቅ አንድ ሰአት ደረሰ  ፍራት ፍራት ይለኝ ጀመር አይኔም የሚመጣዉን የሚሄደዉን ሰዉ ይመልከታል።  ከድንገት አያቴ እልልልል አለች እኔም ዛር ብየ ሳይ........ #ክፍል_8 #ይቀጥላል.... 👇👇🤝👇👇 https://t.me/yefkr_world2 https://t.me/yefkr_world2 https://t.me/yefkr_world2
Show all...
👍 1🥰 1
Repost from N/a
🇪🇺 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ       ⏰ ተጠናቀቀ' አርሰናል 2-2 ባየር ሙኒክ ⚽️ሳካ 12'.   ⚽️ ግናብሪ ⚽️ትሮሳርድ 76   ⚽️ ኬን ድል ለአርሰናል ❤️ "SHARE" . @ETHIO_ARSENAL_221
Show all...
🔥 1
Repost from N/a
🇪🇺 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ       ⏰ 15' አርሰናል 1-0 ባየር ሙኒክ ⚽️ሳካ 12' ◾️ || • ድል ለአርሰናል ❤️ "SHARE" . @ETHIO_ARSENAL_221
Show all...
👎 1🔥 1
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ 🎖#የታሪኩ_ርዕስ ☞ #አደራዬ...... ✍ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር #Part ☞ ስድስት ➏ እሽ ምኑን ነዉ የምነግርሽ አደራየ??? አያቴ ዛሬ ወላሂ ብዙ ጥያቄዎችን ትመልሽልኛለሽ ካልሆነ ግን በትምህርቴ እሰንፍብሻለሁ...  ቅድም የመጠዉን መምህሬን አየሽዉ አይደል? አወ አደራየ እና ምን ሲለኝ አንደነበር ልንገርሽ በትምህርትሽ በጣም እየቀነሽ ነዉ እንደድሮዉ መከታተል አቁመሻል። ችግሩ ምንድን ነዉ?.. እያለ ነዉ የጠየቀኝ እዉነቱን ነዉ አወ እንደ ድሮዉ መከታተል አቁሜለሁ ለምን እንደሆነ ታቃያለሽ አያቴ!... ኧረ አላቅም እሽ ለምንድን ነዉ አደራየ ትምህርትሽን እንደ ድሮዉ የማትከታተይ?  ምክንያቱ አንች፤ እማ፤አባ ናቸሁ ታዉቂያለሽ አያቴ ወላሂ ትምህርት ቤትኮ አባታቸዉ ሲሸናቸዉ አብረዉ ከልጆቻቸዉ ጋር ሲስቁ ሳይ እንባየ ይመጣና ኢንሻ አላህ አንድ ቀን እኔም እንደነሱ ከአባቴ ጋር እስቃለሁ ብየ አንገቴን ወደ መሬት ዝቅ አድርጌ አልፋለሁ። በሌላኛዉ ቀን ደግሞ ከእናታቸዉ ጋር ተቃቅፈዉ ሳያቸዉ እማ ትመጣና እኔም እንደ ነሱ አቅፋታለሁ ብየ ተስፋ አደርጋለሁ ግን ያቀን መቸ ነዉ??? እሽ አናቴ አልሳካልኝ ብሎ ነዉ እንጂ እመጣለሁ ብላለች አባቴስ ጨካኝ ነዉ እንኳን ሊመጣ መች ደዉሎስ ያቅና ግን አንድ ቀን ይመጣል።እኔም በተስፋ እጠብቀዋለሁ። ግን አያቴ በአላህ መቸ ነዉ የማያቸዉ አባቴስ ለምን አይደዉልም?... እናቴስ ለምን አትመጣም?... ለዛሬ እነዚህን መልሽልኝና አደራየ ያልሽኝን ምክንያት ደግሞ በሌላ ቀን ትነግሪኛለሽ።   እሽ ምን ልበላት.......... እኔስ ግራዉ ገባኝ ኧረ ምን ልበላት ሁሌም አስባለሁ እዉነቱን ልነግራት ዛሬ ግን ግድ ነዉ እተነፍሳለሁ ግን ምን ብየ አወራለሁ..... እናቴ ናት እያልሽ እማ የምትያት አትመጭም ወይ ብለሽ የምታናግሪያት እማ አይደለችም ዉዷ አክስትሽ ናት እማ ወዴት ሄደች ብለሽ ከጠየቅሽኝ ሞታለች ብልሽስ እንዴት ነዉ ምታምኝኝ 10 አመት ዉሸት ምን አይነት አያት ነኝ እሽ ምን ልበላት አባቴስ ብትለኝ.... ያዉዱ አባትሽ ፊርዶሴ የሚልሽ ሲወጣ ሲገባ አይቷኳን ማያምንሽ የአይኔ ማረፊያ ፊርዶሴ የኔ ዉድ የስደትን ጉዞ እንዴት ጥያት ልሂድ ብሎ ሚሳሳልሽ ጨካኝ የምትይዉ ጨካኝኮ አይደለም ጨካኝ አትበይዉ አባ አባ ብለሽ ጩከሽ ብትጠሪዉ አልሰማሽ ብሎ ነዉ ጨካኝ ነህ አትበይዉ ሰምቶሽ እንዳይመጣ አፈር ተጭኖበት ስታዝኚ እንዳያይሽ ጨለማ ሁኖበት   አልመጣም እንዳይልሽ   አትሰሚዉ አይሰማሽ በቃ አትጠብቂዉ ሞቷል እንዳልላት እሳሳላታለሁ አትኖርም በሂወት እኔስ ግራዉ ገባኝ እሽ ምን ልበላት? አያቴ መልሽልኝ እንጂ ምነዉ በሀሳብ ተጓሽ አያቴ አያቴ...... አያቴ ምን ሁነሽ ነዉ እያላበሽ እኮ ነዉ! ምንም አልሆንኩም አደራየ። ትንሽ ትንፋሽ አጥሮኝ ነዉ.... እስኪ ደዉይና የመክያን እናት ጥሪልኝ... እሽ አያቴ እደዉላለሁ አይዞሽ ምንም አትሆኝብኝም። እያልኩ እጀ ይንዘረዘራል፣  ሰዉነቴ ይንቀጠቀጣል ለመደወል እጀ እንቢ አለኝ እንባየን መቆጣጠር ተሳነኝ ግን አንደምንም ብየ ሄሎ እእእ.... አያቴ አያቴ የምለዉ ጠፋብኝ ከእጀ ላይ ስልኩ ወደቀብኝ ወደ አያቴ ዛር ስል....... እንባዋ ይፈሳል..... እሩጨ ሂጀ ጥብቅ አርጌ አቀፍኳት እንባዋን እየጠረኩ ምንም አትሆኝብኝም አይዛሽ እያልኩ ሳለቅስ በሩ ተንኳኳ  እኔም እየሮጥኩ ከፈትኩት የመክያ እናት ናት።እኔም ግቢ አያቴን አሞብኝ ነዉ የደወልኩልሽ። ነይ ብየ ይዛት ገባሁ እሷም  ወደ አያቴ  ጠጋ ብላ ተቀመጠች ግንባሮን በእጃ ስትነከዉ በጣም ያተኩሳል ዉሀ አምጭልኝ ብላ በልብስ አየነከረች እግንባሯ ላይ በፎጣ እያረገች ትኩሳቷ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን  ቀነሰችላት አልሀምዱሊላህ።  አኔም በቃ አያቴ ሀኪም ቤት ከመክያ እናት ጋር እንሂድ አልኳት እሷ ግን ፍቃደኛ አልነበረችም ወላሂ አሁን ተሽሎኛል በደንብ መተንፈስም እችላለሁ ትኩሳቱም ቢሆን ቀንሶልኛል  አታስቡ አለችን። የመክያ እናትም አሁን ትኩሳቷ ስለቀዘቀዘላት  አትጨነቂ ግን ፊርዶሴ በምን ምክንያት ነዉ እንደዚህ የሆነችብሺ ስራ አብዝታ ነዉ ነዉስ ተጨንቃ ነዉ አለችኝ እኔም ሁኔታዉን በዝርዝር አስረዳኋት። አሀ... በሽታዋ ጭንቀት ነዉ። በአላህ ፊርዶሴ በእንደዚህ  አይነት ጥያቄ አታጨናንቂያት ብትሞትብሽስ .... አያትሽ ከድሮም ጭንቀት አለባት  እየሰማሽኝ ነዉ.. እኔምእያለቀስኩ  አወ ሰምቸሻለሁ ወላሂ ቃል እገባልሻለሁ ከእንግዲህ ምንም አይነት ጥያቄ አልጠይቃትም። ጎበዝ ፊርዶሴ ጥያቄዎችሽን ጊዜ ይመልስልሻል እንች ብቻ ያን ግዜ ጠብቂዉ። እሽ...... በሉ ደህና ዋሉ ቤቴን ክፍት ትቸዉ ነዉ የመጣሁ አያትሽንም አላህ ያሽርልሽ አለችኝ አኔም እንዴት እንደማመሰግንሽ አላቅም ጀዛከላህ ብያት  ሄደች። ከሄደች ቡሀላ ወደ አያቴ ጠጋ ብየ አያቴ ወላሂ አዉፍ  በይኝ....  አደራየ አዉፍ  ማለት ካለብኝስ እኔን አዉፍ  በይኝ በአላህ አያቴ አንች ምን አጠፋሽና ከእናትም በላይ ዉብእናት እኳ ነሽ.... ነኝ ብለሽ ነዉ አደራየ! የጠየቅሽኝን ጥያቄ መልስ መስማት ከፈለግሽ አዳምጭኝ።  ወላሂ አያቴ በቃ ተይዉ መልሱን አንች ሳትሆኝ ግዜ እራሱ ይመልስልኛል ብቻ አንች ደህና ሁኝልኝ ምንም እንዳያስጨንቅሽ  አብሽሪ እሽ.. እንደዉ ምን ላድርግሽ አላህ አንችን የመሰለ ልጂ  ስለሰጠኝ ሁል ጊዜ አመሰግነዋለሁ አልሀምዱሊላህ ብላ ፈገግ አለች  አይ አያቴ  እንደዚህ ስትስቂ እንዴት እንደሚያምርብሽ ደሞ ፈገግታ ሱና ነዉ አይደል አያቴ.. አወ አደራየ አሁን ምሳሽን ብይ ጥዋትም ሳትበይ ነዉ የሄድሽ እሽ አያቴ ብየ አቅርበን መብላት ስንጀምር የቤቱ ስልክ ጠራ ማን ይሆን ብየ ሳነሳዉ...... ክፍል ❼ #ይቀጥላል.... 👇👇🤝👇👇 https://t.me/yefkr_world2 https://t.me/yefkr_world2 https://t.me/yefkr_world2
Show all...
🥰 1