en
Feedback
መላ የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት

መላ የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት

Open in Telegram

መላ የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት Mela Special Needs Service

Show more
270
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Similar Channels
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
December '24
December '24
+21
in 2 channels
November '24
+41
in 1 channels
Get PRO
October '24
+108
in 0 channels
Get PRO
September '240
in 0 channels
Get PRO
August '240
in 0 channels
Get PRO
July '240
in 0 channels
Get PRO
June '240
in 0 channels
Get PRO
May '240
in 0 channels
Get PRO
April '240
in 0 channels
Get PRO
March '240
in 0 channels
Get PRO
February '24
+272
in 0 channels
Date
Subscriber Growth
Mentions
Channels
09 December+1
08 December0
07 December0
06 December0
05 December+3
04 December+3
03 December+3
02 December+2
01 December+9
Channel Posts
የሥራ ማስታወቂያ ብዛት፦ 1 የሥራ ዓይነት፦ በትምህርት ቤት የአንድ ለአንድ የትምህርት ድጋፍ የት/ቤት ስም፦ Intellect International School ተፈላጊ ባለሞያ፦ የልዩ-ፍላጎት ባለሞያ
የሥራ ማስታወቂያ ብዛት፦ 1 የሥራ ዓይነት፦ በትምህርት ቤት የአንድ ለአንድ የትምህርት ድጋፍ የት/ቤት ስም፦ Intellect International School ተፈላጊ ባለሞያ፦ የልዩ-ፍላጎት ባለሞያ ፣ የሥነ-ልቦና ባለሞያ የሥራ ቦታ፦ ደብረ ዘይት የሥራ ሰዐት፦ በት/ቤቱ የትምህርት ሰዐት ከዚህ በታች በተቀመጠው ስልክ ቁጥር ያመልክቱ 📞 +251952118642 ወይም ከዚህ በታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ ያመልክቱ @MelaSpecialNeedsServiceaccount

2
የሥራ ማስታወቂያ የሥራ ዓይነት፦ የቤት ለቤት የትምህርት ድጋፍ የድጋፍ አይነት፦ ለ2ኛ ክፍል የ8 ዓመት ልጅ ሁሉንም የትምህርት አይነቶች ማስጠናት ተፈላጊ ባለሞያ፦ የልዩ-ፍላጎት ባለሞያ ፣ የሥነ-ል
የሥራ ማስታወቂያ የሥራ ዓይነት፦ የቤት ለቤት የትምህርት ድጋፍ የድጋፍ አይነት፦ ለ2ኛ ክፍል የ8 ዓመት ልጅ ሁሉንም የትምህርት አይነቶች ማስጠናት ተፈላጊ ባለሞያ፦ የልዩ-ፍላጎት ባለሞያ ፣ የሥነ-ልቦና ባለሞያ የሥራ ቦታ፦ አዲስ አበባ ፡ ጀሞ ሚካኤል የሥራ ሰዐት፦ በሳምንት 3 ቀን ከዚህ በታች በተቀመጠው ስልክ ቁጥር ያመልክቱ 📞 +251952118642 ወይም ከዚህ በታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ ያመልክቱ @MelaSpecialNeedsServiceaccount
1 160
3
ልባዊነት 💛💚 የ " Brentford fc " አጥቂ የሆነው " ኒል ሙፔይ " ቅዳሜ ዕለት ከ " Nottingham fc " በተደረገው ጨዎታ ለክለቡ የማሸነፊያ ጎል ካስቆጠረ በኃላ በቀጣዩ ቀን ደስታ
ልባዊነት 💛💚    የ " Brentford fc " አጥቂ የሆነው " ኒል ሙፔይ  " ቅዳሜ ዕለት ከ " Nottingham fc " በተደረገው ጨዎታ ለክለቡ የማሸነፊያ ጎል ካስቆጠረ በኃላ  በቀጣዩ ቀን ደስታውን በክለቡ በሚገኘው ' Down syndrome ' ማዕከል ከልጆቹ አክብሯል፡፡ እኛስ መቼ ይሁን ደስታችንን የምናካፍላቸው?🤔🤔 📞+251952118642 @MelaSpecialNeedsService @MelaSpecialNeedsServiceAccount
301
4
እንኳን ለከተራ እና ለጥምቀት በዓላት በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉን ለምታከብሩ በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የከተራና የጥምቀት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ! መልካ
እንኳን ለከተራ እና ለጥምቀት በዓላት በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉን ለምታከብሩ በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የከተራና የጥምቀት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ! መልካም በዓል! 📞+251952118642 @MelaSpecialNeedsService @MelaSpecialNeedsServiceAccount
408
5
ታሪክን የኃሊት ሉዊስ ብሬል ክፍል ሁለት ( 2 ) አጭር ግጥም « ባርበር በጨለማ ጠላትን ለመውጋት »   ለወታደሮቹ ፈጠረ ብልሃት፣ ይጠቅማል በማለት ባርበር ይህንኑ፣ ወሰደና አሳየ ለአይነስውራኑ፣ በዚሁ ፈጠራ ብሬልም ተደንቆ፣ አሰበ ሊሰራው እጅጉን አራቆ፣ በባርበር ግኝት ላይ ጥናቱን መስርቶ፣ የዳሰሳ ጽሑፍ ሉዊስ ሠራ ተግቶ። በሉዊስ ፈጠራ በጣም ደስ ብሎናል፣ እኛም እንደ ሌሎች አንብበን ጽፈናል።            ሉዊስ ብሬልና የሥራው ፍሬ ሉዊስ ብሬል የረጅም ጊዜ ጥናቱን ውጤት አጥጋቢ ሆኖ አገኘው። ይህንንም በተግባር ለማየት በተማሪዎቹ ላይ  ሞከረ። ሙከራውም ፍሬያማ ሆነለት። በዚህም ጽሑፍ አንድ የታሪክ መጽሐፍ ተገለበጠ። በስራ ላይም ዋለ። ይህንንም መጽሐፍ ተማሪዎቹ ወደዱት። ነገር ግን የተቋሙ አስተዳዳሪና ጥቂት መምህራን ተቃወሙት። ወዲያውም በሥራ ላይ እንዳይውል አገዱት። ሉዊስ የብዙ ዓመታት ልፋቱ ውጤት እንዲኽ በመሆኑ አዘነ። ተስፋ-ቆርጦ ነገሩን ችላ አለው። ቢሆንም አንዳንድ ተማሪዎች የሉዊስን ጽሑፍ በድብቅ ማጥናት ቀጠሉ። በዚህ ሁኔታ ጥቂት ዓመታት ከቆየ በኋላ አጋጣሚ ሆኖ የተቋሙ አስተዳዳሪ ተቀየረ። ቀደም ሲል የነበረውም የባለስልጣኖች ተጽዕኖ ቀነሰ። አዲስ አስተዳዳሪም ተተካ። ይህም አስተዳዳሪ የሉዊስን ሥራ ዐይቶ ደገፈው።  በከፊልም ስራ ላይ እንዲውል ፈቀደ። ሉዊስም ሆነ ተማሪዎቹ በነገሩ ተደሰቱ። ጥቂት እንደ ቆየ አስተዳዳሪው የሉዊስን ስራ አመነበት። ስለዚህ በሃገር ደረጃ እንዲታወቅ ሞከረ። ይህንንም ለበላዮቹ አቀረበ። ሉዊስ ግን የነገሩን ውጤት ሳይሰማ በጸና ታመመ። በሽታውም የሳንባ ነቀርሳ ነበር። በዚህም በሽታ ለ17 ዓመታት ያህል ሲሰቃይ ቆይቷል። በህመሙም ምክኒያት ሉዊስ በተወለደ በ43 ዓመቱ በ1844 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ሉዊስ ቢሞትም ሥራው ግን አልሞተም። ይኽ ሥራው በመላው ፈረንሳይ ታወቀ። ስለዚህም የሃገሩን ከፍተኛ ሊሻን እንዲሸለም ተወሰነ። ሽልማቱንም እናቱ እንዲቀበሉ ተደረገ። የሉዊስ ሥራ በአጭር ጊዜ በዓለም አይነሥውራንም እንዲያነቡና እንዲጽፉ መንገድ ከፈተ። ስራውም በስሙ ብሬል ተብሎ ተጠራ።  ሉዊስ ብሬል የሞተበት መቶኛ ዓመት በታላቅ ድምቀት ተከበረ። በዚህን ጊዜ የሉዊስ ኣጽም ከትውልድ መንደሩ ከኩፕቭራይ ተነስቶ ወደ ፓሪስ ተወስዶ እንዲያርፍ ተደረገ። #ታሪክን_የኋሊት 📞 +251952118642 @MelaSpecialNeedsService @MelaSpecialNeedsServiceGroup @MelaSpecialNeedsServiceaccount
430
6
No text...
376
7
ሳምንታዊ የመፅሐፍ ግብዣ! "ሁሉም በአንድ" ሁሉም በአንድ መፅሐፍ Clinical Psychologist በሆነችው በ እጩ  ዶ/ር መዓዛ መንክር ለልዩ ፍላጎት ወላጆች፣ መምህራን እና ባለሞያዎች ታስቦ የተዘጋጀ በኦቲዝም ሕብር የአእምሮ እድገት መዛባት ጋር የሚኖሩ ልጆችን ለማገዝ፣ ለማስተማር እና ለማከም የሚረዳ ተግባር ተኮር መፅሐፍ ነው። መፅሐፉ በ 2013 ዓ.ም በኢክሊፕስ ማተሚያ ቤት ታትሞ ለንባብ የቀረበ ሲሆን በ 10 ምዕራፍ የተከፋፈለ 242 ገፆች ያሉት ድንቅ መፅሐፍ ነው። በእያንዳንዱ ገፅ እጅግ ጠቃሚ ተግባር ተኮር የሆኑ ትምሕርት አዘል ሐሳቦችን የያዘ ሁሉም ማሕበረሰብ ሊያነበው የሚገባ መፅሐፍ ነው። ምዕራፍ አንድ ኦቲዝም ሕብር የአእምሮ ዕድገት መዛባት ምን ማለት ነው? በኦቲዝም ጥላ ስር በሚኖሩ ልጆች ላይ ጎልተው የሚታዩ ምልክቶች ምንድናቸው? በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖሩ ልጆች የሚታይባቸው ተጨማሪ ችግሮች እነማን ናቸው? የሚሉ መልሶችን በዚህኛው ምዕራፍ የያዘ ሲሆነ በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖሩ ልጆች ያሏቸው ያልተለመዱ ችሎታቸው እና የወላጅ አጠር ያለ የሚያስተምር ታሪክ ይዟል። ምዕራፍ ሁለት በዚህ በምዕራፍ ሁለት ውስጥ መሠረታዊ ክሎቶች የምንላቸው ምንድን ናቸው የማስተማሪያ ዘዴዎችስ? የሚሉ አንኳር ሐሳብ የያዘ ሲሆን በተጨማሪም ስልጠናው እንዴት ይጀምር እና አጠር ያለ ታሪክ ይዟል። ምዕራፍ ሶስት ይህኛው ምዕራፍ የሚያተኩረው የተግባቦት፣ የቋንቋና የንግግር ክህሎቶችን ለማስተማር የሚገቡ መሠረታዊ ነገሮችን፣ የስፒች ቴራፒ መርሆችን፣ መዚቃን በመጠቀም እንዴት ማስተማር እንደሚቻል የሚያብራራ፣ የተለያያ የንግግር ክሎት እክል ላለባቸው ልጆች በየደረጃው ምን እናድርግ የሚል እና አስተማሪ ታሪክ የታከለበት ክፍል ነወ። ምዕራፍ አራት ምዕራፍ አራት የማሕበራዊ ክህሎት ስልጠናን የሚዳስስ ሲሆን በውስጡም በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖሩ ልጆች ላይ የሚታዩ የማኅበራዊ ግንኙነት ችግሮች ምንድ ናቸው? ማኅበራዊ ክህሎትን ለማዳበር የሚረዳ የትምህርት ዕቅድ እንዴት ይዘጋጃል? ማኅበራዊ ክህሎትን ክህሎትን ለማዳበር የትምህረት ቤቶች ሚና እና የአጋዥ መምህራን ድርሻ ምንድ ነው ከሚለው ጋር አጠር ያለ አስተማሪ ታሪክ ይዟል። ምዕራፍ አምስት ምዕራፍ አምስት የሚነግረን ራስን የመርዳት ክህሎት ስለጠና ይዞልናል። በተጨማሪም ስለ ራስን የመርዳት ክህሎት ምንነትና ውጤት እንዲሁም የተለያዩ ራስን የመርዳት ክህሎት ተግባራትን ይነግረናል። ምዕራፍ ስድስት በዚህኛው ክፍል ኦቲዝምና የቀለም ትምህርት፣ ሦስቱ የድጋፍ ደረጃዎች፣ በመጀመሪያ የመዋዕለ ሕፃናት ዓመታት መሠረታዊ ትምህርትን ለማስተዋወቅ ያሉብን ነገሮች እንዲሁም ወላጆች እና መምህራን ሊያደርጋቸው የሚገባ ነገሮችን ከወላጅ ልምድ ጋር በታሪክ ያስተምረናል። ምዕራፍ ሰባት ባህሪን መረዳትና አስቸጋሪ ባህሪያትን መቆጣጠር በሚል ስለ አስቸጋሪ ባህሪ ምንነት፣ በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖሩ ልጆች በብዛት የሚያሳዩዋቸው አስቸጋሪ ባህሪያት እንዲሁም ከባህሪጋ በተገናኘ እጅግ አስተማሪ የሆኑ ርዕሶችን የያዘ ሲሆን አጠር ካለ አስተማሪ ታሪክ ጋር ቀርቦላችኋል። ምዕራፍ ስምንት ምዕራፍ ስምንት አካቶ /Inclusion/ ምንድ ነው? አካቶ የሚያስፈልጋቸውስ እነማን ናቸው? ልዩ ድጋፍ የሚፈልጉ ልጆች በትምህርት ቤት እንዴት ሊካተቱ ይችላሉ እና ከአካቶ ጋር በተገናኘ የተለያዩ ርዕሶችን አጠር ካለ ታሪክ ጋር ያስተምራችኋል። ምዕራፍ ዘጠኝ ለኦቲዝም የሚሰጡ የህክምና አይነቶች፣ ኦቲዝም እና ተያያዥ እክል ላለባቸው ልጆች የሚሰጡ ሕክምናዎች መቼ ይጀምር? እንዲሁም ሕክምናን ለመምረጥ መጠየቅ ያሉብን ነገሮች ምንድ ናቸው? የሚሉትን በተመሳሳይ አጠር ያለ ታሪክ አካቷል። ምዕራፍ ዐሥር ይህኛው የመፅሐፋ መጨረሻ ክፍል ሲሆን በኦቲዝም ጥላ ስር ለሚኖሩ ልጆች የትምህርት መርጃ መሣሪያዎች አዘገጃጀትና ከ ሃምሳ በላይ ውጤታማ የሚያደርጉ የትምህርት የመርጃ መሣሪያ ዓይነቶች አጀብ ይለናል። በመጨረሻም ዋቢ መፅሐፍትን ዘርዝሮ ይዞልናል። "የኦቲዝም መንስኤ ላይ ከማተኮር ይልቅ መፍትሔው ላይ ማተኮር ተስፋን ያለመልማል" አንብቡት መልካም ንባብ! #የመፅሐፍ_ግብዣ 📞 +251952118642 @MelaSpecialNeedsService @MelaSpecialNeedsServiceAccount
374
8
No text...
336
9
ታሪክን የኃሊት ሔለን አዳምስ ኪለር ክፍል ሁለት ( 2 ) ...በኋላም ወደ ኒውዮርክ ከሳራ ፉለር በሆረስ ማን መስማት ለተሳናቸው ትምህርት ቤት ተዘዋወርኩ በካምብሪጅ ትምህርት ቤትም እንዲሁ ተምሬያለሁ። በ1900 ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ራድክሊፍ ኮሌጅ ትምህርቴን ተከታትያለሁ። በተቻለኝ አቅም ከሰዎች ጋር ለመግባባት በቆራጥነት ተምሬያለሁ የሰዎችን ንግግር ከንፈር እና ጉሮሮአቸውን በመዳበስ እግባባለሁ። በብሬል እና በምልክት ቋንቋ መግባባት ላይም ጎበዝ ሆኛለሁ። አሁን በራስመተማመኔ እየጨመረ ነው፤ መምህሬ ብቻም ሳትሆን ጓደኛዬ የሆነችው ባለውለታዬ አን ሱሊቫን በ1905 ጀን ማሲንን አገባች በጊዜ ሂደትም ጤናዋ አየተጎሳቆለ መጣ። በኋላም ማሲ ጋር ተግባባን ማሲ በፀሀፊነት የምታገለግለኝ ረዳቴ ነች። ሱሊቫን እና ማሲ ጋር በመሆን ወደ ፎረስ ሂልስ አቀናን። ወደ 30 ዕድሜ ገደማ ይሆነኛል የፍቅር ግኑኝነት ጀምሬያለሁ ነገር ግን በድብቅ መታጨቴን ሰማሁ የፍቅር ጓደኛዬ ጋር ተመካከርን እና የመጣውን የትዳር እጩነት እንደማልፈልገው እና እንደማልቀበለው አሳወቅሁ። ጓደኛዬ እና አስተማሪዬ እ.ኤ.አ 1936 ከዚህ አለም ድካም አረፈች። ከሕይወት ብዙ ተምሬያለሁ በመደበኛውም ትምህርት ብዙ ገፍቻለሁ። አለም ላይ ታዋቂ ተናጋሪ ፣ ለአካል ጉዳተኛ ዜጎች የመብት ጠበቃ ፣ አነቃቂ ንግግሮች በማድረግ እና የተለያዩ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እያደረግሁ ወደ 20 ሀገራት ተዘዋወሬያለሁ። 1920 የአሜሪካን ሲቪል ነፃነቶች ህብረት መስራች ነኝ። ወደ ጃፓን እየተመላለስኩ ባደረኳቸው እንቅስቃሴዎች በጃፓን ህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፌያለሁ። የተራመድኩባቸው መንገዶች ስኬታማ አርገውኛል። ከብዙ ታዋቂ ሰዎች እና ከአሜሪካ ፕረዚዳንቶች የቀረበ ግንኙነት እና ጓደኝነት አለኝ። በብዙ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ተሳትፌያለሁ በአሜሪካን ፖለቲካ ወስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰው ነበርኩ። 1909 የሶሻሊስት ፓርቲ አባል በመሆን በንቃት ተሳትፌያለሁ ከ 1909 እስከ 1921 ድረስ በንቃት ዘመቻ እና የሰራተኛውን ክፍል በመደገፍ ፅፌያለሁ። ብዙዎቹ ንግግሮቼ እና ጽሁፎቼ ስለሴቶች የመምረጥ መብት እና የጦርነት የሚያመጣው ቀውስ እና ውጤቶች ነበሩ። በነገራችን ላይ የመላ ቤተሰቦች እኔ ለዚህ ሁሉ ስኬት የበቃሁት በብዙ ሰዎች ድጋፍ ብዙ ባለሞያዎች ሞያቸው እና እውቀታቸውን ተጠቅመው ለዚህ ስኬት አብቅተውኛል እናንተም የትኛውም የሚያስጨንቃችሁ እና ከልዩ ፍላጎት ጋር ተያይዞ ግራ የሆነባችሁ ነገሮች የመላ ልዩ-ፍላጎት አገልገሎት ተቋም ብቁ በሆኑ ባለሞያዎች እንናንተን በማገልገል ላይ ናቸው ። ከናንተ የሚጠበቀው በሚከተሉት የግንኙነት መስመሮች ሀሎ ማለት ብቻ ነው። እኔ ሰኔ 1ቀን 1968 ኢስቶን ከነቲካት ዩኤስ  በ87 አመቴ የዚህ አለም ድካም በቃሽ ተብዬ አርፌያለሁ ቸር ሰንብቱ መልካም ዘመን እመኝላችኋለሁ። #ታሪክን_የኋሊት 📞 +251952118642 @MelaSpecialNeedsService @MelaSpecialNeedsServiceGroup @MelaSpecialNeedsServiceaccount
335
10
No text...
304
11
ታሪክን የኃሊት “ የትኛውም ሰንኮፍ የማይበግራት     የ20ኛው ክፍለ ዘመን ፈርጥ! ” ክፍል አንድ ( 1 ) አሜሪካዊት ደራሲ፣ የአካል ጉዳተኞች መብት ተሟጋች ፣ የፓለቲካ ተሟጋች እና መምህርት ነኝ። እንዲኹም የህይወት ታሪኬን ጨምሮ ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ላይ በርካታ መፅሐፍት ፅፌያለሁ። ሰላም! የመላ ልዩ-ፍላጎት አገልግሎት ቤተሰቦች እና ተከታዮች ዛሬ በአጭሩ ታሪኬን እና የሕይወት ልምዴን እንዲሁም ያሳለፍኳቸው ውጣወረዶች የማጋራችሁ ሔለን አዳምስ ኬለር ነኝ። የተወለድኩት ሰኔ 27 በ1880 ዓ.ም በቱስኩምቢያ አላባማ ነው። ቤተሰቤ ሰፊ ነው ብዙ እህት እና ወንድም አለኝ። አባቴ ጎበዝ ሰራተኛ ነው፤  በኮንፌዴሬሽን ጦር ወስጥ ካፒቴን መሆንን ጨምሮ ትልልቅ ተቋማት አገልግሏል ። እናቴ የጄነራል ቻርለስ ደብሊው ልጅ ነች። በዘር ሀረጋችን ስዊዘርላንዳዊ ነን። ቅድመ አያቴ በስዊስ ዙሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መስማት ለተሳናቸው በመምህርነት አገልግሏል። በቤተሰቤ ታሪክ የባርነት ቀንበርም አልፏል፤ ብዙ ጊዜ አንድ አባባል አለኝ " ከቅድመ አያቶቹ መካከል ባሪያ ያልነበረው ንጉስ እና በርሱ መካከል ንጉስ ያልነበረው ባሪያ የለም" እላለሁ ። መገፋት፣ መናቅ እና እንደሰው አለመቆጠር ከባድ ደስ የማይል ስሜት ነው። እናም ወዳጆቼ ገና በለጋ ዕድሜዬ በበሽታ ብዙ ተሰቃየሁ ዶክተሮች አጣዳፊ የሆድ ህመም እና የአዕምሮ መጨናነቅ ባሉት በሽታ ብዙ ተሰቃይቻለሁ። በዘመኑ ይህንን ባክቴሪያ ኒሴሪያሜኒንጊቲዲስ ይባል ነበር ወይም በሄምፊለስ ኢንፍሉዌንዛ የሚከሰት የማጅራት ገትር በሽታ ሊሆን እንደሚችልም ዶክተሮች አረዱኝ። የሚገርማችሁ በዘመኑ 97% የወጣቱ ክፍል በዚህ በሽታ ህይወቱን ያጣ ነበር። ህመሙ እጅግ በጣም ጠናብኝ በሂደት ለመስማት-መሳን እና ለአይነ -ስውርነት ዳረገኝ። በጊዜው ብዙ ችግሮች አሳልፌያለሁ። መቼም አይነ-ስውርነት እናም መስማት አለመቻል ያለው ከባድ ስሜት እና ወጣውረድ ትረዱታላችሁ። ለቤተሰቡ ምግብ አብሳይ ከነበረችው ማርታ ዋሽንግተን ጋር በብዙ ተቀራርበናል በእድሜ ታላቄ ነች፤ የሴትነት ጉዳይ ላይ ብዙ ረድታኛለች ብዙ ምልክቶችም አውቄአለሁ። እኔ ነገሮችን የምረዳው በመዳሰስ እና ምልክቶች በእጄ መዳበስ ሲያመላክቱኝ ወይም ሲፅፉለኝ ነው ። በሰባት ዓመቴ ከቤተሰቦቼ ጋር መግባባት የምንችልባቸውን ከ60 በላይ የቤት ምልክቶች  አውቄአለሁ። አባቴም ብዙ ሰዎችን ፣ የህክምና ባለሞያዎች እና የተለያዩ ተቋማት በማማከር በተሰጠው ጥቆማ ደቡብ ቦስተን ውስጥ የሚገኝ የፐርኪንስ የአይነ ስውራን ትምህርት ቤት በመሄድ የቀድሞ ተማሪ የነበረችው ሱሊቫን ለኔ አስተማሪነት ተጠየቀች ሱሊቫን መጋቢት 5ቀን 1887 ስራዋን ጀመረች። ቤት መጥታም ከኔ ጋር መቀራረብ ጀመረች፤ የአሻንጉሊት ስጦታዎችም አመጣችልኝ። እነዚህን አሻንጉሊቶች በመጠቀምም ቃላቶች ለማስተማር ብዙ ትሞክራለች መረዳት ግን አልቻልኩም ከትምህርት ጋር ምንም ትውውቅ የለኝም ብዙም ቃላት አላውቅም ከእንዲኽ አይነት ትምህርት ጋር ለመቀጠል ብዙ ታገልኩ አንዳንድ ቃላት ስታስተምረኝ እበሳጭ ነበር፤ እቃዎችም አንስቼ እወረውር ፥ እሰብር ነበር። ስሜቴን እና ፍላጎቴን የምገልፅበት መንገድ የለኝም። በብዙ ጥረት ራሴን እያረጋጋሁ እንዴት መማር እንዳለብኝ እየተረዳሁ መጣሁ።  በሂደትም መምህሬ ከእጄ መዳፍ ላይ በጣቶቿ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እያደረገች ነገሮችን ታስተምረኝ ጀመር። አንድ ቀን በአንደኛው እጄ በጣቶቿ የሆነ እንቅስቃሴ እያደረገች በሌላኛው እጄ ደግሞ ቀዝቃዛ ውሀ እያፈሰሰች ውሀ መሆኑን አስተማረችኝ በዚህ መንገድ ሌሎችም ቃላቶች እየተማርኩ እየነቃሁ መጣሁ። በግንቦት ወር 1888 ዓ/ም በፐርኪንስ የአይነስውራን ተቋም መደበኛ ትምህርቴን መከታተል ጀመርኩ። ክፍል ሁለት ( 2 ) ይቀጥላል #ታሪክን_የኋሊት 📞 +251952118642 @MelaSpecialNeedsService @MelaSpecialNeedsServiceGroup @MelaSpecialNeedsServiceaccount
411
12
No text...
307
13
ልዩ-ፍላጎት ያላቸውን ልጆች፣ ተማሪዎችና ዜጎች የሚያሰለጥኑ ፣ የሚያስተምሩ ብቁ ባለሙያዎችን አሠልጥነን ከት/ቤቶች ፣ ከወላጆችና ድርጅቶች ጋር የማገናኘት ፣ የማስቀጠር ፣ የመከታተል ፣ የመገምገም
ልዩ-ፍላጎት ያላቸውን ልጆች፣ ተማሪዎችና ዜጎች የሚያሰለጥኑ ፣ የሚያስተምሩ ብቁ ባለሙያዎችን አሠልጥነን ከት/ቤቶች ፣ ከወላጆችና ድርጅቶች ጋር የማገናኘት ፣ የማስቀጠር ፣ የመከታተል ፣ የመገምገም ፣ ድጋፍና አገልግሎት እንሠጣለን በዚኽም፦ 🟢 ለልዩ-ፍላጎትና አካቶ-ትምህርት መምህራንና ባለሙያዎች 🟢 ለቴራፒ ባለሙያዎች 🟢 ለሥነ-ልቦና ባለሙያዎች 🟢 ለልጆች ዕድገት ባለሙያዎች 🟢 ለሞግዚቶች/ተንከባካቢዎች 🟢 ለተያያዥ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ሌሎች የሥራ ማስታወቂያዎችን ፣ የሥራ ዕድሎችን ፣ ፆታ ሳንለይ ሙያዊ ሕግና አሠራርን በተከተለ መልኩ እናቀርብሎታለን! ለበለጠ መረጃ፦ ገፆቻችንን ይጎብኙ ፣ ይደውሉልን #ማስታወቂያ 📞 0952118642 @MelaSpecialNeedsService @MelaSpecialNeedsServiceGroup @MelaSpecialNeedsServiceAccount
423
14
ታሪክን የኋሊት       ሉዊስ ብሬል ( Louis Braille )    ሉዊስ ብሬል በፈረንሳይ ሀገር በኩፕቭራይ መንደር ጥር 11 ቀን 1801 ዓ/ም ተወለደ። ወላጆቹ ድሀና በኮርቻ ስራ የሚተዳደሩ ነበሩ። ሉዊስ በ 3 ዐመቱ አባቱንና ወንድሙን ተከትሎ ወደ ስራ ቦታ ይሄድ ጀመር። እዚያም እየሄደ መጫወት ለመደ። አንድ ቀን አባቱ ሰው ለማናገር ወጣ። ሉዊስም እንደልማዱ ቁራጭ ጠፍር አንስቶ በወሳፍቻ ለመስፋት ሞከረ። ክንዶቹ ስላልጠነከሩ ጠፍሩ አልተበሳለትም። ስለዚህ እንደገና ባለው አቅሙ ለመብሳት ታገለ። ሆኖም ወሳፍቻውን ስቶ አይኑ ውስጥ ተሰካ። በዚህም ጊዜ ምርር ብሎ አለቀሰ። አባቱም ለቅሶውን ሰምተው ወደ ልጃቸው ሮጡ። እንደደረሱም በልጃቸው አይን ውስጥ ወሳፍቻ ተሰክቶ አዩ። በነገሩም በጣም ተደናገጡ። ህጻኑንም አቅፈው ወደ ቤት ወሰዱት። ሉዊስ አይኑን በጸና ታመመ። ወላጆቹም የልጃቸው አይን እንዲድን ብዙ ጣሩ። የሉዊስ ዐይን ግን ሊድን አልቻለም። እንዲህ ባለ አጋጣሚ ሉዊስ አይነ-ስውር ሆነ። 7 ዓመት እስከሚሞላው ቤት ቆየ። ከዚያም በአቅራቢያው ወዳለው ትምህርት ቤት ተላከ። ትምህርት ቤቱ ሉዊስ አይነ-ስውር በመሆኑ ሊቀበለው አልፈለገም ነበር። ቢሆንም አስተዳዳሪውም የሉዊስን ንቃት እና ቅልጥፍና አይቶ ለሙከራ ተቀበለው። ሉዊስ ማንኛውንም ትምህርት የሚከታተለው በቃሉ ነበር። ከፍተኛ የማስታወስ ችሎታ ነበረው። በችሎታውም ከትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በልጦ ታየ። ስለዚህ አስተማሪዎቹ ይወዱትና ያደንቁት ነበር። በዚህም ከአስተማሪዎቹ አንዱ ሉዊስን በዳሰሳ ፊደል ሊያስተምረው ፈለገ። እርሱም በተለያዩ ዘዴዎች ፊደሎችን ቀርጾ አሳየው። ሉዊስም ፊደሎቹን ለማወቅ ጊዜ አልፈጀበትም። ምንም እንኳ ሉዊስ ፊደሎቹን ቢያውቅም የሚያነባቸው መጽሐፍት አላገኘም። ስለዚህ በጣም ያዝን ነበር። ሉዊስ ብሬል እና ሥራው ሉዊስ ብሬል በአቅራቢያው ባለው መደበኛ ትምህርት ቤት 3 ዓመት ቆየ። በ10 ዓመቱም በወላጆቹ አማካይነት ፓሪስ ወደሚገኘው ተቋም ተላከ። ይህም ተቋም ወጣት አይነ-ስውራን ማሠልጠኛ እንዲሆን የተከፈተ ነበር። ሉዊስ ወደ ተቋሙ በገባ በ2ኛው አንድ ብሩህ ተስፋ  ታየ። ይሄውም ' ቻርለስ ባርቤር ' የሚባል የጦር መኮንን ነበር። መኮነኑም በጦርነት ጊዜ በሌሊት ከወታደሮቹ ጋር ይገናኝ ነበር። ግንኙነቱንም ያደርግ የነበረው በዳሰሳ ጽሁፍ ነው። ጽሁፉንም ለማሳየት አንድ ቀን ባርበር ወደ ተቋሙ መጣ። ባርቤርም ጽሁፉንም ለመምህራኑና ለተማሪዎቹ አሳየ። እነርሱም ዐይተው ጥናትና ምርምር ማድረግ ፈለጉ። በተለይም ተማሪዎቹ ለትናንቱ ከፍተኛ ትኩረት ሰጡት። ከእነርሱም አንዱ ሉዊስ ብሬል ነበር። የባርበርም ጽሁፍ 12 ነጥቦችና ሰረዝ ነበረው። ይህንንም ሉዊስም በሚገባ አጠናው። ነገር ግን ለንባብ ምቹ ሆኖ አላገኘውም። ስለዚህ ሉዊስ 4 ነጥቦችን ብቻ በመጠቀም ጥናቱን ጀመረ። በእነዚህም በመጠቀም 15 አማራጭ ምልክቶች አገኘ። ሆኖም በምልክቶቹ ሃያ አምስቱን የፈረንሳይኛ ፊደሎች እንኳን መቅረጽ አልቻለም። ቢሆንም ሉዊስ በዚህ ተስፋ አልቆረጠም። ይህንኑ መሰረት በማድረግ ሉዊስ ጥናቱን ቀጠለ። በአራቱም ነጥቦች ላይ አምስተኛ ነጥብ ጨመረ። ይህም የአማራጩን ቁጥር ወደ 30 አንድ ከፍ አደረገው። በነዚህም ምክኒያቶች ሉዊ 25ን የፈረንሳይኛ ፊደሎችና ስርዓተ-ነጥቦችን ሊቀርጽፅ ሞከረ። በዚህም ዘዴ አንድ የጂኦግራፊ መጽሐፍ በ1821 ዓ/ም ለሙከራ ተገለበጠ። ይሁን እንጂ ይህም ጥናቱ ሉዊስን አላረካውም። ከ1836 እስከ 1844 ዓ/ም ምርምሩን ቀጠለ። በዚህን ጊዜ የነጥቦቹን ቁጥር ከአምስት ወደ ስድስት ከፍ አደረገው። በእነዚኽም ነጥቦች 63 አማራጭ ምልክቶችን አገኘ። በምልክቶቹም ሉዊስ እንደገና ፊደሎችን፣ ስርዓተ-ነጥቦችን፣ የሒሳብ ምልክቶችንና የሙዚቃ ኖታዎችን አወጣ። ይኽ የሉዊስ ፈጠራ ለመጀመሪያ ጊዜ አይነሥውራንን ማንበብና መጻፍ አስቻለ። #ታሪክን_የኋሊት 📞 +251952118642 @MelaSpecialNeedsService @MelaSpecialNeedsServiceGroup @MelaSpecialNeedsServiceaccount
387
15
No text...
329
16
ባለልዩ-ክህሎቶቹ በዛሬው ሳምንታዊ መርኃ-ግብራችን 3 በ ' America's Got Talent ' የቀረቡ የመስማት መሳን/እክል እና የንግግር እክል ያላባቸው ዓለምን ያስደነቁ ባለልዩ-ክህሎቶችን እንመ
ባለልዩ-ክህሎቶቹ በዛሬው ሳምንታዊ መርኃ-ግብራችን 3 በ ' America's Got Talent ' የቀረቡ የመስማት መሳን/እክል እና የንግግር እክል ያላባቸው ዓለምን ያስደነቁ ባለልዩ-ክህሎቶችን እንመለከታለን። Amanda Mammana ከ10 ዓመቷ ጀምሮ በ 'Speech Impediment' እክል ያደገችው ኤማንዳ ከልጆች ጋር መጫወት እንደሚያሸማቅቃትና ከዚኽ ለመደበቅና ለማምለጥም በጊታርዋ ሙዚቃ ትጫወት እንደነበር ትገልፃለች፤ በ17ኛ ዙር የ ' America's Got Talent ' ውድድር ላይ የ19 ዓመቷ የላይብሪቲ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ኤማንዳ በመድረኩ ምርጥ ብቃትዋን አሳየች፤ በመቀጠልም የራሷን መዚቃዎች ለዓለም አበርክታለች። Mandy Harvey እ.አ.አ በ1988 ዓ/ም በሀገረ አሜሪካ ተወልዳ ያደገችው ሔርቪ ከልጅነቷ ጀምሮ በከፍተኛ የጆሮ ሕመም ምክንያት በ18 ዓመቷ መስማት የተሳናት ሆናለች፤ ወትሮውንም ቢሆን ለሙዚቃ ልዩ ፍቅር የነበራት ቢሆንም መስማት የተሳናት መሆኗ መዚቃ ከመሥራት ግን አላገዳትም። በጃዝ ሙዚቃ በርካታ ሥራዎችን ለመሥራትም በቅታለች። በ12ኛ ዙር የ ' America's Got Talent ' ውድድር 4ኛ ስትወጣ የ ' Golden Buzzer ' አሸናፊም ነበረች። Hayden Kristal ለእንስሳት ልዩ ፍቅር አላት። ለረጅም ዓመት የዱር እንስሳት ጥበቃም ሠርታለች። ሆኖም ቤተሰቦቿና የቅርብ ዘመዶቿ የቀልድና የስላቅ ችሎታዋን ከ ' Kathy Buckley ' እያነፃፀሩ ያደንቋታል፤ ክሪሰታል የ ' Hard of Hearing ' እክል ያላት ዝነኛ ኮሚድያን ሆናለች፤ እ.አ.አ በ2022 ዓ/ም በ ' America's Got Talent ' ቀርባ የኮሜዲ ሥራዋን አቅርባለች። #ባለልዩክህሎቶቹ 📞 +251952118642 @MelaSpecialNeedsService
390
17
ለመላው የመላ የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት ቤተሰቦች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላም፣ የደስታ እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። መልካም የልደት በዓል! #ማስታወቂያ 📞 +2519
ለመላው የመላ የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት ቤተሰቦች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላም፣ የደስታ እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። መልካም የልደት በዓል! #ማስታወቂያ 📞 +251952118642 @MelaSpecialNeedsService @MelaSpecialNeedsServiceGroup @MelaSpecialNeedsServiceaccount
928
18
ሳምንታዊ የፊልም ግብዣ " ልዕልት" ወደኃላ መለስ ብለን በናሆም ሪከርድስ አማካኝነት የቀረበው በ2003 ዓ.ም በኢትዮ ፊልም የተዘጋጀው የ1:18 ደቂቃ ርዝማኔ ያለዉ ግሩም ኤርሚያስ በድርሰትና በተወ
ሳምንታዊ የፊልም ግብዣ                   " ልዕልት"       ወደኃላ መለስ ብለን በናሆም ሪከርድስ አማካኝነት የቀረበው በ2003 ዓ.ም በኢትዮ ፊልም የተዘጋጀው የ1:18 ደቂቃ ርዝማኔ ያለዉ ግሩም ኤርሚያስ በድርሰትና በተወናይነት የተሳተፈበትን ፊልም እንቃኛለን፡፡    በፊልሙ ላይ ብዙ ታዋቂ ተዋንያኖችን የምንመለከተ ሲሆን መነሻ ያደረገዉም አንዲት መስማት የተሳናት እናት  ከልጇ ጋር በመሆን  ቤት ለቤት እየሄደች ልብስ የምታጥብ ሚስኪን  ደሀ ስትሆን አንድ ቀን የተለመደ ሥራዋን  በሀብታም ቤት ስትከዉን፤ የቤቱ ባለቤት ልጅ ተንኮል  ይሸርባል፡፡      ነገሩ እንዲኽ ነው ይህ ሰው ይቺህን እናት አለመስሟቷን ተገን በማድረግ በጨዋታ ላይ የነበችን ልጅን አፍኖ ወደ ክፍሉ በመወሰድ በዚች ጨቅላ  ልጅ ላይ አስገድዶ መድፈር ወንጀል ይፈፅምባታል፡፡ እናትም በአጋጣሚ ወደ ቤቱ ስትገባ የልጇን መደፈር በመመልከት በደፋሪዉ ላይ በብስጭት፣ በፍርሃት፣ በንዴት ስሜት በመገፋፋት የመግደል ሙከራ ተፈፅምበታለች፡፡ህፃኗ ከባድ  የአካል ጉዳት እና የስነ ልቦና ጉዳት ሲደርስባት ያስመለክተናል፡፡   ፖሊስም ይህንን መዝገብ በመያዝ ወደ ፍርድ ቤት ይዞ ይሄዳል፤ ፍርድ ቤቱም ይህንን በመመልከት በእናት ላይ የ10 ዐመት ፍርድ ይፈረድባትና ወደ እስር ቤት እንድትገባ ይደረጋል፡፡     ነገር ግን ይቺህ መስማት የተሳናት  እናት በዚህ ተስፋ አልቆረጠችም በምልክት ቋንቋ በመነጋገር ይግባኝ ጠይቃ በድጋሚ በተከፈት ፍርድ በጎደኛዋ ጥረት በመታገዝ መስማት የተሳናት ሆና በምልክት ቋንቋ ከጠበቃዋ ጋር በመነጋገር ተፈርዶባት የነበረዉ የ10 ዐመት ቅጣት ወደ 2 ዐመት እንዲቀነስ ታስደርጋለች፡፡ ፊልሙን ትመለከቱት ዘንድ ጋበዝን! #የፊልም_ግብዣ 📞 +251952118642 @MelaSpecialNeedsService
1 156
19
መላ የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት Mela Special Needs Service እንኳን ደስ አለዎ! በልዩ-ፍላጎት ላይ የሚሠራ አገልግሎት እነሆ! አገልግሎታችን ልዩ-ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች የቴራፒ እና ት
መላ የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት Mela Special Needs Service እንኳን ደስ አለዎ! በልዩ-ፍላጎት ላይ የሚሠራ አገልግሎት እነሆ!        አገልግሎታችን   ልዩ-ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች የቴራፒ እና ትምህርታዊ ድጋፍ መስጠት ፦ 🟡 ቤት-ለቤት 🟡 በትምህርት ቤት እና 🟡 በተለያዩ ቦታዎች 🟢 የሥራ ማስታወቂያዎች 🟢 ባለሞያዎችን ማገናኘት 🟢 አሰሪና ሰራተኛን ማገናኘት 🟢 የባለሞያ ክትትልና ድጋፍ ሥልጠናዎች፦ 🟡 የምልክት ቋንቋ ሥልጠና 🟡 የብሬል ፅሕፈትና ንባብ ሥልጠና 🟡 ትምህርታዊና ሳይንሳዊ ሥልጠና 🟡 የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና 🟡 የ Mobility - Orientation ሥልጠና አስተማሪና አዝናኝ ኪነጥበባዊ ሥራዎች፦ 🟢 ልዩ-ልዩ ዝግጅቶች 🟢 ቃለ-መጠይቆች 🟢 አጫጭር ድራማዎች 🟢 አስተማሪ ፅሑፎች #ማስታወቂያ 📞0952118642 @MelaSpecialNeedsService
387
20
ይህን ያውቁ ኖሯል? ከ ' Specfic Learning Disability ' ውስጥ አንዱ ስለሆነው ስለ ' ' Dyslexia ' ከንባብ እና ከቃላት ጋር የተያያዘ ውስን የመማር ችግር ሲሆን ቋንቋን መሰ+1
ይህን ያውቁ ኖሯል? ከ ' Specfic Learning Disability ' ውስጥ አንዱ ስለሆነው ስለ ' ' Dyslexia ' ከንባብ እና ከቃላት ጋር የተያያዘ ውስን የመማር ችግር ሲሆን ቋንቋን መሰረት ያደረጉ ክህሎቶችን የሚያስተጓጉል እክል ነው። ' Dyslexia 'ያለባቸው ሰዎች ከሚያሳዩቸው ምልክቶች ውስጥ አንዱ የማንበብ ሲሆን ያለ ስህተት ማንበብ መቸገር ፣ በፍጥነት ለማንበብ መቸገር እና አንብቦ መረዳት መቸገር በአብዛኛው ይታይባቸዋል። ሌላኛው ቃላትን በትክክለኛው የፊደላት ቅደም-ተከተል ለመፃፍ መቸገር ይታይባቸዋል። Dyslexia ያለባቸው ሰዎች ጮክ ብለው ሲያነቡ ያልተፃፈ ነገር በግምት ማንበብ እና እድሜያቸው ከፍ ካለ በኃላ ያለ ስህተት በፍጥነት ማንበብ ይቸገራሉ ። ለ ' Dyslexia ' መንስዔዎች ከሚባሉት ውስጥ አንዱ የአንጎል ይዘት እና ተግባር ከሌሎች ይኽ እክል ከሌለባቸው ሰዎች መለየት ነው። ሌላው በእርግዝና ወቅት የሚወሰዱ መድኃኒቶች ፣ የአልኮል መጠጦች መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ። ' Dyslexia ' በዘርም ሊተላለፍ የሚችል እክል ነው። ' Dyslexia ' ላለባቸው ሰዎች ማድረግ ያሉብን ድጋፎች - በተደጋጋሚ እንዲያነቡ ማበረታታት እና መከታተል - በራስ መተማመናቸው እንዲገነቡ ማበረታታት - እነዚህ ሰዎች በብዛት በስፖርት፣በድራማ፣በስዕል፣ሙዚቃ ላይ ተሰጥኦ ስላላቸው ስጦታዎቻቸውን እንዲጠቀሙ መንገዶችን ማሳየት። የዚህ እክል ተጠቂ ከሆኑ የዓለማችን ታዋቂ ሰዎች መካከል * Albert Einstein * Pablo picasso * Tom cruise *  leonardo da vinci ጥቂቶቹ  ናቸው። በመጨረሻም ' Dyslexia ' ያለባቸውን ሰዎች እንረዳቸው እንደግፋቸው #ይህን_ያውቁ_ኖሯል 📞 +251952118642 @MelaSpecialNeedsService
401