cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Assosa Immigration (ICS Ethiopia)

This is the official channel of the FDRE Immigration and Citizenship Services

Show more
Ethiopia12 645The language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
253
Subscribers
No data24 hours
+57 days
+1930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ ሚስጢራዊ የህትመት ስራ የኢ-ፖስፖርት፣ የክፍያ ካርዶች እና መታወቂያዎች ማምረቻ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡ የኢ-ፖስፖርት፣ የክፍያ ካርዶች እና መታወቂያዎች ማምረቻ ፋብሪካውን ግንባታ ለማስጀመር ከኢትዬጵያ ኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት በተገኘ ቦታ በለሚ ኢንዱስትሪ ፖርክ መሠረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ኢ-ፓስፖርት በሀገር ዉስጥ መመረቱ ከሚያስገኘዉ ጥቅም ባሻገር አዲስ እዉቀትና ቴክኖሎጅ ወደ ሀገር የሚያስገባ እንደመሆኑ መንግስት አስቀደሞ ያለዉን ችግር በመገንዘብ በተለይ ከጊዜዉ ቴክኖሎጅ ጋር አብሮ መሄድ እንዲቻል የተሰራዉ ሥራ የሚያስመሰግን መሆኑን በመግለጽ በአዲሱ የኢ-ፓስፖርት የሀገራችን የቱሪዝም መስህቦችንና መዳረሻዎችን እንዲሁም ታሪካዊ ስፍራዎችን ጨምሮ የበለፀጉ የደህንነት መገለጫዎችን የያዙ አዳዲስ ዲዛይኖችን እንዲካተቱ የተደረገ ሲሆን  ይህ ፕሮጅክት በአገራችን ዉስጥ ለረዥም ጊዜ የቆየዉን የፓስፖርት እጥረት ለመፍታት ፣የደንበኞችን እርካታ ለማሻሻልና በፍተሻ ጣቢያዎች ይጠፋ የነበረዉን ጊዜ ለመቀነስ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ሀገራችን ወደ ኢ-ፓስፖርት መግባቷ ቀደም ሲል ባለፉት ዓመታት ስንጠቀምበት የነበረዉን ፓስፖርት ደረጃውን ከፍ ያደረገ ብቻ ሳይሆን የዲዛይን ባለቤትነትም ወደ ሀገር የተመለሰበት እንዲሁም የዳታና የፕሮሰሲንግ ስራ በራስ አቅም እንዲሰራ መንገድ የተከፈተላትም ሲሆን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የሚሰጣቸዉ ጊዚያዊ እና ቋሚ የመኖሪያ መታወቂያ፣ የትዉልደ ኢትዬጵያዊ መታወቂያ እንዲሁም ሌሎች መታወቂያዎች ከወረቀት ወደ ዲጅታል እንዲያድጉ ከመደረጉም በላይ የቪዛ አዉቶሜሽንም አብሮ እንዲሰራ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በበኩላቸው ይህ ለፍሬ እንዲበቃ የዲዛይን ስራዎችን፣ የህግ ስራዎችን እና አጠቃላይ ስራዉን ከመጀመር አንስቶ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ የተሳተፉትን ክቡር የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ተቋምን፣ የJoint venture CEO የሆኑት ወ/ሮ ቃልኪዳንን እንዲሁም የቶፓን ግራቪቲ የስራ ኃላፊዎችና ባልደረቦችን አመስግነው በቀሩት ወራት በጋራ በመስራት አዲሱን የኢ-ፓስፖርትም ሆነ ፋብሪካዉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የበኩሉን ድጋፍና የሚጠበቅበትን ሁሉ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ __          🤝🤝🤝🤝 ✅Addis Ababa ICS☑️ 📌 @IcsAddisAbaba ✅Head Office ICS☑️ 📌 @IcsEthiopiaOfficial
Show all...
🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
📝🅰️🅰️🅰️🅰️🅰️🅰️🌀 ባለፉት ጥቂት ወራት የደንበኞችን ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ የፓስፖርት ቡክሌት ወደሀገር በማስገባት በ6 ወራት ውስጥ ለአዲስ አበባ 260,371፣ በየአካባቢው ላሉ ቅ/ጽ/ቤቶች 269,358፣ በአስቸኳይ 35,394 እና በውጭ ለሚኖሩ ኢትዬጵያዊያን 81,416 በድምሩ 646,539 ፖስፖርት ታትሞ ማሰራጨት ተችሏል። አሁንም የፓስፖርት ጥያቄዎችን ያለምንም መዘግየት ለደንበኞች ለማድረስ ተግተን እየሰራን ነው።  Over the past few months, we’ve taken significant strides to increase our efficiency and customer satisfaction. In just six months, we were able to print and distribute 260,371 passports in Addis Ababa, 269,358 in various regional offices, 35,394 to urgent cases, and 81,416 to Ethiopians residing abroad. The total number of passports printed and distributed during this time is 646,539. We are working hard to continue delivering passport requests to our customers without any delay. __ ይፋዊ ገጾቻችንን እና ቻናሎቻችንን ብቻ ለታማኝ አገልግሎቶች እና ማስታወቂያዎች ይጠቀሙ። ⚡️Telegram channel https://t.me/IcsEthiopiaOfficial
Show all...
📮Assosa ICS https://t.me/IcsAssosa ⚙Head Office ICS @IcsEthiopiaOfficial
Show all...
አሶሳ፣ መጋቢት.pdf1.27 MB
Photo unavailableShow in Telegram
ሀዋሳ፣ ሆሳዕና፣ ሰመራ፣ አሶሳ፣ አዳማ፣ ደሴ፣ ድሬዳዋ፣ ጅማ እና ጅግጅጋ ቅርንጫፍ  ፓስፖርታችሁን የምትወስዱ ደንበኞቻችን ባመለከታችሁበት ኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚያወጣው ኘሮግራም መሰረት በመገኘት ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ወደ ተቋማችን ስትመጡ ኦንላይን ያመለከታችሁበትን ፕሪንት አውት ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን። Our customers who are collecting their passports in Hawassa, Hosaena, Semera, Asosa, Adama, Dessie, Dire Dawa, Jimma, and Jigjiga branches will be able to collect their passports according to the program issued by the immigration branch office where they applied. Do not forget to bring your online application when you come to collect your passport! ይፋዊ ገጾቻችንን እና ቻናሎቻችንን ብቻ ለታማኝ አገልግሎቶች እና ማስታወቂያዎች ይጠቀሙ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖               🤝🤝🤝🤝 ✈️Official Telegram Channel☑️ 📨Chat Community☑️ 🌍Digital Invea Worldwide☑️ ✔️Passport Checker Team☑️ 🌐Official Facebook page☑️
Show all...
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የአገልግሎቱን የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም አስመልክቶ መግለጫ ሰጡ። አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም የደንበኞችን ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ በ6 ወር ውስጥ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ የፓስፖርት ቡክሌት ወደሀገር በማስገባት በ6 ወራት ውስጥ ለአዲስ አበባ 260,371፣ በየአካባቢው ላሉ ቅ/ጽ/ቤቶች 269,358፣ በአስቸኳይ 35,394 እና በውጭ ለሚኖሩ ኢትዬጵያዊያን 81,416 በድምሩ 646,539 ፖስፖርት ታትሞ ማሰራጨት መቻሉን ገልፀው ይህ የሆነውም የህትመት አቅም በማሳደግ፣ ከውጭ የሚገቡትን በማመቻቸት እና ሠራተኞችን 24/7 በማሰራት የየቀን የማተም አቅም 2000 ከነበረበት ወደ 10,000 በላይ በማሳደግ ነው ብለዋል፡፡ አሁን ላይ ምንም አይነት የተጠራቀመ ፍላጐት የሌለ ስለሆነ ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በኋላ  ዜጎች በተሰጣቸው የቀን ቀጠሮ መሰረት ፓስፖርታቸውን መረከብ ይችላሉ ብለዋል። አሁን ያለዉን የፓስፖርት ቡክሌት ወደ ኢ-ፓስፖርት  በመቀየር በሀገር ውስጥ እንዲመረት ውል በመያዝ የዲዛይን ስራዎች መጠናቀቁንና የግዥ ትዕዛዝ አልቆ ወደስራ የተገባ በመሆኑ በ1 አመት ጊዜ ውስጥ ወደ ኢ-ፖስፖርት የሚገባበት ሁኔታ የተመቻቸ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በ6 ወር ውስጥ ከዋና ቢሮ፣ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ ከቦሌ፣ ከኬላዎች በድምሩ 205 የሚሆኑ ሠራተኞች ውጭ ካሉ ደላሎች ጋር በመተባበርና የአሰራር ክፍተትን በመጠቀም ከህብረተሰቡ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሰሩ የነበሩና መረጃ የተገኘባቸውን ለህግ አካላት የማቅረብና እንደየጥፋታቸው ከስራ እንዲታገዱና የህግ ውሳኔ እንዲሰጣቸው መደረጉን ገልፀዋል፡፡ የውጭ ዜጐች ቁጥጥር ጋር በተገናኘ በኢትዬጵያ ለቱሪስትም ሆነ ለቢዝነስ የሚገቡትን በስፋት ለማስተናገድ 180 ሀገራት ቪዛ ኦን አራይቫል ተከፍተው እየተሰራ መሆኑንና በዚህ 6 ወር ውስጥ በአየር ኬላ ወደሀገር የገቡ 973,552  ከሀገር የወጡ 1,169,316 በድምሩ   2,142,868 መንገደኛ እና በየብስ ኬላ ወደሀገር የገቡ 215,176 ከአገር የወጡ 167,001 በድምሩ 382,177  መንገደኛ አገልግሎት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ለአፍሪካ ህብረት መሪዎች ስብሰባ ከ8,100 በላይ፣ ለ2ኛ ትውልደ ኢትዬጵያዊያን ጥሪ ከ75,000 በላይ የገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከ5,ዐዐዐ በላይ ለሚሆኑ ትውልደ ኢትዬጵያዊ መታወቂያ የተሰጣቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከመደበኛ የውጭ ዜጐች አገልግሎት ጋር በተያያዘ  81,761 ለሚሆኑ የውጭ ዜጐች አገልግሎት መሰጠቱንም ተናግረዋል፡፡ ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም በሀገሪቱ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ የውጭ ዜጐችን አገልግሎቱ ጥሪ በማድረግ 10,467 የውጭ ዜጐች የተመዘገቡ መሆኑንና ወደህጋዊ መንገድ የማስገባት ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ ኢሚግሬሽን፣ የጉምሩክ ኮሚሽን እንዲሁም የአቪዬሽን ደህንነት የመሳሰሉ በርካታ ተቋማት በቅንጅት አገልግሎት የሚሰጡበት መሆኑንና ኢሚግሬሽን የሚሰራው ገቢና ወጭ መንገደኞች በአለምአቀፍ ስታንዳርድ መሰረት ሰነዶቻቸው ትክክል ስለመሆናቸው የማረጋገጥ ለገቢ መንገደኞች ቪዛ ፖስፖርት እና ሌሎች ለመግባት የሚያስችሉ ሰነዶችን የማረጋገጥ እና የመመዝገብ፣ ለሀገር ስጋት ያለመሆናቸውን የማረጋገጥ ከሆኑም ህጋዊ እርምጃ መውሰድን ጨምሮ ስራ የሚሰራና ወጭ መንገደኞች ላይ ወደሚሄዱበት ሀገር ለመግባት የሚያስችል ቪዛ፣ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው መሆኑንና ወደሚሄዱበት ሀገር ለመሄድ የሚያስችል ቦርዲንግ ፖስ መኖሩን የማረጋገጥ ስራ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዚህ 6 ወር ውስጥ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ Departure በ11 ካውንተር አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ሲሆን 15 ካውንተር  በመጨመር ወደ 26 ካውንተር፣ Arrivale በ21 ካውንተር አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ሲሆን 14 ካውንተር  በመጨመር ወደ 35 ካውንተር በማሳደግ የተሻለ አገልግሎት መስጠት መቻሉን ገልፀዋል፡፡   ቅርንጫፎችን የማጠናከር ስራ በተመለከተ ሁሉም ቅርንጫፍ ቢሮዎች በተሟላ መልኩ ወደስራ የማስገባት ስራ የመስራት እና የቦርደር ቁጥጥር የማጠናከር ስራዎች በስፋት እየተሰሩ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ህብረተሰቡ ተመሳስለው ከተሰሩ ዌብሳይቶች ራሱን እንዲጠብቅ እና በግለሰብ አካውንት ምንም አይነት ገንዘብ ገቢ እንዳያደርግ፣ ዜግነት ማጣራት ጋር በተያያዘ ሂደት ያለው ስለሆነ የሚጠየቁ ሰነዶችን በትዕግስት እንዲያቀርብና እንዲተባበር፣ ፖስፖርት ውሰዱ ተብለው የጽሁፍ መልዕክት ሲደርሳቸው በተባለው ቀን እና ሰዓት እንዲወስዱ፣ አስቸኳይ ፓስፖርት በኦንላይን የማይሰጥ ስለሆነ አስቸኳይ የሚያሰጥ ሰነድ ያላቸው ተገልጋዬች በዋናው ቢሮ ብቻ በአካል በመገኘት  መስተናገድ ያለባቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም በ6 ወር ሪፎርሙን ከመፈፀም አኳያ ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩትን ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት፣ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት፣ ፌደራል ፖሊስ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ፍትህ ሚኒስቴር፣ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የኢትዬጵያ አየር መንገድ እና ሌሎችንም ተቋማት አመስግነዋል፡፡
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
🤝🤝🤝🤝🔠©️🔤⏲⏲For all Daily https://t.me/IcsPassportChecker ⏰ማታማታ 🔢🔢🔣🔢🔢 የሁላችሁንም ጥያቄ የምንመልስ ይሆናል። ✅ 𝑰𝒎𝒎𝒊𝒈𝒓𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏 𝒂𝒏𝒅 𝑪𝒊𝒕𝒊𝒛𝒆𝒏𝒔𝒉𝒊𝒑 𝑺𝒆𝒓𝒗𝒊𝒄𝒆 𝑶𝒇𝒇𝒊𝒄𝒊𝒂𝒍𝒔️ ✅ Any question Related to Passport. ✅ Any information related to immigration. 📶✅ጥያቄ ያላችሁ we are ready to response✔️ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ✅if you want to online passport order. ➡️This Official website https://www.ethiopianpassportservices.gov.et                                           ⬇️⬇️ https://t.me/IcsPassportChecker
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
🚨For any information Join officials  channel ♻️ለየትኛውም የኢምግሬሽን ጥያቄ ቻናሉን ይቀላቀሉ። ✅እባኮ በደንብ በማንበበ ወደ  ቻናላችንን ጎራ ይበሉ ሙሉ መርጃ ያገኛሉ።              🔸 Our channel https://t.me/IcsEthiopiaOfficial
Show all...
👍 1
🔎Head Office ICS
♻️Website
🔎Passport Checker ICS
🔎Chat Community ICS
🔎Adama ICS
🔎Hawassa ICS
🔎Hossana ICS
🔎Jimma ICS
🔎Assosa ICS
🔎Gambella ICS
🔎Mekelle ICS
🔎Jigjiga ICS
🔎Samara ICS
🔎Dessie ICS
🔎BahirDar ICS
🔎Addis Ababa ICS
🔎Diredawa ICS
🔎Digital Invea Worldwide ICS
🔎Official Facebook page
Photo unavailableShow in Telegram
➡️🅰️🔤🅰️🔤🅰️⬅️ በዚህ ቀን የኢትዮጵያን ጀግንነት እና አንድነት እናከብራለን! የአድዋ ድልን ስንዘክር የኢትዮጵያ ህዝብን ፅናት እና ሀገር ወዳድነት አብረን እንዘክራለን። ለነፃነታችን እና ለሉዓላዊነታችን የታገሉትን ጀግኖች እያመሰገንን፣ መልካም የአድዋ ድል ቀን እንላለን! On this day, we honor the valor and unity of Ethiopia as we commemorate the Adwa Victory, a testament to our nation's enduring spirit and resilience. Let's remember the heroes who fought for our freedom and sovereignty. Happy Adwa Victory Day! ➖➖➖➖➖➖➖➖➖               🤝🤝🤝🤝 ✈️Official Telegram Channel☑️ 📨Chat Community☑️ 🌍Digital Invea Worldwide☑️ ✔️Passport Checker Team☑️ 🌐Official Facebook page☑️
Show all...
1