cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

🇵🇸🇵🇸ለኸይር ነገር ቁልፍ ሁን🇵🇸🇵🇸

የቁርአን እና ሀዲስ ትምህርቶች

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
198
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-1230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✍ ተው ስማኝ…… ልምከርህ አቦ መንሓጅህ…… አይሁን የደቦ፤ በድንህ…… ቀብር ሳይገባ አልቅሰህ…… ተውበት ግባ!!   ከሆነ…… ስራህ ማይረባ አይጠቅምም… የዘመድ እንባ፤ አልቅሰው…… ጩኸው  ቢሸኙህ አይችሉም…… ከዝያ ሊረዱህ!! ለመስገድ…… ከቤት ስትወጣ ለጌታህ…… አታርግ ባላንጣ፤ የለውም…… አጋዥ ረዳት ልጅ እናት…… የለውም አባት!! ነብዩ…… ሙሐመድ እንጅ አታድርግ…… የልብ ወዳጅ፤ ከማንም…… ትዛዝ ሲመጣ አጣራው…… ፈላሕ ልትወጣ!! አይወፍር…… ልብህ አይወጠር በሰማይ…… ላትችል መብረር፤ ተናነስ…… ለሐቅ ለእውነት አትሁን…… አጋዥ ለውሸት!! በሀሜት…… ሰው ከማባለት ተጠንቀቅ…… ሳታውቅ ከማውራት፤ አትሁን…… ጠባብ ዘረኛ ተላቀቅ…… ከመንደርተኛ!! አትሁን…… ጠባብ ዘረኛ ተላቀቅ…… ከመንደርተኛ!! 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Awelhussen12
Show all...
🇵🇸🇵🇸ለኸይር ነገር ቁልፍ ሁን🇵🇸🇵🇸

የቁርአን እና ሀዲስ ትምህርቶች

✍️    ስትወጣ…… ጠዋት ከቤትህ    በዚክር…… ጀምረው ቀንህ። ለሚያይህ…… ስጠው ፈገግታ ለሁሉም…… አቅርብ ሰላምታ። ተኩራርተህ…… አትንጠባረር  ላትችል…… በሰማይ መብረር፤ ሰደቃ…… አድርግ በቻልከው ይተካል…… ጌታህ ቸር ነው። አምሽተህ…… ቤትህ ስትገባ ጨቅጫቃ…… አትሁን አባ፤ ሰልችታህ…… እንዳትደብራት ሳታኮርፍ…… ለስልሰህ አውራት!! 👇  👇  👇  👇  👇  👇  👇 https://t.me/Awelhussen12
Show all...
🇵🇸🇵🇸ለኸይር ነገር ቁልፍ ሁን🇵🇸🇵🇸

የቁርአን እና ሀዲስ ትምህርቶች

ለዳእዋ መጥፎ የሚባል ቦታ የለም❗️ ብዙ ጊዜ ኡስታዞች ሼኮች እስር ቤት ሲገቡ ሌሎቹን ታሳሪዎች ከሽርክ የማላቀቅ ብዙዎቹም የማስለም ልምዱ በተደጋጋሚ እየሰማን እያየን ነው። ⭕️እስር ቤት መጥፎ ነው።ነገር ግን ዳዕዋ ስታደርግ ለማሰናከል ካሰሩህ እስር ቤት ውስጥ ያሉትን ያልተነካኩ ልቦችን በአሏህ ፈቃድ ወደ አሏህ ታዞራቸዋለህ። ያኔ ለኸይር ነው የሚለው አባባል ይገባሀል። ዛሬም አንዱ ሙስሊም በዳሰነች ወረዳ ብዙዎች ሲያሰልም እስልምና ሲያስተምር እስር ቤት አስገቡት። እዚያው ውስጥ 30 ሰዎች አስልሟቸዋል። ሙስሊም ሆነህ በሆነ ፈን እውቀት ካለህ  የትም ብትጣል ትበቅላለህ። ቆሻሻ ነው ቢሉህ ፍግ ማዳበሪያ ትሆናለህ አንተ ብትሞትም ሌሎች ባንተ ባዳበሪያ በድሎት ይበቅላሉ። በእስር ቤት የሞተው ታላቁ ሼህ ሼይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ ትልቁ رحمه الله ህይወቱ ያለፈው በእስር ቤት ነበር።በወቅቱ አስገራሚ የማይሻር ንግግር ተናግሮ አልፏል። ማንኛውም መጥፎ አደጋ የሚመስለን ነገር ካመንበት ለኸይር ነው። وَعَسَىٰ أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ ۖ وَعَسَىٰ أَن تُحِبُّوا شَيْئًا وَهُوَ شَرٌّ لَّكُمْ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ አንዳች ነገርን እርሱ ለናንተ የበለጠ ሲሆን የምትጠሉት መኾናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አንዳችንም ነገር እርሱ ለናንተ መጥፎ ሲሆን የምትወዱት መሆናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አላህም (የሚሻላችሁን) ያውቃል ግን እናንተ አታውቁም፡፡ https://t.me/Awelhissen12
Show all...

ኒቃቧን አወለቀች‼️          (ልብ የሚነካ አስተማሪ ታሪክ) ⇛የሃይስኩል ተማሪ እያለች ነበር ኒቃብ የለበሠችው፡፡ ያውም በአንድ ቀን ዳዕዋ፡፡ ቀኑና ጊዜውን ለማስታወስ በትዝታ ወደኋላ ርቃ ሄደች፡፡ ዕለቱ ጁሙዓ ነበር፡፡ ከሶላት በኋላ ስለ ሒጃብ ዳዕዋ ያደረገው ኡስታዝ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይናገራል፤ በተለይ ሴቶች ጆሮ እንዲሠጡት ይወተውታል ‹ሴት ልጅ ዐውራ ናት፣ ፈፅሞ ፊቷ መታየት የለባትም፣ ፊት ያልተሸፈነ ምን ሊሸፈን!፣ ኒቃብ ግዴታ ነው፤ ሴቶቻችን አላህን ፍሩ፣ ኒቃብ ልበሱ፤ ወላጆችም እንድታለብሱ …› እያለ ይመክራል፡፡ ⇛እዚያው እያለች ወሠነች፡፡ ወደ ቤቷ ገባች፡፡ ለወላጆቿ ነገረች፡፡ ኒቃብ መልበስ አለብኝ አለች፡፡ ከብዙ ክርክር በኋላ አሳመነቻቸው፡፡ ትምህርት ብትጨርስም ዉጤት አልመጣላትም፡፡ በግል ኮሌጅ አካውንቲንግ ተማረች፡፡ ዉጤቷ ጥሩ ነበር፡፡ ሥራ ፈለገች፡፡ ግና በኒቃቧ ምክንያት ተገፋች፡፡ ተቆጨች፣ ተናደደች …. ↳ዕድሜዋ ሲገፋ ይታወቃታል፡፡ ከአሥራ ቤት ወጥቶ ሀያ ገብቶ ወደ ሰላሳም ተጠግቷል፡፡ በዚህ በኩል የሥራ ማጣት፣ በወዲያ ከትዳር መዘግየት አስጨነቃት፡፡ ወንድ አትቀርብም፤ ወንዶችም ሊቀርቧት ይፈራሉ፡፡ የለበሠችው በልጅነት በመሆኑ ቀይ ትሁን ጥቁር፤ ቆንጆ ትሁን መልከ ጥፉ በአካል አያውቋትም፡፡ ብቻ በሩቅ ይሸሿታል፡፡ አንድም ኢማናቸውን ንቀው አሊያም ታጠብቃለች፣ አክራሪ ናት ብለው በመፍራት፡፡ ሁለት ፈተና በአንድ ጊዜ ወጥሮ ያዛት፡፡ የለፋችበት ትምህርት ቆጫት፤ የምትመኘው ትዳር ራቃት፡፡ ብዙ ጓደኞቿ ሥራ አገኙ፡፡ በዕድሜ ታናሾቿ ተራ በተራ አገቡ፡፡ ሒጃብን ለሥሙ ብቻ ጣል የሚያደርጉት ጥሩ ትዳር ያዙ፡፡ ⇨አላህ እሱን ለማይፈሩት ነው እንዴ የሚያደላው! አለች፡፡ ጥሩዎች ሲጎዱ መጥፎዎች ሲጠቀሙ አየች፡፡ ታዘበች፣ አሰበች፡፡ ኢማኗ እየደከመ መጣ፣ በራስ መተማመኗ ቀነሰ፣ ሌሎች የሚያወሩላት ወሬ ሸረሸራት፡፡ ከራሷ ጋር ታገለች፡፡ ኡስታዞችንና ዓሊሞችን ጠየቀች፡፡ ‹ልጅ ሆኜ ስለ ዲን ብዙም ሳላውቅ ነበር በችኮላ የለበስኩት፤ አሁን ማውለቅ እችላለሁ ?› አለች፡፡ አውልቂ የሚላት ጠፋ፡፡ ወደ ራሷ ተመለሰች፡፡ ከሁለት ያጣች እንደሆነች ታወቃት፡፡ ኒቃብ ከሥራም ከትዳርም እየከለከላት እንደሆነ ሸይጧን ሹክ አላት፡፡ ደስ እያላት ባለመልበሷ ምክንያት ምንም አጅር እንደማታገኝም ነገራት፡፡ ወረደች፣ ተጠራጠረች፣ ግራ ተጋባች …. በጥርጣሬ ዉስጥ ከምዋልል ለምን አላወልቀውም አለች፡፡ ከብዙ ትግል በኋላ ....... አወለቀች፡፡ የመጀመሪያ ሰሞን እርቃኗን የሆነች ያህል ተሰማት፡፡ ግና አንዴ አድርጌዋለሁ ብላ ራሷን አበረታታች፡፡ ያዩዋትና የሚያውቋት ሰዎች ደነገጡ፡፡ እሷ ናት ወይስ ሌላ? አሉ፡፡ እሷነቷን ሲያረጋግጡ ብዙ አወሩ፣ ተሳለቁ፡፡ በወሬያቸው ይበልጥ ባሰባት፣ እልህ ተጋባች፡፡ በዚያው ሄደች፡፡ ወደ ቀደመ ቦታዋ አልተመለሠችም፡፡ እሷ የድሮ ኒቃቧን ረሣች፡፡ እነርሱም አውርተው ሲደክሙ ዘነጓት፡፡ ☞ኒቃብ የለበስሽ እህቴ ሆይ! ① ስለተነገረሽ ሳይሆን አውቀሽና አምነሸበት በዝርዝር አጥንተሸና አገናዝበሽ ልበሺ፣ ②ኒቃብ ስትለብሺ ዒባዳ መሆኑን አስቢ፤ ኒያሽ ቀጥ ያለና የተስተካከለ ይሁን፣ ③- በአንድ ልብ ኑሪ፤ ሁለት ሀሳብ መሆን ላውልቅ አላውልቅ ምንዳ የለውም፤ ④ጊዜው ቢረዝምም፣ ቀኑ ቢቆይም አላህ መልካም ባሮቹን ጥሎ አይጥልም፡፡ ⑤ኒቃብ በማውለቅና ፎቶ በመለጠፍ የሚገኝ ትዳር የለም፤ ⑥በአላህ መመካትሽ እንደ ወፍ ይሁን፣ ባዶ ሆዷን ወጥታ ሆዷን ሞልታ ትገባለች፣ ⑦ በአላህ አምኛለሁ በይና ቀጥ በይ፣ ⑧- ጥሩ መጨረሻ አላህን ለሚፈሩና ለጥንቁቆች ነው፡፡ ⑨- አላህ በመልካም ነገር ላይ ፅናት ይስጠን፡፡ [منقول] =የተወሰ https;//t.me/Awelhussen12
Show all...
የጁሙኣ ኹጥባ REC_0000015.amr4.37 MB
ስለ የኡለማዎች ክብር REC_0000016.amr7.81 KB
28 /10/2016 የተደረገ ኹጥባ ይደመጥ የሚገርም ነው ሰምተን የምንጠቀም ያድርገን
Show all...
የዛሬው የጁምኣ ኹጥባ ስለ እውቀትና ስለ ኦለማወች ይሆናል ኢንሽ አሏህ
Show all...
ወሎ የጊንባ ሰለፍዮች
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.