cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ገጣሚዋ ብዕር ✏️✏️✏️ ( በ እድሜአለም ሞኜ/ እድሜ)) 2016E.C

ለስነ- ፅሁፍ አፍቃርያን በሙሉ ይህ ቻናል ስለተለያዩ ጉዳዮች የምሞነጫጭራቸውን ግጥሞች የማቀርብበት ስለሆነ ግጥሞችን በማንበብ እና ሀሳባቸውን በመረዳት የተመቿችሁን like አድርጉ። ኮሜንታችሁ አይለየኝ ! ሀሳብ አስተያየታችሁን በ 👇 @edmelealem link ገብታችሁ አድርሱኝ።🙋‍ መልካም ጊዜ!!

Show more
Ethiopia13 586Amharic9 557The category is not specified
Advertising posts
200
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
የፍቅር መንገድ😌😌😌 ጥላቻ ለነገሰበት ፤ ሰው ከ አፈር ላነሰበት፤ ፧ ለጠላና ላናናቀህ ፍቅር ስጠው የሚያስቀና፤ የጥላቻ እጥፍ ድርብ መች ሆነ የሚያቀና። ፧ ለቀጠፈ ለሰረቀ አገር ምድር ላስቸገረ፤ ከሰው ልኬት ለወረደ የእምነት ቃልን ለሰበረ፤ ፧ በመሯሯጥ ላትደርስበት ብርቱ ሀቅምህ ከሚፈተን፤ ፖሊስ አርገው ወንጀል ሰሪን በማባረር እንዲሠክን። ፧ ላልታመነ ለዋሾ ሰው ላይተነፍስ ያለውሸት፤ በአደባባይ አታዋርደው በወንጀሉ ላይፀፀት፤ የእምነት ጥግን አሳይና በህሊናው ፅደቅበት። ፧ ያም ሆነ ይህ,,,,,,,,,,,,, ቁጣ መርገም ላላቃናው ፤ ስድብ ውርደት ላልመለሰው፤ ለእኛ አገር ሰው😟😟 ፧ ፍቅር እንጅ እምነት እንጂ የእውነት መንገድ፤ ዝልፊያ አይደለም የሚመልስ ከጥፋት ዘንድ ። ✔️ እድሜ,,,,,,08/10/2016e.c                  ,,,,,,01:13pm
Show all...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
የፍቅር መንገድ😌😌😌 ጥላቻ ለነገሰበት ፤ ሰው ከ አፈር ላነሰበት፤ ፧ ለጠላህ ላናናቀህ ፍቅር ስጠው የሚያስቀና፤ የጥላቻ እጥፍ ድርብ መች ሆነና የሚያቀና። ፧ ለቀጠፈ ለሰረቀ አገር ምድር ላስቸገረ፤ ለወረደ የእምነት ቃልን ለሰበረ፤ ፧ በመሯሯጥ ላትደርስበት ብርቱ ሀቅምህ ከሚፈተን፤ ፖሊስ አርገው ወንጀል ሰሪን በማባረር እንዲሠክን። ፧ ላልታመነ ለዋሾ ሰው ላይተነፍስ ያለውሸት፤ እንዲቃና አታዋርደው በአደባባይ ላይፀፀት፤ የእምነት ጥግን አሳይና በህሊናው ላይ ፅደቅበት። ፧ ያም ሆነ ይህ,,,,,,,,,,,,, ቁጣ መርገም ላላቃናው ፤ ስድብ ውርደት ላልመለሰው፤ ለእኛ አገር ሰው😟😟 ፧ ፍቅር እንጅ እምነት እንጂ የእውነት መንገድ፤ ዝልፊያ አይደለም ከጥፋት ዘንድ የሚታደግ። ✔️ እድሜ,,,,,,08/10/2016e.c                  ,,,,,,01:13pm
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ምን አውቄ,,,,,,😌😌😌 ልቦናዬን ካንኳኳኸው እንድጠጋ ወደ አንተ ጋር፤ የእኔን ፈቃድ አትጠይቀኝ ፈፅምልኝ ሁሉን ነገር፤ ካንተ መጦ ምን ሊከፋኝ ምን ልናገር??? ፧ እኔ ያንተ እንሰሳ ነኝ፤ 'ሚበጀኝን ምን አውቄ ትጠይቀኝ!! ፧ ፈቅደህልኝ፣ ባርከህልኝ  መልፋት የኔ ሳይሆን ቢቀር፤ ማድረግ ሳስብ ብርቱ ጉልበት አንደበቴም ቢተሳሰር፤ ፧ መድኃኔዓለም ሁሉን ነገር ባንተ ጥዬ ባንቀላፋ፤ መጠጊያዬ ባደርግህ ነው ያለ ሃሳብ ማንኮራፋ፤ የእኔን  ጉዳይ ለአንተ ትቼ ነጋ ጠባ ከማስከፋ፤ አማኑኤል ይቅር በለኝ  ጉልበት ስጠኝ እኔም ልልፋ!!!!!! ✔️ እድሜ,,,,,,,,,,,27/09/2016e.c ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,12:12am https://t.me/eedme1221 https://t.me/eedme1221
Show all...
👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
ልምጣ,,,,,,,,, አምላኬ ሆይ ልምጣ ልቅር፤ ይህን ትቼ ወደ አንተ ጋር፤ ከዚህ ብቆይ ምን ልፈጥር። ፧ ፊትህ ልቆም ባይቻለኝ፤ የበደል ትንሽ ካለውማ ዛሬ ነበር የሚሻለኝ። ፧ ባጎድል እንጂ ቀን ሲጨምር፤ ከዚ እያለሁ ከበደል ውጭ ምን ልፈጥር። ፧ ቃልህ ታጥፎ ፍጡር ከፍቷል፤ ህግህ ተጥሶ  ሀገር ፈርሷል። ፧ በዚህ እልቂት አጉል ትግል፤ እኔ አልቻልሁም ዝቅ ብዬ ላገለግል። ፧ አምላኬ ሆይ መንገድ ባጣ ፤ ወደ አንተ ዘንድ የሚያመጣ። ፧ ተማፀንሁኝ  ,,,,,,,,,,,,,,,,,, መምጫ መንገድ እንድትመራኝ ፤ ካንተ አጣልቶ ጎደሎ ቀን እንዳይጠራኝ። "እድሜ,,,,,,,,,,26/09/2016e.c            ,,,,,,,,3:34pm
Show all...
👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
ንስሐ ግባበት !! 😌😌 ከጆሮዬ ሲደርስ የናፈቅሁት እውነት፤ ዝም አልልም እኔ አንተም ተማርበት። ፧ ያኔ ለመሰለህ ነፍሴን የገዛሀት፤ በማላውቀው ሚስጢር ላለበስከኝ ውርደት፤ ማስተዋል 'ንዲሰጥህ ንስሀ ግባበት። ፧ ቃሉን  ለማዳመጥ ከመቅደስ ስትገባ፤ ለሳቅህበት ክብሬ አስገባልኝ መባ። ፧ ለካስ የዚያ ጊዜ ለዘመድ አዝማድህ ሲዳረስ ውርደቴ፤ የለበስኩ ሲመስለኝ ኖሯል በራቁቴ። ፧ ከመሸ ቢሆንም የሠማሁት ጉዴን፤ በምትደረድረው በውሸት ፍቅር ቃል ከህመም መዳኔን። ፧ ሳይፈቅድልኝ ልቤ አንተን መከተሌ፤ ቢሳካ ብዬ እንጂ ,,,,,,,,,,,,,,, ከድንግል ፊት ቆሜ የገባሁት ቃሌ፤ አንተነትህን ማፍቀር  አልነበር አመሌ። ፧ ከልብህ ለሌለው ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ፍቅር ፍቅር እያልህ ለተደበርህበት፤ ፍቅር እንዳይነሳህ ንስሀ ግባበት። ❤❤❤❤❤❤❤❤❤ እድሜ,,,,,20/02/2016e.c ማክ 2:35pm. ......tፃፈ https://t.me/eedme1221 https://t.me/eedme1221
Show all...
👍 7🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
አንዳንዴ,,,,,,😁 አያለሁ እእእ,,,,,,,,,,,, ጭላንጭል ጠብታ፤ ጥልቅ እየመሠለች ሰፍታ ተንሰራርታ፤ ከድቀቷ በላይ ምድር ሞላን ሰፍታ፤ ጎልታ ተለክታ። ፧ ከጠብታ በላይ ገዝፎ የሞላ ባህር፤ ውቅያኖስ ማዕበሉ ባለበት ላይ ሲያድር፤ መገረሜ አይቀርም የደቂቅ ጠብታ፤ ባስተጋባው  ዋይታ። ፧ መታየት የፈራ መንገድ የቀነሰው፤ ጥበብ የተካነ ፀጋ የለበሰው፤ እንዴት አይናፍቅም መታየት እንደሰው። ✔️ እድሜ,,,,,,,,,,,,14/09/2016e.c                 ,,,,,,,,, ,,,,,,,2:25pm,,,,ተፃፃፈች
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
አንዳንዴ,,,,,,,😁😁😁 ዝምታን በማንገስ ---- ልብ እየታገለ፤ ህመምን ደብቆ----- ድ'ነት መሻት አለ። ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ✔️እድሜ,,,,,,10/09/2016E.C                ,,,,,,, 7:43am ✔️ ግን እንዴት ሆኖ???😁 History ሳይወሰድ diagnosis እና treatment !!!!😯😯😁😁 https://t.me/eedme1221
Show all...
👍 1 1😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
የተፈተነ ወርቅ.............😐 ከፈተናዎች ጋር ከብዙ ድካሞች፤ መስማማት ቢቻለው መታገል ባይሰለች። ፧ ከውጣ ውረዶች ልቤ አምኖ ቢታረቅ፤ ውበቱ እልፍ ነበር,,,,,,,,,,,,,,, ከነበልባል መሐል ነጥሮ የወጣ ወርቅ። 😴😴 ✔️እድሜ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,9/09/2016E.C               ,,,,,,,,,,,,,4:05Am https://t.me/eedme1221
Show all...
🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
ይቅር ለአንደበቴ,,,,,,,, ዝም ባለ አፍ ውስጥ ዝንብ አይገባበትም፤ በቦታው ነው እንጂ ቃል የትም አይወድቅም ። ማስመሠል ለጣመው ከንቱ ትንታኔ፤ ትዝብት ነው እንጂ  ፋይዳ አይሰጥም ለ'ኔ። ፧ በመሠለኝ ማክበር በመሠለኝ ማድነቅ፤ በክብር ከፍ ከፍ በገፅታ ማርቀቅ። ፧ ውስጡ ለጠቆረ ላዩ ላማረበት፤ በጭፍን ግምቴ ትሁን ሰው ላ'ረኩት፤ ይቅር ለአንደበቴ ምግባር ላሳየሁት። እድሜ,,,,,,4/09/2016e.c ,,,,,,,,,,,,,,,,,,4:24am
Show all...
👍 2👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
የሰለቹ ጆሮዎች ለሰለቹ ጆሮ'ች ማድመጥ ለበቃቸው፤ ጯሂው እየበዛ ላደነቆራቸው። ማዳመጥ የራቀው መስማት ሆኗል ህጉ፤ ለምልክት ጆሮ ጠብቀው ለተዘጉ። አንቺ አለም ስኬትሽ ሆኖ በገፍ  መግፋት፤ ፍፃሜሽ  ተረግሞ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, በመሠለኝ ኖሮ በመሠለኝ መሞት።😒😒 እድሜ, ,,,,,,,,30/08/2016e.c 10:58am https://t.me/eedme1221 https://t.me/eedme1221
Show all...
👍 4
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.