cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ስንክሳር ዘተዋሕዶ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ይኽ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ስንክሳር የሚቀርብበት ቻናል ነው። እንኳን ደህና መጡ 🙏✝️🙏

Show more
Advertising posts
9 053
Subscribers
-1524 hours
+1837 days
+1 13230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🥰 5 2😍 2🏆 2🕊 1
በዚያን ጊዜም እሊህ ቅዱሳን ስለዚህ ስለ ኃላፊው ዓለም ፍጻሜና በመንግሥተ ሰማያት ስላለው ዘለዓለማዊ የተድላ ደስታ ኑሮ አሰቡ።ከዚህም በኋላ ተስማምተው ወደ እስክንድርያ ከተማ ሔዱ በመኰንኑም ፊት ቁመው ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም ከእሳት እንዲጨምሩአቸውና ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ደማቸው እስኪፈስ ድረስ እንዲገርፉአቸው አዘዘ። ዳግመኛም ስለታምና ረጃጅም በሆኑ ችንካሮች ሥጋቸውን ቸንክረው ከታች እሳትን አነደዱባቸው ጌታችንም መልአኩን ልኮ ከእሳቱ አዳናቸው። እንደገናም በታላቅ ዛፍ ላይ ዘቅዝቀው ይሰቅሏቸው ዘንድ አዘዘ። ከአፍንጫቸውና ከአፋቸው ብዙ ደም ወረደ ጌታችን ፈጣሪያችንም ከመላእክቱ ጋራ ወርዶ አዳናቸው መኰንኑም በፊቱ በቆሙ ጊዜ ከጽናታቸው የተነሣ እጅግ አደነቀ። ከዚህም በኋላ ወደ ሀገረ ፈርማ ላካቸው መኰንኑም ለአማልክት ዕጣን አጢሱ አላቸው እምቢ በአሉትም ጊዜ ከኮምጣጤና ከሙጫ ጋራ ጨው ደባልቆ አፍልቶ በአፋቸውና በአፍንጫቸው ጨመረ እነርሱም ይህን ሁሉ ሥቃይ ታገሡ። ከዚህም በኋላ በብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከታች እሳትን አነደዱባቸው የእጆቻቸውንና የእግሮቻቸውንም ጥፍሮች አወለቁ በብረት በትሮችም አጽንተው መቷቸው። በዚያን ጊዜም የመኰንኑ ሚስት ሞተች እርሱም ደንግጦ ይቅር እንዲሉት ሚስቱንም እንዲአስነሡለት ቅዱሳኑን ለመናቸው። እነርሱም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመኑት ያን ጊዜም ተነሣች መኰንኑም ከሕዝቡ ሁሉ ጋራ በጌታችን አመነ ቅዱሳኑንም ወደ ሀገራቸው ይሔዱ ዘንድ ለቀቃቸው። ወደ ሀገራቸው ወደ ገምኑዲም በደረሱ ጊዜ የቀረ ገንዘባቸውን ለድኆችና ለችግረኞች ሰጡ የቅዱስ አንያኖስንም ሥጋ ስሙ ሰረባሞን ለሚባል አንድ ጻድቅ ሰው አደራ አስጠበቁት እንደቀድሞውም በፊቱ መብራትን እንዲአበራ አዘዙት። ከዚህም በኋላ በርሙን ወደሚባል አገር ሔደው በመኰንኑ ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። መኰንኑም እንዲገርፉአቸውና እንዲጐትቱአቸው አዘዘ ደማቸውም እንደ ውኃ ፈሰሰ ደንቆሮና ዲዳ የሆነች ሴትም መጥታ ከቅዱሳኑ ደም ወስዳ አፏንና ጆሮዎቿን ልቧንም ቀባች ወዲያውኑም ድና ተናገረች ሰማችም። መኰንኑ ግን አሠራቸው ከዚህም በኋላ እነርሱን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው። የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ። በዚያም ከገምኑዲ አገር ሰረባሞንና ሌሎች ሰዎችም ነበሩ በበፍታና በከበሩ ልብሶች ገነዙአቸው መዓዛው ጣፋጭ በሆነ ሽቱም ቀቡአቸው ወደ አገራቸው ወደ ገምኑዲም ወሰዱአቸው። ከገምኑዲም ከተማ ውጭ በደረሱ ጊዜ ሥጋቸው የተጫነበትን ሠረገላ የሚስቡ እንስሶች ቆሙ። ሥጋችን በውስጡ ይኖር ዘንድ እግዚአብሔር የመረጠው ቦታ ይህ ነው የሚል ቃልን ከሰማይ ሰሙ በዚያም አኖሩአቸው። ከዚህም በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሠሩላቸው ሥጋቸውንም ከቅዱስ አንያኖስ ሥጋ ጋር በውስጥዋ አኖሩ በገምኑዲ አገርም ድንቆችንና ተአምራቶችን እያሳዩ እስከ ዛሬ ድረስ አሉ። ለእኒህ ቅዱሳንም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስማቸውን ለሚጠራ መታሰቢያቸውንም እንደችሎታው ለሚያደርግ ኃጢአቱ ይሠረይለታል ሥቃይንም ከቶ አያይም ብሎ መከራ በሚቀበሉበት ጊዜ ቃል ኪዳን ሰጣቸው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_አባ_በላኒ በዚህችም ቀን ከግብጽ ደቡብ አካ በሚባል አውራጃ ባራ በምትባል መንደር ይኖር የነበረ ቅዱስ ሰማዕት አባ በላኒ አረፈ። ይህም ቅዱስ ቄስ ነበር። የምእመናንን መከራቸውን የሰማዕታትንም መገደላቸውን በሰማ ጊዜ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጥቶ ወደ እንዴናው ከተማ ሔደ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመኰንኑ ፊት ታመነ መኰንኑም ጽኑ የሆነ ሥቃይን ብዙ ቀን አሠቃየው ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀዳጀ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አባ_ቢማ_ሰማዕት በዚህችም ዕለት ከላይኛው ግብጽ ከብህንሳ ከተማ አባ ቢማ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ሰው ባለጸጋና በጎ የሚሠራ ድኆችንም የሚወድ በሀገርም ላይ የተሾመ ነበር። በአንዲት ዕለትም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በራእይ ፊቱ ከፀሐይ ብርሃን እጅግ እየበራ አየው እንዲህም አለው ሰላም ለአንተ ይሁን ወደ መኰንኑም ሒደህ በስሜ ታመን። እኔ የክብር አክሊልን አዘጋጅቼልሃለሁና። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ተነሥቶ ገንዘቡን ለድኆችና ለችግረኞች ሰጠ። ከዚህም በኋላ ጸሎት አድርጎ ከቤቱ ወጣ ሉቅያኖስ ወደሚባል መኰንንም ሒዶ በፊቱ ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። መኰንኑም በአየው ጊዜ ሹም እንደሆነ አውቆ ከእርሱ ንዋየ ቅድሳትን ፈለገ ዳግመኛም ለአማልክት እንዲሠዋ ፈለገ ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት ስለ ንዋየ ቅድሳት ከእኔ ልትሻ አይገባህም የረከሱ አማልክትንም ስለማምለክ ትእዛዝህን አልሰማም እኔ ሰማይንና ምድርን በውስጣቸው ያለውን ሁሉ የፈጠረ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አመልከዋለሁና። መኰንኑም ይህን በሰማ ጊዜ ተቆጥቶ ምላሱን ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ጌታችንም እንደ ቀድሞው ምላሱን መለሰለት። ከዚህ በኋላ በማበራያ ውስጥ አበራዩት በብረት ዐልጋ ላይም ቸንክረው በበታቹ እሳትን አነደዱ እግዚአብሔርም አዳነው ያለ ጉዳትም አስነሣው። ከዚህ በኋላ ወደ እስክንድርያ ከተማ ላከው ክብር ይግባውና ጌታችንም ተገልጾለት አጽናናው ከዚህም በኋላ በወህኒ ቤት ጨመሩት በዚያም ተአምራትን አደረገ። ጋኔን ያደረባት የአቅፋሃስ ሀገር ሰው የዮልያኖስ እኅት ነበረች ቅዱስ ቢማም ያንን ጋኔን ከእርሷ ላይ አወጣውና አሳደደው ዜናውም በሀገሩ ውስጥ በተሰማ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ብዙዎች አመኑ። መኰንኑም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም አሠቃየው በመንኰራኵርም የእጆቹንና የእግሮቹን ጥፍሮች አወለቁ በእሳት በአጋሉት በብረት ሰንሰለትም አሥረው ጐተቱት። በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥም ጣሉት ከዚህም ጌታችን አዳነው። ከዚህም በኋላ በአንገቱ ታላቅ ደንጊያ አንጠልጥለው በባሕር ውስጥ ጣሉት አሁንም ጌታችን አዳነው። ሁለተኛም ከእሳት ጨመሩት። ከዚህም ጌታችን አዳነው በእሳቱም መካከል እየጸለየ ቆመ። መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸ ጊዜ ወደ ላይኛው ግብጽ ሰደደው በዚያም ያሠቃዩት ጀመሩ ዘቅዝቀውም ሰቀሉት ከዚህም በኋላ በብረት ምጣድ ውስጥ ጨምረዉ በላዩ እሳትን አነደዱበት ጌታችንም ተገለጠለትና ከእሳቱ አዳነው። ከዚህም በኋላ ጌታችን ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ገድሉን ለሚጽፍ በስሙም ምጽዋት ለሚያደርግ ሁሉ የዘለላም ሕይወትን ያድለው ዘንድ ቃል ኪዳንን ሰጠው። መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንደ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማይ ተቀበለ። የአቅፋሃስ ከተማ ሹም የሆነ የዮልዮስ ባሮችም ሥጋውን አንሥተው ወደ ሀገሩ ወሰዱት እስከ ስደቱ ዘመን ፍጻሜ ድረስም በመልካም ቦታ አኖሩት። ከዚህም በኋላ መልካም የሆነች ቤተ ክርስቲያንንና ገዳምን ሠሩለት ሥጋውንም በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ በሽተኞችም ሁሉ ይፈወሱ ነበርና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
Show all...
🥰 2💯 2👏 1🙏 1😍 1
በዚህችም ቀን አባ ኪሮስ የቀበረው የንጉሥ ልጅ ድኃ የነበረው አባ ሚሳኤል አረፈ። ዜናውም እንዲህ ነው። አባ ኪሮስ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሳት ገዳም ሔደ። ከዚያም ደርሶ ቤተ ክርስቲያኒቱን ተሳለማት በዚያም አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ሥዕል አየ። ከዐይኖቹም ዕንባ እያፈሰሰ እመቤቴ ሆይ አስቢኝ አላት ሥዕሊቱም ኪሮስ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው ከዚህም አትለፍ የአባትህን ዐፅም ትጠብቅ ዘንድ ወደ ማደሪያህ ተመለስ እንጂ አለችው። አባ ኪሮስም ይህን ሰምቶ ከሥዕሏ ፊት ሰባት መቶ ሰግደትን ሰገደ። በዕብራይስጥም ቋንቋ እንግዳ ነህና በቃህ በምሕረት መዝገብም ተመዝግቦልሃል የሚለውን ቃል ሰማ። ከዚያም በአለፈ ጊዜ መነኰሳቱ መልኩ የተዋበ ሁለመናውም ያማረ እንደሆነ ተመለከቱ። እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ ይህ መነኵሴ ከመንግሥት ከተማ ከግብጽ አገር የመጣ ነው ሰውነቱ በጾምና በጸሎት አልጠወለገምና። እጅግም ነቀፉት አልተቀበሉትም።ነገር ግን ወደ ሌላ ወደሚንቁት ቦታ ሰደዱት። በዚያም መስፈርስ በሚባል ሕማም ለብዙ ጊዜ የታመመና በምድር ላይ የተጣለ ድኃ ሰውን አገኘ። በራስጌውም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በግርጌው ቅዱስ ገብርኤልን በቀኙም ሩፋኤልን በግራውም ሰዳካኤልን አየ። እነርሱም በክንፋቸው ጋርደውት ነበር ከሰውም ያለርሱ ያያቸው አልነበረም። በገዳዩች ፊት ሞትን የማይፈራ ጐበዝ እንዴት ነህ ብለው ሰላምታ ሰጡት። አባ ኪሮስም አደነቀ በልዕልና ነዋሪዎች ሆይ ከዚህ ለምን ተቀመጣችሁ አላቸው የህን ድኃ እንድንጠብቀው ከእግዚአብሔር ታዘናል አሉት አባ ኪሮስም እስከ መቼ ነው አላቸው። ከዚህ ድካም እስከሚአሳርፈው ድረስ ነው አሉት። ከዚህም በኋላ ወደ ታመመው ደኃ ተመልሶ በዚህ ቦታ ከኖርህ ምን ያህል ዘመን ነው አለው በሽተኛውም ሰላሳ አምስት ዓመት ነው አለው ሁለተኛም ከታመምክ ስንት ዓመት ነው አለው ሃያ ዓመት ነው ብሎ መለሰ። አበ ምኔቱና የገዳሙ መነኰሳት ይጐበኙሃልን ብሎ ጠየቀው በሽተኛውም አባቴ ሆይ የለም አይጐበኙኝም ፊታቸውን ከአየሁ ዓሥራ አምስት ዓመት ይሆናል ብሎ መለሰ። አባ ኪሮስም ና ንገረኝ አባትህ ማነው እናትህስ ማናት አለው በሽተኛውም እንዲህ ብሎ መለሰ አባቴ የኬልቄዶን ንጉሥ እናቴም የራሕራሕ ንጉሥ ልጅ ናት። አባቴ ኪሮስ ሆይ እውነት እልሃለሁ በአባቴ ቤት ያሉ ሰዎች ወርቁንና ብሩን ቀጭኑንም ልብስ በእግሮቻቸው ይረግጡአቸዋል። አባ ኪሮስም ወደዚች ገዳም ማን አደረሰህ አለው ድውዩም እንዳንተ ያሉ ሁለት ሰዎች ወደ አባቴ ቤት መጥተው በዚያ አደሩ። እኩለ ሌሊትም ሲሆን ፊቱ ብሩህ የሆነ ሰውም ወደኔ መጣ ሚሳኤል ብሎ ጠርቶ ሲነጋ ተነሥተህ ከእነዚህ ቅዱሳን ጋራ ሒድ አለኝ በእንዲህ ያለ ሥራ ወጥቼ ወደዚህ ቦታ ደረስሁ ምንም በጎ ሥራ ሳልሠራም እንደ እነርሱ ሆንሁ። አባ ኪሮስም እኔ አጽናናሃለሁና ወንድሜ ሆይ ስማ ስሙ በብኑዳ የሚባል አንድ እጅግ ድኃ የሆነ በበረሃ የሚኖር መነኵሴ ነበረ። የበጎ ሥራ ጠላት ሰይጣን ወደርሱ መጥቶ አሳተው እግዚአብሔርም ሥጋውን ለአንበሳና ለሰማይ ወፎች ሰጠ እርሱም በወገን የከበረ ከሮም ንገሥ በታች የሚገዛ የኬፋዝ ንጉሥ ልጅ ነበረ። ሁለተኛም እነግርሃለሁ የሮሜ ንጉሥ ልጅ የሆነ አንድ ድኃ ነበረ። እርሱም ከበትር ብቻ በቀር ከአባቱ ቤት ምንም ሳይዝ በቀስታ ወጣ ያንንም ሰው እኔ እጅግ አውቀዋለሁ። ከገዳም ወደ ገዳም ከተራራም ወደ ተራራ ይዞር ነበር ሞቱንም አላስተዋልኩም ሕይወቱንም አላወቅሁም። ዳግመኛም አንድ የንጉሥ ልጅ ድኃ ነበረ። እርሱም በሰንበታት እነጂ በሌላ ቀን ምንም ሳይቀምስ ማቅ ለብሶ በቀንና በሌሊት ለጸሎት ይተጋ ነበር። በእንዲህ ያለ ሥራም ኑሮ አረፈ የብርሃን መላእክትም ነፍሱን ወስደው በመንግሥተ ሰማያት አኖሯት። አሁንም ወንድሜ የምነግርህን ስማ። የፈጣሪህ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አታድንቅ የወደደውን ይገሥጻልና ያም በሽተኛ ድኃ መነኰስ እውነት ነው ለእኔ ይገባኛል ሰለ ኃጢአቴም ይህን ተቀበልሁ ብሎ መለሰ። ይህንንም ብሎ ዝም አለ። በዚያች ሰዓትም ያን በሽተኛ በሞት ያሰናብተው ዘንድ አባ ኪሮስ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በድንገት መጣ። እልፍ አእላፋት መላእክትም በዙሪያው ሆነው ከእርሱ ጋር ነበሩ ለጻድቃን ሞገሳቸውና ንጉሣቸው የሆነ አምላካችንን እናመስግነው ለችግረኞችም ተስፋ የሆነ አምላካችንን እናመስግነው እያሉ ይዘምሩ ነበር። በዚህ ዓለም በገድል የደከሙ በእርሱ ደስ ይላቸዋል። አባ ኪሮስም በአየ ጊዜ በምድር ላይ ሰግዶ ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ ወደዚህ ምን አመጣህ አለ ጌታችንም ስለ ጠራኸኝ መጣሁ አለው። አባ ኪሮስም ይህ ሰው ፃዕር በዝቶበታልና ያርፍ ዘንድ አሰናብተው አለው። ጌታችንም ምን ያህል እንደምወድህ የመላእክት ሠራዊት ያዩና ያውቁ ዘንድ ይቺን የገነት ተክል አበባ ከእጄ ወስደህ በዚህ በሽተኛ በፊቱ ላይ ጣል አለው። አባ ኪሮስም ያንን የገነት ተክል አበባ ከጌታችን እጅ ተቀብሎ በበሽተኛው ፊት ላይ አኖረ ያን ጊዜም ነፍሱ ያለ ፃዕር በፍጥነት ወጣች መድኃኒታችንም ተቀብሎ ሳማት ከእርሱም ጋር በብርሃን ሠረገላ ውስጥ አስቀመጣት አውጥቶም በሰማያዊ ክብር አኖራት። አባ ኪሮስም እያደነቀ አለቀሰ ከዚህም በኋላ ወደ አበምኔቱ ሔዶ እነሆ ያ ድኃ ስለ አረፈ መቃብር ቆፍረው ይቀበሩት ዘንድ ከመነኰሳቱ እዘዝ አለው አበ ምኔቱም ምን ግዴታ አለብኝ አለው አባ ኪሮስም ትኩር ብሎ ተመለከተውና ይህ የሰይጣን ሥራ እንጂ የሰው ሥራ አይደለም አለው። ሰለ አስጨነቀውም ሰባት መነኰሳትን አዘዘለት እነርሱም ማዕጠንታቸውን ይዘው ተነሡ አባ ኪሮስም የሚአጥኑት አሉና የረከሱ ማዕጠንቶቻችሁን አስወግዱ። በቦታቸውም ተዉአቸው ነገር ግን ቅበሩት ብሎ አማላቸው። ያን ጊዜም አራቱ የመላእክት አለቆች ሥጋውን በከርቤና በሚዓ አጠኑ መዓዛውም ያንን በዓት መላው እነዚህ መነኰሳትም የሚያሸተን ምንድነው ይህ መነኰስ ሥራይን ያውቅ ይሆን ተባባሉ። ከዚህም በኋላ ሥጋውን ወስደው በዚያው ገዳም በእንግዳ መቃብር ቀበሩት ከመቃብሩም ጥሩ ውኃ ፈልቆ ለበሽተኞች ፈውስ ሆነ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱሳን_አቤሮንና_አቶም በዚህችም ቀን ዳግመኛ ከእስክንድርያ ከተማና ከገምኑዲ የሆኑ ቅዱሳን አቤሮንና አቶም በሰማዕትነት ሞቱ። የእሊህም ቅዱሳን ወላጆቻቸው እግዚአብሔርን የሚፈሩ ምእመናን ነበሩ። ብዙ ምጽዋትንም ይሰጡ ነበር። የአባታቸውም ስም ዮሐንስ የእናታቸው ማርያም ነበር። አባታቸው በአረፈ ጊዜ የአቤሮን ዕድሜ ሠላሳ የአቶምም ዕድሜ ሃያ ሰባት ዓመት ነበረ። በቤተ ክርስቲያን አገልግሎትም የተፀመዱ ነበሩ የሚራሩም ነበሩ መጻተኞችንም በፍቅር ይቀበሏቸው ነበር በትሩፋት ሁሉና በበጎ ሥራ ፍጹማን ነበሩ። ፈርማ በሚባል አገር ብዙ ሰዎች በሰማዕትነት በሞቱ ጊዜ እሊህ ቅዱሳን ገንዘባቸውን ይዘው ለንግድ ወደ ፈርማ ሔዱ። የንጉሥ ጭፍሮችንም አገኟቸው ከእርሳቸውም ጋራ የሰማዕቱ የቅዱስ አንያኖስ ሥጋ ነበረ ለጭፍሮችም ብዙ ገንዘብ ሰጥተው ከጭፍሮች እጅ ወደ ቤታቸው ወሰዱት ከከበረ ደንጊያ በተሠራ ሣጥን ውስጥም አኖሩት በፊቱም ሁል ጊዜ የሚበራ መብራትን አኖሩ። ከሥጋውም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ።
Show all...
💯 2🥰 1🕊 1😍 1🏆 1
በዚህችም ዕለት በምዕራባዊ በረሀ የሚኖር ታላቅና ክቡር አባት የሆነው የአባ ኪሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። ይህም ቅዱስ የታላቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ወንድሙ ነበር በከተማ ውስጥ የሚሠራውን ዐመፅ በአየ ጊዜ ገንዘቡን ሁሉ ትቶ ከሀገሩ ወጣ። ጌታቸንም መርቶ ወደዚች ምዕራባዊት በረሀ አደረሰው በውስጧም ብዙ ዘመናት ብቻውን ኖረ ከሰው ማንም አላየውም በዚህ ሁሉ ዘመን የዱር አራዊትም ቢሆኑ። በአስቄጥስም ገዳም ስሙ አባ ባውማ የሚባል አንድ ቄስ ነበረ እርሱም የንጉሥ ዘይኑን ልጅ ቅድስት ኢላርያን ሥጋዋን የገነዘ ነው። እርሱም እንዲህ አለ በቤተ ክርስቲያን ወስጥ እያለሁ አባ ባውማ ሆይ ተነሥ ወደ በረሀው ውስጥ ገብተህ ወደ ፀሐይ መግቢያ ሒድ ከቅዱሳን ሁሉ አብዝቶ ፈቃዴን የፈጸመውን የአንድ ገዳማዊ ሥጋ ትገንዝ ዘንድ የሚለኝን ቃል ከሰማይ ሰማሁ። ያን ጊዜም ደስ ብሎኝ ተነሣሁ በበረሀውም ውስጥ ሦስት ቀን ተጉዤ ከአንድ ገዳማዊ በዓት ደርሼ ደጁን አንኳኳሁ አንድ ሽማግሌ ገዳማዊም ከፈተልኝና እርስ በርሳችን ሰላምታ ተለዋወጥን በዚች በረሀ ሌላ ገዳማዊ አለን ብዬ ጠየቅሁት አዎን አለኝ። ሁለተኛም ስምህ ማነው አባቴ ሆይ በዚችስ በረሀ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ኖርክ አልሁት ስሜ ስምዖን ነው በዚች በረሀ የኖርኩትም ሰባ ዓመታት ነው አለኝ። ከእርሱ ዘንድም ወጥቼ ሦስት ቀን ተጓዝኩ ሁለተኛም ስሙ ባሞን የሚባል ገዳማዊ አገኘሁ ሰላምታም ሰጠሁትና በዚች በረሀ ሌላ ገዳማዊ አለን አልሁት አዎን አለ አለኝ። አራት ቀንም ተጓዝኩ ወደ አባ ኪሮስ በዓት ደረስኩ ቅዱስ አባት ሆይ ባርከኝ እያልኩ ደጁን አንኳኳሁ አባ ባውማ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው ብሎ ከውስጥ ተናገረኝ። እግዚአብሔር ያከበረህ ሰው በሰላም በፍቅር ወደእኔ ግባ አለኝ ያን ጊዜ ገብቼ ከእርሱ ተባረክሁ በፊቱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ክብር አየሁ የራሱ ጠጉርና ጽሕሙ እንደ በረድ የነጣ ነበር። ከዚህም በኋላ ተቀመጥሁ በብብቻውም አቀፈኝ እንዲህም አለኝ እነሆ ይችን ሰዓት እየጠበቅኋት በዚች በዓት ሃምሳ ሰባት ዓመት ኖርኩ ይህንንም ሲል ጥቂት ታመመና ተኛ እየደነገጠ ያቺን ሌሊት አደረ ሲነጋም በበዓቱ ውስጥ ታላቅ ብርሃን በራ ብርሃናዊ ሰውም ገባ በእጁም የብርሃን መስቀል አለ በአባ ኪሮስ አጠገብም ተቀምጦ ሳመዉ ባረከውም አጽናናው ሰላምን ፍቅርን አንድነትን አደረገለት ከእርሱም ተሠወረ እኔም ፈራሁ እንዲህ የሚበራ ይህን ክብር የተጐናጸፈ ይህ ማነው አልሁት። እርሱም ልጄ ሆይ ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ልማዱ ስለ ሆነ ሁልጊዜ ይመጣል ያጽናናኛልም አለኝ። በቀዳሚት ሰንበት ዕለትም ዘጠኝ ሰዓት በሆነ ጊዜ እስከ ሰማይ የሚደርስ ታላቅ ጩኸትን ሰማሁ ከጩኸታቸውም ኃይል የተነሣ ምድር ተናወጸች። እኔም ይህ የምሰማው ጩኸት ምንድነው ብዬ ጠየቅሁት እርሱም ልጄ ሆይ ይህ በሲኦል የሚኖሩ የኃጥአን ጩኸት ነው ስለ ቅድስት ትንሣኤው የእሑድ ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ እግዚአብሔር ያሳርፋቸዋልና ስለዚህም እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል አለኝ። በዚችም ዕለት ሐምሌ ሰባት ቀን ቅዱስ አባ ኪሮስ ጩኾ አለቀሰ ዛሬ በግብጽ አገር ታላቅ ምሰሶ ወደቀ ይኸውም የገዳማውያን አለቃ ቅዱስ አባ ሲኖዳ ነው አለ። ከዚህም በኋላ ከደዌው ጽናት የተነሣ እሑድ ሌሊት እጅግ ደነገጠ በበዓቱም ውስጥ እነሆ ታላቅ ብርሃን በራ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ገብቶ በአባ ኪሮስ ራስ አጠገብ ተቀመጠ። አባ ኪሮስም መድኃኒታችንን ጌታዬ ሆይ ይህን ሰው ባርከው አለው መድኃኒታችንም የመረጥሁህ አባ ባውማ ሆይ ጽና አትፍራም ሰላሜ በረከቴም ከአንተ ጋራ ይኑር። አሁንም ታማኝ አገልጋዬ የሆነ የዚህን የቅዱስ ኪሮስን ያየኸውንና የሰማኸውን ወደፊትም ዳግመኛ የምታየውንና የምትሰማውን ገድሉን ጻፍ አለኝ። ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን አባ ኪሮስን እንዲህ አለው እነሆ አንተ ትሞታለህና አትዘን ሞትህ ሞት አይደለም የዘላለም ሕይወት ነው እንጂ። የገድልህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውን የሚሰማውንም ሁሉ በምድርም መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ በደብረ ጽዮን በሚደረገው የሽህ ዓመት በዓል ምሳ ከእኔ ጋር ይቀመጥ ዘንድ አደርገዋለሁ ከቅዱሳኖቼም ጋራ እቆጥረዋለሁ። የኃጢአቱንም መጽሐፍ ቀድጄ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ። ለመሥዋዕት የሚገባውንም ዕጣኑንና ወይኑን መብራቱንም መባ አድርጎ ለሚሰጥም በስምህም ለድኆችና ለችግረኞች ምጽዋትን ለሚያደርግ ዓይን ያላየውን ጆሮም ያልሰማውን በሰው ልቡናም ያልታሰበውን በጎ ዋጋ እኔ እጥፍ ድርብ አድርጌ እሰጠዋለሁ። በበኵር ቤተ ክርስቲያንም ሥጋዬንና ደሜን አቀብላቸዋለሁ በዚህም ዓለም ቤታቸውን እባርካለሁ። ልጆቻቸውን አሳድጋለሁ ከበጎ ነገር ሁሉ ምንም ምን አያጡም። አሁንም ከዚህ ዓለም ድካም ወደ ዕረፍት የዘላለም ተድላ ደስታ ወዳለበት ወደ ብርሃን ቦታ እወስድህ ዘንድ ጊዜው ደረሰ መድኃኒታችንም ይህን ሲናገር እነሆ ነቢዩና ዘማሪው ዳዊት መጣ መሰንቆውም ከእርሱ ጋራ ነበረች። ይቺ ዕለት በእርሷ ፈጽሞ ሐሤት እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር የሠራት ናት እያለ አመሰገነባት። መድኃኒታችንም አባ ኪሮስን እነሆ ዘማሪው ዳዊት መጥቷልና ይዘምርልህ ዘንድ የምትሻውን ንገር አለው። ዳዊትም ቅዱስ አባ ኪሮስን በየትኛው አውታር እንድዘምርልህ ትሻለህ ደግሞስ በየትኛው ዜማ በየትኛው ስልት በመጀመሪያው ነውን ወይስ በሁለተኛው ወይስ በሦስተኛው አለው። ቅዱስ አባ ኪሮስም በዐሥሩም አውታር በየስልታቸውና በየዜማቸው ልሰማ እሻለሁ አለ። ያን ጊዜ ዳዊት መሰንቆውን አዘጋጅቶ የጻድቅ ሞቱ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው አለ ዳግመኛም ጐለመስሁ አረጀሁም የሚወድቅ ጻድቅን አላየሁም አለ። ዳዊትም ድምፁን አሣምሮ ዘመረ መሰንቆውንም በስልት መታት። ያን ጊዜም የቅዱስ አባ ኪሮስ ነፍሱ ወጣች መድኃኒታችንም ተቀብሎ ሳማት ለመላእክት አለቃ ለሚካኤልም ሰጣት። እኔ አባ ባውማም የቅዱስ አባ ኪሮስን ሥጋውን ቀበርኩ ከበዓቱም በወጣሁ ጊዜ በረሀው በሰማይ ሠራዊት ተመልቶ አየሁ መድኃኒታችንም የቅዱስ አባ ኪሮስ ሥጋው ባለበት በዓት ላይ መስቀሉን አኑሮ ዘጋት። ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ለኔ ሰላምታ ሰጥቶኝ መላእክትና የመላእክት አለቆች በፊቱ እያመሰገኑና እየዘመሩ በታላቅ ክብር ዐረገ። የቅዱስ አባ ኪሮስን ነፍስ ከመድኃኒታችን ጋራ እንደዚህ አሳረጓት። እርሷም በተሰጣት ክብር ደስ እያላት ዐረገች። እኔም አባ ባውማ በዚያ ቦታ ብቻዬን ቀረሁ ተመልሼም ወደ አባ አሞን በዓት ደረስሁ። ከዚያም የሦስት ቀን መንገድ ተጉዤ ወደ አባ ስምዖን በዓት ደረስሁ። ከዚያም ሦስት ቀን ተጉዤ ወደ ቦታዬ ወደ አስቄጥስ ገዳም ደረስሁ። ለመነኰሳቱም ሁሉ ያየሁትንና የሰማሁትን ሁሉ የቅዱስ አባ ኪሮስን ገድሉን ስለ አባ ሲኖዳም ዕረፍት ትንቢት እንደ ተናገረ ነገርኋቸው። መነኰሳቱም ሰምተው እጅግ አደነቁ የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። እኔ አባ ባውማም የቅዱስ አባ ኪሮስን ገድሉን ጽፌ ለሚያነበውና ለሚሰማው ሁሉ መጽናኛ ይሆን ዘንድ ወደ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉና ወደ ገዳማትም ላክሁ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አባ_ሚሳኤል_ነዳይ
Show all...
💯 2🥰 1👏 1🕊 1😍 1
#ሐምሌ_8 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ስምንት በዚች ቀን በጎ ስም አጠራር ያለው የዓለም ሁሉ ኮከብ የሆነው #ቅዱስ_አባት_አባ_ብሶይ አረፈ፣ታላቅና ክቡር አባት የሆነው #የአባ_ኪሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ፣ አባ ኪሮስ የቀበረው የንጉሥ ልጅ ድኃ የነበረው #አባ_ሚሳኤል አረፈ፣ #ቅዱሳን_አቤሮንና_አቶም በሰማዕትነት ሞቱ፣ ቅዱስ ሰማዕት #አባ_በላኒ አረፈ፣ #አባ_ቢማ በሰማዕትነት ሞተ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_አባ_ብሶይ ሐምሌ ስምንት በዚች ቀን በጎ ስም አጠራር ያለው የአባ መቃርስ ገዳምና የዓለም ሁሉ ኮከብ የሆነው ቅዱስ አባት አባ ብሶይ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከግብጽ አገር ስሟ ሰነስ ከምትባል አገር ነበር ሰባት ወንድሞችም ነበሩት እናቱም የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔር ያገለግለኝ ዘንድ ከሰባቱ ልጆችሽ አንዱን ስጪኝ ብሎሻል እያለ እንደሚያነጋግራት ራዕይን አየች። እርሷም ጌታዬ ሆይ የወደድከውን ውሰድ ሁሉም ገንዘቦቹ ናቸውና አለችው። መልአኩም እጁን ዘርግቶ የብሶይን ራስ ይዞ ለእግዚአብሔር መልካም ሥራ የሚሠራ ይህ ልጅ ነው አለ። ይህ ብሶይ የከሳና ሥጋው የኮሰሰ ነበርና እናቱ ለዚያ መልአክ ጌታዬ ሆይ እግዚአብሔርን የሚያገለግል ከእነዚህ አንዱን ጠንካራውን ውሰድ አለችው። መልአኩም እግዚአብሔር የመረጠው ይህ ነው አላት። ከዚህም በኋላ ከእርሷ ተሠወረ። በአደገም ጊዜ የምንኵስና ልብስ ሊለብስ ወደደ። ወደ አስቄጥስም ገዳም ሔደ በአባ ባይሞይ ዘንድም መነኰሰ እርሱም አባ ዮሐንስ ሐፂርን ያመነኰሰ ነው። ከዚህም በኋላ እጅግ ጽኑ የሆነ ተጋድሎን መጋደል ጀመረ ምንም ምን ሳይቀምስ አርባ ቀን እስከ መጨረሻው ሦስት ጊዜ ጾመ። በቀንና በሌሊት በጾምና በጸሎት እየተጋ ቅዱሳት መጻሕፍትን አዘውትሮ በማንበብ በመጻሕፍት ቃል ነፍሱን ያረካት ነበር። የእግዚአብሔርን ቃል እጅግ ይወድ ነበርና ከማር ከስኳርም እጅግ ይጥመው ነበርና በውኃ ዳርም እንዳለች ተክል ሆነ። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ያየው ዘንድ የተገባው ሆኖ ነበር ጌታችንም ብዙ ጊዜ ይገለጽለት ነበር። ከእርሱም ጋራ ይነጋገር ነበር። እርሱም እግሩን አጥቦ እጣቢውን ይጠጣው ነበር። በአንዲት ቀንም የመድኃኒታችንን እግሮቹን አጥቦ ግማሹን ጠጥቶ ግማሹን ለደቀ መዝሙሩ እንዲጠጣ ተወለት። ረድኡም በመጣ ጊዜ ልጄ ሆይ ተነሥና በኵስኵስቱ ውስጥ ካለው ውኃ ጠጣ አለው ረድኡም በልቡ በመቅጃው ውስጥ ካለው ከጥሩው ውኃ ለምን አይሰጠኝም አለ። ይህንም ብሎ ቸለል አለ። መምህሩ እንዳዘዘውም አልጠጣም ሁለተኛም ልጄ ሆይ ተነሥና ከኵስኵስቱ ያለውን ያንን ውኃ ጠጣ አለው። ግድ ጠጣ ባለውም ጊዜ ተነስቶ ወደኵስኵስቱ ሔደ። ነገር ግን ውኃ አላገኘም አባ ብሶይም የጌታችንን እግር እንዳጠበና ግማሹን ጠጥቶ ግማሹን እንዲጠጣ ለእርሱ እንደተወለት አስረዳው። በነገረውም ጊዜ እጅግ አዘነ ፍጹም ድንጋፄም ደነገጠ። አባ ብሶይም ረድኡን ራሱን እብድ አስመስሎ ወደሚኖር ወደ አንድ ጻድቅ ሰው ዘንድ ላከው እርሱም አረጋግቶ ወደ አባቱ ወደ አባ ብሶይ መለሰው። ድንጋጤውም ባልተወው ጊዜ ወደዚያ ጻድቅ ሰው ዳግመኛ ላከው በሔደም ጊዜ ሙቶ አገኘው አባ ብሶይም ለረድኡ ይህን በትሬን በላዩ አኑርና ተነሥተህ እንድታነጋግረኝ አባቴ አዞሃል በለው አለው ሔዶም የአባ ብሶይን በትር በዚያ ጻድቅ በድን ላይ አኖረ ወዲያውኑም ተነሥቶ ስማ ለአባትህም ታዘዝ ታዛዥ ብትሆን ይህ ድንጋጤ ባላገኘህም ነበር አለው ይህንንም ብሎ ተመልሶ ተኛ። በአንዲት ቀንም ከቅዱስ አባ ብሶይ ደቀ መዛሙርት አንዱ መጣ ወደ እርሱም ከመግባቱ በፊት ከሰው ጋራ ሲነጋገር ሰማው በገባ ጊዜም ከሰው ማንንም አላገኘም አባቴ ሆይ ከአንተ ጋራ ሲነጋገር የነበረ ማን ነው ብሎ ጠየቀው አባ ብሶይም እንዲህ ብሎ መለሰለት ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ወደኔ መጥቶ ይህ ታላቅ ክብር ለመነኰሳት እንዳላቸው አውቄ ቢሆን ኖሮ መንግሥቴን ትቼ መነኰስ በሆንኩ ነበር አለኝ እኔም ምን ጐደለብህ የጣዖትን አምልኮ አስወግደህ የቀናች ሃይማኖትን ሥልጣን አጽንተሃልና አልሁት። እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ እግዚአብሔር ይመስገን ክብርንስ እጅግ አብዝቶ ሰጥቶኛል ነገር ግን የመነኰሳትን ክብር ያህል አይሆንም እነርሱ በእሳት ክንፎች እየበረሩ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ሲገቡ አይቻቸዋለሁና አለኝ። እኔም እንዲህ አልሁት የእግዚአብሔር ፍርድ በእውነት ትክክል ነው ለእናንተ ቤቶች፣ ሚስቶችና ልጆች፣ ሀብትና ለዓለም የተዘጋጀው ሁሉ አሉአችሁ በእነርሱም ትጽናናላችሁ። መነኰሳት ግን ከዚህ ከተድላ ዓለም የተለዩና በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ ችግረኞች ናቸው ስለዚህም ይህን ታላቅ ክብር እግዚአብሔር ሰጣቸው አልሁት። በአንዲት ዕለትም እግዚአብሔር አባ ብሶይን እንዲህ ብሎ ተናገረው ይህን ገዳም እንደርግቦች ማደሪያ አደርገዋለሁ። በውስጡም መነኰሳትን እመላለሁ። ቅዱስ አባ ብሶይም ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ የበዙ ከሆነ ምግባቸውን ከወዴት ያገኛሉ አለው። ክብር ይግባውና ጌታችንም እኔ አስብላቸዋለሁ ምንም ምን እንዲአጡ አልተዋቸውም አለው። በሀገረ እንዴናው ስለሚኖር ስለ አንድ ገዳማዊ ሽማግሌ ተነገረ በትምህርቱ አምነው ወደ ርሱ ብዙ ሕዝቦች ተሰበሰቡ እርሱ መንፈስ ቅዱስ የለም ብሎ ተሳስቶ ነበርና። ብዙዎችም ተከትለውት ነበርና ቅዱስ አባ ብሶይም ይህን ነገር ሰምቶ ስለዚያ ገዳማዊ እጅግ አዘነ መስሚያውንም ሦስት ጆሮዎች አድርጎ ወደ ገዳመ እንዴናው ሔደ ከዚያ ገዳማዊ ሽማግሌ ጋራ ተገናኘ ብዙ ሕዝቦችንም በእርሱ ዘንድ አገኛቸው ሁሉም ለቅዱስ አባ ብሶይ ሰላምታ ሰጡት። መስሚያ ስለአደረጋቸው ስለ ሦስቱ ጆሮዎችም ጠየቁት እንዲህም አላቸው። ለእኔ ልዩ ሦስት አካላት አሉኝ ሥራዬ ሁሉ በእነርሱ አምሳል ነው በውኑ መንፈስ ቅዱስ አለን አሉት። ከብሉይና ከሐዲስ መጻሕፍትም ይተረጒምላቸው ጀመረ። ከሦስቱ አካላት አንዱ መንፈስ ቅዱስ እንደ ሆነ በመለኮትም አንድ እንደ ሆነ አብራራላቸው። ሁሉም ከስሕተት ተመልሰው ንስሓ ገቡ። ወደ ቀናች ሃይማኖትም ተመለሱ። ለአባ ብሶይም የዋህ ረድእ ነበረው የእጅ ሥራውንም ሊሸጥ በሔደ ጊዜ ከአሕዛብ ወገን አንድ ሰው አገኘ። ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የፅርፈት ቃልን እስከሚናገር ድረስ ከዕውነት መንገድ አሳሳተው። በተመለሰ ጊዜም በክርስትና ጥምቀት ያገኘው የልጅነት ክብር ከእርሱ እንደተለየው አባ ብሶይ ተመልክቶ ልጄ ሆይ በአንተ ላይ የደረሰው ምንድነው አለው። እርሱም ያ ሽማግሌ እንዳሳተው ነገረው አባ ብሶይም ስለርሱ ሰባት ቀን ሲጸልይ ሰነበተ በፍጻሜውም በክርስትና ጥምቀት የተሰጠው የመንፈስ ቅዱስ ልጅነት በርግብ አምሳል በላዩ ወርዶ በውስጡ ሲያድር አየ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም አመሰገነው። ረድኡንም እንዲጠነቀቅና የቀናች ሃይማኖቱን እንዲያጸና ልዩ ከሆነ ሰውም ጋር ስለ ሃይማኖት እንዳይነጋገር አዘዘው። የበርበር ሰዎችም ወደ አስቄጥስ ገዳም በመጡ ጊዜ ወደ እንዴናው ገዳም ሔዶ በዚያ ተቀመጠ ከዚህም በኋላ አረፈ። የመከራውም ወራት ጸጥ ባለ ጊዜ የቅዱስ አባ ብሶይን ሥጋ ከቅዱስ አባ ቡላ ሥጋ ጋር በአንድነት ወደ አስቄጥስ ገዳም አመጡ። ከሥጋውም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ ዘመኑ አምሳ ሰባት ነበር። በአስቄጥስም ገዳም እየተጋደለ ሀያ ሰባት ዓመት ኖረ። በእንዴናው ገዳም ዐሥር ዓመት ኖረ ከመመንኰሱም በፊት በዓለም ውስጥ ሃያ ዓመት ተቀመጠ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አቡነ_ኪሮስ_ጻድቅ
Show all...
🥰 2💯 2❤‍🔥 1🕊 1
🥰 11🙏 5❤‍🔥 4👏 3🎉 1
በዚችም ቀን የሮሜ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አግናጥዮስ በሰማዕትነት ሞተ፡፡ እርሱም ከቅዱስ ጴጥሮስ በኋላ በከሀዲው ንጉሥ በጠራብያኖስ ዘመን ሆነ። ይህም ንጉሥ ስለ አባት አግናጥዮስ የጣዖት አምልኮን እንደሚአቃልል ሕዝቡንም ሁሉ እንደሚያስተምር ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን እንደሚያስገባቸው በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ አስቀርቦ ለአማልክት መሥዋዕት አቅርብ አለው ቅዱሱም እኔ ለረከሱ ጣዖታት አልሠዋም ብሎ መለሰለት። ንጉሡም ብዙ ቃል ኪዳኖችን በመግባት አባበለው በአልተቀበለውም ጊዜ ለአንበሳ ሰጠው ያን ጊዜም ቅዱስ አግናጥዮስ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ሕዝቡን አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ አንዱ አንበሳ ቀርቦ አንገቱን ያዘው ያን ጊዜም ክብር ይግባውና በጌታችን እጅ ነፍሱን ሰጠ። ከዚህ በኋላ ያ አንበሳ ወደ ሥጋው አልቀረበም ምእመናንም መጥተው ሥጋውን ወሰዱ በመልካም ቦታም አኖሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
Show all...
❤‍🔥 5🥰 2😍 1
ተደሰቱ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ሌላው ያጋጠመው ክርክር ቢቱ ከተባለው ሰው ጋር ያደረገው ክርክር ነበር፡፡ ቢቱ ‹‹በምጽዓት ጊዜ የሚመጣው ወልድ ብቻውን እንጂ አብና መንፈስ ቅዱስ አይመጡም›› የሚል ኑፋቄ ማስተማር ጀምሮ ነበር፡፡ ቢቱ ከዚህ ኑፋቄው በተጨማሪ የጥንቆላ ሥራም ይሠራ ነበር፡፡ ቢቱ በጥንቆላ ሥራው የተነሣ በቤተ መንግሥቱ ተቀባይነት የነበረው ሰው ነበረ፡፡ ይህን መሰሉን ተግባር አጥብቆ የተዋጋው ዘርዐ ያዕቆብ እስኪመጣ ድረስ ነገሥታቱ ምንም ክርስቲያኖች ቢሆኑ በዚህ መሰሉ ስንኩል ሕፀፅ ይዋጡ ነበር፡፡ ቢቱና አባ ጊዮርጊስ ወደ ንጉሥ ዳዊት ቀርበው በጉዳዩ ላይ መነጋገር እንደሚፈልጉ ገለጡ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ጳጳሱና ሊቃውንቱ ባሉበት እንዲነጋገሩ ስለወሰነ ጳጳሱ እንዲመጡ አዘዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ተንኮለኛው ቢቱ ከአባ ጊዮርጊስ ጋር ከተከራከረ እንደሚሸነፍ ስላወቀ ‹‹ንጉሡ የአባቶቻችንን ሃይማኖት ክዷልና አትምጣ›› የሚል ደብዳቤ በአባ ጊዮርጊስ ስም ጽፎ ጳጳሱን ሊጠሩ በሄዱት መልእክተኞች እጅ ላከ፡፡ ወድያውም ለዐፄ ዳዊት ይህንን ነገር አሳበቀ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ፈጣን መልእክተኞች ልኮ የፊተኞቹ መልእክተኞች እንዲመለሱ አደረገና ደብዳቤው ተነበበ፡፡ የቢቱ ተንኮል ያልገባው ንጉሥ ዳዊት ይህን ደብዳቤ ሲመለከት አባ ጊዮርጊስን በደም እስኪነከር ድረስ እንዲደበደብ አድርጎ ወደ እስር ቤት አስገባው፡፡ ዐፄ ዳዊት እስኪሞትና ልጁ ቴዎድሮስ እስኪነግሥ ድረስም በዚያ ቆየ፡፡ ቢቱ ግን በመልአክ ተቀስፎ ሞተ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን በወኅኒ ቤት እያለ የከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ እየመጡ ያጽናኑት ነበር፡፡ ‹‹ውዳሴ ሐዋርያት›› የተሰኘውንና ከሐምሌ 5 ጀምሮ በ12ቱም ወራት የሚመሰገኑበት የሐዋርያትን ምስጋና የያዘውን መጽሐፍ ያዘጋጀው በወኅኒ ቤት ሆኖ ጴጥሮስና ጳውሎስ ከጎበኙት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ አንድ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ በእስር ላይ ሳሉ ንጉሡ ዐፄ ዳዊት መሞታቸው ተሰማ፡፡ ሰዎችም ወደ አባታችን መጥተው ‹‹ያሳሰረህ ንጉሥ ሞቷል›› በማለት ነገሩት፡፡ ይህንንም ተቻኩለው የነገሩት ያሰረው ንጉሥ መሞቱን ሲሰማ ይደሰታል ብለው ነበር፡፡ ነገር ግን አባ ጊዮርጊስ በታላቅ ሀዘን ውስጥ ሆኖ የሰጣቸው መልስ ‹‹አይ ንጉሡ ባይሞት እኔም እንደታሰርኩ ብቀር ይሻል ነበር፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትኮ እኔን ባይወደኝ የአምላክን እናት እመቤታችንን ይወዳት ነበር›› አላቸው፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ አባ ጊዮርጊስን ከወኅኒ ቤት አውጥቶት በጥንቱ ቦታ አስቀመጠው፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን የቤተ መንግሥትን ነገር ለመሸሽ ስለ ፈለገ በጋሥጫ ከመቀመጥ ይልቅ ርቆ ጥንት ወደ ነበረበት ወደ ዳሞት በመሄድ ማስተማር ጀመረ፡፡ ወደ ዳሞት ሲሄድ እግረ መንገዱን ወደ ደብረ ሊባኖስ ገብቶ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን መቃብር ተሳልሟል፡፡ በዚያ ጊዜ የደብረ ሊባኖሱ አበ ምኔት እጨጌ ዮሐንስ ከማ ነበሩ፡፡ እርሳቸውም ሰባተኛው የደብረ ሊባኖስ እጨጌ ነበሩ፡፡ አባ ጊዮርጊስን በዕውቀቱ የሚቀኑበት፣ በችሎታው የሚመቀኙት ሰዎች ነገር ሠርተው ከንጉሥ ቴዎድሮስ ጋር ስላጣሉት እልም ካለ በረሃ እንዲጋዝ ተደረገ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ከግዞት የወጣው ዐፄ ቴዎድሮስ ሲሞት ነበር፡፡ የአባ ጊዮርጊስ ሌላው ተማሪ የነበረው ዐፄ ይስሐቅ በ1399 ዓ.ም መንግሥቱን ሲይዝ አባ ጊዮርጊስን ከግዞት አውጥቶ ወደ ጋሥጫ መለሰው፡፡ በዚያ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ እድሜው 42 ዓመት ሲሆን በስደትና በጤንነት መታወክ የተነሣ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜውን በጾም፣ በጸሎትና በድርሰት ያውለው ነበር፡፡ አንድ ቀን ቴዎድሮስ የተባለ መስፍን፣ ዳግመኛም የጦሩ አዛዥ የሚሆን፣ አባ ጊዮርጊስን ስለ ርትዕት ሃይማኖት በጠየቀው ጊዜ አባ ጊዮርጊስም ‹‹ፍካሬ ሃይማኖት›› የተባለውን መጽሐፍ ደርሶ ሰጠው፡፡ ንጉሡና የምሥጢር ሊቃውንት የሆኑ ካህናት ይህንን በተመለከቱና ባነበቡ ጊዜ ‹‹በእውነት ዮሐንስ አፈወርቅና አፈ በረከት የሆነው ቄርሎስ በዘመናችን ተነሥተዋል፡፡ ኢትዮጵያም ቍስጥንጥንያን መስላለች፣ ከእስክንድርያም በላይ ከፍ ከፍ ብላለች›› ብለው አደነቁ፡፡ ይህም ፍካሬ ሃይማኖት የተሰኘው ድንቅ ድርሰቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታምነውንና የምታወግዘውን በግልጽና በዝርዝር የጻፈበት መጽሐፍ ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስ በፍካሬ ሃይማኖት ድርሰቱ ላይ የዘረዘራቸው የመናፍቃን ስሞችንና ክህደታቸውን ስንምለከት በዘመኑ የነበሩ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ስለ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያላቸውን ዕውቀት በግልጽ ያሳየናል፡፡ አባ ጊዮርጊስ መከራ ያልተለየው አባት በመሆኑ አሁንም በቤተ መንግሥት የነበሩ ሰዎች የእርሱን መከበርና መወደድ አይፈልጉትም ነበር፡፡ በተለይም ‹‹ፍካሬ ሃይማኖት›› የተሰኘውን መጽሐፍ በመጻፉ በዚህም ዝናው የበለጠ ስለተነገረ እነርሱ በሁሉም ዘንድ መከበሩን አልወደዱትም ነበር፡፡ ስለዚህም ነገር ሠርተው ከዐፄ ይስሐቅ ጋር አሁንም አጣሉት፡፡ ዐፄ ይስሐቅ አባ ጊዮርጊስን አሳስሮ ውኃ ወደማይገኝበት ዓለታማ ቦታ አጋዘው፡፡ በዚያም በመከራ ለብዙ ጊዜ ኖረ፡፡ በዚያ እያለ ዘወትር በጸሎት አብዝቶ ይተጋ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ዐፄ ይስሐቅ ወደ ልቡናው እንዲመለስ አደረገ፡፡ ንጉሡ በአባ ጊዮርጊስ ላይ የፈጸመው ነገር ሁሉ ስለፀፀተው አገልጋዮቹን ጠርቶ አባ ጊዮርጊስን እንዲያመጡት አዘዘ፡፡ ነገር ግን እነዚያ ተንኮል ሠሪዎች የአባ ጊዮርጊስ መምጣት ተንኮላቸውን ስለሚያጋልጠው ‹‹አባ ጊዮርጊስ ሞቷል›› ብለው አስወሩ፡፡ ይህንን ሲሰማ ዐፄ ይስሐቅ ፈጽሞ አዘነ፡፡ አባ ጊዮርጊስም ሞቷል እየተባለ መወራቱን ከደቀ መዝሙሩ ስለ ሰማ በሕይወት የመኖሩን ዜና ጽፎ ለዐፄ ይስሐቅ እንዲያደርስለት መልእክቱን በአውሎ ንፋስ አሳስሮ ላከለት፡፡ አውሎ ንፋሱ ለአባ ጊዮርጊስ በመታዘዝ ደብዳቤውን ተሸክሞ በመሄድ ዐፄ ይስሐቅ በድንኳን ተቀምጦ በነበረ ጊዜ ጉልበቱ ላይ አስቀመጠው፡፡ ንጉሡ ምትሐት የተሠራበት ስለመሰለው ደነገጠና መኳንንቱንና ሕዝቡን ሰብስቦ ጉዳዩን ገለጠ፡፡ ወዲያውም ነፋሱ ያመጣለትን መልእክት እሳት አስነድዶ ከዚያ ውስጥ ቢጥለው ሊቃጠል አልቻለም፡፡ ወደ ውኃም ቢጨምረው አልጠፋም፡፡ በዚህ ተደንቆ ወረቀቱን ከፍቶ አነበበው፡፡ ደብዳቤው ከአባ ጊዮርጊስ የተላከ መሆኑን ሲያውቅ ዐፄ ይስሐቅ ደነገጠ፡፡ እነዚያን መልእክተኞች ይዞ ወደ ወኅኒ ከጨመራቸው በኋላ አባ ጊዮርጊስን ከግዞት ያወጡት ዘንድ ላከ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሲመጣ ንጉሡ በደስታ ተቀብሎ ማረኝ ብሎ ለመነው፡፡ አባ ጊዮርጊስም ይቅር አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ደብዳቤውን በማን እጅ እንደ ላከው ጠየቀው፡፡ አባ ጊዮርጊስም ደብዳቤውን በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ በነፋስ እንደ ላከው አስረዳው፡፡ ከግዞት ከተመለሰ በኋላ እመቤታችን ተገልጣለት መከራው ሁሉ እንደ ሐዋርያት መሆኑን ገለጠችለት፡፡ አእምሮውን ብሩህ፣ ልቡናውን ትጉኅ የሚያደርግ እጅግ ብዙ ምሥጢርም ነገረችው፡፡ ተሰናብታው ከሄደች በኋላ ‹‹እጅግ ብዙ መብራት አቅርቡ አምስት ፈጣን ጸሐፊዎችንም አምጡ›› ብሎ አዘዘ፡፡ ከዚህም በኋላ እርሱ እየነገራቸው እነርሱ እየጻፉ እረፍት ሳያደርጉ ሦስት ቀን ሙሉ አጽፎ ‹‹መጽሐፈ ምሥጢር›› የተሰኘውን መጽሐፍ ፈጸመ፡፡ አምስቱ ጸሐፍትም የየድርሻቸውን አጠናቅቀው በአንድ አደረጉት፡፡ አባ ጊዮርጊስም ይህን ተመልክቶ በእጅጉ አደነቀ፡፡ ‹‹እኔ የዚህን መጽሐፍ ቃል አልተናገርኩም፤ መንፈስ ቅዱስ በእኔ አፍ ተናገረ እንጂ›› ሲል በወቅቱ መስክሯል፡፡ የመጽሐፉንም ስም ‹‹መጽሐፈ ምሥጢር›› ብሎ የሰየመው ራሱ ነው፡፡ የጻፈው
Show all...
🥰 4 1🕊 1😍 1
በ1409 ዓ.ም እድሜው 52 በደረሰ ጊዜ ሲሆን በወቅቱም የዚህ መጽሐፍ ቅጅ በነጋድያን እጅ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ሄዶ ነበር፡፡ ዐፄ ይስሐቅ ለአባ ጊዮርጊስ ‹‹ምድረ ሰዎን›› የተባለውን የጳጳሳት መቀመጫ የነበረውን ሀገር በርስትነት ሰጥቶት ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ በምድረ ሰዎን ንጉሥ ይስሐቅ ክረምቱን ያሳልፍበት በነበረው ቦታ ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠራ፡፡ በዚያም በማስተማርና በጾም በጸሎት ይተጋ ነበር፡፡ በጋሥጫ እያለ ዐፄ ይስሐቅ አስጠራው፡፡ በዚያ ጊዜ ንጉሡ የመናገሻ ማርያምን ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ ስለነበር እንዲባርክለት ፈልጎ ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ ምንም እንኳን በዚያ ጊዜ ታሞ የተኛም ቢሆን ወደ ንጉሡ ተጓዘ፡፡ እዚያ ሲደርስ በጣም ተዳክሞ ነበር፡፡ ሥርዓቱን ለመፈጸምም አቅም አልነበረውም፡፡ ስለዚህም ንጉሥ ይስሐቅ በአልጋ ተሸክመውት እንዲዞሩና ቤተ ክርስቲያኗን እንዲባርካት አድርጓል፡፡ ቡራኬውን ከፈጸመ በኋላ ደቀ መዝሙሮቹን ሰብስቦ ‹‹ከሞትኩ አባቴ በጸሎተ ሚካኤል መከራ ወደ ተቀበለባትና እኔም ቤተ ክርስቲያን ወዳነፅኩባት ቦታ ወስዳችሁ ቅበሩኝ›› ሲል አዘዛቸው፡፡ ለደቀ መዛሙርቱ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ የመጨረሻ የስንብት ትምህርቱን አስተማራቸው፡፡ እነርሱም በአልጋ ተሸክመውት ወደ ጋሥጫ እያመሩ ሳለ በመንገድ ላይ ሐምሌ 7 ቀን 1417 ዓ.ም በ60 ዓመቱ ዐረፈ፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አባ_ሲኖዳ ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ቅዱስ አባት የባሕታውያን አለቃ የሆነ መስተጋድል አባ ሲኖዳ አረፈ፡፡ ይህም ቅዱስ በግብጽና በአክሚም አውራጃ ስሟ ስንላል ከምትባል ሀገር ከላይኛው ግብጽ ነበር። ስለእርሱም የመላእክት አምሳል የሆነ አባ ሐርስዮስ ትንቢት ተናገረለት። እርሱም ስለ ገዳም አገልግሎት ከመነኰሳት ጋር ሲሔድ የዚህን የቅዱስ ሲኖዳን እናት ውኃ ለመቅዳት ወጥታ አገኛት። ወደርሷ ሒዶ ሦስት ጊዜ ራሷን ሳማትና እንዲህ አላት ዜናው በዓለሙ ሁሉ የሚሰማ የስሙ መዓዛ ከሽቱ የሚጥም የሆነ የሆድሽን ፍሬ እግዚአብሔር ይባርክ። እነዚያ መነኰሳትም በአዩት ጊዜ አድንቀው አባታችን አንተ የሴት ፊት ማየት ከቶ አትሻም ነበር ዛሬ ግን ከሴት ጋራ ትነጋገራለህ አሉት። ልጆቼ ሆይ ሕያው እግዚአብሔርን የእግዚአብሔርን ምሕረት ተስፋ የሚያደርግ ዓለሙ ሁሉ የሚጣፍጥበት ከዚች ሴት የሚወጣ የጨው ቅንጣት አለ አላቸው። አንድ በገድል የጸና ጻድቅ ሰው መነኰስ ነበረ እርሱም መልሶ አባ ሐርስዮስን እንዲህ አለው እግዚአብሔር ሕያው ነው አንተ ራሷን ትስም ዘንድ ወደዚያች ሴት በቀረብክ ጊዜ በእጁ የእሳት ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ በዙሪያዋ አየሁት። ራሷንም በሳምካት ጊዜ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጁ ሆይ ሰላምታ ይገባሃል ሲልህ ደግሞም ከዚች ሴት የሚወለደው የተመረጡ ቅዱሳንን ሁሉ ልባቸውን ደስ ያሰኛል ወልደ እግዚአብሔርም ከርሱ ጋር ብዙ ጊዜ ይነጋገር ነበር ሲል ሰማሁት አለ። በግንቦት ሰባት ቀን ይህ ቅዱስ አባ ሲኖዳ ተወለደ በአደገም ጊዜ አባቱ በጎች ስለነበሩት ለልጁ ለሲኖዳ እንዲጠብቃቸው ሰጠው ይህ ሲኖዳም ምሳውን ለእረኞች ሰጥቶ እስከ ማታ ድረስ ይጾም ነበር። በሌሊትም ከውኃ ዐዘቅት ውስጥ ወርዶ በዚያ ቁሞ እስቲነጋ ድረስ ሲጸልይ ያድር ነበር። በክረምትም ሆነ በቊር ሰዓት እንዲሁ ያደርግ ነበር። አባቱም የሲኖዳ እናት ወንድም ወደ ሆነው ወደ አባ አብጎል እጁን በላዩ ጭኖ ይባርከው ዘንድ ወሰደው። አባ አብጎልም በአየው ጊዜ የሕፃኑን እጅ አንሥቶ በራሱ ላይ አድርጎ ሲኖዳ ሆይ ባርከኝ ለብዙ ሕዝብ ታላቅ አባት ትሆን ዘንድ የሚገባህ ሁነሃልና አለው። አባቱም በአባ አብጎል ዘንድ ተወው። ከዕለታትም በአንዲቱ ቀን አባ አብጎል እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ ሰማ እነሆ ሲኖዳ ለዓለሙ ሁሉ አርሲመትሪዳ የባሕታውያን አለቃ ሁኖ ተሾመ። ይህም ሲኖዳ ለዓለሙ ሁሉ ብርሃን እስከሚሆን በበጎ አምልኮ ያለ ማቋረጥ በጾምና በጸሎት በስግደትና በመትጋት ታላቅ ተጋድሎ መጋደልን ጀመረ። ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን ለአባ አብጎል የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና የኤልያስን አስኬማ የሠለስቱ ደቂቅን ቆብና የመጥምቁ ዮሐንስን ቅናት አመጣለት። እንዲህም አለው እንድትጸልይና የምንኵስና ልብስ ለሲኖዳ እንድታለብሰው እግዚአብሔር አዝዞሃል። ያን ጊዜም አባ አብጎል ተነሥቶ ጸለየ የምንኵስና ልብስንም አለበሰው። ከዚህም በኋላ ተጋድሎውን አበዛ። ለመነኰሳት፣ ለመኳንንት፣ ለሕዝባውያንና ለሴቶች ለሰዎች ሁሉ መመሪያ የሚሆን ሥራትን ሠራ። በኤፌሶንም የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ስለ ከሀዲው ንስጥሮስ በተደረገ ጊዜ ከማኅበሩ አባት ከሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስ ጋራ ወደ ጉባኤው ሔደ ንስጥሮስም ከክህደቱ ባልተመለሰ ጊዜ አውግዘው ለይተው አሳደዱት። ከዚህ በኋላም ወደ ሀገራቸው በመመለሻቸው ጊዜ መርከበኞች ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋራ አትሳፈርም ብለው አባ ሲኖዳን ከለከሉት እርሱም ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ማለደ። ወዲያውኑም ደመና መጥታ ተሸከመችውና አባ ቄርሎስ በመርከቡ ውስጥ እያለ በበላዩ በአንጻሩ አደረሰችው። አባቴ ሆይ ሰላም ለአንተ ከአንተ ጋራ ላሉትም ይሁን ብሎ ሰላምታ አቀረበ። በመርከብ ያሉት ሁሉም ላንተም ሰላም ይሁን በጸሎትህም አትርሳን አሉት። እጅግም አደነቁ ለሚፈሩት ይህን ይህል ጸጋ የሚሰጥ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ወደ ገዳሙም ደርሶ ከልጆቹ መነኰሳት ጋራ የመንፈቀ ሌሊትን ጸሎት አደረገ። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ብዙ ጊዜ ወደርሱ እየመጣ ያነጋግረው ነበር። እርሱም የመድኃኒታችንን እግሩን ያጥበው ነበር እጣቢውንም ይጠጣ ነበር ጌታችንም ብዙ ምሥጢራትን ገለጠለት ትንቢቶችንም ተናገረ። ከዚህም በኋላ ፈጽሞ በአረጀ ጊዜ ሐምሌ ሰባት ቀን ተኛ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መጥቶ እያረጋጋው በእርሱ ዘንድ ተቀመጠ። ብፁዕ አባ ሲኖዳም ጌታችንን እንዲህ አለው ጌታዬ ፈጣሪዬ ልዩ ሦስትነትህንና ጌትነትህን ስለሚነቅፉ ከሀድያን ወደ ጉባኤው እሔድ ዘንድ እንዲጠሩኝ ሊቀ ጳጳሳቱ ወደ እኔ ልኳልና እንደቀድሞው ታጸናኛለህን። ጌታችንም በጸጋና በጥዑም ቃል እንዲህ ብሎ መለሰለት ወዳጄ ሲኖዳ ሆይ ሌላ ዕድሜ ትሻለህን። እነሆ ዕድሜህ ሁሉ መቶ ሃያ ዓመት ከሁለት ወር ሁኖሃል ዕድሜህ ዘጠኝ ዓመት ሲሆን አስኬማን ለበስኽ ከዚያ በኋላ መቶ ዐሥራ አንድ ዓመት ከሁለት ወር ኖርኽ አሁንስ ድካምህ ይብቃህ ይህንንም ብሎ ጌታችን በክብር ዐረገ። በዚያንም ጊዜም የቅዱሳን አንድነት ማኅበር ወደርሱ መጡ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ዳግመኛ አየው ልጆቹንም ክብር ይግባውና ለጌታዬ ለኢየሱስ ክርስቶስ እሰግድ ዘንድ አንሱኝ አላቸው አንሥተውትም ሰገደለት። ከዚህም በኋላ ዳግመኛ እንዲህ አላቸው ወደ እግዚአብሔር አደራ አስጠብቅኋችሁ ነፍሴም ከዚህ ከደካማው ሥጋዬ የምትለይበት ጊዜ ደርሷል እኔም ለአባታችሁ ለዊዳ እንድትታዘዙ አዝዛችኋለሁ ከእኔ በኋላ ጠባቂያችሁ እርሱ ነውና አላቸው። ለልጆቹም ይህን በተናገረ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመረጥሁህ ሲኖዳ ሆይ ብፁዕ ነህ ቸርነቴም ይደረግልሃል በሕይወትህ ዘመን ሁሉ አንተ የምወደውን ሥራ ሠርተሃልና እንግዲህ ወደ ዘለዓለም ተድላ ታርፍ ዘንድ ወደእኔ ና አለው። ያን ጊዜም ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_አግናጥዮስ
Show all...
ጌትነቱ በእርሱ ላይ ይገለጥ ዘንድ ነው እንጂ፡፡ ጸጋ ያለመከራ አይሰጥምና ያለመፈተንም ማብዛት አይቻልም፡፡ ጌታችንን ዕውር ሆኖ ስለተወለደው ሕፃን ደቀ መዛሙርቱ በጠየቁት ጊዜ ‹‹ይህ ሕፃን ዕዉር ሆኖ የተወለደው በማን ኃጢአት ነው? በራሱ ነውን ወይስ በወላጆቹ?›› አሉት፡፡ ጌታችንም ‹‹እርሱም አልበደለም፣ ወላጆቹም አልበደሉም፣ የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ ላይ ይገለጥ ዘንድ ነው እንጂ›› አላቸው፡፡ ዮሐ 9፡1፡፡ ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስ እስኪወርድላቸው ድረስ በትንሽ ዕውቀት ነበሩ፡፡ ‹‹በመጻሕፍት ያለውን ገና ዐላወቁምና›› ተብሎ እንደተጻፈ እንዲሁ አባ ጊዮርጊስም ዕውቀት ስለ ተሰወረውና ጓደኞቹ በትምህርት ሲቀድሙት ባየ ጊዜ እጅግ አዘነ፡፡ ስለዚህም በጾምና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር መጮኽ ጀመረ፡፡ ሁልጊዜም በሥዕለ ማርያም ሥር እየተንበረከከ ጥበብን እንዲሰጠው ወደ እግዚአብሔር አብዝቶ በመለመን እንባንም በማፍሰስ ይጸልይ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ እመቤታችን ተገለጠችለትና አረጋጋችው፡፡ ዳግመኛም እንደምትመጣ ቀን ቀጥራው ከእርሱ ተሰወረች፡፡ በሰጠችውም ቀጠሮ መሠረት በነሐሴ 21ኛው ቀን እመቤታችን ሚካኤልና ገብርኤል በቀኝና በግራ ሆነው ኪሩቤልንና ሱራፌልን አስከትላ ተገለጠችለትና «አይዞህ ዕውቀት የተሰወረብህ ትምህርት ስለማይገባህ ሳይሆን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ እንዲገለጥ ነው» አለችው፡፡ ‹‹የመረጥሁህ የልጄ ወዳጅ ጊዮርጊስ ብላ በስሙ ጠራችው፡፡ ከዕውቀት ወንዝ የመጣና ከጥበብ ምንጭ የተገኘ ከመለኮት ባሕር የተቀዳ ይህን ንጹሕ ጽዋ ንሣ ጠጣ›› በማለት ጽዋዓ ልቡናን አጠጣችው፡፡ ይኸውም ጽዋዕ ልቦና በዮሴፍ ቤት በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት የጠጡት መንፈሳዊና ሰማያዊ መጠጥ ነው፤ በበዓለ ሃምሳ ከጠጡት ያልተለየ ነው፡፡ ይኸውም የሚናገር እሳት፣ የሚያድን እሳት፣ መለኮታዊ እሳት ነው፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ያስጌጠበት የመጻሕፍትን ምስጢራት፣ የማኅሌትንና የድርሳናትን ቃል፣ ምስጋናዎችንም ሁሉ እመቤታችን ገለጠችለት፡፡ እመቤታችን ማርያም ለብፁዕ ጊዮርጊስ ጽዋውን ካጠጣችው በኋላ ያን ጊዜ አምስት የምሥጢር ቃላትን አስተማረችው፡፡ የኅሊናን ዓይኖች ያበራሉና የልቡናንም ጆሮዎች ይከፍታሉና፡፡ ከዚህ በኋላ ከእርሱ ተሰወረች፤ ከማይተኙ ከትጉሃን መላእክትም ጋር ወደ ሰማይ ዐረገች፡፡ የአምስቱ የምሥጢር ቃላት ትርጉምም ዕውቀትን የተመሉ መንፈሳውያን አባቶቻችን እንደ ነገሩን ከእመቤታችን ማርያም እጅ በተሰጠው በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ትምህርት ሳይማር በአንድ ቀን የዳዊትን መዝሙር ማጥናት ነው፡፡ መዝሙረ ዳዊትን ግን ዕብራውያን በአምስቱ የስሜት ሕዋሳት ቁጥር ለአምስት ከፍለውታል፡፡ እነዚህም መስማት፣ ማየት፣ ማሽተት መቅመስና፣ መዳሰስ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ክፍል መጨረሻው 40ኛው መዝሙር ነው፤ የሁለተኛው ክፍል መጨረሻው 71ኛው መዝሙር ነው፡፡ ሦስተኛው ክፍል መጨረሻው 88ኛው መዝሙር ነው፤ አራተኛው ክፍል መጨረሻው 105ኛው መዝሙር ነው፡፡ አምስተኛው ክፍል መጨረሻው 150ኛው ነው፡፡ የእነዚህም ክፍላት መጨረሻ ለይኩን ለይኩን ባለ ጊዜ ይታወቃል፡፡ አባ ጊዮርጊስም የእነዚህን ምስጢር በልቡ ጠበቃቸው፡፡ አምስቱንም ቃላት በልቡ መዝገብነት ሰወራቸው፤ ሊገልጣቸው እግዚአብሔር አልፈቀደላትምና በተረዳ ነገር ግን መዝሙረ ዳዊት ነው፡፡ የገነትን ፍሬዎች ሁሉ የሰበሰበ መዝሙረ ዳዊት የገነት አምሳል ነውና አጋንንትን ያሳድዳል መላእክትንም ያቀርባል፡፡ እመቤታችንም ከእርሱ ተለይታ ካረገች በኋላ ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ የልቡ ዓይን ተከፈተለት፡፡ ኅሊናውም በመንፈስ ቅዱስ ክንፎች ተመሰጠ፡፡ ወደ አብም ደረሰ፤ በዚያም ኢየሱስን በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ጰራቅሊጦስንም በአንድ አኗኗር አገኘው፡፡ ከዚህ በኋላ በሐይቅ እስጢፋኖስ የዜማ የቅኔና የመጻሕፍትን ትርጓሜ ትምህርቱን በሚገባ ተምሮ አጠናቀቀ፡፡ በዕውቀቱም ቀድሞ የሚያውቁት ሁሉ ይደነቁበት ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ የያሬድን ዜማ ከአቡነ ሳሙኤል ተማረ፡፡ በዚያ ዘመን በዐፄ ዳዊት አማካይነት በሰሜን ኢትዮጵያ የያሬድ ድጓ ዋና ማዕከል በሆነው በደብረ ነጎድጓድ ተሾሞ ያስተምር ነበር፡፡ የማስተማር ሥራውን የጀመረው በዚያው በሐይቅ እስጢፋኖስ ነበር፡፡ ከሐይቅ በኋላ በዚያ ዘመን ሸግላ በመባል ትጠራ ወደ ነበረችው ወደ ትውልድ ሀገሩ ወደ ጋሥጫ ተጓዘ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ወደ ሸግላ ሲመጣ አባቱ በጣም አርጅቶና መንኩሶ ነበር፡፡ ስለዚህም በአባቱ እግር ተተክቶ በቤተ መንግሥቱ ያለችውን ሥዕል ቤት እንዲያገለግል ወደዚያው አስገቡት፡፡ በቤተ መንግሥቱም የንጉሡን ልጆች ከማስተማሩም በላይ በቤተ መንግሥቱ ዙርያ ከነበሩት ሊቃውንት መካከል አባ ጊዮርጊስ አንዱ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ግብፃዊው ጳጳስ አቡነ በርተሎሜዎስ “ሥላሴን አንድ ገጽ” ብለው ያምናሉ ተብለው በተከሰሱ ጊዜ ነገሩን እንዲያጣሩ ከተመረጡት ከቄስ ሐፄ ተከሥተ ብርሃንና ከሐይቁ መምህር ከዐቃቤ ሰዓት ዮሴፍ ጋር አብሮ ተልኮ ነበር፡፡ እነዚህ ሦስት አበው ጳጳሱን ካነጋገሩ በኋላ ክሱ ውሸት መሆኑን በማረጋገጥ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የሚገልጠውን የጳጳሱን እምነት በጽሑፍ ይዘው መጡ፡፡ በቤተ መንግሥቱ በነበረ ጊዜ የንጉሡን ልጆች ይስሐቅን፣ ቴዎድሮስን፣ እንድርያስን፣ ሀብተ ኢየሱስን፣ ሕዝቅያስን፣ ኢዮስያስን፣ ዘርዐ ያዕቆብንና ሴት ልጁን እሌኒን በምግባርና በሃይማኖት ቀርጿቸዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ዘርዐ ያዕቆብ በድርሰቱ ሲመስለው ቴዎድሮስ ደግሞ በሕይወት መስሎታል፡፡ ዐፄ ዳዊት የአባ ጊዮርጊስን ሊቅነትና መልካም ሥነ ምግባር በሚገባ ስላወቀ በጋብቻ ሊዛመደው ወዶ ስለነበር ልጁን እንዲያገባ ዘወትር ይጠይቀው ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን በድንግልና ጸንቶ ለመኖር እንደሚፈልግ ከመግለጽ አልተቆጠበም፡፡ የዐፄ ዳዊት ጥያቄ ስለበዛበት ወደ አቡነ በርተሎሜዎስ ሄዶ ቅስናን ከተቀበለ በኋላ ወዲያው መነኮሰ፡፡ ከመነኮሰ በኋላ ወደ ሸግላ በመምጣት ለነገሥታትና በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ካህናት እንዲሁም በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ታላላቆች፣ ለንቡራነ እድና ለመኳንንት፣ ለመሳፍንትና በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ባለሟሎች ሁሉ መምህር ሆነ፡፡ አባ ጊዮርጊስ በሸግላ በነበረ ጊዜ በወባ በሽታ ታምሞ ሊሞት ደርሶ ነበር፡፡ ታምሞ በነበረ ጊዜ አንድ ሌሊት የከበሩ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ተገልጠውለት ‹‹ከእኛ ጋር ትኖር ዘንድ ልንወስድህ መጣን›› አሉት፡፡ እርሱም ‹‹የድርሰት ሥራዬን ሳልሠራና እግዚአብሔርንም አብዝቼ ሳላመሰግነው አሁን አትውሰዱኝ›› ሲል ለመናቸው፡፡ እነርሱም ልመናውን ተቀብለውት ከሕመሙ ፈውሰውት ሄዱ፡፡ ለዚህም ነው ከበሽታው እንደ ተፈወሰ ወድያው የድርሰት ሥራውን የጀመረው፡፡ የመጀመርያ መጽሐፉን ጽፎ እንደ ጨረሰ ጠፍቶበት ነበር፡፡ በማግሥቱ በዚያው ላይ ሊጨምር በወደደ ጊዜ የተጻፈበት ጥራዝ ቀለሙ ጠፍቶ ነጭ ሆኖ አገኘው፡፡ ስለዚህም የተሰረቀ መስሎት ልቡ አዘነ፡፡ የተስተካከሉ ጥራዞችንም በቈጠረ ጊዜ ደኅና ሁነው አገኛቸው ሁለተኛም በድጋሚ ጻፈ፡፡ በማግሥቱም እንደ መጀመሪያው ነጭ ሁኖ አገኘው እስከ ሦስትና ዐራት ቀንም እየተደጋገመ እንዲሁ ሆነ፡፡ ከዚህ በኋላ አባታችን ወደ እመቤታችን ይጸልይ ጀመረ፡፡ ‹‹ይህ የሆነ በኃጢአቴ ነውን? ወይስ አይደለም? ግለጭልኝ›› አላት፡፡ አንድ ቀንም በሌሊት እኩሌታ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለጸሎት ሲሄድ እመቤታችን በድንገት በማይነገር ክብር ለጊዮርጊስ ተገለጠችለት፡፡ ከእርሷም ጋር የቅዱሳን ማኅበር ሁሉ ነበሩ፡፡ በእጇም ከፀሐይና ጨረቃ የበለጠ የሚያበራ መጽሐፍን ይዛ ነበር፡፡ ጊዮርጊስም
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.