cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

✝️📯•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•🍁☪️

ሰላም ይብዛላቹ🙌 ይሄ ቻናል የተከፈተው #ክርስቲያናዊ፟_አስተምሕሮ ለማስተማር እና የ#እስልምናን የስህተት አስተሳሰብ እና አመለካከትም በዚህ ቻናል ላይ ለመቀየርና ለማስተማር እንሞክራለን ። 💬አስታየት ካላቹ በዚ ያስቀምጡ https://t.me/ewnet_ewnetun_bot 🪐 ወንጌል ለአለም ሁሉ 🌍 👇ይሄን 1ጊዜ በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ👇

Show more
Advertising posts
11 252
Subscribers
-1124 hours
-177 days
+52430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

  • File unavailable
  • File unavailable
THE LORD JESUS CHRIST: FULLY MAN AND FULLY GOD
Show all...
the_lord_jesus_christ_fully_man_and_fully_god_ebook_3.86mb.pdf3.86 MB
The-Person-of-Christ-Grudem-.pdf1.08 MB
4👍 1👏 1🎉 1
New Video፦ Did Jesus Rise From the Dead? ⭐️ ከአለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ክስተቶች መካከል አንደኛውና እውቁ ክስተት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ እውን ነውን? https://youtu.be/Xy1ihwaER3s ተጭኗል ሼር ይደረግ።🎉
Show all...
👍 7
ከላይ ያለውን ርዕስ እየመረጣችሁ ቻናላችን ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር ማድረግ እኛን ያግዙንቴሌግራማችን@Yeshua_Apologetics_Ministry ዩቱዩባችንhttps://youtu.be/AUtzBU5M2iY?si=4I-xFAC41Sld0VBG ተባረኩ።
Show all...
6
⚜️ ኢየሱስ ፍፁም አምላክ እና ፍፁም ሰው ነው
👉🏻 ኢየሱስ እንደ ፍፁም አምላክ ነው
1. የዮሐንስ ወንጌል 1:1-14
ዮሐንስ 1 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ² እርሱም በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ። ³ ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ ከተፈጠረው ሁሉ ያለ እርሱ የተፈጠረ ምንም የለም። ⁴ ሕይወት በእርሱ ነበረች፤ ይህች ሕይወት የሰው ብርሃን ነበረች። ⁵ ብርሃንም በጨለማ ያበራል፤ ጨለማውም አላሸነፈውም። ⁶ ከእግዚአብሔር የተላከ ዮሐንስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ። ⁷ ሰዎች ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ፣ ስለ ብርሃን ምስክር ሆኖ ለመቆም መጣ፤ ⁸ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ እርሱ ራሱ ብርሃን አልነበረም። ⁹ ለሰው ሁሉ ብርሃን ሰጪ የሆነው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም እየመጣ ነበር። ¹⁰ እርሱ በዓለም ውስጥ ነበረ፤ ዓለም የተፈጠረው በእርሱ ቢሆንም እንኳ፣ ዓለም አላወቀውም። ¹¹ ወደ ራሱ ወገኖች መጣ፤ የገዛ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም፤ ¹² ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው። ¹³ እነዚህም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፣ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም። ¹⁴ ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም አደረ፤ እኛም ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ ልጅን ክብር አየን።
- የዮሐንስ ወንጌል መክፈቻ ኢየሱስን “ቃል" (ሎጎስ) በማለት ይገልፀዋል ፣ ይህም መለኮታዊ ማንነቱን እና ዘላለማዊ ህልውናውን ለማጉላት ነው። ዮሐንስ 1:14 ከዚያም ይህ መለኮታዊ ቃል የኢየሱስን ሥጋ መገለጥ አጉልቶ የሚያሳይ ሥጋ መሆኑን ይገልጻል። ✅ ይህ ክፍል ኢየሱስ ዘላለማዊ፣ አስቀድሞ የነበረ እና መለኮታዊ ነው የሚለውን እምነት ያጎላል፣ ነገር ግን የሰውን መልክ ለብሷል። 2. ቆላስይስ 2፡9
“የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል በእርሱ ይኖራልና፤” — ቆላስይስ 2፥9 (አዲሱ መ.ት)
- ይህን ክፍል ጳውሎስ የክርስቶስን ልዕልና እና በቂነት እንዲያረጋግጡ ለቆላስይስ ሰዎች ጽፏል። የእግዚአብሄር ሙላት ሁሉ በክርስቶስ በአካል እንደሚኖር አጠናክሮም ይናገራል። ✅ ይህ ኢየሱስ ፍፁም መለኮት መሆኑን እና መለኮታዊ ባህሪው በሰው አካል ውስጥ ሙሉ በሙሉ መኖሩን መረዳትን ይደግፋል። 3. ዕብራውያን 1፡3
“እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራ ቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዞአል፤ የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።” — ዕብራውያን 1፥3 (አዲሱ መ.ት)
- የዕብራውያን ጸሐፊ ወልድ በነቢያትና በመላእክት ላይ ያለውን የበላይነት ገልጾ መለኮታዊ ባሕርይውንና በፍጥረትና በሲሳይ ላይ ያለውን ሚና ያረጋግጣል። ✅ ይህ ጥቅስ የኢየሱስን ፍፁም አምላክነት ፅንሰ-ሀሳብ ያጠናክራል፣ የእግዚአብሔር ማንነት ትክክለኛ መግለጫነቱን እና ፍፁም መለኮታዊነቱን በኃይለኛው ቃሉ ይደግፋል።
👉🏻 ኢየሱስ ፍጹም ሰው ነው
1. ፊልጵስዩስ 2፡6-8
ፊልጵስዩስ 2 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቈጠረውም፤ ⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ፣ በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ፤ ⁸ ሰው ሆኖ ተገልጦም፣ ራሱን ዝቅ አደረገ፤ እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።
- በዚህ መልእክት፣ ጳውሎስ የፊልጵስዩስ ሰዎች እንደ ክርስቶስ ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖራቸው መክሯቸዋል፣ ምንም እንኳን መለኮት ቢሆንም፣ ራሱን ያዋረደ፣ ሰው በመሆን እና በመስቀል ላይ ለሞት መታዘዙን ይገልጻል። ✅ ይህ ክፍል የኢየሱስን ትህትና እና ሰውነት አጉልቶ ያሳያል፣ ይህም የሰውን መልክ ለብሶ የሰው ህይወት እና ሞት እንደተካፈለ አበክሮ ይናገራል። 2. ዕብራውያን 2፡17
“ስለዚህ በሁሉም ነገር ወንድሞቹን መምሰል ተገባው፤ ይህንም ያደረገው መሓሪና ታማኝ ሊቀ ካህናት ሆኖ እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለሕዝቡ የኀጢአትን ስርየት ለማስገኘት ነው።” — ዕብራውያን 2፥17 (አዲሱ መ.ት)
- ጸሐፊው ኢየሱስ ፍጹም ሰው መሆን ያለበት ለምን እንደሆነ ሲገልጽ እንደ መሐሪ እና ታማኝ ሊቀ ካህናት ሆኖ ለሰዎች ኃጢአት የሚያስተሰርይበትን ሚና በማጉላት ነው። ✅ ይህ ጥቅስ ኢየሱስ የክህነት ሚናውን ለመወጣት እና ስርየትን ለመፈጸም ፍፁም ሰው መሆን እንዳለበት ያብራራል፣ ይህም ፍፁም ሰውነቱን ያሳያል። 3. 1 ጢሞቴዎስ 2:5
“አንድ እግዚአብሔር አለና፤ ደግሞም በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አንድ አስታራቂ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5 (አዲሱ መ.ት)
- ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ሲጽፍ፣ ኢየሱስ በእግዚአብሔርና በሰው ልጆች መካከል አስታራቂ ሆኖ የሚጫወተውን ልዩ ሚና አስረግጦ ለሰብዓዊ ተፈጥሮው አጽንዖት ሰጥቷል። ✅ ይህ ጥቅስ ኢየሱስ ሰው የመሆኑን አስፈላጊነት የሚያጎላ በእግዚአብሔርና በሰው ልጆች መካከል መካከለኛ ሆኖ እንዲኖር፣ ይህም በእግዚአብሔር ፊት የሰው ተወካይ ሆኖ የሚጫወተውን ሚና በማጉላት ነው።
❗ ኢየሱስ እንደ ፍፁም አምላክ እና ፍጹም ሰው ነው
#HALWOT5     ❍━〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️━❍           🪐 ወንጌል ለአለም ሁሉ 🌍              ⚠️ሼር ያድርጉ ‼️     ✞●▬▬▬๑۩✞ ◒ ✞۩๑▬▬▬▬●✞  ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━      ✞●▬▬๑۩✞    ✞۩๑▬▬●✞                      ◒◒◒◒◒◒◒                          ◒◒◒◒                   🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺                              🎯     ♡         ❍ㅤ      ⎙ㅤ  ⌲          ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃ🔺
Show all...
👍 4 4👏 2🥰 1
.               〰️ የውርስ ኃጢአት 〰️                     〰️ᴏʀɪɢɪɴᴀʟ sɪɴ                       〰️〰️     〰️〰️ 👳‍♂️የሙስሊም ኡስታዞች ስህተት ለ 👳‍♂️አቡ ሐይደር የተሰጠ መልስ                  📖  ክፍል ❸ 📕 👳‍♂️አቡ ሐይደር፡-ሰው በአላህ እገዛ ያንን ውስን ኃይሉንና ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ፡ ጌታው ያዘዘው ቦታ ላይ ሲገኝ፡ ስራው ‹‹ጽድቅ›› ሆኖ ይቆጠርለታል፡፡ ካልሆነም በሸይጧን ቅስቀሳ የተሰጠውን ውስን ኃይልና ነጻ ፈቃድ ተጠቅሞ፡ አላህ የከለከለው ቦታ ሲገኝ፡ ስራው ‹‹ኩነኔ›› ሆኖ ይቆጠራል፡፡ በጥቅሉ ኸይርና ሸር (ጽድቅና ኩነኔ) ተግባራት የነጻ ፈቃድ ውጤቶች ናቸው፡፡ የመረጠውን መልካም ነገር ለመተግበር ነጻ ፈቃድ የሌለው ሆኖ በግዳጅ የሚፈጽም አካል እንዴት ስራው የተመሰገነ ይሆናል? ደግሞስ የተከለከለውን ነገር ጠልቶ ለመራቅ ፈቃድ የሌለው ሆኖ በግዳጅ የሰራ ሰው እንዴት በስራው ሊኮነን ይችላል? በኢስላም አስተምህሮት መሰረት፡ ሃይማኖታዊ ስርአቶች በጠቅላላ የሚያናግሩት ነጻ ፈቃድ ያለውን አካል ነው፡፡ ስለዚህ ኃጢአትም ሆነ የጽድቅ ተግባር በውርስ የሚተላለፍ ንብረት ወይም ልክፍት ሳይሆን፡ በገዛ ራሳችን ድክመት፡ በዕውቀት ማነስ፡ በኢማን አለመጎልበት፡ በሸይጧን አታላይነት…ሰበብ የምንፈጽመው ተግባር ነው፡፡ ✅መልስ፡-➡️ነፃ ፈቃድ ይህን ያህል ቦታ ካለውና ያለ ነፃ ፈቃድ እስልምና ትርጉም አልባ ከሆነ ቀደም ሲል የጠቀስናቸው የቁርአንና የሐዲስ አንቀፆች ሐሰት ሊሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ከሁለት አንዱን መምረጥ ግድ ይላል፡፡ እስላማዊ መጻሕፍት ቅድመ ውሳኔን አጥብቀው የሚያስተምሩ ሆነው ሳሉ አቡ ሐይደር ሙግቱን በሰው ነፃ ፈቃድ ላይ መመሥረቱ አስገራሚ ነው፡፡ ➡️ሰው ከኃጢአት ዝንባሌ ጋር መወለዱና የኃጢአትን ውጤት መውረሱ በክርስቲያናዊም ሆነ በእስላማዊ መጻሕፍት የተረጋገጠ በተፈጥሮም ደግሞ የሚታይ ጉዳይ በመሆኑ ማስተባበል አይቻልም፡፡ የዘመናችን ሙስሊሞች የውርስ ኃጢአትን መካዳቸው በተፈጥሮ ከሚታያው እውነታ ጋር ብቻ ሳይሆን ከቅዱሳት መጻሕፍታቸውም ጭምር ያጋጫቸዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል ቁርአን እንዲህ ይላል፡- 📖“ከርሷም ሰይጣን አዳለጣቸው በውስጡም ከነበሩበት (ድሎት) አወጣቸው፡፡ «ከፊላችሁም ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ውረዱ፤ ለናንተም በምድር ላይ እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ መርጊያና መጣቀሚያ አላችሁ» አልናቸው፡፡ አደምም ከጌታው ቃላትን ተቀበለ፡፡ በርሱ ላይም (ጌታው ጸጸትን በመቀበል) ተመለሰለት፤ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ «ሁላችሁም ኾናችሁ ከርሷ ውረዱ፡፡ ከኔም የኾነ መመሪያ ቢመጣላችሁ ወዲያውኑ መመሪያዬን የተከተለ ሰው በነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም» አልናቸው፡፡” (ሱራ 2፡36-38)፡፡ ✅በዚህ ጥቅስ ውስጥ የሚገኘው “ሁላችሁም” የሚለው በአረብኛ ከሁለት በላይ ቁጥርን የሚያመለክት ሲሆን ፍርዱ በአዳምና በሔዋን ብቻ ያልተወሰነ መሆኑን ያሳያል፡፡ (Tafsir Ibn Kathir, Abridged: part 1, Surah Al-Fatiah Surah Al-Baqarah, ayat 1 to 141, pp. 109-110) አላህ የአዳምን ንስሐ እንደተቀበለ ተነግሯል ነገር ግን ከገነት መባረሩ አላህ ኃጢአቱን ይቅር እንዳላለ ያሳያል፡፡ ኃጢአቱን ይቅር ቢለው ኖሮ ለምን ወደ ገነት አልመለሰውም ነበር? ፀፀቱን ተቀብሎ ኃጢአቱን ይቅር ከማለት ይልቅ ፀፀቱን ተቀብሎ ወደ ፊት ለዘሮቹ የሚሆን መመርያን ለመስጠትና ይህንን መመርያ የተከተለውን ሰው ብቻ ለመማር እንደወሰነ ከጥቅሱ እንረዳለን፡፡ ይህ የቁርአን ጥቅስ የሰው ልጆች የአዳምን የኃጢአት ውጤት መውረሳቸውን በማረጋገጥ ክርስቲያናዊውን “የውርስ ኃጢአት” እሳቤ ይደግፋል፡፡ ሳሂህ ሙስሊም “ከገነት ያስባረራችሁ የአባታችሁ የአደም ኃጢአት ነው” በማለት ይህንኑ ሐሳብ ያጸናል፡፡ (Sahih Muslim, Book 001, Number 0380) ➡️ቲርሚዚ ሐዲስ የአዳም ክፉ ባሕርይ ወደ ዘሮቹ ሁሉ መዛመቱን እንዲህ በማለት ይገልፃል፡- 📖“አደም ስለ ካደ ዘሮቹ ሁሉ ካዱ፡፡ አደም ዝንጉ በመሆን የተለከለከለውን ዛፍ ስለበላ ዘሮቹም ዝንጉዎች ሆኑ፡፡ አደም ስለተሳሳተ ዘሮቹ ሁሉ ስህተት ፈፀሙ፡፡” (Al-Tirmidhi Hadith, Number 37; (ALIM CD ROM Version)) 📖አል-ቡኻሪ ደግሞ ሙሴ አዳምን “ከገነት እንድንባረር ያደረከን አንተ አባታችን ነህ” በማለት በወቀሰው ጊዜ አዳም መልሶ “አላህ ከመፈጠሬ ከአርባ ዓመታት በፊት ወስኖልኝ ለጻፈብኝ ነገር ትወቅሰኛለህን?” በማለት እንደመለሰለት ዘግቧል፡፡ (Sahih al-Bukhari, Volume 8, Book 77, Number 611) 📖ሳሂህ ሙስሊም “ከገነት ያስባረራችሁ የአባታችሁ የአደም ኃጢአት ነው” ይላል፡፡ (Sahih Muslim, Book 001, Number 0380)እስላማዊ ምንጮች ከዚህም አልፈው ሴቶች “እስከዛሬ ድረስ ለሚያሳዩት ጸባይ” ሔዋንን ተጠያቂ ያደርጋሉ፡- 📖“አቡ ሁራይራ እንዳስተላለፈው ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፡- በእስራኤል ልጆች ምክንያት ባይሆን ኖሮ ሥጋ ባልበሰበሰ ነበር፡፡ በሐዋ ምክንያት ባይሆን ኖሮ የትኛዋም ሴት ባሏን ባልከዳች ነበር፡፡” (Sahih al-Bukhari, Volume 4, Book 55, Number 611. Sahih Muslim Book 008, Number 3472) ➡️በተጨማሪም አል-ጠበሪ የተሰኘ ጥንታዊ ሙስሊም ጸሐፊ ሴቶች የወር አበባ የሚፈስሳቸውና “በአስተሳሰብ ደካማ የሆኑት” በሔዋን ምክንያት እንደሆነ ጽፏል፡፡ (ክርስትና እንደ እስልምና ሴቶች በአስተሳሰብ ደካሞች መሆናቸውን አያስተምርም፡፡) (The History of Al-Tabari: General Introduction from the Creation to the Flood, Translated by Franz Rosenthal, SUNY press, Albany, 1998, Volume 1, pp. 280-281) ✅እነዚህ ሁሉ ማስረጃዎች እንደሚያረጋግጡት እስላማዊ መጻሕፍት ስለ ውርስ ኃጢአት ከመጽሐፍ ቅዱስ ባልተናነሰ ሁኔታ ያስተምራሉ፡፡ 📣ሙስሊም ሰባኪያን የገዛ መጻሕፍታቸውን ማጥናት ያስፈልጋቸዋል፡፡   አስተማሪ ስለሆነ #ለ10 ወዳጅዎ ያጋሩ ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️           🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩       🔶 ⏰🍃✨ይ🀄️ጥላል⏰🔶         ┗━━━━━•🟩🟩•━━━━━┛ for any comment 😀 @ewnet_ewnetun_bot                   ewnetlehulu.net            🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥           🪐  ወንጌል ለአለም ሁሉ  😀                  🚨 ሼር ያድርጉ 🚨     ✞●▬▬▬๑۩✞ ◒ ✞۩๑▬▬▬▬●✞  ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━           ✞●▬▬▬๑۩✞    ✞۩๑▬▬▬▬●✞                        ◒◒◒◒◒◒◒                             ◒◒◒◒                   🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺                              🎯     ♡         ❍ㅤ      ⎙ㅤ  ⌲         ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃ🔺
Show all...
4💯 4 2 1👍 1👏 1
. 🎲ውድድር ተጀምረዋል🏅 ለአሸናፊ ከ 1000-500 ብር ያሸልማል🏆 ለ50 ሰው ብቻ ነው ቶሎ ይጀምሩ ቅዳሜ ያበቃል ቶሎ በሉ እና ጀምሩ ውድድሩን ለማሸነፍ ቀላል ነው Step 1 touch this link ➥https://t.me/Habesha_433_cashbot?start=r07968406374 Step 2 የሚመጣላቹ ቻናል መቀላቀል step 3 Referral Link የሚለውን መጫን 🏆ከዛም ውድድር ውስጥ ገብታቹሀል🏆 ይፍጠኑ https://t.me/Habesha_433_cashbot?start=r07968406374
Show all...
ለ 12ኛ ክፍል (EUEE) ተፈታኝ ተማሪዎች! የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆናችሁ እና ሀገራዊ ፈተና የምትወስዱ ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች ሁሉ መልካም ፈተና ይሁንላችሁ!... እግዚአብሔር አምላክ፦ ▸ የልፋታችሁን ውጤት በፍሬአማነት ይባርክላችሁ፤ ▸ አይምሮአችሁን በማስተዋል በጥበብ ይባርክላችሁ፤ ▸ በምትሄዱበት ዩኒቨርሲቲ ጥበቃው አይለያችሁ፤ ▸ በምትሄዱበት ቦታ በጤንነት ይባርካችሁ፤ ▸ የእናንተን በዛ ስፍራ መገኘት ያልወደደን ጠላት በእጁ ይቅጣላችሁ፤ ▸ በምትገቡ በምትወጡበት ስፍራ ሞገስ ይሁናችሁ፤ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር አብሮነት ፣ ማፅናናት ፣ መገኘትና ጥበቃው አይለያችሁ! ድል አድራጊው ጌታ ከፊታችሁ ይቅደም! አሜን! በድጋሚ መልካም ፈተና! መልካም ነገር የምትሰሙበት እና የምታዩበት እንዲሆን ተመኘሁ ! በድል ተመለሱ! ተባርካችኃል!🙌    12 ክፍል ተማሪዎች አድርሱልን         〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️       🪐 ወንጌል ለአለም ሁሉ 🌍 ᴄʜᴀɴɴᴇʟ    ✞●▬▬▬๑۩✞ ◒ ✞۩๑▬▬▬●✞  ━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━ ━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━ ━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━         ✞●▬▬▬๑۩✞    ✞۩๑▬▬▬●✞                      ◒◒◒◒◒◒◒                          ◒◒◒◒                   🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺                              🎯     ♡         ❍ㅤ      ⎙ㅤ  ⌲         ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃ🔺   
Show all...
🍁📯•ʀᴇᴠɪᴠᴀʟᵀᶜ•🍁📯

. 🌼 በዚህ ቻናል🌼 🌺አጫጭር_አስተማሪ videoዎች🎥 🌺መንፈሳዊ_ግጥሞች✍️ 🌺መንፈሳዊ_ትምህርቶች 🌺መንፈሳዊ_መጽሐፍት📖 🌺የመድረክ_worship📡 🌺መንፈሳዊ ልብወለድ📚 🌺ድራማ 🌺መነባን 🌺መዝሙሮች 🌺TikTok_ወዘተ.... ያገኛሉ 🔰ለማስታወቂያ ስራ @Pentecost_D Second channel

https://t.me/+tFh_sHVyX8E2M2M8

👇ይሄን

🙏 25 4 2👏 2🕊 2👍 1
.               〰️ የውርስ ኃጢአት 〰️                     〰️ᴏʀɪɢɪɴᴀʟ sɪɴ                       〰️〰️     〰️〰️ 👳‍♂️የሙስሊም ኡስታዞች ስህተት ለ 👳‍♂️አቡ ሐይደር የተሰጠ መልስ                  📖  ክፍል ❷📕 ➡️👳‍♂️አቡ ሐይደር፡-በዚህ ፍቺ ከተስማማን፡ በውስጡ አንድ የምናገኘው ቁም ነገር ይኖራል፡፡ እሱም፡– ነጻ ፈቃድ የሚባለው ዋናው ቁልፍ!፡፡ ጌታ አላህ ፈጽሙ ብሎ ያዘዘንን ነገር፡ ለመፈጸምም ሆነ ለመተው የሚያስችል ውስን ኃይልና ፈቃድ ሊኖረን ግድ ነው፡፡ በተቃራኒው አታድርጉ በማለት የከለከለንን ነገር፡ ለመተውም ሆነ ለመዳፈር የሚያስችለን ፈቃድና ውስን ኃይል ሊኖረን ይገባል፡፡ ትእዛዝና እቀባ ፈቃድ አልባ ለሆነ አካል ትርጉም የሌሽ ነውና፡፡ ወደ ታች ይጓዝ የነበረውን ወንዝ፡– ወደ መጣህበት ተመለስ! ማለት ይቻላልን? ➡️መልስ፡-በኃጢአት ትርጓሜ ውስጥ ነፃ ፈቃድ ዋናው ቁልፍ ከሆነ የእስልምና “ቀዳ ወል ቀድር” አስተምህሮ ውኀ ሊበላው ነው፡፡ እስልምና ሁሉም ነገር በቅድመ ውሳኔ እንደሚመራ ያስተምራል፡- 📖ሱራ 10፡100 “ለማንኛዋም ነፍስ በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ ልታምን (ችሎታ) የላትም፡፡ (አላህ ለከፊሎቹ እምነትን ይሻል)፡፡ በእነዚያም በማያውቁት ላይ ርክሰትን ያደርጋል፡፡” 📖ሱራ 2:6 “እነዚያ የካዱት (ሰዎች) ብታስፈራራቸውም ባታስፈራራቸውም በነርሱ ላይ እኩል ነው፤ አያምኑም፡፡ አላህ በልቦቻቸው ላይ በመስሚያቸውም ላይ አትሞባቸዋል፤ በዓይኖቻቸውም ላይ መሸፈኛ አልለ፤ ለነሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡” 📖ሱራ 4:88 “በመናፍቃንም (ነገር) አላህ በስራዎቻቸው ወደ ክሕደት የመለሳቸው ሲሆኑ ሁለት ክፍሎች የሆናችሁት ለናንተ ምን አላችሁ? አላህ ያጠመመውን ልታቀኑ ታስባላችሁን? አላህም ያሳሳተውን ሰው ለርሱ መንገድን ፈጽሞ አታገኝለትም።” 📖ሱራ 5:18 “ይሁዶችና ክርስቲያኖችም እኛ የአላህ ልጆችና ወዳጆቹ ነን አሉ። ታዲያ በኀጢአቶቻችሁ ለምን ያሰቃያችኋል? አይደላችሁም እናንተ ከፈጠራችሁ ሰዎች ናችሁ፣ በላቸው፤ ለሚሻው ሰው ይምራል፤ የሚሻውንም ሰው ይቀጣል፤ የሰማያትና የምድርም በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ንግሥና የአላህ ብቻ ነው። መመለሻም ወደርሱ ብቻ ነው።” 📖ሱራ 5:40 “የሰማያትና የምድር ንግሥና የሱ ፦ የአላህ – ብቻ መሆኑን አላወቅክምን? የሚሻውን ሰው ይቀጣል፤ ለሚሻውም ሰው ይምራል፤ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው። አንተ መልክተኛ ሆይ እነዚያ በክሕደት የሚቻኮሉት ከነዚያ ልቦቻቸው ያላመኑ ሲሆኑ በአፎቻቸው አመንን ካሉትና ከነዚያም አይሁድ ከሆኑት ሲሆኑ አያሳዝኑህ፤ (እነርሱ) ውሸትን አዳማጮች ናቸው፤ ንግግሮችን ከቦታቸው ሌላ ያጣምማሉ፤ ይህንን (የተጣመመውን) ብትሰጡ ያዙት፤ ባትሠጡትም ተጠንቀቁ ይላሉ። አላህም መፈተኑን የሚሻበትን ሰው ለርሱ ከአላህ (ለመከላከል) ምንንም አትችልም። እነዚህ እነዚያ አላህ ልቦቻቸውን ማጥራትን ያልሻላቸው ናቸው፤ ለነርሱ በቅርቢቱ ዓለም በውርደት አላቸው፤ ለነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከባድ ቅጣት አላቸው።” 📖ሱራ 14:4 “ከመልክተኛ ማንኛውንም፤ ለነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ በወገኖቹ ቋንቋ እንጂ በሌላ አልላክንም፤ አላህም የሚሻውን ያጠማል፤ የሚሻውንም ያቀናል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።” 📖ሱራ 7:178 “አላህ የሚያቀናው ሰው ቅን እርሱ ነው፤ የሚያጠመውም ሰው እነዚያ ከሳሪዎቹ እነሱ ናቸው። ከጋኔንም ከሰዎችም ብዙዎችን ለገሃነም በእርግጥ ፈጠርን፤ ለነርሱ በርሳቸው የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው፤ ለነሱም በሳቸው የማያዩባቸው ዓይኖች አሉዋቸው፤ ለነሱም በሳቸው የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሏቸው። እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው፤ ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፤ እነዚያዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡” 📖ሱራ :13 “በሻንም ኑሮ ነፍስን ሁሉ ቅንነቷን (እምነቷንም) በሰጠናት ነበር፤ ግን ገሀነምን አጋንንትና ከሰዎች የተሰባሰቡ ሆነው በእርግጥ እመላለሁ ማለት ቃሉ ከኔ ተረጋግጧል፡፡” 📖አዳም ራሱ የሠራው ኃጢአት ከመፈጠሩ ከአርባ ዓመታት በፊት እንደተወሰነበት በእስላማዊ ሐዲሳት ውስጥ ተጽፏል፡፡ አል-ቡኻሪ ሙሴ አዳምን “ከገነት እንድንባረር ያደረከን አንተ አባታችን ነህ” በማለት በወቀሰው ጊዜ አዳም መልሶ “አላህ ከመፈጠሬ ከአርባ ዓመታት በፊት ወስኖልኝ ለጻፈብኝ ነገር ትወቅሰኛለህን?” በማለት እንደመለሰለት ዘግቧል፡፡ (Sahih al-Bukhari, Volume 8, Book 77, Number 611) ➡️ስለዚህ ነፃ ፈቃድ በኃጢአት ትርጓሜ ውስጥ ቁልፍ ጉዳይ ከሆነ ከላይ በተጠቀሱት የቁርአንና የሐዲስ ጥቅሶች መሠረት ኃጢአተኞች ኃጢአትን እንዲሠሩ አስቀድሞ የተወሰነባቸው በመሆኑ የአቡ ሐይደር ትርጓሜ አያስኬድም፡፡ የአቡ ሐይደር የኃጢአት ትርጓሜ ትክክል ከሆነ እነዚህ የቁርአንና የሐዲስ ጥቅሶች ስህተት ይሆናሉ፡፡   አስተማሪ ስለሆነ #ለ10 ወዳጅዎ ያጋሩ ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️           🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩       🔶 ⏰🍃✨ይ🀄️ጥላል⏰🔶         ┗━━━━━•🟩🟩•━━━━━┛ for any comment 😀 @ewnet_ewnetun_bot                   ewnetlehulu.net            🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥           🪐  ወንጌል ለአለም ሁሉ  😀                  🚨 ሼር ያድርጉ 🚨     ✞●▬▬▬๑۩✞ ◒ ✞۩๑▬▬▬▬●✞  ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━           ✞●▬▬▬๑۩✞    ✞۩๑▬▬▬▬●✞                        ◒◒◒◒◒◒◒                             ◒◒◒◒                   🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺                              🎯     ♡         ❍ㅤ      ⎙ㅤ  ⌲         ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃ🔺
Show all...
👍 11 2
. 〰️ የውርስ ኃጢአት 〰️ 〰️ᴏʀɪɢɪɴᴀʟ sɪɴ 〰️〰️ 〰️〰️ 👳‍♂️የሙስሊም ኡስታዞች ስህተት ለ 👳‍♂️አቡ ሐይደር የተሰጠ መልስ 📖 ክፍል ❶ 📕 ➡️ሙስሊም ወገኖቻችን አጥብቀው ከሚቃወሟቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮዎች መካከል “የውርስ ኃጢአት” አንዱ ነው፡፡ ይህ አስተምህሮ በቅዱሳት መጻሕፍትም ሆነ በተፈጥሮ በሚታዩት እውነታዎች ድጋፍ ያለው ቢሆንም ለብዙ ሙስሊሞች የሚዋጥ አልሆነም፡፡ የዚህም ምክንያቱ “የውርስ ኃጢአት” ምን ማለት እንደሆነ በትክክል አለመገንዘባቸው ነው፡፡ የአስተምህሮውን ምንነት በትክክል ቢገነዘቡና የገዛ መጻሕፍታቸውን ቢያገናዘቡ ኖሮ ትክክለኛውን መረዳት አግኝተው ከክርስትና ጋር በተስማሙ ነበር፡፡ ነገር ግን በርዕሱ ላይ የሚጽፉትና የሚያስተምሩት ብዙዎቹ ኡስታዞች አስተምህሮውን የተረዱና የገዛ መጻሕፍታቸውን ያጠኑ ባለመሆናቸው ምክንያት ሙስሊሙ ማሕበረሰብ በተዛቡ መረጃዎች ላይ በተመሠረቱ ሙግቶች ለስህተት ተዳርጓል፡፡ ያለ በቂ መረዳት በጉዳዩ ላይ ለመጻፍ ብዕራቸውን ካነሱት ኡስታዞች መካከል አቡ ሐይደር (ኡስታዝ ሳዲቅ ሙሐመድ) አንዱ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ እርሱ ያቀረበውን ሙግት የምንፈትሽ ይሆናል፡፡ እንዲህ ሲል ይጀምራል፡- 👳‍♂️አቡ ሐይደር፡-"ከአዳም ለወረሳችሁት ኃጢአት ዕዳውን ማን ከፈለላችሁ?" ➡️እናንተ ሙስሊሞች ኢየሱስ ስለ ሰው ልጅ ኃጢአት አልሞተም አልተሰቀለም ካላችሁ ከአዳም ለወረሳችሁት ኃጢአት ዕዳውን ማን ከፈለላችሁ? ማንስ ሞተላችሁ? ➡️እኛ መጀመሪያውኑ የኃጢአት ውርስ አለ ብለን መች አምነን ነው ይህን ጥያቄ የምታቀርቡልን? ደግሞስ ከአደም (ዐለይሂ ሰላም) ኃጢአትን ወርሰናል ማለት ምን የሚሉት ፍልስፍና ነው? ኃጢአት በምንም አይነት መልኩ ሊወረስ ወይንም ከአያት ቅድም አያት ወደ ልጅ ሊተላለፍ አይችልም፡፡ እንዴት? የሚል ጥያቄ ከተነሳም፡ ➡️ቀጥሎ ያለውን ማብራሪያ በጥሞና ያንብቡ፡– ➡️ኃጢአት በውርስ የማይተላለፍ መሆኑን ለመረዳት፡ ቅድሚያ የኃጢአትን ትርጉምና ፍቺ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ✅ ✝️መልስ👨🏻‍🏫፡-ቅድሚያ “የውርስ ኃጢአት” ማለት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ መታወቅ ያለበት የመጀመርያው ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “የውርስ ኃጢአት” የሚል ቃል አለመኖሩ ነው፡፡ ቃሉ አዳምና ሔዋን የሠሩትን የመጀመርያውን ኃጢአት (Original Sin) ለመግለፅ ሰዎች የተጠቀሙት ቃል ነው፡፡ አንዳንዶች ከዚህ ቃል በመነሳት እንደሚያስቡት መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጆች ራሳቸውን ከማወቃቸው በፊት ኃጢአት እንደሠሩ ወይንም ከተጨባጭ ኃጢአት ጋር እንደተወለዱ አያስተምርም፡፡ ⚜️በክርስትና “የውርስ ኃጢአት” ማለት ሰው ኃጢአትን ከመሥራት ዝንባሌ ጋር ይወለዳል እንዲሁም የኃጢአት ውጤት ሰለባ ይሆናል ማለት እንጂ ራሱን ከማወቁ በፊት ኃጢአት ሠርቷል ማለት አይደለም፡፡ ሁሉም ሰው በፍጥረቱ የቁጣ ልጅ ነው፤ ለዚህም ምክንያቱ ከተጨባጭ ኃጢአት (Actual Sin) ጋር መወለዱ ሳይሆን ኃጢአትን ከመሥራት ዝንባሌ ጋር መወለዱ ነው (ኤፌሶን 2፡3)፡፡ ስንወለድ ከተጨባጭ ኃጢአት ጋር አልተወለድንም፡፡ ነገር ግን ኃጢአትን ከመሥራት ዝንባሌ ጋር ስለተወለድን ኃጢአተኞች የመሆናችን ጉዳይ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ፍርድ ማምለጥ አይቻለንም፡፡ ሌላው “የውርስ ኃጢአት” ትርጉም የኃጢአትን ውጤት ከአዳም መውረሳችን ነው፡፡ የሰው ዘር ሁሉ ወኪል የሆነው አዳም ኃጢአትን በመሥራቱ ምክንያት ሁላችንም ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ነን (ሮሜ 5፡12)፡፡ ከገነት በመባረር ለምድር ሥቃይ መዳረጋችን በአዳም ኃጢአት ምክንያት ነው፡፡ እነዚህን ሁለቱን እውነታዎች ያላገናዘበ ሙግት ነጥቡን የሳተ ነው፡፡ አቡ ሐይደር በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ሁለቱን የውርስ ኃጢአት ግንዛቤዎች አልጠቀሰም፤ ስለዚህ መልስ የሰጠው ለመጽሐፍ ቅዱሳዊው አመለካከት ሳይሆን ለዘልማድ አስተሳሰብ ነው፡፡ 👳‍♂️አቡ ሐይደር፡-"ኃጢአት ማለት፡– የጌታችንን አላህ ፈቃድ በሀሳብም ሆነ በተግባር መቃወምና ጥሶ መገኘት ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህ፡– አንድን ነገር አድርጉ ብሎ ትእዛዝ አስተላልፎ፡ ያን የታዘዝነውን ነገር ማድረግና መፈጸም እየቻልን ከተውነው፣ ወይንም አንድን ነገር አትቅረቡ በማለት ከልክሎን ሳለ፡ እኛ ደግሞ የተከለከልነውን ነገር መተውና መጠንቀቅ እየቻልን ስንዳፈረውና ስንፈጽመው ተግባራችን ኃጢአት ይሰኛል፡፡'' የኃጢአት ፍቺው በአጭሩ ይኸው ነው፡፡ ✅ ✝️መልስ👨🏻‍🏫፡-የክርስትናና የእስልምና የኃጢአት ትርጓሜ እንዲሁ ከላይ ሲታይ የሚመሳሰል ቢሆንም መሠረታዊ በሆነ ሁኔታ ይለያያል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ኃጢአት የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ከመተላለፍም ያለፈ ተግባር ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢአት በእግዚአብሔር ላይ ማመፅ መሆኑን ይናገራል፡- “ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን ደግሞ ያደርጋል፥ ኃጢአትም ዓመፅ ነው” (1ዮሐ. 3፡4)፡፡ በእስልምና መሠረት አንድ ሰው ኃጢአትን ሲሠራ ራሱን ብቻ የሚበድል ሲሆን (ሱራ 7፡22)፤ በክርስትና መሠረት ግን ኃጢአትን የሚሠራ ሰው እግዚአብሔርንም ጭምር ይበድላል (መዝ. 51፡4)፡፡ በተጨማሪም በክርስቲያናዊ ትርጓሜ መሠረት ኃጢአት በሰው ልጆች ሁሉ ልብ ውስጥ ከሚገኝ አመፀኛ አስተሳሰብ የተነሳ መጥፎ ሐሳቦችን በማሰብ ጭምር የሚፈፀም ክፉ ነገር ነው (ዘፍ. 8፡21፣ ያዕ. 1፡14፣ ማቴ. 5፡27-28)፡፡ እስልምና ብዙ ጊዜ ይህንን የኃጢአት ገፅታ እምብዛም ትኩረት አይሰጠውም፡፡ ሌላው ሊተኮርበት የሚገባው ነጥብ እግዚአብሔር ፍፁም ቅዱስ በመሆኑ ምክንያት ኃጢአት ከእርሱ ዕይታ አኳያ በጣም ከባድ ነገር መሆኑ ነው፡፡ እስልምና ኃጢአትን “ማረኝ ማረኝ” በማለት ብቻ የሚታለፍና በሌላ መልካም ሥራ የሚካካስ ስህተት አድርጎ መተርጎሙ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር እጅግ በጣም ስህተት ነው፡፡ “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና…” (ሮሜ 6፡23)፡፡ “…ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች” (ሕዝቅኤል 18፡4)፡፡ አስተማሪ ስለሆነ #ለ10 ወዳጅዎ ያጋሩ ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ 🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩 🔶 ⏰🍃✨ይ🀄️ጥላል⏰🔶 ┗━━━━━•🟩🟩•━━━━━┛ for any comment 😀@ewnet_ewnetun_bot ewnetlehulu.net    🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥           🪐 ወንጌል ለአለም ሁሉ 😀              🚨 ሼር ያድርጉ 🚨     ✞●▬▬▬๑۩✞ ◒ ✞۩๑▬▬▬▬●✞  ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━           ✞●▬▬▬๑۩✞    ✞۩๑▬▬▬▬●✞                        ◒◒◒◒◒◒◒                             ◒◒◒◒                   🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺                              🎯     ♡         ❍ㅤ      ⎙ㅤ  ⌲         ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃ🔺
Show all...
👍 11 4👏 2
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.