cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አቡ ዑመይር

ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ (ሱረቱል ነህል 125) ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Yabekeir ስህተት ባያችሁም ጊዜ አርሙኝ።

Show more
Advertising posts
1 848
Subscribers
-224 hours
+47 days
-1330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አቡ ዑበይዳ (አሚር ኢብኑ አብዱላህ ኢብኑ አል-ጀራህ) በዱንያ ሳሉ በነብያችን ሰ•ዐ•ወ አማካኝነት በጀነት ከተበሸሩ ሰሃባዎች መሃከል አንዱ ነው። "በኑል ሃሪሳ" ተብሎ የሚጠራው የቁረይሽ ጎሳ አባል የሆነው የአል-ሀሪስ ኢብኑ ፊህር ጎሳ አባል ነበር። ቤተሰቡ በሂጃዝ (በምእራብ አረቢያ) ውስጥ የቁረይሽ መገኛ በሆነችው ዝቅተኛ የመካ ስፍራ ነው። የአቡ ኡበይዳ አባት አብደላህ በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ በሃዋዚን ዘላኖች ላይ በተደረገው የፊጃር ጦርነት ከቁረይሾች አለቆች ውስጥ አንዱ ነበር። እናቱም ቁረይሻዊ ነበረች። አቡ ኡበይዳህ የተወለዱት በዚሁ ስፍራ እ.ኤ.አ በ583 ዓ.ል አካባቢ ሲሆን። እስልምናን ከመቀበላቸው በፊት ከቁረይሽ መኳንንቶች ውስጥ አንዱ እንደሆኑ ይቆጠሩ የነበሩ ሲሆን በጎሳቸዉ ሰዎች ዘንድም በጨዋነታቸው እና በጀግንነታቸው የሚታወቁ ዝነኛ ሰው ነበሩ። እ.ኤ.አ በ611 ዓ.ል ነብያችን ሙሀመድ (ሰ•ዐ•ወ) ለመካ ሰዎች፣ ለቅርብ ባልደረቦቻቸው እና ዘመዶቻቸው በግል እና በመነረገድ ላይ ዳዕዋ የአላህን አንድነት ይሰብኩ በነበረበት ጊዜ አቡበክር ረ•ዐ ከሰለሙ ከአንድ ቀን በኋላ በ28 አመታቸው ኢስላምን ተቀበሉ። አቡ ዑበይዳ ሙስሊሞች በመካ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ባሳለፉት ከባድ እንግልት እና መከራ ውስጥ ኖረዋል። በአንድ ወቅት መኳንንት የነበሩት እኒህ ሰው ለኢስላም ሲሉ ከሌሎች ቀደምት ሙስሊሞች ጋር ሆነው የቁረይሾችን ስድብና እንግልት ተቋቁመው አልፈዋል። ነብያችን ሙሀመድ (ሰ•ዐ•ወ) ከመካ ወደ መዲና በተሰደዱ ጊዜ አቡ ኡበይዳም እንዲሁ ወደ መዲና ተሰደዱ። ነብያችን ሙሀመድ (ሰ•ዐ•ወ) መዲና በደረሱ ጊዜ ሙሃጅሩን ከአንሷሪዩ ጋር በወንድማማችነት ሲያጣምሩ ከሙሀመድ ኢብኑ መስለማህ ጋር በወንድማማችነት ተጣመሩ። አቡ ዑበይዳህ የሙስሊሞች ጀግና የጦር አዛዥ ሆነው ካለፉ የነብያችን (ሰ•ዐ•ወ) ድንቅ ባልደረባዎች መሃል አንዱ ነበሩ። ከቁረይሽ ሙሽሪኮች ጋር በተደረገው የበድር ዘመቻ ወላጅ አባታቸውን ለኢስላም ሲሉ በሰይፋቸው መቅላታቸው የሚታወስ ነው። በዚህ ቆራጥ ተግባራቸው ሰበብ አላህ ሱ.ወ የቁርአን አንቀፅ ሊያወርድላቸው ችሏል። በሁለተኛው ኸሊፋ በኡመር ረ.ዐ ዘመን የጦር ሰራዊት አዛዥ ሆነው ኢስላምን አገልግለዋል። ኡመር ረ.ዐ እኔን ይተኩኛል ብለው በዝርዝር ከያዟቸው ሹማምንቶች ውስጥ አንዱ የነበሩት አቡ ዑበይዳህ ኢብኑ ጀራህ ረ•ዐ እ.ኤ.አ በ639 ዓ.ል በዑመር የአገዛዝ ዘመን ከነብያችን (ሰ•ዐ•ወ) ዘንድ ቃል ወደ ተገባላቸው አኼራ አለፉ። የAthamina, Khalil, "አቡ ኡበይዳ ኢብን አል-ጀራህ" ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው። ✍ አቡ ዑመይር ( ቀን, መጋቢት 5, 2016 ) || ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2
Show all...
2👍 1
| | ሁሉ ሀሳብ መቋጫ አለው፣ ሁሉ ጭንቀት መጨረሻ ይኖረዋል፣ ሁሉ ዉጥረት ይረግባል ፣ ከችግር በኋላ እፎይታ አለ፣
Show all...
8👍 3🔥 3😍 1
ዓሊሟ  በዱቤ የሚታከምባት ኡማ!    ▪️ ለሸይኽ ዐብዱለጢፍ እስካሁን የተሰበሰበው ብር 499,000 (አራት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሽ) ብር ነው። አጠቃላይ የሚፈለገው $8500 (ስምንት ሽ አምስት መቶ የአሜሪካን ዶላር ) ነው። ይህ ማለት 1,037,000  (አንድ ሚሊዮን ሰላሳ ሰባት ሽህ)  የኢትዮጲያ ብር ገደማ ነው። ከዚህ ላይ ግማሹን እንኳን መሰብሰብ አልተቻለም!!    ▪️ ሸይኻችን ከእስር ቤት ሲወጡ በስጦታ የተበረከተላቸው መኪና ይሸጥ ቢሉም እያሰባሰቡ ያሉ ሽማግሌዎች በጭራሽ እኛ ሙስሊሙን ይዘን አሰባስበን እንከፍላለን እንጅ መኪናው አይሸጥም በማለት የህዝቡን ትብብር እየጠበቁ ነው!    ▪️ ጉዳዩ እንዲህ ነው ፦ ህመሙ ወደ ካንሰር የመለወጥ እድል የነበረው እጢ በመሆኑ እናሳክማችሁ ብለው ወደ ቱርክ የወሰዷቸው ወንድምና እህቶች ከህዝቡ ሰብስበን እንከፍላለን በሚል መተማመን ከሰዎች በብድር አንስተው ነበር የከፈሉት።    ▪️ መጀመሪያ $4000  የተገመተ ህክምና ኋላ ላይ $7500 ተጨማሪ ተጠየቀበት። ይህ ሁሉ ሲሆን ሸይኻችን አያውቁም ነበር። ከዚያ የተወሰኑ ቅርብ ሰዎች ጉዳዩን ሲነግሯቸው ነበር «መኪናዬ ይሸጥ» የሚል ሀሳብ ያመጡት ። ይህም ጠቅላላ ህክምናው $11,000 ዶላር ሲሆን $2500ው በወንድሞች ስለተከፈለ ለህዝብ የተጠየቀው $8500ው ብቻ ነው። የአንድ መርፌ ዋጋ $300 (36,600 ብር ) ሆኖ ህክምናው እንደቀጠለ ነው። መርፌውም የሚቆም ሳይሆን  በየ3ወሩ የሚቀጥል ነው። ▪️ ወደርሳቸው አካውንት ገቢ እንዳይደረግ የተደረገውም በዚሁ ምክንያት ብቻ ነው። ከአካውንትህ አውጣና ዱቤ ክፈል እንዴት ይባላል? ለሸይኽ አይደለም ለተርታ ሰውስ ነውር አይደለም? ስለሆነም በኮሚቴ አካውንት እንዲሰበሰብ ተወሰነ። ▪️ አሰባሳቢ ኮሚቴዎቹ በእምነታቸው ድፍን የሰንበቴ ከተማ ነዋሪ የሚመስክርላቸው ዓሊሞችና ሽማግሌዎች እንዲሁም የሸይኹ የቅርብ ጓደኞች ናቸው። ስለሆነም ሙስሊሙ ኡማ ይህንን ተገንዝቦ «ሀብታሞች ገቢ ያደርጋሉ» ብለን ሳንዘናጋ ትንሽም ብትሆን ሁሉም የራሱን ገቢ እያደረገ ሸይኻችንን  እናሳክም! የከሸፍን ትውልዶች ሆነን እንጅ ወላሂ በዚህ መልክ ለሸይኻችን ስፅፍ ክብራቸውን ዝቅ ያደረግኩ እየመሰለኝ ነው!  የንግድ ባንክ አካውንት ፦ 1000392652788 የአካውንት  ስም ፦ YEJILE TIMUGA W/COMMUNITY SUPPORT (የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሚዩኒቲ ሰፖርት) አሰባሳቢ ኮሚቴዎች ፦ 1) ሸኽ ጡሃ ሸኽ መሀመድ 2) ሸኽ ሁሴን ሀሰን ሱሩር 3) ሸኽ አህመድ አሊ ሃሰን
Show all...
👍 5
አንዳንዴ ያ እንዲያምርልህ በዜማ የምትቀራው ቁርአን፣ ሲነበብ የሰዎች ልብ ውስጥ እንዲገባ ለአንባቢዎች አጣፍጠህ የምትፅፈው መጣጥፍ፣ ያ በአለህ መንገድ ላይ የምትጋደለው ተጋድሎህ ነፍሲያህ አሸንፋህ ሰዎች እንዲመሰክሩልህ ትሻ ይሆናል። ማሻ አላህ ኢስላም ባዘዘን ኢባዳዎች ላይ ሁሉ እንሳተፍ ይሆናል ግና ምን ያረጋል ይታይልህ፣ ይታይልሽ የምትል ነፍስ በውስጣችን ሸሽገናል። ኢኽላስ ያለው ኢባዳ ላይ የፉጥራን ምስክርነት ምን ያደርግልናል? አኼራችንስ ላይ ከማዋረድ ውጪ በምን ይጠቅመናል? አዋጅ! ኢኽላስ ያለው ኢባዳ ምስክርነቷ በአላህ የበቃ ነው። ከአላህ ሌላ መስካሪም የማያሻ ነው። አላህ ሱ•ወ በቅዱስ ቃሉ እንዲህ ይላል፦ وَكَفَى بِاللَّهِ شَهِيدًا መስካሪም በአላህ በቃ ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው ✍ አቡ ዑመይር ቴሌግራም፦ https://t.me/Abu_Umair2
Show all...
👍 3 1
| | አንድ አዕራቢይ የሞት ፍራሹ ላይ ሆኖ ሰዎች አንተኮ ልትሞት ነው አሉት ከሞትኩ ውዴት ነው ምሄደው አላቸው ወደ አሏህ አሉት ሞት ምንኛ አማረ አሏህን መገናኘት ምንኛ አማረ አለ
Show all...
10
| | በብሄርተኝነት አትቀልድ ሳታውቀው ዘረኝነት ውስጥ ትገባለህ። በሺርክ እና በቢድዐ አትቀልድ ሰዎች ዘንድ ቀላል የሆነ ተግባር ሆኖ እንዲታይ ታደርጋለህ። በሰዎችም ሀይማኖት አትሳለቅ በአንተ ሀይማኖት እንዲሳለቁ በር ትከፍታለህና። (አላህ ሙስሊም ስላደረገህ ከማመስገንህ ጋር ጌታህን አጥራው)።
Show all...
10👍 4🥰 1
ከመተኛትህ በፊት . ከመተኛትህ በፊት ይህንን አስብ በዛሬው ቀን አሏህን ያመፅኩት ወይስ የታዘዝኩት የቱ ይበልጣል ብለህ መዝን ያመፅከው ከበለጠ ጌታህ እጅግ መሀሪና አዛኝ ነው መሀርታውን ጠይቀህ ተኛ የታዘዝከው የበለጠ መስሎህ ከተሰማህ እንኳን ደስ አለህ ግን ግን የታዘዝከው ነገር በራሱ መሀርታው እንደሚያስፈልገው እንዳትረሳ ምን ብትታዘዘው በስራህ ጀነት መግባት እንደማትችል ለማይክሮ ሰከንድ እንዳትረሳ ስለዚህም መሀርታውን እና እዝነቱን ለምነህ ተኛ ጌታዬ ሆይ ስላጓደልኩት ይቅር በለኝ በለው ጌታዬ ሆይ ስለተላለፍኩት ይቅር በለኝ በለው ጌታዬ ሆይ እኔን ብትቀጣኝ ባርያህ ይጎዳል ወዳጅህ መልክተኛውም ያዝናሉ ጠላትህ ሸይጧን ደግሞ ይደሰታል ጌታዬ ሆይ አንተ ደግሞ ባርያህ ተጎድቶ ወዳጅህ አዝነው ጠላትህ እንዲደሰት ምትፈቅድ ጌታ አይደለህም ጥራት ይገባህ ማረኝ በለው ጌታዬ ሆይ ብተቀጣኝ ባርያህ ነኝ ብትምረኝ አንተ አሸናፊው እና ጥበበኛ ነህ በለው
Show all...
🥰 5 1🔥 1
"አንዴ እየተጓዝን ነበር አንድ ቦታ ላይ ነዳጅ ልንቀዳ ቆምን በስህተት አንድ ሰው በነዳጅ ፋንታ መኪናው ላይ ናፍጣ አደረገ በዚህም መኪናው ቆመ ሹፌሩም እኛም የተለያዩ መንገዶችን ሞከርን(መኪናውን ለማንቀሳቀስ) ግን እምቢ ብሎ ቀረ ይሄኔ የመኪናው መቆም ምክንያት በስህተት ያስገባነው ናፍጣ እንደሆነ ተረዳን በዛ ቀን እኔ አንድ ነገር ተረዳውኝ አንድ በሰው እጅ የተሰራ ማሽን የተሳሳተ ነዳጅ ከተሰጠው አንድ ማይል እንኳን ማይጓዝ ከሆነ አማኝ እንዴት በሀራም ምግብ እና የሰውነት ግንባታ ጀነት ይደርሳል ለዛም ነው የተከበራቹ ወንድሞቼ እና ታላቆች ዋነኛው የተቅዋ ምልክት አማኝ ሀራምን መመገብ(መፍጨት) አለመቻሉ ነው" ሸይኽ ሙሃመድ ሰዐድ ከንደህለቪ
Show all...
🥰 1
"መካሪ ባልሆኑ ህዝቦች ውስጥ ኸይር የለም እንዲሁም ምክርን በማይወዱ ህዝቦች ውስጥም ኸይር የለም" ሰይዱና ዑመር ኢብኑል ኸጧብ እኛ ተገላቢጦሽ ነን አይደል ? በሚገባ
Show all...
4
በዕለት ተዕለት የዱንያ ሂወታችሁ ላይ አላህ (ሱ•ወ) እንዲወዳቹ ከሻቹ ፤ ከታች በተጠቀሱት ስራዎች ላይ በቻላቹት አቅም የሙጢኝ በሉ። 1ኛ. "በአላህም መንገድ ለግሱ፡፡ በእጆቻችሁም (ነፍሶቻችሁን) ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና፡፡" [ሱረቱል በቀራ:195] 2ተኛ. የገባቹትን ቃል ኪዳን ሙሉ። ጥንቁቅም ሁኑ "… በቃል ኪዳኑ የሞላና የተጠነቀቀ ሰው አላህ ጥንቁቆችን ይወዳል፡፡" [ሱረቱል ኢምራን: 76] 3ተኛ. "ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት (ተደግሳለች)፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡" [ሱረቱል ኢምራን: 134] 4ተኛ. ታገሱ "አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡" [ሱረቱል ኢምራን: 146] 5ተኛ. "ቁርጥ ሐሳብም ባደረግህ ጊዜ በአላህ ላይ ተመካ፡፡ አላህ በርሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና፡፡" [ሱረቱል ኢምራን :159] 6ተኛ. ውሸትን አዳማጮች እርምን በላተኞች ወደ አንተ ቢመጡ በመካከላቸው ፍረድ፡፡ "ብትፈርድም በመካከላቸው በትክክል ፍረድ፡፡ አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና፡፡" [ሱረቱል ማኢዳ: 42] 7ተኛ. በአላህ መንገድ ላይ ጂሃድ አድርግ። "አላህ እነዚያን እነርሱ ልክ እንደ ተናሰ ግንብ የተሰለፉ ኾነው በመንገዱ (በሃይማኖቱ) የሚጋደሉትን ይወዳል፡፡" [ሱረቱል ሶፍ: 04] 8ተኛ. ወደ አላህም ተመለሱ "አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው፡፡" [ሱረቱል በቀራ: 222] ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው። ✍ አቡ ዑመይር ( ቀን, መጋቢት 3, 2016 ) || ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2
Show all...
👍 3 1