cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የስኬት መንደሮች

¥251 በዚህ ቻናል የተለያዩ ወደ ስኬት ሚወስዱ ትምርት አዘል ነገሮች ይለቁበታል መልካም የስኬት ጉዞ ለአስተያየት inbox ላይ ያውሩን

Show more
Advertising posts
215
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሁለት መንገዶች አሉልህ፦ አንደኛው መንገድ ምንም ፈተና የለውም ነገር ግን መንገዱ በጣም እረጅም እና መድረስ የምትልግበት ቦታ ላይ ለመድረስ እረጅም አመታቶችን ይፈልጋል። አንደኛው መንገድ ደግሞ በጣም በፈተና የተሞላ ሲሆን ፈተናውን እንዳለፍከው ግን መንገዱ አጭር እና በጥቂት ጊዜ ውስጥ ስኬታማ የሚያደርግህ ነው። የቱን ትመርጣለህ ? ብዙ ሰው ፈተና የሌለውን ተደጋጋሚውን መንገድ መርጦ መኖርን ለምዶአል። ጥቂት ሰዎች ግን ፈተናውን መርጠው ስኬታማ ሆኖዋል። ለዚህ ነው በአለማችን ላይ ያሉት ስኬታማ ናቸው የምንላቸው ሰዎች እጅጉን ጥቂት የሆኑት ✏️yared drems
Show all...
ተረጋጉ! አንድ እጅግ የከራረመ አፈ-ታሪክ እንዲህ ይነበባል፡- አንድ ሰው ያለበት የገንዘብ እጦትና የወቅቱ የኑሮ ሁኔታ እጅግ ስለከበደው ራሱን ለማጥፋት የሚታነቅበትን ገመድ ይዞ ወደ አንድ ስውር ቦታ ሄደ፡፡ ልክ እዚያ ቦታ ሲደርስ አንድ ሰወር ብሎ የተቀመጠ ሳጥን አየ፡፡ ጠጋ ብሎ ሲመለከተው አንድ ሰው ማንም ሰው አያይብኝም ብሎ የደበቀው በውስጡ ብዙ ገንዘብ ያለው ሳጥን ነው፡፡ ልክ ይህንን በሳጥን የተቀመጠ ገንዘብ እንዳገኘ ራሱን ለማጥፋት ያሰበውን ሃሳብ በመቀየርና ለመሰቀል ያዘጋጀውን ገመድ እዚያው በመጣል ያገኘውን ገንዘብ ይዞ ሄደ ይባላል፡፡ ከተወሰኑ ሰዓታት በኋላ ገንዘቡን በሳጥን የደበቀው ሰው ሲመጣ ያስቀመጠውን ንብረት በማጣቱ በጣም ደነገጠ፡፡ ወዲህና ወዲያ ቢል ስላጣው ሁሉም ነገር ጨለመበት፡፡ በድንገት ዘወር ሲል ቀድሞ መጥቶ የነበረው ሰው ጥሎት የሄውን ገመድ አየና አንስቶ ራሱን ሰቀለ ይባላል፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች ማንነታቸውንና የመረጋጋታቸውን ሁኔታ ባላቸው የገንዘብ አቅም ላይ የመሰረቱ ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ገንዘብ ዛሬ ይመጣል፣ ነገ ደግሞ ይሄዳል፡፡ የሃብት ነገር ዛሬ ይከማቻል፣ ነገ ደግሞ ይባክናል፡፡ ከዚህ ተለዋዋጭ ሁኔታ ባሻገር ዘልቆ የሚሄድን አመለካከትና ስብእና መገንባት እንደ ወቅቱ ሁኔታ ከመጨነቅ፣ ከመደበትና አልፎም ሞትን ከመመኘት ይጠብቀናል፡፡ የጀመርነውን አመት መልካምነት በፍጹም ባላችሁ የገንዘብ አቅም አትገምቱት፡፡ በዚህ አመት የሚኖራችሁን የመረጋጋት ሁኔታ በፍጹም ያላችሁ የገንዘብ ሁኔታ እንዲወስነው አትፍቀዱ፡፡ እናንተ ሰላም ስትሆኑና ውስጣችሁ ሲረጋጋ ዛሬ የሌለ ነገር ነገ ይመጣል፤ ባለፈው አመት የባከነው በዚህ አመት ይመለሳል፡፡ ቆንጆ ምሽት ተመኘን🙏 ✏️yared
Show all...
👍 2
ተረጋጉ! አንድ እጅግ የከራረመ አፈ-ታሪክ እንዲህ ይነበባል፡- አንድ ሰው ያለበት የገንዘብ እጦትና የወቅቱ የኑሮ ሁኔታ እጅግ ስለከበደው ራሱን ለማጥፋት የሚታነቅበትን ገመድ ይዞ ወደ አንድ ስውር ቦታ ሄደ፡፡ ልክ እዚያ ቦታ ሲደርስ አንድ ሰወር ብሎ የተቀመጠ ሳጥን አየ፡፡ ጠጋ ብሎ ሲመለከተው አንድ ሰው ማንም ሰው አያይብኝም ብሎ የደበቀው በውስጡ ብዙ ገንዘብ ያለው ሳጥን ነው፡፡ ልክ ይህንን በሳጥን የተቀመጠ ገንዘብ እንዳገኘ ራሱን ለማጥፋት ያሰበውን ሃሳብ በመቀየርና ለመሰቀል ያዘጋጀውን ገመድ እዚያው በመጣል ያገኘውን ገንዘብ ይዞ ሄደ ይባላል፡፡ ከተወሰኑ ሰዓታት በኋላ ገንዘቡን በሳጥን የደበቀው ሰው ሲመጣ ያስቀመጠውን ንብረት በማጣቱ በጣም ደነገጠ፡፡ ወዲህና ወዲያ ቢል ስላጣው ሁሉም ነገር ጨለመበት፡፡ በድንገት ዘወር ሲል ቀድሞ መጥቶ የነበረው ሰው ጥሎት የሄውን ገመድ አየና አንስቶ ራሱን ሰቀለ ይባላል፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች ማንነታቸውንና የመረጋጋታቸውን ሁኔታ ባላቸው የገንዘብ አቅም ላይ የመሰረቱ ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ገንዘብ ዛሬ ይመጣል፣ ነገ ደግሞ ይሄዳል፡፡ የሃብት ነገር ዛሬ ይከማቻል፣ ነገ ደግሞ ይባክናል፡፡ ከዚህ ተለዋዋጭ ሁኔታ ባሻገር ዘልቆ የሚሄድን አመለካከትና ስብእና መገንባት እንደ ወቅቱ ሁኔታ ከመጨነቅ፣ ከመደበትና አልፎም ሞትን ከመመኘት ይጠብቀናል፡፡ የጀመርነውን አመት መልካምነት በፍጹም ባላችሁ የገንዘብ አቅም አትገምቱት፡፡ በዚህ አመት የሚኖራችሁን የመረጋጋት ሁኔታ በፍጹም ያላችሁ የገንዘብ ሁኔታ እንዲወስነው አትፍቀዱ፡፡ እናንተ ሰላም ስትሆኑና ውስጣችሁ ሲረጋጋ ዛሬ የሌለ ነገር ነገ ይመጣል፤ ባለፈው አመት የባከነው በዚህ አመት ይመለሳል፡፡ ቆንጆ ምሽት ተመኘን🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ😊
Show all...
ሕይወት እንደ ማዕበል ሲሆን! አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ ማዕበል ነው፡፡ በሰላም ይሄዱ የነበሩ ነገሮች ልክ የተመካከሩ ይመስል በአንድ ላይ ይናጋሉ፡፡ የሁኔታዎች አልሳካ ማለት፣ ድንገተኛ ወጪዎች፣ የገንዘብ እጥረት፣ የጉዳዮች መጥመም፣ የሰዎች ክህደት፣ ስጋትን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች መከሰት፣ የጤንነት መቃወስን የሚጠቁሙ ምልክቶች . . . ልክ እንደ ማዕበል በአንድ ላይ ይመጣሉ፡፡ ይህ የተለመደ የሕይወት አካል የሆነ ክስተት በእኛም ላይ ሲደርስ መረጋጋት ወሳኝ ነው፡፡ ማዕበል ይመጣል፣ ልክ እንደመጣ ደግሞ ይሄዳል፡፡ ነፋስ ከየት እንደመጣ ሳናውቀው ወደ እኛ ይነፍሳል፣ ወደየት እንደሚሄድ ሳናውቀው ደግሞ ወደሌላ ቦታ ይነፍሳል፡፡ አይዟችሁ! ጽኑ! አትናወጡ! ተንጋግቶ የመጣው ተንጋግቶ ይሄዳል! ቆንጆ ምሽት ተመኘን🙏 ✏️yared drems
Show all...
👍 2
"የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ እያለሁ ሁለት ቁልፍ ፈተናዎች ነበሩብኝ ሆኖም ሁለቱንም ወደኩ….የመካከለኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁም ፈተና ከመውደቅ አልዳንኩም ለውድቀት ሶስት ጊዜ እጄን ሰጠሁ፡፡ ኮሌጅ ለመግባት ፅኑ ፍላጎት ቢኖረኝም መግቢያ ፈተናዎቹን ሁለቴ ወስጄ በሽንፈት ተመለስኩ፡፡ የሚገርመው ደግሞ ያመጣሁት ውጤት  አሳዛኝ ነበር። መውደቅ አንድ ነገር ቢሆንም በሂሳብ ትምህርት  ከ120 ነጥብ 1 ማምጣት ግን  በርግጥም ከባድ ነበር፡፡ ውድቀቴ ይቀጥላል…ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ 10 ጊዜ አመልክቼ ውድቅ ተደርጎብኛል፡፡ ከኮሌጅ ተመርቄ ከወጣሁ በኋላ ስራ የመቀጠር ፅኑ ፍላጎት ቢኖረኝም 30 ስራ እድሎች በተከታታይ ብሞክርም አልተሳካልኝም፡፡ KFC ስራ አወጣ ተደሰትኩ በዚህኛው ግን ስራ ለማግኘት የማደርገው ጥረት በድል እንደሚደመደም አስቤ ተራመድኩ፡፡ ብዙ ፈተናዎችን አልፈን ለስራ የመጣነው 24 ነን፡፡ 23 ሰው አለፈ በሚደንቅ ሁኔታ የወደቀው አንዱ ሰው እኔ ነበርኩ፡፡" ይህንን ያለው ጃክ ማ ነው። ይህ ሰው ከዚህ ሁሉ ውድቀት በኋላ ቻይናን የቀየረ አማዞንን መሰል የአሜሪካ ካምፓኒዎችን የሚገዳዳረውን አሊባባን የመሰረተ እና እዚህ ያደረሰ የዘመናችን እጅግ ስኬታማ ሰው ነው፡፡ #በፍጹም_ተስፋ_አትቁረጡ!!! ✏️yared drems
Show all...
👍 1
ቻይናዊው የታክሲ ሹፌር! "ትኩረታችሁን ቢዝነሳችሁ ላይ አድርጉ!" አንድ ሰው ይህንን አጭር ታሪክ ሲናገር ሰማሁት፡- አንዲት ራቁቷን የሆነች እንግሊዛዊት ሴት አንድ ቻይናዊ የሚያሽከረክረውን ታክሲ አስቁማ ገባች፡፡ ቻይናዊው የታክሲ ሹፌር ደጋግሞ ከላይ እስከታች ሲያያት ጊዜ እንግሊዛዊቷ አስተያየቱ ስላሳሰባት፣ “ምነው! ራቁቷን የሆነች ሴት አይተህ አታውቅም እንዴ?” አለችው፡፡ ቻይናዊው በመመለስ፣ “ከላይ እስከታች ያየሁሽ ራቁትሽን ስለሆነሽ ሳይሆን፣ ከላይ እሰከታች ደጋግሜ ያየሁሽ የምትከፍይኝን ገንዘብ የያዝሽበትን ስፍራ ስላጣሁት ነው፡፡” ከታሪኩ የምንማረው ትምህርት፣ እንደ ቻይናዊ የታክሲ ሹፌር ሁኑ፡፡ ትኩረታችሁን ከሚስበውና ከሚበታትነው ነገር ላይ አንሱና ትኩረታችሁን ዋናው ተግባራችሁና ቢዝነሳችሁ ላይ አድርጉ፡፡
Show all...
ሁለት ዝንቦች ወተት የያዘ ብርጭቆ ውስጥ ይሰምጣሉ። አንደኛው ዝንብ ትንሽ ከተንፈራገጠ በኋላ መውጣት ሲያቅተው ተስፋ ቆርጦ ሰምጦ ሞተ። ሁለተኛው ዝንብ ግን ያለማቋረጥ ወተቱ ላይ ሲንፈራገጥ፤ ብዙ ከመንፈራገጡ የተነሳ ወተቱን ንጦ ወደቂቤነት ለወጠው። ቂቤው ላይ ቆሞም ከጠርሙሱ ለመወጣት ቻለ። ተረቱ ቀልድ ቢመስልም እወነታ አለው። ያለጽናት ስኬት የለም። ጽናት የሚፈተነው ደግሞ ምንም እንኳን የሚያበረታታን ብናጣም ጉዞዋችንን መቀጠል ስንችል ነው።
Show all...
ደስታ ማግኘት ቀላል ነው! 1, እውነትህን ኑር :- እውነትህን ተጋፈጥ አታስመስል ከራስህ አትደበቅ ምንም ቢሆን ልብህ  እውነቱን ያውቃል ከላይ ከላይ ላስመስል ልሸውደው ብትልም አይቀበልህም ስለዚህ ደስታህን ይነፍግሀል መደሰት ከፈለክህ የእውነትህን ኑር እውነቱ ከባድ ቢሆንም ተጋፍጠህ ስታሸንፈው የምታገኘውን ደስታ እና እርካታ ማንም አይሰጥህም! 2 , በፍቅር ኑር :- ከሰዎች ጋር ከልብ በሆነ እውነተኛ ፍቅር ኑር ምንም ሳትጠብቅ ፍቅር  ስጥ ለሰዎች ሰላም መስጠት የምትችል ሁን ብርቱ ሁን ከልብህ ተቀበላቸው ለመጠንከራቸው ለመሳቃቸው ለማሸነፋቸው ለሰላማቸው ምክንያት ሁን ፍቅር በመስጠትህ ብቻ ህይወቱን የምታተርፍለት አንድ ሰው መኖሩን እወቅ ፤ ሞቅ ያለ ፈገግታህን በማየት ከህይወቱ ጨለማ የሚወጣ የሆነ ሰው አለ ስለዚህ በሄድክበት ሁሉ ፍቅርን የምትሰጥ እና ፈገግታህ ተስፋን የሚፈነጥቅ መሆኑን እወቅ ያኔ  ደስታ ሳትጠራው ራሱ ፈልጎህ ይከተልሀል ካንተ ርቆ መሄድ አይችልም!      "እነዚህን ካደረግህ ደስታ ራሱ ካንተ ጋር መሆን ያስደስተዋል " የደስታ ቀን ተመኘሁ🙏
Show all...
... ያቺ በመጨረሻ የምታቃስትባት ቀን ሳትመጣ! በአልጋ የምትያዝባት አይምሬዋ ቀንህ ሳትመጣብህ! ከሥራ ባልደረባህ ጋር እስቲ የልብህን አውራው፡፡ እስቲ አብረህ ሻይ ጠጣ፡፡ እስቲ የልብ ትርታውን ስማው! እስቲ ዙሪያህ ያሉ ሰዎችን አተኩረህ እያቸው፡፡ እስቲ ሁሌ በፊትህ የሚመላለሰውን ችግረኛ ለአንዲት ቀን ቀርበህ በፈገግታ ሠላም በለው፡፡ አብረኸው ቁጭ ብለህ አውጋ፡፡ የህይወት ታሪኩን ጠይቀው፡፡ ... እስቲ ፊትህ የምታያትን ምስኪን ለአንዲት ቀን ስለ ልጇ ትምህርት ቤት ጠይቃት፡፡ አዋራት፡፡ እስቲ የበታች ሠራተኞችህን ስታገኛቸው ጥሩ ስለሆኑባት፣ ጎበዝ ስለሆኑባት አንዲት ጎናቸው አንስተህ አመስግናቸው፡፡ አድንቃቸው፡፡ እስቲ የድሮ ጓደኞችህን አስታውሰህ፣ አፈላልገህ... እንደምንም ለአንዲት ቀን የሻይ ቡና አፍታ ፍጠርና አውራቸው፡፡ ተጫወት የድሮውን እያነሳህ፡፡ ጠይቃቸው ህይወት አሁን እንዴት እንደያዘቻቸው፡፡  ወንድሞችህን፡፡ እህቶችህን፡፡ እስቲ ካሉበት ቀረብ ብለህ፡፡ ካልቻልክም ስልክ ደውለህ፡፡ አውራቸው እስቲ፡፡ እንዴት ናችሁ በላቸው፡፡ እናት አባቶችህን አስታውስ፡፡ እስቲ ለአፍታ ተጫወት የባጥ የቆጡን እያነሳህ፡፡ አብራችሁ ያሳለፋችኋትን ውብ ልጅነት እያሰብክ፡፡ እያነሳህ፡፡ እስቲ ከራስህ ቅፅርና ሰብዕና ወጣ በልና ከጓደኞችህ ጋር የሚሆኑትን ሆነህ፣ ወይ ወደ አንተ ጎትተህ፣ እስቲ አንዲት የጋራ ትዝታ የምትሆናችሁን ደስ የምትል ቀን አሳልፍ፡፡ ክብርህን፣ ዝናህን፣ ኩራትህን እስቲ ለአፍታ እርሳውና እንደ ጓደኛ ተጫወት፡፡ በቃ አውራ፡፡ ለፍልፍ፡፡ ሳቅ፡፡ አንጎራጉር፡፡ ስለ ሰሜን ወይ ስለ ደቡብ አውራ፡፡ ካሻህ ስለ ገነት፣ ካላሻህም ስለ ገሃነም አውራ እስቲ ከሰው ጋር! የምታወራው ስለ ሰማዩ ሆነ ስለ ምድሩ... ዋናው የምታወራው ነገር ሚዛን ላይ አይደለም ዋጋው ያለው! አይደለም! ማውራትህ፣ ከሰው ጋር መጫወትህ፣ ሀሳብህን መጋራትህ፣ ለአንዲት ቀንም ስሜትህን መጋራትህ ነው ዋናው ትልቁ የደስታ ሙላት!  አንተ ውስጥህ ያለውን ደስታ ስታወጣው፣ ሌሎችም የየራሳቸውን ያወጣሉ! እነዚያ ቅፅበቶች ናቸው በእውነት የኖርካቸው የደስታ ቅፅበቶችህ! ሌላው የሰበሰብከው ሀብት፣ ያፈራኸው የዚህች ዓለም ቅራቅንቦ ሁሉ... ሁሉም ትርፍ ነው!       በዚህች ዓለም ላይ ስትኖር አራት ፈፅሞ ልትረሳቸው የማይገቡ እውነታዎች አሉ፡- 1ኛ/ ልጆችህን ሀብታም እንዲሆኑ አታስተምራቸው! ደስተኛ መሆንን አስተምራቸው! ያን ስታደርግ ልጆችህ ሲያድጉ የነገሮችን ዋጋ ሳይሆን፣ በህይወት ውስጥ ዋጋ ያላቸውን ነገሮች አሳምረው የሚያውቁ ይሆናሉ! 2ኛ/ ወደ አፍህ የምታስገባውን ምግብ ሁሉ፣ ልክ እንደ መድኃኒት ቆጥረህ፣ በጥንቃቄ እየመረጥክ ብላ፣ ጠጣ! ምግብን እንደ መድኃኒት ሳትቆጥር ሁሉን እያግበሰበስክ ብትኖር.. በመጨረሻ፣ መድኃኒቶች ቋሚ ምግቦችህ ይሆናሉ፡፡ መድኃኒትን እንደ ምግብ እየቃምክ ህይወትህን ታገባድዳለህ!  3ኛ/ በሰዎች መካከል ልዩነት መኖሩን ልብ ብለህ አስተውል! አንተን በእውነት የሚወዱህ፣ እና ስላንተ ደስታ የሚጨነቁ ሰዎች፣ ካንተ ጠፍተው አይጠፉም! ባንተ ተስፋ አይቆርጡም! ሁሉነገርህ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሆኖ ቢያገኙት እንኳ፣ የሆነች ባንተ ተስፋ የሚያደርጉባትን ምክንያት ያገኙ (እና ካንተ ርቀው ያልራቁ) ሰዎችን የከበረውን የልብህን ክፍል ቆርሰህ ሁልጊዜም በደስታህ ሰዓት አስባቸው! ይበልጥ አስጠጋቸው! ሰው ከሰው ይለያል! 4ኛ/ አንድ ነገር በጣም ልብ ብለህ አስተውል! ባዶ እጅህን ወደዚህች ዓለም ስትመጣ፣ ገና በእንቦቃቅላነትህ፣ ሁሉም ሰው ወዶህ ነው ጨቅላዋን ዕድሜህን ያለፍካት! ባዶ እጅህን ተወልደህ ሳለ፣ ሁሉም ይወድሃል፡፡ ፍቅርን ያዘንብልሃል፡፡ ይሳሳልሃል፡፡ ምንም ባልነበረህ የህይወትህ ጅማሮ ሰዎች ሁሉ በባዶህ እንደወደዱህ አስታውስ፡፡  ደግሞም ስትሞት ስለመለየትህ ብቻ ብለው ሁልጊዜም አንተን በሀዘኔታና በፍቅር የሚያስቡህ ብዙ ሰዎች እንዳሉ እመን፡፡ ሁሉን የዚህችን ዓለም ነገር ጥለህ ባዶ እጅህን በሞት ስታሸልብም አንተን በትዝታቸው የሚያስቡ፣ የሚናፍቁ፣ ክፉህን ማየት የማይሹ፣ ብዙ ሰዎች እንደሚኖሩ እወቅ፡፡ ✏️yared drems
Show all...
15 ወርቃማ #አባባሎች! ሼርይደረግ 1) ምቀኞች መብዛታቸው በስኬት መንገድ ላይ የመሆንህ ምልክት ነው! … 2) #ወንድ #ልጅ እናቱ በሕይወት እስካለች ድረስ #ሕፃን ነው..ለእናቱ! … 3) በፈተና ላይ አለመታገስ ሌላ #ፈተና ነው! … 4) #ፈገግታ ቃላት የሌለው መልካም ንግግር ነው! … 5) ካንተ የባሰ አለና አመስግን ፈገግ በል! … 6) ትንሽን ለመስጠት አትፈር ምንም አለመስጠት ከሱ የባሰ ነውና! … 7) የተሸናፊዉ #ፈገግታ ያሸናፊውን #ደስታ ይቀንሳል! … 8) የሁሉን #ሰው ውዴታ ማግኘት ሊደረስበት የማይቻል ግብ ነው! … 9) #ነፍስ በኩራት ስትሞላ ጎደሎ የመሆኗ መገለጫ ነው! … 10) ኩራተኛ ሰው ተራራ ጫፍ ላይ ሆኖ ሌሎችን ትንሽ አድርጎ እንደሚያይ ነው ነገርግን እሱንም ትንሽ አድርገው እንደሚያዩት አያውቅም! … 11) ብዙ ጊዜ በጉጉት ከምንጠብቀው ይልቅ ድንገት የምናገኛቸው ነገሮች ውብ ናቸው እኛ ከለፋነው ጌታ የፃፈው መልካም ነውና! … 12) ግኡዝ የሆኑት ውሃና አፈር ለእፅዋት አግልጋይ ናቸው ፤ እፅዋቶች ደግሞ ለእንስሳት ያገለግላሉ እንስሳት ፣እፅዋትና ግኡዛን ደግሞ የሰውን ልጅ ያገለግላሉ ... በተቃራኒው የሰው ልጅ ወደታች ወርዶ ለግኡዛን አገልጋይ (አምላኪ) መሆን ከጀመረ ያኔ ከነሱ የባሰ ይሆናል። … 13) ብዙ ሰው ልጅ ለዘለዓለም እንደሚኖር ሆኖ ይለፋል አንድ ቀን ሳያልፍለት ይሞታል! … 14) በሕይወት ትልቁ ስኬት የሕይወትን ትርጉም ማግኘትና አላማ ያለው ኑሮ መኖር ነው፡፡ … 15) በዚህ ቦታ .... ካነበባችሁት ፣ ከሰማችሁት ፣ ከምትከተሉት እምነት የምትወዱትን አባባል በcomment አሳውቁኝና ሌሎችም ያንብቡት፡፡ ሜሎሪና መጽሐፍ♥ #Share ይደረግ ✏️yared tewederos
Show all...