cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

ስለ አዕምሮ ጤና እንወያያለን! ለማማከር በ 0949476776 ይደውሉ:: Inbox me via telegram @DrEstifanos

Show more
Advertising posts
916
Subscribers
+524 hours
+377 days
+24230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
"የኔ ውብ ከተማ" ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር፣ ካለ ሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር? የእኔ ውብ ከተማ- ሕንጻ መች ሆነና የድንጋይ ክምር፣ የኔ ውብ ከተማ- መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር፣ የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር፣ የሰው ልጅ ልብ ነው የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር። ሕንጻው ምን ቢረዝም፣ ምን ቢፀዳ ቤቱ፣ መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ፣ ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ? በዓሉ ግርማ ኦሮማይ- ገጽ 250 ድንቅ መጽሃፍ!!
Show all...
🙏 7 5
የአልፍሬድ አድለር እይታ ስለ 'ግለኝነት እና ለማህበረሰብ ተቆርቋሪነት ስነልቦና' **** ወደዚህች ምድር ስንመጣ በአካልም ይሁን በስነልቦና ያላደግን ደካሞች ሁነን ነው:: ይህም የበታችነት እና ያለመቻል ስሜትን ይፈጥራል:: ለመራመድ ፣ ራሳችንን ችለን ለመመገብ፣ ለማውራት ጊዜያቶችን መጠበቅ ግድ ይለናል:: የስነልቦናችን መዋቅርም ለመብሰል ጊዜን ይፈልጋል:: እነዚህ እድገቶቻችን የወላጆቻችንን/ አሳዳጊዎቻችንን እገዛ የሚሹ ናቸው:: በነዚህ ሰዎች እገዛና ድጋፍ በጊዜ ሂደት በአካልና በልቦና እየጎለመስን እንሄዳለን:: ለማህበረሰብ ማሰብን አሃዱ ብለን የምንማረው ከወላጆቻችን/አሳዳጊዎቻችን ነው:: ደመነብሳዊ ልቦናችን ምልአትን የምትሻ በመሆኗ፡ ከ 4- 5 አመታችን ሁላችንም ልዕልናን እና ስኬትን (striving for success and superiority) ለመቀዳጀት ማለም እንጀምራለን:: ይህ ትልማችን ግላዊ ጥቅመኝነትን(striving for personal superiority): አልያም የሌሎችን ሰዎች ጥቅምን ከግምት ውስጥ ያስገባ(striving for social interest) ሊሆን ይችላል:: ይህ የአድለር አተያይ ውስጣዊ ሃይልን (sex and aggression) እንደ የሰው ልጅ አብይ ባህርይ ዘዋሪ አድርገው ከሚቀበሉት  ቀደምት የሳይኮዳይናሚክ አስተምህሮ ተከታዮች ለየት ያደርገዋል:: ታዲያ በዚህ ሁሉ ሂደት አስተዳደጋችን ወሳኝ ሚና አለው::                                                                                                                                                                                           እድገታችን በፍቅር የተዋጀ እንደሆነ ፥  አብሮን የተፈጠረው የበታችነት ስሜት ለማሸነፍ የሚኖረን መሻት ከማህበረሰቡ ፍላጎት እና እሴት ያላፈነግጠ እና ለራስ ጥቅም ብቻ ያላደላ ይሆናል::  በጥቅሉ ውለታችንን አንረሳም እንደማለት ነው::  እነዚህ ሰዎች መዳረሻቸውን በአግባቡ የሚረዱ እና ንቃተ ህሊናቸው የዳበረ ነው:: በአንጻሩ ደግሞ አጉል ተቀማጥለው አልያም ትኩረት ተነፍገው ያደጉ ልጆች ከልክ ያለፈ ለራስ ጥቅም የማድላትና ግላዊ ልዕልናን የመሻት ዝንባሌ ይስተዋልባቸዋል:: በበታችነት ስሜት የሚፈተኑ ናቸው ይለናል አድለር::    ▪️ ትኩረት ተነፍገው ያደጉ እንደሆነ: ማህበረሰቡን በጥርጣሬ አይን     የሚያዩ: ከሌሎች ጋር መተባበር የሚቸግራቸው: ቀናተኞች ሊሆኑ     ይችላሉ::                                                                               ▪️ ቅምጥሎቹ ደሞ ከወላጆቻቸው ጋር የነበራቸው ጥገኛ ግንኙነት    በሌላ የህይወት ምዕራፋቸውም አብሯቸው ይዘልቃል:: ሁሌም ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ይሻሉ:: ትኩረት ፈላጊዎችም ይሆናሉ:: በዚህ ጽንሰሃሳብ መሰረት ሰዎችን እንረዳለን የሚሉ ግለሰቦችን በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን:-      የምር የሰዎች መቸገር አስጨንቋቸው የሚረዱ                Vs    በመርዳት ስም ተረጂው ከነሱ በታች መሆኑን ለማሳየት እና እንዲሽቆጠቆጥላቸው በመፈለግ: እንዲሁም ለጋስ ናቸው ተብለው እንዲወራላቸው በማሰብ የሚረ'ዱ (በእርዳታ ወቅት ካሜራ የማይለያቸው ሰዎችን ለዚህ እንደምሳሌ ማቅረብ ይቻል ይሆን?😏)                                                                                                                እርስዎ የግል ጥቅምዎን ያስቀድማሉ ወይንስ የግል ጥቅምዎን ከማህበረሰብ ፍላጎት ጋር ሳያጋጩ ማስኬድን ያውቁበታል? ቸር ይግጠመን ❕ ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት https://t.me/DrEstif https://www.facebook.com/DrEstif https://www.tiktok.com/@drestifanospsychatrist?_t=8n5FE9pFB5C&_r=1
Show all...
1
እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ? አቶ A የ 40 አመት ጎልማሳ ነው:: በልጅነቱ ነበር ውትድርና የተቀጠረው:: ታድያ ''በውትድርና ህይወቴ ብዙ ብዙ ደጋግ ሰዎች ስራብ አብልተውኛል፣ ስጠማ አጠጥተውኛል፣ ስታረዝ አልብሰውኛል እና ውለታቸው አለብኝ'' ይላል:: እናም ገንዘብ ሲኖረው ሰዎችን መርዳት የሁል ጊዜ ህልሙ ነበር:: ከአመታት አገልግሎት በኋላ ጡረታ ይወጣል:: ለአገልግሎቱም ተደራጅቶ መሬት ይሰጠውና ያንን መሬት በጥሩ ገንዘብ ይሸጠዋል:: ታድያ ይሄኔ ሰዎችን የመርዳት ህልሙ ያይልና ተቸገርኩ ላሉት ሰዎች በሙሉ የችሮታ እጁን መዘርጋት ይጀምራል:: ያው በወጣው ልክ አልተካውም እና ገንዘቡ እየተመናመነ ወደማለቁ ይቃረባል:: አቶ A እንዲህ ይላል.. ''ሰዎች ጠይቀውኝ ሳልረዳቸው ከቀረሁ ጸጸቱን አልችለውም:: እናም ይህ ጸጸት እንዳይሰማኝ እና የህሊና እረፍትን ለማግኘት ስል ሰዎችን መርዳት እንዳለብኝ አምኛለሁ::'' አሁን ላይ አቶ A ትዳር ለመያዝና እና ልጆችን ለመውለድ ወጥኗል ፤ ግን ደግሞ ወረቱ እያለቀበት ነው እና እንቅፋት እንዳይሆንበት ሰግቷል::  ወረት መያዝ ቢሻም ንፉግ የሆነ እየመሰለው ተጨንቋል:: እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ? ▪️ለአቶ A ምክራችሁ ምን ይሆን?  መስጠቱን መቀጠል ነው ያለበት ወይንስ ስለራሱ ማሰብን መጀመር አለበት? ▪️ለመሆኑ ለጋስነት ችግር ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ? ▪️የአቶ A ለጋስነት የስነልቦና እክል ወይንስ በጎ ምግባር? ይህን ታሪክ በፋና ሬዲዮ ከሚተላለፈው  'እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ' የሚል ዝግጅት የወሰድኩት ነው:: እኔም ሙያዊ አስተያየቴን ለመስጠት ሞክሬያለሁ:: ስለ አዕምሮ ጤና መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የማህበራዊ አማራጮች ይከተሉ:- https://t.me/DrEstif https://www.facebook.com/DrEstif https://www.tiktok.com/@drestifanospsychatrist?_t=8n5FE9pFB5C&_r=1
Show all...
Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

ስለ አዕምሮ ጤና እንወያያለን! ለማማከር በ 0949476776 ይደውሉ:: Inbox me via telegram @DrEstifanos

እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ? አቶ A የ 40 አመት ጎልማሳ ነው:: በልጅነቱ ነበር ውትድርና የተቀጠረው:: ታድያ ''በውትድርና ህይወቴ ብዙ ብዙ ደጋግ ሰዎች ስራብ አብልተውኛል፣ ስጠማ አጠጥተውኛል፣ ስታረዝ አልብሰውኛል እና ውለታቸው አለብኝ'' ይላል:: እናም ገንዘብ ሲኖረው ሰዎችን መርዳት የሁል ጊዜ ህልሙ ነበር:: ከአመታት አገልግሎት በኋላ ጡረታ ይወጣል:: ለአገልግሎቱም ተደራጅቶ መሬት ይሰጠውና ያንን መሬት በጥሩ ገንዘብ ይሸጠዋል:: ታድያ ይሄኔ ሰዎችን የመርዳት ህልሙ ያይልና ተቸገርኩ ላሉት ሰዎች በሙሉ የችሮታ እጁን መዘርጋት ይጀምራል:: ያው በወጣው ልክ አልተካውም እና ገንዘቡ እየተመናመነ ወደማለቁ ይቃረባል:: አቶ A እንዲህ ይላል.. ''ሰዎች ጠይቀውኝ ሳልረዳቸው ከቀረሁ ጸጸቱን አልችለውም:: እናም ይህ ጸጸት እንዳይሰማኝ እና የህሊና እረፍትን ለማግኘት ስል ሰዎችን መርዳት እንዳለብኝ አምኛለሁ::'' አሁን ላይ አቶ A ትዳር ለመያዝና እና ልጆችን ለመውለድ ወጥኗል ፤ ግን ደግሞ ወረቱ እያለቀበት ነው እና እንቅፋት እንዳይሆንበት ሰግቷል::  ወረት መያዝ ቢሻም ንፉግ የሆነ እየመሰለው ተጨንቋል:: እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ? ▪️አቶ A ምን ምክራችሁ ምን ይሆን?  መስጠቱን መቀጠል ነው ያለበት ወይንስ ስለራሱ ማሰብን መጀመር አለበት? ▪️ለመሆኑ ለጋስነት ችግር ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ? ▪️የአቶ A ለጋስነት የስነልቦና እክል ወይንስ በጎ ምግባር? ይህን ታሪክ በፋና ሬዲዮ ከሚተላለፈው  'እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ' የሚል ዝግጅት የወሰድኩት ነው:: እኔም ሙያዊ አስተያየቴን ለመስጠት ሞክሬያለሁ:: ስለ አዕምሮ ጤና መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የማህበራዊ አማራጮች ይከተሉ:- https://t.me/DrEstif https://www.facebook.com/DrEstif https://www.tiktok.com/@drestifanospsychatrist?_t=8n5FE9pFB5C&_r=1
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ለሌሎች ማዘናችን ከንፈር ከመምጠጥ(pity) እና ከስሜት አልባ 'ችግርህን/ችግርሽን እረዳለሁ' ይትበሃል (Sympathy)  ከፍ ያለ ቢሆን እንዴት መልካም ነበር:: ለኛ ቀላል የመሰለን ለሌሎች ከባድ የህይወት ሸክም ሊሆንባቸው እንደሚቻል መረዳት ተገቢ ነው:: ቢቻለን ጉዳዩን በባለጉዳዩ ቦታ ሁኖ ለመመልከት መሞከር... ከፍ ሲልም አለንላችሁ ልንላቸው የተገባ ነው::  ያኔ የአንድን ክቡር ሰው ህይወት አቀናን ማለት ነው:: 'ለሰው መድሃኒቱ ሰው ነው' ይባል የለ! መልካምነት ደግሞ ለራስ ነው እንደሚባለው.. አንድ ቀን እኛም የሰዎችን እርዳታ የምንሻበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላልና: ለሌሎች መልካምነትንና ርህራሄን ለማሳየት አንስነፍ:: ቸር ይግጠመን! ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይወዳጁ: ለሌሎችም ያጋሩ https://www.facebook.com/DrEstif https://t.me/DrEstif https://www.tiktok.com/@drestifanospsychatrist?_t=8n5FE9pFB5C&_r=1
Show all...
👍 4💯 1
Photo unavailableShow in Telegram
ለሌሎች ማዘናችን ከንፈር ከመምጥ(pity) እና ከስሜት አልባ 'አይዞህ/አይዞሽ' መባባል(Sympathy) ከፍ ያለ መደጋገፍ ቢኖረን መልካም ነው:: ለኛ ቀላል የመሰለን ለሌሎች ከባድ የህይወት ሸክም ሊሆንባቸው እንደሚቻል መረዳት ተገቢ ነው:: ቢቻለን ጉዳዩን በባለጉዳዩ ቦታ ሁኖ ለመመልከት መሞከር... ከፍ ሲልም አለንላችሁ ልንላቸው የተገባ ነው:: ያኔ የአንድን ክቡር ሰው ህይወት አቀናን ማለት ነው:: ለሰው መድሃኒቱ ሰው ነው:: መልካምነት ደግሞ ለራስ ነው እንደሚባለው.. አንድ ቀን እኛም የሰዎችን እርዳታ የምንሻበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላልና: ለሌሎች መልካምነትንና ርህራሄን ለማሳየት አንስነፍ:: ቸር ይግጠመን! ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት
Show all...
1
Photo unavailableShow in Telegram
ስሜቶቻችን አውድ ጠብቀው መፈራረቃቸው ለህይወታችን ጣዕምን ሰጠውልናል:: በሚያስደስተው እየተደሰትን፣ ማልቀስም ሲኖርብን እያለቀስን ሰውነታችንን መዋጀት አለብን:: አልያ ከሮቦት አልተሻልን! አሁን ላይ በስፋት ስለ ድብርትና ከፍተኛ የሃዘን ችግር(Prolonged grief disorder) መስማታችን: ምናልባትም በሃዘን ወቅት ይደረግ የነበረው 'እርምን የማውጣት' ክዋኔ እየቀረ ከመምጣቱ ጋር ይገናኝ ይሆን?? የታመቀ ስሜት ልክ እንደ ረመጥ ነው: እፍ የሚለው ሽውታ ሲያጋጥመን መልሶ መፋጀቱ አይቀርም:: ደግሞም እንደ አዥ ነው: ቀስ በቀስ ሙሉ የሰውነት ስርአትን የሚያውክ እና ከበሽታ የሚጥል:: ስሜቶቻችንን አጉል መግታት ከተፈጥሮ እና ከፈጣሪ እንደመጣላት ነው:: ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት https://t.me/DrEstif https://www.facebook.com/DrEstif
Show all...
👍 6🤔 2
ልጆች ልክ እንደወላጅ | Parentification ወላጆች በጽኑ ቢታመሙ፣ በሞት ሲለዩ፣ በሱስ: በአለመግባባትና መሰል ጉዳዮች ቤተሰቡን ማስተዳደር ሲሳናቸው እና በመሳሰሉ ምክንያቶች ልጆች የወላጅን ሚና ተክተው ቤተሰብን እንዲያስተዳድሩ ሊገደዱ ይችላሉ:: ▫️ይህ ጉዳይ በሃገራችን በስፋት ይስተዋላል:: በተለይም የመጀመርያ ልጆች ታናናሾቻቸውን ልክ እንደ ወላጅ ሁነው እንዲያሳድጉ ሃላፊነት ሲወስዱ ማየት የተለመደ ነገር ነው:: ታናናሾቻቸውን ለማሳደግ ራሳቸውን መስዋዕት ያደረጉ ብዙ አሉ:: 🔻እነዚህን ሃላፊነቶች በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን:- ▪️Instrumental/ቁሳዊ/ parentification- ይህ ልጆች የቤተሰብን ቁሳዊ/አካላዊ ፍላጎት እንዲያሟሉ ሃላፊነት ሲጣልባቸው ነው:: ለቤተሰቡ ምግብን ማቅረብ: ስራ ሰርቶ ገቢ ማስገኘት: የቤተሰብ ቢዝነሶችን ማሳለጥ እና የመሳሰሉ ጉዳዮችን እንዲከውኑ ይጠበቅባቸዋል:: ▪️Emotional Parentification- ይህ ደግሞ ለቤተሰቡ ስነልቦናዊና እና የስሜት ድጋፍን የመስጠት ሃላፊነት የተጣለባቸውን ይመለከታል:: ✅ ስነልቦናዊና ማህበራዊ ዳራው ምን ይመስላል? ▫️ይህን ሃላፊነት በተለይም ከአፍላነታቸው ጀምረው የተሸከሙት እንደሆነ: እንደየእድሜያቸው የሚጠበቀውን ስነልቦናዊና ማህበራዊ የእድገት ደረጃዎች(psychosocial development) እንዳያሳኩ እንቅፋት ሊሆንባቸውና ለተለያዩ ስነልቦናዊና ማህበራዊ ቀውሶች ሊያጋልጣቸው ይችላል:: ▫️በእድሜያቸው አለመብሰል ምክንያት አስቸጋሪ አጋጣሚዎችን የመቋቋምያ መንገዶቻቸው(coping) በደምብ የዳበሩ አለመሆኑ ለችግር ተጋላጭነታቸውን ይጨምረዋል:: ነገሮችን በጥልቀት እንድንመዝን እና እንድናገናዝብ የሚያደረገው የአንጎላችን ክፍል( Prefrontal cortex) ስራውን በደምብ መከወን የሚጀምረው በሃያዎቹ እድሜያችን ገደማ እንደሆነ ይታመናል:: አንዳንድ ቀድመው የሚበስሉ(early matures) እንዳሉ ሁነው:: ▫️በትምህርት አለመግፋት፣ በኢኮኖሚ አለመደርጀት፣ ለጭንቀት: ለድብርት ህመም ፣ ለአጽ ተጠቃሚነት: የስብዕና መዛነፍና ለመሳሰሉ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ችግሮች የሚጋለጡት ብዙ ናቸው:: ▫️ ደግሞም በሌላ አንጻር ቤተሰብ በመምራት ሂደት የሚኖራቸው ተሞክሮ መልካም ከሆነ: በራስ መተማመናቸው የዳበረ እና ችግሮችን የመቋቋም እና የመፍታት ችሎታቸው የተሻለ ሊሆን ይችላል:: Internal locus of control ይኖራቸዋል:: ** አሻም! ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት https://www.facebook.com/DrEstif https://t.me/DrEstif
Show all...
👍 6

Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

The_Body_Keeps_the_Score_Brain,_Mind,_and_Body_in_the_Healing_of.pdf8.04 MB
👍 7