cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

chirstian Tube

🎤 ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻውን ያድናል፤ ተመልሶም ይመጣል

Show more
Advertising posts
327
Subscribers
No data24 hours
+17 days
-230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የፀሎት ሃይል .pdf6.24 MB
🥰 2
የኢየሱስ ስሞች ማዕረጎች የእርሱን #መለኮትነት ያመለክታሉ --> ኢየሱስ -------- ጌታችን አዳኝ ነው (ማቴ 1;21) --> አማኑኤል -------- እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው (ማቴ 1;23) -->ኤሎሂም -------- እግዚአብሔር ኃያል ፈጣሪ ነው (2ጴጥ 1;1) -->የሰው ልጅ --------ይህ ስም በራሱ በኢየሱስ የተወደደና የተከበረ የማዕረግ ስም ነው (ማቲ 26;63-66 , ማር 10:45 ,ማቲ 19:20 ) -->ክርሰቶስ ------የተቀባ/መሲህ (ማቴ 11:1-6 , 16:16) -->ያህዌህ ------"እግዚአብሔር ካዳኑን የሚጠብቅ አምላክ ነው /የማንነቱ መገለጫ ስሙ ነው" ( ዘፀ 3:14 , ዮሐ 8:58 ) -->የእግዚአብሔር ልጅ ------ከዘላለም ከአብ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚገልፅ ሆኖ እግዚአብሔር እንደሆነ ያሳየናል። -->የዳዊት ልጅ  ------ለዳዊት ልጅ በተሰጠው ቃል መሠረት ለዘላለም በዙፋኑ የሚቀመጥ ንጉሥ መሆኑን ለማመልከት ነው (2 ሳሙ 7:1-16 , ሉቃ,1:26-33, ማቴ 21:9-11) -->የበኩር ልጅ ------ከሌሎች ልጆች ቀድሞ የተወለደ ለማለት ሳይሆን ያለውን የመውረስ መብት ለማሳየት ሲባልና ያለውን ስልጣን ለማመልከት ነው። (ቆላ 1:15-18 , ሮሜ 8:29,, መዝ 2:6-9 , ዕራ 1:5)
Show all...
🔥 1🥰 1👏 1
#እንደ_እባብ_ልባም_ሁን! #1ኛ_እባብ_ጥገኛ_አይደለም! እንደ እባብ ልባም ሁን ማለት ሰረኛ ሁኑ ተንኮለኛ ሁን ማለት አይደለም ጥገኛ አትሁን ማለት ነው፡፡ #2ኛ_እባብ_የኃይል_ስፍራውን_ያውቃል! ቀድሞ የምገነባው ውስጣዊ ማንነቱ ስብዕናውን ነው እንደ እባብ ልባም ሁን ማለት ከክስ ይልቅ ውስጥ ስብዕና ግንባታ ቅድምያ ስጥ ማለት ነው፡፡ ለውስጥ አንተነትክ ለመንፈሳዊነትክ ማለት ነው #3ኛ_ጉድለቱ_እንቅፋቱ_አይደለም! እባብ እግር የለውም እጅ የለውም የአይን ሽፋን የለውም የማየት አቅም በጣም ደካም ነው #እባብ ዶንቆሮ ነው ጆሮ የለውም የምገርመው ከየትኛው ፍጥረት በላይ አካባብውን ያስሳል፡፡ ይሄ ሁሉ ነገር ስይኖረው አሳድዶ ይውጣል ከአንበሳና ከዝሆን ጋር ይገጥማል እንደ እባብ ልባም ሁን ማለት በሌለህ ነገር ተስፋ ቆርጠህ ስለለህ ነገር እያሰብክ አትቀመጥ ማለት ነው ያለህ ነገር ይበቃሃል ለመቀጠል ማለት ነው፡፡ #4ኛ_እብባ_ላመነበት_ነገር 💯% ራሱን ይሰጣል! በራሱ ሙሉነትን ጥንካሬ ያምናል Self Confidence ይኑርህ አይን የለውም ጆሮ የለውም እንደሚያሸንፍ እርግጠኛ ሆኖ እራሱን ይሰጣል እንደ እባብ ልባም ሁን ማለት ለተሰማራህበት ጉዳይ ለአገልግሎት ለጌታ ሙሉ ለሙሉ እራስን ስጥ ማለት ነው፡፡ #5ኛ_እባብ_በችግር_ውስጥ_ፀባየኛ_ነው፡፡ እባብ በጣም በረሃ በጣም ቀዝቃዛ ምግብ በሌለባቸው ቦታዎች ረጅም ሰዓት ይቆያል አድኖ እስከሚያገኝ ድረስ አፈር ይበላል ድንጋፍ ይበላል #አፈር እየበላ የራብ ዘመኑን ያሳልፋል ፀባየኛ ነው ትዕግስተኛ ነው፡፡ እባብ በየትኛውም Condition የመኖር አቅም አለው ይጠግባል ይኖራል ይርበዋል ይኖራል፡፡ #6ኛ_እባብ_አባካይኝ_አይደለም! አያባክንም ምግቡን ሳያባክን ነው የምጠቀመው #አንድን ነገር አድኖ ስውጠው ቀንዱም ጥፍሩን ፀጉርንም ቆዳውንም ነው የምውጠው Effectively ነው የምበላው፡፡ #7ኛ_እራሱን_መጠበቁ_ነው_ለራሱ_ይጠነቀቃል እኛ ብዙዎቻችን ለራሳችንን አንጠነቅቅም ጳውሎስ ጢሞቶስን ለራስ እና ለትምህርትህ ተጠንቅቅ አለው በዚህም እራስህንም የምሰሙህ ታድናለህ አለው፡፡ #እባብ እየተጠላ የሚበዛበት ምክንያት ይሄው ነው እነዚህ ናቸው፡፡ “እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።” — ማቴዎስ 10፥16
Show all...
🔥 3
ጆሆቫ_ዊትነስ_jw.pdf3.33 KB
🔥 1
awaled-all-cr.pdf1.04 MB
🥰 1
ሞርሞን_mormonism_.pdf2.17 KB
1
WHAT IS FAITH by R.C. Sproul.pdf6.48 KB
ኖስቲሲዝም ምንድን ነው? መልስ፤ ኖስቲሲዝም የእግዚአብሔርን መኖር ማወቅ ወይም ማረጋገጥ አይቻልም የሚል አመለካከት ነው፡፡ኖስቲክ / agnostic/ የሚለው ቃል በመሰረቱ ያለእውቀት መሆን “without knowledge.” ማለት ነው፡፡ ኖስቲሲዝም በእወቀት የሆነ የእግዚአብሔር የለሾች ክህደት ነው፡፡ ክህደት /atheism/ የሚለው ሊረጋገጥ በማይችልበት መልኩ እግዚአብሔር የለም ነው የሚለው፡፡ ኖስቲሲዝም የሚከራከረው የእግዚአብሔርን መኖር ማረጋገጥ ይቻላል ውይም አይቻልም፤ ለዛም እግዚአብሔር መኖሩን ወይም አለመኖሩን ማወቅ አይቻልም በማለት ነው፡፡ በዚህ ኖስቲሲዝም ትክክል ነው፤ የእግዚአብሔርነ መኖር በተግባር በተፈተነ በተለመደ መልኩ ማረጋገጥ ወይም አለማረጋገጥ አይቻልም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን መኖር በእምነት መቀበል እንዳለብን ይነግረናል፡፡ ዕብ 11፡6፤- ‹‹ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።›› እግዚአብሔረ መንፈስ ነው፡፡ (ዮሐ 4:24) ስለዚህም በዓይን ሊታይ ወይም ሊዳሰስ አይችልም፡፡ እግዚአብሔር ራሱን ሊገልጠ ካልወደደ በቀር በእኛ የስሜት ህዋስ ሊታይ አይችልም፡፡ (ሮሜ 1:20). መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን የእግዚአብሔር መኖር እንዲሁ በፍጥረት ላይ በግልጽ ማየት ይቻላል፡፡ (መዝ 19:1-4) በተፈጥሮ ውስጥ ሊታወቅ ይችላል፡፡ (ሮሜ 1:18-22) በልባችን ደግሞ እርግጠኞች እንሆናለን፡፡ (መክ 3:11). ኖስቲሲዝም የእግዚአብሔርን መኖር ወይም አለመኖር ማረጋገጥ አይፈልግም፡፡ እንዲሁ በአጥሩ ዙሪያ ርቆ እንደመቆም አይነት “straddling the fence” ነው፡፡ አማኒያን /Theists/ እግዚአብሔር አለ ብለው ያምናሉ፡፡ አምላክ የለሽ ካሃዲዎች /atheism/ እግኢአብሔር የለም ብለው ያምናሉ፡፡ ኖስቲስዝም/agnosticism/ እግዚአብሔር አለ ወይም የለም ብለን ማመን የለብንም ብሎ ያምናል፤ ምክንያቱም በሁለቱም መልኩ ማወቅ ስለማይቻል፡፡ ለክርክር እንዲሆነን የእግዚአብሔርን መኖር በግልጽና በማይካድ መልኩ ሊያረጋግጥልን የሚችል መረጃ እናንሳ፡፡ ሴይዝም /አማኒያን/ እና ኖስቲሲዝምን በአንድ ተርታ ብናስቀምጥ የትኛው ነው ከሞት በኋላ ህይወት እንዳለ የበለጠ መረዳት ሊሰጠን የሚችለው? እግዚአብሔር ከሌለ ሴይዝም /አማኒያን/ እና ኖስቲስዝም ተቀባይነት በሌለው መልኩ ከሞት በኋላ መኖር አይችሉም፡፡ እግዚአብሔር ካለ ግን ኖስቲሲኮች /agnosticism/ እና በሚሞቱበት ጊዜ ምላሽ የሚሰጥላቸው ያስፈልጋቸዋል፡፡ ከዚህ ሃሳብ በመነሳት ኖስቲክ/agnosticism/ ከመሆን ወይም በኖስቲስዝም ከማመን ይልቅ ሴይዝም አማንያን መሆን ትርጉም ይሰጣል፡፡ በሁለቱም ስፍራ በመሆን ሊረጋገጥ ቢችልም ባይችልም መጨረሻ በሌለው እና በዘለአለም ተገቢውን ውጤት ሊያስገኝ የሚችለውን ስፍራ በሂደት መፈተን የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ ጥበበኘነት ሳይሆን አይቀርም የጥርጣሬ መኖር የተለመደ ነገር ነው፡፡ በዚህ አለም ላይ ልንረዳቸው የማንችላቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ብዙዎች የእግዚአብሔርን መኖር ይጠራጠራሉ ምክንያቱም እርሱ በሰራቸውና በፈቀዳቸው ነገሮች አይስማሙም ውይም አልተረዱትም፡፡ ሆኖም ግን እኛ ውስን የሆንን ሰዎች ወሰን የሌለውን አምላክ ልንረዳው አንችልም፡፡ ሮሜ 11:33-34፡-‹‹የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም። የጌታን ልብ ያወቀው ማን ነው? ወይስ አማካሪው ማን ነበር? ወይስ ብድራቱን ይመልስ ዘንድ ለእርሱ አስቀድሞ የሰጠው ማን ነው?›› በእምነት በእግዚአብሔር ልናምን ይገባል፤ መንገዱንም በእምነት ልንታመነው ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር በእርሱ ለሚያምኑ በአስደናቂ ሁኔታ ራሱን ለመግለጽ ፈቃደኛ እና ዝግጁ ነው፡፡ ዘዳ 4፡26 ‹‹ ነገር ግን ከዚያ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትሻላችሁ በልብህም ሁሉ በነፍስህም ሁሉ የፈለግኸው እንደ ሆነ ታገኘዋለህ።
Show all...
👍 1
መጽሐፍ ቅዱስ ስለብልጽግና ወንጌል ምን ይላል? መልስ፤ በብልጽግና ወንጌል እንደሁም የእምነት ቃል “Word of Faith,” ተብሎ በሚታወቀው አማኞች መጽሐፍ ቅዱሳዊ የክርስትና እውነት ጋር የተቃረነ እግዚአብሔር ክርስቲያኖችን የሚጠቀምባቸው ሆኖ ሳለ እግዚአብሔርን መጠቀሚያ እንዲያደርጉ ተነግሮአቸዋል፡፡ የእምነት ቃል ወይንም የብልጽግና ስነመለኮት መንፈስ ቅዱስ አማኞችን የፈቀዱትን ሁሉ ለማስፈጽም የሚጠቅም አድርጎ ያስቀምጣል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው እንደሆነና አማኞች የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲፈጽሙ የሚያስችላቸው እንደሆነ ነው፡፡ የብልጽግና ወንጌል በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ሰርጎ የገባውን አጥፊ ስስታም አካለት ጋር በጣም ይመሳሰላል፡፡ ጳውሎስና ሌሎች ሐዋሪያት እንደዚህ አይነት ነፋቄ ከሚያስተምሩ ከሃሰት አስተማሪዎች ጋር አልተባበሩም ወይም አልተስማሙም፡፡ አደገኛ የስህተት አስተማሪዎች ብለው ለይተው አወጧቸው እና ክርስቲያኖችም እንዲሸሹአቸው እጥብቀው አስገነዘቡአቸው፡፡ ጳውሎስ ስለእንደነዚህ አይነት ሰዎች ጢሞቲዎስን አስጠንቅቆታል 1 ጢሞ 6:5, 9-11. ይህም ማለት በተበላሸ አይምሮ እግዚአብሔርን መምሰል የፍላጎቶቻቸውና የምኞታቸውን የሚያገኝበት አድርጎ ለሚወስዱ ባለጠጎች የባለጥግነት ምኞት በወጥመድ ይጥላቸዋል ቁ.9፡፡ ኃብትን ማሳደድ ለክርስቲያኖች አደገኛ መንገድ ነው፤ እግዚአብሔርም ከሚያስጠንቅቅበት ነገር አንዱ ነው፡፡ ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።ቁ.10 ባለጠግነት ምሳሌነት ላለው ህይወት ምክንያታዊ ግብ ቢሆን ኢየሱስ ይከተለው ነው፡፡ ነገር ግን እርሱ እንደዚያ አላደረገም፤ የመረጠው በእርሱ ሃሰብ ምንም ስፍራ እንዳይኖረው ነው(ማቲ8:20) ደቀመዛሙርቱም እንደዚሁ እንዲያደርጉ አስተማራቸው፡፡ ከደቀመዛሙርቱ ለሃብት ቦታ የነበረው ብቸኛው ሰው ይሁዳ ብቻ እንደነበር ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ጳውሎስ መመኝት ጣኦትን ማምለክ ነው ብሎአል፡፡(ኤፌ 5:5) ለኤፌሶን ሰዎች ማንም የመመኘትን የኃጢያተኝነትን ሃሳብ እንዳያቀርብ መመሪያን ሰጥቶአቸዋል፡፡ (ኤፌ 5:6-7). ብልጽግና እግዚአብሔር በራሱ እንዳይሰራ ይከለክለዋል ማለትም እግዚአብሔር የሁለም ነገር ጌታ ባለቤት አይሆንም ምክንያቱም እኛ እንዲሰራ እስካልፈቀድንለት ድረስ ሊሰራ አይችልም፡፡ እንደ እምነት ቃል አስተምህሮ ለእግዚአብሔር መሸነፍ በእግዚአብሔር መታመን አይደለም፤ እምነት የብልጽግና አስተማሪዎች አለመን የሚቆጣጠር መንፈሳዊ ህጎችን የማምታታት ስልት ቀመር ነው፡፡ ‹‹የእምነት ቃል›› ስም የሚያመለክተው ይህ እንቅስቃሴ የሚያስተምረው እምነት እኛ የምንለው ከምንታመነውና ወይንም ምንም አይነት አውነት ብንይዝ በልባችንም እርግጠኛ ከሆንበት ከዛ ይበልጣል፡፡ በእምነት እንቅስቃሴ የተለመደው የተወደደ ቃል መልካምን ማወጅ ነው “positive confession.”፡፡ይህ የሚያመለክተው ቃሎቹ በራሳቸው የመፍጠር ኃይል እንዳለቸው ነው፡፡ አንተ የምትናገረው የእምነት እንቅስቃሴ አስተማሪዎች እንደሚሉት ለአንተ የሚሆነውን ሁሉ ይወስናል፡፡ የአንተ አዋጅ ከእግዚአብሔር ለመቀበል ከፈለግክ ሁልጊዜ ያለመናውጥ መልካም መናገር አለብህ፡፡ እግዚአብሔርም ለመመለስ ይገደዳል (እግዚአብሔርን ሰው ሊያስገድደው እንደሚችል ይመስል!) እንግዲህ የእግዚአብሔር እኛን የመባረክ ችሎታ በእኛ እምነት ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ ያዕ 4፡13-16 ከዚህ ትምህርት ጋር በቀጥታ ይጋጫል፡፡‹‹ አሁንም ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና።ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና።›› እንኳን ወደፊት ነገሮች ወደ መኖር እንዲመጡ ለመናገር ቀርቶ ነገ የሚያመጣውን እንኳን አናውቅም፤ መኖራችንንም እንኳ አናውቅም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኃብት አስፈላጊነት ትኩረት ከመስጠት ይልቅ በተቃራኒው እንዳንከተለው ያስጠነቅቀናል፡፡ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ክርስቲያኖች ይልቁንም አማኞች ከገንዘብ ፍቅር ነጻ መሆን አለባቸው (1 ጢሞ 3:3) (ዕብ 13:5). ገንዘብን መውደድ ወደ ክፋት ሁሉ ይመራል፡፡l (1 ጢሞ 6:10). ኢየሱስ አስጠንቋል፡- ‹‹የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ አላቸው።›› (ሉቃ 12:15). ከዚህ ፈጽሞ በተለየ የእምነት ቃል ገንዘብን ስለማግኝት እና በኑሮ መክበር /possessions in this life/ ኢየሱስ ሲናገር፤- ‹‹ ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤›› (ማቲ 6:19). ሊታረቅ የማይችል ግጭት በብልጽግና ወንጌል ትምህርት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ትምህርት መካከል በተጨማሪ በይበልጥ በኢየሱስ በኢየሱስ ክርስቶስ ንግግር ተገልጾአል ማቲ 6:24, “ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም”
Show all...
ሰባቱ ገዳይ ኃጢአቶች ምንድናቸው? መልስ፤ ሰባቱ ገዳይ ኃጢአቶች ዝርዝራቸው በመነሻ ጥቅም ላይ የዋለው በጥንት የክርስቲያን ትምህርት ነው፣ ተከታዮችን ለማስተማርና ለማስጠንቀቅ፣ የወደቀውን ሰው ኃጢአት አዝማሚያ በተመለከተ። በሰባቱ “ገዳይ” ኃጢአቶች ላይ ያለው የተዛባ መረዳት፣ እነዚህን ኃጢአቶች እግዚአብሔር ይቅር እንደማይል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ ያደረገው፣ እግዚአብሔር ግልጽ ያደረገው ብቸኛው ኃጢአት ቀጣይነት ያለው አለማመን ነው፣ ምክንያቱም እሱ ብቸኛውን ይቅርታ የሚገኝበትን መንገድ ስላልተቀበለ— ኢየሱስ ክርስቶስ እና የእሱን ምትክ ሞት በመስቀል ላይ። የሰባቱ ገዳይ ኃጢአቶች ሐሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን? አዎንም አይደለምም፣ ምሳሌ 6፡16-19 ያውጃል፣ “እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፡ 1) ትዕቢተኛ ዓይን፥ 2) ሐሰተኛ ምላስ፥ 3) ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥ 4) ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ 5) ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥6) በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር፣ 7) በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።” ሆኖም፣ ይህ ዝርዝር አብዛኞቹ ሰዎች የሚረዱት እንደ ሰባቱ ገዳይ ኃጢአት አይደለም። እንደ ታላቁ አቡነ ግሪጎሪ 6ኛ ክፍለ-ዘመን፣ ሰባቱ ገዳይ ኃጢአቶች የሚከተሉት ናቸው፡ ኩራት፣ ምቀኝነት፣ በላተኝነት፣ መጎምጀት፣ ቁጣ፣ ስስት፣ እና ስንፍና። ምንም እንኳ እነዚህ ኃጢአት መሆናቸው ባይካድም፣ እነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ “ሰባቱ ገዳይ ኃጢአቶች” የሚል ገለጻ አያሰጣቸውም። ልማዳዊ የሆነው የሰባቱ ገዳይ ኃጢአቶች ዝርዝር፣ ያሉትን በርካታ የተለያዩ ኃጢአቶች ለመመደቢያ መንገድ ሆኖ ማገልገል ይችላል። ባመዛኙ እያንዳንዱን ዓይነት ኃጢአት ከሰባቱ ምድቦች በአንደኛው ማኖር ይቻላል። እጅግ ጠቃሚ የሚሆነው፣ እነዚህ ሰባት ኃጢአቶች ካሁን በኋላ “ገዳይ” አለመሆናቸውን ነው፣ ከሌላው ኃጢአት በበለጠ። ሁሉም ኃጢአት ውጤቱ ሞት ነው (ሮሜ 6፡23)። እግዚአብሔር ይመስገን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአታችን ሁሉ፣ “ሰባቱን ገዳይ ኃጢአቶችን” ጨምሮ ይቅር ልንባል እንችላለን (ማቴዎስ 26:28፤ ሐዋ. 10:43፤ ኤፌሶን 1:7)።
Show all...