cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Together We Share Mindset

ምላጭ ዛፍ አትቆርጥም ፣ መጥረቢያም ጸጉር አይቆርጥም ሁላችንም ለተፈጠርነበት ዓላማ በጋራ ስንሰራ ተፈጥሮን ምቹና ሳቢ እናደርጋለን ፣ ከብቸኝነት ይልቅ በጋራ ሰርተን በጋራ እንጠቀም ፣ ከአንድ ብርቱ ሁለት መድኃኒቱ እንዲሉ ከኖረ-ሞተ ትርክት ለመውጣት የጋራማድነት አስተሳሰብን አስርጸን በሁለንተናዊ ነገሮች ራሳችንን ሕዝብና አገራችንን ለመጥቀም እንነሳ ፣ ያለፈው ዘመን ይበቃል !

Show more
Advertising posts
219
Subscribers
+124 hours
+27 days
+230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የማንነትህ መለኪያ ስኬት አይደለም “በቅርጫት ኳስ ጨዋታ ዘመኔ:- 👉 9 ሺህ ኳሶችን ሞክሬ ስቼአለሁ፡፡ 👉 300 ውድድሮችን ተሸንፌአለሁ፡፡ 👉 ቡድኔ ለዋንጫ የሚያበቃውን ኳስ እንድወረውር አምነው ሰጥተውኝ ስቼ አውቃለሁ፡፡ 👉 በሕይወቴ ደግሜና ደጋግሜ ወድቄአለሁ፡፡ ለዚህ ነው ስኬታማ የሆንኩት” - Michael Jordan አብዛኛው ሰው ውስጡን የሚነዳው አንድ ጥማት አለው፡፡ ይህ ጥማት የተመሰከረለትና ጥንቅቅ ያለ ስኬታማ ሆኖ ለመታየት ያለው ጥማት ነው፡፡ “እንደዚህ ባደርግ፣ ይህኛውና ያኛው ነገር ቢኖረኝ፣ እዚያኛው ደረጃ ብደርስ ኖሮ … እረካና ሙሉ ስኬት ውስጥ እገባ ነበር” የሚል የውስጥ ጩኸት በብዙ ሰዎች ውስጥ ሲያስተጋባ ይሰማል፡፡ ስለዚህም፣ አንዳንድ ሰዎች ይህንን ጥማት ለማርካት ምንም ነገር ከማድረግና የትኛውንም ድንጋይ ከመፈንቀል አይመለሱም፡፡ የዚህ አመለካት ምንጩ፣ “ሙሉ ማንነት እንዲኖረኝ በኑሮዬ ስኬታማ መሆን አለብኝ” የሚለው አመለካከት ነው፡፡ የዚህ አመለካከትና የሕይወት ዘይቤ ውጤቱ ደግሞ “ስውር” ፍርሃት ነው፡፡ ሙሉ ማንነት እንዲኖረው ስኬታማ መሆን እንዳለበት ያመነ ሰው አለመሳካትን፣ ስህተትንና መውደቅን እጅግ የሚፈራ ሰው ነው፡፡ የሚሰራው ማንኛውም ስራ ስኬታማ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ከማንነቱ ዋጋ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ባለማወቁ ምክንያት ለብዙ ስነ-ልቦናዊ ጥቃት ራሱን ያጋልጣል፡፡ የአንድ ሰው ማንነት የሚለካው በተሳካለትና ባልተሳካለት ነገር ከሆነ፣ ለዚያ ሰው ሩጫ ማቆሚያ፣ ለውድድሩም መጨረሻ የለውም፡፡ ይህ አይነቱ የሕይወት ዘይቤና አመለካከት የሚያስከትለው ዋነኛ መዘዝ የመውደቅ ወይም ስኬት የማጣት ፍርሃት ነው፡፡ ከዚህ የተዛባ የማንነት መመዘኛ ቀውስ ለመውጣት በስኬት ላይ ያለንን አመለካከት መቃኘት አስፈላጊ ነው፡፡ 1. ስኬት ዘርፈ-ብዙ ነው ለምሳሌ፣ አንድ ሰው በስራው ወይም በንግዱ አለም የተዋጣለት ሆኖና ያሰበው ደረጃ ደርሶ፣ በማሕበራዊውም ሆነ በቤተሰባዊው ኑሮው የተበላሸ ሁኔታ ውስጥ ራሱን ሊያገኘው ይችላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ጤንነቱን ችላ ብሎ እውቀትን ወይም ንብረት ሲሰበስብ የሚኖር ሰው በቀኑ መጨረሻ “ስኬታማ ነኝ” ብሎ እንዲናገር የሚያደርገው ነገር ምንድን ነው? ስለዚህም፣ ስኬት የብዙ መሰረታዊና አስፈላጊ እውነታዎች ጥርቅም ነች እንጂ አንድ ገጽታ ብቻ የላትም፡፡ 2. ስኬት የሂደት ጉዳይ ነው ስኬት የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን የሂደት ጉዳይ ነው፡፡ ስኬት፣ “አንድ ደረጃ ካልደረስኩ አልረጋጋም” ማለት ሳይሆን ጉዞውን በመጀመራችንና በሂደት ላይ በመሆናችን መርካትና መረጋጋት ማለት ነው፡፡ ዘርፈ-ብዙ የሆነው የስኬት ምስጢር ዘርፈ-ብዙ የሆነ ጥረትና ትጋት ይጠይቃል፡፡ ስኬታማ ሰው በሁሉም አቅጣጫ በአንድ ጊዜ ጥሩ ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው ነው ብሎ ማሰብ ከእውነት እንድንርቅ ያደርገናል፡፡ 3. ስኬት ተለዋዋጭ ነው ትናንት ቀለል ያለው ሁኔታ ዛሬ ከበድ ሲል፣ ዛሬ የጨመረው ሁኔታ ነገ ሊቀንስ፣ ዛሬ የተነሳሳውና የጋለው ፍላጎት ነገ ቀዝቀዝ ሊል ይችላል፡፡ እንደ ሁኔታውና እንደ እለቱ ስሜት ጥረቱን የሚቀያይር ሰው እንደዚያው አይነት ውጤትን ያተርፋል፡፡ እንደ እለቱ ሁኔታና ስሜት ሳይሆን ከዓላማው አንጻር የሚሰራ ሰው ደግሞ ከዚያው አንጻር ስኬታማ ይሆናል፡፡ ይህ በፍጹም የማይለወጥ ሕግ ነው፡፡ http://t.me/psychologypages
Show all...
ትገዛለህ ፣ ትሸጣለህ ፣ ትጠቀማለህ ! ምንአልባት ይኽ የኑሮ ዘዴ ቀመር ነው ብዬ ልወስደው እችላለሁ። ዓለም ጠቅላላ በመግዛትና በመሸጥ ፣ በመስጠትና በመቀበል ሕግ የምትተዳደር ናት ። በየትኛውም መመዘኛ ከመግዛትና መሸጥ ሕግ የሚወጣ ሰው የለም ! አውቃለሁ መግዛትና መሸጥ ሲነሳ ቀድሞ አዕምሯችን ውስጥ ድቅን የሚለው ከንግድ ሥራ (ማርኬቲንግ) ብቻ ይመስለናል ፣ ይሁን እንጅ ይኸ ከግብይት አንዱ ክፍል ነው እንጅ ከዚህ ውጭም የመግዛትና የመሸጥ አሰራር አለ። ✔️ ከልጅነት እስከ እውቀት ትምህርት ቤት ገብተህ ስትማር እውቀትን እየገዛህ(እየሸመትህ ወይም እየገበየህ) ነበር :: የክፍል በር ሳይረግጡ ዲግሪና ዲፕሎማቸውን በፎርጅድ የሚሸምቱትን ልክም ስለሆነ ለማብጠልጠል ከሸማች ሱቅ የተገዛ ነው ለማለት ቢያስደፍርም ቅሉ በነገሮች አለመመቻቸት በተፈቀደ መመሪያ በርቀት (Distance ) የተማሩትንም ሸማች ማለት ግን face to face የተማርነውንም ቢሆን እጅ በእጅ ገዛነው እንጅ ከሸማችነት አይወጣም ፣ ዋናው ቁምነገሩ እጅ በእጅም ይገዛ በርቀት ዙሮ ዙሮ የተፈጸመው ሽመታ /ግዥ ነው ። ከመጻፍ በፊት ማንበብ ፣ ከመናገር በፊት ማዳመጥ እንደሚቀድመው ሁሉ ከመሸጥ በፊትም መግዛት ይቀድማል (ከመጠምጠም መማር ይቅደም እንዲሉ )። አሁን ተምረህ(እውቀትን ሸምተህ/ገዝተህ) በየትኛዉም የሥራ ዘርፍ ብትቀጠር ፣ ራስህን በራስህ ብቅቀጥር ፣ የፈለግኸውን ያክል ኢንቨስተር ብትሆን #ሽያጭ ላይ ነህ። እውቀትህን ፣ ጉልበትህን ፣ ጊዜህን እየሸጥህ እየተጠቀምህ እንደሆነ አስብ ። ደመወዝ ማለትኮ የጊዜ ፣ የጉልበት ፣ የእውቀት የልምድ ሽያጭ ውጤት ማለት ነው። በቀን ሰራተኛና በመንግሥታዊም ሆነ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በሚሰሩ ሠዎች መካከል ያለው ልዩነት በትንሽና በትልቅ ደመወዝ የመሸጥና ያለመሸጥ ጉዳይ እንጅ ሁላቸውም #ራሳቸውን_የሸጡ ሰዎች ናቸው። (ራሳቸው የሸጡ ማለት ሕሊና የሌላቸው ማለት አይደለም) ያልተማረው ጉልበቱን የተማረው እውቀቱን ሽጦ እየበላ ነው። በአጠቃላይ ዓለም በመግዛትና በመሸጥ መሐል ነው። የሆነ ነገር ትገዛለህ የሆነ ነገር ትሸጣለህ በዚህም ትጠቀማለህ ፣ ሽያጭ ሲነሳ ሸቀጣሸቀጡን ርሳውና:- ✔️ ሐሳብ ይገዛል ሐሳብ ይሸጣል ✔️ መረጃ ይገዛል መረጃ ይሸጣል ✔️ አገልግሎት ይገዛል አገልግሎት ይሸጣል ✔️ ቁስ አካል ይገዛል ቁስ አካል ይሸጣል ✔️እውቀት ይገዛል እውቀት ይሸጣል ✔️ሚዲያው ይገዛል ሚዲያው ይሸጣል ✔️ ቦታው ይገዛል ቦታው ይሸጣል ስለዚህ እውቀትን ብቻ በመሸጥ የሚገኘው ጥቅም አነስተኛ ነውና ሌሎች አማራጮችን (ለምሳሌ ከላይ የተጠቀሱትን) ግዛ ! ሽጥ ! ተጠቀም !
Show all...
✨✨ብሒለ አበው✨✨ 👉 ከቁጣ፡ ከችኮላና ከጥድፊያ ራስህን ትቆጣጠራለህ። ፈጥነህም አትናገር ፡ ፈጥነህም አስተያየት አትሰንዝር፡ ሌሎች ሰዎች ሲናገሩ ጣልቃ አትግባ። እርግጠኛ ባልሆንክበት ነገር ላይ ውሳኔ አታስተላልፍ፡፡ / አቡነ ሺኖዳ/ 👉 ትዕግስት ከሰፊ አእምሮ፡ ግበ ሰፊ ከመሆን የሚገኝ ነው። /ማር ይስሃቅ/ 👉ሰዎች ከሚወቅሷቸው ዳኞች ይልቅ የገዛ ህሊናቸው እየወቀሰ የሚያሰቃያቸው እጅግ ብዙህ ናቸው። /አንጋረ ፈላስፋ/ 👉 ትዕግስት የመልካምነት ዘውድ ነው። /ዮሃንስ አፈወርቅ/ 👉ሳትዘራ ምርት የምትመለከት ከሆነ ትጸጸታለህ፡ የመዝራትን ጊዜ አባክነሃልና። /አቡነ ሺኖዳ/ 👉የሃጥያት መጀመርያና መንደርደርያው ግድየለሽነት፡ አለመጠንቀቅ ነው። / አባ ጴሜን/ 👉መርከብ ያለ ምስማር ሊሰራ እንደማይችል ሁሉ ድኅነትም ያለ ትሕትና ሊገኝ አይችልም። /ቅድስት ስንቀሌጢቃ/ 👉ክርስትያን በተፈጥሮ የማስተዋል፡ የአርምሞ የጥንቃቄ እና የሰላም ሰው ነው። /ቀለሜንጦስ ዘእስክንድርያ/ 👉እርሱ ጻድቅ የሆነ አምላክ ተስፋን ሲሰጥ እታለል ይሆንን ብሎ መጠራጠር ለማን ይቻለዋል! ሊሰጠን ባይፈልግ ኖሮ እንለምነው ዘንድ ባላሻው ነበር፡ /አውግስጦስ/
Show all...
ውድ ቤተሰቦቸ ሰላም እንዴት አላችሁ ? እግዚአብሔር ይመስገን እኔ በጣም ደህና ነኝ ። ይኸንን Together we share mindset የተሰኘን ቻናል ስከፍት ዋና ዓላማዬን ከዲስክሪፕሽን ላይ ያነበባችሁት ይመስለኛል ፣ ዋና ዓላማው የሥራ መንፈስን ማበረታታት አማራሪና ሰዎችን ወቃሽ ከማድረግ ራስን የመፍትሔው አካል አድርጎ መውሰድና ከበጋራ እንብላ( ዛሬ ዛሬ እንብላ የአፍ ልማድ ብቻ ሆኗል እንጅ) ወደ በጋራ እንስራ ፣ በቢዝነሱ ዓለም አንዱ ለአንዱ ሐብቱ ነው(social capital) በማለት በቅንነት የተመሠረተ ነው። ጊዜ ኖሮኝ የማውቀውንና ያለፍኩበትን ሁሉ በየዕለቱ ለእናንተ ለአንባቢያን ለማቅረብ ሰነፍኩኝ ፣ አንድ መያዝ ያለበት ነባራዊ ነገር ምክርና ቡጢ ለሰጪው ቀላል ነው እንዲሉ ዝም ብዬ አቅጣጫ ጠቋሚ ሳልሆን እኔም በመስመሩ እያለፍኩበት ያለ ስለሆነ እኔን ከጠቀመኝ ሰውም ይጠቀም በአፌ ከምናገርም ለውጡን ራሱ ኑሮዬ ይመስክር ብየ እንጅ በ Direct selling industry ሥራ ከጀመርኩ ወራት ተቆጥረዋል ፣ ይኸ ሥራ በትርፍ ሰዓትና ቅዳሜና እሑድ የሚሰራ ኖርማል የመንግሥት ሥራን የማይጋፋ ነው።ሁላችሁም ገለጻ ወስዳችሁ ብትሳተፉ መልካም ነው እያልኩ ምናልባት ወረቱም ጊዜውም እውቀቱም የሚቸግር ከሆነ ዝም ብሎ አንዲትን ደመወዝ ለብዙ ሺህ ጉዳይ ብቂ ብቂ ከማለት በየትኛውም ትርፍ ጊዜ በእጃችሁ በያዛችሁት ስልክ ቢዝነስ መስራት የሚያስችሉ ዘዴዎችን ለጥፌላችኋለሁና ገብታችሁ አይታችሁ ከጠቀማችሁ እንድትሞክሩት ብዬ አጋራኋችሁ። ከቻላችሁ የያዝኩት መስመር ለእኔ አዋጭነቱ ጠቅሞኛል ካልሆነም ከእኔ ጋ ባትሳተፉም በባሌም ይሁን በቦሌ ሰው ተጨማሪ ገቢ በሚያስገኙ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፍ ከምቾት ቀጠናው ወጥቶ ሌሎች አማራጮች ላይ እንዲያተኩር እፈልጋለሁና እናንተ ምናልባት በወቅታዊ ትኩሳት ተጠምዳችሁ እንዲህ ሆነ እንዲህ ተደረገ ፣ ሰይፉ ማንትሴን አቀረባት ፣ እግርኳስ የከሌ አሸነፈ ፣ የየከሌ ፊልም አቤት ሲማርክ ፣ እዚህ ጋ መንገድ ተዘጋ እዚህ ጋ ተከፈተ ጦርነት ሆነ ረሃብ መጣ ወዘተ ዩቱብ ላይ ተጥዶ መዋል ፣ ከማንም ቲክቶከራም ጋር ሲንተከተኩ ከመዋል ( ቲክቶከሮች ፣ ዩቱበሮች እንዲህ የማይሆነውን የሚሆኑት ለአንተ አዝነው ሳይሆን ለቢዝነሳቸው ነው) አንተም እንደ እነርሱ ዘመኑ ባመጣው ቴክኖሎጅ ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኙ ሥራዎችን መፈለግና መተግበር ግድ ይልሃል ወንድማዊ ምክሬ ነው። ንግድ ብትል ካፒታሉ ፣ መስሪያ ቦታ ፣ የሰው ሃይል እውቀቱም ወዘተ ሊያስፈልግህ ይችላል የማንንም እንቶ ፈንቶ ለመለቃቀም ዓይናችን ስክሪን ላይ ከፈጠጠ ላይቀር online Business መስራት የማንችለው ለምንድነው ? ተቀጣሪ ሆኖ ተጨማሪ ገቢ ላይ ቢያንስ ተማሪ በማስረዳትም ይሁን ፣ በድለላ ወይም በሰንደይ ማርኬት የሚሳተፉት 5% አይሞሉም 95%ቱ ግን ለጥ ብሎ ተኝቶ ኧረ ኑሮ ተወደደ ደመወዝ ይጨመረን ጠባቂ ነው። እውነቱን ስነግራችሁ ኑሮው የገቢ ምንጭን በመጨመር እንጅ 15ሺ ቢከፈልህም ለውጥ አያመጣም። እዚህ ጋ ተደብቃችሁ ኃላፊ ጋ እየተሞዳሞዳችሁ በውጭ የምትሰሩ ሰዎች በግልም ሳታሳውቁ የምትሰሩ ወገኖች ቢያንስ አጠገባችሁ ላለ ጓደኛ ኦፖርችኒቲዎችን ንገሩ እናንተ እየተቀየራችሁ በመረጃ እጦት ፣ በግንዛቤ ችግር ወንድማችሁ ወይም እህታችሁ በችግር ስትሰቃይ ማየት ያሳፍራሉ ፣ እኔ ብር የለኝም ፣ ብዙ የተቀየረ ለውጥም የለኝም ግን ከበለጸግሁ በኋላ የስኬት ምስጢሬን አልናገረም ገና እንደጀመርኩት የምሰራውን ለማንም እናገራለሁ የተመቸው ይቀጥላል ያልተመቸው በነበረበት ይቀጥላል ፣ ከሕሊና ወቀሳ ነጻ ነኝ። መልካም ወንድምና ባሕርዛፍ አንድ ነው ምቀኝነት የለም እደግ እንደግ ነው እንዲሉ ፣ መልእክቴ በጋራ እደጉ እንደግ ነው ፣ አንዳንዶች ተኝተው የአንተን መለወጥ ይጠብቃሉ ፣ የቢዝነሱን ስኬትና ውድቀት በአንተ ለመሞከር ይፈልጋሉ Risk taker ካልሆንክ በየትኛውም ዘርፍ ውጤታማ አትሆንም Don't afraid to take cakculated risk in life ! ባይገባን ባንረዳው እንጅ ተምረን ሰዎችን መርዳት ፣ ማግባት መውለድ ፣ የተሻለ ቤት ከመከራየትም በላይ መግዛት እየቻልን የእግር መዘርጊያ በማትበቃ ቤት የደሞዝ እኩሌታ እየከፈልን ያውም ደግሞ ላጤነትን ብቸኛ መፍትሔ አድርገን መኖራችንኮ በራሱ Risk ነው። ስለዚህ ደፋርና ጭስ መውጫ ስለማያጣ የቢዝነሱን Risk አትፍራ ወይ ታተርፋለህ ወይ ትከስራለህ ፣ ሁልጊዜ አታተርፍም ሁልጊዜም አትከስርም ነገር ግን ከየትኛውም ፍርሐት ተላቀህ የትኛውንም ሕጋዊ የገቢ ማግኛ ዘዴ ሞክር ምክሬ ነው።
Show all...
ምንግዜም ስኬት ያለው ከፍርሃት ጀርባ ነው ፣ ራሳችሁ ችግሮች በራሱ ለችግሮች መፍትሔዎች ናቸው ፣ ችግራችን ችግሮችን ወደ መፍትሔ የመለወጥ ሒደት ነው !
Show all...
Show all...
ምንም ገንዘብ ሳታወጡ ጽሁፍ ስለጻፋቹ ብቻ በ1 ገፅ 25$ ድረስ ምታገኙበት ምርጥ ስራ || How to make money online by typing words

#make_money_online #remotejobs #ethiopia ምንም ገንዘብ ሳታወጡ ጽሁፍ ስለጻፋቹ ብቻ በ1 ገፅ 25$ ድረስ ምታገኙበት ምርጥ ስራ || How to make money online by typing words ሊንክ 👉🏽

https://www.textbroker.com/

🚩 Connect with me on social: ✔️ Telegram 👉🏽

https://t.me/sotubee

✔️ TikTok 👉🏽

https://www.tiktok.com/@ashebelay

✔️ ቻናል ማሳደጊያ 👉🏽

https://t.me/sosubtosub

Job from anywhere, remote job from anywhere, online job from anywhere, online job from anywhere in the world, how job online, how to work remote job, how i work remotely, remote jobs ethiopian prophets, evangelical tv, eyu chufa, fana tv, fraytv, holy spirit tv, , jesus tv, kana tv, ltv show, marsil live worship, marsil , zemen drama, youtube research, ዩቱብ ሪሰርች, ሪሰርች, ኢሜል አካውንት, ጂሜል አካወንት, #tiktokvideo #sotube #growontiktok #habesha #CapCut Editing#Effects #tips #ethiopiantiktok #ethiopia #ቴሌግራም #ዩቱዩብ #ethiopian #marketingdigital #abel #capcut ስልክ ጠለፍ | ስልክ መጥለፍ | ኢሞ ጠለፍ | ዋትሳፕ ጠለፍ | ዋይፋይ | ዋይፋይ ጠለፍ | ከርቀት ስልክ መጥለፍ | ነፃ ኢንተርኔት | ዋይፋይ ፓስዎርድ ለመቀየር#yesufapp #ethiopia #eytaye #ethiopiantiktok #ቴሌግራም #አድሰንስ #ethiopian #block #abel #ዋይፋይ #እንዴት #ዮኒማኛ#እሸቱመለሰ #ድንቅልጆች #ድንቅ_ልጆች #wifi #wifi_router #windows10#ethiopia #ethiopiantiktok #ቴሌግራም #አድሰንስ #block #block #ዩቱብ #ዩቱዩብ #ethiopian #marketingdigital #habeshatiktok #phone #lock #lockscreen #how #howto #fix #solve #add #sumsung #android #ebs #fanalamrot #abelbirhanu #donkey #eshetumelese #yonimagna #etvnews #how #እንዴት #ስልክ #አብይአህመድ #ገንዘብ #አደጋ "ስለሞባይልማወቅ ያለብን ድብቅ ሚስጥር" "የሰውንስልክመጥለፍ" #ካርጎ #ቪዛ #ፖስፖርት #ኢትዮጵያ #ህዳሴግድብ #ሳዉዲ #አረቢያ #መካ #ስልክ #መጥለፍ#ጠለፋ #ለመጥለፍ #ከተጠለፈብን #በቀላሉስልክ #ሀክማድረግ#ሀክለማድረግ#ስልክመ ጥለፍ#የፍቅረኛህን #የፍቅረኛህንስልክ #የፍቅረኛህን #በቀላሉ #tstapp #ethioapp #ስልክ ጠለፋ #ሞባይል ለመጥለፍ #እንዴት ይጠለፋል#ሞባይል ሀክ #ሀክ ለማድረግ#ኢሞ ጠለፋ #ኢሞ #ከተጠለፈ #ቢጠለፍ #እንዴት #ፌስቡክ #አቤልብርሀኑ#abelbirhanu #abelbirhanu #የወይኗልጅ #የወይኗ ልጅ #ኦላይን #ቢዝነስ #ወሲብ #ፍቅር #ትዳር #የነቢያት #ታሪክ #የኢሳ #ታሪክ #አድዋ #ዋትስአፕ #ዋትሳፕ#ዋትሳፕጠለፋ #ዋትሳፕእንዴትይጠለፋል #ባቢ #babi #ቀልድ #ኮሚዲ#ሰይፉ#ዋትስአፕ መጥለፍ #ዋትስአፕ #ዋትስአፕ ግሩፕ #ቴሌ ግራም መጥለፍ#ቴሌ ግራም ሀክ #ቴሌግራም ግሩፕ #ቴሌ ግራም አፕ #ቴሌ ግራም ቻናል #ፌስቡክ አርበኞች #ፌስቡክ ሀከር # ፌስቡክ እንዴት ይጠለፋል#ፌስቡክ ሀክ #ፌስቡክ ለመጥለፍ#ፌስቡክ ስልክ ቁጥር #ፌስቡክ ድራማ#ፓስወርድ #ፓስወርድ መቀየር #የጠፋብንን ፓስወርድ#ዋይፋይ ፓስወርድ #ኢሜል ፓስወርድ#የስልካችን ፓስወርድ #ፊስቡክ ፓስወርድ #ዋይፋይ_ያለ_ፓስወርድ #የተረሳ ፓስወርድ #dani dope app #ኢሞ ጠለፍ #ኢሞ ዱባይ #የፍቅረኛችሁን ስልክ ጠለፍ#የባልሽን ስልክ ጠለፍ #yesufapp #ስልክ ከርቀት መጥለፍ #ሚስጥራዊ ኮዶች #ethioapp #lij bini tube #habi faf #tst app #eytaye #shambel app tube #የስልክ ጥሪዎች #ኢሞ #ሴክስ #artstv #seyfufantahun #ebs #mabriyamatfiya #ethiopiancomedy #ethiopiannewmovie #newamharicmoviefilm #easattv #ethionews #amharicnews #abelbrhanu #abugidamedia #tiktokvideo #ethiopiantiktok #amharicmusic #zetenegnawshi #ዘጠነኛውሺ #trgumfilm #tigraytv #amaratv #oromiyatv #debubtv #Hanen ሃነን #Eritrea News #Best Ethiopia music 2023 #Viber #Ts #App #Camera #Youtube #Yesuf #whatsapp #EthiopianMusic #ethiopianmovie #howtodownload #zetenegnawshi #9th #ዘጠነኛውሺ #howtolearn #kanadrama #howtouse #ethiopiandrama #iphone #android #hopemusicethiopia #seifu #seifuonebs #tenaadam , ፐይታል አካዉንት ኢትዮጵያ, free PayPal earnings, how to earn PayPal money, make money online, ተጨማሪ ገንዘብ ኢትዮጵያ, extra income online, ኦንላይን ስራዎች ኢትዮጵያ, online jobs in Ethiopia, አዲስ ኦንላይን ስራ,የትኬት ዋጋ,yonimagna,abyi ahemed,ሰበር መረጃ #amharic #tiktok #shorts #ethiopia_tiktok #newethiopianmusic #ethiopiantiktok #ቴሌግራም #ኢትዮቲክቶክ #ኢትዮቶክ #ስልክ, #ስልክ_መጠለፉን_ለማወቅ, ምርጥ አፕሊኬሽን, ምርጥ አፕ, አፕ #ኢሞ #ቴሌግራም #እንዴት #ethiopiantiktok #ዋትስአፕ #ethiopian #abelbirhanu #trending #premium #premiumapp #immigration #canada #ethiopia #ካናዳ #ካናዳ ለመሄድ #ካናዳ የስራ ቪዛ #ካናዳ ፕሮሰስ #teespringstore #makemoney #makemoneyethiopia #ካናዳ #ካናዳ የስራ ቪዛ #ካናዳ ፕሮሰስ #ካናዳ ለመሄድ how to make money online by typing words, how to make money online by typing words, how to make money online by typing, how to make money by typing words, how to make money online, earn money online earn money online, make money online, how to make money online #makemoneyonline #chatgpt #PassiveIncome #earnmoneyonline #workfromhomejobs #workfromhome #earnmoney #onlinemoney #ai #openai #upwork #upworkethiopia #ገንዘብ upwork | ethiopia | How to earn money online | money | freelance | make money | online | upworkethiopia | ገንዘብ | ኦላይን | ኦንላይን…

✅በነፃ በቴሌግራም ገንዘብ የምትሰሩበት ቀላል እና ምርጥ መንገድ ከነሙሉ ማብራሪያው👇 https://youtu.be/9r2l2-wsU1A?si=ICwQ_ScAFmDug4e5 https://youtu.be/9r2l2-wsU1A?si=ICwQ_ScAFmDug4e5
Show all...
በቴሌግራም ገንዘብ የምትሰሩበት ምርጥ መንገድ | How To Make Money Online By Using Telegram

በቴሌግራም ገንዘብ የምትሰሩበት ምርጥ መንገድ | How To Make Money Online By Using Telegram | Telegram Wallet | Earn Free Hot Token Airdrop | Hot Mining | Free Telegram Earning Bot | Money Earning Game የምትሰሩበት Link👇

https://t.me/herewalletbot/app?startapp=1755887-village-50699

የቴሌግራም ቻናላችን👇

https://t.me/mullerapp

➤የTrust Wallet አከፋፈት 👇

https://youtu.be/4ppzx4eGpIg

📌የFaucetpay አካውንት አከፋፈት👇

https://youtu.be/GAUBzTLkwbg

💡Sms ስለገባ ገንዘብ የሚከፍል አፕ👇

https://youtu.be/deTEdaad_kY

➔ Money Making Videos 👇

https://www.youtube.com/playlist?list=PLOQOx5sYp-8-PtDfE3_WM3Id1s9W1XZsG

➔ Make Money Online by Telegram👇

https://youtu.be/J3AS_PCJ-rA

➔ Make money Online By Playing Simple Games👇

https://youtu.be/lYC4QD9cpEU

➔ Make Money by Listening Music👇

https://youtu.be/0zFTmrDJv5g

➔ Make Money by Receiving Sms👇

https://youtu.be/deTEdaad_kY

---------------------------------------------------------- 🔥 Business Enquiries(For Promotion) 📌Telegram:

https://t.me/mulualm

📌Email: [email protected] ---------------------------------------------------------- ------------------------------------------------ እኔን በተለያዩ አማራጮች ለማግኘት ---------🔽Contact me🔽----------- ➱ Intsagram:

https://instagram.com/muller_app

➱ TikTok:

https://tiktok.com/@muller_app

➱ Facebook:

https://m.facebook.com/mullerapp20

----------------------DISCLAIMERS-------------------------- DISCLAIMER: This Channel DOES NOT Promote or encourage Any illegal activities, all contents provided by This Channel is meant for EDUCATIONAL PURPOSE only. #web3 #Money #Website #online #binance #airdrop #bitcoin #wallet #HotWallet #nearwallet #HotMining #notcoin #toncoin #binance #bybit #kucoin #MullerApp ገንዘብ መስሪያ | ኦንላይን ስራ | ነፃ የሞባይል ካርድ | የሞባይል ካርድ | ለካርድ ብር ማውጣት ቀረ | How to make money online | Make Money Online | Online Money Making | How to earn money online | Free airtime package | How to get free airtime package | Make Money Online | Aki Image | Base ባስ | Mamisha Online | Aby Game Zone | Mike Tech | Abel Birhanu | Ethiopia | Muller App 2024 #eytaye #ethiopia #abelbirhanu

#ሰላም_ውድ_ቤተሰቦች 💪💯 አንድ ውሳኔ! 💪💯 ካለፈው ታሪክ የአሁኑና የወደፊቱ ላይ የመምረጥ ፣ ከችግሩ በላይ መፍትሔው ላይ የማተኮር ፣ የተዘጋውን በር በመተው ክፍት ወደሆነው ፊትን የማዞር ፣ ጥበቃን በማቆም በእራስ አቅም የመንቀሳቀስ ፣ ወቀሳን በመተው ለእያንዳንዱ ነገር ሃላፊነት የመውሰድ ውሳኔህ ሙሉ በሙሉ ለተለየ ህይወት ያበቃሃል ። ዛሬ ከምንኖረው ህይወት ከፍ ለማለት ፣ ለውጥን ለመመልከት ፣ የተሻልን ሆነን ለመገኘት ምንም አደጋ ቢኖረውና ፈታኝ ቢሆንም ግዴታ አንድ ወሳኝ እርምጃ መውሰድ ፣ አንድ አስገራሚ ውሳኔ መወሰን አለብን ። ማቆም ያልብንን ልማድ የማቆም ውሳኔ ፣ መለየት ካለብን ሰዎች የመለየት ውሳኔ ፣ ወደፊት ብቻ የመመልከት ፣ ህልማችን ላይ የማተኮር ፣ መሰናክሎቻችንን የመሻገር ፣ ሰበብኝነትን የማስወገድ ብርቱ ውሳኔ ያስፈልገናል ። 💪💯 አዎ! ጀግናዬ..! አንድ ውሳኔ የህይወትህ ሙሉ ማርሽ ቀያሪ ነች ፤ አንድ ውሳኔ የውድቀትህም የስኬትህም ሚስጥር ነች ፤ አንድ ውሳኔ የደስታም የሃዘንህም ምክንያት ነች ። ምንም ነገር መወሰን ካለብህ በፍጥነት ወስን ፤ ነገር ግን ሃላፊነቱን ለመቀበል እራስህን በሚገባ አዘጋጅ ። ለትልቁ ህልምህ ብለህ ስራህን ብታቆም ከጀርባው ተከትለው ለሚመጡብህ ችግሮችና አደጋዎች እራስህን አዘጋጅ ፤ ለውሳኔህ ቆራጥ እንደሆንከው ማማረርን ለማቆምና ሰበብ ከማብዛትም ቆርጠህ ውጣ ። እኔ እንደዚህ ነኝ ስትል በማንነትህና በሃሳብህ ሊያሸማቅቅህና ሊጥልህ የሚፈልግ ቢኖር ዳግም አንገትህን ከመድፋት ይልቅ ከቀድሞው በላይ ቀና በማለት ትክክለኛውን አንተነትህን አሳየው ። ማንኛውም ሊያከብርህና ሊያውቅህ የሚገባው ሰው በሙሉ አቅምና ወኔህ ሊያውቅህና ሊያከብርህ ይገባል ። እራስህን የማስከበር ውሳኔውም በእጅህ ነው ። 💪💯 አዎ! እራስህን አክብር ፤ የሚመጥንህን ፣ የሚቀይርህን ፣ የሚያሳድግህን ውሳኔ ከመወሰን ወደኋላ አትበል ። ቀን ቀንን ወልዶ ፣ ጊዜም በሌላ አዲስ ጊዜ ተሽሮ ፣ ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ተፈጥረው ጠቃሚው አንድ ውሳኔህ ዋጋ ከሚያጣ በፍጥነት ወስን ። ከምታልመው ፣ ከምታስበውና ከምታቅደው ህይወት ያለህ ርቀት የአንድ ቆራጥ ውሳኔ ርቀት ያክል ብቻ ነው ። ያ ውሳኔ ከተወሰነ ፣ ወደ ተግባርም ከተገባበት ሙሉ በሙሉ ከምታማርርበት ህይወት ትወጣለህ ፤ የማትወደውን ማንነት እያሻሻልክ ትመጣለህ ፤ ለተሻለው የህይወት ደረጃ እራስህን ታበቃለህ ። በውስጥህ የሚመላለሰውን ህልም ለመኖር አንድ የማያዳግም የተጠና ውሳኔ ብቻ እንደሚያስፈልግህ እመን ። በጥቃቅን ውሳኔዎች የተሞላው ህይወትህ ለውሳኔ ባይቸገርም መሰረታዊውን ለውጥ ለማምጣት ግን መሰረታዊ ውሳኔ መወሰን ይኖርብሃል ። ለረጅም ጊዜ ያስጨነቀህን ውሳኔ ወስን ፤ የሚያሳስብህ ጉዳይ ላይ በፍጥነት እርምጃ ውሰድ ፤ የምታልመውን አስደሳች ህይወትም በእጅህ አስገባ ። ═════════❁✿❁ ═════════ 💪💯 ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!!👌 ምንጭ 👇👇👇 @yeskatmender
Show all...
Help and encourage  We all need help and encouragement at different times.  As we began life, we had our parents, then our teachers and family members, then team-mates, then business colleagues and bosses and mentors. All helped and encouraged us in some way.  Many influenced us greatly. Those who were there for us in tough times are never forgotten. Try to help others who are going through tough times.  They may feel alone. When you help someone, you often have a friend for life. When you encourage someone and see them grow and develop, you get great satisfaction.  Be there for people when you can.  You will not regret it.  There are many who need help and encouragement. ( all of the above lessons are taken from best life lessons' app )
Show all...
Forgive all Most people whom we meet are kind and helpful.  Only a few have been unkind and unhelpful.  Forgive them!  It is over!  Don’t let anger and hurt stay in your system.  Let them go. Be kind to those who you forgive. Once you forgive, your health will improve. Don’t harbour any bad feelings or grudges.  They make you old. Then, as you move at a slower pace, remember that everyone has much bigger challenges than appear on the surface. Make allowances.  Most people are doing their best. Like you, they have made many mistakes and have many regrets. They are human, too.
Show all...