cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የን/ስ/ላ/ክ/ከ ወ9 ሒክማ መስጂድ ጀመዓ

በቁርኣን እና በሀዲስ በሰለፎች አረዳድ ህዝበ ሙስሊሙን አንድነት ማጠናከር።

Show more
Advertising posts
200
Subscribers
No data24 hours
+17 days
+330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

• - قالَ العلّامـةُ صالِحُ الفوزان • - حَفِظَهُ اللهُ تباركَ وَتَعَاْلَىٰ  - : • - ( بالهدى ) أي: العلم النافع وهو كل ماجاء به النبي صلى الله عليه وسلم من الإخبارات الصادقة والأوامر والنواهي وسائر الشرائع النافعة . ☆ والهدى نوعان : - النوع الأول : هدى بمعنى الدلالة والبيان ، ومنه قوله تعالى : { وأما ثمود فهديناهم فاستحبوا العمى على الهدى } الآية ( ١٧ ) فصلت . وهذا يقوم به الرسول صلى الله عليه وسلم كما في قوله تعالى : { وإنك لتهدي إلى صراط مستقيم } . - النوع الثاني : هدى بمعنى التوفيق والإلهام وهذا هو المنفي عن الرسول صلى الله عليه وسلم ولا يقدر عليه إلا الله تعالى كما في قوله تعالى : { إنك لا تهدي من أحببت ولكن الله يهدي من يشاء } الآية ( ٥٦ ) القصص .                 📜【العقيدة الواسطية (١ / ٧ )】 ═════ ❁✿❁ ══════
Show all...
ስልጣንና ጥቅማ ጥቅም_1.m4a19.21 MB
Photo unavailableShow in Telegram
የአልጀዚራ ጋዜጠኛ የተናገረው ንግግር ግልፅ መልዕክት ነው። ኮሜቴ እና አመራር አስተሳሰቡ ሰፊ ካልሆነ ለሚመራው አካል የተሻለ ለውጥ አያመጣም።
Show all...
👍 2 1
* ተወካዪች ከሁለቱም ከሰጪና ከተቀባይ ወገን ተወከሉ ከተረከቡ ወቅቱ ካለፈም በኋለ ለወከሉዋቸው ለምስኪኖች ቢሰጡ ችግር የለውም ነገር ግን የተወከሉ በሰጪዎች ብቻ ከሆነ የግድ ወቅቱ ሳያልፍ ለሚገባቸው ሰዎች ማድረስ ይኖርባቸዋል ። ★ ለሌላ አካባቢ ስለመስጠት * መሆን ያለበት ዘካተል ፊጥርን ወደ ሌላ ቦታ ከመላክ እያንዳንዱ ሙስሊም በጾመበት ቦታ ማውጣት ነው ነገር ግን የሚቀበል ሚስኪን ከሌለ ችግረኞች ወዳሉበት ቦታ መላክ ይቻላል ። تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال መልካም ስራዎቻችንን አላህ ይቀበለን ተፈፀመ ። ጥንቅርና ዝግጅት ፣ ሙሀመድ ፈረጅ አቡ ሙስዐብ —————————————
Show all...
★★★ዘካቱል ፊጥር / የፍስግ ምጽዋት/ ★ ለግንዛቤ ያህል ዘካተል ፊጥር ከዘካተል ማል በምን ይለያል ። * ዘካተል ፊጥር የረመዳን ወር ፆም እንደተጠናቀቀ በዚህ ወቅት ሙስሊም ሁኖ በህይወት ባለ ሰው በነፍስ ወከፍ ግዴታ የሚሆን የዘካ / ሰደቃ/ አይነት ነው ፡፡ * ዘካተል ማል በንብረት ላይ የተደረገ ግዴታ ነው አንድ ንብረት በተወሰነ ግዜ ውስጥ የተወሰነ መጠን ሲደር የተወሰነ መጠን ለተወሰኑ አካሎች የሚሰጥ ሰደቃ ነው ። ★ ዘካተል ፊጥር * እያንዳንዱ አባወራ ወይም እማወራ ወይም አስተዳዳሪ የራሱን ጨምሮ በእርሱ ስር እየቀለባቸው ላሉ ቤተሰቦቹ ሁሉ መስጠት ይኖርበታል ፡፡ ★ ማስረጃ * አብዱላህ ኢብን አባስ አላህ ይውደዳቸውና እንዲህ ይላሉ፤ ﻋﻦ ﺍﺑﻦ ﻋﺒﺎﺱ ـ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﻤﺎ ـ ﻗﺎﻝ : ” ﻓﺮﺽ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﺯﻛﺎﺓ ﺍﻟﻔﻄﺮ ﻃﻬﺮﺓ ﻟﻠﺼﺎﺋﻢ ﻣﻦ ﺍﻟﻠﻐﻮ ﻭﺍﻟﺮﻓﺚ ﻭﻃﻌﻤﺔ ﻟﻠﻤﺴﺎﻛﻴﻦ، ﻓﻤﻦ ﺃﺩﺍﻫﺎ ﻗﺒﻞ ﺍﻟﺼﻼﺓ ﻓﻬﻲ ﺯﻛﺎﺓ ﻣﻘﺒﻮﻟﺔ، ﻭﻣﻦ ﺃﺩﺍﻫﺎ ﺑﻌﺪ ﺍﻟﺼﻼﺓ ﻓﻬﻲ ﺻﺪﻗﺔ ﻣﻦ ﺍﻟﺼﺪﻗﺎﺕ” ﺭﻭﺍﻩ ﺃﺑﻮ ﺩﺍﻭﺩ ﻭﺍﺑﻦ ﻣﺎﺟﻪ ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በ እርሳቸው ላይ ይሁን) ዘካተል ፊጥርን ለፆመኛ በጾሙ ወቅት ከፈፀማቸው ውድቅ ንግግሮችና ተግባሮች ጥፋት እንዲሁም የተቃራኒ ፆታ ስሜትን ቀስቃሽ ለሆኑ ንግግሮቹ ጥፋት ማጽጃ ይሆንለታል ። ለሚስኪኖች (ድሆች) ደግሞ መብል እንዲሆን በግዴታ መልኩ ደንግገውታል ። ስለዚህም ከኢድ ሰላት በፊት (ዘካውን በመስጠት ግዴታውን የተወጣ) ተቀባይነት ያለው ዘካን ሰጥቷል፤ ከ ኢድ ሶላት ቦሃላ ዘካውን የሰጠ እንደማንኛውም ሰደቃ አንዱ እንደሆነ ይታሰብለታል ።)) (አቡዳውድ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል)። * ኢብኑ ሙንዚር አል ኢጅማዕ’ በተሰኘው ኪታባቸው ‹‹ዒልምን የተማርንባቸው ዑለሞች ሁሉ ዘካተል ፊጥር ግዴታ መሆኑን ተስማምተውበታል›› በማለት የ ኡለሞችን አጠቃላይ ስምምነት (ኢጅማዕ) የተገኘበት መሆኑን ጠቁመዋል ። ★ የተደነገገበት ጥበብ ከላይ ግዴታነቱን ለማመላከት በተጠቀሰው ሀዲስ እንደተጠቀሰው ፣ ድሆች በባዕሉ (ዒድ) እለት ሰዎችን ከመለመን እንዲድኑና የእለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲሁም በፆም ወቅት ተከስተው ላለፉ አንዳንድ ጉድለቶች (ግድፈቶች) ማሟያ እንዲሆን ነው ። ★ መጠኑ * የዘካተል ፊጥር መጠን ኢብኑ ኡመር ረዲየላሁ አንሁ ከነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ይዘው ባስተላለፉት ሀዲስ እንዲህ ብለዋል: – ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ከተምር ወይም ከገብስ አንድ ቁና መስጠት በ እያንዳንዱ ሙስሊም፤ ባሪያም ሆነ ጨዋ (ባሪያ ያልሆነ)፣ሴት፣ ህፃን፣ አዋቂ ላይ ግዴታ አድርገዋል፡፡ እንዲሁም ሰዎች ወደ (ዒድ) ሰላት ከመውጣታቸው በፊት ለሚገባቸው ሰዎች እንዲደርስ አዘዋል፡፡›› (ቡኻሪና ሙስሊም ) 1 ሷዕ / ቁና/ በመካከለኛ ሰው እጅ አራት እፍኞች ነው ። ወደ ኪሎ ግራም ሲቀየር መጠኑ እንደየ እህሉ ክብደትና ቅለት ይለያያል ። ለምሳሌ ፣ — አንድ ቁና(ሳእ) ፉርኖ ዱቄት 2ኪሎ ግራም — አንድ ቁና (ሳእ) ጤፍ 2·5 ኪሎ ግራም — አንድ ቁና (ሳእ) ሩዝ 2·6 ኪሎ ግራም — አንድ ቁና (ሳእ) ስንዴ 2·5 ኪሎ ግራም — አንድ ቁና (ሳእ) ገብስ 2·5 ኪሎ ግራም — አንድ ቁና (ሳእ) ማሽላ 2·25 ኪሎ ግራም — አንድ ቁና (ሳእ) በቆሎ 2·5 ኪሎ ግራም ★ ግዴታ የሚሆነው በማን ነው — ሙስሊም በሆነ — ረመዷን ወር ሲጠናቀቅ በህይወት የነበረ — በእለቱ ለ24 ሰዓት ለራሱና ለሚያስተዳድራቸው ሰዎች ወጪ የሚያደርገው ሀብት ኑሮት ከዚያ የተረፈ ነገር ባለው ሰው ነው ። — * ዘካተል ፊጥር በነፍስ ወከፍ የሚደረግ ኢባዳ ስለሆነ በቤተሰብ ስር የሚኖር ሰው ለራሱ ሚያወጣበት ነገር ካለው ቤተሰቦቹን ከመጠበቅ ራሱ ማውጣት ይኖርበታል ። ★ ግዜው * ዘካተል ፊጥርን ማውጣት ግዴታ የሚሆነው የረመዷን ወር የመጨረሻው እለት ፀሀይ ከጠለቀችበት ወይም ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰዓት አንስቶ የኢድ ሷላት ተሰግዶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ነው ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢብኑ ዑመርን ጨምሮ ሌሎቹም ሰሀቦች (ረዲየላሁ አንሁም) ከዒድ አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀድሞ ዘካተል ፊጥርን ማውጣት እንደሚቻል ይገልጻሉ ሲተገብሩትም ነበር ። * ዘካተል ፊጥርን ከ(ዒድ) ሰላት በኋላ ማዘግየት የተከለከለ ነው ። ድንገት አንድ ሰው ረስቶ ወይም ሳይመቸው ቀርቶ በወቅቱ ሳያወጣ ቢቀር ባስታወሰና በተመቸው ወቅት ማውጣት አለበት ። ★ የሚሰጠው ነገር * ለዘካተል ፊጥር የሚሰጡ የእህል አይነቶችን በተመለከተ አውጪዎቹ በሀገራቸው ከሚመገቡዋቸው እህሎች ውስጥ ነው ለምሳሌ እንደ ተምር ፣ ዱቄት ፣ እሩዝ ፣ በቆሎ፤ ጤፍ …. ወዘተ ባሉ የምግብ እህል አይነቶች ነው ። ይህን አስመልክተው የአላህ መልእተኛ ነብያችን (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) በሀዲሳቸው የጠቀሷቸው የምግብ እህሎች ( ገብስ፤ ተምር፤ ዘቢብ) ፣ የመሳሰሉት ሲሆኑ፣ ነገር ግን የምግብ አይነቶቹ በነዚህ ላይ ብቻ እንደማይገደቡ የኢስላም ሊቃውንቶች ያስረዳሉ ። በዚህም መሰረት በማንኛውም አካባቢ የሚኖር ሙስሊም ማህበረሰቡ አዘውትሮ ከሚመገባቸው የምግብ እህሎች ዘካተል ፊጥሩን ማውጣት ይችላል፡፡ ★ ለማን ይሰጥ * ዘካተል ፊጥር ለምስኪኖች እና ለድሆች ብቻ ነው ሚሰጠው አብደላህ ብኑ አባስ ባስተላለፉት ሀዲስ ላይ ነብያችን (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ‹‹ለምስኪኖች መብል …›› በማለት ስለገለፁ ። ★ በገንዘብ ቀይሮ ስለመስጠት * ዘካተል ፊጥርን በዋጋ ተምኖ መክፈል አይፈቀድም ። ምክንያቱም፤ በኢብኑ አባስ ሀዲስ ላይ ነብያችን (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ዘካተል ፊጥር የተደነገገበትን አላማ ሲገልፁ ‹‹ለምስኪኖች መብል …›› ከማለታቸው ጋር የተያያዘ ነው ። አቢ ሰዒድ አልኹድሪይ የተባሉ ሰሃባም እንዲህ ብለዋል፤ “የአላህ መልዕክተኛ በነበሩበት ዘመን ዘካተል ፊጥር የምናወጣው ከምግብ አንድ ሷዕ ነበር” ። ይህ በእንዲህ እያለ ዘካተል ፊጥርን በእህል ማውጣት ያልቻለ ሰው ከሚበላው እህል አይነት መጠኑን ወደ ገንዘብ ቀይሮ ገንዘቡን ቢሰጥ ውድቅ አይሆንበትም ። ለችግርተኞች የሚጠቅመውን ማድረግ ይቻላል የሚል ሀሳብ ያላቸው ጥቂት ኡለሞች ስላሉ ። ይሁን እንጂ አስተማማኙ እና ሱናው በእህል መስጠት ነው ። ምክንያቱም በገንዘብ መተመን በቀደምት ሙስሊሞች ሰለፎች በነብያችንም ዘመን አልተፈፀመም ። ዒባዳ ሁል ጊዜ በአሏህ እና መልእክተኛው የሚደነገግ እንጂ በግል አስተያየት የምንፈፅመው አይደለምና ። ★ በዘካተል ፊጥር ስለመወከል * ዘካተል ፊጥር የሚሰጥበት ወቅት የተገደበና ግዜውም አጭር ከመሆኑ አንፃር አውጪዎች ባሉበት ሀገር ወይም ሁኔታ ምክንያት በተወሰነለት ግዜ ማውጣት ካልቻሉ ወቅቱ ሳያልፍ ዘካውን ሚያወጣላቸው ሰው መወከል ይችላሉ ። በተመሳሳይ ዘካተል ፊጥርን የሚቀበሉ ምስኪኖችም ራሳቸው መቀበል ካልቻሉ ሚቀበልላቸውን ሰው መወከል ይችላሉ ።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
አንድ ቀን የቀድሞው የሳዑዲ ዐረቢያ ንጉስ ኻሊድ ቢን ዐብዱልዐዚዝ (ረ.ዐ) ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚንን (ረ.ዐ) ለመጎብኘት ወደቤታቸው ጎራ አለ። መኖሪያ ቤታቸውን ሲመለከት ለዓይን ደስ የሚያሰኝ ነገር የሌለው አሮጌ ቤት እንደሆነ አስተዋለ። ከዚያም «የእርስዎን ደረጃ የሚመጥን አዲስ ቤት እንዲገነባልዎ እናዛለን» አላቸው። ሸይኹም «አላህ ምንዳህን ይክፈልህ፤ ነገር ግን ሷሊሒያ ውስጥ የምናዘጋጀው እና ወደ እሱም የምንሸጋገርበት ቤት አለን» አሉት። ንጉስ ኻሊድም ሸይኹ አዲስ ቤት እየገነቡ እንዳለ ተረድቶ በሰጡት ምላሽ ተረጋጋ። ንጉስ ኻሊድ ሸይኹን ተሰናብቶ ከሄደ በኋላ ተማሪዎቹ ሸይኻቸውን ኢብኑ ዑሰይሚንን «በሳልሒያ ቤት እንዳለዎት አናውቅም ??» በማለት በአግራሞት ጥያቄ አነሱ። ሸይኹም አላህ ይዘንላቸውና *❝ ለመሆኑ የመቃብር ቦታ የሚገኘው ሷሊሒያ ውስጥ አይደለምን ?? እንዲህ ያልኩት የመጪው ዓለም ቤታችን ግንባታው እውን የሚሆነው እዚያ በመሆኑ ነው» በማለት ለተማሪዎቻቸው ምላሽ ሰጡ።*
Show all...
የኢስላም ገርነት፣ የእኛ ግትርነት_1.m4a15.56 MB