cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethiopian Youth Council

ይህ የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። Welcome to the Ethiopian Youth Council Official Telegram Channel. https://www.ethiopianyouthcouncil.org/

Show more
Ethiopia8 666Amharic7 117The category is not specified
Advertising posts
370
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
#የውድድር ጥሪ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀንን ምክንያት በማድረግ ''በኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞችን መብትና ተደራሽነት ማሳደግ'' በሚል መፈክር ወጣቶችን ያሳተፈ ውድድር በይፋ ተጀምሯል። ይህንን ልዩ ቀን በማክበር በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልግዎትን ጠቃሚ መረጃ ያገኙ ዘንድ የጎግል ድራይቭ አቃፊችንን ማስፈንጠሪያ ከታች አያይዘናል። https://shorturl.at/npUX7 በዚህ ማስፈንጠሪያ ውስጥ የዩኔስኮ ዳይሬክተር የተባበሩት መንግስታት ቀንን እና የወጣቶች ተሳትፎ ውድድር በይፋ መጀመሩን አስመልክቶ ያስተላለፉት መልእክትና አጠቃላይ የውድድሩን መመሪያዎች ያቀፈ የቪዲዮ መልእክት( በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ በሁለቱም ቋንቋዎች) ይገኛል። የቀረቡትን መመሪያዎች በአንክሮ በመመልከትና አስፈላጊውን የውድድር መስፈርት በማሟላት አዳዲስና ፈጠራ የታከለባቸው የውድድር ሀሳቦችን በመያዝ በውድድሩ እንድትሳተፍ ተጋብዛችኋል። በኢትዮጵያ ውስጥ የአካል ጉዳተኞችን መብትና ተደራሽነት ለማሳደግ የእርስዎ ተሳትፎ ወሳኝ ነው። ለውድድሩ ያዘጋጁትን ልዩ የፈጠራ ሀሳብ በፈረንጆች አቆጣጠር እስከ ህዳር 20 ድረስ ማስረከብ ይጠበቅብዎታል። ውድድሩን በተመለከተ ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካሎት፣ ማብራሪያ ከፈለጉ ወይም በሂደቱ ላይ እርዳታ ከፈለጉ እባክዎን በ [email protected] ላይ ያጋሩን በማህበረሰባችን ውስጥ ለውጥ ለማምጣት እና አካታችነት እና ተደራሽነትን ለማሳደግ በጋራ እንስራ። መልካም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀን!!! ✨ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን።          🌐 የማህበራዊ ገጾቻችንን ይከታተሉ! Telegram              []  Facebook           []   Website
Show all...
"ኡርጂን" የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል!! ኡርጂን የተሰኘ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ ሞተር ሳይክል በኢትዮጵያ ተመርቶ ለገበያ ቀረበ። የወጣቱ የቴክኖሎጂ ባለሙያ ሺሀብ ሱሌይማን የፈጠራ ውጤት የሆነው የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል አስፈላጊው የፍተሻ ስራ ተደርጎለት በኢትዮጵያ ውስጥ ተመርቶ ለገበያ ቀርቧል። የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክሉ በሰአት 60 ኪ.ሜ የመጓዝ አቅም ያለው ሲሆን አንድ ጊዜ ሙሉ ሀይል ቻርጅ ለማድረግ ስድስት ሰአት ይፈጅበታል ተብሏል። የሞተር ጉልበቱ 1500 ዋት ሲሆን ያለ ቁልፍ መነሳት እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ነው። ሞተር ሳይክሉ ስርቆትን ለመከላከል የሚረዳ የማንቂያ ደውል(አላርም) የተገጠመለት ስለመሆኑ ተገልጿል። የአንዱ ሞተር ሳይክል የመሸጫ ዋጋ 80 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ነው። ሞተር ሳይክሉን ወደ ስራ ለማስገባት ለአመታት ያክል የተለፋበት ስለመሆኑ የተነገረ ሲሆን ከካርበን ልቀት ነጻ የሆነና በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ ነው። ከከባቢ ጋር ተስማሚ እና የኢትዮጵያን ስነ-ምህዳር ከግንዛቤ ባስገባ ዲዛይን የተመረተ ስለመሆኑም ተመላክቷል። የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክሉ በሀገር ውስጥ መመረቱ ኢትዮጵያውያን በአለም ላይ በቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ብቁና ተወዳዳሪ ሆነው መውጣት እንደሚችሉ ምስክር ነው። የኢትዮጵያ ታምርት እንቅስቃሴ ውጤት ነውም ማለት ያስችላል። ወጣት ሺሀብ ሱሌይማን የበርካታ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ባለቤት ሲሆን ለቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ልዩ ፍቅር አለው። መሰል የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች ይበራከቱ ዘንድ ለወጣት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ስራ ፈጣሪዎች አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል። የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክሉ ዝርዝር መረጃ(specification) በፎቶ ተያይዟል። ✨ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን።         
Show all...
👍 1🥰 1👏 1
https://youtu.be/ytf30ma8esI?si=Xrqm_NUkxr1Jty7g ✨ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን።          🌐 የማህበራዊ ገጾቻችንን ይከታተሉ! Telegram              []  Facebook           []   Website
Show all...
የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት መመስረትና የወጣቱ ተጠቀሚነት

#ፋና #አዲስ_አበባ #Ethiopia #ኢትዮጵያ #FANA_TV #FANA_NEWS #ፋና_ዜና

1🥰 1
ዩኒሴፍ በ98 ሀገራት ተግባራዊ ሲያደርግ የቆየውን የ U-Report ሥርዓት እያስተዋወቀ ነው። ዩኒሴፍ፥ በኢትዮጵያ ወጣቶች በሚመለከታቸው ነገር ላይ እንዲሁም ማኅበረሰባቸውን በሚጠቅም ጉዳይ ላይ ድምጽ እንዲሆኑና እንዲሳተፉ የሚያስችል ሥርዓት መጀመሩን ገልጿል። በ98 ሀገራት ላይ ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው ይህ ሥርዓት ወጣቶች በልማት ሥራዎች፣ በሰብዓዊ ተግባራት እንዲሁም በራሳቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉና ድምጻቸውን እንዲያሰሙ የሚያግዝ ነው። በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ U-Report አስተባባሪ ሕይወት ገበየው ይህ ሥርዓት በኢትዮጵያ መተግበሩ፥ የወጣቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎን ከመጨመር በላይ ዓለም አቀፍ ተቋማትም የወጣቱን ሀሳብ ትኩረት ያደረገ ሥራዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚያስችል መሆኑን ይገልጻሉ። ይህ አዲስ የሚተገበረው የዩኒሴፍ U-Report ኢኒሽዬቲቭም በጅማሮው ከ200,000 በላይ ወጣቶችን በበጎፈቃደኝነት ለማሳተፍ አስቧል። ወጣቱ ድምጹን ለማሰማት፣ ተጽዕኖ ለመፍጠርና ለማኅበረሰቡ ድምጽ ለመሆን ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ የጠየቁት አስተባባሪዋ ዩኒሴፍ የ U-Report መመዝገቢያ መንገዱን ለቲክቫህ ቤተሰቦች አስተዋውቀዋል። በዚህም ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች ቦት(Bot) የተዘጋጀ ሲሆን @ureportethiopia_bot በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል። @tikvahethiopia
Show all...
Show all...
U-REPORT ETHIOPIA

U-Report is

https://www.unicef.org/

platform that allows youths to amplify their voices.

Photo unavailableShow in Telegram
👍 8👏 1🎉 1🤩 1
ወጣቶች በመደመር እሳቤ አንድነታቸውን በማጥበቅ ለሀገራቸው ዘላቂ ሰላምና ልማት መስራት አለባቸው- የኢትዮዽያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ፤ መስከረም 24/2016(ኢዜአ)፦ ወጣቶች ከከፋፋይ አጀንዳዎች በመውጣት በመደመር እሳቤ አንድነታቸውን በማጠናከር ለኢትዮዽያ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ብልፅግና ሊሰሩ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና ገለፀ። በመደመር እሳቤ ላይ ኢዜአ ያዘጋጀው አራተኛው ምእራፍ የውይይት መድረክ "መደመር ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታና ብሔራዊ አንድነት" በሚል በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና፣ "መደመርና ወጣቶች ለዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ ብልፅግና" በሚል የውይይት መነሻ ሃሳብ አቅርቧል። በማብራሪያውም በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም በመፍጠር የተጀመሩ የልማት እቅዶች እንዲሳኩ ወጣቶች የላቀ ሚና ይጠበቅባቸዋል ብሏል። አሁን ላይ ወጣቶች በዓለም እያደገ የመጣው የቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራ ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሶ፤ የዲጂታል ዘመን እንደመሆኑ ወጣቶች በአሉታዊና ተፅእኖዎች እንደሚፈተኑም ገልጿል። በመሆኑም የኢትዮጵያ ወጣቶች መልካም ተሞክሮዎችን በመውሰድ በመደመር እሳቤ ለሀገራቸው ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ብልፅግና መስራት አለባቸው ብሏል። ሀገር በቀል እውቀትና ክህሎቶችን በማዳበርና አንድነትን በማጠናከር ለሀገር ልማትና የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲሰሩም ጠይቋል። በመሆኑም ወጣቶች ከከፋፋይ አጀንዳዎች በመውጣት በመደመር እሳቤ በአንድነት ለኢትዮዽያ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ብልፅግና ሊሰሩ ይገባል ነው ያለው።
Show all...
👍 6🥰 1👏 1
ከመድረኩ ተሳታፊዎችም ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፤ የመደመር እሳቤ ሀገር በቀል እውቀቶችን መሰረት በማድረግ ኢትዮጵያ የምትመራበት ሁነኛ መንገድ በማድረግና እሳቤው ለትውልድ እንዲተላለፍም “መደመር”፣ “የመደመር መንገድ” እና “የመደመር ትውልድ “ የሚሉ መጽሐፍትን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወቃል። ©Ethiopian News Agency ✨ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን።          🌐 የማህበራዊ ገጾቻችንን ይከታተሉ! Telegram              []  Facebook           []   Website
Show all...
👍 5🥰 1👏 1
▪️ የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የተከበሩ አቶ ፍአድ ገና ከኬንያ አቻቸው ጋር ተወያዩ። (መስከረም 2016 ዓ.ም፤ ናይሮቢ) **** የኬንያ ብሔራዊ የወጣቶች ምክር ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ ማርጋሬት ኪጎራ የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የተከበሩ አቶ ፍአድ ገናን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። አመራሮቹ በኬንያውያን እና በኢትዮጵያውያን ወጣቶች መካከል በሚኖሩ የትብብር ማዕቀፎች ዙርያ ውይይት አድርገዋል። የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የተከበሩ አቶ ፍአድ ገና የአህጉሪቷን ብልፅግና ለማረጋገጥ ወጣቶች የማይተካ ሚና ያላቸው መሆኑን ገልጸው ዘላቂነት ያለው ግንኙነት ለመፍጠር በትብብር መስራትና የእውቀትና የልምድ ልውውጥ ማድረግ  ይገባል ብለዋል። ከኬንያ አቻቸው ጋር ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት ስለማካሄዳቸውም ፕሬዝዳንቱ አመላክተዋል። ✨ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን።          🌐 የማህበራዊ ገጾቻችንን ይከታተሉ! Telegram              []  Facebook           []   Website
Show all...
👍 7🥰 3👏 1👌 1
Photo unavailableShow in Telegram
▪️ በኬንያ ናይሮቢ ከመስከረም 14-16 በኢጋድ  በወጣቶች ፖሊሲ ዙርያ በተካሄደው የከፍተኛ የቴክኒክ ባለሞያዎች ስብሰባ እና የሚኒስትሮች ኮንፍረንስ ላይ የተወሰደ። ✨ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን።          🌐 የማህበራዊ ገጾቻችንን ይከታተሉ! Telegram              []  Facebook           []   Website
Show all...
👍 4 1🥰 1👏 1🤩 1