cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

Advertising posts
217
Subscribers
No data24 hours
+27 days
+430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"#ሴት_ልጅ_ክቡር_ነች፡፡ ተከብራ ነው መኖር ያለባት፡፡ እድሜዋ የተቆጠረና የተሰፈረ ነው፡፡ ለወንድ ነገ አለው ለሴት ግን ነገ አደገኛ ነው፡፡ ማንም ጎረምሳ ሕልም አለኝ ባይ ሁሉ በቃዠ ቁጥር አብራ ልትባክን አይገባም፡፡ ሚስት ወንዱ ቃዥቶ ሲጨርስ በፈጠረው ወይም ባሳካው ሕልሙ ላይ የምትሾም እመቤት እንጂ ለጉዞው ጫማ፤ ለድካሙ ማበሻ ጨርቅ፤ ለገረጣው እግሩ ውሃ እያመጣች የምታጥብ ገረድ አይደለችም፡፡" 😍 ከክብር መጽሐፍ የተወሰደ
Show all...
ያለ ይበልጣል ኣ !! ምሬት፣ እሮሮ፣ እዬዬ ምን ያመጣል ?! አድካሚ ጨፍጋጋ energy ከመፍጠር ውጪ !! ማመስገን ተስፋን ይወልዳል ያለንን ያሳየናል ። የሌሉንን በረከቶችን ይሰበስባል ። ማመስገን ደስታ የሚፈጥር ሆርሞንን ያበራክታል ። በዙርያችን ያሉ ሰዎችን ሰላም ይሰጣል ። ማመስገን መልካም ነገርን አሻግሮ ያመላክታል ። ጠንክረን እንድንሰራ አቅም ይሰጣል ። እያመሰገንን🙏
Show all...
👏 1
የብዙ ሰው ምሬት ላንዳንዱ የሰርክ ፀሎቱ ነው። ሳይነግሩን ለዋሉልን እየነገርን መዋል ነውር ነው አይደል ? ትግላችን ያለንበትን ደረጃ ያማከለ ቢሆን በትግላችን የሚያተርፉ ብዙ ናቸው ። አንድ እቅፍ ለሊቱን ሁሉ ከመተቃቀፍ የምትበልጥበት ግዜ አለ ማለት ነው ? እኔ ግን ትግሌ ከራሴ ትናንት ጋ ነው!!! የልብ እውነት ይኖራል እንጂ አይብራራም !! አንዳንድ ማጣት እፎይታው ማግኘትን ያህላል። ዳሩ ፍጡር ምን ስልጣን አለው። ስህተቱ ሲነገረው ያላመኻኘ ፣ያላላከከ ወደ ራሱ ለማየት የሞከረ እሱ ምስጉን ነው። ሰነፍ ብቻ ነው የመጣበትን ረስቶ የደረሰበት ላይ ተመርኩዞ ውሳኔ የሚሰጠው!!!
Show all...
🔥 1
የምንወዳቸው ሰወች ምን ያህል እንደምንወዳቸው ካለ እጦት እንዴት መረዳት ያቅተናል? ለራስ ሰው አለመድረስን ያህል አርፋጅነት የለም።
Show all...
መንፈስህ አይሰበርም! ፨፨፨፨///////////፨፨፨፨ ተስፋህ ሊጨልም ይችላል፤ ገንዘብህ ሊዘረፍ ይችላል፤ ሰዎች ሊርቁህ ይችላሉ፣ ብቻህን ልትቀር፣ ደጋፊ ልታጣ፣ አበርታች ላታገኝ ትችላለህ ነገር ግን በእርግጥ ከእውነተኛው መንፈስህ ጋር ከሆንክ፣ ከትክክለኛው ስሜትህ ጋር ከተዋሃድክ ያጣሀውን ሁሉ ማግኘትህ፣ ጎደለኝ የምትለውን በሙሉ ማስመለስህ የማይቀር ጉዳይ ነው። ማንነትህ የሚለካው ውስጥህ በሚመላለሰው ውስጣዊ ሃይል ነው። ብዙ ጊዜ ውጫዊ ነገሮች ጊዜያዊ ናቸውና በየሰዓቱ ይቀያየራሉ፤ ውስጣዊና ትክክለኛው ነገር ግን የሚቀየር ሳይሆን የሚሻሻል፣ የሚያድግና የሚጨምር ነው። ስለ እውነተኛው ማንነትህ ማውራት ብትፈልግ ትክክለኛው የውስጥ ስሜትህን፣ መንፈስህን ጠንቅቀህ እወቀው፤ በእርሱም ላይ ተደገፍ፤ እርሱን እመን፤ በእርሱ ተመራ። አዎ! ጀግናዬ..! መንፈስህ  አይሰበርም!በአሉታዊ ሰዎች ብትከበበ፣ ተስፋ አስቆራጭ ቃላት ቢሰነዘሩብህ፣ መጠቋቆሚያ ብትሆን፣ መጥፎ አስተያየት ቢሰጥህ፣ ዝቅ ተደርገህ ብትታይ፣ ብትናቅ፣ ብትታማ፣ ብትገፋ በእርግጥ ከውስጣዊ ስሜትህ ጋር እየተጓዝክ ከሆነ፣ ትርጉም የሚሰጥህን ነገር እያደረክ ከሆነ የተግባርህ መነሻ መንፈስህ ነውና እዴትም ተሰብረህ ልትቆም አትችልም። ምንም ስታደርግ በእርግጥም የመጣው ከውስጥህ መሆኑን እርግጠኛ ሁን። የጀመርከው በውጫዊ ግፊት ወይም ከምታየው ጊዜያዊ ነገር ብቻ እንዳልሆነ ተማመን። መንፈስ በማንም በምንም ሊቆም አይችልም፤ ትክክለኛው የውስጥ ስሜት እንዴትም ሊሰበርና ተንኮታኩቶ መቅረት አይችልም። አዎ! በእርግጥም የመንፈስ ስብራት ቀላል እንዳልሆነ የምታውቀው ውጫዊውን ጫጫታ መስማት ስታቆም፣ ትኩረትህን በሙሉ እራስህና ተግባርህ ላይ ስታደርግ፣ የጉዞህን ፍጥነት ስትጨምር ነው። የተባረክበት አንድ ነገር አለ፤ አምላክ የሚሰራብህ አንድ ተግባር አለ፤ ብቻህን ሳይሆን ከፈጣሪህ ጋር የምታሳካው፣ ከፍ የምትልበት፣ የምትታወቅበት፣ የምትደነቅበት፣ የምትኮራበት አንድ ያንተ ብቻ የሆነ ነገር አለህ። በጫና ሳይሆን እራስህ ማቆም ብትፈልግ እንኳን ልታቆመው አትችልም፤ ልትለየው ብትፈልግ እርሱ አይለይህም። ምክንያቱም ድርጊትህ ከማንነትህ ጋር ተዋህዷልና ነው፤ ምክንያቱም መነሻው ውስጥህና መንፈስህ ስለሆነ ነው። መፍቀድ ብትችል ትክክለኛው የውስጥ ስሜትህ በነፃነት ይፈስ ዘንድ፣ ተገልጦ ይታይ ዘንድ፣ አምላካም ስራውን ይሰራበት ዘንድ ፍቀድ፤ ሌላኛውንና ትክክለኛውን ማንነትህንም አሳይ።  ውብ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
Show all...
📚ከመፅሀፍት ገፅ አቀራረብን ማሳመር.... ኮምጣጤና ማር የሚሸጡ ሁለት ሰዎች ነበሩ። ብዙ ሰዎች የማሩን ባለቤት ትተው ከኮምጣጤው ባለቤት ይገዙ ነበር። ይህን ያስተዋለው ማር ሻጭ አንድ ቀን ባልደረባውን ጠየቀ። "ሰዎች የኔን ማር ትተው ወደ ኮምጣጤህ የሚያዘነብሉት ለምንድነው?" አለው። ኮምጣጤ ሻጩም መለሠለት። "እኔ ኮምጣጤዬን በማር ምላስ ነው ምሸጠው፤ አንተ ግን ማርን የመሰለ እቃ በኮምጣጤ ምለስ እየሸጥክ ነው።" አለው። 📖ሶባሐል ኸይር(✍️ ደራሲ፦ ሙሀመድ ሰዒድ) 🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት ሰናይ ምሽት ይሁንልን❤️❤️ 🙏 ቴክቶክ አካውንታችን ፎሎ ያድርጉ፡ https://vm.tiktok.com/ZM6a5oBDe/ join and follow our channel 👉 Share Share Share 👈 https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
Show all...
👍 2
#ዋጋህን_እወቀው! መነበብ ያለበት አስተማሪ ታሪክ "ትናንት ማታ አንድ ቪዲዮ እያየሁ ነበር። ሰባኪው የመቶ ብር ኖት ይዟል። እንዲህ ሲል ሰማሁት 'ይህ የብር ኖት እንደታተመ ምንም ዓይነት መጨማደድ አልነበረበትም። ከዚያ በኋላ ግን ሰዎች፦ ➡️እጽ ለመግዛት ተጠቅመውታል። ➡️ ለዝሙት ከፍለውታል። ➡️ጭቃ ውስጥ ነበር። ➡️ተቀዷል፣ ➡️ጠርዞቹ ተቆርጠዋል። ✅️ከዚህ ሁሉ ቀኋላ ይህ የመቶ ብር ኖት አሁን ዋጋው ስንት ነው? አሁንም ዋጋው ያኔ አዲስ በነበረበት ጊዜ የነበረው ዋጋ ነው። አምላካችንም እኛንም የሚያየን እንደዚህ ነው። ያለፈው ታሪካችን ምንም ሆነ ምንም፣ የቱንም ያህል የተጎዳን እንሁን፤ ለእሱ ዋጋችን ያኔ ሲፈጥረን እንደነበረው ነው።' " ✅️👉#የተሰቀለው_ንጉሥ መጽሐፍ (አዲስ መጽሐፍ) 👉 #The_Crucifixion_of_the_King_of_Glory ✅️@Enmare1988 ✅️✅️@Enmare1988
Show all...
👍 1
የሆነ ጊዜ ነበር ከልቤ ስስቅ የነበረበት፣ ግን ሌላ ጊዜም ነበር በጣም ሳለቅስ የነበረበት፣ ከዛም ሳልፍ ግን በህይወት ላይ ለማዘንም ለመደሰትም ጊዜ እንዳለዉ ያመንኩበት፥ የሆነ ጊዜ ነበር ለህይወት መጓጓት የጀመርኩበት፣ ግን ሌላ ጊዜም ነበር ሁኔታዎች ማያልፉ መስሎኝ የተጨነኩበት፣ ከዛም ሳልፍ ግን ሁሉም እንደሚያልፍ ያየሁበት፣ ህይወቴ ዉስጥ ለተፈጠሩት ነገሮች ትርጉም መስጠት የጀመርኩበት የሆነ ጊዜ ነበር ተስፋ የቆረጥኩበት፣ ግን ሌላ ጊዜም ነበር ከእንቅልፍ መንቃቴ ተአምር እንደሆነ የተረዳሁበት፣ ከዛም ሳልፍ ግን የሆነ ቀን እንደምሞት ያወኩበት ሁላችንም ይሄን ህይወትን እየኖርን ያለነዉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነዉ፣ ራሳቹ ላይ አትክበዱ ፣ ለራሳቹ ሌላ እድል ስጡ፣ የህይወትን ሌላ ጎን ለማየት አትስነፉ፥
Show all...
🥰 2
¹⭐ በእንባ ብዛት የረጠበ ሀሳቤን ስጨምቅ አልፋለው እንጂ መች የልቤን ፅፌ አውቃለው፤ህመሜን በማስታመም እከርማለው እንጂ ቁስሌ የቱጋ እንደሆነ ለማስረዳት ፋታም ሰጥቶኝም አያቅም። ``እንዴት ነሽ `` ስትለኝ ``እንዴትም `` ነበረ መልሴ...!
Show all...