en
Feedback
70/30 ኮንዶሚኒየም ማህበር

70/30 ኮንዶሚኒየም ማህበር

Open in Telegram
370
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Similar Channels
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
October '23
October '23
+370
in 0 channels
Channel Posts
ማስታወቂያ                  የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ካሉት አማራጭ የቤት ልማት አቅርቦት ውስጥ አንዱ የሆነውን የጋራ ህንጻ መኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር በከተማው ተግባራዊ ለማድረግ የ2005 ዓ.ም. የ20/80 እና የ40/60 የቤት ፈላጊ ተመዝጋቢዎችን ፍላጎትና አቅም ያላቸውን በህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው ቤት እንዲሰሩ መመሪያ በማዘጋጀት ምዝገባ ማካሄዱ፣የመሬትና ዲዛይን ስራ አጠናቆ፣ ማህበራቱን የሚጠበቅባቸውን የግንባታ 70 በመቶ በማስቆጠብ መሬት ለማስረከብ እና ወደ ግንባታ ለማስጀመር ጫፍ ላይ መድረሱ የሚታወቅ ነው፡፡ በመሆኑም ለ2ኛ ዙር አዲስ ለማደራጀትና ለ1ኛ ዙር ለተጓደሉት ማህበራት ማሟያ የህንጻ ከፍታው ቀደም ሲል በወጣው ማለትም B+G+9 እና 2B+G+13 ከመጪው ማክሰኞ 27/10/15 እስከ 30/10/15 ዓ. ም. ባሉት 4 ተከታታይ የስራ ቀናት በምትኖሩበት ወረዳ በመገኘት የሚከተሉትን መረጃዎች እንድታሟሉ፡- 1. የ20/80 እና የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን የተመዘገበ እና የቁጠባ ደብተሩን ያልዘጋ፣ 2. የ20/80 ተመዝጋቢ ከሆኑ ፕሪንት አውት ኮፒ ወይም ቢጫ ካርድ ኮፒ ማቅረብ የ40/60 ተመዝጋቢ ከሆኑ የባንክ መቆጠቢያ ደብተር ኮፒ፣( ከዋና ጋር ተገናዝቦ የሁለቱም የቤት ልማት ፕሮግራም የቁጠባ ደብተር ኮፒ ይያያዛል) 3. የቢሮው ማህተም ኖሮት በወረዳው ማህተም የሚረጋገጥ ቅፅ-01 ከምትኖሩበት ወረዳ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት በመውሰድ የሚጠየቀውን መረጃ በትክክል የመሙላትና አረጋግጦ የመፈረም፣ 4. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክልል በራሳችሁም ሆነ በትዳር አጋራችሁ ስም ቤት ወይም ቤት መስሪያ ቦታ የሌላችሁ ወይም ኖሯችሁ ከ1997 ዓ.ም ወዲህ በስጦታ ወይም በሽያጭ ያላስተላለፋችሁ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ከወረዳው የሚያቀርብ፣ 5. የታደሰ የአዲስ አበባ የኑዋሪነት መታወቂያ፣ 6. የጋብቻ ሁኔታ ሰርተፊኬት ማስረጃ፣ 7. ምዝገባው እንደተጠናቀቀ በቀጣይ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ በመመሪያው በተቀመጠው አግባብ የወቅቱን የግንባታ 70 ከመቶ ክፍያ መክፈል የሚችል። ከላይ በተጠቀሰውን መረጃ በሟሟላት በተጠቀሰው ጊዜ ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ዲያስፖራዎች ቅጽ 001 ለመሙላት ማሟላት የሚገባችሁ ማስረጃዎች፡- ምዝገባችሁ ወረዳ ሳይሆን ባምቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601 በመቅረብ ተመዝጋቢዎች ወይም በህጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት በአካል ቀርባችሁ፡-  1. የተመዝጋቢው ፓስፖርት ኮፒ፣ 2. የዲያስፖራነት ማረጋገጫ ቢጫ ካርድ ኮፒ ካልተቻለ ከዲያስፖራ ኤጀንሲ ዲያስፖራነቱን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ፣ 3. የ20/80 ተመዝጋቢ ከሆኑ ፕሪንት አውት ኮፒ ወይም ቢጫ ካርድ ኮፒ ማቅረብ የ40/60 ተመዝጋቢ ከሆኑ የባንክ መቆጠቢያ ደብተር ኮፒ፣ 4. የጋብቻ ሁኔታ ሰርተፊኬት ኮፒ፣ 5. የወቅቱን የግንባታ 70 በመቶ በውጪ ምንዛሪ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ። 6.  በተወካይ የሚፈፀም ከሆነ የተወካይ የውክልና ደብዳቤ ኮፒ እና የታደሰ መታወቂያ ማቅረብ፣ የተዘጋጀውን ቅፅ 001 መሙላት እንዳለባችሁ እንገልጻን፡፡ቢሮው ሁሉም ተመዝጋቢ ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲስተናገድ እያሳወቀ ፤ ጊዜውን አሳልፈው ለሚመጡ ኃላፊነት እንደማይወስድ ያሳስባል። የበለጠ መረጃ ከክፍለ ከተማ የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን  ያሳውቃል።