cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

እውነት አርነት ያወጣል

የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና። ሉቃስ 4፥17

Show more
Advertising posts
300
Subscribers
+124 hours
No data7 days
+3330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ኤፌሶን 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁸ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ⁹ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ድነታች በእግዚአብሔር ብቻ የተሰራ ፣ የሰው እጅ የሌለበት፣ በፀጋው ብቻ የሆነ ድንቅ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው!!!
Show all...
6🥰 2
ሮሜ 4 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ እንግዲህ በሥጋ አባታችን የሆነ አብርሃም ምን አገኘ እንላለን? ² አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም። ³ መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት። ⁴ ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርለትም፤ ⁵ ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።
Show all...
⚜️እግዚአብሔር ምላጭ ይከራያል በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ምሳሌያዊ ወይም ዘይቤያዊ የሆኑ አነጋገሮች በብዙ ስፍራዎች ተጽፈው ይገኛል። ታዲያ እነዛን የመፃፍ ቅዱስ ክፍሎች አንብቦ በቀጥታ እንደዚህ ነው ሚለው ብሎ መተርጎም የተሳሳተ መረዳት ውስጥ እንድትገቡ ያደርጋል። ስለዚህ ዜይቤያዊ የሆኑ የመፃፍ ቅዱስ ክፍሎችን በቀጥታ ሊተረጎሙ አይገባም። እስቲ ዛሬ ሙስሊሞች እግዚአብሔር ምላጭ ይከራያል ጢሙንም ይላጫል ብለው የሚያነሱትን የመፃፍቅዱስ ክፍል እንመልከት:- “በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከወንዙ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሥ የራሱንና የእግሩን ጠጕር ይላጨዋል፤ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይበላል።”   ኢሳይያስ 7፥20 በመጀመሪያ የክፍሉ ሀሳብም የሚያወራው ስለ ማነው የሚለው ግልፁ መሆን አለበት። የክፍሉ ሀሳብ የሚያወራው ስለ እግዚአብሔር ሳይሆን ስለ አክዓብ ህዝብ መሆኑን ከላይ ጀምሮ ስታነቡ ግልጽ ይሆንላችኋል። በተከራየው ምላጭ ማለት የራሱ ህዝብ ወይም እስራኤላዊ ያልሆነ ከግብጽና ከአሶር የሆነውን ህዝብ አስነስቶ እግዚአብሔር አምላክ እንደሚቀጣቸው  የሚያሳይ ነው። በዚህ ክፍል ላይ የአሶር ንጉስ እግዚአብሔር የተከራየው ምላጭ ተብሏል። #በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሥ ኢሳ 7:20 ፀጉር መላጨትና ጢምንም ደግሞ መቁረጥ (መላጨት) ትልቅ ውርደት ለመግለፁ የተጠቀመው ቃል ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ጠጉርን መላጨት የሚለው ቋንቋ  የሚያመለክተው ከክብር ማውረድን(ውርደትን) ወይም ስልጣንን ማሳጣትን እንደሆነ በብዙ የመፃፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ መመልከት ይቻላል። 👇👇👇 “ጢማቸውን ላጭተው ልብሳቸውንም ቀድደው ገላቸውንም ነጭተው፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያቀርቡ ዘንድ የእህል ቍርባንና ዕጣን በእጃቸው እየያዙ፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ ከሰማርያም መጡ።” ኤርምያስ 41:5 ሐኖንም የዳዊትን ባሪያዎች ወስዶ የጢማቸውን ገሚስ ላጨ፥ ልብሳቸውንም እስከ ወገባቸው ድረስ ከሁለት ቀድዶ ሰደዳቸው።" (መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 10:4) “ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፤ ሞዓብ በናባው በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፤ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቶአል።” ኢሳይያስ 15፥2 በአጭሩ በኢሳ 7:20 እግዚአብሔር በአሶር ንጉር አማካኝነት የአክዓብን ህዝብ ውርደት ላይ ይጥላል ማለት ነው። ይህ አይነት ቋንቋ ለሰው ልጆች ሲውል ቀጥተኛ ትርጉም የሚኖረው ሲሆን ለሀገር ሲሆን ተምሳሌታዊ ይሆናል። የኢሳ 7:20 ንግግር ደግሞ ለሀገር የዋለ በመሆኑ ተምሳሌታዊ ንግግር ነው ስለዚህ በኢሳ 7:20 እግዚአብሔር በአሶር ንጉስ አማካኝነት ወይም የአሶር ንገስን ተጠቅሞ የአክዓብን ህዝብ ውርደት ላይ ይጥላል ማለት እንጂ እግዚአብሔር ጺሙን ይላጫል ማለት አይደለም!!!✅Join us https://t.me/gospel_all እውነት አርነት ያወጣል!!!
Show all...
እውነት አርነት ያወጣል

የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና። ሉቃስ 4፥17

👍 3 3
የምድያም ነጋዶችም አለፉ፤ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጕድጓድ አወጡት፤ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሀያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።”  ዘፍጥረት 37፥28 📌 ዮሴፍ እግዚአብሔር ወዳሳየዉ የንግስና ህልም የሚደርስበት መንገድ ባርያ ሆኖ በመሸጥ ዉስጥ እንደሆነ አያዉቅም ነበር። ወደ ግብፅ በባርነት ሲሸጥ በደስታ እየሳቀ አልሄደም። ወንድሞቹ ሲሸጡት በዮሴፍ ልብ ዉስጥ ደስታ ሳይሆን የመከዳት: ያለመፈለግ የብቸኝነት ስሜት ነበር። እግዚአብሄር ግን በማይመስል መንገድ ወደ ንግስና እየወሰደዉ ነበር። ለዮሴፍ ከሚታየዉ ባርነት ጀርባ እግዚአብሔር ወደ ንግስና እየመራው ነበር። ዛሬ በህይወታችሁ ተስፋ የቆረጣችሁ በጣም በከባባድ ፈተና ውስጥ የምታልፉ እህትና ወንድሞቼ  በህይወታችሁ በሚሆነው ነገር ግራ ተጋብታችሁ እግዚአብሄር የተዋቹ የረሳቹ በሰዉም የተጠላችሁ ወዳጅ ጓደኛ የከዳችሁ ሊመስላችሁ ይችላል። ነገር ግን በዛ ዉስጥም እግዚአብሔር መንገድ አለዉና ባይመስላችሁም የተናገራችሁን ለመፈፀም ከነገሩ ጀርባ እየሰራ ነዉ። አሁን በምታልፉበት የህይወት መንገድ እየተደሰታችሁ ላይሆን ይችላል ግን እርግጠኛ እንድትሆኑ ምፈልገው ነገር finally እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ result በምታገኙት ውጤት ደስተኛ ትሆናላችሁ። ዳዊት ሲናገር “ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።” መዝሙር 119፥71 አለ። ዳዊት በአስቸጋሪ ህይወት ውስጥ ሲያልፍ ለመልካም አይመስልም ነበር። ነገር ግን መጨረሻ ላይ ያገኘውን result ሲናገር ለመልካም ሆነልኝ እንኳንም በዛ መንገድ አለፍኩኝ ብሎ ይናገራል እናም ዛሬም  በህይወታችሁ በተለያየ አስቸጋሪ መንገድ ውስጥ ስታልፉ የምታልፉበት መንገድ አስቸጋሪ:ተስፋ አስቆራጭ ሊሆን ይችላል ግን በስተመጨረሻ የምታልፉበት አስቸጋሪ መንገድ ህልማችሁን የምታገኙበት እንደሆነ ሲገባቹ እንኳንም በዚህ ነገር ውስጥ አለፍኩኝ እንድትሉ እግዚአብሔር ያደርጋችኋል። ስለዚህ ፅኑ በርቱ መፀለያችሁን ከእግዚአብሔር ጋር ህብረታችሁን ቀጥሉ ትጋታችሁን ጨምሩ። እናንተ በፅናት ከጌታ ጋር ቁሙ እንጂ ባርነት መከዳት: ብቸኝነት :መጣል በሚመስልም መንገድ ውስጥ እግዚአብሔር ግን ከዘመናት በፊት ወዳየላችሁ ወደ ንግስናችሁ እየመራችሁ ነውና አይዟችሁ። ✅Join us https://t.me/gospel_all እውነት አርነት ያወጣል!!!
Show all...
እውነት አርነት ያወጣል

የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና። ሉቃስ 4፥17

👍 2 2😍 2
02:09
Video unavailableShow in Telegram
ህፃናትን ማግባት በእስልምና 🧏‍♂🧏‍♀👂 ✅Join us https://t.me/gospel_all እውነት አርነት ያወጣል!!!
Show all...
10.41 MB
ህፃናትን ማግባት በእስልምና 🧏‍♂🧏‍♀👂✅Join us https://t.me/gospel_all እውነት አርነት ያወጣል!!!
Show all...
እውነት አርነት ያወጣል

የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና። ሉቃስ 4፥17

02:10
Video unavailableShow in Telegram
ህፃናትን ማግባት በእስልምና 🧏‍♂🧏‍♀👂
Show all...
2.55 MB
አዳም በሃጢአት ከወደቀ በኋላ እግዚአብሔርን የፈለገው አዳም ሳይሆን አዳምን ​​የፈለገው እግዚአብሔር ነው። አዳም በሰራው ሀጢያት ምክንያት ከእግዚአብሔር ፊት ኮብልሎ ነበር እግዚአብሔር ግን አዳምን ፍለጋ ያለበት ድረስ መጣ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህ ቅደም ተከተል አልተቀየረም። ዛሬም እኛ ሳንፈልገው ፈልጎ ያገኘን እራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ክብር ለስሙ ይሁንለት!!!
Show all...
8👍 1
እግዚአብሔር  ኢየሱስን መስዋዕት ሳያደርገው ይቅር ሊለን አይችልም ነበር ??? ለምን ኢየሱስን መቅጣት አስፈለገው?? ሙስሊም እህትና ወንድሞቼ ብዙ ጊዜ ይሄንን ጥያቄ ይጠይቃሉ። በእርግጥም ጥያቄው ተገቢና መጠየቅ ያለበት ነው። እግዚአብሔር ኢየሱስን መስዋዕት ሳያደርገው ይቅር ሊለን አይችልም ነበር ወይ ለሚለው አይችልም!!! ምክንያቱም እኛ ሁላችን ኃጢአተኞች የነበርን የእግዚአብሔር ፍርድ የሚጠብቀን በራሳችን ጥረት ከእግዚአብሔር ፍርድና ቁጣ ልናመልጥ የማንችል ሰዎች ነበርን። መፃፍ ቅዱስ ሲናገር “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው" ሮሜ 6፥23 ይላል። ሰው ሁሉ ደግሞ ሀጥያትን ሰርቷል። ለሰራው ሀጢያት ደግሞ የሚከፈለው ደሞዝ ሞት ነበር። እግዚአብሔር ፍፁም ፃድቅና ፍትሀዊ በመሆኑ ሰው ይህን የሀጥያት እዳ መክፈል ነበረበት። ላጠፋው ጥፋት ፍርድን መቀበል ይገባው ነበር፡፡ ፍርዱም የዘላለም ሞት ነው። ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ እግዚአብሔር ቸርና መሀሪ በመሆኑ በመልኩና በምሳሌው የፈጠረውን የሰው ልጅ ሊያጠፋና እስከመጨረሻው ሊቀጣ አልወደደም። ያለምንም ቅጣት እንዲያው ይቅር ሊል የእርሱ ባህሪ አይፈቅድለትም፡፡ እግዚአብሔር በባህሪው ጻዲቅ ፈራጅ ነውና ፍርዱን ሟጓደል አይችልም፡፡ ምክንያቱም እርሱ ፍትሃዊ አምላክ ስለሆነ ለምሳሌ ሰውን የገደለ ሰው 10 አመት እንደሚታሰር ሕግ ቢወጣና ይሄንንም ህግ ተላልፎ ከበደ የሚባል ግለሰብ ሰው ገድሎ ዳኛ ጋር ቢቀርብ ዳኛው ፍትሃዊ ነው የሚባለው ማንም የሚጠይቀው አካል ስለሌለ ወይም ማንም ከእኔ ስልጣን በላይ የለም ብሎ ሲፈርድ ሳይሆን ሕጉን መሠረት አድርጎ ሲፈርድ ነው። ነገር ግን ማንም ከበላዬ የሚከሰኝ የለም ብሎ ቢፈርድ ኢ- ፍትሐዊ ከመሆን አያድነውም። ፍትህን የሚያደርግ እውነተኛ ሲሆን የማያደርግ ግን ሀሰተኛ ነው። ልክ እንደዛው ሁሉ እግዚአብሔር ለአዳም እና ለሔዋን መልካም እና ክፉን ከምታስታውቀው የዛፍ ፍሬ እንዳይበሉ ሕግ ሰጥቷቸዋል። ይሄንንም ህግ ተላልፈው ከበሉ ሞትን እንደሚሞቱ ፍርዱንም አብሮ ነግሯቸው ነበር። ይህም ፍርድ ዘላለማዊ ሞት ነው። እግዚአብሔር እውነተኛ ነው የምንለው አዳምና ሔዋን የዘላለም ሞት ሲፈረድባቸው ነው። ሰውን የገደለው ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ ዳኛው በቃ ገድለኸዋል ግን ነፃ ለቀንሃል ቢለው ዳኛው ታማኝነቱ ያጣል፡፡ ፍትህ ይጓደላል፡፡ እንዴት ሰውየው አጥፍቶ ያለምንም ቅጣት በነፃ ይለቀቃል?? የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ልክ እንደዛው እግዚአብሔር የሰው ልጅ ላጠፋው ጥፋት ተገቢውን ቅጣት ሳይቀጣ ይቅር ቢል ፍትህ ይጓደላል። እግዚአብሔር ፍትሃዊ አምላክ መሆኑ ይቀራል። ስለዚህ ዳኛው ፍትሃዊ የሚሆነው በህጉ መሰረት ሲፈርድ እንደሆነ እግዚአብሔርም ፍትሃዊ የሚሆነው በህጉ መሰረት ሲፈርድ ነው። ነገር ግን ዳኛው መሀሪ ሊሆን በፍጹም አይችልም። ምክንያቱም መሀሪ ለመባል ከበደን ይቅር ማለት አለበት። ይቅር ካለው ደግሞ በሕጉ መሠረት ስላልፈረደ ኢ-ፍትሃዊ ይሆናል። ሕጉን ማስተካከያ ቢያደርግለት መጀመሪያ የወጣው ሕግ ፍጹም ወይም ፍትሀዊ አልነበርም ማለት ነው። ይህ ደግሞ ሕግ አውጪውን አካል ደካማ ወይም በሰጠውን ህግ የማይጸና ያስብለዋል። እግዚአብሔር  ደግሞ ለሰዎች የሰጠው ሕግ መተዳደሪያ ደንብ ሳይሆን የእርሱ ባህርይ ነው። ህጉ የእርሱ ባህሪ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር መጀመሪያ ያወጣውን ህግ ጥሶ ምህረት ቢያደርግ ፍትሀዊ አምላክ መሆኑ ይቀራል። ከባህሪው ጋር ይጣረሳል። ምክንያቱም ሰው ለሰራው ጥፋት በህጉ መሰረት ፍርድ ይገባዋልና። ይሄም ሞት ወይም ከእግዚአብሔር መለየት እና ለዘላለም በፍርድ ስር መሆን ነው። እግዚአብሔር ይህን ፍርድ አለማስተላለፉ እርሱን ሀሰተኛ ያደርገዋል። ይህን ፍርድ ካስተላለፈ ደግሞ መሀሪ አምላክ መሆኑ ሊቀር ነው። ስለዚህ እኛን ከዘለአለም ፍርድ ለማዳን የግድ አምላክ ሰው ሆኖ  ወደ ምድር መምጣት ነበረበት አለበለዚያ እውነትና ምህረት በፍጹም ሊስማሙ አይችሉም፡፡ እውነት በአንድ ጎን ቆማ ሰው ለሰራው ኃጢአት ፍርድ ይሰጠው ስትል ምህረት ደግሞ በሌላ ጎን ቆማ ይቅርታ ይደረግላቸው ትላለች፡፡ እውነትና ምህረት አንድ ማድረግ በጣም አስቸጋሪ ነው ምክንያቱም እግዚአብሔር ሁሉት ልዩ ባህርያት አሉት። እግዚአብሔር ፃድቅም ነው ፍቅርም ነው። እግዚአብሔር ፃድቅ ነው ማለት ሀጥያተኛውን ዝም ብሎ ይቅር አይልም ፃድቁ ላይ አይፈርድም ማለት ነው። እግዚአብሔር ፍፁም ፍትሀዊ የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ እግዚአብሔር በፍቅር የተሞላ መሀሪ አምላክ ነው። እግዚአብሔር እነዚህን ሁለት ባህሪያቶች በአንድ ላይ የያዘ ነው አምላክ ነው። ስለዚህ ይሄንን ሁለት ባህሪያት ለማስማማት የእግዚአብሔር ትልቁ እቅድ ምህረትና እውነትን አንድ ማድረግ ነበር፡፡ ሁሉቱም አንድ እንዲሆኑ የሁለቱም የምህረትና የእውነት ጥያቄ መመለስ አለበት፡፡ የምህረት ጥያቄ ብቻ ቢመለስ እውነት ዘላለም ጥያቄዋን ማቅረብ አታቆምም፡፡ እውነት ሰው ለሰራው ኃጢአት ፍርድ እንዲሰጠው ምህረት ደግሞ ይቅርታ እንዲደረግላቸው፡፡ ታድያ ይሄን ነገር ማስታረቅ የሚችል ሰው አልነበረም። ስለዚህ እውነት እና ምህረትን ለማስማማት አምላክ ሰው በመሆን በእኛ ምትክ በመስቀል ላይ መሞት ነበረበት። ይህን የቤዛነት ስራ ሊሰራ የሚችል ሀጢአት የሌለበት ከሰዎች መካከል ስለሌለ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰጠን፡፡ ከስላሴ አካል አንዱ የሆነው ወልድ በገዛ ፈቃዱ በእኛ ላይ የነበረውን የሞት ፍርድ ሊቀበል በስጋ ተለገለጠ፡፡ ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እኛን ሆነ፡፡ ከዘላለም ጀምሮ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ቃል(ኢየሱስ ክርስቶስ) ስጋ ሆነ። እውነትና ምህረትም በክርስቶስ ኢየሱስ ተስማሙ እኛም ከእግዚአብሔር ቁጣ እና ፍርድ አመለጥን ከእግዚአብሔር ጋር በኢየሱስ ታረቅን። ከሥላሴ አካላት መካከል አንዱ የሆነው ወልድ የኃጢአት ዕዳችንን በመክፈል ከእግዚአብሔር ፍትሃዊ ፍርድ ነፃ አወጣን። እግዚአብሔር አፍቃሪ አባት የሆነውን ያህል ፍትሃዊ አምላክም ጭምር በመሆኑ ምክንያት በኃጢአተኞች ላይ እንዲፈርድ ፍትሃዊ ባሕርዩ ግድ ስለሚለው ኢየሱስን መስዋዕት ሳያደርገው እንዲያው ይቅር ሊለን አይችልም ነበር ነገር ግን በእኛ ላይ የነበረውን የዘላለም ፍርድ እግዚአብሔር በልጁ ላይ አድርጎ እኛን ከዘላለም ፍርድ አዳነን። የእግዚአብሔር ፍትህና የእግዚአብሔር ፍቅር በእኩል ሁኔታ የተገለጡበት ብቸኛ ቦታ የክርስቶስ መስቀል ነው፡፡   “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።” ሮሜ 6፥23 ✅Join us https://t.me/gospel_all እውነት አርነት ያወጣል!!!
Show all...

3👍 1🥰 1
እግዚአብሔር አብ ኢየሱስን መስዋዕት ሳያደርገው ሊያድነን ወይም ይቅር ሊለን አይችልም ነበር ??? ሙስሊም እህትና ወንድሞቼ ብዙ ጊዜ ይሄንን ጥያቄ ይጠይቃሉ። በእርግጥም ጥያቄው ተገቢና መጠየቅ ያለበት ነው። እግዚአብሔር ኢየሱስን መስዋዕት ሳያደርገው ሊያድነን አይችልም ነበር ወይ ለሚለው አይችልም!!! ምክንያቱም እኛ ሁላችን ኃጢአተኞች የነበርን የእግዚአብሔር ፍርድ የሚጠብቀን በራሳችን ጥረት ከእግዚአብሔር ፍርድና ቁጣ ልናመልጥ የማንችል ሰዎች ነበርን። መፃፍ ቅዱስ ሲናገር “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው" ሮሜ 6፥23 ይላል። ሰው ሁሉ ደግሞ ሀጥያትን ሰርቷል። ለሰራው ሀጢያት ደግሞ የሚከፈለው ደሞዝ ሞት ነበር። እግዚአብሔር ፍፁም ፃድቅና ፍትሀዊ በመሆኑ ሰው ይህን የሀጥያት እዳ መክፈል ነበረበት። ላጠፋው ጥፋት ፍርድን መቀበል ይገባው ነበር፡፡ ፍርዱም የዘላለም ሞት ነው። ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ እግዚአብሔር ቸርና መሀሪ በመሆኑ በመልኩና በምሳሌው የፈጠረውን የሰው ልጅ ሊያጠፋና እስከመጨረሻው ሊቀጣ አልወደደም። ያለምንም ቅጣት እንዲያው ይቅር ሊል የእርሱ ባህሪ አይፈቅድለትም፡፡ እግዚአብሔር በባህሪው ጻዲቅ ፈራጅ ነውና ፍርዱን ሟጓደል አይችልም፡፡ ምክንያቱም እርሱ ፍትሃዊ አምላክ ስለሆነ ለምሳሌ ሰውን የገደለ ሰው 10 አመት እንደሚታሰር ሕግ ቢወጣና ይሄንንም ህግ ተላልፎ ከበደ የሚባል ግለሰብ ሰው ገድሎ ዳኛ ጋር ቢቀርብ ዳኛው ፍትሃዊ ነው የሚባለው ማንም የሚጠይቀው አካል ስለሌለ ወይም ማንም ከእኔ ስልጣን በላይ የለም ብሎ ሲፈርድ ሳይሆን ሕጉን መሠረት አድርጎ ሲፈርድ ነው። ነገር ግን ማንም ከበላዬ የሚከሰኝ የለም ብሎ ቢፈርድ ኢ- ፍትሐዊ ከመሆን አያድነውም። ፍትህን የሚያደርግ እውነተኛ ሲሆን የማያደርግ ግን ሀሰተኛ ነው። ልክ እንደዛው ሁሉ እግዚአብሔር ለአዳም እና ለሔዋን መልካም እና ክፉን ከምታስታውቀው የዛፍ ፍሬ እንዳይበሉ ሕግ ሰጥቷቸዋል። ይሄንንም ህግ ተላልፈው ከበሉ ሞትን እንደሚሞቱ ፍርዱንም አብሮ ነግሯቸው ነበር። ይህም ፍርድ ዘላለማዊ ሞት ነው። እግዚአብሔር እውነተኛ ነው የምንለው አዳምና ሔዋን የዘላለም ሞት ሲፈረድባቸው ነው። ሰውን የገደለው ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ ዳኛው በቃ ገድለኸዋል ግን ነፃ ለቀንሃል ቢለው ዳኛው ታማኝነቱ ያጣል፡፡ ፍትህ ይጓደላል፡፡ እንዴት ሰውየው አጥፍቶ ያለምንም ቅጣት በነፃ ይለቀቃል?? የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ልክ እንደዛው እግዚአብሔር የሰው ልጅ ላጠፋው ጥፋት ተገቢውን ቅጣት ሳይቀጣ ይቅር ቢል ፍትህ ይጓደላል። እግዚአብሔር ፍትሃዊ አምላክ መሆኑ ይቀራል። ስለዚህ ዳኛው ፍትሃዊ የሚሆነው በህጉ መሰረት ሲፈርድ እንደሆነ እግዚአብሔርም ፍትሃዊ የሚሆነው በህጉ መሰረት ሲፈርድ ነው። ነገር ግን ዳኛው መሀሪ ሊሆን በፍጹም አይችልም። ምክንያቱም መሀሪ ለመባል ከበደን ይቅር ማለት አለበት። ይቅር ካለው ደግሞ በሕጉ መሠረት ስላልፈረደ ኢ-ፍትሃዊ ይሆናል። ሕጉን ማስተካከያ ቢያደርግለት መጀመሪያ የወጣው ሕግ ፍጹም ወይም ፍትሀዊ አልነበርም ማለት ነው። ይህ ደግሞ ሕግ አውጪውን አካል ደካማ ወይም በሰጠውን ህግ የማይጸና ያስብለዋል። እግዚአብሔር  ደግሞ ለሰዎች የሰጠው ሕግ መተዳደሪያ ደንብ ሳይሆን የእርሱ ባህርይ ነው። ህጉ የእርሱ ባህሪ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር መጀመሪያ ያወጣውን ህግ ጥሶ ምህረት ቢያደርግ ፍትሀዊ አምላክ መሆኑ ይቀራል። ከባህሪው ጋር ይጣረሳል። ምክንያቱም ሰው ለሰራው ጥፋት በህጉ መሰረት ፍርድ ይገባዋልና። ይሄም ሞት ወይም ከእግዚአብሔር መለየት እና ለዘላለም በፍርድ ስር መሆን ነው። እግዚአብሔር ይህን ፍርድ አለማስተላለፉ እርሱን ሀሰተኛ ያደርገዋል። ይህን ፍርድ ካስተላለፈ ደግሞ መሀሪ አምላክ መሆኑ ሊቀር ነው። ስለዚህ እኛን ከዘለአለም ፍርድ ለማዳን የግድ አምላክ ሰው ሆኖ  ወደ ምድር መምጣት ነበረበት አለበለዚያ እውነትና ምህረት በፍጹም ሊስማሙ አይችሉም፡፡ እውነት በአንድ ጎን ቆማ ሰው ለሰራው ኃጢአት ፍርድ ይሰጠው ስትል ምህረት ደግሞ በሌላ ጎን ቆማ ይቅርታ ይደረግላቸው ትላለች፡፡ እውነትና ምህረት አንድ ማድረግ በጣም አስቸጋሪ ነው ምክንያቱም እግዚአብሔር ሁሉት ልዩ ባህርያት አሉት። እግዚአብሔር ፃድቅም ነው ፍቅርም ነው። እግዚአብሔር ፃድቅ ነው ማለት ሀጥያተኛውን ዝም ብሎ ይቅር አይልም ፃድቁ ላይ አይፈርድም ማለት ነው። እግዚአብሔር ፍፁም ፍትሀዊ የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ እግዚአብሔር በፍቅር የተሞላ መሀሪ አምላክ ነው። እግዚአብሔር እነዚህን ሁለት ባህሪያቶች በአንድ ላይ የያዘ ነው አምላክ ነው። ስለዚህ ይሄንን ሁለት ባህሪያት ለማስማማት የእግዚአብሔር ትልቁ እቅድ ምህረትና እውነትን አንድ ማድረግ ነበር፡፡ ሁሉቱም አንድ እንዲሆኑ የሁለቱም የምህረትና የእውነት ጥያቄ መመለስ አለበት፡፡ የምህረት ጥያቄ ብቻ ቢመለስ እውነት ዘላለም ጥያቄዋን ማቅረብ አታቆምም፡፡ እውነት ሰው ለሰራው ኃጢአት ፍርድ እንዲሰጠው ምህረት ደግሞ ይቅርታ እንዲደረግላቸው፡፡ ታድያ ይሄን ነገር ማስታረቅ የሚችል ሰው አልነበረም። ስለዚህ እውነት እና ምህረትን ለማስማማት አምላክ ሰው በመሆን በእኛ ምትክ በመስቀል ላይ መሞት ነበረበት። ይህን የቤዛነት ስራ ሊሰራ የሚችል ሀጢአት የሌለበት ከሰዎች መካከል ስለሌለ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰጠን፡፡ ከስላሴ አካል አንዱ የሆነው ወልድ በገዛ ፈቃዱ በእኛ ላይ የነበረውን የሞት ፍርድ ሊቀበል በስጋ ተለገለጠ፡፡ ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እኛን ሆነ፡፡ ከዘላለም ጀምሮ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ቃል(ኢየሱስ ክርስቶስ) ስጋ ሆነ። እውነትና ምህረትም በክርስቶስ ኢየሱስ ተስማሙ እኛም ከእግዚአብሔር ቁጣ እና ፍርድ አመለጥን ከእግዚአብሔር ጋር በኢየሱስ ታረቅን። በእኛ ላይ የነበረውን የዘላለም ፍርድ እግዚአብሔር በልጁ ላይ አድርጎ እኛን  ከዘላለም ፍርድ አዳነን!!! ✅Join us https://t.me/gospel_all እውነት አርነት ያወጣል!!!
Show all...
እውነት አርነት ያወጣል

የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና። ሉቃስ 4፥17