924
Subscribers
No data24 hours
-67 days
-2730 days
Posts Archive
924
"እቀናለሁ"...ትለኛለች..."በተጠጋው ሰይጣን ሳይቀር ነው የምቀናው...በሚምገው ሲጋራም ጭምር".......የቅናቷን ጥግ ታብራራልኛለች...
"አሁን እኔን አስቀምጦ እንዲህ ሲጋራ መለምጠጥ ነበረበት...እኔን ራሱ እንደዛ ስሞኝ አያውቅም እኮ....?"
"ካካካካ እና ሲጋራውን ባደረገኝ እያልሽ ነበራ.."
"በናትህ አንተ ደግሞ አትጨምርብኝ...ተቀምጦበት ሲያሞቀው የዋለን ድንጋይ ጥሎ ላለመሄድ እኮ ነው አልሸኝሽም ያለኝ...ከድንጋይም ያቀለለኝ ምን አድርጌው ነው...."...ድምጿ ላይ ድካም አለ...ደስ አለኝ...የደከማት ስለመሰለኝ ደስ አለኝ....
"እስቲ ተወት አርጊው...."....አልኳት ልቤን አልሰማ ብዬ...ልቤ ልቡን አስፍቶ በላት ያለኝን ብላት ከኔ አርባ ክንድ እንደምትርቅ ስለማውቅ ......
"ከነመፈጠሩ እርሺውና ከኔ ጋር ሁኚ...አፈቅርሻለሁ እኮ ቀላል ነው...ላንቺ የሚሰማኝን ስሜት ለመግለፅ ገና አዲስ ቃል እስኪፈጠር እየጠበቅኩ ነው...አፈቅርሻለሁ አልበቃኝም....".....ልቤ ነው ያለው...አፌ አላላትም...
"ምንድን ነው እንደዚህ መጃጃል..."....ይሉኛል ያልተነኩ ጓደኞቼ ከቅዠቴ ጋር ሊያገላግሉኝ....
"በጌታ እንደዚህ አትበለኝ....አፈቅረዋሁ...አንድም ሳላስቀር ስለ እርሱ ማወራህ እኮ እንደሌሎቹ ጓደኞቼ 'ተይው ይቅርብሽ' ስለማትለኝ ነው.... "...ከዛ እምባዋ ተዥጎደጎደ....ተጠጋኃት...ቀስ እያልኩ ከትንፋሿ በላይ ቀረብኳት...ከአይኗ ሽፋሽፍት በላይ ለአይኗ ቀረብኩ....የታቆረው እንባዋ ተጋፍቶ ሲወጣ እኔ እንድገባ ቦታ እየለቀቀልኝ መሰለኝ....ይሄን ሁሉ ድፍረት ከየት እንዳመጣሁት እግዜር ይወቀው...
ግባ ብሎ ቦታ የለቀቀልኝ እንባዋን አላሳፈርኩትም...ገባሁ...በዛች ቅፅበት ከምስኪን ነብሷ ጋር የተጣበቅኩም መሰለኝ....በደንብ ያወቅኳት...አውቄ ያልናቅኳት ብቸኛ ነብስ...አወቅኩሽ ናቅኩሽ ባህሪዬ በነነ...ቀረብኳት አላልኳችሁም...አይኗ የኤዶም ገነት እምባዋ ደግሞ ከዛ እንደሚፈልቀው ማርና ወተት...አፍንጫዋ ስንደዶ...ከንፈሯ ላይ ቆየሁ...አይኗ ውስጥ ያየሁት ግራመጋባት ድንጋጤ እና ፍርሀት አልያዘኝም...የበሰበሰ ዝናብ አይፈራማ..በስብሻለኃ..እንኳን ዘንቦብኝ ድሮም ብስብስ ነኛ...ፍቅሯ ካበሰበሰኝ ሰነባብቷላ...
"ምን እየሆንክ ነው....".....ከንፈሯ ቃላት ሲተፋ ሌላ ነው...ምንም ትበል...ከዛ አንደበት ስለወጣ ብቻ የተቀደሰ ቃል ነው..."ነብሴን ቀድሽው...የምፈራው ነገዬ ላይ ኑሪበት...ነገን እንዳልፈራ...."...አሁንም ልቤ ነው ይሄን ባዩ....
"ሄኒ...."...ጠራችኝ....ሚሰማት ያለ መስሏት...ከንፈሯ ይንቀጠቅጣል.... ትልቅ ጥፋት ሰራሁ... ልቤን ሰማሁት....ያ ከንቱ ፍቅረኛዋ ይለመጥጠዋል ካለችው ሲጋራ በላይ ከንፈሯን ኖርኩበት...
ገፈተረችኝ...ከንፈሯ ላይ የቆየሁበት ቅፅበት እንደ ዘመን ተለቀብኝ..አንድ ነገር አስተዋልኩ...መልሳ ስማኛለች...ደስ አለኝ...
"ምን እየሆንክ ነው ሄኖክ...."...በሙሉ ስሜ ጠርታኝ አታውቅም...አሁን ደግሞ ከፋኝ...ምን እንደምላት ስለማላውቅ ተርበተበትኩ....የቅድሙ ድፍረቴን ማን እንደወሰደብኝ አላውቅም....
"መልሰሽ ስመሺኛል...ሩታ በማርያም ንገሪኝ ለእኔ ስሜት አለሽ...?
"ለእርሱ ራሴን መቼም ይቅር አልለውም....."....
አንደበቴ ተሳሰረ....የቅድሙ ሄኖክ ጥሎኝ ሄደ እርሷም ዝም እንዳልኳት በቆምኩበት ጥላኝ ሄደች....
አሁን ድል ያለ ድግስ ላይ ነኝ....ከሲጋራው በላይ መቼ ቦታ እንደሰጣት አላውቅም....ያ ሰው አገባት....ለመጨረሻ ጊዜ ያወራነው ያኔ ነው....የማላውቀው ሄኖክ አብሮኝ የነበረ ጊዜ....
"ወደ ኬክ ቆረሳው ፕሮግራም ልናልፍ ስለሆነ ሙሽሮች ወደ ፊት...."....ኬኩ ሲቆረስ እኔ የተቆረስኩ ያክል ሰውነቴ ሲቆራረጥ ታወቀኝ...ደግሞ ትስቃለች....በጣም ከልክ በላይ ትፈግጋለች....አዳራሽ ውስጥ ከተሰበሰቡት ሰዎች ፈልጋ ሰርቃ ታየኛለች....አይኗ ላይ ሳይቀር ሳቅ አለ....
"ብዙ የምትስቀው ሲከፋት እኮ ነው"....የሚል የግጥም ስንኝ አቃጨለብኝ....እያየችኝ ትስቃለች....እኔ ደግሞ እያየኃት ጥጌን ይዤ
እጠጣለሁ....
አንድ ጊዜ እንኳን ደፍሬ ለምን አገባሽው ብዬ ሳልጠይቃት ባመቱ ክርስትና ተጠራሁ...
እሺ እንደፈለገች ትሁን...ግን ባትጠራኝ ምን ትሆናለች....?
✍Shewit dorka
ወገን ግቡ እንጂ😁👇
https://t.me/shewitdorka
924
ባህሪዎን መቀየር ይፈልጋሉ?
አሪፍ Challenge ከሊቅነት እነሆ!
ዲሲፕሊንድ ነህ/ነሽ? ዲሲፕሊን የስኬታችን ቁልፍ ነውይታወቃል! የብዙዎች ደግሞ ክፍተት ነው!
ለ1ወር ከለሊት 9-10 ስለዲሲፕሊን ከሊቁ ጋር እንማራለን። If you want Success Join Us!
https://t.me/liquism
በ0929192323 ስማችሁን በቴክስት ላኩልን!
924
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል።
(መስከረም 27/2016 ዓ.ም) የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል። በዚህም ዙሪያ ትምህርት ሚኒስቴር ነገ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ይሆናል።
924
Baga ayyaana Irreechaan isin gahe. Ayyaanni kun nagaa fi kan namaaf yaadu akka ta'u hawwina
እንኳን ለኢሬቻ በአል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም እና የመታሳሰብ ይሆን ዘንድ ተመኘን
924
✨✨✨በነገራችን ላይ.....✨✨✨
በነገራችን ላይ 'እኛ ኢትዮጵያውያን' ምናምን ብለን ከምንፎክረው ማንነታችን ጀርባ ትልቅ ደም መጣጭ አውሬ አለ....በስም ተከልሎ ያለ....እኮ እኛ ...ማንንም አትይ አንተን ነው ማወራው...
.....አዎ እኛ ኢትዮጵያውያን በሰይፍ አንገት አንቀላም....በምላሳችን ግን ስንገዘግዝ እንውላለን...አንደኛውን በተሳለ ሰይፍ አንገት መቁረጥ እኮ ገላግሌ ነው....እኛ እኮ ባልተሳለ ሰይፍ በዚህ በምላሳችን ስንከረክም እንከርማለን...ከአንገቱ በፊት ሰውነቱን እንቦጫጭራለን.....
በነገራችን ላይ እኛ ኢትዮጵያውያን እንለያለን....
እንለያለን...በምላሳችን በቁም አፈር እናለብሳለን...ቀን ሲከዳ እኛም ተደርበን እንከዳለን...
ከቤተሰብ አቅም ልጆች እናበላልጣለን...ቀን የጣለው ልጃችን ላይ ፊታችንን ባናዞር እንኳን ቅንድባችን እሺ ብሎ አይፈታልንም...አንዳንዶቻችን የሰው አፍ ፈርተን ነው ሁላ አንቅረን የማንተፋቸው... .ጊዜ ያስጎነበሰው አንሶ እኛ የእኔ የሚለን ሰዎች እጥፍ እናስጎነብሰዋለን....ሰው ከቤተሰቡ በላይ ማን ያውቀዋል...ገንዘብ ሲኖረው እኮ እናውቀዋለን እንዴት እንደነበር...ብሶት ሳያይልበት እኮ እናውቀዋለን እንዴት ተጫዋች እንደነበር...ሰላም ሲኖረው እኮ እናውቀዋለን ዲዳ ጠርቶ እንደሚያናግር.....ኩርምትምት ከማለቱ በፊት እናውቀዋለን....በሰበብ በአስባቡ የሚያነጫንጨው መሰበርን ከመሰበሩ በፊት በፊት...ከስብርባሪው በፊት ያለውን እርሱ እናውቀዋለን....
ቀን ሲስቅ የዋለ ቤተሰባችን ማታ ጎኑን ሊያሳርፍ የመጣበት ቤቱ ውስጥ ጠብ ጠብ ሲለው አንድ ነገር እንጠርጥር...እኛ ጋር ማስመሰል እንዳልቻለ እንወቅለት....እናም እናመስግን...ትክክለኛ ስሜቱን ስላሳየን...ከዛም እንቀፈው...ልክ እንደ ልጅነቱ...ከዛም
"...ምንድን ነው የሆንከው...?" እንበለው...የምር በጣም ቀላል እኮ ነው....
ብዙ ጊዜ ስላጋጠመኝ ነው..."ሰላም እኮ ነው የዋለው...ቤት ሲመጣ ነው ሴጣኑ ሚነሳው...ለውጭ አልጋ ለቤት ቀጋ...."....የሚሉ ወጊ ምላሶች....በእኛ ምላስ ቤተሰብነት ትርጉም ያጣል....ተራ ስም ብቻ ይሆናል....እና ከልብ የልብ ሰው እንሁን...ከሰዎች ንጭንጭ ጀርባ ያለውን መከፋት እና ያልተሰማ ብሶት እንመርምር....
ህይወት ከውስጥ ወደ ውጪ ነው ይባል የለ...ውስጣችን ሰላም ሲሆን እኮ ያለ ምክንያት ጥርሳችን ይፈግጋል...የማያስቅ ቀልድ ያስቀናል.....በቃ አለም ዘጠኝ ላትሞላ አስር እያልን መዝፈን ሁላ ያምረናል...የእኔማ ይለያል... የሆነ የአበባ ማሳ ውስጥ ኩቹ ኩቹ ሆታሄ እያልኩ በዝናብ ስጨፍር ከዛ ሻሩክ መጥቶ "ሸዊትዬ እኔኮ በጣም ነው የምወድሽ...ለምንድን ነው የምትኮሪብኝ...ቆይ ምን ያንሰኛል...ይኸው ባንቺ ምክንያት አረቄ ከጀመርኩ ድፍን አንድ አመት ሆነኝ."...ብሎ ሲለማመጠኝ ሁላ ይታየኛል😂(ይሄማ እብደት ነው እንዳትሉኝ ብቻ)....ደግሞ እኮ በአማርኛ ነው የሚያወራው...ከዛ ድንገት ኩዚ ከየት መጣ ሳይባል "አንዴ ላናግራት...ዞር በልልን...."...(ይሄም በአማርኛ ነው😂)...ሲለው ሻሩክ ተናዶ እዛው ሲደባደቡ በቃ ከራሴ ምናብ ጋር ስዝናና መሽቶ ይነጋል...ውስጣችን ሰላም ሲሆን ቀልድ አንፈጅም....እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው የሰውን ስሜት ለመረዳት እንሞክር...ሰው እስከሆንን ድረስ ውድቀት አያስገርመን...
አንድ አባት ምን አሉ "ወልዶ ያልጨረሰ በልጅ እንደማይስቀው...እኛም ኖረን አልጨረስንምና መውደቅ አያስገርመን....ክፋት አይሙቀን...መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበለን...ያ ሰው መከራውን ተስሎ አላመጣውምና በሰው ውድቀት ጮቤ አንርገጥ...የሰውን ድክመት ስንሰማ በጆሮአችን እየሰማን በልባችን እንፀልይ...ፈተናው ፈተናችን እንዳይሆን....."
ሰላም ዋሉልኝ😊
✍Shewit dorka
https://t.me/shewitdorka
924
✨✨✨ይለያል✨✨✨
ታቅፌ አቃለው....የሱ ግን ይለያል ....ስጋዬን ብቻ ሳይሆን ነብሴንም የሚነካ ይመስለኛል... እቅፉ አለም ነው.... ጫጫታ...ሁካታ ሁሉን አስቀርቶ ሰላም ፍቅር ብቻ የሚሰጥ ልስልስ ብሎ ጠንከር ያለ ምቾትም ደንነትም ያለው.....
ማንም አይገባውም....እኔ ግን አውቀዋለሁ እና ይለያል...ትንፋሹ ሌላ ነው .....አዎ ትንፋሽ ያሞቃል...ሰውነት ቀስ በቀስ እንዲግል ያደርጋል አውቃለሁ.... የሱ ግን ከዚህም ይልቃል... እያንዳንዱን ሰውነቴን ሲያነዝረው ይሰማኛል... ልቤም ምቷን እየቀነሰች መታ ዝም ያለች ይመስለኛል.... ከትንፋሹ ውጪ ምንም ሙቀት ምንም አየር ወደ ውስጤ አይገባም...የሱ ብቻ እሱ ብቻ።
ለሌላው አይገባም አውቃለሁ...ብቻ ግን ይለያል.. ዓይኖቹን ሳያቸው ሀጥያቴ በሙሉ የሚሰረይልኝ ይመስለኛል..ፈጣሪ ሀጥያትሽን ሰርዤልሻለሁ ሽልማትሽን ሰጥቼሻለሁ ብሎ የሰጠኝ ይመስለኛል እሱን። የኔን እሱ። ለዛ ነው መሰለኝ በአይኑ ሀፅያቴን ሲሰርልኝል በራሴ አፍሬ አይኔን ከአይኑ ስነቅል ቀና አርጎኝ "እገባሻለው" ይለኛል...ከዛ ደስ ይለኛል እንዲህ ማን ይገኛል በእይታ ነብስንም ስጋንም ሚያስደስት።
ለሌላው አይገባም አውቃለሁ... ብቻ ግን ይለያል ። ሰውነቴን ሲነካኝ አለም መሽከርከዋን ድንገት ታቆማለች... ከኔ ሰውነት ጋር የሷም የተነካ ይመስል አብራኝ ታፍራለች። ህመሜ በሙሉ ይፈወሳል ። ፀጥ...ልስልስ...ሞቅ.. ይለያል ።የእውነት 😊 ብዙ እንዲነካኝ ብዙ በታመምኩኝ እሱ እንዲያክመኝ ብዙ በቆሰልኩኝ እስክል ያደርሰኛል ።
አውቃለሁ ለሌላው አይገባም...ብቻ ግን ይለያል። ልክ ሲስመኝማ ውይይይይ የልቤ የሀሴት ምት ኒዩክለርን ያስንቃል... የሰውነቴ አካሎች በሙሉ ከንፈር እስኪመስሉ ድረስ ሲያጣጥሙት ይታወቀኛል.... እየሳመኝ እጁን ሰውነቴ ላይ ሲያንሸራሽር በቃ ያን ጊዜ የመፈጠሬን አላማ ያገኘው ይመስለኛል ። በሱ ለመሳም በሱ ለመነካት የሱን ጠረን ለማሽተት የሱ ለመሆን የሱ ብቻ ። የኔ እሱ 😚።ለሌላው አይገባም አውቃለሁ.... ብቻ ግን ይለያል።
የእውነት.......
✍Kalkidan
https://t.me/shewitdorka
924
"ይበርዳል"....እንዳልኩት ጃኬቱን ትከሻዬ ላይ አኖረው....ሳላስበው የሆነ አይነት አስተያየት አየሁት መሰለኝ "ምነው"....አለኝ በትኩረት እያየኝ....
"ያንተ ጃኬት የሚሽረው አይነት ብርድ አይደለም የሚበርደኝ...."....አሁን ደግሞ በትኩረት ከማየቱ ላይ ግራ መጋባት አከለበት...
"ያን ያሀል ወፍራም አይደለም...ወይ ከውስጥ ሸሚዜን ደርቢ..."...አለኝ ቡናማ ሸሚዙን እንደማውለቅ እያለ....
"አይደለም...አይደለም...እያልኩ ያለሁት ጭራሽ አልገባህም..."...አልኩት እንዴት እንደማስረዳው ለራሴም ሳይገባኝ
"አሁን ገባኝ...የምን ዙሪያ ጥምጥም ነው...መታቀፍ ፈለግኩ አትይም...ጦጣ..."....አለኝና ከሰፊው ደረቱ ለጠፈኝ....
እቅፉን መንጭቄ ወጥቼ የእርሱ ትንፋሽ እና የእርሱ ጨርቅ እንደማያሞቀኝ ልነግረው ቃጣኝ...
"ምነው ቀበጥሽ"....ይሉኛል ጓደኞቼ ገና እርሱን መውደድ ልቤ አሻፈረኝ እንዳለኝ ለማውራት ዳር ዳር ስል...ምን ላድርግ...እኔም ልቤን ምነው ቀበጥክ ልበለው....?ብለውስ ልብ ከራሱ ውጪ ማንን ይሰማና ነው .... the heart want what it wants....ተብሎ የተዘፈነለት እኮ ያለ ነገር አይደለም....ምናል አሁን ይቺ ልጅ የምታስጠልለኝ ማረፊያዬ ናት ብሎ እንኳን ትንሽ ቢራራልኝ...
አሁንም እየበረደኝ ነው...እየበረደኝ ነው...ዮናስ እቅፍ ውስጥ ሆኜ የቢኒ ድምፅ እየራበኝ ነው... ልቤ ወደ ቢኒ ይጎትተኛል...ልቤ የእኔ እንዳልሆነ ነገር ከቢኒ ጋር ያዳብለኛል.. በለሊት ሳይቀር ይቀሰቅሰኛል...አንዳንዴ መተንፈስ እራሱ ዳገት ይሆንብኛል....
አሁንም ከእቅፉ መውጣት ያምረኛል...ግን አልወጣም....እሱ እቅፍ ውስጥ ቢኒን እየሳልኩ አንገቱን እስመዋለሁ...በምላሹ ጥብቅቅቅ አድርጎ ያቅፈኛል...እርሱ መች ገባው በምናቤ ከማን ጋር እየተሟሟቅኩ እንዳለሁ...
አሁን እቅፉ ውስጥ ሰርጌ ነው....አዎ እየተዳርኩ ነው...ቢኒን እያገባሁት....ከዛ ጫጉላዬ ይከተላል...በምናቤ ዛሬም ሰርጌ ነው...ነገም ሰርጌ ነው...የሙሽራ ቀሚሴን አድርጌ ብቅ ስል ልክ ፊልም ላይ እንደማያቸው ወንዶች የሚያለቅስ ይመስለኛል...ደግሞ በሆነኛው ቀን የማርገዜን ዜና ሳበስረው የደስታ እንባውን ይደግመዋል....በውኔ ስላስለቀሰኝ ነው መሰለኝ በምናቤ እንባ አስገብረዋለሁ....በምናቤ ሁሌ ከበሮ ይደለቃል....ክራሩ ይከረከራል...በገናው ይደረደራል....ነጋሪቱ ይጎሰማል.....ቢኒ በጋሪው ላይ ጉብ ብሎ ሊወስደኝ ሲመጣ ዮናስ ደግሞ ፈረሱን ይመስለኛል...
"ያለ ፈረስ ጋሪ 'ጋሪ' አይባል ...ወደፊት እየገሰገስሽ ያለሽው እኮ በሚያሻሽሽ ቢኒ ሳይሆን ተሸክሞሽ በሚሮጠው ዮናስ ነው"....ይለኛል ህሊና የሚባለው ምቀኛ...
"እያሻሸኝ ዘመኔ ይለቅ...ባለሁበት ልቅር...እርሱ ካለ መሮጥ ይቅርብኝ...ወዴትም አልሂድ..."....እለዋለሁ
"ታዲያ እንደሱ ከሆነ ፈረሱን ሸኝዋ...."
"ምን ብዬ ልሸኘው...ታኝኮ ታኝኮ የተተፋ ማስቲካ...ጣፋጩ ያለቀን ሸንኮራ አንስቶ ነፍስ የዘራባትን ሰው...ምን ብዬ...ምን ጎደለኝ ብዬ...በሰርጓ እለት ሙሽራዋ ለቀረባት ሴት ...ለተዋረደች ሴት ክብር የሆነን ባል ምን ብዬ ልሸኘው....'ክብር አይወድልኝም ልበለው....ምን ልበለው...."
"ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም ...ልበለው...እንኳን ሊወጋኝ ቀርቶ በሙሉ አይኑ እንኳን አያየኝም እኮ..."....ከህሊናዬ ጋር ሙግት ይዣለሁ....
ከሙግቱ በኃላ ይቺን አልኩ.....
"ዮኒ...."
"ወዬ እማ...."
"እባክህ ከምናቤ ጋር ተወኝ...."
"አልተውሽም....ምናብሽ ከእኔ ይነጥቅሻል...እማ አንቺን ይወስድብኛል....ምናብ እኮ ምናብ ነው....አንድ ቀን ትመለሻለሽ....ስትመለሺ እንድታጪኝ አልፈልግም....የትም አልሄድም.... በዛ ሰውዬ ስም ስትጠሪኝ በፈገግታ ወዬ የምልሽ አንድ ቀን ስሙን ከአፍሽ ነጥለሽ የእኔን ትሰይሚያለሽ በሚል ተስፋ ነው....ቀሽም ተስፋ ሊሆን ይችላል....ግን ተይኝ ልቀሽም....ካንቺ ጎን እስካለሁ ድረስ...ዞር ስል አንቺን እስካየሁ ድረስ ሌላው ትርፍ ነው....በቃ ፍቀጅልኝ አንቺ እስክትመለሺ ልጠብቅ... "
"እቀፈኝ....".....አልኩት ከሚወርደው እንባዬ ጋር እየታገልኩ.....
"እሺ...እሺ...".....ታቅፌ እንደማላውቅ አቀፈኝ.......
"አልሂድ....አትሸኚኝ....ትንሽ ሞክሪ....እማ ምናብሽን ፊት ለመንሳት....አንዴ እንኳን እኔን ለማየት....."....ይለኛል እቅፉ ውስጥ ደብቆኝ....
"እሺ...እሺ...ትንሽ አይደለም በደንብ እሞክራለሁ....."
✍Shewit dorka
Telgram👉https://t.me/shewitdorka
Tiktok👉https://vm.tiktok.com/ZMjfJW4eb/
924
Repost from አስተማሪ ሀሳቦች እና አጫጭር ወጎች
እራስህን ውደድ !!
እራስን መውደድ ማለት ምን ማለት ነው? መልሱ እንደየገለጻችን የተለያየ ልሆን ይችላል
እኔ ልበላችሁ ;እራስን መውደድ ማለት ለራስህ ቦታ መስጠት ማክበር ለራስህ መልካም ምኞት መመኘት እና እራስህ መንከባከብ ነው እራሱን የማይወድ ሰው እንኳን ለራሱ ያልጠቀመ ለበተሰቡ ለማህበረሰቡ ለሀገሩ አይጠቅምም ለምሳሌ እራሱን የሚወድ ሰው እራሱን አይጎዳም እራሱን ሱስ ውስጥ አይደብቅምም አይቅም ጪስ ወደ ውስጡ አያስገባም መራራውን አልኮል ወደውስጡ አያስገባም አንተ የጠላህውን ማንነት ማንም አይወድም ሰውንም የምትወደው የሚታከብረው እራስን ስትወድና ስታከብር ነው b/c ባንተ ውስጥም የከበረ ማንነት አለና ስትቆሽ የምትታጠበው እግሮችህ ስቆሽሹ የምትታጠበው እራስህን ስትወድ ነው እራስህን መውደድ እና ራስ ወዳድነት ለየቅል ናቸው እራስህን መውደድ ከልክ በላይ ስሆን ራስ ወዳድነት ልሆን ይችላል እራሳችሁ ውደዱ አክብሩ ከማንም እኩል እንደሆናችሁ ለራሳችሁ ንገሩ "እችላለሁ ""አደርጋለሁ" እያላችሁ ከራሳችሁ አልፋችሁ ለራሳችሁ የምት ሰጡትን ቦታ ለሰውም አጋሩ 🙏✍ሲሳ
924
Repost from አስተማሪ ሀሳቦች እና አጫጭር ወጎች
ለማመስገን ምክንያት አትጠብቅ ዛሬን ያላዩ በርካታ ናቸውና በህወት በመኖርህ ብቻ ተመስገን በል ነገም እንድ ሰምሪልህ 🙏🙏ተመስገን አምላኬ🙌🙌🙌🙏
