cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

Show more
Advertising posts
7 954
Subscribers
+6224 hours
+2157 days
+60430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት አንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ከእኩለ ለሊት ጀምሮ ዛሬ እስከ ረፋድ ባለው በከባድ መሣሪያ የታገዘ ውጊያ መካሄዱ ተሰማ! ውጊያውን የከፈቱት መነሻቸውን ከልዩ ዞኑ ያደረጉ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከገዢው ቡድን ወታደሮች ጋር በጋራ በመሆን ነው ተብሏል። እነዚህ ፀረ ሰላም ኃይሎች የከፈቱትን ጥቃት የአማራ ፋኖ በሸዋ ዕዝና የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጋራ በመናበብ መመከታቸውን ነው የአማራ ድምፅ ሚድያ የሸዋ ዘጋቢዎች ያረጋገጡት። በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ሀገረ ማርያም ሟጨራ ቀበሌ ልዩ ስሙ መስኖ የተባለ አከባቢን ጨምሮ ጨቀጨቅ፣ አምቦ ውሃ፣ ገተም ጎጆ ውሃና አንቀር ኮብኮብ የተባሉ ቀበሌዎች ላይ ዛሬ ግንቦት 12/2016 ዓ/ም እኩለ ለሊት ገደማ ጀምሮ በድሽቃና በሌሎች ከባድ መሣሪያዎች የታገዘ ውጊያ የተካሄደ ሲሆን፡ በዚህም በርካታ ቁጥር ያላቸው የሸኔ ኃይሎችና የገዢው ቡድን ወታደሮች መገደላቸውን ነው የአማራ ፋኖ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአስቴ ጎማ ተራራ ክ/ጦርና የአማራ ፋኖ በሸዋ ዕዝ አፄ ይኩነአምላክ ክ/ጦር የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ብርጌድ ቃል አቀባዮች ለአማራ ድምፅ ሚድያ የገለፁት። የገዢው ቡድን ወታደሮች በልዩ ዞኑ መሽጎ ከሚገኘው የሸኔ ኃይል ጋር ጥምረት በመፍጠር በሸዋ ቀጠና ስር ባሉ አከባቢዎች ላይ ጥቃት ሲያደርሱ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ከዚህ ቀደም በዚኸው በልዩ ዞኑ መሽገው የሚገኙ የአሸባሪ ኃይሎችን በማስታጠቅና የከባድ መሣሪያ ሽፋን በመስጠት ተደጋጋሚ የሆነ ጥቃት በመሰንዘር በርካታ ንፁኋን አርሶ አደሮችን ሲገድሉ በተጨማሪም ንብረት ማውደማቸውንም የአማራ ድምፅ ሚድያ ተጎጂዎችን ዋቢ በማድረግ መዘገቡ አይዘነጋም። ዛሬም በተመሣሣይ ከእኩለ ለሊት ጀምሮ እስከ ረፋድ ባለው ጥቃት ከፍተው የነበሩት የገዢው ቡድን ወታደሮችና የሸኔ ታጣቂዎች ከባድ ኪሳራን አስተናግደው ወደ መጡበት መመለሳቸው ነው የተገለፀው። ከእኩለ ለሊት ጀምሮ እስከ ረፋድ ባለው ተከፍቶ የነበረውን ጥቃት የአማራ ፋኖ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአስቴ ጎማ ተራራ ክ/ጦርና የአማራ ፋኖ በሸዋ ዕዝ አፄ ይኩነአምላክ ክ/ጦር የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ብርጌድ ፋኖዎች በጋራ በመሆን መመከታቸውን የሁለቱም ዕዝ ፋኖ ቃል አቀባዮች ለአማራ ድምፅ ተናገረዋል። በአሁን ሰዓት ቀጠናው በፋኖ ቁጥጥር ስር የገባ ሲሆን በጥቃቱ ተደናግጦ የነበረውን ማሕበረሰብ የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል። ተጨማሪ👉https://www.youtube.com/watch?v=xi4dfpvoHsI
Show all...
ዜና! የድል ዜና ሸዋ አንፆኪያ ገምዛ!ሁለቱ ዕዞች ተቀናጅተው የፈፀሙት ጀብድ!

#Amharanewsservice #አማራዜና አግልግሎት #thevoiceofamhara #amhara #fanopinions #gobeze_sisay #ethiopia

👍 13
Show all...
ዜና! የድል ዜና ሸዋ አንፆኪያ ገምዛ!ሁለቱ ዕዞች ተቀናጅተው የፈፀሙት ጀብድ!

#Amharanewsservice #አማራዜና አግልግሎት #thevoiceofamhara #amhara #fanopinions #gobeze_sisay #ethiopia

7
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት አንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ከእኩለ ለሊት ጀምሮ ዛሬ እስከ ረፋድ ባለው በከባድ መሣሪያ የታገዘ ውጊያ መካሄዱ ተሰማ! ውጊያውን የከፈቱት መነሻቸውን ከልዩ ዞኑ ያደረጉ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከገዢው ቡድን ወታደሮች ጋር በጋራ በመሆን ነው ተብሏል። እነዚህ ፀረ ሰላም ኃይሎች የከፈቱትን ጥቃት የአማራ ፋኖ በሸዋ ዕዝና የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጋራ በመናበብ መመከታቸውን ነው የአማራ ድምፅ ሚድያ የሸዋ ዘጋቢዎች ያረጋገጡት። በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ሀገረ ማርያም ሟጨራ ቀበሌ ልዩ ስሙ መስኖ የተባለ አከባቢን ጨምሮ ጨቀጨቅ፣ አምቦ ውሃ፣ ገተም ጎጆ ውሃና አንቀር ኮብኮብ የተባሉ ቀበሌዎች ላይ ዛሬ ግንቦት 12/2016 ዓ/ም እኩለ ለሊት ገደማ ጀምሮ በድሽቃና በሌሎች ከባድ መሣሪያዎች የታገዘ ውጊያ የተካሄደ ሲሆን፡ በዚህም በርካታ ቁጥር ያላቸው የሸኔ ኃይሎችና የገዢው ቡድን ወታደሮች መገደላቸውን ነው የአማራ ፋኖ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአስቴ ጎማ ተራራ ክ/ጦርና የአማራ ፋኖ በሸዋ ዕዝ አፄ ይኩነአምላክ ክ/ጦር የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ብርጌድ ቃል አቀባዮች ለአማራ ድምፅ ሚድያ የገለፁት። የገዢው ቡድን ወታደሮች በልዩ ዞኑ መሽጎ ከሚገኘው የሸኔ ኃይል ጋር ጥምረት በመፍጠር በሸዋ ቀጠና ስር ባሉ አከባቢዎች ላይ ጥቃት ሲያደርሱ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ከዚህ ቀደም በዚኸው በልዩ ዞኑ መሽገው የሚገኙ የአሸባሪ ኃይሎችን በማስታጠቅና የከባድ መሣሪያ ሽፋን በመስጠት ተደጋጋሚ የሆነ ጥቃት በመሰንዘር በርካታ ንፁኋን አርሶ አደሮችን ሲገድሉ በተጨማሪም ንብረት ማውደማቸውንም የአማራ ድምፅ ሚድያ ተጎጂዎችን ዋቢ በማድረግ መዘገቡ አይዘነጋም። ዛሬም በተመሣሣይ ከእኩለ ለሊት ጀምሮ እስከ ረፋድ ባለው ጥቃት ከፍተው የነበሩት የገዢው ቡድን ወታደሮችና የሸኔ ታጣቂዎች ከባድ ኪሳራን አስተናግደው ወደ መጡበት መመለሳቸው ነው የተገለፀው። ከእኩለ ለሊት ጀምሮ እስከ ረፋድ ባለው ተከፍቶ የነበረውን ጥቃት የአማራ ፋኖ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአስቴ ጎማ ተራራ ክ/ጦርና የአማራ ፋኖ በሸዋ ዕዝ አፄ ይኩነአምላክ ክ/ጦር የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ብርጌድ ፋኖዎች በጋራ በመሆን መመከታቸውን የሁለቱም ዕዝ ፋኖ ቃል አቀባዮች ለአማራ ድምፅ ተናገረዋል። በአሁን ሰዓት ቀጠናው በፋኖ ቁጥጥር ስር የገባ ሲሆን በጥቃቱ ተደናግጦ የነበረውን ማሕበረሰብ የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል። ### አዲሱን የአማራ ድምፅ ሚድያ ተቋም አንድ አካል የሆነውን አማራ ዜና አገልግሎት/Amhara News Service ቻናልን ሰብስክራይብ አድርጋችኋል ወይ? http://www.youtube.com/@AmharaNewsService
Show all...
Amhara News Service (ANS)

Share your videos with friends, family, and the world

👍 19 1
በሰሜን ወሎ እና በደቡብ ወሎ ዞን ተሰማርተው ከነበሩ የአድማ ብተና አባላት መካከል ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ ከ150 በላይ የሚሆኑት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸው ተሰማ! በራያ የአማራ ክልል መዋቅር እንዲፈርስ ከተደረገ ወዲህ ከአሃዳቸው እየከዱ ወደ ፋኖ የሚቀላቀሉ የአድማ ብተናና ፖሊስ አባላት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ነው የተመላከተው። ያለፉት ሁለት ቀናት በደቡብ ወሎ ዞን በሐይቅ፣ በቢስቲማ፣ በወረባቦ፣ በውጫሌ ዙሪያና በአምባሰል እንዲሁም በሰሜን ወሎ ደግሞ በመርሳ፣ በውርጌሳ፣ በወልድያ ዙሪያ፣ በቆቦ፣ በላስታ እና በሙጃ ዙሪያ በቁጥር ከ150 በላይ የአድማ ብተና አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸውን ነው የአማራ ድምፅ ሚድያ የወሎ ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ የቻሉት። የአማራ እርስት በሆኑት ግራ ካሱን ጨምሮ በሌሎች የራያ አከባቢዎች የተከሰከሰው የጓዶቻችን አፅም ሳይነሳ የሞቱለት አላማ ከግብ ሳይደርስ በመቅረቱ፡ በገዢው ስርዓት ላይ ያለን እምነት አብቅቷል፣ አማራጫችን አፈሙዝ ማዞር ብቻ ነው ሲሉ የአድማ ብተና አባላቱ ለአማራ ድምፅ ሚድያ ገልፀዋል። ግምቦት 09/2016 ዓ/ም እና ግምቦት 10 እንዲሁም በትናንትናው ዕለት ብቻ በሰሜን ወሎ ዞን በላስታ 24 የአድማ ብተና አባላት፣በወልድያ ዙሪያ 13፣ በመርሣ 12፣ በኒኒ በር 5፣ የአድማ ብተና አባላት እንዲሁም በደቡብ ወሎ ዞን ደግሞ በሐይቅ 17፣ በቦቀቅሳ 22፣ በውጫሌ 9፣ በወረባቦ 5(አንድ መቶ አለቃ ከነ አጃቢዎቹ) በአምባሰል 22፣ በፀሀይ መውጫ 4፣ በወግዲና በሌሎች ምዕራብ ወረዳዎች በቁጥር 19 የአድማ ብተና አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በአቅራቢያቸው የሚገኙ የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ክፍለጦሮችን መቀላቀላቸውን ነው የአማራ ድምፅ ሚድያ የወሎ ዘጋቢዎች ካሰባሰቡት መረጃ ለማረጋገጥ የቻሉት። በተመሣሣይ በራያ ቆቦ ወረዳ ስር ባሉ አከባቢዎች ተሰማርተው የነበሩ በርካታ የአድማ ብተና እንዲሁም የሚሊሻና የፖሊስ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ ፋኖ ተቀላቅለዋል። ከሦስት ሳምንታት በፊት ከ970 በላይ የሚሊሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የአሁኑ የአማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ አንድ አካል የሆነውን የቀድሞው የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝን መቀላቀላቸውን በወቅቱ ዕዙ በሰጠው መግለጫ ማስታወቁ አይዘነጋም። በሁለቱ ዞኖች ያለፉት ሁለት ቀናት ብቻ ከ150 በላይ የአድማ ብተና አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸውን ተከትሎ በክልሉ ፀጥታ ቢሮ ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤ መፈጠሩም ተሰምቷል። ተሰማርተው ከነበሩበት የሐይቅ ከተማ አከባቢ ከድተው ወደ ፋኖ የተቀላቀሉት በቁጥር 17ቱ የአድማ ብተና አባላት፡ "እስከ ዛሬ ይሰጣችኋል ተብሎ ቃል የተገባልንን የቤት መስሪያ ቦታ ከዛሬ ነገ ይሰጠናል ብለን ብንጠብቅም ነገር ግን የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል። በዚህ መኃል በርካታ ጓዶቻችን ተሰውተውብናል" ሲሉ ለአማራ ድምፅ ሚድያ ገልፀዋል። በተጨማሪም "በርካታ ጓዶቻችንን ገብረን፣ ስጋና አጥንታችን ከስክሰን ያስመለስነውን የራያና የወልቃይት እርስታችን በድጋሚ ተመልሶ ለሕወሓት ተሰቶብናል፣ ለምን ብለው የጠየቁ አባሎቻችንም ታፍነው ተወስደው የደረሱበትን አናውቅም። በዛላይ ከወንድሞቻችን ጋር እንድንገዳደል ተገደናል። በዚህ ሁኔታ ይሄንን የአገዛዝ ስርዓት እንዴት ልናገለግል እንችላለን?" ሲሉ ጥያቄም አንስተዋል። የቤት መስሪያ ቦታ ስንጠብቅ በምትኩ እየተሰጠን ያለው የቀብር ጉድጓድ ነው ያሉት የአድማ ብተና አባላቱ፡ ከማለቃችን በፊት እስከ ዛሬ ክህደት የፈፀምንባቸውን ፋኖ ወንድሞቻችን ይቅርታ ጠይቀን ያሳዘነውን ህዝባችንን ልንክስ በአዴንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ክድተን ወጥተናል ብለዋል። ያለፉት ሁለት ቀናት በሁለቱ ዞኖች ፋኖን ከተቀላቀሉት ከ150 በላይ የአድማ ብተና አባላት መካከል አብዛኻኞቹ ልዩ ኃይሉ ሳይፈርስ በፊት 2ኛና 3ኛ ዙር ሰልጥነው የመክት ብርጌድ፣ የጣና፣ የበላይ እና የመቅደላ ብርጌድ አባላት እንደነበሩ የአማራ ድምፅ ሚድያ የወሎ ዘጋቢዎች ካሰባሰቡት መረጃ ለማረጋገጥ ችለዋል። እንሆ ተጨማሪ👉 https://www.youtube.com/watch?v=VG7tlLRutow
Show all...
ዜና!አድማ ብተናና ሚሊሻው አፈሙዙን አዞረ!በሁለት ቀናት ውስጥ ከ150 በላይ ከነትጥቁ ከዳ!

#Amharanewsservice #አማራዜና አግልግሎት #thevoiceofamhara #amhara #fanopinions #gobeze_sisay #ethiopia

👍 27
"84.5 በመቶ የሚሆነውን ሰራዊቴን አጥቻለሁ" የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናንት ጀኔራል ብርሀኑ በቀለ! ጀኔራሉ ይህንን ያሉት በጎንደር ምርኮኛ ወታደሮቹን በምስል ከተመለከቱ እና የኮበለሉ የሰራዊቱን አባላት በሰዉ ሀብት አስተዳደሩ በኩል ሪፖርቱን ካዳመጡ በኋላ ነዉ ሲሉ መረጃውን ለአማራ ድምፅ ሚድያ ያደረሱ የውስጥ አዋቂዎች ገልፀዋል። ጀኔራሉ ከዚህ በፊትም ሰራዊቱ በየጊዜው የሚኮበልል የሰራዊቱ አዛዦች ጦር መምራት ስለማይችሉ ነዉ ማለታቸዉ የሚታወስ ነዉ። በጎንደር ደጎማ፣በአርማጭሆ፣ በደንቢያ በአንባ ጊዮርጊስ፣በአጊሳ፣ በአይንባና በእስቴ መካነ እየሱስ ብቻ በቁጥር ከ200 በላይ የሰራዊቱ አባላት መማረካቸውን በምስል ከተመለከቱ በኋላ የክፍለጦር አመራሮችን ሰብስበዉ ትችትና ወቀሳ መሰንዘራቸውን ውስጥ አዋቂዎች ለአማራ ድምፅ ሚድያ ገልፀዋል። ሰራዊቱን እና የሰራዊቱን አመራሮች በመዉቀስ የሚታወቁት ጀኔራሉ በሰዉ ሀብት አመራሩ በኩል የቀረበላቸው ሪፖርት ያዳመጡ ሲሆን፡ በሪፖርቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የሞቱ የሰራዊቱ አባላትን፣ቆስለዉ በጦረታ የተገለሉትን፣ቆስለዉ በሆስፒታል ህክምና የማከታተሉትን እንዲሁም የከዱትን የሰራዊት ብዛት ቀርቦላቸዋል ነው የተባለው። በሪፓርቱ 84.5 በመቶ የሚሆነዉ የሰራዊት አባል ማጣታቸዉን ተከትሎ ለጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ብርሀኑ ጁላ ሪፖርት ማቅረባቸውን የዉስጥ አዋቂ ምንጮች ለአማራ ድምፅ ሚድያ ጨምረው ገልፀዋል። ዝርዝሩን ይከታተሉ! https://www.youtube.com/watch?v=pauUrNr0G4Q
Show all...
''84.5 በመቶ የሚሆነው ሰራዊቴን አጥቻለሁ'' ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ! ብርሀኑ በቀለ ዲሽቃን እያስታጠቀን ነዉ የጎንደር ፋኖ!

#Amharanewsservice #የአማራዜናአገልግሎት #gobeze_sisay #thevoiceofamhara #amhara #fanopinions #ethiopia

👍 19
Show all...
''84.5 በመቶ የሚሆነው ሰራዊቴን አጥቻለሁ'' ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ! ብርሀኑ በቀለ ዲሽቃን እያስታጠቀን ነዉ የጎንደር ፋኖ!

#Amharanewsservice #የአማራዜናአገልግሎት #gobeze_sisay #thevoiceofamhara #amhara #fanopinions #ethiopia

Photo unavailableShow in Telegram
👍 3
ኮሎኔል ይመር ገበዬሁ! ስለ መራዊ እውነታ በሚል የተሰራውን ዘጋቢ ፊልም ያስተባበረው ይህ ኮሎኔል ይመር ገበዬሁ የሚባል አዛዥ ነው። የገዢው ቡድን ወታደሮች ጥር 21/2016 ዓ/ም የአስተርዕዮ ማርያም ዕለት መራዊ ላይ ለመስማት የሚቀፍ፡ ለማየት የሚዘገንን ግፍ በከተመዋ ነዋሪዎች ላይ መፈፀማቸው ይታወቃል። በዚህ ጭፍጨፋ ወቅት አስር አለቃ በላይ አባተ የተባለ አንድ የአማራ ተወላጅ እና አስር አለቃ ገ/ጊዮርጊስ የተባለ ሌላ አንድ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት "ለምን ያለ አግባብ ንፁኋንን እንጨፈጭፋለን? ተልዕኳችንም  ይኼ አይደለም። የታጠቀውን አካል ለይተን ለምን አንመታም?" ብለው በመጠየቃቸው ብቻ  ታፍነው  ተወስደው የት እንዳደረሷቸው አይታወቅም። በዕለቱ ከ100 በላይ ንፁኋን በጅምላ መጨፍጨፋቸውን የአማራ ድምፅ ሚድያ የሟች ቤተሰቦችን በማነጋገር መዘገቡ አይዘነጋም። የገዢው ፓርቲ ወታደሮች በከተማዋ ቤት ለቤት እየዞሩ ነዋሪዎችን ከቤታቸው እያወጡ እንደረሸኗቸው፣ በርካቶችን ደግሞ በተሽከርካሪ ጭነው ወደ በከተማዋ ዳርቻ በመውሰድ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደሏቸው የሟች ቤተሰቦች በወቅቱ ለአማራ ድምፅ ሚድያ ገልፀዋል። መከላከያ ሰራዊቱ በመራዊ ከተማ ነዋሪዎች ላይ  የፈፀመውን ጭፍጨፋ እውነታውን ለማስቀየርና እጃችን የለበትም ለማለት የሰሩት ዘጋቢ ፊልም ግን ዘግናኙ ጭፍጨፋ በተፈፀመበት የከተማዋ ማሕበረሰብ ቁስል ላይ እንጨት የሚሰድ ሆኗል። ይህን ዘጋቢ ፊልም ከአለቆቹ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በበላይነት በማስተባበር ያሰራው የ99ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ የሆነው  ኮ/ል ይመር ገበየሁ ነው። ይህ ወታደራዊ አዛዥ ዘጋቢ ፊልሙ ላይ በፋኖ የተጎዱ መስለው የሚተውኑ ተዋናዮች የመመልመል እንዲሁም ይሄንን ትርኢት የሚቀርፁ የሚድያ አካላትን የመምራት ስራ ሲሰራ ነበር። በዘጋቢ ፊልሙ መንገድ ላይ በርካታ መኪና ተደርድሮ የሚያሳይ ምስል እና አሽከርካሪዎቹ ደግሞ በአንድ ቤት ተሰብስበው ሰራዊቱን ሲያዩ በደስታ ከተሰበሰቡት ቤት ወጥተው ወደ ሰራዊቱ በመሄድ ታግተን ነበር በሚል ሲያወሩ ይሰማሉ። የሚገርመው ግን ይህ ቀረፃ ከመካሄዱ ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ ከኛ ሻለቃ ለዚሁ ተግባር የተመለመሉ በቁጥር 15 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲቪል እንዲለብሱ ተደርገው በመንገድ ላይ የሚያልፍ መኪና በማስቆም ዝርፊያም ሲፈፅሙና የተሽከርካሪዎችንም ጎማ በጥይት ሲመቱ ጋዜጠኞቹና ካሜራማኖቹ  በድብቅ ሲቀርፁ ነበር። ዝርፊያና እገታውን የሚፈፅሙት የሰራዊቱ አባላት ካሜራ ውስጥ እንዳይገቡ በጥንቃቄ ነበር ቀረፃው የተካሄደው። ይሄንን ሁሉ በበላይነት ያስተባበረው ኮሎኔል ይመር ነው። የ99ኛ ክ/ጦር አዛዥ የሆነው ኮሎኔል ይመር ገበየሁ በሰሜኑ ጦርነት የ27ኛ ክ/ጦር ምክትል አዛዥ የነበረ ሲሆን በወቅቱ ከክፍለ ጦሩ አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል አዲስ ሙሀመድ ጋር በመሆን ከደሴ እስከ ኮምቦልቻና ከሚሴ ድረስ ከጤፍ እስከ ሌሎች ንብረቶች ሲዘርፉ የነበሩ  ሰዎች ናቸው። ኮለኔል ይመር በተለይ ከሚሴ ላይ ከጄነራል ጌታቸው ጉዲና ጋር በመሆን ከፍተኛ የሆነ ዝርፊያ የፈፀመ ሰው ነው። ኮሎኔል ይመር በመቀጠልም ሶማሌ ሴክተር ሶስት ዱንስር በሚባል ቦታ የአንዲት ሻለቃ አዛዥ ተደርጎ የተዛወረ ሲሆን ታድያ ይህ ሰው በተለይ የአማራ ተወላጆችን የፋኖ ደጋፊ ናችሁ እያለ ሲያስርና ከሰላም አስከባሪነታቸው ሲያባርር የነበረ ግለሰብ ነው። ከተባረሩት መካከልም አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ተወላጅ የሆነ ሃምሳ አለቃ አበበ የሚባል የመሐንድስ ሙያተኛ  ይገኝበታል። በተጨማሪም በዚያው በሶማሌ ሴክተር እያለን አድስ አበባ ለሚገነባው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ቤተ መንግስት ማሰሪያ በሚል ለሻይ ቡና ከሚሰጠን ብር ላይ ይቆርጥብን ነበር። በመጨረሻም የአማራ ክልሉ ጦርነት እየከበደ ሲመጣ በሱማሌ ሴክተር እሱ ሲመራት የነበረችውን ሻለቃ ይዞ ወደ ጎጃም በመምጣት ከ99ኛ ክ/ጦር ጋር በማቀላቀል ክ/ጦሩንም እየመራ ይገኛል። ይህ ኮለኔል ውልደቱና እድገቱ ደቡብ ወሎ ዞን ሲሆን መከላከያ ሰራዊቱን ከተቀላቀለ ጀምሮ ሲዘርፍ፣ ሲገድልና ሲያስገድል የነበረና አሁንም ከዚህ ድርጊቱ ያልታቀበ ሰው ነው። ይህ ወታደራዊ አዛዥ ከአምስት ወራት በፊት ጀምሮ በአማራ ክልል ከተሰማራ ወዲህ በርካታ ንፁኋን አርሶ አደሮችን የፋኖ ደጋፊ ናቸው በሚል በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለ ሲሆን፡ በተጨማሪም ባለሀብቶችን በማገትና በማሰር ከመቶ ሺ ብር ጀምሮ እየከፈሉ እንዲወጡ ሲያስገድድ ከርሟል። አሁንም በዚሁ ድርጊቱ ቀጥሏል። ለተጨማሪ https://youtu.be/DacBYNIQCsI?feature=shared (ይህ መረጃ የተላከው በአሁን ሰዓት ኮለኔሉ በሚመራው ጦር ስር ከሚገኙ አባላት ነው።)
Show all...
የኮሎኔሉ ጓደኛ ያጋለጠው ሚስጥር!የመራዊ እውነታ በሚል ሀሰተኛ ዶክመንተሪ ያሰራው ኮሎኔል ታወቀ!የአገዛዙ ወታደሮች ወልድያ ከተማ ላይ  የፈፀሙት ግፍ

#Amharanewsservice #የአማራዜናአገልግሎት #gobeze_sisay #thevoiceofamhara #amhara #fanopinions #ethiopia

👍 8 2