en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Daily thought

Daily thought

Open in Telegram
588
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
አስደሳች ዜና ለመላው ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በሙሉ!!!🤗 ከቤት ሆነው 🏡፣ በUSD ያግኙ፣ * በሶፍትዌር እና ቴክኖሎጂ * በግራፊክስ ዲዛይን * በኮንተንት ራይቲንግ እና ሌሎችም - ይስሩ፣ ይሄን
አስደሳች ዜና ለመላው ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በሙሉ!!!🤗 ከቤት ሆነው 🏡፣ በUSD ያግኙ፣ * በሶፍትዌር እና ቴክኖሎጂ * በግራፊክስ ዲዛይን * በኮንተንት ራይቲንግ እና ሌሎችም - ይስሩ፣ ይሄንን እድል ይጠቀሙ! 💻 💰💵💸 #freelancelife💥 ጉዞውን ዛሬውኑ ከእኛ ጋር ይጀምሩ። www.CDIWork.com ✨✨ ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/CDIHub

እስከዛሬ ካየዋቸው airdrop 100% እርግጠኛ ሁኜ የሰራችሁትን ብር ወዲያው ይከፍላል ብዬ ምለው Preton air drop ነው 🔥🔥 ከዚ በተጨማሪም እራሱን የቻለ Meme token ነው ያ ማለት
እስከዛሬ ካየዋቸው airdrop 100% እርግጠኛ ሁኜ የሰራችሁትን ብር ወዲያው ይከፍላል ብዬ ምለው Preton air drop ነው 🔥🔥 ከዚ በተጨማሪም እራሱን የቻለ Meme token ነው ያ ማለት list day አለው  ከጀመረ ስለቆየ ከዚ በኋላ ሊስት ለመሆን ብዙ ጊዜ አይቀረውም የምሰሩት ሰዎችን invite በማረግ ብቻ ነው 1 ሰው invite ስታረጉ 50 Preton እና 0.003TON ይሰጣቹሃል ቶኑን ከ 0.5 ጀምሮ ወዲያው withdraw ማረግ ትችላላች በቀን እስከ 8$ድረስ  ትሰራላችሁ withdraw ለማረግ ምንም አይነት fee አይጠይቅም የሰራችሁት Preton ደሞ ተጠራቅሞ list ሲሆን ወደ TON ተቀይሮ በአሪፉ ይከፍላችኋል:: መጀመር የምትፈልጉ ፈጥናችሁ ጀምሩ 100% ህጋዊ 👇👇 https://t.me/preton_drop_bot?start=2b7f73a1-e86a-47d1-8c55-8cb8abd84c59

🦋°•Living alone is better than enjoying with fake people.° °Butterfly🦋°
🦋°•Living alone is better than enjoying with fake people.°                                    °Butterfly🦋°

It's so painful to love someone who doesn't love you. lim posting for you guys, mine loves me.😂💀 𝘔🚀𝘰𝘯 𝘵𝘩𝘰𝘶𝘨𝘩

You are what surrounds you: people, work, hobbies, books 😇 Start changing yourself now with the channel recommended by psychologists - Buzz 💬 Quotes

«Mayber true happiness is when we are happy with ourselves,. 𝑚𝑜𝑜𝑛𝑙𝑖𝑔ℎ𝑡
«Mayber true happiness is when we are happy with ourselves,. 𝑚𝑜𝑜𝑛𝑙𝑖𝑔ℎ𝑡

Nothing brings neighbors together like a few cops car in front of another neighbor's house that no one likes. #Fun 𝐌𝐲 𝐅𝐞𝐞𝐥𝐢𝐧𝐠𝐬 ☂️

It is what it is If you cannot accept the situation as it is, know that this is the root of your suffering. Learn to come to terms with what you cannot change. This way you won’t waste your energy on pointless mental anguish and will be able to think clearly. Also, amazing fact: once you let go, truly and completely, everything will get better. Daily thought

Listen to yourself Always do what you want, even if sometimes it seems pointless, even if you are afraid of judgment or ridicule from others. Your heart knows best what you need. Listen to him. Infinity ∞ Thoughts✅️

Don't be afraid to be simple The world has enough important ones. They are unhappy. Every day they need to fight for the artificial throne. Stay simple. This is the key to a happy life. Daily 💎Thoughts

ገላሽ ቢያብረቀርቅ እንደአልማዝ ቢያበራ ሰሳኙን ነው እንጂ ሌላውን አይጠራ ጊዜ የለገሰሽ ይሄ የውበት ጎርፍ መልሶ ሲነጥቅሽ አንዱን'ኳን አይተርፍ ለተራው አድናቆት ለተራው ሙገሳ ጨርቅሽን ብትገልጭ ከ
ገላሽ ቢያብረቀርቅ እንደአልማዝ ቢያበራ ሰሳኙን ነው እንጂ ሌላውን አይጠራ ጊዜ የለገሰሽ ይሄ የውበት ጎርፍ መልሶ ሲነጥቅሽ አንዱን'ኳን አይተርፍ ለተራው አድናቆት ለተራው ሙገሳ ጨርቅሽን ብትገልጭ ከገላሽ ቢነሳ በዓይንና ሀሳቡ ስንቱ ተሳሳተ በለስ የቀናውም በተግባር ዘሞተ መላ አካልሽን ሁሉም ጎብኝቶታል እፍረት ጭንሽ ሳይቀር በአደባባይ ታይቷል ምን ይሆን ጥቅሙ መገለብ ያሰኘሽ ጉዳቱን አስተዋልሽ ወይ ደሞ ጠቀመሽ? እንዲ ያደረገሽ የባዕዱ መንፈስ ነፍስን ከእሳት ነው መጨረሻ 'ሚያደርስ ተሸፈኚ ይልሻል በህጉ ፈጣሪ ተመለሽ ከስህተት አምላክሽን ፍሪ ከእግዜር ተቃራኒ ቆመሽ አትገኚ ውብ መሆን ካሻሽ ይልቅ ተሸፈኚ ተፈጥሮሽን ይዘሽ ክብርቷን ሴት ሁኚ ✍️የተክልዬዋ

ኪራላይሶን🙏 .............................................ሴናዬ✍️           ኪራላይሶን ሞታቸው ባንተ ተገምሶን             ኪራላይሶን      ገደሉክ ከነርሱም ብሶን   ብሶ.. ያንተ ደም ለመዳን ደርሶ ስለ ዓለም በዓለም ክብርህ ተጥሶ ደምህ ፈሶ ስጋህ ፈርሶ            ኪራላይሶን ክቡር ደምህ ለእርኩስ ነፍሴ አልበቃትም ጨርሶን         ኪራላይሶን ለኔ.. የእናትህ እምባ ፈሶ ባንተ.. የገነት በር ተጥሶ           ኪራላይሶን ዛሬም አለው ደሜ በሀጢያት ረክሶን       ምነው አባቴ ስለኔ የምትሞት       አይገባኝም ያንተ ሞት እውነት ምነው ክርስቶስ ዝቅ አልክ ለኔ    እያጎረስከኝ ነከስኩህ እኔ        ስሞ እየሸኘ ይሁዳስ ሸጠህ        ሞተህለትም ድጋሚ ገደለህ እውነት ከኔ እኮ የሱ ምን ጣመ እኔ ሳስመስል እሱ እየሳመ      ኪራላይሶን ሞታችን ባንተ ተገምሶን             ኪራላይሶን      ገደልንክ ከእኛም ብሶን             የሴቷ ልጅ

እየሱስ ግን... ከህመማት ጸሎት ከብሉይ ኪዳኑ ክርስቶስ ሳይወለድ ሞቱ መወጠኑ ተጨንቃ ይቺ ምድር በትዕቢት ጅረት እነ ጎልያድ ተራ በተራ ተፈራርቀዉባት ብዙ ሺህ ዘመናት አዳም ከገነት መባረሩን ጠያቂ ጠፍቶ የዕዳ ደብዳቤውን ጨለማዉ ዘመን ላይ በቃየል      አምሳያ የወሰደዉን የአቤል ነፍስ እንደ አሻዉ ሲሆን አርዮስ ወይንም ዲያብሎስ ተጣፍቶ መልካም ሁሉ በሀጥያት ምድር ላይ ተስፋፍቶ የክርስቶስ ጠላት    ማይሻር ሁኖ ቃሉ ግርግም ተወልዶ እስኪ ሰቀል ከመስቀሉ ይቺ ምድር ተተራምሳ በክፉዎች ታ'ምሳ ግን ግን እየሱስ ቀድሞ አኑሮን ከገነት ህጉም ሁኖ ፍቅር አዳምን    ቢለዉ ያቺን ፍሬ አትብላት በልቶ ሲወረወር ዳግም ክርስቶስ      ሆዱ ራርቶ መልስሃለዉ አለዉ ነፍሱኑ ሰዉቶ ግን ግን ክርስቶስ!!? የማርያም ልጅ የዮሴፍ አደራ የአለሙ መሪ የመንፈስ ቅዱስ ስራ ቀድሞዉኑ...በረት መወለዱን እጅግ ቢደንቀንም ሰዉ ሁኖ ተፈጥሮ የኛን ባህሪ መያዙንም ምድር ላይ ተመላልሶ   ሲያስተምር ወልድን ሁኖ ሰዉ ግን ያስባል ጥርሱን ነክሶበት       ሊሰቅለዉ ጨክኖ እዉር ስላበራ ሽባ ሙርኩዝ ሲያስጥል ተማከርንበት እሱን ከመስቀል ልንሰቅል እኛ እኮ ነን ቅድስቷን ቤተክርስቲያን ነገድ አርገን ሸቀጥ ካህን ሁነን ለጠላት አሳልፈን ምንሰጥ እኛ እኮ ነን.. ተማክረን ዕረቡ ሀሙስ ልናሲዘዉ እንደ ይሁዳ ሀነን ስመን የሸኘነዉ እኛ... ሲያዳፉ ሲገርፉት አካሉን ከቆራረጡት አለንበት ከነዛ ጅራፉን ከያዙት ደሞም እኛ አይደለን    እንሞትልሃለን ዝተን ምለን በጠየቁን ጊዜ የካድነዉ      አናቀዉም ብለን እስከ ቀራኒዮ መስቀል ያሸከምነዉ አጣ የጣልንበት ልብሱን የገፈፍነዉ እኛ ነን ዉሃ ጠማኝ ሲል  የሞላት አለሙን በባህር ሀሞት የሰጠነዉ ጎኑን የወጋነዉ ሁነን የሱ ፍጡር እኛ .... እንደዛ ወንበዴ የሰዉ ነፍስ የሚገድል መስቀል ላይ እንኳን ሁኖ ''እስኪ ራስህን አድን '' የም'ንል እኛ ማርያምን ያስነባን ፣ እናቱን በአይንዋ ያሳየናት ሞቱን እኛ ወንበዴ? ነፍሰ በላ?! ለክፋታችን ቃልም አይገኝም እንደኛ በደልስ ዝማዊ ሀጥያተኛ አይባልም እግዚኦ...ለኛ ማርያም እኮ ስታለቅስ እንባዋን ስታፈስ ልጇን ሰቅለንባት ሀዘን አንጀቷን ሲበጥስ የማርያም ዕንባ እንኳን እንደዛ ፈሶ ምልጃዋ እንኳን ምድርን   ለምለም ያደርጋል አ'ርሶ ማን ያዉቃል ..? ማርያም ..እኮ ያዘነችዉ ምክኒያቱ ቢሆንም ልጇን መስቀል ላይ ስላየችዉ ከቶ ግን ልቧን እጅግ የሰበረዉ ስላየች ፍጡር ፈጣሪዉን መስቀል ላይ ሲሰቅለዉ እግዚኦ...አቤት ያንተ ቸርነትህ መስቀል ላይ ሁነህ ማራቸዉ ማለትህ ጎንህን ወግተዉ በችንካር ሲቸነክሩ ጨለማ ና ብረሃን ሰዓት ሲቀያየሩ አቤቱ ..ማረን ስለ ማርያም ስለ አባቷ ካህኑ እያቄም ህማሙን ባናነባ ባናስብ ስለ እርሱ ምን አለ ቢሰማን የእናቱ እንባዋ መፍሰሱ አዲስ ኪዳኑን ነዉ የታወጀልንን የዕዳ ደብዳቤያችን የተቀደድልንን ገነት መዉረሳችን ተሰዉቶ           የፋሲካችን በግ እንዴት እንሆን ይሆን    ይሄ ሁሉ ለኛ ባይደረግ አቤት ..ምህረትህ🙏!!!። 🙏🙏 ✝️🙏 ✍️ገጣሚ ዳዊት

በሀሰት ሸንጎ ፣ ቢያቆሙት ለፍርድ አልተረዱት ኖሮ  ፣ የእርሱን' የሰው መውደድ አላወቁም እና ፣ የሱን የእውነት መንገድ ይመክሩበት ጀመር ፣ መቃብር እንዲወርድ።                           አቆሙት ከጲላጦስ ፣ በወታደር አስከብበው ያልፈፀማቸውን ፣ ሀጥያቶች ሸልመው። እሱ ግን ትንቢቱ እንዲፈፀም ፣ ቃል ካፉ አልወጣም "አላረኩም!" ብሎም ፣ አልተከራከረም። ጲላጦስም...... ከካህናቱ ጫጫታ ፣ በልጦበት ዝምታው አላቸው.... "ልግረፍ እና ልፍታው" ግን ሞቱን ወደው ነበር ፣ ሁለቱ ካህናት ህዝቡም አገዛቸው ፣ እያሉ "ስቀሉት" ጌታም...... ከሁሉ አስቀድሞ ፣ ያውቅ ነበርና ውስጡን አዘጋጀ ፣ ለፅኑ ፈተና። ጲላጦስ.... እጁን ታጠበና ፣ ዞሮ ወደ ህዝቡ "ከደሙ ንፁህ ነኝ ፣ ለራሳችሁ አስቡ " አለ። እነሱም አሉ... "በኛ እና በልጆቻችን ፣ ይሁን " ለፍርጃቸውም ፣ ተወው ጌታን ። አይሁድም... እስከ ቀራንዮ ፣ አሸክመው መስቀል በደከመው ጊዜም ፣ ከመሬት  ሲንጋለል ምንም ሳይራሩለት ፣ አየገፈተሩት ቀራንዮ ተራራ ፣ ላይ አደረሱት። መስቀልም ላይ ፣ አስተኙት ሚስማሮቻቸውንም ፣ በእጁ  ቸነከሩት በርሱ ህመም ጊዜም ፣ ቆመው ተሳለቁበት የእሾህ አክሊልም ፣ በጫንቃው ጫኑበት በገመድም ይዘው ፣ መስቀሉን አቆሙት። ቃሉ እንዲፈፀም ፣ የተነገረው ትንቢት በቀሚሱም ላይ ፣ እጣ ተጣጣሉበት ። ምድርም ተቆጣች ፣ ተሰቅሎ አምላኳ ፀሀይም ጨለመች ፣ በአይሁድ በመታወኳ። ህዝቡም ተደናግጦ ፣ ፍፁም ተረበሸ ከቀኑ በቀትር ፣ ሰማይ ስለመሸ።                                        በሶስተኛውም ቀን ፣ በዕለተ ሰንበት ሊያዩት ፈልገው ፣ ወደ ቀበሩበት ገስግሰው ሲደርሱ ፣ መግቢያው ክፍት ሆኗል ወደውስጥ ሲገቡም ፣ ክርስቶስ ተነስቷል። ∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞ ነግሯቸው ነበረ ፣ አስቀድሞ ከስቅለቱ እርግጥ እንደሆነ ፣ የእርሱ መሞቱ                   ግን ልክ እንደ ዮናስ ፣ ለሶስት ቀን ይተኛል በሶስተኛው ቀንም ፣ ትንሳኤው ይሆናል ።

#እንዴት?... ይረሳኛል . . ከቤተመቅደሱ ማለዳ ተገኝተን ቆመን ለቅዳሴ፣ እዉነተኛ መስዋዕት ለአምላክ ስናቀርብ ክብርና ዉዳሴ፣ በሕማማት ሰሞን እንሞት እንደሆን ፍትሐት ስንፈታ፣ ከያዙት ዘንባባ ጥ
#እንዴት?... ይረሳኛል . . ከቤተመቅደሱ ማለዳ ተገኝተን ቆመን ለቅዳሴ፣ እዉነተኛ መስዋዕት ለአምላክ ስናቀርብ ክብርና ዉዳሴ፣ በሕማማት ሰሞን እንሞት እንደሆን ፍትሐት ስንፈታ፣ ከያዙት ዘንባባ ጥቂት ዝንጣፊ ሲሰጡን የኔታ፣ በጣቴ ለክተሺ  ፈጥነሺ ስታበጃጂ ያማረ ቀለበት፣ ኪዳን እንዲሆነን ከእጄ ልታጠልቂው በዚህ ቅዱስ ሰንበት። ትክ ብዬ ሳይሽ..... አይንሽን ስራሽ ላይ ነው፣ ልብሽ ሀሳቤ ላይ ነው። እንዴት ይረሳኛል...... #በሆሳዕና እለት ከእጄ ያገባሽው ዉቡ ቀለበቴ፣ ላይወልቅ ተሰፍቷል ተለይቶ አያዉቅም ከአራተኛው ጣቴ፣ ዛሬም እንደትናንት በአዝማናት ንጉደት ፈፅሞ አላረጀም፣ መዓዛሽ ሳይጠፋ እንደለጋነቱ ካይኔ አልተሰወረም። የልጅነቴ ማህተም አይበጠስ ክሩ፣ የፈገግታዬ ልክ አይለካም ስፍሩ። ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ #ገጣሚ_ኤደን ...✍

የአምላክን ትዛዝ ልቤ እሺ ቢልም ካንቺ ጋር የሆንኩት ሀጥያት አይባልም

ወሬ ወሬ... ባልተፈፀመ ቃል ባልዋለ ንግግር ዋሽተህ አሳምነህ  አጋነህ በማቅረብ እንጀራህን ጋግር ብለን ያፀደቅነው ህግ አለን ወረኞች እድሜ ለአማኞች... ይሄን ዘመን የሚገልጽ አሪፍ ግጥም 👏👏👏👏 ሙሉውን አድምጡት 🗣

#ሰው_አብዷል በልቡ ማህፀን ደም እየፈሰሰ፣ አካሉ ጎስቁሎ ደስታን እያሰሰ፣ የስቃዪን ህመም ከቶ እንዳልቀመሰ፣ በውሸት አንደበት ነብሱን አቆሸ፣ ደስተኛ ነኝ ብሎም እራሱን ዋሸ። #ገጣሚ_ሄኖክ_ፀጋዬ
#ሰው_አብዷል በልቡ ማህፀን ደም እየፈሰሰ፣ አካሉ ጎስቁሎ ደስታን እያሰሰ፣ የስቃዪን ህመም ከቶ እንዳልቀመሰ፣ በውሸት አንደበት ነብሱን አቆሸ፣ ደስተኛ ነኝ ብሎም እራሱን ዋሸ። #ገጣሚ_ሄኖክ_ፀጋዬ  

ይሄን ግጥም ስሰሙ አስተሳሰባችሁን ትታዘቡታላችሁ☺️😁 ይንፉሽ ይነፋፉሽ ገራሚ ግጥም ተጋበዙልኝ😁😁

እንዴት ነሽ ጨረቃ፣ ኤኔ እንዳለው አለው ዛሬስ ጠፋሽብኝ ፣ ምንስ አጋጥሞሽ ነው የ ሆዴን ላወራሽ ፣ ምናል ቶሎ ቢመሽ ቀኑን ገፋውትኝ ፣ ጓጓው እስከሚመሽ ታውቂያለሽ ጨረቃ የሆዴን ሳወራሽ ፣ ይልልኛል ቀለል በምሽት ጠፍተሽ  ፣ አለው ስንቀዋለል የመጣሽ ጊዜና ፣ አለው ከዛች ቦታ ቀኑንስ ገፋሁት ፣ ያላንቺ ግን ይከብደኛል ማታ ቶሎ ብቅ በይ ፣ እምነግርሽ አለኝ ያ የነገርኩሽ ልቤ ፣ በሰው ታለለብኝ ብቻዬን ቀረውኝ ፣ ተጓዳብኝ ልቤ አልወጣ አለቺኝ ፣ ከዚህ ሞኝ ሀሳቤ : : : ነይልኝ ጨረቃ ፣ አለኝ እማወጋሽ ቆየሽብኝ ምነው፣ አንቺም እንደሷ ሆንሽ