cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኔ ግጥም

Join my channel & enjoy poems ✍️✍️✍️

Show more
Advertising posts
648
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

00:51
Video unavailableShow in Telegram
ስማ ስማ... @astawesegnregasa @astawesegnregasa ❤️
Show all...
7.50 MB
👍 3 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሽሽሽሽ የልብ ቃል መገለጫው ከወደዱ ዝምታ ነው ኮዱ። ✍️N.D. @Myppoem
Show all...
😱 2👌 2
አርፋጅ በቃሽኝ ስትለኝ በቅተኸኝ ነበረ ልቤ ሰነባብቶ አንተን ከቀበረ ሄጃለሁኝ ስትል እኔም አልነበርኩኝ ደጅህን አልጠናው አትሂድ አላልኩኝ ይልቅ ላትመለስ ጓዝህን ጠቅልለው አረፋፍደህ መሄድ መቼም አመልህ ነው። ✍️ህይወት ቢራራ @Myppoem @Myppoem @Myppoem
Show all...
👏 2
ክፍል 1 ውቧ ልዕልት ዲያና ከእንግሊዝ ንግስት ኤልሳቤት II እና ከግሪኩ ልዑል ፊሊፕ የተወለደው ልዑል ቻርልስ የ32 አመት ወጣት ሳለ ነበር ውቧንና የ19 አመቷን የመዋዕለ ህፃናት አስተማሪ የነበረችውን ዲያናን ማግባት እንደሚፈልግ ለንጉሳዊያን ቤተሰቦቹ ያበሰረው።በወቅቱ ሁሉም ደስተኛ ነበሩ።ምክንያቱ ደግሞ የዲያና አባት ለንጉሳዊያን ቤተሰብ ጌደኛ መሆኑና ዲያና እጅግ ውብ ሴት በመሆኗ ነበር። የዲያናን ሰርግም ልዩ ለማረግ ሽርጉዱ ተጀመረ።በእለቱ እንድትለብሰው የተዘጋጀላት የሙሽራ ልብስ አለም ባደነቃቸው ታዋቂ ልብስ ሰፊዎች በዴቪድና ኤልሳቤት ነበር።የልዑሉና የልዕልቷ ጋብቻ በ July 28/1981 የተፈፀመ ሲሆን 750 million ህዝብ በቴሌቪዥን ተከታትሎታል።ከጋብቻው በኋላ ዲያና የዌልሷ ልዕልት በመባል መጠራት ጀመረች።ከጥቂት ጊዜያት በኋላም ዊሊያምና ሀሪ የተባሉ ወነድ ልጆች ወለዱ። ታይም የተሰኘው አለም አቀፍ መፅሄት <<በአለም ላይ ብዙ ፎቶግራፎችን የተነሳች ሴት>>ሲል የልዕልቷን ታዋቂነት መስክሯል። ቻርልስና ዲያና ከተጋቡ ከ 11 አመት በኋላ ሁሉም ተለዋወጠ።በሁለቱ መሀል የተፈጠረው አለመግባባት ገንፍሎ ጋዜጠኞች ጆሮ ደረሰ።ከውጪ ለሚመለከተው ዉዋስቀና የነበረው የሁለቱ ልዑላን ፍቅር እንዳልነበር ሆነ።ዲያና በበኩሏ የጥላችን መንስኤ ቻርልስ ነው ብትልም ቻርልስም ጣቱን ወደሷ መጠቆሙ አልቀረም።የሆነው ሆኖ ጋብቻቸው በ11 አመቱ በፍቺ ተጠናቀቀ። በፍቺውም 1780 ፓውንድ የሚፈጁት 14 አውሮፕላኖች እና 32 የሮያል ወታደራዊ አውሮፕላኖች ለዌልሷ ልዕልት ዲያና ለግል ጉዳይዋ መገልገያ እንዲሆኑ ተፈቀደላት።በተጨማሪም ሊሰጣት የተዘጋጀው 17 million ፓውንድ ለፍቺ የተከፈለ ተወዳዳሪ የማይገኝለት የገንዘብ መጠን ተብሏል።
Show all...
👍 2
ክፍል 2 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ልዕልት ዲያና አለም ላይ አለ የተባለውን የግብፅ ከበርቴ መሀመድ አልፋይድ ልጅ ዶዲ አልፋይድ ጋር ፍቅር ጀመረች።ከብዙ ታዋቂ ሴቶች ጋር ግንኙነት የነበረው ዶዲ ሌሎቹን እርግፍ አርጎ በመተው ከልዕልቷ ጋር ሆነ።አባቱም በደስታ ተቀበላቸው።ብዙ ጋዜጦችና መፅሔቶች ምርጥ ጥምረት ሲሉ አሞካሿቸው።ይሁንና ፍቅራቸውን በግልፅ ይፋ አላደረጉም ነበር።የዶዲ አባት መሀመድ አልፋይድ ድብቁን ፍቅር ይፋ ለማውጣትና የልጁን እና የልዕልት ዲያናን የቀለበት ስነስርዓት ለህዝቡ ይፋ ለማረግ ዝግጅቱን በጨረሰበት ዋዜማ ሁሉም ተቀየረ። ዶዲ አልፋይድና ልዕልት ዲያና አስከ እኩለ ሌሊት ድረስ paris ውስጥ በሚገኘው የመሀመድ አልፋይድ ቅንጡ ሆቴል ውስጥ ሲዝናኑ አምሽተው ወደ ቤታቸው ለመሄድ ተነሱ።በተዘጋጀላቸው ማርቼዲስ መኪና ውስት ገብተው መንገድ ጀመሩ።መኪናዋ 6:24 ላይ በከፍተኛ ፍጥነት ውስጥ ሆና ስትበር ቆይታ ተጋጨች።የዲያና ፍቅራኛ የነበረው ዶዲ እና ሹፌሩ ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ ዲያና እያጣጣረች ነበር። ልዕልት ዲያና በርህራሄዋና በበጎ አድራጎቷ የህዝብን ልብ ውስጥ የቀረች ልዕልት ነበረች።እንደንጉሳዊያን ቤተሰብ ሳትኮራና ሳትጠየፍ ከጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር ሳይቀር ወርዳ ፍቅር ስትሰጥና ስትረዳቸው ኖራለች።ያ ሁሉ ፍቅርና ክብር ዲያናን ከሞት ሳያስቀራት ቀረ።በ36 አመቷ ህይወቷ አለፈ። ከሞቷ በኋላ እስከ ዛሬ መልስ ያለገኙ ጥያቄዎች አሉ።በወቅቱ ዲያና ነፍሰ-ጡር ነበረች ተብሏል።እሷን ከአደጋው ቦታ አንስቶ ሆስፒታል ለመውሰድ 1:40 ደቂቃ የፈጀበት ምክንያት እንቆቅልሽ ሆኖ ቀርቷል።ሲከታተላቸው የነበረው ነጭ ፊያት መኪና በቅፅበት መኪና መሰባበሪያ ውስጥ ገብቶ ወደ ቁርጥራጭ ብረትነት የተቀየረው በ1 ደቂቃ ውስጥ ብቻ ነበር።በወቅቱ ሹፌራቸው አይኑን በጨረር ተመቶ እንደነበርም ተነግሯል።የመንገድ ላይ ካሜራዎች ቅጂ ተደምስሷል።ሲከታተሏቸው የነበሩ ጋዜጠኞች ፎቶዋቸውንም ሆነ ምንም መረጃ አላወጡም።ለምን???? የዶዲ አባት መሀመድ አልፋይድ በበኩሉ ለልጁና ለልጁ የተቀነባበረ ሞት ተጠያቂ ያረጉት ሞሳድን ነው። JOIN &SHARE 🙏 @Myppoem @Myppoem @Myppoem
Show all...
ሿ ሳይል ሰማዩ ከመዝነቡ በፊት አቁሜ ደመና ከሙሴ ተማፅኖ ከፀሎቱ ቀድሞ እግዜር እንዳሰበው የእስራኤል መነ ባላሰብሽው ዕድሜ ሳትመጪ እያሰብኩሽ አህዛብ ያውቃሉ ልትመጪ እንደሆነ ከመምጫሽ ቦታ ላይ እኔ እንደቀደምኩሽ ከጎጆሽ እንዳለሽ ከሞላለት ታዛ እግርሽ ሳይነሳ እኔ አለሁኝ ከዛ። ከዛ.... ከዛስ? ከዛማ... ወደ ፍቅር ማማ ወደ ናፍቆት ጻማ ሰማይ ያህል ህይወት በምድር ቃል ማሰስ በሚያዩት መታወር ለማን ነው ሚከሰስ? ሳልጽፍ የማነብሽ ሳልኖር የማስብሽ ባለሽበት ያለሁ መኖር ንሴብሆ በኖርሽበት ነበርኹ አለሁኝ እነሆ። በቀን ያልተነካ በቀን ያልተለካ ከቀን በቀደመ ከቀን በፈጠነ በቤተ መቅደሱ መከረኛው ልቤ አንቺን እያጠነ አንቺን ተማጠነ። የማፍቀር ድግምቴ ነፍሴ ቢያጠናልሽ አንቺዬ... ከደጅ የምጠናሽ ደጅ የምጠናልሽ አንቺን እንድትሰጪኝ አንቺኑ ምለምን ቆሜ ተንበርክኬም ተቸገርኩ አለሜ... ኹለት ሆነሽብኝ ፀሎቴም አምላኬም። ✍ኤልያስ ሽታሁን @Myppoem @Myppoem @Myppoem
Show all...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
አቀፈኝ አቀፍኩት ዋሸ ዋሸሁት አማኝ አማሁት በወደደኝ ልክ ወደድኩት ሲቀርበኝ ቀርቤ ሲርቅ እየራቅኩት ፍቅራችን ውድድር ሲሻ አሸናፊ እየነፈኩት አለን እኩል ሆነን === እኩል ስቃይ ተቀብለን። ✍N.D. @Myppoem @Myppoem @Myppoem
Show all...
👍 3 1
Photo unavailableShow in Telegram
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
Show all...
👏 3
ነግጄም አየሁት አርሼም አየሁት አልሰመረም ሀብቴ አልቅሼ በላለው ፥እንደ ልጅነቴ @tekelklunjoin @tekelklunjoin @tekelklunjoin ❤️
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.