cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

💝ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ለዘላለም ትንገስ 🙏 ✝️...ክርስቶስ ነው ህይወቴ..! ✝️...ማርያም ናት እናቴ..! ✝️...መስቀል ነው ጉልበቴ..! ✝️...ተዋህዶ ናት እምነቴ..!😍 የዚህ ግሩፕ አላማ 👇 የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርት እንዲሁም መዝሙር የሚለቀቅበታ ቻናል ነዉ 💒 ኦረቶዶክስ ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር አሜን ፫🙏

Show more
Advertising posts
793
Subscribers
No data24 hours
+37 days
+16930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ከቅዱሳን_ባሕታውያ_ጋር በአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡-ከዕለታት አንድ ቀን በሀገረ ስብከቴ ሥር በነበሩ በሜዲትራኒያን ባሕር በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ምእመናንን  ለመጎብኘት አሰብሁ፡፡ ከእኔ ጋር ቀሳውስትንና ዲያቆናትን አስከትዬ በጀልባ ተሳፍሬ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዝሁ፡፡ በደሴቱ ውስጥ ስንዘዋወር የሰው ዱካ ብንመለከትም  ምንም ሰው ማየት አልቻልንም ነበር፡፡ በአሸዋው ላይ ታትሞ የነበረውን የሰው ዱካ ተከትለን ስንጓዝ ካልተፈለፈሉ ዐለቶች የተሠራ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ዋሻ ላይ ደረስን፡፡ ዋሻው በርም ሆነ መስኮት የለውም፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ ልክ እንደ ሰባቱ ደማቅ ከዋክብት እጅግ በጣም አንጸባራቂ ብርሃን ቆመው ከሚጸልዩ ሰባት አባቶች ዘንድ ሲወጣ ተመለከትን፡፡ እኛም ከእነርሱ ጋር ለመጸለይ ባለንበት ቆምን። አባቶች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ እኛ ዞሩና በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ። በመቀጠልም ሰላምታ ሰጡን፡፡ እኔ ዮሐንስም ‘እኔ አባታችሁና ፓትርያርካችሁ ዮሐንስ ነኝ’ አልኳቸው፡፡ ቅዱሳኑ እንደገና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በፊቴ ሰገዱ እና እኔን ደካማውን እንዲህ አሉኝ፡- “የምንወደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትባርከንና እኛም አንተን በማየት እንድንበረታ ወደዚህ አመጣህ” አሉ። እኔም “እባካችሁ ታሪካችሁን ንገሩኝ” አልኋቸው፡፡ ሰባቱ አባቶችም “ከብዙ ዓመታት በፊት ሰባታችንም ከቍስጥንጥንያ ወጥተን በአንድነት ተሰባስበን ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና በአምልኮ ብቻ ለማሳለፍ ወደዚህ ደሴት መጣን፡፡ ከዚህ ደሴት በደረስንበት ዕለት ከባሕሩ ከሚመጣው አስቸጋሪ ነፋስ ራሳችንን ለመከላከል ዋሻዎችን ለመገንባት ዐለቶችን ሰበሰብን፤ በሁለተኛው ቀን ደግሞ ይህን ቤተ ክርስቲያን መሥራት ጀመርን፡፡  በዐለቶች መካከል ከሚበቅለው ሣር እንበላለን፤ ውኃም ከባሕሩ እንጠጣለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን የከበቡትን እነዚህን የአሸዋ ክምሮች ለማስወገድ ፈልገን ነበር፤ ግን አእምሯችንና አሳባችን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስለተያዘ ጊዜ አጣን” በማለት ታሪካቸውን ነገሩኝ። እኔም “መንፈሳዊ አባታችሁ የት ነው?” ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ ይህን ጥያቄ ከመጠየቄ ወዲያውኑ አንድ ሽማግሌ በትሩን ተደግፎ ወደ እኔ ቀረብ አለና “እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ” አለኝ፡፡ አረጋዊው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ራቁቱን ነበረና “ሰውነትህን የምትሸፍንበት ትንሽ ልብስ ትፈልጋለህ?” ስለው እሱም “ጌታ ከክረምቱ ቅዝቃዜ፣ ከበጋው ሙቀት ይከላከልልናል፤ ይጠብቀናልም” በማለት መለሰልኝ፡፡ “ምግብ ያስፈልጋችኋል?” ብዬ ስጠይቀው እርሱም “የሚበቃንን ያህል ከእነዚህ ዕፅዋት እንመገባለን ከዓለም የሆነ ምንም ነገር አያስፈልገንም” በማለት መለሰልኝ፡፡ እኔም “አባቶቼ እባካችሁ ለእኔ እና ስለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ጸልዩ” አልሁት። የእነዚያን ቅዱሳን ባሕታውያን አባቶች በረከት ከተቀበልን በኋላ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም ምሥጋና የሚገባውን የምንወደውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ወደ መጣንበት ተመለስን” ይለናል ቅዱሱ አባታችን ዮሐንስ አፈ ወርቅ። ምንጭ፦ ግሑሣን አበው
Show all...
"ሚካኤል ስዩም " ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ሚካኤል ስዩም /3/ሊቀ መላእክት መዝገበ ርራሄ/3/ወየዋህ የደሀ አደጉን ልጅ ስለተቀበልከኝ በአውደ ምህረትህ በፍቅር አሳደከኝ ከመቅደስ ተክለህ መገብከኝ ህይወት አዘጋጅተኸኛል ለሰማይ መንግስትህ አዝ ...... በከንቱ እንዳልደክም ነብሴ እንዳትዝል ትመግበኝ ነበር የህወትን ቃል ወጣሁኝ ከአለም ተሰሎንቄን ረሣሁ መጠማቴ ቀረ የህይወት ውሀ ጠጣሁ አዝ ......... መዳንን እንድወርስ ሞትን እንዳላይ ትረዳኝ ነበረ ከኔ ሣትለይ በመንገዴ ሁሉ ከፊቴ ቀደምክ አማኑኤል ብዬ ጌታን እንዳመልክ አዝ ........ ምልጃህን ታምኜ ስኖር በመቅደስህ ታሻግረኝ ነበር እጆቼን ይዘህ በጎልማሣ ነቴ ነህና ከጎኔ ጉልበቴም አንተው ነህ በእርጅና ዘመኔ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09
Show all...
#ግንቦት_12 #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ባሕረ ምስጢራት የሆነ የሰውን ፊት አይቶ የማያደላ "መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ" (በርሱ ዘንድ ንጉሥ፣ ሐብታም፣ ደሃ፣ ነዳይ እኩል ነውና)፣ አፈ በረከት፣ አፈ መዐር (ማር)፣ አፈ ሶከር (ስኳር)፣ አፈ አፈው (ሽቱ)፣ ልሳነ ወርቅ፣ የዓለም ሁሉ መምሕር፣ ርዕሰ ሊቃውንት፣ ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)፣ የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)፣ ጥዑመ ቃል... እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እረፍቱ ነው። ምልጃውና የከበረች ጸሎቱ ከእኛ ጋር ትሁን!
Show all...
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እና ሕይወቱ - @sol-zenamewael #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ

በእኔ ቢጠቁር ሰማይ በእኔ ቢጠቁርም ሰማይ በእኔ ቢጠልቅም ፀሐይ በነፋሳት የማይጠፋ ፋኖሴ ኢየሱስ ነው የመኖር እስትንፋሴ እርሱን ታምኜ እወጣለሁ እርሱን ታምኜ እገባለሁ ድብቅ ሰራዊት አለው ለእኔ የሚጠብቀኝ በዘመኔ እግዚአብሔር ለእኔ ብርሃኔ ነው የሚያስደነግጠኝ የሚያስፈራኝ ማነው ሰው አልባ ሁኜ በስደት ወዳጄ የሆነኝ የእኔ አባት ክርስቶስ ለእኔ ሕይወቴ ነው እርሱን ታምኜ እኖራለሁ የለም የሚያስፈራኝ በዘመኔ ብርሃን ነውና እግዚአብሔር ለእኔ መች ይሰጠኛል ለጠላት አይሰለጥንም በእኔ ሞት የሚጠብቀኝ ጌታ ነው የትኛው ጠላት ሊደፍረው በቤቴ መቃን ላይ ደም ይታያል እኔን ከእግዚአብሔር ከቶ ማን ይለያል ይኸው አቆመኝ በመቅደሱ እየጠበቀ በመንፈሱ እኔን ሊያከብር ራሱን ሰጥቶ ግዝቶኛል ጌታ ሞቴን ሙቶ ይገዛ ለስሙ ስጋ መንፈሴ በእርሱ ነውና ለዛሬ መድረሴ በዓለም ሳለሁ የዓለም ብርሃን ነኝ። ዮሐ 9፥5    ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ   👇👇👇👇👇👇👇 👉@Mazemurachne 👈 👉@Mazemurachne 👈 👉@Mazemurachne 👈      👆👆👆👆👆👆👆   👇 #Join_group 👇 https://t.me/mezmurahen
Show all...
ያሬድ ነጎድጓድን ..ከደመናት ተውሶ ዜማን ....ከመላዕክቱ ማዕድ ቆርሶ ብስራትን ...ከገብርኤል ቀንሶ የሚካኤልን ሰይፍ... ተንተርሶ ያሬድ በልሳኑ እያዜመ ...በልቡ እየተቀኘ የድጓውን ባህር ቀዝፎ...በቅኔው ማዕበል እየዋኘ ከላይ....ከመላዕክቱ ነጥቆ ምድርን ..በዜማ ሰንጥቆ በመወድሱ ጎርፍ ...አጥለቅልቆ በዝማሬው ሰረገላ ...አምጥቆ መሬት ላይ አንስቶ...ከሰማይ ያደረሰን ከመላዕክቱ ጋር አቁሙ...ግዕዝና ዕዝል ያዘመረን አራራይ ብሎ በርህራሔ...በዝማሬ ሲቃ ያስለቀሰን ያሬድ ዋይ ዜማ እያለ....ዋይታን አጥፍቶ ዋይታ ልቅሶአችን ቀይሮ...ዋይ ዜማ ዝማሬን ተክቶ እንደ መላእክቱ አርቅቆ እንደ ሰውም አድምቆ ሰማይና መሬት አስተባብሮ ከመላእክቱ ጋር ደምሮ "ሃሌ ሉያ" ብሎ አዘምሮ በዜማ ቁልፉ ከፍቶ...በቅኔው በትር ገልጦ አሳየን ከላይ እግዜርን...ከዜማ ወንበር ላይ አስቀምጦ ያሬድ ኢትዮጵያ ላይ... የቆመ የዜማ ብርሃን ሻማ ጥበብን ያገኘንበት ...የመስፈሪያው አውድማ ይህ ነው ብርሃን የአለሙ...ኢትዮጵያዊ ነው ቀለሙ ከያሬድ በተጨማሪ..."ምድራዊ መልአክ" ነው ስሙ Moges Hunyalew
Show all...
ሰባኬ ወንጌል መጋቤ ሃይማኖት ለቤተ ክርስቲያን ዘይደምፅ ቀርን ነባቤ ለቤተ ክርስቲያን፡፡ ያሬድ ፀሐያ ለኢትዮዽያ ዓምደ ብርሃን ለቤተ ክርስቲያን መልአክ ዘበምድር፡፡                     ትርጉም፡- ቅዱስ ያሬድ ሰባኬ ወንጌል መጋቤ ሃይማኖት ለቤተ ክርስቲያንም የሚመሰክር መለከት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፀሐይ የብርሃንም ምሰሶ በምድር ላይ ያለ መልአክ ነው፡፡
Show all...
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ 4ቱ ቅዱስ ወንጌላውያን አለምን በወንጌላቸው ያጣፈጡ ናቸው ። እኔህ ቅዱሳን ወንጌላውያን የጻፉት ወንጌል ምን ምን ናቸው ?
Show all...
✟የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ✟
✟የቅዱስ ማርቆስ ወንጌል ✟
✟የቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ✟
✟የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ✟
✣ሁሉም መልስ ናቸው ✣
Promotion ለማሰራት
Photo unavailable
ኢትዮጵያ ከመላእክት ጋር የሚዘምር ማሕሌታዊ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሚያጥን ካህን የምታፈራ ሀገር ናት። ለሰማይ አገልጋዮችን ገና ሳይሞቱ የምትልክ፣ ከተዋጊዎች መካከል ወደ ድል ነሺዎች መልእክተኛ የምትልክ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ያለች ናት? ቅዱስ ያሬድ በትሕትናው ከትል ተማረ። ትሑታንን ከፍ የሚያደርግ ፈጣሪም ከፍ አደረገውና ከመላእክት ጋር ዘመረ። ትልዋን ከዛፍ አውርዶ ቢጨፈልቃት ኖሮ ለአንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት ያልነጠፈው የምስጋና ጅረት በሀገራችን ባልፈሰሰ ነበር። ኃይል አለኝ ብለህ የምትጨፈልቃቸው ትሎች ሰማይ የሚያደርሱህ መምህራኖችህ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ ይላል የታሪኩ ተግሣፅ። ቅዱስ ያሬድ እግሩን በጦር እየተወጋ እንኩዋን ዝማሬው ሰማያት ወስዶት አልተሰማውም ነበር። የእኛው ሲላስ የእኛው ጳውሎስ ቅዱስ ያሬድ ሆይ በዘመርክባት ሀገርህ ዛሬ ብዙ ጦር ተሰክቶባታል። ከአንተ ዜማ በቀር ዛሬም መጽናኛ የለንምና በምልጃህ አስበን። ጥዑመ ልሳን ያሬድ: ሊቀ ጠበብት ያሬድ: ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ የቤተ ክርስቲያን ጌጥ!! (Deacon Henok Haile)
Show all...
👍 1
✝ኦርቶዶክሳዊ ቻናል ይፈልጋሉ ❓🌱 🔴ኦርቶዶክሳዊ ስብከቶች 🟠ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች 🟡ኦርቶዶክሳዊ ስንክሳሮች 🟢ኦርቶዶክሳዊ  ግጥሞች 🔵ኦርቶዶክሳዊ  ታሪኮች 🟣ኦርቶዶክሳዊ  ፊልሞች ⚪️ኦርቶዶክሳዊ  ፎቶዎች 🟤ኦርቶዶክሳዊ ምስለ ስዕሎች 🔵የአበው ትምህርቶች እንዴሁም ሌላ ብዙ ነገሮች የሚለቀቅባቸው  ቻናሎችን መርጠዎ ይቀላቀሉ   ። ሊንክ  👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @ኦርቶዶክሳዊ_ቻናል_እና_ግሩፖች ሺር በማረግ ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ🙏 ፍልደር ( ፕሮሞሽን ማሰራት የሚፈልግ  በዚህ ሊንክ ያናግረኝ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @Amen1226
Show all...
Join
ይ🀄️ላ🀄️ሉ
"ከማንም ሰው ጋር ሳልጋጭ የሰላም ሕይወት ለመኖር ብችልና ቢፈቀድልኝ ኖሮ ለእኔ ለግል ሰብእናዬና ጠባዬ በእጅጉ ይሻለኝ ነበር። ነገር ግን አሁን የእግዚአብሔር ከተማ የሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጠላት ተከብባ እያለች ፣ ታላቁ የእምነት አጥርና ቅጥር ዙሪያውን በከበቡት የኑፋቄ የጦር መሣሪያዎች እየተመታ ከመሆኑ የተነሣ እየተነቀነቀና እየተናወጸ እያለ ፣ ከዲያቢሎሳዊ ተንኮላቸውና ጥቃታቸው የተነሣ የእግዚአብሔርን ቃል ለጥፋታቸውና ለኑፋቄያቸው ምርኮኛ ሊያደርጉት ቀላል በማይባል ሥጋት ላይ ጥለውት እያየን ፣ በዚህ ሁኔታ ላይ በዚህ የክርስትና ውጊያ አለመሳተፍና ድርሻን አለመወጣት አስጨናቂና አሳዛኝ ነገር እንደሆነ በማሰብ ወደዚህ ሰልፍ ውስጥ ገብቻለሁ። እያንዳንዱ ሰው ሐዋርያው እንዳለ እንደየድካሙ ዋጋውን እንደሚቀበል ሁሉ ከአቅሙ አንጻር መድከም የነበረበትን ያህል ድካም ያልደከመ ሰው ደግሞ ቅጣት ይጠብቀዋልና።" (ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ - መድሎተ ጽድቅ ገጽ 16 https://t.me/+bOicYz3yMwAxNTdk
Show all...
ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

💒 በስመአም በወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፫ 💒🙏 የዚ ግሩፕ አላማ የተለያዩ በስነ ጹሑፍ መንፈሳዊ ትምህርት እንዲሁም መዝሙር የሚለቀቅበታ ቻናል💒 ኦረቶዶክስ ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር አሜን ፫🙏