SCHOOL OF KAREODE
Open in Telegram
516
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-130 days
Posts Archive
👨🏫👩🏫"መምህርነት የሙያዎች ሁሉ ምንጭ ነው። ስለዚህም የሙያዎች አባት ብለው ይጠሩታል። በየትኛውም ዘርፍ የትኛውም ልኅቀት ላይ ቢደረስ፣ መምህርነት ያልነካው አይሆንምና፤ አንድም በዚህ የተነሳ የተለየ ክብር ይሰጣቸዋል።"
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
ውድ መምህራኖቻችን እንኳን ለአመታዊው የመምህራን ቀን አደረሳችሁ።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ኬሮድ ትምህርት ቤት መስከረም 24/2016ዓ.ም አመታዊው የመምህርነት ቀን በግሬድ ግቢ ከመምህራኖቻችን፣ ከተማሪዎቻችን እና ከአጠቃላይ ሰራተኞቻችን ጋር በደማቁ ተከብሮ ውሏል።
እናመሰግናለን
ትምህርት ቤቱ ።
👉የተጓዳኝ ትምህርት ክበባት ተግባራት
👯🌿የተጓዳኝ ክበባት ተግባራት የምንላቸው ተማሪዎች ላይ ሁለንተናዊ እድገት ለማምጣት በመማሪያ ክፍልና ከመማሪያ ክፍል ውጪ የሚተገበሩ ተግባራት ናቸው፤
🏃♂🌿የተጓዳኝ ክበባት ተግባራት በግል ወይም በቡድን፣በመማሪያ ክፍል ወይም ከመማሪያ ክፍል ውጪ እንደ ተገባራቱ ሁኔታና ባህሪ ሊከናወኑ ይችላሉ፤
🏃♀የተጓዳኝ ክበባት ተግባራት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ከሚማሩት ሥርዓተ-ትምህርት ጋር በቀጥታም በተዘዋዋሪም ተዛማችነት ያላቸው ሲሆኑ ለሚማሩት ትምህርት መስታወት ናቸው፤
👩👧🌿የተጓዳኝ ክበባት ተግባራት ለተማሪነት ህይወት እጅግ አስፈላጊ/መሰረታዊ ክፍሎች ናቸው፤
👭🌿ተማሪዎች በተጓዳኝ ክበባት ተግባራት ላይ የመሳተፍ ግዴታ አለባቸው (compulsory activities)።
👉የተጓዳኝ ክበባት ተግባራት ሚና እና ጠቃሚነት
🏈ለአካላዊና አእምሯዊ ጤና /Physical and Mental Health
ተማሪዎች በአትሌቲክስ (athletics)፣ በጂምናስቲክ (gymnastics)... እና በመሳሰሉት የክበባት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሲሳተፉ ለአካል ብቃት መዳበር (physical fitness) እና ለአእምሮ ጤንነት (mental health) ሁነኛ አስተዋፅኦ ይሰጣል/ያበረክታል፡፡ይህ ደግሞ ንቁ እንዲሆኑ ያደርጋቸውል፣በትምህርት አማካኝነት ከሚመጣ አላስፈላጊ ጭንቀት/መጨናነቅ እፎይታ ይሰጣቸዋል… ፡፡
🥏የመማር ልምድ/Learning Experience
-ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ የመገኘት ፍላጎታቸውን/ልምዳቸውን ይጨምራል/ያሻሽላል/ያዳብራል፡፡
ከትምህርት ገበታቸው ላይ የመቅረት፣የመፎረፍ እና የማቋረጥ ባህሪያትን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል፡፡
🪀የቡድን አመራር ችሎታዎች/Team Leadership Skills
– ተማሪዎች በተጓዳኝ ክበባት ተግባራት ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ ከክፍል ወይም ከሌሎች ክፍል ጓደኞቻቸው ጋር አብረው በሚሳተፉበት ጊዜ የመሪነት ክህሎታቸው፣የተሟላ የቡድን አቋም የመፍጠር(team integrity) እና የማስተባበር ክህሎቶቻቸው(coordination skills) እንዲያድግ/ እንዲዳብር ይረዳል፡፡
🏀የሞራል እሴቶች/Moral Values
–ተማሪዎች በተጓዳኝ ክበባት ተግባራት ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ ባህሎች እሴቶችን፣ሀይማኖት፣ ብሔራዊና አለማቀፋዊ ክስተቶች፣የተማሪነት ህይወት ሥነ-ምግባር፣ማህበራዊ ሥነ-ምግባር(social ethics)፣ትዕግሥት(patience)፣ እንደራስ/የሌላውን ስሜት መረዳትን(empathy)፣የማበረታታት ክህሎት፣ከሌላው ጋር አብሮ መኖርን (compatibility) ፣መደሰትን/መርካትን(contentment.)…ይማራሉ ፡፡
🥎አመክንዮዋዊ እና ትንተናዊ አስተሳሰብ/Logical and analytical thinking
– ሁኔታዎችንና ክስተቶችን በምክንያት የማሰብና የመተንተን አቅም እንዲያሳድጉ ይረዳቸዋል፡፡
🏓በጥልቀት ማሰብና ማገናዘብ/Critical thinking
–ፅንስ ሀሳቦችን (concepts)፣ ሀሳቦችን (ideas)፣ችግሮችን/ተግዳሮቶችን/እንቅፋቶችን/ጉዳዮችን (problems/case/challenge/trouble) እና ርዕሰ ጉዳይን (issues) የማጤን/የመመርመር አቅም ይሰጣቸዋል፡፡
⚽️የፈጠራ አስተሳሰብ/Creative thinking
– አዳዲስ ሀሳቦችን/ነገሮችን የማመንጨት/የመፍጠር/የማምረት አቅም እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡
🏀ችግሮችን የመፍታት ችሎታዎች/Problem-solving skills
–የተለያዩ/ልዩ ልዩ መፍትሄዎችን በመጠቀም ችግሮችን የመቅረፍ/የመፍታት ክህሎታቸውን ያዳብራል፡፡
🏌♀የአመራር ክህሎት/ Leadership skills
–ኃላፊነትን ቀድሞ የመቀበል፣ለመልካም ስራ/ጉዳይ ሌሎችን ተፅኖ ውስጥ የመክተት፣ዕቅድ የማውጣት፣ተጠያቂነትን አምኖ የመቀበል…እና የመሳሰሉትን ክህሎቶች እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል፡፡
🏄♂ማህበራዊ ክህሎቶች/Social skills
– ከሌላው ጋር በትብብር (collaboration) እና በመረዳዳት (teamwork) የመስራት ክህሎታቸውን ይገነባል፡፡
🏋♂ስሜታዊ ችሎታዎች/Emotional skills – የራስን ጠንካራና ደካማ ጎን የመረዳት፣ስሜትን የመቆጣጠር እንዲሁም የሌላውን ስሜት የመረዳት ክህሎት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡
🥊የተግባቦት ክህሎት/Communication Skills
–የተግባቦት፣ሀሳብን የመግለፅ/የመናገር፣የሌላውን ሀሳብ አክብሮ የማድመጥ፣ ህዝብ ፊት ቆሞ ሀሳብ የማቅረብ/የመናገር፣…ክህሎታቸውን ያዳብራል፡፡
🏸ማህበራዊ እሴቶች/Social values
– በግለሰቦች መካከል ያሉ ልዩነቶችን፣የሌላውን እሴትና ባህል እንዲያከብሩ ያደርጋል፡፡ማህበራዊ ፍትህን/social justice፣ዴሞክራሲያዊ እሴቶችን/Democratic values ለምሳኔ friendship ያዳብራሉ፡፡
⛳️የሥነ ምግባር እሴቶች/Ethical values
– በይፋዊ ሕይወታቸው (public life) ውስጥ ሥነ-ምግባር ጠብቀው መልካም የግብረ ገብነት እሴቶችን እንዲላበሱ ያደርጋል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ለተማሪዎች፣የተማሪ ወላጆች እና አሳዳጊዎች የምናስተላልፍላችሁ መልእክት ቢኖር ✍ተማሪዎች ከትምህርታቸው ጎን ለጎን በተጓዳኝ የክበባት ተግባራት እንቅስቃሴ ውስጥ እንደየ ዝንባሊያቸው/ተሰጧቸው መሰረት የሚሳተፉ ከሆነ አማራጭ የህይወት/የስኬት ጉዞ/መንገድ/መስመር/🔹#PLAN B ይኖራቸዋል ብለን እናምናለን፡፡ ምናልባትም ከተፈጥሮ የተሰጣቸው መክሊት ይሄ ሊሆን ከቻለ በራሳቸው ላይ ሁለንተናዊ ዕድገት ማምጣታቸው አይቀሬ መሆኑን ከራሳቸውም አልፈው ቤተሰብን፣አካባቢን፣ማህበረሰብን፣ሀገርን እና አለምን የሚያኮራ/የሚጠቅም/የሚቀይር ስራ የሚሰሩ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡
ስለዚህ በ2016 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ተሰጧችሁን በመለየት በተቋማችን በተቋቋሙ ልዩ ልዩ የተጓዳኝ ትምህርት ክበባት ውስጥ የነቃ ተሳትፎ እንድታደርጉ፤🎼🎻የተማሪ ወላጆችም ይህንን ተረድታችሁና በተጓዳኝ ክበባት ላይ የነበራችሁን ዝቅተኛ ግምት/ስሜት/ቦታ ቀይራችሁ ለልጆቻችሁ በቂ ድጋፍና ክትትል እንድታደርጉላቸው ስንል መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡📢
ከታላቅ ትህትና፣ከልዩ አክብሮት እና ከከበረ ሠላምታ ጋር!!!
እንዴት አመሻችሁ ክቡራን ወላጆች የወረዳው ት/ት ጽ/ቤት ዓርብ መስከረም 25 ቀን2016 ዓ.ም የኢሬቻን በዓል ምክንያት በማድረግ አዲስ አበባ ብዙ እንግዶች ልታስተናግድ ስለምትችልና የመንገድ መዘጋጋት ስለሚኖር የግልም ሆኑ የመንግስት ት/ቤቶች እንዲዘጉ ወስኗል። ስለሆነም ት/ቤታችን ከወዲሁ ያሎትን ፕሮግራም እንዲያስተካክሉ ስንል እጅግ በታላቅ አክብሮት እናሳውቃለን!!
ትምህርት ቤቱ!!
🪡☔️የወላጆች የቤት ሥራ
🧍♂ወላጆች የተሳሳተ ወይም የተዛባን ትምህርት መከላከል እንዲችሉ ልጆቻቸው ምን ትምህርት እየተሰጣቸው እንዳለ ማወቅ አለባቸው፡፡ስለዚህ ወላጆች እናንተም የቤት ስራ እንዳለባችሁ አስተውሱ!ልጆቻችሁ የሚማሩትን ትምህርት በሚገባ ተከታተሉ፡፡ከትምህርት ቤት ሲመጡ አወያዩአቸው፡፡ምን እየተማሩ እንዳሉ፣በጣም የሚወዱት ትምህርት ምን እንደሆነና በጣም ከባድ ሆኖ ያገኙት የትኛው እንደሆነ ጠይቋቸው፡፡የተሰጣቸውን የቤት ሥራ፣በደብተራቸው የጻፉትን ማስታወሻና ያገኙትን የፈተና ውጤት ተመልከቱ፡፤አስተማሪዎቻቸውን ለማወቅ ጣሩ፡፡አስተማሪዎቹ ሥራቸውን እንደምታደንቁላቸውና በምትችሉት መንገድ ሁሉ ልትረዷቸው እንደምትፈልጉ እንዲገነዘቡ አድርጉ፡፡
👉የልጆቻችሁ ጓደኞች
👬"ለመሆኑ ይሄን ከየት ነው የተማርከው?"ልጃቸው ፈጽሞ ከጠባዩ ውጪ የሆነ ነገር በመናገሩ ወይም በማድረጉ በጣም ደንግጠው ይህን ጥያቄ የጠየቁ ወላጆች ስንቶቹ ይሆኑ?ከትምህርት ቤት ወይም ከሰፈር ጓደኛዬ የሚል መልስ የሚሰጣቸውስ ምን ያህል ጊዜ ይሆን?አዎ፣ትንንሾችም ሆኑ ትልልቆች ጓደኞቻችን ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድሩብናል፡፡በተለይ ወጣጦች ለእኩዮች ተፅዕኖ በጣም የተጋለጡ ናቸው፡፡ራሳቸውን የመጠራጠር ዝንባሌ ያላቸው ከመሆኑም በላይ አንዳንድ ጊዜ ጓደኞቻቸውን ለማስደሰትና ተወዳጅነትን ለማትረፍ ያላቸው ፍላጎት ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድርባቸው ይችላል፡፡እንግዲያው ጥሩ ጓደኞች መምረጣቸው ምንኛ አስፈላጊ ነው!
👭ማንኛውም ወላጅ እንደሚያውቀው ልጆች ጥሩ ምርጫ የማያደርጉባቸው ጊዚያት አሉ፤ስለዚህ መመሪያ ያስፈልጋቸዋል፡፡ጓደኞቻቸውን እናንተ ልትመርጡላቸው ይገባል ማለት አይደለም፡፡ከዚህ ይልቅ እያደጉ ሲሄዱ ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ እንዲኖራቸውና ምን ዓይነት ባሕሪያት ያላቸውን ልጆች ጓደኛ አድርገው መምረጥ እንደሚገባቸው አስተምሯቸው፡፡ጓደኛ አድርገው የሚመርጧቸው ልጆች በመጀመሪያ ደረጃ ፈጣሪቸውን የሚወዱና ትክክለኛ ነገር ሚያደርጉ መሆን አለባቸው፡፡ሐቀኞች፣ደጎች፣ለጋሾችና ትጉዎች የሆኑትን እንዲወዱና እንዲያከብሩ አሰልጥኗቸው፡፡
📘የልጆቻችሁን ጓደኞች ታውቋቸዋላችሁ?
👯♀ልጆቻችሁ ጓደኞቻቸውን እቤት ይዘው መጥተው በደንብ እንዲያስተዋውቋችሁ ለምን አታደርጉም?በተጨማሪም ሌሎች ልጆች ለልጆቻችሁ ጓደኞች ምን አይነት አመለካከት እንዳላቸው ራሳቸውን ልጆቻችሁን ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ፡፡በአቋም ጽናታቸው የሚታወቁ ናቸው ወይስ ሁለት ዓይነት ኑሮ ሚኖሩ?ሁለት ዓይነት ኑሮ የሚኖሩ ከሆነ ልጆቻችሁ እንዲህ ዓይነቱ ጓደኝነት እንዴት ሊጎዳቸው እንደሚችል እንዲገነዘቡ አርዷቸው፡፡በልጃችሁ ጠባይ፣አለባበስ፣አመለካከት ወይም አነጋገር ረገድ ተገቢ ያልሆነ ለውጥ ከተመለከታችሁ ስለ ጓደኞቹ ወይም ጓደኞቿ ልታነጋግሯቸው ይገባል፡፡ምናልባት ልጃችሁ መጥፎ ተጽዕኖ ከሚያሳድርበት ጓደኛ ጋር መዋል ጀምሮ ይሆናል፡፡
🧍🏾♀🧍ሆኖም ልጆቻችሁ ከመጥፎ ጓደኞች እንዲርቁ ማድረግ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ጥሩ ጓደኞች ማግኘት እንዲችሉ እርዷቸው፡፡
👯♀ጥበበኛ የሆኑ ወላጆች ልጆቻቸው ጥሩ ጓደኞች እንዲያገኙና ከእነርሱ ጋር ጤናማ በሆነ መዝናኛ እንዲዝናኑ ይረዷቸዋል፡፡ይሁን እንጂ ለብዙ ወላጆች መዝናኛ ራሱ፣የራሱ ሆነ ፈታኝ ሁኔታዎች ይፈጥርባቸዋል፡፡
👉ለልጆች ምን ዓይነት መዝናኛ ያስፈልጋቸዋል?
🏄♂🤸🏾♀ልጆች በተፈጥሯቸው ፍልቅልቆች ከመሆናቸውም በላይ በጨዋታና በመዝናኛ ወቅት ሊወጣ የሚችል የታመቀ ኃይል አላቸው፡፡በሚገባ ታስቦበት የተመረጠ መዝናኛ ከደስታም ሌላ የሚያስገኘው ነገር አለ፡፡አንድን ልጅ እንዲማርና እንዲጎለምስ ያደርገዋል፡፡ወላጆች መዝናኛን ጨምሮ ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ የሟሟላት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ይሁን እንጂ ሚዛናዊ መሆን ያስፈልጋል፡፡
🧘♂🤼♀በብዙ ህይወት ውስጥ ትልቁን ቦታ የያዘው ነገር መዝናኛ ነው፡፡ይበልጥ አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች በቀላሉ ጊዜ እንድናጣ ሊያደርገን የሚችል ብዙ መዝናኛ አለ፡፡በከተማችን ቁርራቸው እየተበራከተ የመጣው የመዝናኛ ስፍራዎች የፆታ ብልግና፣ጠበኝነት፣ጫት መቃም፣የዕርቃን ጭፈራ ቤቶች ፣አደንዛዣ ዕፆች የሚከናወኑባቸውና ሌሎች እጅግ ጎጂ የሆኑ ድርጊቶችን የሚያራምዱ ናቸው፡፡
🤽♀⛹♀ልጆችን ጎጂ ከሆኑ መዝናኛዎች ለመጠበቅ ወላጆች ገደቦችና እገዳዎች ማበጀት አለባቸው፡፡ከዚህ ይበልጥ ግን ልጆቻችሁ ጎጂ መዝናኛን ለይተው ማወቅ እንዲችሉ ልታስተምሯቸው ይገባል፡፡
🏇እርግጥ፣ልጆች ጎጂ ከሆኑ መዝናኛዎች እንዲርቁ ማድረጉ ብቻ በቂ አይደለም፡፡መጥፎውን በጥሩ መከላከል ያስፈልጋል፤አለዚያ ግን ልጆች ወደ መጥፎ ጎዳና ሊያመሩ ይችላሉ፡፡አንዳንድ ጥበበኛ የሆኑ ወላጆች ወደ አንድ ቦታ ለሽርሽር መሄድ፣ረጅም የእግር ጉዞ ማድረግ፣ኃይማኖታዊና ታሪካዊ ቦታዎችን መጎብኘት፣የተለያዩ ጨዋታዎችን መጫወትና ዘመዶችን ወይም ወዳጆችን መጠየቅ፣ስዕል መሳል፣የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጫወት፣ በመሳሰሉት መዝናኛዎች በቤተሰብ ደረጃ አንድ ላይ ሆነው በመዝናናት በርካታ አስደሳች ትዝታዎችን ያሳልፋሉ፡፡ለመጫወት ብሎ በርከት ብሎ መገናኘትም በጣም አስደሳች መዝናኛ ነው፡፡
🤹♂በመጨረሻም ለወላጆች ማስተላለፍ የምንፈልገው መልእክት ቢኖር በዚህ አስጨናቂና🤦♀ አስደንጋጭ የሥነ-ባህሪ ጉድለት በሚታይበት፣በሚስተዋልበት ዓለም🌍ጊዜ ⏰ ወቅት🕰 ልጆቻችሁን ከቻላችሁ ሳይንሳዊ በሆነ የልጆች አስተዳደግ ጥበብ አልያም ወደ ሀይማኖት ተቋማት እንዲሄዱ በማድረግ መንፈሳዊ ህይወታቸው እጅጉኑ እንዲጎለብት ማድረግ ትልቁ የቤት ሥራችሁ መሆኑን አጥብቀን እንመክራለን❗️
💯እናመሰግናለን⁉️🙏🙏
ስኩል ኦፍ ኬሮድ ትምህርት ቤት
👉 መስከረም 20/2016ዓ.ም
#መልእክቶች
👉#ዐርብ [18/01/2016] በሙሉ ቀን #ትምህርት የሚቀጥል ይሆናል፤
👉ወደ ትምህርት ቤት ልጆን ሲልኩ የበኩልዎን ክትትል ያድርጉ፤
➤ አለባበሳቸውን [የትምህርት ቤቱን የደንብ ልብስ ብቻ]፣ የጸጉር አሰራር፣ የታሸጉ የምግብና መጠጥ ምርቶች አለመያዛቸውን፣ የተሟላ የትምህርት ግብዓት መያዛቸውን እና ዝግጁነታቸውን፣ የመግቢያ ሰዓት ማክበርን፣
👉 ከትምህርት ቤት ሲመለሱ ...
➤ አብሮነታችሁን፤ የተማሩትን እንዲያነቡ፣ እገዛና ድጋፍ በሚያስፈልጋቸው በዕለቱ መፈጸምዎን አይዘንጉልን።
መልካም በአል።
ሰኞ፣መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም
🫵የወላጅ እና አሳዳጊ ኃላፊነቶች/Parental Responsibilities
ህፃናትን ማሳደግ ቀላል ነው ብሎ የሚናገር ሰው አለ ብለን አናምን።ህፃናት ይህችን ምድር ሲቀላቀሉ ከመመሪያዎች፣ደንቦች እና ሥርዓት ጋር አብረው አይመጡም፡፡የሚመጡት ባዷቸውን ነው፡፡ስለሆነም አካላዊ እና ስሜታዊ ፍላጎቶቻቸው በተገቢው ሁኔታ ሊሟላላቸው ይገባል፡፡ወላጆች እነዚህን የተለዩ ፍላጎቶች ካጎደሉባቸው/ካላሳኩላቸው/ካላሟሉላቸው በህፃናቱ ቀጣይ ህይወት ላይ ከፍተኛ ውድቀት/ኪሳራ ይከተላል፡፡
ከዚህ ቀጥሎ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች ተግባራዊ ብታደርጓቸው በህፃናቱ አካላዊና ስሜታዊ ጤናማ እድገት ላይ አዎንታዊ ሚና ይጫወታሉ/ይኖራቸዋል ብለን ከተጠኑ ጥናቶች ያገኘናቸውንና ያመንባቸውን መሰረታዊ ኃላፊነቶችን መርጠን መጥነን አቅርበናቸዋል፡፡እባካችሁ ወላጆች ተግባራዊ አድርጓቸው!!!
1. ምቹ የሆነ አካባቢ መፍጠር
⚖ህፃናትን ከአካላዊ፣ፆታዊ እና ስሜታዊ በደሎች/ጥቃቶች መጠበቅ/ነፃ ማድረግ፤
🔪💊ለጤና ጠንቅ/አደገኛ የሆኑ ቁሶችን ህፃናት በማይደርሱበት ቦታ ላይ ማስቀመጥ
🧑🚒ልጆን እንዲጠብቅልዎ/እንዲንከባከብልዎ/እንዲያሳድግልዎ ብለው የቀጠሩዋቸውን ሰራተኛ ወይም ኃላፊነት የሰጧቸውን ግለሰብ ማንነት በቅጡ መረዳት/የኋላ ታሪካቸውን ማወቅ/ማረጋገጥ/መከታተል ይጠበቅብዎታል፤
🙅♂በቤት ውስጥ አደጋ የማድረስ አንዳች ኃይል አላቸው ብለው ያመኑባቸውን ነገሮች ማስተካከል/ማረም፤
2. መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማዘጋጀት/ማቅረብ/ሟሟላት
🚰ንፁህ ውሀ
🥬 አልሚነት ያላቸው ምግቦች
🛖መጠለያ
🛌ሙቀት የሚሰጥ አልጋ ከአንሶላ፣ብርድልብስ እና ትራስ ጋር ማመቻቸት/ማዘጋጀት፤
💊የጤና እክል ሲገጥማቸው ወደ ህክምና ጣቢ መውሰድ
3. ህፃናት ለራሳቸው የሚሰጡት ግምት( SELF-ESTEEM ) ከፍ እንዲል መስራት
🤜የልጅዎን ማንነት መቀበል እና ማክበር፣
⛹♀ በተለያዩ አዎንታዊ ተግባራትና እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ ማበረታታት(ስፖርታዊ ውድድሮች፣የበጎ ፈቃድ ስራዎች፣…)
🧏♂የልጅዎን ውጤት/የሥራ ክንውን እና አዎንታዊ ማህበራዊ ባህሪያትን ልብ ማለት፣ ማወቅ፣ ማየት፣ ትኩረት መሰጠት፣ ማስተዋል፣…
🚽የግል ንፅህናቸውን በአብባቡ እንዲጠብቁ ማስተማር(የጤና ጥበቃ ዘዴ) -ጥሩ ሆነው ሲታዩ መልካም ስሜት ይፈጠርባቸዋል
☔️ህፃናት በሚያጠፉበት/ያልተገባ ባህሪያትን በሚያሳዩበት ወቅት ከመተቸት፣ከመሳቅ፣ከመሳለቅ፣ከማፌዝ፣ከማሾፍ፣ከመንቀፍ ይልቅ…ቅፅበቱን እንደማስተማሪያ መድረክ ተጠቅሞ/ወስዶ ማረም/መገሰፅ መቻል
4. የሥነ-ምግባር/ግብረ ገብ እሴቶችን ማስተማር
💖ታማኝነት/Honesty፡- ስለታማኝነት በተለያዩ መንገዶች ግንዛቤ መፍጠር(ተምሳሌታዊና ሀይማኖታዊ ምሳሌዎችን ማቅረብ)፡፡በተጨማሪም ራስን ሞዴል አድርጎ ማሳየት፡፡ለምሳሌ ለትዳርዎ፣ለራሳቸው፣ለፈጣሪዎ፣ለምትገቧቸው ልዩ ልዩ ቃልኪዳኖች፣ለባህልዎ፣ለማህበረሰብዎ፣ለህሊናዎ…ታማኝ ሆነው መታየት፡፡
🤝አክብሮት/Respect፡- ስለአክብሮት ፅንስ ሀሳብና ጥቅም በተለያዩ መንገዶች ማስተማር(ተምሳሌታዊና ሀይማኖታዊ ምሳሌዎችን ማቅረብ)፡፡በተጨማሪም ራስን ሞዴል አድርጎ ማሳየት፡፡ለምሳሌ ለትዳር አጋርዎ፣ለልጅዎ፣ቤተሰብዎ፣ማህበረሰብዎ፣ፈጣሪዎ፣ባህልዎ፣ማንነትዎ… አክብሮት መስጠት መቻል፡፡
🤷♀ ኃላፊነት/Responsibility፡- ስለ ኃላፊነት ፅንስ ሀሳብና ጥቅም በተለያዩ መንገዶች ማስተማር(ተምሳሌታዊና ሀይማኖታዊ ምሳሌዎችን ማቅረብ)፡፡በተጨማሪም ራስን ሞዴል አድርጎ ማሳየት፡፡
💜ርህራሄ/Compassion፡- ስለ ርህራሄ ፅንስ ሀሳብና ጥቅም በተለያዩ መንገዶች ማስተማር(ተምሳሌታዊና ሀይማኖታዊ ምሳሌዎችን ማቅረብ)፡፡በተጨማሪም ራስን ሞዴል አድርጎ ማሳየት፡፡
🧗♀ትዕግሥት/Patience፡- ስለ ትዕግሥት ፅንስ ሀሳብና ጥቅም በተለያዩ መንገዶች ማስተማር(ተምሳሌታዊና ሀይማኖታዊ ምሳሌዎችን ማቅረብ)፡፡በተጨማሪም ራስን ሞዴል አድርጎ ማሳየት፡፡
💞ይቅርታ/Forgiveness፡- ስለ ይቅርታ ፅንስ ሀሳብና ጥቅም በተለያዩ መንገዶች ማስተማር(ተምሳሌታዊና ሀይማኖታዊ ምሳሌዎችን ማቅረብ)፡፡በተጨማሪም ራስን ሞዴል አድርጎ ማሳየት፡፡
🫴ልግስና/Generosity፡-ስለ ልግስና ፅንስ ሀሳብና ጥቅም በተለያዩ መንገዶች ማስተማር(ተምሳሌታዊና ሀይማኖታዊ ምሳሌዎችን ማቅረብ)፡፡በተጨማሪም ራስን ሞዴል አድርጎ ማሳየት፡፡
5. የመከባበርን መንፈስን ማሳደግ
🎼ሥርዓት ያለው ቋንቋ መጠቀም
🤹♂ ስሜታቸውን ማክበር
👏ሀሳባቸውን/አስተያየታቸውን ማክበር
🌿ግላዊነታቸውን(የራሳቸው ብቻ የሆነ ነገር)/ ማክበር
🙍♀ማንነታቸውን /individuality ማክበር ማንነት
6. በልጅዎ ትምህርት ላይ ተሳትፎ ማድረግ
📞ከሚያስተምሯቸው መምህራን ጋር መደበኛ ግንኙነት ማድረግ
📝 በየጊዜው የሚሰጣቸውን የቤት ስራ ሰርተው ማጠናቀቃቸውን ሁል ጊዜ ማታ ማታ ማረጋገጥ.
🌐የቤት ስራ ሲሰሩ መርዳት/ማስጠናት(የቤት ስራዎን መስራት ሳይሆን በምሳሌ ማስረዳት)
🤵♀ ሁልጊዜ ስለ ት/ቤት ማናገር/ማውራት (ስለተማሩት ትምህርት፣በት/ቤት ውስጥ ስለተከናወኑ ድርጊቶች/ ክስተቶች)
🪷በትምህርታቸው ከፍተኛ ወይም አበረታች ውጤት ሲያስመዘግቡ እውቅና መስጠት/ማበረታታት(መሸለም)/Recognition and acknowledgement
7. ከልጅዎ ጋር ቀረቤታ መፍጠር/get to know your child.
⏰ በቂ ሰዓት መድቦ ከልጅዎ ጋር አብሮ ማሳለፍ
♻️ ለመግባባት በሚያስችል መልኩ ልጅዎን መቅረብ
❓ጥያቄ መጠየቅ
☎️ መገናኘት፣ መገናኘት፣መገናኘት፣...
👏እናመሰግናለን❗️🙏
☀️🌟⭐️⭐️🌟✨☀️⭐️እንኳን ለ 2016 ዓ.ም የት/ት አመት በሰላም አደረሳችሁ። የት/ት አመቱ የመክፈቻ ፕሮግራም በግሬድ ግቢ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም.⭐️☀️☀️🌟🌟🌟☀️⭐️
ለውድ የኬሮድ ትምህርት ቤት ወላጆች በሙሉ፡-
ከዚህ ቀደም መጥቶ የነበረው የሁሉም የክፍል ደረጃ መፅሀፍት ተሸጠው ያለቁ በመሆኑ ሲመጣ የምናሳውቅ ይሆናል።
✍ክፍያ ፈፅማችሁ መፅሀፍ ያልወሰዳችሁ ወላጆች መፅሀፉ ሲመጣ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ትምህርት ቤቱ
ለውድ የኬሮድ ትምህርት ቤት ወላጆች በሙሉ፡-
እንኳን ለ 2016ዓ.ም የት/ት ዘመን አደረሳችሁ እያልን ቅዳሜ መስከረም 12 , 2016ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ድረስ የተማሪዎች የሰርቪስ እና የትምህርት ቤት መታወቂያ ስለሚሰጥ ወላጆች በት/ት ቤት በመገኘት የልጆቻችሁን መታወቂያ ፈርማችሁ እንድትወስዱ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ተማሪ መታወቂያ ሳይዝ የሰርቪስ አገልግሎት የማይሠጠው መሆኑን እንገልፃለን።
👉 ከ KG - 8ኛ ክፍል መታወቂያ የሚሰጠው በግሬድ ግቢ መሆኑን እንገልፃለን።
ትምህርት ቤቱ
የተከበራችሁ ወላጆች በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ታትመው የቀረቡት መፅሃፍቶች ከዚህ በታች ያሉ ሲሆን ከመስከረም 8-11/2016ዓ.ም ባሉት ቀናቶች ብቻ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
Repost from Schoolofkareode@grade2
ውድ የኬሮድ ወላጆች በነገው ዕለት 06/06 2015 መደበኛ ት/ ት የሚጀምር ሲሆን በመደበኛ ሰዓት ልጆችን ወደ ት/ት ቤት እንድትልካቸው እናሳስባለን::
ት/ቤቱ
ውድ ወላጆች፣
ነገ፣ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ትምህርት ለተማሪዎች ዝግ ሆኖ በተማሪዎች የ1ኛ ሴምስተር ውጤት ላይ ከመምህራን ጋር ውይይት እንዲደረግ ከወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት አሁን ከረፈደ በተላለፈልን መመሪያ መሰረት ተማሪዎች ነገ አርብ፣ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ትምህርት ቤት የማይመጡ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን።
የትምህርት ቤቱ አስተዳደር
