SCHOOL OF KAREODE
Open in Telegram
516
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-130 days
Posts Archive
✍ተማሪዎች በየክፍል ደረጃው ከሚማሩት የትምህርት ዓይነት በተጨማሪ ከክፍል ውጭ ሊሳተፉባቸው በሚችሉ #የተጓዳኝ ትምህርት ዘርፎች/ክበባት/ ላይ እንዲሳተፉ ማስቻል ለሁለንተናዊ እድገታቸው ወሳኝ ነው፤
🧠#የተጓዳኝ ትምህርት /Co-Curricular/ ከክፍል ውስጥ ትምህርት ውጭ በመደበኛው የትምህርት አሰጣጥና ስሌት መሠረት ከሚፈፀሙ ተግባራት በተጨማሪ የተማሪዎችን ፍላጎት መሠረት በማድረግ የሚከናወን ተግባር ነው፡፡
[Co-Curriculars= Learning Beyond The Classroom]
👩💻ተጨባጭ ሙከራዎች እንዲያደርጉ፣ በክፍል ውስጥ የሚሰጠውን የንድፍ ሃሳብ ትምህርት በተግባር መረዳት እንዲችሉ በማድረግ የግልና የማኀበራዊ ዕድገትን ያፋጥናል፣ የሰብዓዊ ግንኙነት ክህሎትን በማዳበር ሌሎችንም የማክበርና የመከበር ስርዓትን ይማሩበታል፣ ራስን የመግለጽ ከሰዎች ጋር የመወያየት፣ የማመንና የማሳመን፣ የማወቅና የማሳወቅ፣ የውይይት ሥነ ሥርዓቶችን የማወቅ፣ ውሣኔ የመስጠትንና በውይይት የመተማመንን ሂደት እንዲሁም አመራርን፣ ሓላፊነትን፣ ተጠያቂነትን እንዲማሩበትና እንዲለማመዱበት ያግዛል፣ ለሥራ አክብሮት መስጠትን፣ የጊዜን ጠቀሜታ መረዳትን፣ ሥራ ማኀበራዊ መሆኑን የመገንዘብና የቡድን ሥራን እንዲለማመዱ ይረዳል፣ የፈጠራ ችሎታ በማሳደግ የቴክኖሎጂ ዕድገት መሠረት የሚጥሉ የተማሪዎች ልዩ ልዩ ፈጠራዎችና ተሰጥዖ እንዲጎለብት ያድርጋል፤
🙏#ምስጋና
በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በተገለጸው አግባብ ለተግባሩ አስተዋጽኦ ለነበራችሁ መምህራን እና የተማሪዎቻችን ቤተሰቦች ከልብ እናመሰግናለን።
#ነገን ደግሞ የበለጠ የተሻለ ማድረግ ይቻላል።በመሆኑም እርሶም በቀጣይ ከልጆ ጋር በመወያየት ትኩረት ሰጥተው፤ በዕለት ተዕለት የትምህርት ጉዳዮች ዓላማን መሠረት አድርገው ሁሌም የሚያነቡ፣ የሚጠይቁ፣ የሚመራመሩ መሆን እንዲችሉ፣ ለራሳቸው እና ለሌሎችም በአመለካከት እና በሥነ ምግባር መልካም እና የተግባር ሰው መሆንን በሕይወት ተሞክሮ እናለማምዳቸው፤ ብዙ የምንጠብቅባቸው ልጆቻችን ትልቅ ደረጃ መድረስ እንደሚችሉ እንመን፤ ያለሙትን መሆን እንደሚችሉም ራሳቸው እንዲያምኑ ሆኖ እምነትን ከተግባር አዛምደው እንዲኖሩ መንገዱን እናሳያቸው፤ ይህ ለውጤታማነታቸው ቁልፍ፤ ለስኬታቸው በራሱ ድርሻ አለውና።
ትምህርት ቤቱ
🗝የልጆችን ጠባይ ለማሻሻል የሚረዱ ቀላል መንገዶች
👩💼🧑💼ቀጥሎ የቀረቡት ቀላል ዘዴዎች ካሁን ጀምረን በመጠቀም ልጆቻችን መልካም ጠባይ እንዲይዙ ማበረታታት እንችላለን:: ሁሉም የቀረቡት መንገዶች መልካም የሆኑና ከልጆች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረን የሚረዱን እንዲሁም የልጆችን በራስ መተማመን እና ለራሳቸው የሚሰጡት ክብር እንዲጨምር ከማድረግም አልፎ መልካም ጠባይን እንዲይዙ ይረዳቸዋል::
🗣👥 ለልጆች አቅም በንግግር እውቅና መስጠት
ልጅዎ ስለሰራው/ችው ነገር እንደኮሩበት/ባት በግልጽ መንገር:: ለምሳሌ ትላንት ማታ ከትምህርት ቤት የተሰጠህን/ሽን የእንግሊዘኛ ሰርቶ ማሳያ በሙሉ ትኩረት ስትሰራ/ሪ ነበር በዚሁ ቀጥል/ይ በማለት ማድነቅ ያስፈልጋል::
ልጆች ስለሰሩት መልካም ነገር እውቅና ካገኙ ተመሳሳይ ነገሮችን ያለማቋረጥ ይተገብራሉ::
👏👏ለመልካም ጠባይ በጠቋሚ የአካል እንቅስቃሴ/ምልክት አድናቆትን መግለጽ
😁እንደ ፈገግታ፣👍 አውራ ጣትን ወደ ላይ ማሳየት፣ጀርባን ቸብ ማድረግ እና
🤜🫷🤌የመሳሰሉት ከጠቋሚ የአካል እንቅስቃሴ/ምልክት ውስጥ ይጠቃለላሉ:: አንዳንድ ልጆች ጀርባቸውን ሲነኩ ላይወዱ ስለሚችሉ ወይም ሌሎችም ካሉ የሚወዱትን በመለየት እና በማወቅ ለማበረታታት መጠቀም ያስፈልጋል::
👨👩👧👦በጥሩ የጫወታ ለዛ ከልጆችዎ ጋር ይጫወቱ
👧🧒ይቀልዱላቸው፤👂የነሱንም ቀልድ ይስሙ:: ለቀልዳቸውም ፈገግታን ያሳይዋቸው:: ልጆችዎን ስላገኟቸው ደስተኛ መሆንዎን ይግለፁላቸው ወዳሉበት ሲመጡ በፈገግታ ይቀበሏቸው ፤እጅዎን ዘርግተው በማቀፍ ስለ ቀን ውሏቸው በመጠየቅ ያዳምጧቸው::
👌ልጆችዎ ሁሌም በራሳቸው እንዲኮሩ ያስታውሷቸው
ይሄ የልጅዎን ውስጣዊ በራስ መተማመን ከመጨመሩም በላይ ያለማቋረጥ ጠንክሮ መስራት እና ለሌሎች መልካም መሆን እንደሚያኮራ ይማራሉ:: ስኬታማ እንደሆኑ ከተሰማቸው ለወደፊቱም ስኬታማ ይሆናሉ::
🤝ከልጅዎ ፍላጎት ጋር ይተባበሩ
ልጅዎን የሚያዝናና ነገር ይጠይቁት/ቋት፤ ስለሰራው/ችው በጎ ስራ ያድንቁት/ቋት፤ ስለነገሮች ያለውን/ትንአመለካከት ይጠይቁት/ቋት፤ ትምህርታዊ የሆኑም ያልሆኑም ልጆችዎ የሚወዱትን ነገር እርስዎ ባይወዱትም አብረው ይስሩ::
🫵የልጆዎን ስሜት እንደራስዎ ይረዱ
አንድን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሞክሩበት ወቅት የሚፈጠር ንዴት ሲኖር ወይም ለነሱ የሚከብድ የጽሁፍ ስራ በመሰጠቱ ምክንያት ሲደናገጡ ወይም በጓደኞቻቸው ልደት ሊይ ባለመጋበዛቸው ሲያዝኑ ወይም ጓደኞቻቸው በምክንያት ሲስቁባቸው በወቅቱ ጭንቀታቸውን በመካፈል ከጎናቸው እንደሆኑ በሚገባ ያስረዷቸው::
🧠ልጆችዎ ከእርሶ የተለየ አመለካከት ወይም አስተሳሰብ ሲኖራቸው በቀናነት ይቀበሉ
ይህ ማለት የራስዎን ሀሳብ እና አመለካከት ከማካፈል አያግድም ነገር ግን የእነሱ ሀሳብ ወይም አመለካከትበጥቅሉ ስህተት መሆኑን መንገር አይገባም:: በዚህ መልኩ ሀሳባቸውን የምንሰማ ከሆነ ሌሎች ከበድ ያሉ ችግሮችንም ለመናገር ድፍርት ይኖራቸዎል::
🧑🎓👨🎓መልካም አርአያ ይሁኑ
ልጅዎ ለሌሎች አክብሮት እንዲኖረው/ራት ከፈለጉ ተመሳሳይ ነገር ያድረጉ:: ልጅዎ ታማኝ እንዲሆን ከፈለጉ ምሳሌ ሆነው ያሳዩት::
👨⚖👩⚖በህገ ደንብ ይመሩ ቃልዎን ይጠብቁ
በጋራ ከልጆዎ ጋር ባወጡት ህግ ይመሩ:: ቃልዎን ሁልጊዜም ይጠብቁ:: ለምሳሌ አንዱ ህግ ልጆችዎ ቴሌቪዢን የሚመለከቱት ከጥናት በኋላ ከሆነ ሁሌም ይህንኑ ይከተሉ:: ይህን ያለማቋረጥ ከተገበሩ ልጆችዎ በመካከላችሁ ያለውን መስመር ስለሚረዱ ለእርሶዎ ያላቸው ክብር ይጨምራል::
#የትምህርት ሒደት
👉ሙከራ 1 ተሰጥቶ የተጠናቀቀ ቢሆንም የተማሪዎች ዝግጅት ለፈተና ብቻ ስላልሆነ ሁሌም የተግባር ሒደትን አጠናክረው እንዲቀጥሉ፤
👉በቤተሰብ ደረጃ ውጤታቸውን በመገምገም በጥናት ዘዴ፣ በራሳቸው መማርን እንዲያዳብሩ እና የሥነ ልቦና ግንባታ ላይ እንዲሰራ፤
👉በመማር ሒደት ውስጥ ሁለገብ አቅም እንዲኖራቸው፤ በትምህርት እና በመማር ሒደት ተሳትፎን በሚጠይቁ ሁነቶች እንዲሳተፉ ማበረታታት ያስፈልጋል፡፡
ትምህርት ቤቱ።
ስኩል ኦፍ ኬሮድ ትምህርት ቤት
ዛሬ በቀን 05/02/2016ዓ.ም የ16ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን "የሰንደቅ ዓላማችን ለሕብረ ብሔራዊ አንድነታችንና ሉአላዊነታችን ዋስትና ነው" በሚል መሪ ቃል 4፡30 ተከብሯል።👏👏👏👏👏👏👏
#ሒደታዊ ተግባራት፤#የቀጣይ ትኩረቶች
🙏ውድ የኬሮድ ትምህርት ቤት ወላጆች በዚህ 2016ዓ.ም የትምህርት ዘመን ያለፋትን አንድ ወር በጅምሩ ለታየው የሁሉም ተሳትፎ ሁላችሁንም ከልብ እናመሰግናለን፤
#ለልጆቻችን ቤተሰቦች
👉በእውቀት፣ አመለካከትና ክህሎት፤ በውጤታማነት እና ስኬት፤ በሥነ ምግባር፣ ግብረ-ገብና ተግባር ባለው ለውጥ፤ ከልጆቻችን ጋር በምክክር፣ በግንዛቤ ማስጨበጥ እና ሀላፊነትን በማለማመድ የጀመርናቸው ተግባራት መልካም ስለሆኑ ሁላችንም ጅምሩን እንድናጠናክር ይሁን፤
#አክብሮት እና ምስጋና
👉 ከመስማት በላይ ለሚያደምጡ፣ በጅምሩም ተስፋን ላሳዩን ልጆቻችን ስኬታማነትን በሥራ እና እምነት እንመኛለን።
#በእስካሁኑ ጉዟችን
👉በመስከረም ወር ለመምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ስልጠና፣ ለተማሪዎቻችን የትምህርት ቤቱን ህግና ደንብ በማሳወቅ፣ ሰርቶ ማሳያ 1 [Worksheet 1] በመስጠት፣ከ 5ኛ - 8ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን የጥናት ፕሮግራም ተዘርግቶላቸው ጥናት መጀመራቸው፣ በባህሪ ላይ ለሚታዩ ክፍተቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ለተማሪዎች መሰጠቱ እና የወላጅ ትምህርት ቤት ግንኙነት መፅሀፍ መሰጠቱ እንደ ጅምር የምናነሳቸው የ2016 የትምህርት ቤቱ አበይት ክንውኖች ናቸው፡፡
👉በላክነው የትምህርት መርሐ ግብር መሠረት ከመለማመጃ ጥያቄው ቀጥሎ #ሙከራ 1 [Test 1] ስለሚሰጥ ቅድመ ዝግጅቱ ይጠናከር፤
#ከሙያዊ እይታ መነሻ
👉ብዙ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት #የትምህርት ውጤት የሥርዓተ ትምህርቱ፣ የቤተሰብ፣ የትምህርት ግብዓት [የሥርዓተ ትምህርት ግብዓቶች፣ የስልጠና፣ የመምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራር እና ስታንዳርድ ማሟላት] የተማሪዎች የራሳቸው ሁለንተናዊ ሁኔታ፣ ዝግጁነት እና ጥረት፤ የሒደት ጥራት፤ የየራሱ አስተዋጽኦ እና ትስስራዊ መንስኤ እና ትግበራ ስለሆነ ለሁሉ ዝግጁ እንሁን።
# ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች
👉በተጓዳኝ ትምህርት(ክበባት) ላይ ተማሪዎቻችንን ማሳተፍ፣ከግራንድ ስታንድ መረጃ ሲስተም ጋር በመሆን የተማሪዎቻችንን ውጤት በየሳምንቱ ሲስተም ላይ ለወላጆቻችን የውጤት መረጃ መስጠት (በቀጣይ በስፋት እንመለስበታለን)፣የእርስ በእርስ ግንኙነት ከወላጆች ጋር በመሆን መስራት፣ማጠናከሪያ ትምህርት መጀመር፣የተማሪዎቻችንን ተወዳዳሪነት ማሳደግ እንዲሁም በሂሳብ፣በፈጠራ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ ላይ አዳዲስ ነገሮችን መስራት ዋንኞቹ ናቸው።
➤ በአመለካከት፣በእድገትና አስተሳሰብ፣ የተግባር ሰው ስለመሆን፣ የውስጥ እምነት ለውጤታማነትና ስኬት፣በራስን ማዘጋጀትና ሀላፊነት፣ምክክሩና፣ ማስገንዘቡ በሁሉም ቤተሰብ እንዲዳብር ይሁን።
ጥቅምት 1/2016 ዓ.ም
ትምህርት ቤቱ።
