cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

Advertising posts
826Subscribers
No data24 hours
No data7 days
+1130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🔺በአለማችን ቢራን በመጥመቅ እና በማክከፋፈል የሚታወቀው Heineken (ሄኒከን) ቢራ ከሁለት ሌሎች ድርጅቶች ጋር በመተባበር አዲስ ስልክ ለገበያ አቅርበዋል ስሙንም “Boring Phone” ብለውታል። #Heineken #Smartphone
Show all...
🔰ሞባይል ዳታ በሚከፈትበት ጊዜ ካርድ ወይም የተሞላውን የዳታ ጥቅል በቶሎ የሚጨርስበት ምክንያትቶችና መፍትሔዎች ምክንያቶች :- 1.የሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሳይዘጋ ሲቀር 2.ኢንተርኔት ክፍት ሆኖ ከተለያዩ ደህረ ገፆች ላይ ቀጥታ ቪዲዮች ሲታዩ 3.System settings እና Applications በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ 4.በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቃሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሊ 5.በሞባይል ስልኩ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር መፍትሔዎች :- 🌀ሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሲቆይ እንደ ሶሻል ሚዲያና ኦንላይን የሚሰሩ አፕሊኬሽኖች ከተጠቃሚው እይታ ውጪ ስራቸውን ያከናውናሉ። በዚህ ጊዜ በሞባይሉ ላይ የተሞላው ክሬዲት ሰዓት ይቀንሳል ወይም ያልቃል ስለዚህም ኢንተርኔት ተጠቅመው ከጨረሱ በኋላ የሞባይሉን ዳታ ያጥፉ። 🌀በሞባይል ዳታ ኢንተርኔት ከፍቶ ከተለያዪ ድህ ገፆች ላይ በቀጥታ ቪዲዮ መመልከት የተሞላውን ካርድ መጠን በጊዜ ከሚያሳጥሩት ነገሮች ወስጥ አንደኛው ሲሆን ለዚህም ዋነኛው ምክንያት በኢንተርኔት ቪዲዮ ቀጥታ መመልከት የሚቆጥረው የዳታ መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ነው ስለዚህ ቪዲዮ ማየቱ ግዴታ ከሆነ በ Vidmate እና በሌሉች ቪዲዮ ዳውሎደር አፕሊኬሽኖች የቪዲዮ ይዘት በመቀነስ ጭኖ መመልከቱ ወጪን ይቆጥባል። 🌀System settings እና Application በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ የተሞላውን ዳታ(ካርድ) ይወስዳሉ ታዲያ ይህን ለማስቀረት Free wifi ከተገኘ አፕዴት ማድረግ ይህ ማድረግ የማይቻል ከሆነ system settings አፕዴት እንዳያደርግ ማስቆም:   🌀Settings ----About----Software Update--- Automatic update የሚለውን ማጥፋት Applications አፕዴት እንዳያደርጉ ከተፈለገ ደግሞ -Google Play መክፈት. - hamburger የሚመስለውን በለ ሶስት ሆሪዞንታል ምልክት ያለበትንም አናት ላይ በስተግራ በኩል Settings በመንካት Auto-update apps.- disable automatic app updates, የሚለውን በመክፈት እና በመምረጥ መዝጋት ይቻላል 🌀በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቀሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሊ ከእይታ ውጪ በመሆን የክሬዲት መጠን ይቀንሳሉ ታዲያ ይህን ለመከላከል:     🌀Settings----data usage ---Restricted Background data የሚለውን መክፈት... ከዚህ ይበልጥ ደግሞ Mobile data saver አፕሊኬሽኖች በመጫን መጠቀም 🌀በሞባይል ሰልክ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር የተሞላውን ሞባይል ዳታ ከመቅስፈት እድሜው እንዲያጥር ያደርጋል ብሎም ቫይረሱ በራሱ ጊዜ የሞባይሉን ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማዘዝ ያለማንም ትዕዛዝ ዳታ ይከፍታል ዳውንሎድ ያደርጋል አላስፈላጊ ነገሮችና ማስታወቂያዋች ይለቃል ከዚህም የተነሳ በፍጥነት የሞባይል ካርድ( ዳታ ጥቅል) ይጨርሳል ይህ ነገር በሞባይሉ ላይ ቢከሰት አንቲ ቫይረስ በመጫ ሰካን ማድረግ ይህ መፍትሔ የማይሆን ከሆነ ለባለሙያ ማሳየቱ ተገቢ ነው:: ⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ 🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻 💡 | @Endre_Techs ✅® 2024 | ሁሉንም በእጅዎ!
Show all...
👍 1
📉 Statistics 🔺ቴሌግራም በቅርቡ ያስተዋወቀው እና ተፈላጊነቱ እየጨመረ የመጣው $TON Coin በMarket ካፕ ከ Dogecoin ቀደሞ 8ኛ ደረጃን መያዝ ችሏል።
Show all...
🔰Notcoin 3 ዜሮዎችን ሰርዟል❕ 🔻10.000.000 ነጥብ የነበራቸው አሁን 10,000 ነጥብ ይኖራቸዋል፣ ይሄ የሆነበት ምክንያት ለማንበብ ቀላል ለማድረግ ሲሆን ባሁኑ ሰአት ከሁሉም ሰው ባላንስ ላይ 3 ዜሮዎች እንዲቀነሱ ተደርገዋል። 🔻ያ ማለት ያለን Notcoin ላይ 3 zero ተቀንሶ ወደ $Not token ይቀየራል ለምሳሌ 10 million notcoin ያለው ሰው ወደ 10 ሺ $Not token ይቀየርለታል። 🔻 ባሁኑ በአት አንድ ኖትኮይን በ 0.0127$ ዶላር ገበያ ውስጥ እየተዘዋወረ ሲሆን April 20 ወይም ከ 8 ቀናት ቡሀላ ሊስት ሲደረግ ከዚህም በላይ ዋጋ ሊያወጣ እንደሚችል በብዙዎች ዘንድ እየተገመተ ይገኛል። Stay tuned for more informations 📣 | @TechBamargna
Show all...
👍 5
የግእዝ ቁጥሮች #Ethiopia | በአኀዝ፣ በፊደል እና በዐረብኛ – አልቦ =0 ፩ አሐዱ =1 ፪ ክልኤቱ =2 ፫ ሠለስቱ =3 ፬ አርባዕቱ =4 ፭ ሐምስቱ =5 ፮ ስድስቱ =6 ፯ ስብዓቱ =7 ፰ ስመንቱ 8 ፱ ተሰዓቱ 9 ፲ አሠርቱ 10 ፲፩ አሠርቱ ወአሐዱ 11 ፲፪ አሠርቱ ወክልኤቱ 12 ፲፫ አሠርቱ ወሠለስቱ 13 ፲፬ አሠርቱ ወአርባዕቱ 14 ፲፭ አሠርቱ ወሐምስቱ 15 ፲፮ አሠርቱ ወስድስቱ 16 ፲፯ አሠርቱ ወሰብዓቱ 17 ፲፰ አሠርቱ ወስመንቱ 18 ፲፱ አሠርቱ ወተሰዓቱ 19 ፳ እስራ 20 ፳፩ እስራ ወአሐዱ 21 ፳፪ እስራ ወክልኤቱ 22 ፳፫ እስራ ወሠለስቱ 23 ፳፬ እስራ ወአርባዕቱ 24 ፳፭ እስራ ወሐምስቱ 25 ፳፮ እስራ ወስድስቱ 26 ፳፯ እስራ ወሰብዓቱ 27 ፳፰ እስራ ወሰመንቱ 28 ፳፱ እስራ ወተሰዓቱ 29 ፴ ሠላሳ 30 ፴፩ ሠላሳ ወአሐዱ 31 ፴፪ ሠላሳ ወክልኤቱ 32 ፴፫ ሠላሳ ወሠለስቱ 33 ፴፬ ሠላሳ ወአርባዕቱ 34 ፴፭ ሠላሳ ወሐምስቱ 35 ፴፮ ሠላሳ ወስድስቱ 36 ፴፯ ሠላሳ ወሰብዓቱ 37 ፴፰ ሠላሳ ወሰመንቱ 38 ፴፱ ሠላሳ ወተሰዓቱ 39 ፵ አርብዓ 40 ፶ ሃምሳ 50 ፷ ስድሳ 60 ፸ ሰብዓ 70 ፹ ሰማንያ 80 ፺ ተሰዓ 90 ፻ ምዕት 100 ፻፩ ምዕት ወአሐዱ 101 ፻፪ ምዕት ወክልኤቱ 102 ፻፫ ምዕት ወሠለስቱ 103 ፻፬ ምዕት ወአርባዕቱ 104 ፻፭ መዕት ወሐምስቱ 105 ፻፮ ምዕት ወስድስቱ 106 ፻፯ ምዕት ወሰብዓቱ 107 ፻፰ ምዕት ወስመንቱ 108 ፻፱ ምዕት ወተሰዓቱ 109 ፻፲ ምዕት ወአሠርቱ 110 ፻፲ወ፩ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 111 ፻፲ወ፪ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 112 ፻፲ወ፫ ምዕት አሠርቱ ወሠለስቱ 113 ፻፲ወ፬ ምዕት አሠርቱ ወአርባዕቱ 114 ፻፲ወ፭ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 115 ፻፲ወ፮ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 116 ፻፲ወ፯ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 117 ፻፲ወ፰ ምዕት አሠርቱ ወስመንቱ 118 ፻፲ወ፱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 119 ፻፳ ምዕት ወእስራ 120 ፻፴ ምዕት ወሠላሳ 130 ፻፵ ምዕት ወአርብዓ 140 ፻፶ ምዕት ወሃምሳ 150 ፻፷ ምዕት ወስድሳ 160 ፻፸ ምዕት ወሰብዓ 170 ፻፹ ምዕት ወሰማንያ 180 ፻፺ ምዕት ወተሰዓ 190 ፪፻ ክልኤቱ ምዕት 200 ፪፻ወ፩ ክልኤቱ ምዕት ወአሐዱ 201 ፪፻ወ፪ ክልኤቱ ምዕት ወክልኤቱ 202 ፪፻ወ፫ ክልኤቱ ምዕት ወሠለስቱ 203 ፪፻ወ፬ ክልኤቱ ምዕት ወአርባዕቱ 204 ፪፻ወ፭ ክልኤቱ ምዕት ወሐምስቱ 205 ፪፻ወ፮ ክልኤቱ ምዕት ወስድስቱ 206 ፪፻ወ፯ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓቱ 207 ፪፻ወ፰ ክለኤቱ ምዕት ወስመንቱ 208 ፪፻ወ፱ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓቱ 209 ፪፻ወ፲ ክልኤቱ ምዕት ወአሠርቱ 210 ፪፻፲ወ፩ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 211 ፪፻፲ወ፪ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 212 ፪፻፲ወ፫ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሠልስቱ 213 ፪፻፲ወ፬ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአርባቱ 214 ፪፻፲ወ፭ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 215 ፪፻፲ወ፮ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 216 ፪፻፲ወ፯ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 217 ፪፻፲ወ፰ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ 218 ፪፻፲ወ፱ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 219 ፪፻፳ ክልኤቱ ምዕት ወእስራ 220 ፪፻፴ ክልኤቱ ምሪዕት ወሠላሳ 230 ፪፻፵ ክልኤቱ ምዕት ወአርብዓ 240 ፪፻፶ ክልኤቱ ምዕት ወሃምሳ 250 ፪፻፷ ክልኤቱ ምዕት ወስድሳ 260 ፪፻፸ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓ 270 ፪፻፹ ክልኤቱ ምዕት ወሰማንያ 280 ፪፻፺ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓ 290 ፫፻ ሠለስቱ ምዕት 300 ፬፻ አርባዕቱ ምዕት 400 ፭፻ ሐምስቱ ምዕት 500 ፮፻ ስድስቱ ምዕት 600 ፯፻ ስብዓቱ ምዕት 700 ፰፻ ስመንቱ ምዕት 800 ፱፻ ተሰዓቱ ምዕት 900 ፲፻ አሠርቱ ምዕት 1000 ፳፻ እስራ ምዕት 2000 ፴፻ ሠላሳ ምዕት 3000 ፵፻ አርብዓ ምዕት 4000 ፶፻ ሃምሳ ምዕት 5000 ፷፻ ሳድስ ምዕት 6000 ፸፻ ሰብዓ ምዕት 7000 ፹፻ ሰማንያ ምዕት 8000 ፺፻ ተሰዓ ምዕት 9000 ፻፻ እልፍ 10,000 ፪፻፻ ክልኤቱ እልፍ 20,000 ፫፻፻ ሠለስቱ እልፍ 30,000 ፬፻፻ አርባዕቱ እልፍ 40,000 ፭፻፻ ሐምስቱ እልፍ 50,000 ፮፻፻ ስድስቱ እልፍ 60,000 ፯፻፻ ሰብዓቱ እልፍ 70,000 ፰፻፻ ስመንቱ እልፍ 80,000 ፱፻፻ ተሰዓቱ እልፍ 90,000 ፲፻፻ አሠርቱ እልፍ 100,000 ፳፻፻ እስራ እልፍ 200,000 ፴፻፻ ሠላሳ እልፍ 300,000 ፵፻፻ አርብዓ እልፍ 400,000 ፶፻፻ ሃምሳ እልፍ 500,000 ፷፻፻ ስድሳ እልፍ 600,000 ፸፻፻ ሰብዓ እልፍ 700,000 ፹፻፻ ሰማንያ እልፍ 800,000 ፺፻፻ ተሰዓ እልፍ 900,000 ፻፻፻ አእላፋት 1,000,000 ፲፻፻፻ ትእልፊት 10,000,000 ፻፻፻፻ ትልፊታት 100,000,000 ፲፻፻፻፻ ምእልፊት 1,000,000,000 ⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ 🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻 💡 | @Endre_Techs ® 2024 | ሁሉንም በእጅዎ!
Show all...
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የቡና ቅጠል በሸታን የሚለይ መተግበሪያ እያበለፀገ መሆኑን ገለፀ የቡና ቅጠል ምስልን በመጠቀም ብቻ የቡና ቅጠል በሸታን ለመለየት፣ የጉዳት መጠንን ለማወቅ የሚያስችል ኮፊኔት የተሰኘ መተግበሪያ እያበለፀገ መሆኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ውጤት ነው የተባለው ይህ መተግበሪያ ከሰው ሰራሽ አስተውሎት የምርምር መስክ በሆነው ኮምፒውተር ቪዥን መበልፀጉ ተሰምቷል። ቴክኖሎጂው ሶስት የቡና ቅጠል በሽታዎችን መለየት ይችላልም ነው የተባለው። ምንጭ: @TikvahethMagazine
Show all...
🤣 1
ቴሌግራም የቢዝነስ ሶሻል ሚዲያነት እየተቀየረ እንደሆነ ይታወቃል። ቴሌግራም በዚህ አመት ካስተዋወቃቸው ፊቸሮች መካከል አንዱ Telegram business ነው ። እነዚህ ፊቸርች ምን ምን እንደሆኑና ለምትጀምሩትን ቢዝነስ ምን ጠቀሜታ እንዳለው አንድ በአንድ ለማየት እንሞክር። ✅️Location: ቢዝነሳችሁን የምትሰሩበትን አካባቢ ሰዎች በቀላሉ እንዲውቁትና Google map ተጠቅመው እንዲመጡ ፕሮፋይላችሁ ላይ  መሙላት ትችላላችሁ። ✅️ Opening houre: ቢዝነሳችሁን የምትከፍቱበትና የምትዘጉበትን ሰአት ሰዎች በቀላሉ እንዲያውቁት ፕሮፋይላችሁ ላይ  መሙላት ትችላላችሁ። ✅️ Quick Replies: ብዙ ሰዎች Contact የሚያድርጓችሁ ከሆነና ለሁሉም ተመሳሳይ አይነት መልዕክት የምትልኩ ከሆነ ሁሉንም አንድ በአንድ መፃፍ ሳይጠበቅባችሁ በshortcut መላክ ትችላላችሁ። ✅️Greeting message: ሰዎች Contact ሲያደርጓችሁ የመጀመርያውን ቻት እናንተ መመለሾ ሳይጠበቅባችሁ automatically በራሱ መልስ እንዲስጥ የምታደርጉበት ነው። ይህን ፊቸር ለመጠቀም የምትፈልጉትን ፅሁፍ አስቀድማችሁ መሙላት አለባችሁ። ✅️Away message: ለተወሰነ ጊዜ online የማትገቡና ለሰዎች መልስ መስጠት የማትችሉ ከሆነ ሰዎች contact ሲያደርጓችሁ መልሲ እንዲሰጥላችሁ የፈለጋችሁትን መልዕክት መሙላት ትችላላችሁ። ✅️Links to chat: አዳዲስ ሰዎች ቴሌግራም ላይ contact እንዲያደርጓችሁ ፈልጋችሁ ነገር ግን ዩሰርኔማችሁን ወይም ስልክ ቁጥራችሁን መስጠት ካልፈለጋችሁ ምንም ችግር የለም ይህን ፊቸር መጠቀም ትችላላችሁ።  የተለያዩ ሊንኮችን በመፍጠርና ሊንኩን ለሰዎች share በማድረግ ዩሰርኔማችሁንና ስልክ ቁጥራችሁን መስጠት ሳይጠበቅባችሁ inbox እንዲያደርጉላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ። ✅️Custom Intro: ሰዎች ለመጀመርያ ጊዜ ሊፅፉላችሁ ቻቱን ሲከፍቱት የሚመጣውን ፅሁፍና sticker እንደተመቻችሁ edit ማድረግ ትችላላችሁ። ✅️ChatBots: ቦት ካላችሁ አካውንታችሁ ላይ በማካተት ለሰዎች automatically መልስ እንዲሰጥ ማድረግ ትችላላችሁ። ⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ 🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻 💡 | @Endre_Techs ÂŽ 2024 | ሁሉንም በእጅዎ!
Show all...
👍 1
🔰 በአለማችን ትልቁ ዲጂታል የጠፈር ካሜራ የሌሊት ሰማይን በበለጠ ለመቃኘት እና በከርሰ-ምድር ላይ ያሉ አስትሮይድስ ለመለየት ዝግጁ የሆነው የመጪው የቬራ ሩቢን ኦብዘርቫቶሪ ካሜራ ለእይታ በቅቷል። ይህ 3,200 ሜጋፒክስል አቅም ያለው ለሥነ ፈለግ ጥናት በዓለም ትልቁ ዲጂታል ካሜራ ሲሆን በቺሊ በሚገኘው ሩቢን ኦብዘርቫቶሪ ውስጥ ይገኛል። #space #digitalcamera #camera #tech #technews 📣 | @TechBamargna
Show all...
👍 3
⚡️⚡️ Telegram 🌐Telegram ክፍያ ሊጀምር ነው።🌐 ቴሌግራም ቻናሎች ላይ ማስታወቂያዎችን ማስተላለፍ ሊጀምር ነው። ከነዚህ ማስታወቂያዎች የሚገኘው ገቢም ለቻናል ባለቤቶች ግማሽ የሚያካፍል ይሆናል። ለማስታወቂያው ብቁ የሚሆኑ public ቻናሎች ሲሆኑ ቢያንስ 1000 ሰብስክራይበሮች ሊኖራቸው ይገባል። ክፍያው የሚፈፀመው በTON coin ሲሆን ያለምንም ክፍያ ወደ ton ዋሌታቸው መላክና ማውጣት እንደሚችሉ ተገልጿል። የቻናሉን monetization states የቻናሉ owner channel settings > Statistics > minitization ውስጥ ገብቶ ማየት ይቻላል። ለመመዝገብና የሰራነውን ገንዘብ ለማየት ✅1. fragment.com ላይ መግባት ✅2. Connect Telegram የሚለውን በመምረጥ telegram አካውንታችንን connect ማድረግ ✅3. Telegram Ads የሚል አዲስ የተጨመረ ምርጫ አለ እሱን በመንካት ማስታወቂያ ማስነገር ወይም በቻናላችን የሰራነውን ማውጣት እንችላለን። የማስታወቂያው አይነት ከሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች ለየት ያለ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል። ይህም ✔️ በuser data ላይ መሰረት አያደርግም። ✔️ቪዲዮና ረዘም ያለ ፅሁፍ አይኖረውም። ✔️ፕሪምየም ቴሌግራም ያለው ሰው እነዚህን ማስታወቂያዎች አያይም። ማስታወቂያ የሚተላለፍባቸው ቻናሎች እንደሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች የተለመደውን የኮፒራይት ህግን ማሟላት ይኖርባቸዋል። ✔️ ቻናሉ ላይ የሚተላለፈው original content መሆን አለበት። ❌ ከሌሎች ቻናሎች ወይም ሲሻል ሚዲያዎች ቀጥታ የተገለበጡ ኮንቴንቶች monetize አይሆኑም። ❌ ወሲብ ነክ ይዘት ያላቸው፣ የተሳሳተ መረጃና የጥላቻ ንግግር የሚያስተላልፉ ቻናሎችም ለማስታወቂያ ብቁ አይሆኑም። ✍️ምን ተሰማችሁ? ልክ እንደ ▶️Youtube ብዙ ሰው በቴሌግራም ህይወቱ የሚቀየር ይመስላችኋል? ⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ 🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻 💡 | @Endre_Techs ® 2024 | ሁሉንም በእጅዎ!
Show all...
👍 1