cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

𝐇𝐀𝐍𝐀𝐍 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐏𝐎𝐒𝐓

ረሱል ሰ.ዐ.ወ እንዲ ብለዋል "ዱኒያ አላህ ዘንድ የትንኝ ክንፍ ምታክል ቦታ ቢኖረው ኖሮ በአላህ የካዱ ሰዎች አንድ ጉንጭ ውሀ አይጎነጭም ነበር::" 📚ቲርሚዚ ዘግበውታል: 2320

Show more
Advertising posts
6 365
Subscribers
+1924 hours
+1297 days
+1 10230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
የትም ያልተነበበ ተከታታይ ታሪክ በቅርቡ ልንጀምር አስበናል። እንዲጀመር የምትፈልጉ like 👍 አርጉት 200 ሲገባ መለቀቅ ይጀምራል
Show all...
👍 43
ካጋጠመኝ አጠር ያለ አስተማሪ ታሪክ ስንቀለቀል ከሞተር ላይ ወድቄ ያቆሰልኩትን እጅ ቁስል ለመታጠብ ከአቅራቢያዬ ወዳለው አንድ ሆስፒታል ቁጭ ብዬ ተራዬን እየጠበኩ ሳለሁ... ከአጠገቤ ቆመው የሚያወሩትን ነርሶች ወሬ አዳምጣለሁ። " ኤሚ... ዛሬ ደግሞ አምሮብሻል ማሻአላህ " አለች አንዷ ነርስ ከሌላኛዋ ኋላ ከሩጫ በማይተናነስ እርምጃ ወደርሷ እየገሰገሰች " ሂኩዬ እንዴት አደርሽ " ብላ በለሰለሰ አንደበት መለሰችላት " ባክሽ ቲኒሽ አሞኛል እና ወደቤት እየገባሁ ነው... ሳላገኝሽ አልሄድም ብዬ ነው እና ደግሞ ከሰዓት ላይ እመለሳለሁ እስከዛ የኔን ቦታም ሸፍኚልኝ " " ችግር የለሁም ሀቢብቲ ግን ካመመሽ ወዴት ነው ምትሄጂው? እዚሁ መድሃኒት ወስደሽ እረፍት ብታደርጊ አይሻልም? " " ባክሽ ትልቅ ህመም አይደለም ድግሴ ተበላሽቶ ነው። " እኔ ደግሞ ግራ ተጋብቼ "ስለ ምን ድግስ ነው ልጅቷ የምታወራው መቼም ስለ ሀይድ አይሆንማ?.... ሃሃሃ አይ ሴቶች " እያልኩ በውስጤ አሰላስላለሁ " ኦው... እሺ በቃ ግቢ እኔ ሸፍንልሻለሁ " ብለው ተሳስቀው ተለያዩ.... እኔም የማይመለከተኝን ወሬ አዳምጬ ጨረስኩ። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ተራዬ ደርሶ ስሜ መጠራት ጀመረ " ሱፍያን አህመድ... ሱፍያን... " " አለው አለው " ብዬ ወደ ውስጥ ስዘልቅ ያቺ የቅድሟ ነርስ ነበረች ውስጥ ያለችው። ፈገግ ብላ " ተቀመጥ " አለችኝ እኔም ፈገግታዋ ተጋብቶብኝ ፈገግ እያልኩ ከወንበሩ አረፍኩ " ምን ሆነህ ነው እጅህን? " ከቁስሌ ላይ የተጠቀለለውን ፋሻ እየፈታች ያቀረበችልኝ ጥያቄ ነበር " Utalan male hin caban... ይላል ኦሮሞ " ብዬ ፈገግ አልኩ " ምን ማለት ነው " አለች ፈገግታዬ ተጋብቶባት ፈገግ እያለች " ያው ስቀብጥ ነው ከሞተር የወደኩት " " ኦው ያሳዝናል... ግን አብሽር ቁስልህ እየዳነ ነው " አለች ፋሻውን ፈታው ስታበቃ " ከአላህ በታች እንዳንቺ አይነት መልካም ነርሶች እያሉማ እንደኔ አይነቶቹ ቀበጥ ሰዎች ምንም አይሆኑም " ብዬ ልክ ከአፌ እንደጨረስኩ " ሰላም ዶክተር ኤሚ " አለ አንድ ሰው በሩን ከፍቶ.... " ወይኔ!!! " አልኩ ለካስ ዶክተር የሆነችዋን ሴት ነበር ነርስ ስል የቆየሁት ምኑ ደደብ ነኝ በአላህ... ሰላምታ ተለዋውጠው ሲያበቁ ሰውዬው ተሰናብቷት ሄደ እኔም እድሌን ተጠቅሜ መለፍለፌን ተያያዝኩት። " ለካስ ዶክተር ነሽ ነርስ መስለሽኝ ነበር " " ለምን ዶክተር አልመስልም እንዴ? " " ያው ብዙ የህክምና ባለሞያ ሴቶች ነርስ እንጂ ዶክተር አይደሉም ለዛ ነው " " እንግዲህ እኔ ዶክተር ነኝ ይሄ ነው እውነታው.... ደግሞኮ የአንደኛችንን ቦታ አንደኛችን መሸፈን እንችላለን ልክ አሁን እኔ የአንተን ቁስል በነርሶች ቦታ ሆኜ እያጠብኩ እንዳለሁት ማለት ነው ስለዚህ ብዙም ልዩነት የለንም " ቁስሌን ማጠብ ጀምራለች " እንደዛ ከሆነ አሪፍ..." አልኩ ለጥቂት ሰኮንዶች ዝምታ ሰፈነ ያው እኔ በተፈጥሮዬ ዝምታ ያመኛል አፌን ይበላኛልና ደግሜ መለፍለፌን ተያያዝኩት " ደግሞ ስምሽ ያምራል " " ነግሬህ ነበር እንዴ? " " አይ ቅድም ሰው ሲጠራሽ ሰምቼ... ኤሚ ነዋ ባልሳሳት " " አይደለም " ብላ ዳግም ፈገግ አለችልኝ " እና ማን ነው ታዲያ? " " ኤሚ የሚሉኝ አቆላምጠው ሲጠሩኝ or ደግሞ ስሜ ረጅም ስለሆነ አሳጥረው ሲጠሩኝ ነው። " " እና ስምሽን ማን ልበል ዶክተር...? " " አመተልሃፊዝ " " ማሻአላህ በጣም ቆንጆ ስም ነው? " " አመሰግናለሁ " ብላ ወደ መቀመጫዋ አመራች.... ለካስ እኔ ሳላስተውል ቁስሌን አጥባና አሽጋ ጨርሳ ነበር። ያው እንግዲህ እቺን የመሰለች ሴት ለማመቻቸት ድጋሚ እድል አላገኝም በሚለው " እና ስልክ ቁጥር እንቀያየር " አልኩ አይን አይኗን እየተመለከትኩ " ይቅርታ ባለትዳር ነኝ " አለች ከጣቷ ላይ ያጠለቀችውን ቀለበት እያሳየችኝ " ግንኮ አትመስይም.... ማለቴ ገና ልጅ ነው ምትመስይው " አልኩ ተገርሜ " አየህ ሁሉም ነገር እንደምናየው እና እንደምናስበው አይለም... በሁሉም ግልፅ ነገር ውስጥ የሆነ ድብቅና ስውር የሆነ ነገር ይኖራል። ለምሳሌ ስሜ አመተልሃፊዝ ሆኖ ሳለ ሌላ ሰዎች ኤሚ ብለው ስለጠሩኝ ብቻ አንተም ኤሚ ነው ስሟ ብለህ እራስህን አሳመንክ። ሲቀጥል ደግሞ ባለትዳር ሆኜ ሳለሁ እዲሁ ሁኔታዬን ብቻ ተመልክተህ እንዳላገባች ሴት አርገህ አሰብከኝ። ሌላው ትልቁ ስህተትህ ደግሞ ነጭ የለበሰች ሴት ሁሉ ነርስ ናት የሚል አስተሳሰብ በውስጥህ ስለቀረፅክ ዶክተር የሆንኩትን ሴት ነርስ አልከኝ። ደግሞኮ ነጭ ለባሽ ሁሉ የጤና ባለሞያ አይደለም... ነጭ በለበሰ ከሆነማ ስጋ ቆራጭም ነጭ ለባሽ አይደል እንዴ?.. ስኳር እና ጨውም ነጭ ናቸውኮ ግን ደግሞ ከምላስህ አቅርበህ እካላጣጣምካቸው ድረስ በአይን ብቻ አይተህ ይህ ስኳር ነው ይህ ደግሞ ጨው ነው ማለት አትችልም... እንዲሁ ሰዎችንም የውስጥ ማንነታቸውን ሳታውቅ ከላይ ባየህው ማንነትታቸው መለካት አትችልም። " ብላ ንግግሯን ቋጨች እኔም ለሰጠችኝ ማብራሪያ አመስግኜ ሌላ ቃል ሳልተነፍስ ከነ ክብሬ ተሰናብቺያት ወጣው። ዛሬ ካጋጠመኝ ክስተት የተማርኩት.... ሁሉም ነገር ከላይ እንደምናየው እንዳልሆነ ፣ ያየነው የሰማነው ነገር ሁሉ እውነት እንዳልሆነ እና አንድ አንድ ግልፅ መሳይ ነገሮች የተለየ ድብቅ እውነታን የያዙ መሆናቸውን ነው። ✍ ሂባ
Show all...
👍 36 2👏 2👌 1💯 1
Photo unavailableShow in Telegram
ማሪያ❤️ ማሪያ😊  የተሰኘዉን አጉዋጊ😱 አስተማሪ ልብ አንጠልጣይ😍 የ ፍቅር 🥰ታሪክ ልናስነብባችሁ ወደድን❤️ ታሪኩን ለማግኘት join ሚለዉን ንኩ👇👇
Show all...
join
ይቀላቀሉ🤗
ተስፋ አትቁረጪ... አንድ ቀን ያንቺ እናት እና አባት በስኬትሽ ምክንያት ፈገግ ይላሉ::😊 @hanan_islam
Show all...
24🥰 6🙏 4
ከዛሬ ጀምሮ ማለትም ቅዳሜና እሁድ የረሱል ሰ.ዐ.ወ እና የከድጃን የፍቅር ታሪክ እንጀምራለን ወደ ቻናሉ በመግባት ታሪኩን ማግኘት ትችላላችሁ
Show all...
ታሪኩን ለማንበብ ይጫኑ