cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

#ተዋህዶ ደጅሽ አይዘጋ

ኑ አብረን ተዋህዶ ሐመኖተችንን እናፅና የጠፈዉን እንፈልግ የገኛነዉን እሰብስብ የለዉን እናፅና ኑ አብረን ኦርቶዶክስን እናፅና ቤትኛዉም የአለመችን ክፍል ብንሆንም ኦርቶዶክስ እምነታችን አንድነት በዘር በቋንቋበቤሄር አትበተንም አትፈርስም ኑ በጋራ ሆነን ሒዱና አዘብን በአብ በወልድ መንፈስቅዱስ ሥም እየጠመቀችሁ ደቀመዘሙሬ አድርጓቻዉ የሚለዉን ቃል እንፈፅም ይሄ የተዋህዶ ሃመኖተችንድምፅነዉ

Show more
Advertising posts
277
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"በባልንጀራህ ላይ የምትቆጣ ከሆነ የአንተ ቁጣ በእግዚአብሔር ላይ ነው፡፡ በባልንጀራህ ላይ ቂምን በልብህ የያዝክ ከሆነ ቂምህ በጌታ ላይ ነው፡፡ ባልንጀራህን በከንቱ የምትቆጣው ከሆነ ኃጢአት በአንተ ላይ ይሰለጥንብሃል፡፡ ልብህን የፍቅር ማደሪያ ካደረከው በምድር ላይ አንዳች ጠላት አይኖርህም፡፡" ...✍ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
Show all...
ፈራሁ..😢 አዲስ ልብ የሚነካ ዝማሬ✞ 🔔 ዘማሪት በዛ ወርቅ አስፋው ቀኑ ከረፈደ ከመሸብኝ መጣሁ ደጃፍህ ላይ ቆምኩኝ እንዳልገባ ፈራሁ በደሌን ሳትመዝን ግቢ ብትልኝም ሀጥያቴ ከበደኝ አላራመደኝም /2/ የሰው እድሜ አጭር ነው ጥቂት ነው እንዴት ነው ሳላውቅህ ዘመኔ ያለቀው ጉብዝናዬን አለም ሲቃ ተጫወተብኝ እንዴት ብዬ ልርገጥ ደጅህን በድፍርት ፈራሁኝ ልግባ ወይ አልግባ እንዴት ይመዝናል ያንተ ደም በኔ እንባ እኔ ፈራሁ እንጂ አንተ እኮ አታስፈራም መምጣቴ ነው ደስታህ ፍቅርህ አይታማም ሽምቅቅ አለች ነፍሴ መስቀልህን ሳየው በደሌን አሰብኩት ደምህን እያየሁ ፈራሁኝ ልግባ ወይ አልግባ እንዴት ይመዝናል ያንተ ደም በኔ እንባ በንፅህና ፊት እንዴት እቆማለሁ እንደ መላእክቱ በምን ጋርዳለሁ እራሴን መሸፈኛ ክንፍ የለኝም እኔ ይታያል ሀጥያቴ የበደል እርቃኔ ፈራሁኝ ልግባ ወይ አልግባ እንዴት ይመዝናል ያንተ ደም በኔ እንባ ጠዋት እና ማታ ለመጣህ አንድ ነው አምሽቶም ለገባ እኩል ትከፍላለህ አብርሃም ወይ ይስሃቅ በድንኳንም ቢያድሩ በአንተ መንግስት ግን ከወንበዴ አይቀድሙም ፈራሁኝ ልግባ ወይ አልግባ እንዴት ይመዝናል ያንተ ደም በኔ እንባ ሼር🥺 @Maryam_Maryam2127 @Maryam_Maryam2127
Show all...
3
ሠላም እዴትነችሁ
Show all...
🙏 2
እኚህ በት ነበሩ እግዚአብሄር ይመሥግ ከክምና በኋላ በሠላም አጋግመዉ በጤና ተመልሰዋል
Show all...
6🙏 2👍 1
❝ የተባረከች አይን የእግዚሐብሔርን ቃል በማንበብ ትጠመዳለች፤የተባረከች ጆሮ የንስሀ መዝሙር በመስማት እራሷን ታንጻለች፤ የተባረከ ጉሮሮ ላይ የተቀደሰ ውሀ ይንቆረቆርበታል፤ የተባረከች ምላስ የአምላኳን ስጋና ደምን ትቀበላለች፤ የተባረከ አንደበት ላይ እግዚሐብሔር ይመስገን የሚል ቃል አይጠፋበትም፤ የተባረከች አንገት የአምልኮ ደም የፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል ትሸከማለች፤ የተባረከች ልብ ኢየሱስን እስከ እናቱ አንግሳ በፍቅር ትሞላለች፤ የተባረከች እጅ የቀረበላትን ምግብ በአምልኮ ስም ትባርካለች፤ የተባረከች እግር ጠዋትና ማታ የአምላኳን መቅደስ ትረግጣለች፤ ዘሌ 11:44 “እኔ እግዚሐብኤር አምላካቹ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ ቅዱስም ሁኑ እኔ ቅዱስ ነኝና” ❝ ሆዳችሁ ጠግቦ ከምታቀርቡት አንድ መቶ ጸሎትና ተራራ ከሚያርድ ድምጻችሁ ይልቅ በጾም ውስጥ ሆናችሁ የምታቀርቡት አንድ ጸሎት ተሰሚነት አለው። ❝ ጻዲቁ ዮሴፍ እጅግ ከባድ የሆነ ውጪያዊ ውጊያ ከጲጥፋራ ሚስት ቢገጥመውም አልወደቀም። እርሱ ኃጢአትን በልቡ ውስጥ ስላልተቀበለው ፈተናውንም አልተቀበለውም። ስለሆነም ጥቃቱን ሊቋቋም ችሏል። ዲያብሎስ አሳቦችን ያቀርብልሃል እንጅ ተቀብለህ ተግባራዊ እንድታደርጋቸው አያስገድድህም። ❝ ክፉ ሰው ክፋትን ለመስራት ደፍሮ ሲሄድ መልካም ሰው በጎ ነገር ለማድረግ ፈሪ ሆነ። ❝ ሞት እንዳለ አስታውስ፦ እንዲሁ በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ። “ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።” መክብብ 1፡14 ማለትን ትረዳለህ። ❝ አንተ ሐሳብህን ልትመራዉ እንጂ፤ ሐሳብህ አንተን ሊመራ ቦታ አትስጠዉ፥ እዉነተኛ ክርስቲያን ስሜቱ የሚመራዉ ሳይሆን ስሜቱን የሚወመራ ነዉ። ❝ ጨዋ ሰው በሌሎች ሰዎች መጎሳቆል ላይ የራሱን ምቾት አይገነባም እርሱ የሌሎችን ሰዎች ምቾት ለማደላደል የራሱን ምቾት ይረሳልና። ❝ ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች። ❝ ወንድሜ አንተ በመከራ ውስጥ ካለህ የዩናስን ዓሣ ነባሪ አስታውስ። ከፍራቻ ትገላገላለህ። መከራው እግዚአብሔር ጸጋውን ሊያበዛልህ ስለፈለገ ያዘጋጀው ዓሣ ነባሪ እንደሆነ የምታውቅበት ጊዜ ይመጣል። የዚህ ዓለም የባሕር ዓሣዎች ብዙ ስለሆኑ ስትዋጥ እንዳይከፋህ መጠንቀቅ ይኖርብሃል። የመጀመሪያው ባህታዊ ጻድቁ አባ ጳውሊ የተናገረውን መዘንጋት የለብህም "ከመከራ መራቅ የሚወድ ከእግዚአብሔር ይርቃል" ብሏል። በእውነት መከራ የጸሎት ትምህርት ቤት ነው። "በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ጮኽሁ እርሱም ሰማኝ። በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ። ቃሌንም አደመጠ" ዮናስ 2፥3 ❝ በንስሐ ሕይወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደር እና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም። ❝ ኃጢአት ከበጎ ነገር በተቃራኒ መስራት ብቻ አይደለም። በጎውን አውቆ አለመስራትም ኃጢአት ነው። ❝ በእግዚአብሔር ፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ፦ ያኔ ኃጢአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና። ❝ ሊቅ በሊቅነቱ ቢያስተምርህ ሊቅ ትሆናለህ ሊቅ በህይወቱ ቢያስተምርህ ግን ክርስቲያን ትሆናለህ። ❝ ከቅዱሱ ስፍራ ከቤተክርስቲያን በቅዳሴው፣ በትምህርቱ፣ ሚስጥራቱን ሁላ ተሳትፋችሁም ሆነ የግል ጸሎት አድርጋችሁ እንዲሁ በጎ ነገር ሰርታችሁ ስትጨርሱ ውስጣችሁን የደስታ፣ የእረፍት፣ የተስፋ፣ አንዳች ስሜት በውስጣችሁ ከተሰማችሁ እርሱ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ አስተውሉ። ❝ በዚህ ዓለም እንግዳ መሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ፦ ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ። ❝ ከዚህች ዓለም ምንም ነገር አልፈልግም፣ ዓለም ለመስጠት በጣም ድሃ ናትና። በዚህ አለም እንግዳ እንደሆንክ ሁልጊዜ አስተውል፣ ወደ ሰማያዊ ቤትህ ትመለሳለህ። ❝ ማንም ከእግዚአብሔር ትዕዛዛት የተለየ ነገር ቢነግርህ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ለካህናቱ አልቃ የተናገረውን መልስለት 'ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔርን እንታዘዛለን ❝ ኃጢአት ምን እንደሆነና ፍፃሜውንም ብታውቅ ትሸሸዋለህ! ❝ ሰው ኃጢአትን ጨርሶ ሲጠላ፣ ኃጢአትንም ሁሉ ሲተውና ከልቡናው ፈጽሞ ሲያጠፋው የልብ ንጽሕናን ያገኛል፡፡
Show all...
6👍 1
አልገህን ተሸክመህ ሂዲ ድነሃል
Show all...
የያዕቆብ መልእክት James 5 ምዕራፍ፡5፤ 1፤አኹንም፡እናንተ፡ባለጠጋዎች፥ስለሚደርስባችኹ፡ጭንቅ፡ዋይ፡ዋይ፡እያላችኹ፡አልቅሱ። 2፤ሀብታችኹ፡ተበላሽቷል፥ልብሳችኹም፡በብል፡ተበልቷል። 3፤ወርቃችኹም፡ብራችኹም፡ዝጓል፥ዝገቱም፡ምስክር፡ይኾንባችዃል፡ሥጋችኹንም፡እንደ፡እሳት፡ ይበላል።ለዃለኛው፡ቀን፡መዝገብን፡አከማችታችዃል። 4፤እንሆ፥ዕርሻችኹን፡ያጨዱት፡የሠራተኛዎች፡ደመ፡ወዝ፡በእናንተ፡ተቀምቶ፡ይጮኻል፥የዐጫጆችም፡ ድምፅ፡ወደ፡ጌታ፡ጸባኦት፡ዦሮ፡ገብቷል። 5፤በምድር፡ላይ፡ተቀማጥላችዃል፡በሴሰኝነትም፡ኖራችዃል፤ለዕርድ፡ቀን፡እንደሚያወፍር፡ልባችኹን፡ አወፍራችዃል። 6፤ጻድቁን፡ኰንናችኹታል፡ገድላችኹትማል፤እናንተን፡አይቃወምም። 7፤እንግዲህ፥ወንድሞች፡ሆይ፥ጌታ፡እስኪመጣ፡ድረስ፡ታገሡ።እንሆ፥ገበሬው፡የፊተኛውንና፡የዃለኛውን፡ ዝናብ፡እስኪቀበል፡ድረስ፡ርሱን፡እየታገሠ፡የከበረውን፡የመሬት፡ፍሬ፡ይጠብቃል። 8፤እናንተ፡ደግሞ፡ታገሡ፥ልባችኹንም፡አጽኑ፤የጌታ፡መምጣት፡ቀርቧልና። 9፤ወንድሞች፡ሆይ፥እንዳይፈረድባችኹ፡ርስ፡በርሳችኹ፡አታጕረምርሙ፤እንሆ፥ፈራጅ፡በደጅ፡ፊት፡ቆሟል። 10፤ወንድሞች፡ሆይ፥የመከራና፡የትዕግሥት፡ምሳሌ፡የኾኑትን፡በጌታ፡ስም፡የተናገሩትን፡ነቢያትን፡ ተመልከቱ። 11፤እንሆ፥በትዕግሥት፡የጸኑትን፡ብፁዓን፡እንላቸዋለን፤ኢዮብ፡እንደ፡ታገሠ፡ሰምታችዃል፥ጌታም፡እንደ፡ ፈጸመለት፡አይታችዃል፤ጌታ፡እጅግ፡የሚምር፡የሚራራም፡ነውና። 12፤ከዅሉም፡በፊት፥ወንድሞቼ፡ሆይ፥በሰማይ፡ቢኾን፡በምድርም፡ቢኾን፡በሌላ፡መሐላም፡ቢኾን፡በምንም፡ አትማሉ፤ነገር፡ግን፥ከፍርድ፡በታች፡እንዳትወድቁ፡ነገራችኹ፡አዎን፡ቢኾን፡አዎን፡ይኹን፥አይደለምም፡ ቢኾን፡አይደለም፡ይኹን። 13፤ከእናንተ፡መከራን፡የሚቀበል፡ማንም፡ቢኖር፡ርሱ፡ይጸልይ፤ደስ፡የሚለውም፡ማንም፡ቢኖር፡ርሱ፡ ይዘምር። 14፤ከእናንተ፡የታመመ፡ማንም፡ቢኖር፡የቤተ፡ክርስቲያንን፡ሽማግሌዎች፡ወደ፡ርሱ፡ይጥራ፤በጌታም፡ስም፡ ርሱን፡ዘይት፡ቀብተው፡ይጸልዩለት። 15፤የእምነትም፡ጸሎት፡ድውዩን፡ያድናል፡ጌታም፡ያስነሣዋል፤ኀጢአትንም፡ሠርቶ፡እንደ፡ኾነ፡ይሰረይለታል። 16፤ርስ፡በርሳችኹ፡በኀጢአታችኹ፡ተናዘዙ።ትፈወሱም፡ዘንድ፡እያንዳንዱ፡ስለ፡ሌላው፡ይጸልይ፤የጻድቅ፡ ሰው፡ጸሎት፡በሥራዋ፡እጅግ፡ኀይል፡ታደርጋለች። 17፤ኤልያስ፡እንደ፡እኛ፡የኾነ፡ሰው፡ነበረ፥ዝናብም፡እንዳይዘንብ፡አጥብቆ፡ጸለየ፥በምድርም፡ላይ፡ሦስት፡ ዓመት፡ከስድስት፡ወር፡አልዘነበም፤ኹለተኛም፡ጸለየ፥ 18፤ሰማዩም፡ዝናብን፡ሰጠ፡ምድሪቱም፡ፍሬዋን፡አበቀለች። 19፤ወንድሞቼ፡ሆይ፥ከእናንተ፡ማንም፡ከእውነት፡ቢስት፡አንዱም፡ቢመልሰው፥ 20፤ኀጢአተኛን፡ከተሳሳተበት፡መንገድ፡የሚመልሰው፡ነፍሱን፡ከሞት፡እንዲያድን፥የኀጢአትንም፡ብዛት፡ እንዲሸፍን፡ይወቅ፨
Show all...
2👍 1