cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ማንበብ ህይወት ነው 🤼‍♂️📕

ሰላም 🤚 - 📯 📯  እንኳን በደህና መጡ!  📯 📯 በዚህ ቦት አማካኝነት https://t.me/hopereding ➡️.  ትረካዎችን 🎙 ➡️.  ልቦለዶችን 📖 ➡️.  ኢ-ልቦለዶችን 📕 ➡️.  መፅሐፍትን በpdf 📚 ➡️.  ግጥሞችን 📝 ➡️.  አጫጭር ትረካዎችን 🎙 ➡️.  የመፅሐፍ ቻናሎችን 📌 ያገኛሉ። አስተማሪና አነቃቅ ንግግሮች ከተለያዩ መፅሐፎች ▫️ቦቱን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ

Show more
Advertising posts
216
Subscribers
No data24 hours
-27 days
+230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🙏#ሠላም_ለዕናንተ_ይሁን__ቀዳሜ📖🙏 • …"በሰፊው መስታውት ወደፊት እያየን ከመጓዝ ይልቅ በጠባቧ የኋላ መስታውት አብዝተን እያየን ከኋላ ታሪካችን ጋር ግብግብ ገጥመን ከፊት ለፊት ያለውን ተስፋችንን ለማጨለም እንዳክራለን። ትንሽ የሄድን ሲመስለን ተንገራግጨን እንቆማለን ወይ ወደ ኋላ እንመለሳለን። የሠራነውን እናፈርሳለን፣ የገነባነውን እንንዳለን፣ ቁመን ያጨበጨብንለትን ቁጭ ብለን ለማየት እንጠየፋለን። በጭፍን እንደግፋለን፣ በደምሳሳው እንቃወማለን፣ ሰውን ወይ መልኣክ አለበለዚያ ሠይጣን እናደርጋለን። ሚዛናችንን ስተን እንገዳገዳለን። ከአንድ ሙሉ ሰው ብልቶች ውስጥ ከዐይን ጆሮን አቅርበን፣ ከእግር እጅን አስበልጠን አድልዎ እንፈጽማለን። ከተወለድንበት መንደር ማዶ ካለው ጋራ ወዲያ ያለውን ሰፊ ሐገርና ወገን መዋጀት አቅቶን ድክ ድክ እንላለን።…" • #ምንጭ:- "ዝጎራ" በዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር) ገጽ-41 • #ፍቅር_ያሸንፋል! #እውቀት_ነፃ_ያወጣል! • 📚#በማንበባችን_እጥፍ_ብናተርፍ_እንጂ_ከቶ_አንከስርበትም!📚 • 🙏#መልካም_ሠናይ_ምሽት 🌃!🙏 https://t.me/hopereding
Show all...
ማንበብ ህይወት ነው 🤼‍♂️📕

ሰላም 🤚 - 📯 📯  እንኳን በደህና መጡ!  📯 📯 በዚህ ቦት አማካኝነት

https://t.me/hopereding

➡️.  ትረካዎችን 🎙 ➡️.  ልቦለዶችን 📖 ➡️.  ኢ-ልቦለዶችን 📕 ➡️.  መፅሐፍትን በpdf 📚 ➡️.  ግጥሞችን 📝 ➡️.  አጫጭር ትረካዎችን 🎙 ➡️.  የመፅሐፍ ቻናሎችን 📌 ያገኛሉ። አስተማሪና አነቃቅ ንግግሮች ከተለያዩ መፅሐፎች ▫️ቦቱን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ

የፍቅሬ ጅማሬ 1 ክፍል     ጊዜው ጠዋት ነው ገና በማለዳ ፀሐዩ ቀኑን ቀትር አሥመስሎታል ሀይ ስሜ ቤዛ ይባላል የ አዳማ ዩንቨርስቲ የ ሁለተኛ አመት የ ኢንጅነሪንግ ተማሪ ነኝ                   ቤዚ....ቤዚ ተነሽ በጌታ ዛሬኮ የሀይሚ ልደት ነው አንቺ ቤዛ የሚል ጥሪ ነበር ከእንቅልፌ ያነቃኝ ሀዊን ተዋወቋት እሷም እንደኔ የ ሁለተኛ አመት ተማሪ ናት  እኔ ሀይሚ እና ሀዊ ከጓደኛም በላይ እህታሞች ሆነናል እና ዛሬ ለ ሀይሚ ልደት ሥጦታ ልንገዛ ልንወጣ ነው   "ስሚ ቤዚ ያለን ብር አራት መቶ ብቻ ነው እሽ በዚ ብር ምን እንደምንገዛ እናያለን"የብሩ ትንሽነት ያሣሠባት ሀዊ በንዴት ጦፋ ነበር ያለችው ስጦታውን ለመግዛት ፍራክኮ በሚል ታክሲ ውሥጥ ገብተናል ሀዊ ጥሎባት ጋቢና መቀመጥ ትወዳለች እኔ ደሞ በተቃራኒው በዛ ብር ምን እንደምንገዛ እያሠብኩ ነበር"ይቅርታ ትንሽ ጠጋ ቲ"የሚል ድምፅ የሰማሁት ጠይም እና የደሥ ደሥ ያለው ልጅ ፈገግ ብሎ በድጋሚ "sorry"አይ ችግር የለውም ብዬ ተጠጋሁ ፊቱ ግን አዲሥ አልሆነብኝም "ግን አቅሻለሁ ልበል "አው እኔም የሆነ ቦታ ማቅህ ይመሥለኛል "ይሆናል ማቲዎስ እባላለሁ ግን ማቲ ብለሽ ብጠሪኝ ደስ ይለኛል"ቤዛዊት "እሺ ቤዛ የት እንደማውቅሽ አስታወሥኩ የጊቢ ተማሪ ነሽ አይደል "አው አንተሥ "እኔም የጊቢ ተማሪ ነኝ እዛ ነው ማለት ነው የምንተዋወቀው "አይኔን ከጥርሱ ላይ ማንሳት አቃተኝ ፈገግታው ልብ ይማርካል ሳላውቀው ፍራንኮ ደርሠናል ወርደን ከሀዊ ጋ መንገድ ሥንጀምር "ሀዊ "የሚል ድምፅ ሠማሁ "አቤት"ብላ ሀዊ ዞረች ማለት ቤዚ ስልክችን አልሠጠሽኝም ገና ተናግሮ ሣይጨርሥ ሀዊ"09........" የሷ ነው ደውልላት ብላው ተለያየን የሆነ የደሥታ ሥሜት እየተሠማኝ ነው "አንቺ የማን ሸበላ ነው"አንቺን አይደል እንዴ ማናግረው የት ነው ምታውቂው የሀዊ ተከታታይ ጥያቄዎች ነበሩ ጊዜው መሽቷል ሁላችንም ዶርም ውስጥ ተሰባስበናል ሀይሚ ሥጦታዋን በመክፈት ላይ እያለች ነበር ድንገት ሥልኬ የጮኸው ሄሎ "ሄሎ ቤዛ ነሽ"........             ይቀጥላl   https://t.me/hopereding
Show all...

👍 1
ይህ የምታዩት የቤልጂየምና የኔዘርላንድ ድንበር ነው! ከመስመሮቹ ወደዚህ ቤልጂየም ከመስመሮቸቹ ወደዛ ደግሞ ኔዘርላንድ! ወታደር የለም! ታንክ የለም! መትረየስ የለም! ... የሰው ልጅ እንዲህ ሰልጥኖ ድንበሩን በነጭ ቀለም ብቻ በሚያሰምርበት በዚህ ዘመን አንተ እገሌ ከክለሌ ይውጣልኝ እያልክ ከገዛ ወንድምህ ጋር በገጀራ ስትከታከት ትውላለህ! ዓለም ጥሎህ ሄዷል ወዳጄ!! በ 👉 https://t.me/hopereding
Show all...
👍 2
የጭን qus ሙሉ በሙሉ እውነተኛታሪክ የብዙዎቹን ጓዳ የሚፈትሸ፣ በቀላሉ የማይረሳ፣ አሳዛኝና ልብ ሰቃይ ታሪክ በተክሉ ጥላሁን
Show all...
2
'''የፍቅሬ ጀማሬ ''''ምርጥ በጣም ደስ የሚል ... ኣጥር ያለ  ኣሰተማሬ ዛሬ የጀምራል..
Show all...
​​መቀራረብ ጀመርን ጓደኝነታችን እየጠበቀ መጣ  ብዙ ምክሮችን ትመክረኝ ነበር እያለ ናዲ ታሪኩን በሰፊው አጫወተኝ እንዴት ሰሙ እሱን እየመከረች እንዳስተካከላችው ምናምን ሁሉንም ታሪክ አንድም ሳይቀር አጫወተኝ ለሰአታትት ሳይደክመው አወራኝ እኔም በጣም ተመስጬ ሳልሰለች እየሰማሁት ነበር። እንዴት የተበላሸ ማንነቱን አስተካክሎ ከቀድሞ የበላጠ ጠንካራ እንደሆነ እንዴት በሁለት ዲግሪ  ትምህርቱን በማእረግ እንደጨረሰና ከነሰሙና ኤቤጊያ ጋር አንድላይ እንደተመረቁ እንዴት ቤተክርስቲያ ቀለብት እንዳሰረላት እና እንደተጋቡ  በቅርቡ እፁዬን እንደወለዱ በሰፊው አጫወተኝ  በጣም ደስ አለኝ ታሪኩ ከጠበቅኩት በላይ አስተምሮኛል ናዲ እውነት ፍቅርን፣ የራስ ማንነት ጥንካሬን፣ ከምንም በላይ ደግሞ ይቅርታንና መልካምነት አስተማርከኝ አልኩት። ደስ ብሎኛል ስላስተማረክ ህይወት እንዲህ ናት እንግዲ  ብዙ ውጣ ውረድ ቢኖራትም ፈተናዋን ስታልፍ ሽልማቷ ብዙ ነው አለኝ ከውጪ በር ተንኳኳ.... ናዲ እጁ ላይ ያለውን ሰአት አየት አደረገና ኦ.... ምሳ ሰአት ደርሷል ሰሙ ናት መሰለኝ አለና ከመቀመጫው ተነስቶ በር ሊከፍት ሄደ። የሳሎኑ መጋረጃ ስስ ስለነበር ውጪ ያለውን ክዋኔ በደምብ ያሳያል ናኦል በሩን ሲከፍተው አንዲት ዝንጥ ያለች ሴት ወደውስጥ ገብታ ጥምጥም አለችበት ፍቅር.... ብላ ከንፈሩን ሳመችው ሰምሃል እንደሆነች አልተጠራጠርኩም ነበር ከውስጥ ሆኜ ሁኔታቸውን አይቼ ፈገግ አልኩና ወደኮርኒሱ አንጋጥጬ አምላክ አንድ ቀን እንዲህ ለኔም..... አልኩና ተመለስኩ ሰምሃልና ናኦድ እንደተቃቀፉ ወደ ቤት ገቡ ልክ ሳሎኑ ጋር ጫማዋን አውልቃ ስትገባ ከሰሙ ጋር አይን ለአይን ተገጣጠምን ረሙ ያገሬ... ልጅ አለችኝ ሰሙዬ ብዬ ተነሳውና ተቃቀፍን። ሰምሃል ማለት ናዝሬት ሃይስኩል እማቃት በእድሜና በክፍል ትንሽ እምትበልጠኝ ጓደኛዬ ናት ቤተሰቦቿ ወደ አዲስ አበባ ጠቅልለው እስኪገቡ ድረስ የቅርብ ጒደኛሞች ነበርን እዚ ከገቡ በኃላ ግን ለረጅም ግዜ ተራረቀን በናኦድ ምክንያት ዳግም ተገናኘን የአጋጣሚ ነገር ይገርማል። እንዴት ነሽ ባክሽ ሰሙ ወፍረሻል ይሄ ትዳር ተመችቶሻል አይደል አልኳት እየሳቀች ኣው ባክህ ምን እናድርግ ብለህ ነው አላችኝ። እፁ ከእንቅልፏ ተነሳች መሰለኝ ማልቀስ ጀመረች ሰሙ የእናት አንጀት ሆኖባት እኔን ልጄ እኔን ልጄ መጥቼልሻለው መጥቼልሻለው እያለች በፍጥነት ወደመኝታ ክፍል ገባች። ኤቤጊያም የእፁን ድምፅ ሰምታ ነው መሰል እየሮጠች መጥታ መኝታ ክፍል ገባች። ሰሙና አቢጊ ለሁለት እፁን እያባበሏት ይዘዋት ወደሳሎን መጡ ሰሙ አቢጊን እያየቻት እጡዬ ኔኔ ማል አክትሽ አቢጊ በደም ተንተባተበትሻ አለቻት ጥፍጥ ባለ በኮልታፋ የህፃን አንደበት። አቢጊ እኔ የክርስትና እናቷ እያለውማ ምን ትሆናለች በደምብ አድርጌ ነው የምይዛት አለች የእፁን እጅ እየሳመች። ሁኔታቸውን ሳይ አስቀናኝ ያንን ሁሉ ግዜ አልፈው አሁን ላይ ለዚ በቅተዋል ደስ ይላል። ናዲ ከሰሙ እጅ ላይ እፁን ተቀበላትና ፍቅር ታጣጥበሽ ነይና ምሳ እንብላ አላትና ወደ አቢጊ ዞሮ አክስት ተብዬዋ ምሳ ደርሷል አይደል አላት አው ላቀራርብ እንደውም ብላ ሄደች። ናዲ እኔን ፍፁም እረስቶኝ ከእፁ ጋር ጨዋታ ጀመረ.... አይ የልጅ ፍቅር! አልኩ በልቤ። ምሳ  ቀራርቦ ከበላን በኃላ ሰሙ ቡና አፍልታ መጨዋወት ጀመርን በመሃል ናዲ ስልኩላይ ያለውን ሰአት አየና እንዴ ኪያር አይመጣም እንዴ ቆየ አለና ደወለለት ስልኩን ስፒከር ላይ አድርጎት ነበር። ምናባክ ነው ምትጨቀጭቀኝ በር ላይ ደርሻለው ክፈት አለው ናኦድ እየሳቀ ሄዶ ከፈተለት ተያይዘው ገቡ ኪያር መጥቶ በአንዴ ቤቱን ሞቅ አደረገው! ከሰአቱን ከነሰሙና ናዲ ጋር ስጫወት አመሸው አራቱም በእድሜም ሆነ በሌላም ነገር ከኔ ይበልጣሉ ታላላቆቼ ናቸው በዛች እለት ናዲ በነገረኝ ታሪክ እና እኔም ባየሁት እውነታ ብዙ ነገር ተማርኩ! ሁሉም ያላቸው ወዳጅነትና ፍቅር በጣም ያስቀናል እኔም እንደነሱ ብሆን ብዬ ተመኘው። ግዜው እየመሸ ደንገዝገዝ ብሎ ለአይን ያዝ ማድረግ ሲጀምር እኔ ለመሄድ ተነሳው ሰሙ ቅር እያላት ልትሄድ ነው አታድርም አለችኝ አይ መሄድ አለብኝ ይቅርታ ሰሙ ባይሆን ሌላ ግዜ አድራለው አልኳት እሺ በቃ ካልክ ምን ይደረጋል አለችኝና ተሰናበትኳት ኪያርና ኤቤጊያንም ተሰናበትኳቸው እነሱ ትንሽ ይቆዩ ነበር። ከናኦድ ጋር ትንሽ ሊሸኘኝ አብረን ወጣን ከቤት እንደወጣን ወደ ታክሲ መያዣው ቦታ እየሸኘኝ እያለ ናኦድ ዛሬ ቤትህ ስለጠራኀኝ በጣም ደስ ብሎኛል ብዙ ነገር ነው ያስተማራችሁኝ አልኩ። አው ቅድም እኮ ያው በደምብ ሳልመክርህ  ሁሉም ተሰባሰበ ደስ ስላለህ እኔም ደስ ብሎኛል አየህ አይደል ፈተናህን ታግለህ ስታሸንፍ ደስታህን ትሰጥሃለች ሁሌም ጠንካራ ማንነት እና ቅን ልቦና ይኑርህ ሁሉን ታሸንፋለህ የሚበድሉህን ይቅር በላቸው ባለማወቅ በድለውህ ሊሆን ይችላል ግን ሰው ይቀየራል ሁሌም አንድ ቦታ ላይ አታገኘውም መልካምነትና ይቅርታን በልብህ ሁሌም አኑራቸው ጥለው ኣይጥሉህም እህቴ ናሆሚ ስላንተ ብዙ ነገር ነግራኛላች ለሷ ያደረክላትን ነገር በሙሉ አውቃለው ለዛም አመሰግንሃለው አስተዋይ ልጅ ነህ ብዙ ምክር አላብዛብህ አለኝ እየሳቅኩ አረ ናዲ እንደውም ብትጨምርልኝ ደስ ይለኛል እንዲ ስለህይወር እሚያስተምረኝና እሚመክረኝ ሰው ነው እምፈልገው አልኩት እሺ ብዙ እምናውራቸው ነገሮች ይኖራሉ ወደፊት አለኝ። ቦሌ... ቦሌ ቦሌ ቦሌ አለ አንድ ወያላ የታክሲውን በር እየከፈተ። ከናዲ ጋር መሰነባባት ጀመርን ስለመከረኝና ስላስተማረኝ ነገር ሁሉ ከልብ ኣመስግኜው እና ሌላም ግዜ እንዲጨምርልኝ ነግሬው ቻው ተባብለን ታክሲው ውስጥ ገባው። ጋቢናው ውስጥ ከሹፌሩ ጋር ብቻዬን ስለነበርኩ በሃሳብ ማእበል እየተናጥኩ ናኦድ የነገረኝን ታሪክ አሰብኩና ተገረምኩ ይገርማል የሰው ልጅ እንደመፅሃፍ ገልጠው እስካላነበቡት ድረስ ማወቅ አይቻልም ምን ቀን ከናኦድ ጋር እንደተዋወቅን ለማስታወስ ሞከርኩ...። ናኦድ ግቢ እያለው ከአርክ ውጪ ሌላ  ትምህርትም እድማር  መንፈሳዊ ቅናት ያሳደረብኝ  ልጅ ነው እኔም እሱ በአንዴ ሁለት ዲግሪ ስይዝ አቀናኝ እኔም በሱ ፈለግ ተከተልኩ።  ይሄ ታሪክ መፃፍ አለበት እኔ እንደተማርኩበት ብዙ ሰው ይማርበታል  አልኩ በልቤ  እፅፈዋለው! ስልኬን ኣወጣው አዲስ ኖት ከፈትኩና ትንሽ ማሰላሰል ጀመርኩ ...መጣልኝ!!!! ከላይ ርእሱን "ሞሮ" አልኩት ክፍል አንድ ......ታክሲው እየሄደ መፃፌን ቀጠልኩ። እነሆ አንድ ብልህ አስተዋይ ወዳጄ የነገረኝ የግል ታሪኩን እኔ እንደተማርኩበት እናንተም ትማሩበት ዘንድ ፃፍኩላችው ሞሮ ተፈፀመ ፍቅር ከበቀልና ጥላቻ በላይ ናት የፅድቅ ሁሉ ፍፃሜም ፍቅር ናት ፍቅር ለዘልአለም ትኑር በመፅሃፍ መልክ ታትሞ በሰፊው ተስተካክሎና ሌሎች ያልተፃፉ ታሪኮችም ተፅፈውበት ዳግም በመፅሃፉ እንገናኝ    ┈•✿•˚•❀•˚•✿•˚•❀•˚•✿•˚•✿•┈ ✥┈┈┈┈┈••◉ተፈፀመ◉●••┈┈┈┈┈✥ እንግዲ ሞሮ እዚ ላይ ቢያልቅም በመፅሃፍነት ታትሞ ሲወጣ ብዙ ያልተፃፉ ታሪኮች ተጨምረውበት ይመለሳል። https://t.me/hopereding
Show all...
ማንበብ ህይወት ነው 🤼‍♂️📕

ሰላም 🤚 - 📯 📯  እንኳን በደህና መጡ!  📯 📯 በዚህ ቦት አማካኝነት

https://t.me/hopereding

➡️.  ትረካዎችን 🎙 ➡️.  ልቦለዶችን 📖 ➡️.  ኢ-ልቦለዶችን 📕 ➡️.  መፅሐፍትን በpdf 📚 ➡️.  ግጥሞችን 📝 ➡️.  አጫጭር ትረካዎችን 🎙 ➡️.  የመፅሐፍ ቻናሎችን 📌 ያገኛሉ። አስተማሪና አነቃቅ ንግግሮች ከተለያዩ መፅሐፎች ▫️ቦቱን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ

​​💓💓💓💓💓 💓 💓💓💓💓💓 💓💓💓💓💓ሞሮ 💓💓💓💓💓 💓💓💓💓    ፍፃሜ     💓💓💓💓 💓💓💓💓💓 💓  💓💓💓💓💓 https://t.me/hopereding ፀሃፊው ነኝ .... ከጥቂት ወራት በፊት በአንደኛው እለተሰንበት በእድሜ የሚበልጠኝ አንድ ጓደኛዬ ሲአምሲ አከባቢ ከሚገኘው ቤቱ እንደመጣ ጋበዘኝ እናንተ "ናኦድ" በሚለው ለፅሁፍ እንዲያመች በተቀየረው ስሙ ታውቁታላችው። እናም ግብዣውን ተቀብዬ ቤቱ ሄድኩ  ወደቤቱ እየገባን እያለ አዲሱ ትዳር እንዴት ይዞሃል አልኩት በፈገግታ እሱም እየሳቀ አሪፍ ነው በልጄም በሚስቴም ደስተኛ ነኝ አለኝ አሪፍ ነው አልኩት። እንደለመደብኝ አዲስ ቦታ ስሄድ እንደማደርገው በአርክቴክት አይኔ ቤቱን ቃኘሁት ደስ ይላል ቀለል ያለ ኮተታኮተት ያልበዛበት የባለትዳር ቤት ይመስላል።  ልክ ሳሎን ውስጥ እንደተቀመጥን ከመኝታ ቤት አንዲት ሴት ወጣች  እንዴ... አቢጊ ብዬ አቀፍኳት ረጅም ግዜ ሆኖኝ ነበር ካገኘኃት ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጠኃት ናኦድን ሰላም ልትለው ስትል ከመኝታ ቤት የህፃን ልጅ ለቅሶ ሰማን ኤቤጊያ ውይ እፁዬ አለቀሰች ብላ እየሮጠች ወደመኝታቤት ተመለሰች ናኦድም ተከትሏት ሄደ። ትንሽ ከቆየ በኃላ ትንሿ በጣም እምታምረው ልጁን ይዟት ወጣ ብዙ ግዜ እኔ ህፃናት ብዙም አይመቹኝም ግን እፁብን እንዳየኃት ውድድድ አደረኳት እንዴት እንደምታምር ቀይ ድንቡሽቡሽ ልጅ ሉጫ ፀጉር ትልልቅ አይን ያላት ቆንጅዬ ልእልት ናት እፁብ። ከሶፋው ላይ ተነሳውና ወደናኦድ ተጠጋው ናዲ እምታምር ልጅ አለህ በጣም ነው ምታምረው አልኩና ግንባሯን በስሱ ሳምኳት አው ባክህ ቆንጅዬ ልእልት ናት ትንሽ እንቅልፏ ሲመጣ ለቅሶዋ መከራ ነው እንጂ አለኝ ህፃኗን እፁብ እሹሩሩ እያለ እንግዲ እኔ ስለህፃናት እማውቀው ነገር የለም አልኩት እየሳቀ ባክህ አንተም አግብተህ ስትወልድ ታየዋለህ አለኝ እኔም እየሳቅኩ ኡ.... ገና አልኩት። እፁብ ማልቀስ ስትጀምር እያባበላት ወደመኝታ ቤት ይዟት ሄደና ለአቢጊ ሰጥቷት ተመለሰ። እሺ እስራኤል እና ደህና ነህ ተጠፋፋን አይደል ያው ታውቀዋለህ ትዳር ስራ ምናምን ሲደራረብ አሁን ደግሞ እፁዬ መጥታለች ተጠፋፋን አለኝ አው ተጠፋፋን አልኩትና ከመቀመጫዬ ዳግም ተነሳውና ፊትለፊቴ ወዳለው ግርግዳ ሄድኩ የናዲ እና የሚስቱ የሰርግ ፎቶ በትልቁ በፍሬም ታሰቅሏል ባዶ ቦታዎቻቸው ላይ በወርቃማ እስክርቢቶ የወዳጅ ዘመዶቻቸው መልካም ምኞት አውቶግራፍ ተሞልቷል አይኔን አጥብቤ የተወሰኑትን ለማንበብ ሞከርኩ ደስ ይላሉ። ወደ ናኦድ እየዞርኩ ሳቅ ብዬ ለሰርጋቹ ግን ሳትጠሩኝ በጣም ታዝቢያቹሃለው አልኩት ናዲም እየሳቀ እኛማ ጠርተንህ ነበር አንተ አልመጣም አልክ እንጂ አለኝ። እና መቀሌ ነበርኳ ግቢ የእህቴን ሰርግ እራሱ አንድ ቀን ቆይቼ ነው የተመለስኩት ምናለ ለእረፍት እስከምንመለስ ብትጠብቁኝ እንኳን አንድ ብሬ ብጨርስ ነው አልኩት እየሳቅኩ ናዲም እየሳቀ አይ ረም ዘንድሮም ትኮምካለህ አ አለኝ እየሳቅኩ የቴሌቭዥኑ ስታንድ ጋር ሄጄ እዛ ላይ  በፍሬም የተቀመጡትን ፎቶዎች እያነሳው ማየት ጀመርኩ ካሉት ውስጥ  የምርቃታቸውን ፎቶ በእጄ አንስቼ አየሁት ናዲ መሃል ሆኖ ሰምሃል እና ኤቤጊያ በጎና በጎን ሆነው የተነሱት ፎቶ ነበር ወደናዲ እየዞርኩ ይሄ ፎቶዋቹ ደስ ይላል አልኩት። አውው... ባክህ ጥሩ ትውስታ ነው ግዜው ይሮጣል አይደል ከተመረቅን እንኳን አራት አመት ሆነን አይ ግዜዜዜ.... አለና ትንሽ በሃሳብ ሰመመን ሄደ። እኔ ፎቶዎቹን እያነሳው አይቼ ስጨርስ አስቀምጥና ሌላ አንስቼ ማየት ጀምራለው። ናዲ እንዳጎነበሰ ሲያስብ ከቆየ በኃላ ረምሃይ ብሎ ጠራኝ እእእ ናዲ አልኩት። እስኪ ና ቁጭ በል ስለ ግቢ አንድ ታሪክ ልንገርህ አንተ አስተዋይ እንደሆንክ አውቃለው ናሆሚም ነግራኛላች ግን ምናልባት እምትማርበት ነገር ይኖራል አለኝ እኔም ሄጄ አጠገቡ ተቀመጥኩ። ትንሽ አጎንብሶ ግንባሩን እያሸ  ካሰላሰለ በኃላ ታውቃለህ ግቢ እያለው ብዙ ትዝታ ነበረኝ ብዙዎቹ መጥፎና አሳዛኝ ቢሆኑም በዛው ልክ ደግሞ ክፉውን ግዜ የሚያስረሱ ጥሩ ትዝታዎችና ምርጥ ጓደኞች ነበሩኝ። ግቢ ፍሬሽማን እና ሁለተኛ አመት ላይ በጣም ጎበዝ ተማሪ ቀለሜ ነበርኩ ብዙ ደሳስ እሚሉ ጓደኞች ነበሩኝ። ደስ የሚል ጊዜ እናሳልፍ ነበር በአስተማሪዎቼም ተወዳጅ ተማሪ ነበርኩ ግን ህይወት ልታስተምርህ ስትፈልግ ከፊትህ ፈተና ማስቀመጥ ትጀምራለች ልክ 2004 ሶስተኛ አመት እንደገባን አንዲት ሴት በፍቅር አንባረከከችኝ ሲለኝ በዚያው  ቅፅበት ኤቤጊያ ከመኝታ ክፍሉ ቀስ ብላ እያተራመደች ወደኛ ጠጋ ብላ እፁ ተኝታለች  ቀስ ብላችው ተጫወቱ እኔ ሰሙ ሳትመጣ ምሳ ልሰራራ ብላን በእግሮቿ ጣት ብቻ ቀስ ብላ እየተራመደች ከሳሎን ሄደች። ናዲ ወደኔ እያየ በእጁ አቢጊ ወደወጣችበት በር እየጠቆመ ያቺ በፍቅር ያንበረከከችኝ  ሴት አቢጊ ነበረች አለኝ በአግራሞት ምን!? አልኩት አው አቢጊ በጣም ቆንጅዬ ቀበጥባጣ ልጅ ነበረች ያኔ አሁን እንደምታያየት የተረጋጋች አልነበረችም እና ስለሷ ሳስብ  ስለሷ ሳልም ትምህርቴን እረሳው ያኔ ፍቅሯ ልቤን አውሮት በጣም እፈራት ነበር  ገና ከርቀት ሳያት መንገዴን እቀይራለ ጓደኞቼ ሁኔታዬን እያዩ ይስቁብኝ ነበር ግዜያት እየተቆጠሩ ሲሄዱ እኔም ፍቅሯ በጣም እየባሰብኝ ሄደ.... ከውስጥ ኤቤጊያ ሽንኩርት ስትከትፍ የመክተፊያው ድምፅ ይሰማናል ተመስጬ እየሰማሁት ስለነበር ብዙም ልብ አላልኩትም ነበር ናዲ ብድግ አለና መኝታ ቤቱን ከፍቶ እፁ አለመነሳቷን ካረጋገጠ በኃላ ተመልሶ መጣና ፈገግ እያለ እና.... ራሴን መጣል ጀመርኩ እሷ እኔን አትመጥነኝም እል ነበር ፍቅሬን ድፍረት ኖሮኝ ብገልፅላት  እንኳን ምሏሿ ተቀራኒ እንዳይሆን እልና እፈራለው እተወዋለው ስለሌላ ነገር ማሰብ ተሳነኝ ስልቹና ቸልተኛ ለምንም ነገር ግድ የማይሰጠኝ ሰው ሆንኩ ጓደኜቼ ለኔ ያላቸው ከበሬታ ቀስበቀስ እየቀነሰ ሄደ ይባስ ብለው ይስቁብኝና ይሳለቁብኝ ጀመር ታውቃላሃ "ሞሮ" ይሉኝ እንደነበር አለኝ አው አውቃለው ሰሙም ናሆሚም ነግረውኛል አልኩት። አው ሞሮ ማለት ምንም የማይገባው ደደብ ማለት ነበር  የሚገርምህ ይህንን ስም ያወጡልኝ የገዛ ጓደኞቼ ናቸው የልብ ጓደኞቼ እምላቸው ነበሩ ሁሉም ከዱኝ ከአንድ በስተቀር ኪያር! ኪያር አሁንም ድረስ በጣም እምወደው እና እማከብረው የልብ ጓደኛዬና የስራ ባልደረባዬ ነው ከዛም በላይ ደግሞ የእህቴ ናሆሚ እጮኛም ነው። ሶስተኛ አመት ሙሉ ስለኤቤጊያ ሳስብና ሳልም ኖርኩ ጓደኞቼ ሸሹኝ እኔም ከትምህርት ራቅኩ መማር አስጠላኝ ቀን ከቀን ተኝቼ እውላለው የጓደኞቼ ስድብና ኤቤጊያን መቼም እንደማላገኛት ሳስብ መጠጣት ጀመርኩ ሱስ ውስጥ ተዘፈቅኩ ዶርም ተኝቼ ካልሆነ  በጠርሙስ ተደብቂያለው ወይ በሲጋራ ጭስ ራሴን ደብቂያለው ደህና የነበርኵት ልጅ በግዜ ሂደት መውጣት እማልችለው አዘቅት ውስጥ ተዘፈቅኩ ብዙ ግዜ ራሴን ላስተካክል ጣርኩ ግን አልሆነልኝም እንዲው እንደሆንኩ አራተኛ አመት ገባን የግቢው ቁጥር አንድ ጀዝባ እና ሞሮ ሆንኩ ለምንም ነገር ግድ አይሰጠኝም። አንድ ቀን ኤቤጊያን ከአንድ ራስታ ልጅ ጋር ስትሳሳም አየኃት በጣም ተናደድኩ በማግስቱ ልጁን ሺሻ ቤት አጊንቼ ተጣላን ጓደኞቹ ማታ ላይ ጠብቀው በጩቤ ወጉኝ ያኔ... ያኔ... ነበር ህይወቴን በሙሉ የምትቀይረዋን ሴት ያገኘሁት ሰምሃል! ኣለኝ ከሰሙ ጋር የተዋወቃቹት ያኔ ነው አልኩ በመገረም። አው ያኔ በሞትና በህይወት መካከል ሆኜ ያተረፈችኝ እሷ👇👇👇
Show all...
ማንበብ ህይወት ነው 🤼‍♂️📕

ሰላም 🤚 - 📯 📯  እንኳን በደህና መጡ!  📯 📯 በዚህ ቦት አማካኝነት

https://t.me/hopereding

➡️.  ትረካዎችን 🎙 ➡️.  ልቦለዶችን 📖 ➡️.  ኢ-ልቦለዶችን 📕 ➡️.  መፅሐፍትን በpdf 📚 ➡️.  ግጥሞችን 📝 ➡️.  አጫጭር ትረካዎችን 🎙 ➡️.  የመፅሐፍ ቻናሎችን 📌 ያገኛሉ። አስተማሪና አነቃቅ ንግግሮች ከተለያዩ መፅሐፎች ▫️ቦቱን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ

https://t.me/hopereding "ታክሲ ውስጥ" የኋላ ወንበር ላይ ተቀምጬ አጠገቤ ያሉ ሰዎች ስለመቸገር እያወሩ ነበር። በተለይ አንደኛው "እቸገር ነበር" ብሎ ስለጀመረ ጆሮዬን ወደጨዋታቸው ጣልኩኝ። ያው ችግርን "ነበር" ብሎ እንደመግለጽ ደስ የሚል ነገር የለም። ሁሉም ሰው "ነበር" እያለ የሚያወራበት ዘመኑ ላይ ያድርሰው። "የምሬን ነው የምልህ በልጄ ፊት እንዴት እንደምሳቀቅ ሃሳቡ የለህም" "ማለት እንዴት?" "ከስራ ስወጣ ትደውልና 'አባዬ እንትን ይዘህ ና፣ እንትን ግዛልኝ ትላለች" "ሳትገዛ ገብተህ 'ረሳሁት' ትላት ነበር?" "ኧረ እሱማ ቢሆን ባልከፋ!" "እና ምን ታደርግ ነበር?" "ከባለቤቴ ጋር በስልክ ውስጥ በቃላት እንጠቃቀስና ወደቤት ልገባ ያልኩት ሰውዬ ሰፈር ያለ ድዳ ማስጫ ላይ ተቀምጬ አመሻለሁ" "እንዴ፣ ለምን?" "ባለቤቴ ደውላ፣ ልጃችን መተኛቷን እስክትነግረኝ" ............🤔 እንዳልኩት ነው፣ ሁሉም ሰው "ነበር" እያለ ለሚያወራበት ዘመኑ ያመጣልን!
Show all...
ማንበብ ህይወት ነው 🤼‍♂️📕

ሰላም 🤚 - 📯 📯  እንኳን በደህና መጡ!  📯 📯 በዚህ ቦት አማካኝነት

https://t.me/hopereding

➡️.  ትረካዎችን 🎙 ➡️.  ልቦለዶችን 📖 ➡️.  ኢ-ልቦለዶችን 📕 ➡️.  መፅሐፍትን በpdf 📚 ➡️.  ግጥሞችን 📝 ➡️.  አጫጭር ትረካዎችን 🎙 ➡️.  የመፅሐፍ ቻናሎችን 📌 ያገኛሉ። አስተማሪና አነቃቅ ንግግሮች ከተለያዩ መፅሐፎች ▫️ቦቱን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ

👍 1
https://t.me/hopereding ​​፨--•••••••• ሞሮ •••••••••--፨             ፨--••ክፍል•••--፨ 43 ወደ ሰምሃል እየሮጥኩ ስሄድ ሊዲያ ትንሽ ወደኃላ ቀረት ብላ አስቆመችኝ ናኦድ አንተ በጣም መጥፎ ሰው ነህ እንዲ አይነት ሰው አትመስለኝም ነበር አለችኝና ጥላኝ ሄደች እዛው ቆሜ ቀረው ኤቤጊያ ከኃላዬ መጥታ ቀስ ብላ ትከሻዬን ነካ አድርጋኝ አይዞህ ናዲ ሁሉም ነገር ግዜውን ጠብቆ ይስተካከላል አለችኝ። እዛው መሬት ላይ ቁጭ ብዬ አላቀስኩ እኔ ቆይ ለምድነው ሁሉም ነገር እሚጠምብኝ!!! ኤቤጊያ አፅናናችኝ በቃ ወደ ዶርም ሂድና እረፍት አድርግ አለችኝ ው ተባብለም ተለያየን። ዶርም አከባቢ ስደርስ የዶርሜ ልጆች ሳለቅስ እንደነበር ቢያውቁ.... ደበረኝና መኪናዬ ውስጥ ገብቼ ተኛው እዛው ተጋድሜ እንዳለ ለራሴ አንድ ነገር ቃል ገባው ማንንም ሴት ከዚህ በኃላ ላልቀርብ! ሴትን በማሰብ ያቃጠልኩትን ግዜ ጠንክሬ ተምሬ ላካክስ ወስንኩ። በማግስቱ ከኤቤጊያ ጋር ስንገናኝ ዶርም ሰምሃልን ለማናገር ስትሄድ እንደተጣላቻትና ከዶርሟ እንዳሶጣቻት ነገረችኝ ሰምሃልና ኤቤጊያም ተጣሉ።  ሁለት ሳምንት ሙሉ ሰምሃልን ሳላገኛት አለፈ ትምህር... ተጀመረ... ሙሉ ሃሳቤን ወደ ትምህርቴ አድረጌ መማር ጀመርኩ ቢከብደኝም ራሴን አልጥልም አልሰላችም   በራሴ ተስፋ አልቆርጥም እንደቀድሞዬ ጠንካራ እና ሰቃይ ሆንኩ። ከሰምሃል ጋር ከተጣላን በወራችን ላይብረሪ ስገባ እሷ ደግሞ ስትወጣ በር ላይ ተገናኘን ደንገጥ ብላ ቆማ አየችኝ እኔን ትንሽ ቆሜ አየኃትና ፈጠን ብዬ ወደላይብረሪ ገባው ሰምሃልም ሄደች ግዜውም ሄደ.... የፋይናል ፈተና ደረሰ ላይብረሪ ውስጥ ሁሌ አያታለው አንነጋገርም ሌላው ቀርቶ ሰላምታም የለንም ድንገት እንኳን መንገድ ላይ ብንገጣጠም እንዳልተያየ ሆነን እንተላለፋለን። 2006  የአንደኛ ሴሚስተር ግዜ አልቆ ሁለተኛ ሴሚስተር ገባ ከሰምሃል ጋር ከተጣላን ከአምስት ወር በላይ ሆነን ሁልግዜ ስልኬን አነሳና ልደውልላት አስቤ እተወው ነበር አሁን ግን በሰምሃል ተስፋ ቆረጥኩ ስልኳን ከስልኬ ላይ አጠፋሁት። የአንደኛ ሴሚስተር ውጤት ሲለቀቅ ከክላሴ ከፍተኛውን ነጥብ አስቆጠርኩ 3.98 በሚቀጥለው 4 ነጥብ ለማምጣት ወሰንኩ ሰምሃልን ረሳኃት ... ሁለተኛውም ሴሚስተር ማንንም ሳይጠብቅ ገሰገሰ እኔም ግቢ መኖር ስላስጠላኝ ከግቢያችን ቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ቤት ተከራይቼ መኖርና መማሬን ቀጠልኩ ብዙ ግዜ ሲደብረኝ ወይም ብቸኝነት ሲሰማኝ ኪያር ወይም ኤቤጊያ መጥተው ያዳብሩኛል። ሁለተኛ ሴሚስተር ሲጀምር የማታ ሌላ ትምህር ጀምሬ ስለነበር በጣም እጨናነቃለው ግዜውም ሳይታወቀኝ በትምህርት ራሴን እንደወጠርኩ ገሰገሰ የሚድተርም ፈተና ከተፈተንን በኃላ አንድ ቀን ኤቤጊያና ኪያር ቤት እንድጠብቃቸውና አስቸኳይ እሚነግሩኝ ነገር እንዳለ ነገሩኝ ምን እንደሆነ ለናወቅ ጓጓው ከአንድ ሰአት በኃላ አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ መፅሃፍ እያነበብኩ ኪያር እና አቢጊ ዘው ብለው ገቡ። አቢጊ እንኳን ደስ ያለ...ህህክ ብላ እዛው አልጋው ላይ እንደተቀመጥኩ መጥታ ተጠመጠመችብኝ እየሳቅኩ ምን ተገኘ አልኳቸው ሁለቱንም እያየኃቸው። ምን ሆነ መሰለህ ብሎ ኪያር ሲጀምር እኔ አይደል እንዴ ሰምቼ የነገርኩ እኔ እራሴው ነው እምነግረው ብላ ኤቤጊያ እየሳቀች አቋረጠችው የውልህ ናዲ ቅድም እነሰምሃል ስፔስ ቁጭ ብዬ እያጠናው እያለ ሰሙ ሊዱ እና ራኪ ሆነው ሊያጠኑ መጡ እኔ ከኃላ ያጥቁሩን ባለሁዲ ጃኬት ከነኮፍያው አድርጌው ስለነበር አላወቁኝም ነበር ብዙም አላዩኝም እናም እያጠኑ እያለ በመሃል ሰምሃል ማልቀስ ጀመረች እና እነ ራኪ ምነው አሏት ናዲ ናፈቀኝ ፍቅሩ አሁንም አልወጣልሽ አለኝ ይባስ ብሎ ተጣልተን ስንራራቅ ፍቅሩ ባሰብኝ ኣረሳው አልቻልኩም አለቻቸው። ኤቤጊያ ይህንን ስትነግረኝ ደነገጥኩ እስከዛሬ እሷ ስታፈቅረው የነበረው ሌላ ወንድ አልነበረም እኔኑ ነው!? እኔኮ ፍቅሬን ያልነገርኳት እሷ ሌላ እምታፈቅር ስለመሰለኝ ነው አልኳት አቢጊም እየሳቀች አው አይገርምም  አንተን ነበር እንጂ ሌላ ሰው አልነበረም አለችኝ።  ሁለታችሁም አሁን ትዋደዳላችው አይደል አሁን ወደ ቤተክርስቲያን እየወጡ ነው ሂድና አግኛት አለኝ ኪያር አይ አይሆንም አሁን ግዜው ረፍዷል ወደ ስምንት ወር ምናምን ሆነን ከተጣላን አሁን ላይ ምን ብለን ነው እምንታረቀው በዛ ላይ እኔ በፍቅር ተስፋ ቆርጫለው ዳግም ሴት ቀርቤ መጎዳት አልፈልግም በሰምሃል  ተስፋ ከቆረጥኩ ቆየው አልኩት ኪያር ተናዶ ምን? አለኝ እኔ ከዚ በላይ ልታገስህ አልችልም ናኦድ ቻው ብሎኝ ወጥቶ ሄደ አልጋዬ ላይ ተመልሼ ዘፍ አልኩ። ኤቤጊያ ባዘነ አንደበት ለምን አለችኝ ለምን እንደሆነ ታውቂያለሽ አቢጊ እኔ በዚ አለም ላይ ለፍቅር ያልተፈጠርኩ ሰው ነኝ ምንም ነገር አይሳካልኝ አልኳት አቢጊ እንደዛ አትበል ናዲ አንተ ጥሩ ሰው ነህ እኔ እንኳን ብዙ ነገር አድርጌህ ይቅር ብለኀኛል ይኀው አሁን ላይ ካንተና ከኪዩ ውጪ ምንም ጓደኛ የለኝም እባክህ በፍቅር ተስፋ አትቁረጥ እኔንም ፍቅርና ይቅርታን ያስተማርከኝ አንተ ነህ አንተ ተስፋ ስትቆርጥ አይቼ እኔም ተስፋ መቁረጥ አልገልግም ብላ አቀፈችኝ። አቀፍኳት!                 🍁ክፍል-44🍁 👈👈  ላይ ያበቃል!! ሞሮ -1-   ክፍል ብቻ ቀረው እንዲቀጥል አብሮነታችሁ አይለየን እንደ ላይክ ብዛት እንፈጥናለን.. 🌹🌹🌹🌹🌹🍃🍃🌹🌹🌹🌹🌹
Show all...
ማንበብ ህይወት ነው 🤼‍♂️📕

ሰላም 🤚 - 📯 📯  እንኳን በደህና መጡ!  📯 📯 በዚህ ቦት አማካኝነት

https://t.me/hopereding

➡️.  ትረካዎችን 🎙 ➡️.  ልቦለዶችን 📖 ➡️.  ኢ-ልቦለዶችን 📕 ➡️.  መፅሐፍትን በpdf 📚 ➡️.  ግጥሞችን 📝 ➡️.  አጫጭር ትረካዎችን 🎙 ➡️.  የመፅሐፍ ቻናሎችን 📌 ያገኛሉ። አስተማሪና አነቃቅ ንግግሮች ከተለያዩ መፅሐፎች ▫️ቦቱን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ

https://t.me/hopereding ይነበብ 🙏 ወንድሜ እኮ ነው! አ ይ ከ ብ ደ ኝ ም :: ይህ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ታሪክ በጃፖን አገር  የሆነ እውነተኛ  ክስተት ነው :: ልጁ በጃፓን በጦርነቱ ወቅት : የሞተውን ወንድሙን በጀርባው አዝሎ አብሮት ካለው ወታደር ጋር ረዥም የእግር ጉዞ ያደርግ ነበር:: ወታደሩ ክስተቱን አስተውሎ ልጁን በጉዞው እንዳይዝልበት በማሰብ በቃ  "ወንድምህ ሞቷል : ቅብረውና ጉዟችንን እንቀጥል" ብሎ ይጠይቀዋል ::  ልጁም መልሶ ወንድሜ እኮ ነው!  ለእኔ አይከብደኝም ሲል መለሰለት:: ወታደሩም ልጁ ለወንድሙ ያለውን እውነተኛ ፍቅር  ተመልክቶ እንባውን አፈሰሰ።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህ ምስል በጃፓን አገር  የአንድነት ምልክት ሆኖ ይኖራል:: ምንም እንኳን ታሪኩ በጃፓን አገር የሆነ ቢሆንም :የዚህ ፎቶ እውነተኛ ታሪክ  ለእኛም የወንድማማችነትና የእህታማማችነት እውነተኛ  ፍቅር  ምልክት ነው! "ወንድምህ ለአንተ  አይከብድህም ምክንያቱም ወንድምህ ነውና... እህትህም  ለአንተ አትከብድህም እህትህ ናትና:: ከዚህ እውነት ውጭ ተፈጥሮአዊ አይደለም ቢወድቅ አንሳው:: ቢደክም ደግፈው:: ቢቸግረው እርዳው:: ፍትህ ቢነፈግ ስለፍትህ ድምጽ ሁንለት:: እርሱን በመሸከም ድከም:: እርሱን ለመደገፍ  ጥረት አድርግ ። ስህተት ቢያደርግ ይቅር በለው:: ቢስት መልሰው ! ሰዎች ጀርባቸውን ቢያዞሩበት አንተ ግን በጅርባህ ተሸከመው :: ለአንተ አይከብድህም :ወንድምህ ነውና ::
Show all...