cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዮቶር ልጅ _፩

መሃይምነት የዕውቀት አለመኖር ሲሆን ሞኝነት ግን ዕውቀት ቢኖርም ለመጠቀም አለመፈለግ ነው ።

Show more
Advertising posts
214
Subscribers
+124 hours
+27 days
-230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አንድ የህግ ባለሙያ በባቡር እየተጓዘ ሳለ አንድ በጣም ቆንጆ የሆነች ልጅ መጥታ ፊት ለፊቱ ከሚገኘው ወንበር ላይ ተቀመጠች በዚህ የህግ ባለሙያው ደስ አለው ። ቀና ብሎ ሲመለከታት ዓይን ለዓይን ተያዩ ከዛም ፈገግ አለች። አሁን ደግሞ ይበልጥ ደስ አለው ።ትንሽ ቆይታ አጠገብ ሄዳ ተቀመጠች ።በዚህ ጊዜ አጅገ በጣም ደስ አለው ። ትንሽ ቆየችና ወደ ጆሮው ጠጋ ብላ በሹክሹክታ "ያለህን ገንዝብ ; የATM ካርድህን ከነፓስ ዎርዱ እና የሞባይል ቀፎህን አሁኑኑ ካልሰጠኽኝ ስትጎነትለኝ እንደ ነበረና ፆታዊ ትንኮሳ እንደደረሰብኝ እዚህ ባቡር ውስጥ ላሉት ሁሉ በመንገር እጮኻለሁ ።" አለችው ። የህግ ባለሙያው በቸልተኝነት ቀና ብሎ ተመለከታት ከቦርሳው ውስጥ ወረቀትና እስርብቶ አውጥቶ እንዲህ ብሎ ፃፈላት " ይቅርታ መናገርና መስማት የተሳነኝ ነኝ ። እባክሽን ማለት የፈለግሽውን ሁሉ እዚህ ወረቀት ላይ ፃፊልኝ ።" ልጅቷም ቀደም ብላ ስትነግረው የነበረውን ሁሉ ፅፋ ሰጠችው ። የህግ ባለሙያው ወረቀቱን ተቀበሏት በጥሩ ሁኔታ አጥፎ ኪሱ ከከተተው በኃላ ከተቀመጠበት ተነስቶ ጎርነን ባለ ድምፅ ምን ቢላት ጥሩ ነው " አሁን እንደፈለግሽ መጮህ ትችያለሽ ። መልካም ምሽት 🙂😁
Show all...
ጀግና ፣ ብልኀ ፣ጎበዝ ጠንካራ ልትባል ትችላለህ ፣ ርኅርኄ ትዕግሥት ፣ፍቅር ከሌለህ ግን ራስህን ማወቅ ስሜትህን መቁጣር ፣ የሚያቁጡና የሚያስጨንቁ ስሜቶችን መቁጣጠርና ማስተዳደር ውጤታማ ግንኙነት መፍጠር ፣ ያለህበት ዐውደ መገንዘብ ካልቻልኽ ሩቅ መሄድ አትችልም
Show all...
ወዳጅነት friendship "በጥሩ ባለትዳሮች መካከል ጥልቅ የሆነ ወዳጅነት አለ ። ወዳጅነት ማለት መወዳጀት ፤ መተሳሰር መልካም ግንኙነት ለጠላት ክፍተት ከአለመስጠት ወዘተረፈ እንደማለት ነው ። #ወዳጅነት#
Show all...
ሰዕልና ሰው ራቅ ብለሸ ስታያቸው ነው የሚያምሩት ። በጣም ጥቂቶቹ ስትቀርቢያቸው ያምሩ ይሆናል ። 🙄🙄
Show all...
1. #ይሰለቹሃል አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ! 2. #ሼም_ነው የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ! 3. #አይባልም እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም። 4. #ክፈል አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ። 5. #ነውር_ነው ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ። 6. #አታቋርጥ ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ።ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው። 7.# አታብሽቅ ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው።ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ። 8. #አመሥግን ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመሥግን። 9.# ያለስስት_አድንቅ ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው። 10. #ክፉ_አስተያየትህን_ቆጥብ ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ። 11. #ካልሆኑ_ጥያቄዎች_ታቀብ ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል። 12. #ስነ_ስርዓት ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው። 13. #ክብር_ለሁሉም ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም። 14. #ስልክህን_አስቀምጥ ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው። 15. #አድብ ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው። 16. ተቆጠብ ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ። 17. #መነጽርህን_አውልቅ ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው! 18. #አትሳሳት በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ። 19. #ለስልክ_መልዕክት_ምላሽ_መስጠት በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው።ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው። 20. #ዕቃ_መልስ የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።
Show all...
ሰባት ቁጥር (፯) ሰባት ቁጥር የወርቅ ዘንግ ነው፡፡ ከምጥቀት በላይ ከጥልቀት በታች ያለ ማንኛውም ፍጥረት የተፈጠረው በወርቅ ዘንግ እየተለካ ነው፡፡ የወርቅ ዘንጉ ሰባት ደረጃዎች ያሉትና በሰባቱ የፈጣሪ እይታዎች የፀደቀ የተፈጥሮ ሚዛን መጠበቂያ ውሃ ልክ ነው፡፡ ሰባት ቁጥር የሰው ልጅ ባህሪይው ናት፡፡ በዚች ምድር ላይ የሰው ልጅ በሙሉ አንድ አይነት ባህሪይና የተለያየ ጠባይ አለው፡፡ ባህሪይና ጠባይ ለየቅል ናቸው፡፡ ባህሪይ የማይለወጥ የማይቀየር ሲሆን ጠባይ ግን ሊሻሻልና ሊቀዬር የሚችል ነው፡፡ በመንፈሳዊ መንገድ ስንገባ ሰውን ያልተበረዘ ማንነቱን ከጥንተ ማንነቱን ስንቀዳው ሰባት አይነት ጠባይ አለው፡፡ ሰባቱ የብርሃን መንገዶች ተብለው ይጠራሉ፡፡ አፍቃሪነት፣ ይቅርባይነት፣ አመስጋኝነት፣ በጎነት፣ አማኝነት፣ ተስፈኝነትና እውነተኝነት ሰባቱ የብርሃን መንገዶች ናቸው፡፡ ለሰው ልጅ ከመለኮት ከተሰጡት ፀጋዎች አንዱ ፍቅር ነው። ልባችንን እና አይምሮአችንን ፍቅር እንዲያመነጩ ካደረግናቸው ከሰማይ በታች የማናሸንፈው ነገር የለም። ፍቅር በልቦና ፅላት ተፅፎ የሚገኝ የአለም ክፋት ማሸነፊያ ሃይለኛ ፈውስ ነው፡፡ ተፈጥሮን አስተውለን ብንመለከት ከመስጠት አቋርጣ አታውቅም፡፡ እፅዋትን ብንመለከት ያለስስት አየር ይሰጡናል፡፡ አንተስ/አንቺስ ለወገን ምን ሰጣችሁ? ምን አካፈላችሁ? የተፈጥሮ ህግ በመስጠት ላይ የተመሰረተ ነው ስስት የለበትም፤ አንተ ለቤተሰብህ፣ ለአከባቢህ፣ ለሀገርህ ምን አካፈልክ? ህይዎትህን እስኪ መርምረው ምን ያህል ለፍቅር የተገዛ ነው? በክፋት፣በክህደት፣ በዘረኝነት፣ በቂም፣ በበቀል መንገድ ላይ ነው ያለኸው? ወይስ በቤተሰብህ በአካበቢው በበጎነት የሚታወቅ ለህፃናት መልካም ነገር የሚያሰተምር ጠባይ ነው ይዘህ ያለኸው? በተፈጥሮ ህግ ተመርተህ መጓዝ ስትጀምር ፈጣሪ በአንተ ውስጥ አስደናቂ ነገሮችን መስራት ይጀምራል በሽታም አያጠቃህም፡፡ . . . . ሰባት ቁጥር... የተፈጥሮ ምስጢር !!
Show all...
እንዴ ብልጣብልጦች በአፌ እያሳለጥኩ ትናንሽ ሕልም እየፈለፈልኩ ለትናንሽ ግብ ወደዚህ ምድር እንዲሁ ለመኖር አልመጣሁም
Show all...
"አዋቂ ያልሆነ ሰነፍ ሰው አንተ ስታምነው እርሱ ይከዳሃል ። ከምስጢርህም ያካፈልካው እንደሆነ ሊገድልህ ወይም ሊያስገድልህ ምሥጢርህን ያወጣብሃል ።
Show all...
ምዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ። እኛ ቀዳማዊ ሃይል ስላሴ ስዩም እግዚአብሔር ንጉሥ ነገስት ዘ-ኢትዮጵያ ። ፲፱፻፳፰ __፲፱፻፴፫ በኅዳር ፳፩ ቀን ፲፱፻፴፯ ዓ.ም የሰጠነውን ድንጋጌ ተመልክተን ተጠቅቶ የሚያውቀው የኢትዮጵያ ነፃነት በኢጣሊያ ፋሺስት በተደፈረበት ጊዜ ስለ ንጉሥ ነገስት ክብር ሀገር ፍቅር ከተጋደሉ አርበኞቻችን ለታመነ አገልጋያችን #ለደጃዝማች ውብነህ ተሰማ የአርበኛ ሜዳይ ከእምነት ____ዘንባባ ጋራ ሸልመናል ። ይህንንም ሜዳይ በደረቱ እንዲያደርገው ፈቀደናል ።
Show all...
! አንዲት አጠር ያለች አሮጊት መቶ ሺ ብር ተሸክማ ወደ ባንክ ቤት አመራች። አዲስ የባንክ አካውንት ለመክፈትም ወደ ባንኩ ማናጀር ቢሮ ገባች። ጥርጣሬ የገባውም ማናጀር፣ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣችው ጠየቃት። “በቁማር” አለች አሮጊቷ “ቁማር ላይ ጎበዝ ነኝ” ማናጀሩም አቋረጣትና በአግራሞት ጠየቀ “ምን አይነት ቁማር ነው የምትቋመሪው? “ኦ ሁሉም አይነት፤ ባገኘሁት ነገር እቋመራለሁ” አለች “ለምሳሌ ነገ ከቀኑ አስር ሰዓት በፊት ግራ ቂጥህ ላይ የቢራቢሮ ምስል ትነቀሳለህ ብዬ ሃያ አምስት ሺ ብር ላስይዝ እችላለሁ” “እኽ ይሄማ አይሆንም” አለ ባንከሩ መገረሙን እንደቀጠለ “እናም እኔ አሸንፌ ብርሽን እወስድብሻለሁ” “ችግር የለውም እንቋመር እና ማን እንደሚያሸንፍ እናያለን”አሮጊቷ መለሰች፡፡ ማናጀሩም ተስማማ፡፡ በነጋታውም ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ ምስክር እንዲሆናት ጠበቃዋን ይዛ መጣች። ማናጀሩ ዞረ፤ ሱሪውንም አውልቆ ቆመ፡፡ ጠበቃው እና አሮጊቷ መረመሩት። “እሺ” አለች አሮጊቷ “በደንብ እንዲታየን በትንሹ ልትጎነበስልን ትችላለህ?” ማናጀሩም የእርሷን ትዕዛዝ ተቀብሎ ተጎነበሰ። አሮጊቷ ሃያ አምስት ሺ ብር ቆጥራ ለማናጀሩ ሰጠችው። የእርሷ ጠበቃ እንደተከፋ እጆቹን ጭንቅላቱ ላይ አድርጎ ይንጎማለላል። ማናጀሩም የተቀበለውን ገንዘብ እየቆጠረ “ጠበቃው ምን ነካው?” ብሎ አሮጊቷን ጠየቃት። “ኦ! ቁማር በልቼው ነው” አሮጊቷ መለሰች “ዛሬ አስር ሰዓት ላይ የባንክ ማናጀሩን ቢሮው ውስጥ መለመላውን አስጎነብሰዋለሁ ብዬ በመቶ ሺ ብር ከእርሱ ጋር ተወራርደን ነበር።” አለችው፡፡ በብዙ የሕይወት ሁነቶቻችን ውስጥ እንቋመራለን። ዛሬ ይዘንባል አይዘንብም፣ መኪናውን ቀድሜ ዜብራውን መሻገር እችላለሁ ወይስ መኪናው ካለፈ በኋላ ልሻገር እና ወዘተ። በፈጣሪ መኖር ወይም አለመኖር ላይስ መቋመር እንችላለን? አ#የፍልስፍና_ማዕድ መጽሐፍ @tofamotivationallife @tofamotivationallife
Show all...