cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መንፈሳዊ ጥቅሶች

ተሰርቶ እንድለቀቅ ምትፈልጉት ጥቅስ/መዝሙር ካለ አሳውቀን ሰርተን እንለቃለን @army_keyss ሀሳብ አስታያየት ካለቹ በዝ @army_keyss አውሩኝ

Show more
Advertising posts
261
Subscribers
-124 hours
-67 days
-2330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
👍 3
ዲና {DINA} ተከታታይ ልበወለድ ✍written by Aksan Adane            PRESENT BY ARMONEM ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ክፍል °1⃣1⃣°""""""""""""" ተንገብግቤ ሳየው ማቲ ነበር እዮብ ባለመሆኑ ብናደድም ናቲም ስለፃፈልኝ ደስ ብሎኛል ዲኑ ቅድም በደንብ ደስታዬን ሳልገልጥልሽ በእውነት አንቺ ማለት ድጋሚ መኖር እንድጀምር ያደረግሽኝ ከማውቃቸው ሰዎች ጋር የማላወዳድርሽ የመለወጤ ምክኒያት ብልህ ና ትሁት ሴት ነሽ በመወለድሽ በጣም ደስተኛ ነኝ ብዙዙዙዙዙዙዙ አመት ኑሪልኝ ደግሞ ብዙ ያልነገረኩሽ ነገር አለ ያው ጊዜው ሲደርስ አይቀርም ደህና እደሪልኝ ።     ይል ነበር ቴክስቱ አመሠግናለሁ ውዱ ጓደኛዬ ሁሉ ነገሬ ለአንተም ረጅም እድሜና ጤና ይስጥህ ብዬ መለስኩለት ማቲ በጣም ያሳዝናል እኔና እዮባ ቢያንስ እናቶቻችን አጠገባችን ናቸው እሱ ግን እናቱም አባቱም አጠገቡ የሉም ደግሞ ከታላቅ ወንድሙ ጋር በአባት አይገናኙም ስለ ራሱ ሲነግረኝ ታላቅ ወንድሙና እናቱ በችግር ብቻቸውን እየኖሩ ሳሉ የሱ አባት ለወንድሙ የእንጀራ አባት ሆኖ እርሱ ከተወለደ በኋላ ሁለቱንም እንዳጣ ወንድሙ የነገረውን ነግሮኛል እናቱ እሱን ስትወልድ ነበር የሞተችው ወንድሙ ነው ከልጅነት እስከ እውቀት ያሳደገው ። በቃ በጣም አዝንለታለው የሱ ነገር አይሆንልኝም ሁለቱንም በጣም እወዳቸዋለው ። ሁለቱም ሊነግሩኝ ያሰቡትን ለማወጣጣት ብሞክር አልተሳካልኝም በፈተና እያሳበቡ በጣም እያናደዱኝ ነው ግን ጥናታችን ላይ በርትተናል ኢንትራንስ ልንፈተንም አደል አልፎ አልፎ ለሶስት ወክ እንወጣለን ዛሬ ሳናስበው ሰአቱ በጣም መሸ ሰፈራችን ወደ ውስጥ ስለሆነ ብርዱ ደመናው ሰማዩን ሸፍኖት ያለ ሰአቱ ጭልም ብሏል የከተማውም መብራት ጠፍቶ ጭላንጭል ብርሀን እንኳን አይታይም ወይኔ ማቲ እዩ እኔ ፈርቻለሁ አልኳቸው ሁለቱም ፈርተዋል ግን እኔን ለማፅናናት አይዞሸ እየደረስን ነው ይሉኛል ኸረ ጨለማውስ እኔ መደፋቴ ነው አልኳቸው ቆይ ብሎ እዮባ ከኪሱ ስልኩን አውጥቶ ባትሪ አበራ ወዲያው ከየት መጡ ሳይባል 4ግዳንግድ ሰዎች ከበቡን እንዳልጮህ አንዱ ቀድሞ አፌን አፈነኝ....... ........ይቀጥላል........ ✍written by Aksan Adane
Show all...

ዲና{DINA} {ተከታታይ ልበወለድ} ✍written by Aksan Adane           PRESENT BY ARMONEM           ---------------ክፍል 1⃣0⃣---------------- ሰላም ብዬው ወደ ውስጥ ገባን ለመስማት እንደጓጓ በጣም ያስታውቅበታል ዲኑ ለምን ፈልገሽኝ ነው አለኝ ማቲ ሰሞኑን ከእዮብ ጋር ያላችሁ ቅርርብ ቀንሷል ይሄ ደግሞ እኔን እየረበሸኝ ነው አልኩት ወዲያው ደስተኛ የነበረው ፊቱ ቅጭም አለ ምነው ስለው ለዚ ነው ይሄንንማ አንድ ላይ አድርገሽ ጠየቅሽን አደል ምንም አልሆንንም አለኝ እና ምን ጠብቀህ ነበር አልኩት ተናዶ ምንም በቃ ልሂድ  አለኝ ግራ አጋባኝ ይሄ ያናዳል እንዴ እማ ወዴት ነው ቁርስ ሰርቼ ሳትበላ ብላ መለሰችው አብረን እየበላን እዮባ እየሮጠ ዲኑ ዲኑ እየተጣራ ገባ ሁለታችንም መኖራችን ግራ አጋብቶታል ድምፁ ቀነሰ ወይ እዩ ምነው ናቁጭ በል አልኩት ተቀመጠ ሁለቱም እየተያዩ ተኮሳትረዋል እናንተ ቆይ ምንድነው ችግራችሁ አልኳቸው ሁለቱም ዝም አሉ እሺ ምን ልትነግረኝ ነበር እየተጣደፍክ የመጣኸው አልኩት አይ ማሚ ፈልጋሽ ልጠራሽ ነበር በቃ ልሂድ አለኝ እንዴ ቆይ እንሂድ እሺ አልኩት ና አንተም አለው ማቲን እሺ ምክኒያታችሁን አትንገሩኝ ግን እንደ በፊት ለመሆን ቃል ግቡልኛ ተቃቅፋችሁ ሰላም አውርዱ አልኳቸው ባይዋጥላቸውም እንዳልኳቸው አደረጉ የበላንበትን አነሳሁና እማ እያልኩ ጓዳ ስገባ የለችም ተጣርቼ ሲያቅተኝ እንሂድ በቃ አልኳቸው ጊቢ ከገባን በኋላ ሁለቱም ወደ ኋላ ቀሩ ምን እንደሚያወሩ አልገባኝም ኑ እንጂ ስላቸው መጡ ቤዚ ከየት መጣች ሳልል ዲኑ ብላ ከቤት ወጥታ ተጠመጠመችብኝ ምን ትሰሪያለሽ እዚ ስላት  በሌላ ወሬ ያዘችኝ የዚህኔ እዮባ ና ማቲ ወደ ውስጥ ገቡ ያልጠየኳትን ስታወራ ቆየችና እንግባ አለችኝ ወደ ውስጥ ስገባ ሰርፕራይዝ ብለው ጮኹ በጌታ ስም ምን እንዳስበረገገኝ ባላውቅም ደርቄ ቀረሁ የቸርች ልጆች የክላስ ልጆች እማ ዝኑ ና መዓዚም ነበሩ ቤቱን አሳምረውት ልዩ ሆኗል ለካ ዛሬ ልደቴ ነው ቅዳሜን በልደቴ ቀን ተደስተን አሳለፍን ሁሉም ወደ ቤት ሄደዋል እኔ እማ መአዚ ዝኑ እና እዮብ የተሰጠኝን ስጦታዎች እያየን ስንጨዋወት አመሸን እነ እማ የጦፈ ወሬ ላይ ናቸው እዮባና እኔም ዲኑ ግን እንደኔ ባህሪ ቢሆን አንቺን የመሰለች ልጅ አጥቼ ነበር በአንቺ ትህትና በግድ ባትቀርቢኝ ሰው ከመሬት ተነስቶ ሰው ይጠላል ለነገሩ ያኔ ሰይጣንም ሳይኖርብኝ አይቀርም አለኝ ቀላል ዋናው ነበር አንተ ላይ ያለው ብዬ ሳኩበት ኸኸኸኸ ጭራሽ ብሎ ጆሮዬን ቆነጠጠኝ እንዲሁ እየተዛዛግን እማ ኸረ ዲኑ ተነሽ 3:ሰዓት ሆነልሽ አለችኝ ከነሱ ጋር ስንሆን ሰአቱም አይታወቀንም ዝኑም እንኳን ለ19 አመት አበቃሽ ቀሪ ዘመንሽ የተባረከ ይሁን ብላ መረቀችኝ ወደ ቤት ልንሄድ ተነሳን ዝኑም እዮባም ሊሸኙን ወጡ እነ እማ ወጥተውም ወሬ አያቆሙም የጊቢው በር ጋር እየጠበቅናቸው ነው ። እኚ ደግሞ ውይይይ እያልኩ ድንገት ዲኑ አለኝ ወዬ አዝጉ አልከት ፀጥ አለኝ ምነው እዩ ደህና አደለህም አልኩት አይ ተይው በቃ ሌላ ቀን ነግርሻለው አለኝ እምቢ እምቢ ብዬ ደበደብኩት ኸረ ዲኑ ሌላ ቀን በናትሽ ሲል አልፈልግም እያልኩ ስከራከረው እማና ዝኑ መጡ እየተናደድኩ ወደ ቤት ገባሁ ምን ሊነግረኝ ይሁን እንዲ ሌላ ቀን ምናምን ብሎኝ ስለ ማያውቅ ለመስማት ጓግቼ ማሰላሰል ቀጠልኩ ይሄኔ የስልኬ ድምፅ ጮኸ text ሲገባ ተንገብግቤ ሳየው ማቲ ነበር........... ..............ይቀጥላል............. written by Aksan Adane ✍
Show all...
ዲና{DINA} {ተከታታይ ልበወለድ} ✍written by Aksan Adane            Present by Armonem        ..............ክፍል9⃣......... ያለሁበት መጣ ስፖርቱን አላቆምኩም ገመድ ዝላይ ነበር ባለማቆሜ የተገረመ ይመስላል ረጅም ደቂቃ ዘለልኩና አስቀምጬው ውሀውን አንስቼ መጠጣት ጀመርኩ እኔም ልሞክረው አለኝ ሰጠሁት እየቆጠርኩለት ጨረሰና ወደ ቤት ገብቸን ዪኒፎርም ቀይረን ቁርስ በልተን ወደ ትምህርት ቤት ልንሄድ ወጣን ቅርብ ስለሆነ ታክሲ አንጠቀምም ዱኑ ይቅርታ አለኝ ለምኑ አልኩት አንቺ እኔ እንድለወጥ ለኔው ብለሽ ስትከታተይኝ ስላስቀየምኩሽ አለኝ ኸረ ወንድሜ እንኳን ለመለወጥ አበቃህ አልኩት የማንበብ ፍላጎቴ ተመለሰ ለሊት ረጅም ሰአት አነበብኩ ከአሁን በኋላ በስርአት እንደምከታተል ቃል ገባልሻለው አለኝ ማቲ በራቸው ጋር እየጠበቀን ነበር እሱንም ይቅርታ ጠየቀው እና አብረን ሄድን እዮባ አልፎ አልፎ እየተደበቀን የባለፈው ቤት ይሄዳል ግን እንደበፊቱ አያበዛም ዘፈን መስማት ምናምን አቁሞ ከኛ ጋር መዝሙር ያዳምጣል ፌሎ ያለን ቀንም ከክላስ በኋላ  ከኛ ጋር ይካፈላል ሰሞኑን ፍቅራችን ጨምሯል እማም ከሄደች 3 ወር ሞልቷታል ሁሌ ትደውልልኛለች ታትዬም ቅዳሜ እና እሁድ ትደውልልኛለች እዮባ ሙሉ ለሙሉ ክርስቲያን ሆኗል ዝኑም አልተቃወመችም በፊትም ሀይማኖት የለውም እንጂ ኦርቶዶክስ አይባልም ደህንነት ተምሮ ተጠመቀ ቤቢሾም በጉብዝናው እንደ ቀጠለ ነው አሁን ቀኖች ሳምንታትን ሳምንታት ወራትን አስቆጥረው 12 ኛ ክፍል ማገባደጃው ላይ ነን አብረን እናጠናለን ቸርች አንለያይም ወክ ምናደርገው አብረን ነው መጪ አመት ልንለያይ መሆኑን ማናችንም ማሰብ አንፈልግም ። ሰሞኑን ግን ሁለቱም ከኔ ጋር ሰላም ናቸው እርስ በእርስ ግን የተቀያየሙ ይመስላሉ  እኔ ብቻ ነኝ ማወራው ስጠይቃቸው ምን ሆንን ይሉኛል ማናቸውም ሊነግሩኝ አይፈልጉም ስለጨነቀኝ ለእማ ነገርኳት ለብቻ ብቻ በስልት እንድጠይቃቸው መከረችኝ ተስማምቼ በቅድሚያ ማቲን ላገኝህ እፈልጋለሁ ጠዋት አልኩት እሺ ግን ለምንድነው በናትሽ አሁን ንገሪኝ ብሎ ነዘነዘኝ ወረኛ ምን ያንገበግብሀል ብዬው ስልኩን ዘጋሁ ጠዋት 12 ሰአት ሲል ፊቴን ታጥቤ ወደ ውጪ ስወጣ ማቲ በዛ ብርድ በር ላይ ቆሟል ሰላም ብዬው ወደ ውስጥ ገባን ........ ............ይቀጥላል.......... ✍written by Aksan Adane
Show all...
ዲና{DINA} {ተከታታይ ልበወለድ}written by Aksan Adane            PRESNT BY ARMONEM            ---------------""""""""""""""""-----------------                   ክፍል 8⃣ ቴክስት ፃፍኩለት አልመለሰም ነበር ከብዙ ቆይታ በኋላ ውይ ዲኑ አላየሁትም ነበር እሺ እኔም ደስ ይለኛል ብሎ መለሰልኝ በጠዋት ስራዬን ሰርቼ ወጣሁ ማቲ በር ላይ እየጠበቀኝ ነበር ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ እሺ ማቲ ለምን ነበር ትናንት የፈለከኝ አልኩት ዲኑ ትናንት የተናገርሽኝ ነገር ሰላም ነሳኝ በናትሽ መለወጥ እፈልጋለሁ አለኝ በጣም ነበር ደስ ያለኝ በፊት ቸርች ውስጥ አገለግል ነበር ከእዮብ ጋር ስሆን እሱን መለወጥ ሲገባኝ እኔም እንደሱ ሆንኩ ልክ ነሽ እኔ የደረቀ ዛፍ ማለት ነኝ ስለዚህ መለወጥ እፈልጋለሁ አለኝ ዋው ማቲ ደስ ይላል አልኩት ሰሞኑን ከማቲ ጋር በጣም ተቀራርበናል አብረን ቸርች መሄድ ጀመርን ንግግሩ ተቀይሯል በትምህርትም በርትቷል እቤት እየመጣ እናጠናለን እኔም እነሱ ቤት እየሄድኩ አሳልፋለው ከታላቅ ወንድሙ ብሩክ ጋር ነው ሚኖረው የወንድሙ ሚስት ራሄልም በጣም ጥሩ ሴት ናት እዮብ ደግሞ ሊያየን አይፈልግም ጓደኛውን እንዳሳጣሁት ነው ሚሰማው ግን ተስፋ አልቆርጥም እሱም እንደሚለወጥ ። ደብረ ዘይት አክስት አለችኝ እና ልትወልድ ስለሆነ እማ ልትሄድ ነው እኔ እንዳልሄድ ትምህርቴ ይስተጓጎላል  ስለዚህ እነ እዮብ ጋር ልሆን ነው ዝኑ ደስ ብሎአታል እሷ እዮብ ብቻውን እንዳይሆን ነው እሱ ለአይኑ ጠልቶኛል እማ ሄደች እኔም እነዝኑ ጋር አንድ ክፍል ተሰጥቶኝ ገባሁ ዛሬ ቅዳሜ ነው እዮብ በጠዋት ተነስቶ ሊወጣ ሲል ወንድሜ ወዴት ነው አልኩት ምን ወንድሜ እንደ አንቺ አይነት እህት እንድትኖረኝ አልፈልግም ደሞ ስለእኔ ምን አገባሽ ነው ማቲ መሠልኩሽ እኔ እኮ ለአንተ ብዬ ነው ብርድ ነው በዛ ላይ ቁርስ ሳትበላ ተይ እንጂ በጣም ያሽቃበጥሽ አይመስልሽም ። መውጣቴን ማሚ ብታውቅ የምለቅሽ አይምሰልሽ ደግሞ አትከታተይኝ ሰማሽ ብሎ አፈጠጠጠብኝ ልጁ አመመው እንዴ ሰሞኑን ስድቡ ና ንትርኩን ለምጄዋለው ስድቡማ ብሔራዊ መዝሙር ሆኖብኛል አጠገቡ ከተቀመጥኩ ወደ ክፍሉ ይገባል ጊቢም ወጥቶ አየር ሲቀበል ከወጣሁ ወደ ውስጥ ይገባል እኔም ሆን ብዬ እከታተለዋለው ቁጭ ብሎ ቲቪ እያየ ነበር ዝኑ እንድትሰማ ጮክ ብዬ እዮባ እናጥና ያልገባኝ ነገር አለ አልኩት እንዴት እንደገላመጠኝ ዝኑ ጎሽ ተባረኪ የኔ ቅመም ብላ ቦርሳውን አመጣችለት ቢያንቀኝም ደስ ሚለው ይመስለኛል ፊት ለፊታችን ቁጭ ብላ ስልኳ ላይ ተመስጣለች ዛሬ የተማርነው አልገባኝም ይሄን አብራራልኝ አልኩት እያየሁት አይኑ ደም ለበሰ ዝኑ ጎበዝ ተረዳዱ አለችን ቀና ብላ ይሄ እያለ ዝምብሎ ያነበው ጀመር በነገራችን ላይ አይጠቀምበትም እንጂ ጎበዝ ጭንቅላት አለው ስለ ማያነብ እንጂ ቶሎ መረዳት ይችላል ። ቅድም ስንማር ክፍል አልነበረም አነበበው ና በሚገርም አገላለፅ አብራራልኝ ሁሉንም እንዲ እንዲያብራራልኝ አደረኩት ከዛ ስንጨርስ  እራት ቀረበ ቅድም ሊባላ የሚመስለው ፊቱ ትንሽ ደስ ያለው ይመስላል ዝኑ በርቱልኝ ልጆቼ ጥሩ ቦታ እንደምትደርሱ እተማመናለሁ አለችን በጠዋት ተነስቼ ጊቢው ውስጥ ስፖርት መስራት ጀመርኩ ሌላቀን ስደርስበት ሚሸሸው ልጅ አይኑን እያሻሸ ያለሁበት መጣ ..... .......... ይቀጥላል........ ✍written by Aksan Adane
Show all...
ዲና{DINA} {ተከታታይ ልበወለድ}written by Aksan ©PRESNT BY ARMONEM          --------------"""""""""""""""""------------------                  ክፍል7⃣ ይሄ ልጅ ታናሼ መሆኑ እያጠራጠረኝ ነው ልክ በሩ ጋር ስንደርስ ቆይ ዲኑተ ተብዙ ናቸው ስለዚ ድምፃቸው ጫጫታ ስላለው ልብ አይሉም እዮብን አይተሽ እንድትለውጪው ነው እንዳመጣሁሽ ካወቀ ይገለኛል አይተን ብቻ እንሄዳለን አለኝ እሺ የኔ ሚጢጢ ወንድም እዚ ነዋ አልኩት ወደ ውስጥ ሳይ ምድረ ወጣት በኔ እድሜ ትንሽ ትልቅ ተሰብስበው ይቅማሉ ያጨሳሉ ሺሻ ይነፋሉ የማየውን ማመን አልቻልኩም ማቲም እዮብም ቤዛም አሉ በቃ ነይ እንሂድ አለኝ ፊልም እየመሰለኝ ነው ከውጪ ለሚያያቸው ምንም ሱሰኛ አይመስሉም እንደ እብድ እየለፈለፍኩ እኔ እንኳን በስም የማውቀውን ይሄ ህፃን ልጅ በአይኑ እያየ አእምሮው ውስጥ እስከአሁን ምን ተፈጥሮ ይሁን የወደፊት ህይወቱ አሳሰበኝ ግን ደግሞ የእግዚአብሔር አይን ያረፈበት አስተዋይና የተባረከ ልጅ ነው ለካ ለኛ ባህሪ የቤተሰቦቻችን ፀሎት ና እንባም አስተዋዕፆ አለው ቦታው ከሰፈራችን ስለሚርቅ ቸርቹንም ቀርተን ወደ ቤት ተመለስን ቤቢን ለመዓዚ ሰጥቼው ወደ ቤት ገባሁ ቁጭ ብዬ ያየሁትን አሰላስላለሁ አሁን ዝኑ ብትሰማ አታብድም አንድ ልጇ ደሞ ሀብታም ሆኜ ምናምን እያለ ይጃጃላል ግራ ተጋብቼ እንቅልፍ ሳይዘኝ ነጋ በጠዋት ተነስተን ቸርች ለመሄድ ጉድ ጉድ ተጀመረ እማ መአዚን ጠብቃለሁ ብላኝ እኔ ደግሞ እነ ቤቢ ቤት ሄጄ አለባብሼው መፅሀፍ ቅዱሴን ይዤ ከባቢ ጋር ወጣን ቸርች ስሄድ ቀሚስ ነው ምለብሰው ልክ ስንወጣ እዮብን ና ማቲን አገኘናቸው እንዴዴዴዴ ይሄ ነገር አሁንም አለ እንዴ ነው ለሙድ ነው የያዝሽው አለኝ ማቲ ነበር ባክህ አክራሪ ናት አላልኩህም ስታሽቃብጥ ነው አለ እዮብ እንድናደድ ፈልገው ነው ስሙ ይሄ የቆማችሁበት ምድር ከምን ተሰራ አልኳቸው ከአፈር ነዋ ብለው ሳቁ እሺ ይሄ ሰማይስ አልኳቸው ሰማዩ ከምንድነው አንተ እንቺ በጠዋት አትጨቃጨቂ ሆሆሆሆሆ ቀስ እያልን መሄድ ጀመርን እሺ እናነተስ እንዴት መኖር ጀመራቹ አልኳቸው ተፈጥረን ነዋ በጣም ጥሩ ማን ፈጠራችሁ እሱን ተመራምረን ስንደርስ እንነግርሻለን አላሉም አያቹ ይሄ ተአምር በሚመስል ያለምሶሶ የተዘረጋው ሰማይ በዚ ቃል ነው የፀናው ምድርም እንዲሁ እናንተ ናችሁ ከአፈር የተሰራችሁት ወደ አፈርም ትመለሳላችሁ እርከዛው ግን በጉብዝናችሁ ወራት ፈጣሪያቹን አስቡ አልኳቸው እቺ ያማታል እንዴ ምንድነው አስሬ ስለ ሞት ምታወሪው አለኝ ማቲ ቆይ ቆይ አሁን እኔም ሞታለሁ ብሎ ፈዘዘ ባክህ በምድር እስካለን ፈታ በል አለው እዮብ አትሳሳት አሁን ፈታ ያልክ መሰለህ እንቺ አንተ ማለት የደረቀ ዛፍ ማለት ነህ ዝም ብሎ የቆመ ትንሽ ከቆየህ ከግራም ከቀኝም መጥረቢያ ይዘው ይፈላልጡሀል የለመለመን ዛፍ ግን ሁሉም ለጥላነት ይፈልገዋል ብዬ በፍጥነት ጥያቸው ቤቢን ይዤው በታክሲ ቸርች ሄድን የሚገርም የአምልኮ ጊዜ ነበር ፕሮግራም አልቆ ወደ ቤት ተመለስን መዓዚ ቡና አፍልታ እሷ ጋር እየተጫወትን ቤቢ መጥቶ በጆሮዬ ማቲ እየፈለገሽ ነው አለኝ ቀስ ብዬ ወጣሁ ከጊቢ ውጪ ሀይ ዲኑ አለኝ እሺ ለምን ፈልገኸኝ ነው አልኩት ወዲያው እዮብ መጣ አንቺ ልጁን እንደጠዋቱ እየነዘነዝሽው ነው ከአንቺ ከተለየን ማደንዘዣ እንደተወጋ ሰው ፈዟል ናና ጓደኛዬ እኔ ነኝ ማዋጣህ ብሎ እየጎተተ ይዞት ሄደ ተናደድኩ ገብቼ ቤዚን የማቲን ስልክ ላኪልኝ ብያት ላከችልኝ ወደ 12 ሰአት አከባቢ ማቲ ነገ ጠዋት አብረን ነው ትምህርት ቤት ምንሄደው ብዬ ቴክስት ፃፍኩለት...... .............ይቀጥላል.............. °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ✍written by Aksan Adane
Show all...
ዲና{Dina} {ተከታታይ ልበወለድ} ✍written by Aksan Adane             ©PRESENT BY ARMONEM            _°°°°°°°°°°°°°°°°____                   ክፍል6⃣ በዚ ቅፅበት እዮብ እና የሱ ቢጤ መጡ ኸ ቺኳ ማቲ እባላለው ቤቢን ትሰጪን አለኝ የትም አይሄድም አልኩት እዮብ ምን አገባሽ ወልደሽዋል አለኝ ታየኝ እኮ ከአንተ ጋር ውሎ የት እንደሚደርስ አልኩት ጓደኛው ማነሽ ዲና ደረቅ እንደሆንሽ እዮብ ነግሮኛል በቃ ፋራ አትሁኚ ልንልከው ነው አሉኝ ቤቢም አልፈልግም እነሱ መጥፎ ቦታ ነው ሚልኩኝ ዲኑ እንዳትፈቅጂ አለኝ ። አንተ እናትህን እሺ በኋላ ማትገኝ መስሎህ ነው ጩጬ ምናምን ብለው ሰድበውት ወጡ ቤቢ ቸርች አትወስደኝም አልኩት ኸረ ወስድሻለው ሚስንም አስተዋውቅሻለሁ አለኝ የሆነ ቅመም ነገር ይሄ ለአይን የሚያሳሳ ህፃን አእምሮው እንዲበላሽ አልፈልግም ። ዛሬ ሰኞ ነው እነ እዮብ ትምህርት ቤት ልገባ ከዝኑ ጋር ሄድን ዝኑ ጨራርሳልኝ ነገ መጀመር እንደምችል ተነገረኝ ። ማክሰኞ ትምህርት ጀመርኩ በጣም ነው ሚያስፈራው ሁሉም ተላምደዋል እኔ ግን ማንንም አላውቅም እንዲ እንዲያ እያልኩ 1ሳምንት ሞላኝ እረፍት ሰአትም ብቻዬን ነው ምቀመጠው ትምህርቴን እንደበፊቱ መከታተል ቀጠልኩ አንዲት ልጅ ልትቀርበኝ ጥረት እያደረገች ነው ቤዛ ትባላላች ምኗም አላማረኝም ከአለባበሷ ጀምሮ ። ችኩል ናት ሰሞኑን ግን ተቀራርበናል ቤቢ ቸርች ወስዶኝ የሰንደይ ስኩል አስተማሪውን ስለተዋወኩለት ደስ ብሎታል 1ኛ ክፍል ነው ። ቤዚ ቅዳሜ እሁድ ምናምን አልፎ አልፎ ትመጣለች እማ ግን አለባበሷን እና ሁኔታዋን አይታ አልወደደቻትም ሱቅ ውስጥ ቁጭ ብለን የእዮብ ጓደኛ መጣ እንዴ ቤዚ እዚ ምን ትሰሪያለሽ አላት ማቲዬ ሰፈርህ እዚ ነው እንዴ ተጠመጠመችበት ሁኔታቸውን ላየ ሲቀፍ አንድ ወንድና ሴት ያለምክኒያት ሰላምታ በሚል ሰበብ እንዲ ሲሆኑ ደስ አይልም ዛሬ እማ መጥታ ቤቴን መዳሪያ አረግሽው ብላ ሳትገለኝ አሳልኩ ና አነቃዋቸሁ እኔን እንኳን አያፍሩም ዲኑ ቻው ቻው ማቲን አጊንቺው እዚ መቀመጥ አልችልም አለችኝ እነዚማ ጤና የላቸውም እማን ሱቅ ጊቢ ብያት ወደ ቸርች ልሄድ ነው ቸርች ውስጥ ብዙ ጓደኞች አግኝቻለሁ ቅዳሜ የወጣቶች አምልኮ ልሄድ ነው ቤቢም ሰፈር ውስጥ እንዲውል ስለማልፈልግ ይዤው ነው ምሄደው  ዲኑ እነ እዮብ የሚውሉበትን ቤት ላሳይሽ አለኝ አዎን የት ነው አልኩት ይዞኝ ሄደ በጣም ራቀብኝ አንተ ግን እዚ ድረስ ከማን ጋር መጣህ አልኩት ከእዮብ ጋር አለኝ የሆነ ጉራንጉር ሰፈር ነው ውስጥ ለውስጥ ገብተን የሺሻ ምናም ሽታ ሸተተኝ ልቤ እየደነገጠ ነው ቆይ ቆይ ቤቢ እነ እዮብ እዚ ምን ይሰራሉ አልኩት ነይ ላሳይሽ አደል ይሄ ልጅ ታናሼ መሆኑ እያጠራጠረኝ ነው ......ይቀጥላል...... °°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°__ ✍written by Aksan Adane
Show all...
ዲና{DINA} {ተከታታይ ልበወለድ} ✍written by Aksan Adane           PRESENT BY ARMONEM           ---------------ክፍል 1⃣0⃣---------------- ሰላም ብዬው ወደ ውስጥ ገባን ለመስማት እንደጓጓ በጣም ያስታውቅበታል ዲኑ ለምን ፈልገሽኝ ነው አለኝ ማቲ ሰሞኑን ከእዮብ ጋር ያላችሁ ቅርርብ ቀንሷል ይሄ ደግሞ እኔን እየረበሸኝ ነው አልኩት ወዲያው ደስተኛ የነበረው ፊቱ ቅጭም አለ ምነው ስለው ለዚ ነው ይሄንንማ አንድ ላይ አድርገሽ ጠየቅሽን አደል ምንም አልሆንንም አለኝ እና ምን ጠብቀህ ነበር አልኩት ተናዶ ምንም በቃ ልሂድ  አለኝ ግራ አጋባኝ ይሄ ያናዳል እንዴ እማ ወዴት ነው ቁርስ ሰርቼ ሳትበላ ብላ መለሰችው አብረን እየበላን እዮባ እየሮጠ ዲኑ ዲኑ እየተጣራ ገባ ሁለታችንም መኖራችን ግራ አጋብቶታል ድምፁ ቀነሰ ወይ እዩ ምነው ናቁጭ በል አልኩት ተቀመጠ ሁለቱም እየተያዩ ተኮሳትረዋል እናንተ ቆይ ምንድነው ችግራችሁ አልኳቸው ሁለቱም ዝም አሉ እሺ ምን ልትነግረኝ ነበር እየተጣደፍክ የመጣኸው አልኩት አይ ማሚ ፈልጋሽ ልጠራሽ ነበር በቃ ልሂድ አለኝ እንዴ ቆይ እንሂድ እሺ አልኩት ና አንተም አለው ማቲን እሺ ምክኒያታችሁን አትንገሩኝ ግን እንደ በፊት ለመሆን ቃል ግቡልኛ ተቃቅፋችሁ ሰላም አውርዱ አልኳቸው ባይዋጥላቸውም እንዳልኳቸው አደረጉ የበላንበትን አነሳሁና እማ እያልኩ ጓዳ ስገባ የለችም ተጣርቼ ሲያቅተኝ እንሂድ በቃ አልኳቸው ጊቢ ከገባን በኋላ ሁለቱም ወደ ኋላ ቀሩ ምን እንደሚያወሩ አልገባኝም ኑ እንጂ ስላቸው መጡ ቤዚ ከየት መጣች ሳልል ዲኑ ብላ ከቤት ወጥታ ተጠመጠመችብኝ ምን ትሰሪያለሽ እዚ ስላት  በሌላ ወሬ ያዘችኝ የዚህኔ እዮባ ና ማቲ ወደ ውስጥ ገቡ ያልጠየኳትን ስታወራ ቆየችና እንግባ አለችኝ ወደ ውስጥ ስገባ ሰርፕራይዝ ብለው ጮኹ በጌታ ስም ምን እንዳስበረገገኝ ባላውቅም ደርቄ ቀረሁ የቸርች ልጆች የክላስ ልጆች እማ ዝኑ ና መዓዚም ነበሩ ቤቱን አሳምረውት ልዩ ሆኗል ለካ ዛሬ ልደቴ ነው ቅዳሜን በልደቴ ቀን ተደስተን አሳለፍን ሁሉም ወደ ቤት ሄደዋል እኔ እማ መአዚ ዝኑ እና እዮብ የተሰጠኝን ስጦታዎች እያየን ስንጨዋወት አመሸን እነ እማ የጦፈ ወሬ ላይ ናቸው እዮባና እኔም ዲኑ ግን እንደኔ ባህሪ ቢሆን አንቺን የመሰለች ልጅ አጥቼ ነበር በአንቺ ትህትና በግድ ባትቀርቢኝ ሰው ከመሬት ተነስቶ ሰው ይጠላል ለነገሩ ያኔ ሰይጣንም ሳይኖርብኝ አይቀርም አለኝ ቀላል ዋናው ነበር አንተ ላይ ያለው ብዬ ሳኩበት ኸኸኸኸ ጭራሽ ብሎ ጆሮዬን ቆነጠጠኝ እንዲሁ እየተዛዛግን እማ ኸረ ዲኑ ተነሽ 3:ሰዓት ሆነልሽ አለችኝ ከነሱ ጋር ስንሆን ሰአቱም አይታወቀንም ዝኑም እንኳን ለ19 አመት አበቃሽ ቀሪ ዘመንሽ የተባረከ ይሁን ብላ መረቀችኝ ወደ ቤት ልንሄድ ተነሳን ዝኑም እዮባም ሊሸኙን ወጡ እነ እማ ወጥተውም ወሬ አያቆሙም የጊቢው በር ጋር እየጠበቅናቸው ነው ። እኚ ደግሞ ውይይይ እያልኩ ድንገት ዲኑ አለኝ ወዬ አዝጉ አልከት ፀጥ አለኝ ምነው እዩ ደህና አደለህም አልኩት አይ ተይው በቃ ሌላ ቀን ነግርሻለው አለኝ እምቢ እምቢ ብዬ ደበደብኩት ኸረ ዲኑ ሌላ ቀን በናትሽ ሲል አልፈልግም እያልኩ ስከራከረው እማና ዝኑ መጡ እየተናደድኩ ወደ ቤት ገባሁ ምን ሊነግረኝ ይሁን እንዲ ሌላ ቀን ምናምን ብሎኝ ስለ ማያውቅ ለመስማት ጓግቼ ማሰላሰል ቀጠልኩ ይሄኔ የስልኬ ድምፅ ጮኸ text ሲገባ ተንገብግቤ ሳየው ማቲ ነበር........... ..............ይቀጥላል............. written by Aksan Adane ✍
Show all...
ዲና{DINA} {ተከታታይ ልበወለድ} ✍written by Aksan Adane             PRESENT BY ARMONEM ---------------****----------------------                   ክፍል5⃣ እንግድነቴ አላበቃም እማን ሱቅ ውስጥ ፍራሽ አንጥፌላት እኔ መሸጥ ጀመርኩ ምሳ ሰአት ሲደርስ የመአዚ ልጅ ቤቢ ትንሽዬ ነው ግን ጨዋና ታዛዥ ነው እኔን የስንት አመት ታላቁን ይመክረኛል እሱ ሱቁን ጠብቃለሁ ብሎ እኔ ውብዬ እና መዓዛ እነ ዝኑ ቤት ሄድን ቤቱ በምግብ አይነት እና በቡና ምናምን ደምቋል ገብተን ምሳ እየተበላ ነው ሆሆ ይሄ ቅንጡ ልጅ እንጀራ አይበላም አሉ መአዚ እስቲ ዲኑን እያት እንጀራ አይገድል እስቲ ቅመስ አለችው No no ማም የሰውነቴ ቅርፅ ይበላሻል አላለም ምን ሰውነት አለህ ቋንጣ እያልኩ በሆዴ የታትዬ ሽሮ ትዝ አለኝ ዝንዬ ሽሮ የለም ስላት እንዳረገዘች ሴት ወደላይ ወደላይ አለው መሠለኝ እየሮጠ ሄደ ልጄ ምን ሆነ እያለች ተከትላው ሄደች የእናት ነገር በዚ ቅብጠቱ በሳማ ነበር መግረፍ ሆሆሆሆ ሽሮ ሲባል ሚያስመልሰው ሰውም አለ ጌታዬ የማታሳየኝ ጉድ የለም አረጋግታ ይዛው መጣች መጥቶ ተቀመጠ እማ እና መዓዚ ምነው እዮቤ ብለው ሲያሽቃብጡለት ሽሮ ምናምን ያለችው ነገር አይመቸኝም ። ወይኔ ቆሽቴ አረረ ዝኑን ፈርቼ እንጂ እንዴት እንዳበሸቀኝ ምሳው ተበልቶ አለቀ እነ እማ እዛው እየተጨዋወቱ ነው እሱ ተነስቶ ቲቪ ማየት ጀመረ ይሄ ልጅማ በዚህ ከቀጠለ ታየኝ ተነስቼ አጠገቡ ተቀመጥኩ አየኝና ምን ፈለግሽ አለኝ ከአንተ ምን ይፈለጋል ቆይ ለምንድነው ምትኖረው አልኩት ኸኸኸኸ ስላልሞትኩ ነዋ አለኝ እሺ የምትኖርለት አላማስ አልኩት ሳድግ ማለትሽ ነው አለኝ ኸረ ከዚ በላይ ቀንድ ታበቅል አልኩ በሆዴ ይሄን ኩሳንኩስ ቤት ሸጬው ኢትዮጵያ ውስጥ አንደኛ ባለሀብት ሆኜ በቃ ከእማ ጋር የተንደላቀቀ ኑሮ እየኖርኩ የሀገሪቱን ቆንጆ የተባሉ ሴቶችን ሚስቶቼ ማድረግ እስቲ በእውነት በለኝ ብዬ ሳኩ ማሪያምን ብዬሽ ደስ ይላል አደል ብሎ ሲስቅ ማሪያም ትውሰድህ በቃ ይሄ ነው አላማህ ብዬ አፈጠጥኩበት እናስ አለኝ በቃ ይሄ ልጅ እውነትም አላደገም ቁመት ብቻ አልኩኝ ደግሞ ይሄን ቤት ነው ኩታንኩት ያልከው አልኩት አዎና የአባቢ ወንድሞች በዚህ ቤት ምክኒያት ሠላም ነስተዋታል ስለዚህ ይሄን ኩታንኩታቸውን ጥለን በምን አይነት ቤት ውስጥ እንደምንኖር አሳያቸዋለው አለኝ ለእነሱ እልህ ማለት ነው አልኩ አዎን አንቺ ግን ምነው ተጨቃጨቅሽ ልከውሽ ነው እንዴ አለኝ እሺ በዚህ ምድር ላይ ምን ትፈልጋለህ አልኩት ደስታ ገንዘቤን እየበተንኩ እንደ ፈለኩ መኖር አለኝ እሺ ስትሞትስ አልኩት  ኸ ለምንድነው ምሞተው አለኝ ሰው ስለሆንክ ነዋ ሰው ደግሞ ሟች ነው አልኩት ሴትዮ ንግግርሽ በቁሜ ሳይገለኝ ልሂድበት ሞት ምናምን ትላለች እንዴ ሟርተኛ እያለ ስልኩን ይዞ ሊወጣ ተነሳ ወዴት ነው አለችው ዝኑ መጣው ማቲ ጋር ነኝ አላት ልጅቷን ብቻዋን ትተህ እህህህ እማ ደግሞ ልታስሪኝ አማረሽ ለነገሩ ነገ ሰኞ አደል ትገላገይኛለሽ ብሏት ወጣ ዝንዬ ጣጣ የለውም እንደውም ቤቢ ሱቅ ብቻውን ነው ልሂድለት ብዬ ወጣሁ ቤቢ ትንሹ ወንድሜ ደበረሽ እንዴ አልኩት አልደበረኝም ስለመጣሽ ግን ደስ ብሎኛል የኔ ሚጢጢዬ በቃ ሂጂ ተጫወቺያ ስለው ኸረ መጫወት አልፈልግም አለኝ ለምን ጓደኞች የሉህም አልኩት አሉኝ ግን መጥፎ ናቸው አለኝ ምን አረጉህ ቤቢዬ መቱህ አልኩት አይ እነሱ ዘፈን ይወዳሉ የወንድማቸውን ስልክ አምጥተው መጥፎ ነገር ያያሉ አለኝ ቆሌዬ ነው የተገፈፈው ይሄ ህፃን ልጅ እንዴት እንዲ ያወራል ሰንደይ ስኩል ደግሞ ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ ብላ ሚስ ከመፅሀፍ ቅዱስ አስተምራኛለች አለኝ ምን እንደምለው ግራ ገባኝ ወዴት እየሄድን ነው ግን በዚ ቅፅበት እዮብና የሆነ የሱ ቢጢ መጡ ....... ...........ይቀጥላል........ _∞∞∞∞∞∞____ _∞∞∞∞∞∞_written by Aksan
Show all...
👍 1