cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

🎵ዘፀአት ለ ሁላችን✝️🎤🎤🎹🔥🔥

በእግዚአብሔር የታመነ አምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው እሱ ብሩክ ነው :: (ትንቢተ ኤርምያስ 17:7) አዳዲስ መዝሙሮቺን ቆየት ያሉ መዝሙሮቺን ዎርሺፕ ዝማረዎቺን እዚህ ያገኛሉ 🙏🙏 @NadegimeBehiyiwete520

Show more
Advertising posts
229
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

መስቀሉ ይናገር የሆንከው መልካም ውሎ 🙏🏽🙏🏽 @Zetseat_Zema ♥️❤❤❤🙏🏽😭😭
Show all...
መስቀሉ_ይናገር(251).mp39.41 MB
🔥 1
ዮሐንስ 19 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁵ እነርሱ ግን፦ አስወግደው፥ አስወግደው፥ ስቀለው እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም፦ ንጉሣችሁን ልስቀለውን? አላቸው። የካህናት አለቆችም፦ ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም ብለው መለሱለት። ¹⁶ ስለዚህ በዚያን ጊዜ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጣቸው። ¹⁷ ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ። ¹⁸ በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት፥ አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ። ¹⁹ ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም፦ የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ የሚል ነበረ። ²⁰ ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበረና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽሕፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር። ²¹ ስለዚህ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን፦ እርሱ፦ የአይሁድ ንጉስ ነኝ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ አሉት። ²² ጲላጦስም፦ የጻፍሁትን ጽፌአለሁ ብሎ መለሰ።
Show all...
ብዙ ፍጥረት ያለው ባህር ውቅያኖሱ ለየብስ ሩብ ሰጥቶ ቀሪውን መልበሱ ላጥፋ ካለ አጥፊ ጡንቻ አለው ፈርጣማ ካንዱ ጌታ በቀር ማንንም አይሰማ ጥም አርኪ ይመስላል ግን ለጠማው ደሃ ውስጡ ስለሌለው ለመጠጥ የሚሆን አንድ ብርጭቆ ውሃ ሰነፍ መርከበኛ ውቅያኖሱ ዳር ሚጠጣውን ሰይዝ መጓዝ ቢጀምር ውሃ መሃል ደርሶ ውሃ ይጠማዋል ውሃ በረሃ ላይ በውሃ ጥም ይሞታል አንድ ጉድጓድ አለች በጣም ትንሽዬ ህፃን ነህ አዋቂ ጨዋ ነህ ዱርዬ ሳትል ሳታዳላ ሁሉን ታጠጣለች ይህን ንፁህ ውሃ ታመነጨዋለች ጠቢቡ ገበሬ እሷ ዳር ይዘራል ዘሩም ምንጯን ነክቶ ማን ደርቆ ይቀራል ጌታ ኢየሱስን በዕምነቱ የነካ ከህይወት ውሃ ምንጭ ጠጥቶ እረካ ስንት ምስኪን አለ ሳይተኛ ሚያነጋ ነፍሱ ምትገረፍ በጥማት አለንጋ እግዚአብሔር ነፍሱን ነይ ላርካሽ ቢላት የእግዚአብሔርን ሳይሆን ለነፍሱ ሆዱን ሰማላት ጌታ በሌለበት በዚያ ባዶ ቦታ ምኑንም ቢከቱ አይሰጥም እርካታ ሰማይ እና ምድር ባንዴ ተጠቅልሎ የኢየሱስን ቦታ አይሞላውም ችሎ የተከበበ በማይጠጣ በዓለም ያለ ሰው ኢየሱስን ያጣ በጀልባ እንደጠፋ ውቅያኖስ ላይ ኢየሱስ የሌለው ሰው እሱ አይደል ወይ ተበልቶ ተጠጥቶ የለም እርካታ ኑሮ ማለት ሃሩር ከሌለው ጌታ ዳግመኛ አልጠማኝም አንዴ ጠጥቼው ጎዶሎ የለኝም ውስጤ ሙሉ ነው የውሀው በረሐ በረከት ተስፋዬ sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈ https://t.me/christian_4_life https://t.me/christian_4_life
Show all...
12_Bereket_Tesfaye_የውሃ_በረሐ_Yeweha_Bereha_በረከት_ተስፋዬ_የውሃ_በረሐ_9BOLt8hjbJ4.m4a5.01 MB
.                áŠ áˆáˆžá‰ľáŠŠáˆ›            á‹˜áˆ›áˆŞ ኤፍሬም አለሙ        sʜᴀʀᴇ◆sʜᴀʀᴇ◆sʜᴀʀᴇ 🎙Agape Worship Ministry🎙          ♻️ @Agape_zema♻️          ♻️ @Agape_zema♻️         @Agape_zema_group                    ▲Join Us▲
Show all...
ll_አልሞትኩማ_ll_ኤፍሬም_አለሙ(128k).mp35.99 MB
ሉቃስ 7 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁷ እነሆም በዚያች ከተማ ኃጢአተኛ የነበረች አንዲት ሴት፤ በፈሪሳዊው ቤት በማዕድ እንደ ተቀመጠ ባወቀች ጊዜ፥ ሽቱ የሞላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ አመጣች። ³⁸ በስተ ኋላውም በእግሩ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመረች፥ በራስ ጠጕርዋም ታብሰው እግሩንም ትስመው ሽቱም ትቀባው ነበረች። ³⁹ የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፦ ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፥ ኃጢአተኛ ናትና ብሎ በልቡ አሰበ። ⁴⁰ ኢየሱስም መልሶ፦ ስምዖን ሆይ፥ የምነግርህ ነገር አለኝ አለው። እርሱም፦ መምህር ሆይ፥ ተናገር አለ። ⁴¹ ለአንድ አበዳሪ ሁለት ተበዳሪዎች ነበሩት በአንዱ አምስት መቶ ዲናር ነበረበት በሁለተኛውም አምሳ። ⁴² የሚከፍሉትም ቢያጡ ለሁለቱም ተወላቸው። እንግዲህ ከእነርሱ አብልጦ የሚወደው ማንኛው ነው? ⁴³ ስምዖንም መልሶ፦ ብዙ የተወለቱ ይመስለኛል አለ። እርሱም፦ በእውነት ፈረድህ አለው። ⁴⁴ ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፥ ውኃ ስንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርስዋ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች በጠጕርዋም አበሰች። ⁴⁵ አንተ አልሳምኸኝም፤ እርስዋ ግን ከገባሁ ጀምራ እግሬን ከመሳም አላቋረጠችም። ⁴⁶ አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች። ⁴⁷ ስለዚህ እልሃለሁ፥ እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል፤ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል። ⁴⁸ እርስዋንም፦ ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል አላት። ⁴⁹ ከእርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጠው የነበሩት በልባቸው፦ ኃጢአትን እንኳ የሚያስተሰርይ ይህ ማን ነው? ይሉ ጀመር። ⁵⁰ ሴቲቱንም፦ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ አላት።
Show all...
👍 3
አሞጽ 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በእናንተ ላይ ለሙሾ የማነሣውን ይህን ቃል ስሙ። ² የእስራኤል ድንግል ወደቀች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሣም፤ በምድርዋ ላይ ተጣለች፥ የሚያስነሣትም የለም። ³ ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላልና፦ ሺህ ከሚወጣባት ከተማ መቶ ይቀርላታል፥ መቶም ከሚወጣባት ከተማ ለእስራኤል ቤት አሥር ይቀርላታል። ⁴ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላልና፦ እኔን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ ⁵ ነገር ግን ጌልገላ ፈጽሞ ትማረካለችና፥ ቤቴልም ከንቱ ትሆናለችና ቤቴልን አትፈልጉ፥ ወደ ጌልገላም አትግቡ፥ ወደ ቤርሳቤህም አትለፉ። ⁶ በዮሴፍ ቤት እሳት እንዳትቃጠል፥ በቤቴል የሚያጠፋትም ሳይኖር እንዳትበላ፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ። ⁷ ፍርድን ወደ እሬት የምትለውጡ፥ ጽድቅንም በምድር ላይ የምትጥሉ እናንተ ሆይ፥ ⁸ ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮከብ የፈጠረውን፥ የሞትን ጥላ ወደ ንጋት የሚለውጠውን፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልመውን፥ የባሕሩንም ውኆች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸውን፥ ⁹ አምባውም እንዲፈርስ በብርቱ ላይ የድንገት ጥፋት የሚያመጣውን ፈልጉ፤ ስሙ እግዚአብሔር ነው። ¹⁰ በበሩ አደባባይ የሚገሥጸውን ጠሉ፥ እውነትም የሚናገረውን ተጸየፉ። ¹¹ ድሀውንም ደብድባችኋልና፥ የስንዴውንም ቀረጥ ከእርሱ ወስዳችኋልና ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ሠርታችኋል፥ ነገር ግን አትቀመጡባቸውም፤ ያማሩ የወይን ቦታዎች ተክላችኋል፥ ነገር ግን ከወይን ጠጃቸው አትጠጡም። ¹² ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችጋረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ፥ በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና። ¹³ ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና በዚያ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላል። ¹⁴ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፤ እንዲህም እናንተ እንደ ተናገራችሁ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል። ¹⁵ ክፉውን ጥሉ፥ መልካሙንም ውደዱ፥ በበሩም አደባባይ ፍርድን አጽኑ፤ ምናልባት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ለዮሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆናል። ¹⁶ ስለዚህ ጌታ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በየአደባባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆናል፤ በየመንገዱም ሁሉ ላይ ወዮ ወዮ ይባላል፤ ገበሬዎቹም ወደ ልቅሶ፥ አልቃሾቹም ወደ ዋይታ ይጠራሉ። ¹⁷ በመካከልህ አልፋለሁና በወይኑ ቦታ ሁሉ ልቅሶ ይሆናል፥ ይላል እግዚአብሔር። ¹⁸ የእግዚአብሔርን ቀን ለምትፈልጉ ወዮላችሁ! የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትፈልጋላችሁ? ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም። ¹⁹ ከአንበሳ ፊት እንደ ሸሸ ድብም እንዳገኘው ሰው፥ ወይም ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ነው። ²⁰ የእግዚአብሔር ቀን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ አይደለምን? ፀዳል የሌለውም ድቅድቅ ጨለማ አይደለምን? ²¹ ዓመት በዓላችሁን ጠልቼዋለሁ ተጸይፌውማለሁ፤ የተቀደሰውም ጉባኤአችሁ ደስ አያሰኘኝም። ²² የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁና የእህሉን ቍርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ ለምስጋና መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡትን እንስሶች አልመለከትም። ²³ የዝማሬህንም ጩኸት ከእኔ ዘንድ አርቅ፤ የመሰንቆህንም ዜማ አላደምጥም። ²⁴ ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም እንደማይደርቅ ፈሳሽ ይፍሰስ። ²⁵ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በውኑ በምድረ በዳ አርባ ዓመት ሙሉ መሥዋዕትንና ቍርባንን አቅርባችሁልኛልን? ²⁶ ለራሳችሁም የሠራችኋቸውን ምስሎች፥ የሞሎክን ድንኳንና የአምላካችሁን የሬፋን ኮከብ አነሣችሁ። ²⁷ ስለዚህ ከደማስቆ ወደዚያ አስማርካችኋለሁ፥ ይላል ስሙ የሠራዊት አምላክ የተባለ እግዚአብሔር። https://t.me/Siprtual_songs https://t.me/siprtual_song
Show all...
🎤🎻 መንፈሳዊ መዝሙሮች🎸🎻🎷🎺🎧🎼🎤

👉 በዚህ ግሩፕ ውስጥ 🎧አዳዲስ መዝሙሮች 🎤አዳዲስ ስብከቶች 📆የ ኮንፍራን ፕሮግራሞች 📖የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች 📝መንፈሳዊ ግጥሞችን share የምንደራረግበት group ነው።በ ጥቅሉ ስለ ወንጌል📖 እናወራለን። 🔴50 ሰው add ያደረገ admin ይሰጠዋል። Channel👇 @siprtual_song_bot Bot👇 @siprtual_song_bot

ባይህ (3*) እኔ አልጠገብኩም አልረካሁም አልሰለችም 🙏🏽♥️🙏🏽🔥 @Zetseat_zema🙏🏽♥️
Show all...
LEWI_CHOIR_ናፍቆቴ_ሆነሀል_New_Ethiopian_Protestant_Song_2022360p.mp34.95 MB
🔥 1
ዕብራውያን 12 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹-² እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። ³ በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፥ ከኃጢአተኞች በደረሰበት እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን አስቡ። ⁴ ከኃጢአት ጋር እየተጋደላችሁ ገና ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም፤ ⁵-⁶ እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር፦ ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል። ⁷ ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? ⁸ ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም። ⁹ ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን? ¹⁰ እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና፥ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል። ¹¹ ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል። ¹² ስለዚህ የላሉትን እጆች የሰለሉትንም ጉልበቶች አቅኑ፤ ¹³ ያነከሰውም እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ፥ ለእግራችሁ ቅን መንገድ አድርጉ። ¹⁴ ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና። ¹⁵ የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥ ¹⁶ ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ። ¹⁷ ከዚያ በኋላ እንኳ በረከቱን ሊወርስ በወደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታውቃላችሁና፤ በእንባ ተግቶ ምንም ቢፈልገው ለንስሐ ስፍራ አላገኘምና። ¹⁸ ሊዳሰስ ወደሚችል ወደሚቃጠልም እሳት ወደ ጭጋግም ወደ ጨለማም ወደ ዐውሎ ነፋስም ወደ መለከት ድምፅም ወደ ቃሎችም ነገር አልደረሳችሁምና፤ ¹⁹ ያንም ነገር የሰሙት ሌላ ቃል እንዳይጨመርባቸው ለመኑ፤ ²⁰ እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ ተወግሮ ይሙት የምትለውን ትእዛዝ ሊታገሡ አልቻሉምና፤ ²¹ ሙሴም፦ እጅግ እፈራለሁ እንቀጠቀጥማለሁ እስኪል ድረስ የሚታየው እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤ ²² ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥ ²³ በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥ ²⁴ የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል። ²⁵ ለሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ በምድር ላስረዳቸው እምቢ ባሉ ጊዜ ካላመለጡ፥ ከሰማይ ከመጣው ፈቀቅ የምንል እኛስ እንዴት እናመልጣለን? ²⁶ በዚያም ጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጠ፥ አሁን ግን፦ አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል። ²⁷ ዳሩ ግን፦ አንድ ጊዜ ደግሜ የሚል ቃል፥ የማይናወጡት ጸንተው እንዲኖሩ፥ የሚናወጡት የተፈጠሩ እንደሚሆኑ ይለወጡ ዘንድ ያሳያል። ²⁸ ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤ ²⁹ አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና። https://t.me/siprtual_song https://t.me/siprtual_song
Show all...
🎤🎻 መንፈሳዊ መዝሙሮች🎸🎻🎷🎺🎧🎼🎤

👉 በዚህ ግሩፕ ውስጥ 🎧አዳዲስ መዝሙሮች 🎤አዳዲስ ስብከቶች 📆የ ኮንፍራን ፕሮግራሞች 📖የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች 📝መንፈሳዊ ግጥሞችን share የምንደራረግበት group ነው።በ ጥቅሉ ስለ ወንጌል📖 እናወራለን። 🔴50 ሰው add ያደረገ admin ይሰጠዋል። Channel👇 @siprtual_song_bot Bot👇 @siprtual_song_bot

🔥 2👍 1
ኢሳይያስ 41 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁰ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ። ¹¹ እነሆ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፥ ይዋረዱማል፤ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፥ ይጠፉማል። ¹² የሚያጣሉህንም ትሻቸዋለህ አታገኛቸውምም፥ የሚዋጉህም እንዳልነበሩና እንደ ምናምን ይሆናሉ። ¹³ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፦ አትፍራ፥ እረዳሃለሁ ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና። ¹⁴ አንተ ትል ያዕቆብ የእስራኤልም ሰዎች ሆይ፥ አትፍሩ፤ እረዳሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው። ¹⁵ እነሆ፥ እንደ ተሳለች እንደ አዲስ ባለ ጥርስ ማሄጃ አድርጌሃለሁ፤ ተራሮችንም ታሄዳለህ ታደቅቃቸውማለህ፥ ኮረብቶችንም እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ። ¹⁶ ታበጥራቸዋለህ፥ ነፋስም ይጠርጋቸዋል፥ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል፤ አንተም በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፥ በእስራኤልም ቅዱስ ትመካለህ። ¹⁷ ድሆችና ምስኪኖችም ውኃ ይሻሉ አያገኙምም፥ ምላሳቸውም በጥማት ደርቋል፤ እኔ እግዚአብሔር እሰማቸዋለሁ፥ የእስራኤል አምላክ እኔ አልተዋቸውም። ¹⁸ በወናዎቹ ኮረብቶች ላይ ወንዞችን፥ በሸለቆችም መካከል ምንጮችን እከፍታለሁ፤ ምድረ በዳውን ለውኃ መቆሚያ፥ የጥማትንም ምድር ለውኃ መፍለቂያ አደርጋለሁ። ¹⁹-²⁰ የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንደ ሠራች፥ የእስራኤልም ቅዱስ እንደ ፈጠረው ያዩ ዘንድ ያውቁም ዘንድ ያስቡም ዘንድ በአንድነትም ያስተውሉ ዘንድ፥ በምድረ በዳ ዝግባውንና ግራሩን ባርሰነቱንና የዘይቱን ዛፍ አበቅላለሁ፥ በበረሀውም ጥዱንና አስታውን ወይራውንም በአንድነት አኖራለሁ። ²¹ ክርክራችሁን አቅርቡ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ማስረጃችሁን አምጡ፥ ይላል የያዕቆብ ንጉሥ። ²² ያምጡ፥ የሚሆነውንም ይንገሩን፤ ልብም እናደርግ ዘንድ ፍጻሜአቸውንም እናውቅ ዘንድ፥ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ተናገሩ፥ የሚመጡትንም አሳዩን። ²³ አማልክትም መሆናችሁን እናውቅ ዘንድ በኋላ የሚመጡትን ተናገሩ፤ እንደነግጥም ዘንድ በአንድነትም እናይ ዘንድ መልካሙን ወይም ክፉውን አድርጉ። ²⁴ እነሆ፥ እንዳልነበረ ናችሁ፥ ሥራችሁም ከንቱ ነው፤ የሚመርጣችሁም አስጻያፊ ነው። ²⁵ አንዱን ከሰሜን አነሣሁ መጥቶአልም፤ አንዱም ከፀሐይ መውጫ ስሜን የሚጠራ ይመጣል፤ በጭቃ ላይ እንደሚመጣ ሰው አፈርም እንደሚረግጥ ሸክለኛ በአለቆች ላይ ይመጣል። ²⁶ እናውቅ ዘንድ ከጥንት የተናገረው፦ እውነት ነው እንልም ዘንድ ቀድሞ የተናገረው ማን ነው? የሚናገር የለም፥ የሚገልጥም የለም፥ ቃላችሁንም የሚሰማ የለም። ²⁷ በመጀመሪያ ለጽዮን፦ እነኋቸው እላለሁ፤ ለኢየሩሳሌምም የምስራች ነጋሪን እሰጣለሁ። ²⁸ ብመለከት ማንም አልነበረም፤ ብጠይቃቸውም የሚመልስልኝ አማካሪ በመካከላቸው የለም። ²⁹ እነሆ፥ እነርሱ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፥ ሥራቸውም ምንምን ናት፤ ቀልጠው የተሠሩት ምስሎቻቸውም ነፋስና ኢምንት ናቸው። https://t.me/siprtual_song https://t.me/siprtual_song
Show all...
🎤🎻 መንፈሳዊ መዝሙሮች🎸🎻🎷🎺🎧🎼🎤

👉 በዚህ ግሩፕ ውስጥ 🎧አዳዲስ መዝሙሮች 🎤አዳዲስ ስብከቶች 📆የ ኮንፍራን ፕሮግራሞች 📖የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች 📝መንፈሳዊ ግጥሞችን share የምንደራረግበት group ነው።በ ጥቅሉ ስለ ወንጌል📖 እናወራለን። 🔴50 ሰው add ያደረገ admin ይሰጠዋል። Channel👇 @siprtual_song_bot Bot👇 @siprtual_song_bot

.            ላውድልህ ሀገሩን   ይድነቃቸው ተካ - || - New album        sʜᴀʀᴇ◆sʜᴀʀᴇ◆sʜᴀʀᴇ 🎙Agape Worship Ministry🎙          ♻️ @Agape_zema♻️          ♻️ @Agape_zema♻️         @Agape_zema_group                    ▲Join Us▲
Show all...
ll_ላውድልህ_ሀገሩን_ll_ይድነቃቸው_ተካ128k.mp36.01 MB
🔥 1